መጣጥፎች

37


ኢስላም አምስት መሰረቶች አሉት እነሱም፡-


1- ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር፤


2- ሶላትን መስገድ፤


3- ዘካን መስጠት፤


4- የረመዷንን ወር መፆምና


.5- የቻለ ሰው የአላህን ቤት በእድሜው አንድ ግዜ ሐጅ ( ጉብኝት) ማድረግ ናቸው።


የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ኢስላም በአምስት ነገሮች ላይ ተመሰረተ፡-


ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፤ ሶላትን መስገድ፤ ዘካን መስጠት፤ ሐጅ ማድረግና የረመዷንን ወር መፆም ” ብለዋል።


እነኚህ የእስልምና መሰረቶች በሁለት ይከፈላሉ፡-


አንደኛው ክፍል ሁለት ዋናዋና ነጥቦችን ያካትታል እነሱም፦


1 - ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፤


2- አምስት ወቅት ሶላቶችን መስገድ ናቸው። እነዚህ ሁለት ነገሮች የእስልምና ኃይማኖት ዋና መሰረታዊ ነጥቦች ስለሆኑ ያለነሱ አንድ ሰው ሙስሊም ሊባል አይችልም ።


ሁለተኛው ክፍል ሦስት ነገሮችን ያካትታል እነሱም፡-


38


1- ዘካን መስጠት፤


2- የረመዷንን ወር መፆም፣


3- የቻለ ሰው የአላህን ቤት ጉብኝት ማድረግ ናቸው።


እነዚህ ሦስት ነገሮች ደግሞ እስልምናን የሚያሟሉ ነጥቦች ናቸው።


የኢማን ትርጉም፡-


ኢማን በቋንቋ ደረጃ እውነት ማለትና መናገር ሲሆን ኃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ፡-


1- በልብ ማመን፤


2- በምላስ መናገርና


3- በአካል መተግበር ነው።


ኢማን አላህን በመገዛት ይጨምራል እርሱን በማመጽ ይቀንሳል።


የእምነት ማዕዘናት


እምነት ስድስት ክፍሎች ወይም ማዕዘናት አሉት እነሱም፡-


1_ በአላህ ማመን፤


2- በመላእክት ማመን፤


3- በመፅሕፍት ማመን፤


4- በመልእክተኞች ማመን፤


5- በመጨረሻው ቀን ማመንና


39


6- ማንኛውም ነገር ጥሩም ሆነ ክፉ በአላህ ውሳኔ እንደሚፈፀም ማመን ናችው።


በአላህ ማመን የሚለው አራት ዋና ዋና ነጥቦችን ያካትታል እነሱም፡-


1- አላህ መኖሩን ማመን፣


2- አላህ የዓለማት ፈጣሪና አስገኝ መሆኑን ማመን፣


3- ከእርሱ ውጭ በሀቅ የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን ማወቅና ማመን፣


4- በስሞቹና በባህርያቱ ማመን ናቸው።


በመላዕክት ማመን የሚለው አራት ነጥቦችን ያካትታል እነሱም ፦


1- አላህ ከብርሃን የፈጠራቸውና እሱን የማይወነጅሉ ቀናኢ አገልጋዮች መሆናቸውን ማወቅና ማመን ፤


2- ከእነሱ ውስጥ በስም የተጠቀሱትን ከነስሞቻቸው ማወቅና ማመን፣


3- ከሰዎች የተለዩ ባህርያት እንዳሏቸው ማወቅና ማመን፤


4- በስራ ድርሻቸው የታወቁትን ከነስራ ድርሻቸው ማወቅና ማመን ናቸው።


በመጻሕፍት ማመን በሚለው ስር አራት ነጥቦች ይካተታሉ እነሱም፡-


1- የአላህ ቃልና ከእርሱ የወረዱ መሆናቸውን ማመን፤


2- በስማቸው የታወቁትን ለምሣሌ ፦ እንደ ቁርዓን ፤ ተውራት(ኦሪት) ፤ ኢንጂል(ወንጌል) እና ዘቡር(መዝሙር) ያሉትን ከነስሞቻቸው ማወቅና ማመን፤


3- ቁርዓን የተናገረው እውነት መሆኑን ማመን እና ቀደምት ሰማያዊ መፃሕፍት የተናገሩትም የተዛባና የተበረዘ ካልሆነ በስተቀር እውነት ብሎ ማመንና መቀበል


40


4 -ቀደምት ሰማያዊ መጻሕፍት በሙሉ በቁርኣን መሻራቸውን አምኖ መቀበል ናቸው።


በአላህ መልእክተኞች ማመን በሚለው ስር አምስት ነጥቦችን እናገኛለን፡-


1- አላህ ከሰዎች መካከል መርጦና አብልጦ ሰዎችን ያስተምሩ ዘንድ የላካቸው መሆኑን በእርግጠኝነት ማመን፤


2- ከእነሱ በአንዱ መልእክተኛ መካድ በሁሉም እንደመካድ መሆኑን አውቆ በሁሉም መልእክተኞች ማመን፤


3-ከእነሱ በስሞቻቸው የተጠቀሱትን ለምሳሌ ፦ ሙሀመድ ፤ ኢብራሂም ፤ሙሳ፤ዒሳ፤ኑህ እና በመሳሰሉት ከነስሞቻቸው አውቆ ማመን፤


4- እነሱ የተናገሩትን እውነት ነው ብሎ ማመንና መቀበል፤


5- በጠቅላላ ለሰዎችና ለአጋንንት በተላኩትና የነቢያት መጨረሻና መደምደሚያ በሆኑት መልእክተኛ- በነቢዩ ሙሀመድ // ህግና ስርዓት መሰረት አላህን መገዛት ናቸው።


በመጨረሻው ዕለት ማመን አራት ነገሮችን ያካትታል፡-


1- ከሞት በኋላ መነሳት የማይቀር መሆኑን ማመን፣


2- በዚች ዓለም በሰሩት ስራ በትንሣኤ ቀን መጠየቅና የስራ ውጤት እንደሚሰጥ ማመን፣


3- ጀነት እና እሳት የሚባሉ ሁለት ቋሚ አገሮች መኖራቸውን ማመን ፣


4- ከሞት በኋላ በሚያጋጥሙ ነገሮች ለምሳሌ፦ በቀብር ውስጥ መጠየቅ ፤ መቀጣት፤ መጠቀምና መደሰት መኖሩን ማመን ናቸው።


በቀደር ማመን፡--


41


በአላህ ውሳኔ ማመን በአራት ነገሮች ማመንን ያጠቃልላል። እነሱም፡-


1- አላህ በጥቅልም ሆነ በዝርዝር ሁሉን ነገር የሚያውቅ መሆኑን ማወቅና ማመን፣


2- አላህ ሁሉን ነገር በተከበረው ሰሌዳ ላይ ቀደም ሲል እንደፃፈውና እንዳ ሰፈረው ማመን፤


3- ማንኛውም ግኝት በአላህ ውሳኔ እና ፍቃድ እንጂ ሊገኝ እንደማይችል ማመን፣


4- ማንኛውም ግኝት በአካሉ፤ በባህሪውና በእንቅስቃሴው የአላህ ፍጡር መሆኑን ማመን ናቸው።


የእነዚህ ስድስት እምነቶች ማስረጃ፡-


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምእራብ አቅጣጫ ማዞራችሁ መልካም ስራ አይደለም ነገር ግን ትክክለኛ መልካም ስራ የሚባለው በአላህ፤ በመጨረሻው እለት፤ በመላእክት፤ በመፃሕፍትና በነቢያት ያመነ ብቻ ነ” (አል-በቀራህ: 177) ።


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እኛ ማንኛውንም ነገር በውሳኔ/በልክ/ ፈጠር ነው” (አል-ቀመር: 49)


-የአላህ መልክተኛ // ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ጅብሪል የተባለው መልእክ ስለ እምነት አስረዳኝ ሲላቸው፡-


42





“በአላህ፤ በመላእክት፤ በመጻሕፍት፤ በነቢያትና ደግም ሆነ ክፉ በአላህ ውሳኔ እንደሚፈፀም ማመን ነው” አሉት።


በጎ ስራ፡--


በጎ ስራ ማለት በቋንቋ ደረጃ የማስቀየም ተቃራኒ ሲሆን ኃይማኖታዊ ትርጉሙ


ደግሞ በገሀድም ሆነ በሚስጥር አላህን መፍራት ለሚለው ያገለግላል።


እርሱም አንድ ማዕዘን አለው እሱም አላህን ልክ እንደሚያይ ሆኖ መገዛት ይህም ካልተቻለ አላህ እንደሚያየውና እንደሚቆጣጠረው አውቆ መገዛት ማለት ነው።


በጎ ስራ ሁለት ክፍሎች አሉት እነሱም፡-


1- አላህን በሚገባ መገዛት ሲሆን ይህም ሁለት ደረጃዎች አሉት። እነሱም፡-


አንደኛ- አላህን ልክ እንደሚያየው ሆኖ መገዛት ይህም ከሁለቱ ደረጃዎች ከፍተኛው ሲሆን ፣


ሁለተኛ- አላህ እንደሚያየውና እንደሚቆጣጠረው አምኖ መገዛት ናቸው።


የአላህ መልእክተኛ // ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ጅብሪል የተባለው መልኣክ ስለ በጎ ስራ ንገረኝ ሲላቸው፦





“አላህን እንደምታየው ሆነህ መገዛት አንተ የምታየው ባትሆን እሱ ያይሃልና” አሉት።


2- ለፍጡር በጎ መዋል ይህም በአራት ነገሮች ይገለፃል። እነሱም፡-


43


በገንዘቡ፤ በእውቀቱ ፤በአካሉና በክብሩ ለሰዎች በጎ መዋል ናቸው።


አላህ እንዲህ ይላል፦





“አላህ በእርዳታውና በእንክብካቤው ከነዚያ እሱን ከሚፈሩትና ከበጎ አድራጊዎች ጋር ነው ” (አነሕል: 128)።


* - ኢስላም፤ኢማን እና ኢህሳን ያላቸው ግንኙነት፡-


እነዚህ ሶስት ቃላት በጣምራ ሲጠቀሱ የተለያየ ትርጉም አላቸው ለምሳሌ፡-


1- ኢስላም የሚለው በገሃድ ለሚሰሩ ነገሮች ሲያገለግል፤


2- ኢማን የሚለው ደግሞ ህዋሳት ሊደርስባቸው በማይችሉ ሩቅና ሚስጥር ነገሮች ማመን የሚለውን ያስረዳል፣


3- ኢህሳን የሚለው ደግሞ ከኃይማኖት ደረጃዎች ከፍተኛውን ክፍል ይሸፍናል ።


እነዚህ ሦስት ቃላት በተናጠል ሲነገሩ ደግሞ አንዱ በሌላው ስር ይጠቃለላል ለምሳሌ፦


- ኢስላም የሚለው ብቻውን ከተጠቀሰ በውስጡ ኢማንን ሲያካትት፣


- ኢማን የሚለው ተነጥሎ ሲጠቀስ በውስጡ ኢስላም የሚለውን ያካትታል።


- የተጠቀሰው ኢህሳን የሚለው ብቻ ከሆነ ግን በውስጡ ኢስላምና ኢማን ይካተታሉ ።


የአምልኮ ምንነት፡--


44


የአምልኮ ቋንቋዊ ትርጉም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት ሲሆን ኃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ ማንኛውም አላህ የሚወደው ነገር ቃልም ሆነ ተግባር ግልፅም ሆነ ስውር አምልኮ ይባላል።


- አምልኮ ሦስት ማዕዘናት አሉት እነሱም፡-


1- መውደድ፤


2- መፍራትና


3- መከጀል ናቸው።


ይህ ማለት አላህን በመውደድ፤ እዝነቱን በመከጀል እና ቅጣቱን በመፍራት መገዛት ማለት ነው ።


የአምልኮ መስፈርቶች


ማንኛውም አምልኮ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው እነሱም፡-


1- ኢኽላስ ወይም አምልኮን ለአላህ ብቻ ማድረግ አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ ኃይማኖትን ፍፁም ለአላህ ብቻ አድርገው ሊገዙት እንጂ አልታዘዙም” (አል-በይና: 5)


2- ሙታበዓ(መከተል) ይህም የሚረጋገጠው ማንኛውም ዒባዳ በአላህ መልእክተኛ // አስተምህሮና አሰራር መሰረት ሲፈፀም ብቻ ነው የአላህ መልዕክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ትዕዛዛችን የሌለበትን ተግባር በአምልኮ ስም ያከናወነ ስራው ተመላሽ ነው”ብለዋል።


45


አምልኮ በሁለት ይከፈላል፡-


1- ተፈጥሮአዊ አምልኮና


2- ኃይማኖታዊ አምልኮ ናቸው።


ተፈጥሮአዊ በሆነው በአላህ ትዕዛዝ ስር ማደር ተፈጥሮአዊ አምልኮ ይባላ ይህም የአምልኮ ክፍል ሁሉንም ፍጥርታት ያካትታል።


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“በሰማያትና በምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ ለረህማን ባሪያዎች ሆነው ይመጣሉ”(መርየም: 93)።


ለአላህ ህግና ስርዓት ታዛዥና ተገዥ መሆን ደግሞ ኃይማኖታዊ አምልኮ ይባላል። ይህም የአምልኮ ክፍል በአላህ አምነው እሱን ብቻ ለሚገዙና መልእክተኞችን ለሚከተሉ ሰዎች የተለየ ማዕረግ ነው ።


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ የረህማን ባሮች እነዚያ በምድር ላይ ረጋ ብለው የሚሄዱ ናቸው ” (አል-ፉርቃን: 63)


አምልኮን ለአላህ ብቻ በማድረግ ረገድ ዋና መለኪያና መመዘኛ፡-


ማንኛውንም አምልኮ ለአላህ ብቻ ማድረግ ተውሂድ ይባላል ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ደግሞ ማጋራት ይባላል ። አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ አላህን ተገዙ በእሱም ምንንም አታጋሩ ” (አኒሳእ: 36)


46


አላህ በሌላ አንቀፅ ላይም እንዲህ ይላል፦





“ ጌታህ እሱን ብቻ እንጂ ከእሱ ሌላ ማንንም አትገዙ በማለት አዘዘ (ወሰነ)” (አል-ኢስራእ: 23)


*- ዱዓን( ፀሎትን) ፤ፍርሐትን ፤እርድን ፤ስለትንና የመሳሰሉትን የአምልኮ ዘርፎች ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል አሳልፎ መስጠት ከመንገድ (ከኢስላም) የሚያስወጣ የሽርክ ወንጀል ነው።


የውዴታ ዓይነቶች፡--


ውዴታ አራት ዓይነቶች አሉት እነሱም፡-


1- አላህንና አላህ የሚወደውን ነገር ሁሉ መውደድ ከአምልኮ ይመደባል አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ እነዚያ ያመኑትም አላህን ከማንኛውም በላይ ይወዳሉ”(አልበቀራህ: 165)


2- ለአላህ እንጂ ለማንም የማይገባን ውዴታና ክብር ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት በአላህ እንደማጋራት ይቆጠራል አላህ እንዲህ ይላል፡-





( 165 )


“ከሰዎችም እንደ አላህ አድርገው የሚወዷቸውን ጣዖታት የሚገዙ አሉ” (አልበቀራህ: 165)።


3- ኃጢኣትን ፤ በኃይማኖት ፈጠራን እና አላህ እርም ያደረጋቸውን ነገሮች መውደድ ከወንጀል ይመደባል፦


47


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እነዚያ በአማኞች ላይ ፀያፍ ተግባር እንዲሰራጭና ስማቸውን ማጉደፍ የሚወዱ ሰዎች ለነሱ በዚች በቅርቢቱ ሕይወትና በመጨረሻይቱም ዓለም አሳማሚ የሆነ ቅጣት አለባቸው አላህም ያውቃል እናንተ አታውቁም ” (አኑር: 19) ።


4- ሚስቶችን፤ ልጆችን፤ ገንዘብንና የመሳሰሉትን መውደድ ተፈጥሮአዊ ውዴታ ይባላል ይህም ዓይነቱ ውዴታ የተፈቀደ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ሴቶችን፤ ወንድ ልጆችን፤ ከወርቅና ከብር የሆኑ ብዙ ገንዘቦችን፤ ለተመልካች የሚያስደስቱ ፈረሶችን፤ የቤት እንስሳትንና አዝእርትን መውደድ ለሰዎች ተዋበላቸው። እነዚህ ሁሉ ነገሮች የቅርቢቱ ህይወት መገልገያና መጠቀሚያ ናቸው አላህ ከእርሱ ዘንድ ጥሩ መመለሻ አ”(አሊዒምራን: 14)።


ፍርሐት፡--


ችግር ሊያመጣ በሚችል ነገር መረበሽና መጨነቅ ፍርሐት ይባላል። እሱም ብዙ ዓይነቶች አሉት ከነሱም ዋና ዋናዎቹ፡-


1- ከአምልኮ ዘርፎች የሚቆጠር የፍርሐት ዓይነት ሲሆን እሱም አላህን ብቻ መፍራት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-


48





“ ከጌታውም ፊት(እንደሚቆም አምኖና ፈርቶ መልካምን የሰራ ሰው) ሁለት ገነቶች አሉት”(አረሕማን: 46)


አላህን መፍራት በሁለት ይከፈላል፡-


አንደኛ- ከወንጀል ለመራቅ የሚያግዝና ግዴታዎችን ለመፈፀም የሚያነሳሳ ከሆነ ፍርሐቱ የተወደደና የተመሰገነ ሲሆን፦


ሁለተኛ- ከአላህ እዝነትና ምሕረት ተስፋ የሚያስቆርጥ ከሆነ ደግሞ ፍርሐቱ የተወገዘና የተጠላ ይሆናል።


2- ተናካሽ የሆኑ የዱር እንስሳትን ፤ጠላትን ፤ግፈኛ ባለስልጣንና የመሳሰሉትን መፍራት ደግሞ ከአምልኮ ጋር ግንኙነት የሌለው ተፈጥሮአዊ ፍርሐት በመባል ይታወቃል እሱም የተፈቀደ ነው።


3- አላህ እንጂ ሌላ አካል ሊያደርሰው የማይችለውን ችግር ለምሳሌ፦ ድህነትን፤ ህመምን፤ አለመውለድንና የመሳሰሉትን ችግሮች ከአላህ ሌላ የሆነ አካል ያደርስብኛል ብሎ መፍራት ከትልቁ ሽርክ ይመደባል ይህም ስውሩ ፍርሃት በመባል ይታወቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ አትፍሯቸው ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ እኔን ብቻ ፍሩ”(ኣሊ-ዒምራን: 175)።


4-ሰዎችን በመፍራት አላህ ግዴታ ያደረገውን አለመፈፀም ወይም የከለከለውን መስራት የተወገዘ ፍርሐት ይሆናል።





“ ሰዎችንም አትፍሩ እኔን ብቻ ፍሩ” (አል-ማኢዳ: 44)


49


ተስፋ፡--


መልካምን ነገር መመኘትና መከጀል ተስፋ ይባላል። እሱም ሦስት ክፍሎች አሉት፦


1- አላህን ብቻ መከጀልና ተስፋ ማድረግ ከአምልኮ የሚመደብ ተስፋ ሲሆን እሱም ሁለት ክፍሎች አሉት፡-


ሀ - ተስፋው ከመልካም ስራ ጋር የተጣመረና የተዛመደ ከሆነ የተመሰገነና የተወደደ ተስፋ ይባላል ። አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ የጌታውንም መገናኘት የሚከጅል ሰው፤ መልካምን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት ማንንም አያጋራ”(አል-ከህፍ: 110)


ለ - ተስፋው ከመልካም ስራ ጋር የተዛመደ ካልሆነ ደግሞ የተጠላና የተወገዘ ከንቱ ምኞት ይባላል።


2- ሰዎች ማድረግ በሚችሉት ነገር አንዱ ከሌላው መከጀል የተፈቀደ ነው ይህም ተፈጥሮአዊ ተስፋ ይባላል።


3- ከአላህ ውጭ ማንም አካል መስጠት የማይችለውን ነገር ለምሳሌ፦ ጤናን፤ ሀብትን፤ ልጅንና የመሳሰሉትን ነገሮች ከአላህ ሌላ ከሆነ አካል መከጀል በአላህ የማጋራት ወንጀል ይሆናል።


ተወኩል ወይም መመካት፡--


50


የተወኩል ቋንቋዊ ትርጉም መጠጋት (መደገፍ) ማለት ሲሆን ኃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ ልቦናን በአላህ ላይ ብቻ እንዲመካና እንዲፀና ማድረግ ተወኩል ይባላል ። ተወኩል(መመካት) በሦስት ይከፈላል እነሱም፡-


አንደኛ - ከአምልኮት የሚመደብ ተወኩል ሲሆን እሱም በአላህ ላይ ብቻ መመካት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-





" አማኞችም ከሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ " (አል-ማኢዳ: 23)


ይህ የተወኩል ክፍል አምልኮ ይሆን ዘንድ ሦስት ነገሮች መሟላት አለበት እነሱም፡-


1- በአላህ ላይ በእርግጠኝነት መመካት፤


2- በአላህ ላይ ሙሉ እምነት መኖር እና ማንኛውም ነገር በአላህ እጅ መሆኑን ማመን፤


3- የተፈቀዱ ቁሶችንና ምክንያቶችን መስራት ናቸው ።


ሁለተኛ - ከአላህ ውጭ በሆነ አካል ላይ መመካትና በቁሶች ወይም በምክንያቶች ላይ መመካት ከሽርክ ይቆጠራል።


ሦስተኛ- መተካት ወይም መወከል ሲሆን ይህም አንድ ሰው ሌላውን ግለሰብ የግል ስራውን ያከናውንለት ዘንድ መተካት/መወከል/ ነው። ይህም የተፈቀደ ነው ።


በመመካትና በመወከል መካከል ያለው ልዩነት፡-


1- ተወኩል ወይም መመካት ውስጣዊና የልቦና ተግባር ሲሆን እሱም ከአምልኮት ጋር ተያያዥነት አለው ።


2- መተካት ወይም መወከል ግን ከአምልኮ ጋር ግንኙነት የሌለው ውጫዊ ስራ ነው ።


51


ዱዓ ወይም ልመና፡--


ዱዓ ከአምልኮት ዘርፎች ትልቁን ሥፍራ ይይዛል እሱም በሁለት መልኩ ይገለፃል፡-


አንደኛው- በጥያቄ መልኩ የሚገለፅ ልመና ነው ለምሳሌ፦


አላህ ሆይ! እዘንልኝ ፤ ማረኝ እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በማንሳት አላህን መለመንና መማፀን፤


ሁለተኛው- በሥራ የሚገለፅ የጸሎት ዓይነት ነው ለምሳሌ፦ ሦላትን በመስገድ ፤ ዘካን በመስጠት ፤ ፆምን በመፆም ፤ ሐጅን በማድረግ ፤ ሶደቃን በመስጠትና የመሳሰሉትን መልካም ስራዎች በማከናወን የሚገለፅ የአምልኮ ተግባር ነው። እነዚህም የአምልኮት ዘርፎች ዱዓ በሚል ስያሜ የተሰየሙበት ምክንያት አንድ ሰው እነዚህንና የመሳሰሉትን መልካም ስራዎች ሲፈጽም የአላህን ውዴታና ጀነትን ፈልጎ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ የአላህን ቁጣና ጀሃነምን ፈርቶ ነው።


ልመና በሁለቱም ክፍሎቹ ለአላህ ብቻ መሆን ያለበት ትልቅ የአምልኮት ዘርፍ ነው። ስለዚህ ይህን ትልቅ አምልኮ ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል አሳልፎ የሰጠ ሰው አጋሪ( ከሃዲ) ይባላል።


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ ለአምላክነቱ ማስረጃ ሊኖረው የማይችልን አካል ከአላህ ጋር የሚገዛ ሰውም ምርመራው ከጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም ”(አል-ሙእሚኑን: 117)።


በሌላም አንቀፅ ላይ አላህ እንዲህ ይላል፡-





52


“ መስገጃ ቦታዎችም የአላህ ብቻ ናቸው (በውስጣቸውም) ከአላህ ጋር ማንንም አትገዙ( አትፀልዩ)”(አል-ጅን: 18)


የአላህ መልእክተኛ // ቲርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ዱዓ ኢባዳ (አምልኮ) ነው ” ብለዋል ።


ሩቅያ//የበሽታመከላከያ//፡--


ሩቅያ በቋንቋ ደረጃ መጠበቂያ ወይም መከላከያ ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ በበሽተኛው ላይ የሚነበቡ የቁርኣን አንቀፆች ፤ዚክሮችና ዱዓዎች ማለት ነው።


ሩቅያ ሁለት ዓይነቶች አሉት እነሱም፡-


አንደኛው- የሚከተሉትን ሦስት መስፈርቶች ካሟላ የተፈቀደ ሲሆን እነሱም


1- በአረበኛ ቋንቋና ትርጉሙ በሚታወቅ ነገር መሆን፣


2- በአላህ ቃል(በቁርኣን)፤ በስሞቹና በባህርያቱ መሆን፣


3- ሙሉ በሙሉ በበሽታ መከላከያ ላይ አለመመካት እና መከላከያው በአላህ ፍቃድ እንጂ በራሱ ጊዜ ለውጥ ወይም ፈውስ እንደማያመጣ ማመን ናቸው።


የአላህ መልእክተኛ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፣-





53


“ የበሽታ መከላከያችሁን አሳዩኝ (አቅርቡልኝ) የበሽታ መከላከያ በውስጡ የማጋራት ተግባር እስከሌለበት ድረስ የተፈቀደ ነው ” ብለዋል ።


ሁለተኛው- ከእነዚህ መስፈርቶች አንዱ ከተጓደለ መከላከያው የማጋራት ወንጀል ይሆናል።


የአላህ መልእክተኛ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ አቡዳውድ እና አህመድ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ያልተፈቀዱ የበሽታ መከላከያዎች፤ ህርዞች እና መስተፋቅር በአላህ የማጋራት ኃጢኣት ናቸው ” ብለዋል ።


ተማኢም((ህርዞች))፡--


በሕፃናትና በእንስሳት አንገት ላይ ከዐይን ለመከላከል በሚል የሚታሰር ነገር ህርዝ ይባላል።


ህርዝ በሁለት ተከፍሎ ይታያል። እነሱም፡-


አንደኛ- ከቁርኣንና ነቢያዊ ዱዓ( ፀሎቶች) የሚዘጋጅ ሲሆን ይህ የህርዝ ዓይነት ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም በሚል ዑለሞች ሁለት አስተያየቶች አሏቸው። ይሁን እንጂ ትክክለኛውና አመዛኙ አይቻልም የሚለው ነው። ለዚህም የሚከተሉትን ምክንያቶች ይጠቅሳሉ፡-


1- ህርዝን የሚከለክሉት ሐዲሶች አጠቃላይነት ስላላቸው፤


2- የሽርክ በሮችን ለመዝጋት ስለሚረዳ። ምክንያቱም ሰዎች በዚህ አስታከው ሽርክ አዘል ነገሮችን ሊያስሩ(ሊጠቀሙ)ስለሚችሉ፤


3- የቁርኣንና ነቢያዊ ዱዓዎችን ክብር ለመጠበቅ ሲባል" ምክንያቱም አንድ ሰው እነሱን አስሮ (አንጠልጥሎ) ወደ ተለያዩ ቆሻሻ ሥፍራዎች ሊገባ ስለሚችል ።


54


ሁለተኛ- ከቁርኣንና ከነቢያዊ ዱዓ ውጭ በሆነ ነገር የሚሰራ ለምሳሌ፦ በሰይጣናት ስም፤ ትርጉማቸው በማይታወቅ ፁሁፎች እና በሰንጠረዦች አማካኝነት የሚሰራ ህርዝ ነው ። ይህ የህርዝ ዓይነት ከአላህ ሌላ በሆነ ነገር ማመንን ስለሚያስከትል የተከለከለና ከከፍተኛው የማጋራት ኃጢኣት ይመደባል።


ከዚህ የምንማረው ዋና ቁም ነገር ህርዝ ከቁርኣን ከሆነ የተጠላ መሆኑንና ከቁርኣን ሌላ ከሆነ ደግሞ የማጋራት ወንጀል መሆኑን ነው። የአላህ መልእክተኛ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ አቡዳውድና አህመድ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ያልተፈቀዱ የበሽታ መከላከያዎች፤ህርዞች እና መስተፋቅር በአላህ የማጋራት ኃጢኣት ናቸው ” ብለዋል ።


በረከትን ወይም ረድኤትን መፈለግ፡--


በረከትን መፈለግ በሁለት ይከፈላል እነሱም፡-


1ኛ- የተፈቀደ ሲሆን ይኽውም፡-


- በአላህ መልእክተኛ// አካል፤ በፀጉራቸው እና በላበታቸው በረከትን/ረድኤትን/ ማገኘት ሲሆን ይህም በህይወት በነበሩበት ዘመን የተለየና የተገደበ ነው።


- ቅዱሳን በሆኑ ሥፍራዎች ለምሳሌ ፦ መካ በሚገኘው በተከበረው መስጂድ ፤ መዲና በሚገኘው በነቢዩ // መስጂድ እና በሌሎችም ቅዱሳን ሥፍራዎች የተፈቀዱ ኢባዳዎችን በማድረግ ከአላህ በረከትን ማገኘት።


- አላህ በደረጃ ባበለጣቸው ወራትና ቀናት ለምሳሌ፦ በረመዷን ወር፤ ከዙል ሂጃ ወር በአስሮቹ ቀናትና ሌሊቶች፤ በተከበረችው ሌሊት(ለይለቱ- አል-ቀድር)ና በመሳሰሉት ወራትና ቀናት የተፈቀዱ ዒባዳዎችን በማድረግ ከአላህ ረድኤትንና በረከትን ማገኘት፤


55


- አላህ በረከት ያደረጋቸውን ምግቦች ለምሳሌ፦ ዘይት ዘይቱንን(የወይራ ዘይት) ፤ ማርን ፤ጥቁር አዝሙድን ፤ የዘምዘም ውሃን እና የመሳሰሉትን በመጠቀም በረከትን(ረድኤትን) ማገኘት ነው።


2ኛ- የተከለከለ ሲሆን እሱም፡-


- የተቀደሱ ሥፍራዎችን በመሳም ፤ በመንካት፤ ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያለውን ነገር ቆርጦ መያዝ እና አፈሩን በመጠጣት ወይም በመሞቅ በረከትን ወይም ፈውስን ለማገኘት ማሰብ፤


- በደጋግ ሰዎች ቅሪት፤ በመቃብራቸው እና ታሪካዊ በሆኑ ሥፍራዎች ለምሳሌ ፦ ነቢዩ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ በተወለዱበት ሥፍራ ፤ ሂራ በተባለው ተራራ እና በመሳሰሉት ሥፍራዎች በረከትን ለማገኘት መሞከር።


- የአላህ መልእክተኛ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ የተወለዱበትን ቀን ወይም ሌሊት፤ ወደ በይተል- መቅዲስ እና ከዚያም ወደ ሰማይ የወጡበትን ሚዕራጅ በመባል የሚታወቀውን ሌሊት፤ ከሻዕባን ወር አስራ አምስተኛዋን ሌሊት እና የመሳሰሉትን ቀናትና ሌሊቶች በማክበር በረከትን(ረድኤትን) ለማገኘት ማሰብ ናቸው።


በረከትን(ረድኤትን) ሊገድቡ የሚችሉ ወሳኝ ነጥቦች፡-


1- በረከትን ወይም ረድኤትን መፈለግ የአምልኮ ዘርፍ መሆኑንና አምልኮ ደግሞ በማስረጃ መወሰን እንጂ መፍጠር የማይቻል መሆኑን በሚገባ መረዳት፤


2- በረከት(ረድኤት) በሙሉ የአላህ መሆኑንና መስጠትም ሆነ መንሳት የሚችለው እሱ ብቻ መሆኑን አምኖ ከእርሱ ብቻ መጠየቅ እንጂ ከሌላ አካል መጠየቅ እንደማይፈቀድ ማወቅ፤


3- በረከት የሚያስገኝን ነገር ሲያከናወን ህጋዊ በሆነ አሰራር መፈፀም ናቸው።


ምክንያቶችን በመጠቀም ረገድ መኖር ያለባቸው ወሳኝ ነጥቦች፡-


1ኛ- ምክንያቶችን ያስገኘና ምክንያት እንዲሆኑ ያደረገው አላህ ብቻ ስለሆነ በአላህ ላይ እንጂ በምክንያቶች ላይ አለመመካት፤


56


2ኛ- ምክንያቶች ከአላህ ውሳኔ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ማወቅና መረዳት ናቸው።


አንድ ነገር ምክንያት መሆኑ በሁለት መንገድ ይታወቃል፡-


1- በቁርዓንና በሓዲስ አማካኝነት ለምሳሌ ፦ የማር መድሃኒትነት በቁርአን የተነገረ ሲሆን የጥቁር አዝሙድ መድሃኒትነት በሐዲስ ተዘግቧል።


2- በትክክለኛ ሙከራም ሊታወቅ ይችላል።


ተወሱል ወይም መጠጋት፡--


ተወሱል(መጠጋት) በሁለት ይከፈላል እነሱም፡-


አንደኛ- የተፈቀደ ሲሆን እሱም በሦስት መልኩ ይገለፃል።


1- አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ በማወደስና በመለመን ወደ እርሱ መጠጋት፤


2- አንድ ሰው የሰራውን መልካም ስራ በማንሳት አላህን መማፀንና ወደ እሱ መጠጋት፤


3- በሕይወት ባሉ ደጋግ ሰዎች ዱዓ(ፀሎት) ወደ አላህ መቃረብ ናቸው ።


ሁለተኛ- የተከለከለ የተወሱል ዓይነት ሲሆን እሱም ከተፈቀዱት የተወሱል ዓይነቶች ውጭ በሆነ ነገር ወደ አላህ ለመጠጋት መሞከር ነው። ይህም በሦስት ተከፍሎ ይታያል፡-


1- በሰዎች ትልቅነትና ክብር ወደ አላህ ለመጠጋት መሞከር፣


2- ወደ አላህ ለመጠጋት ለአላህ ወዳጆችና ለደጋግ ሰዎች መሳል ፤


57


3- በአላህ ወዳጆች መቃብር አካባቢ በመቀመጥ እና በማረድ ወደ አላህ ለመቃረብ ማሰብ ናቸው ።


እርድ፡--


እርድ ሦስት ክፍሎች አሉት እነሱም፡-


1- የተፈቀዱ አምልኳዊ እርዶች፤


2- ለምግብነት ብቻ የሚታረዱ እርዶች፣


3- የማይፈቀዱ አምልኳዊ እርዶች ናቸው።


አንደኛ -የሚፈቀዱ አምልኳዊ እርዶች፡-


1- ለዒደል- አድሃ ማረድ፤


2- ለአላህ የተሳለውን የእርድ ስለት ማረድ፤


3 - በሐጅ ወቅት ሶደቃ ለመስጠት ማረድ፣


4 - በሐጅና ዑምራ ስራ ላይ እያለ ላጠፋው ጥፋት ማካካሻ ማረድ፣


5 -ልጅ ሲወለድ ለዓቂቃ ማረድ፤


6 - እንግዳን ለማስተናገድ ማረድ እና የመሳሰሉት ናቸው ።


ሁለተኛ - ለመመገብ እና ለመሸጥ ማረድ ሲሆን ይህ ዓይነት እርድም የተፈቀደ ነው ።


ሦስተኛ- የማይፈቀዱ አምልኳዊ እርዶች፡-


58


1 - ከአላህ ውጭ ለሚመለኩ ለባዕድ አማልክት ማረድ፣


2- ለአጋንንት ፤ ለመቃብር፤ ለአድባር(ለቆሌ)እና ለመሳሰሉት ነገሮች ማረድ፤


3 - በአዲስ ቤት ለመኖር ሲፈልግ ከመገባቱ በፊት ከአጋንንት ለመከላከል በሚል ስሜት ማረድ፣


4- ሁለት ተጋቢዎች(ሙሽሮች) ወደ ቤት ሲገቡ ደሙን ረግጠው ይገቡ ዘንድ ማረድ፣


5- ከአላህ ሌላ በሆነ አካል ስም ማረድ እና የመሳሰሉት ናቸው።


 ከዚህ የምንረዳው ዋና ቁም ነገር


1- አምልኳዊ የሆነውን እርድ ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል አሳልፎ መስጠት የማይፈቀድ መሆኑንና ፣


2- ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል ማረድ ከአላህ እዝነት የሚያርቅና የሚያስረግም ከፍተኛ የማጋራት ወንጀ መሆኑን ነው።


አላህ እንዲህ ይላል፤





“ስግደቴ ፤ እርዴ(መገዛቴ) ፤ ህይወቴና ሞቴም ለዓለማት ፈጣሪ ለአላህ ብቻ ነው በል” (አል-አንዓም: 162) ።


የአላህ መልእክተኛ // ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል የሚያርድ ሰው አላህ ይረግመዋል” ብለዋል።


ነዝር ((ስለት))፡--


59


ስለት አላህ ብቻ መሆን ያለበትና ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት የማይፈቀድ የአምልኮ ዘርፍ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ እነዚያ የአላህ ባሮች ለእርሱ የተሳሉትን ስለት ይሞላሉ”(አል-ኢንሳን: 7)


ከአላህ ውጭ የሆነን አካል ለማክበርና ወደ እርሱ ለመቃረብ ብሎ መሳል በአላህ የማጋራት ወንጀል ይሆናል። ለምሳሌ ፦ልጅ ከተወለደልኝ፤ በሽተኛው ከዳነልኝ ወዘተ… እገሌ ከተባለው ወሊይ ቀብር ዘንድ እንደዚህ ዓይነት በግ ወይም ከብት አርዳለሁ ብሎ መሳል የሽርክ ተግባር ነው።


እርዳታንና ጥበቃን መለመን፡--


እነዚህ ነገሮች ከአላህ ብቻ መጠየቅ ያለባቸው የአምልኮ ዘርፎች ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ አንተን ብቻ እንገዛለን አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን ” (አልፋቲሃ: 5) አላህ በሌላም አንቀፅ ላይ እንዲህ ይላል፡-





“ፈጣሪያችሁን እርዳታ በጠየቃችሁ ጊዜና እሱም ወዲያውኑ ምላሽ በሰጣችሁ ጊዜ ያለውን አስታውሱ ” (አል-አንፋል: 9)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ በሰዎች ፈጣሪ ( በአላህ) እጠበቃለሁ በል ” (አናስ: 1) ።


60


ከአላህ ሌላ ከሆነ አካል እርዳታንና ጥበቃን መለመን በሁለት መልኩ ይታያል፡-


አንደኛው፦አራት መስፈርቶችን ካሟላ የተፈቀደ ሲሆን እነሱም፡-


1- እገዛ (እርዳታ) የሚጠየቅበት ነገር ሰዎች ማድረግ የሚችሉት መሆን፦ ስለዚህ ጤናን፤ ልጅን፤ሀብትን፤ እምነትንና የመሳሰሉትን ከአላህ ሌላ ከሆነ አካል መጠየቅ አይፈቀድም ምክንያቱም እነዚህንና የመሳሰሉትን መስጠት የሚችለው አላህ ብቻ ስለሆነ፤


2- እርዳታ የሚጠየቅበት ነገር በሰዎች ሃይል ሊፈፀም የሚችል መሆን፤


3 - እርዳታ/እገዛ/ የሚጠየቀው አካል በሕይወት መኖር እና


4- እርዳታ የሚጠየቀው አካል ጥያቄውን መስማት የሚችል መሆን ናቸው ።


ሁለተኛው- የማይፈቀድ ሲሆን እሱም በመጀመሪያው ነጥብ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ ሲቀር ነው ።


ምልጃ፡--


ምልጃ በሁለት ይከፈላል፡-


አንደኛው- ኢስላም እውቅና የሰጠውና ያፀደቀው ምልጃ ሲሆን ይኽውም ሁለት መስፈርቶችን ሲሟላ ነው።


1- አማላጁ እንዲያማልድ አላህ የፈቀደለት መሆን፣


2- የአማላጁና ምልጃ የሚጠየቅለት ግለሰብ ስራ አላህ የሚወደው መሆን ናቸው።


አላህ እንዲህ ይላል፡-





61


“ በአላህ ፍቃድ እንጂ ማንም ከእርሱ ዘንድ የሚያማለድ የለም ” አል-በቀረህ: 255)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“በሰማያት ውስጥ በርካታ መላእክት አሉ እነዚህ መላእክት አላህ ለፈለገውና ለወደደው ሰው ከፈቀደ በኋላ እንጂ ማንንም ማማለድ አይችሉም ” (አነጅም: 26)።


ሁለተኛው- ምልጃው በመጀመሪያው ነጥብ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ከሆነ የተከለከለ ይሆናል ።


 ከሰዎች ምልጃን መጠየቅ ይፈቀድ ዘንድ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው፡-


1ኛ- ምልጃ የሚጠየቀው ግለሰብ በህይወት ያለና የተጠየቀውን ነገር ማድረግ የሚችል መሆንና፤


2ኛ- ምልጃ የተጠየቀበት ጉዳይ በሰዎች አቅምና ችሎታ የሚፈፀም መሆን ናቸው።


መቃብርን መዘየር//መጎብኘት//፡--


ቀብርን መዘየር በሦስት ይከፈላል፡-


አንደኛ- ጉብኝቱ ለሚከተሉት ዓላማዎች ከሆነ፡-


62


1- የመጨረሻውን ጉዞ ለማስታወስ፤


2- በመቃብር ውስጥ ለሚገኙ ለሙስሊም ሙታን ሰላምታን


ለማቅረብና


3- ለሙታን ዱዓ ለማድረግ ከሆነ የተፈቀደ ይሆናል።


ሁለተኛ- ጉብኝቱ ወይም ዚያራው ለሚከተሉት ዓላማዎች ከሆነ ደግሞ ለምሳሌ፦


1- ከቀብሩ ዘንድ ሆኖ አላህን ለመገዛት፣


2- በቀብሩ ውስጥ ከሚገኘው ሟች በረከትን/ረድኤትን/ ለመጠየቅ፣


3- ቁርኣን ቀርቶ ምንዳውን ለቀብሩ ባለቤት ለመስጠት እና ለመሳሰሉት መጥፎ ዓላማዎች ከሆነ ተውሂድን የሚያጓድል ብሎም ወደ ማጋራት ወንጀል የሚያመራ የፈጠራ ተግባር ይሆናል።


3ኛ - ዚያራው/ጉብኝቱ/ ከአምልኮት ዘርፎች ለምሳሌ ፦ እንደ- ዱዓ፤ እርዳታ መጠየቅ፤ ስለት፤ ማረድና የመሳሰሉትን አምልኮዎች ለቀብሩ ባለቤት አሳልፎ ለመስጠት ከሆነ ዚያራው ተውሂድን በቀጥታ የሚያፈርስ የማጋራት ተግባር ይሆናል።


ድግምት፡--


ድግምት በአላህ ውሳኔ በአካልም ሆነ በስነልቦና ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ትልቅ ኃጢኣት ነው።


ድግምት ሁለት ዓይነት ነው ፡-


1- ከእስልምና ሃይማኖት የሚያስወጣና ሟርተኛው በግድያ እንዲቀጣ የሚያደርግ ከፍተኛ የማጋራት ወንጀል ሲሆን እሱም በሰይጣናት በመታገዝ የሚሰራ የድግምት ዓይነት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-





63


“ድግምትን ያስተምሩ የነበሩ ሁለት አስተማሪዎችም “ እኛ ፈተናዎች ነን ድግምትን በመማር አትካድ በማለት ሳያስጠነቅቁ በፊት ማንንም አያስተምሩም ” (አልበቀረህ: 102)።


ይህ አንቀፅ የሚያስረዳው ድግምትን መማር ከኢስላም የሚያስወጣ ክህደት መሆኑን ነው ።


2- ከእስልምና ሃይማኖት ባያስወጣም ነገር ግን ደጋሚው ወይም ሟርተኛው በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ችግር ለመቅረፍ ሲባል እንዲገደል የሚያደርግ ትልቅ ወንጀልና አመፅ ሲሆን እሱም ከተለያዩ መድሃኒቶች የሚሰራ የሟርት ዓይነት ነው ።


ድግምትን መፍታት (ማክሸፍ)፡-


ድግምትን መፍታት (ማክሸፍ) በሁለት ተከፍሎ ይታያል፡-


1ኛ- ድግምትን በድግምት መፍታት (ማክሸፍ) የተከለከለና የሰይጣን ስራ ሲሆን፤


2ኛ- ኃይማኖታዊ መከላከያዎችንና የተፈቀዱ መድሃኒቶችን በመጠቀም ድግምትን መፍታት (ማክሸፍ) ግን የተፈቀደ ነው ።


ከሟርተኞች ማስጠንቀቅና የነሱን ጉዳይ ለሚመለከተው አካል መናገር፡-


*- የድግምተኞችን ጉዳይ ለሚመለከተው አካል መጠቆምና ሙስሊሞች ከእነሱ እንዲጠንቀቁ ማድረግ ኢስላማዊ ግዴታ ነው።


የድግምተኛ ምልክቶች፡-


1ኛ- የበሽተኛውንና የእናቱን ስም መጠየቅ፣


2ኛ- ከበሽተኛው አካል ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች ለምሳሌ፦ ከቀሚስ፤ ከቢጃማ፤ ከራስ ማሰሪያ፤ ከውስጥ ልብስና ከመሳሰሉት ቆርጦ ማስቀረት፤


3- ሰንጠረዦችን ማስመር፤


64


4- ትርጉሙ ማይታወቅ ነገር ማነብነብ፤


5- በሽተኛው ወረቀቶችን አቃጥሎ ጪሱን እንዲታጠን ማዘዝ፣


6- የተለየ የቆዳ ቀለም ያለው የቤት እንስሳ አስመጥቶ የአላህን ስም ሳያወሳ አርዶ ህመም ያለበትን የበሽተኛውን የሰውነት ክፍል በደም መቅባት፣


7- በሽተኛው አራት መዓዘንና በውስጡ ፊደሎች ወይም ቁጥሮች ያሉበትን ሂጃብ ወይም ልብስ እንዲለብስ ማዘዝ፤


8- በሽተኛው የተለያዩ ነገሮችን በጉድጓድ ውስጥ እንዲጨምር/ እንዲቀብር ማዘዝ እና የመሳሰሉት ናቸው ።


ማሳሰቢያ፡-


ለሰዎች የህክምና አገልግሎት እሰጣለሁ የሚል አካል ከእነዚህ ምልክቶች አንዱንም ቢሆን ከተጠቀመ ድግምተኛ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል።


ጠንቋይና አዋቂ ነኝ ባይ፡--


በሰይጣናት በመታገዝ ወደፊት ሊከሰት የሚችልን ነገር ወይም የተሰረቀና የጠፋን ነገር ሥፍራ አውቃለሁ ብሎ የሚናገር ሰው ጠንቋይ ይባላል ብያኔውም ቁርኣንን የማስተባበል ክህደት ነው። ምክንያቱም አላህ በቁርኣን እንዲህ ስለሚል፡-





“ አላህ እንጂ በሰማያትና በምድር ያሉ ፍጥረታት በሙሉ ከሰዎች ድብቅና ስውር የሆነን ነገር አያውቁም በል ” (አነምል: 65)


አንድ ጠንቋይ ከሌላው የሚለይበት የአሰራር ስልትና ተጨማሪ ስያሜው፡-


65


1ኛ- የሩቅ ሚስጥሮችን አውቃለሁ ብሎ ሲናገር በጅኖች በመታገዝ ከሆነ ጠንቋይ ይባላል።


2ኛ- በከዋክብት አማካኝነት ከሆነ ደግሞ ሙነጂም/ ኮከብ ቆጣሪ/ ይባላል።


3ኛ-የጠፋና የተሰረቀን ነገር ሥፍራ የሚናገር ከሆነ አውቃለሁ ባይ ይባላል።


4ኛ- በመሬት ላይ በማስመር ከሆነ ደግሞ ረማል (ጠጠር ቆጣሪ) ይባላል ።


ወደ ጠንቋይ የመሄድ ብይን፡-


ወደ ጠንቋይ የመሄድ ብይን በሁለት መልኩ ይታያል።


1ኛ- ከጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለ አንድ ነገር የጠየቀ ሰው የጥያቄውን መልስ እውነት ብሎ ባይቀበልም በመሄዱ ብቻ የአርባ ቀን ሦላቱ/ስግደቱ/ ተቀባይነትን ያጣል። የአላህ መልእክተኛ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ወደ ጠንቋይ ሄዶ ስለ አንድ ነገር የጠየቀ ሰው ያአርባ ቀን ስግደቱ ተቀባይነት አያገኝም ” ብለዋል።


2ኛ- ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የጠየቀና የተሰጠውን መልስ እውነት ብሎ የተቀበለ ሰው በቁርኣን እንደ ካደ ይቆጠራል።


የአላህ መልእክተኛ // ሃኪምና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ፡-





"ወደ ጠንቋይ ሄዶ ጠንቋዩ የሚናገረውን እውነት ብሎ የተቀበለ ሰው በሙሀመድ ላይ በተወረደው ቁርዓን በእርግጥ ካደ" ብለዋል ።


በገድ ማመን፡--


66


በገድ ማመን ተውሂድን የሚያበላሽ የማጋራት ኃጢአት ነው።


የአላህ መልእክተኛ // አቡ ዳውድና ትርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ በገድ ማመን የማጋራት ወንጀል ነው ” ብለዋል።


የአላህ መልእክተኛ // በገድ ማመን በኢስላም የማይፈቀድ መሆኑን ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“አንድ በሽታ በራሱ ጊዜ የመተላለፍ ችሎታ የለውም ፤ ገድ፤ ጉጉትና ሶፈር የለም” ሲሉ ተናግረዋል።(1)


በገድ ማመን በሁለት መልኩ ተውሂድን ያብላሻል፡-


1- በአላህ ላይ ብቻ በመመካት ፈንታ በገድ ላይ መመካትና፤


2- ትክክለኛ ባልሆነ ነገርና በብዢታ ማመን ናቸው።


በገድ አማኙ ሁለት ሁኔታዎች ይኖሩታል፡-


1ኛ- የሚያምንበት ገድ ሲያጋጥመው ያሰበውን ዓላማ ሰርዞ ከተመለሰ ይህ እምነቱ ከተውሂድ ጋር የሚፃረር የገድ እምነት ይሆናል ።


2ኛ- ያመነበት ገድ ሲያጋጥመው ተፅዕኖ ካሳደረበትና ከተረበሸ በዓላማው ላይ ቢፀናም ወንጀልነቱ እንደ መጀመሪያው ባይከብድም ነገር ግን ተውሂድን የሚያጓድልና በግለሰቡ ላይ ችግርን የሚያስከትል እምነት ይሆናል።


የገድን እምነት ሊያስወግዱ የሚችሉ ነጥቦች፡-


(1(ከዚህ የምንረዳው በነኝህ ነገሮች ማመን ለምሳሌ፦ ጉጉት የተባለው ወፍ በጮከበት አካባቢ ሰው እንደሚሞትና ሶፈር በተባለው ወር የተለያዩ ክስተቶች እንደሚከሰቱ ማመን በኢስላም የተከለከለና መሰረተ-ቢስ እምነት መሆኑን ነው።


67


1ኛ- ቀጣዩን ዱዓ ማድረግ፡-





“ አላሁመ ላ የእቲ ቢልሀሰናቲ ኢላ አንተ ወላ የድፈዑ አሰይኣቲ ኢላ አንተ ወላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ትርጉሙም “ አላህ ሆይ! መልካምን አንተ እንጂ ማንም ማምጣት(መስጠት) አይችልም። መጥፎን(ጉዳትንም) አንተ እንጂ ማንም መከላከል አይችልም። ባንተ ፍቃድ እንጂ ሀይልና ዘዴ አይጠቅምም " ማለት ነው። አቡ ዳውድ ዘግበውታል።





“ አላሁመ ላ ጦይረ ኢላ ጦይሩከ ወላ ኸይረ ኢላ ኸይሩከ ወላ ኢላሀ ኢላ አንተ ” አህመድ ዘግበውታል።


ትርጉሙም፡-“ አላህ ሆይ! ገድንና እድልን ወሳኙ አንተ ብቻ ነህ። መልካምንም መስጠትና መቸር የምትችለው አንተ ብቻ ነህ። ትክክለኛ አምላክ ከአንተ በስተቀር የለም።”


2ኛ-በገድ ማመን በተውሂድ ላይ የሚያስከትለውን አደጋ ማወቅና መረዳት።


3ኛ- በአላህ ውሳኔ ማመን።


4ኛ- ራስን መታገልና በአላህ ላይ ጥሩ እምነትንና ጥርጣሬን ማሳደርና።


5ኛ- መልካሙን ነገር አንተ ምረጥልኝ ብሎ አላህን መማፀን ናቸው ።


አንድ ሰው በገድ አመነ የሚባለው መቼ ነው?


የአላህ መልእክተኛ // አህመድ በዘገቡት ሐዲስ፡-





68


“በዓላማህ ላይ እንድትፀና ወይም ከዓላማህ እንድትመለስ ያደረገህ ነገር የገድ እምነት ይባላል” ብለዋል።


ተስፈኝነት፡--


መልካምን ቃል በመስማት መደሰት ለምሳሌ፡- አንድ መንገደኛ ሰላም የሚል ቃል ሲሰማ መደሰት ተስፈኝነት ይባላል። እሱም የተፈቀደ ነው። የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ መልካም ቃል ያስደስተኛል ” ብለዋል።


በተስፈኝነትና በገድ እምነት መካከል ያለው ልዩነት፡-


1- በአላህ ላይ መጥፎን መጠራጠር፤ አምልኮ የሆነውን ተወኩልን ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል አሳልፎ መስጠትና መጥቀምም ሆነ መጉዳት በማይችል ነገር ላይ አዕምሮን ማሳመን የገድ እምነት ሲሆን ፣


2- በዓላማው ላይ ፀንቶ መልካምን ነገር ከአላህ መከጀል ደግሞ ተስፈኝነት ይባላል ።


* በከዋክብት ዙሪያ ያሉ እምነቶችና አጠቃቀሞች በሁለት መልኩ ይታያሉ፡-


አንደኛው ፦ የተከለከለ ሲሆን እሱም በሦስት ይከፈላል፡-


1- ከዋክብት በራሳቸው ጊዜ ችግሮችንና ክስተቶችን ይፈጥራሉ ብሎ ማመን ከከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ይመደባል።


69


2- በከዋክብት አማካኝነት ከህዋሳት የራቁና የተሰወሩ ነገሮችን አውቃለሁ ብሎ መናገር እንደ ከፍተኛው ክህደት ሲታይ ፣


3- ከዋክብት ለጥሩም ይሁን ለመጥፎ ነገር ምክንያት /ሰበብ ናቸው ብሎ ማመን ደግሞ ከመለስተኛው ማጋራት ይቆጠራል።


ሁለተኛው ፦ክፍል የተፈቀደ ሲሆን እሱም በከዋክብት አማካኝነት አቅጣጫዎችንና የወራቶችን መለዋወጥ ማወቅ ነው ።


ከዋክብት ለምን ተፈጠሩ ??


ከዋክብት የተፈጠሩት ለሶስት ዓላማዎች ብቻ ነው እነሱም፦


1- ለሰማይ ውበትና ጌጥ፤


2- ለሰይጣናት መቀጥቀጫ እና


3- አቅጣጫዎችን ማወቂያ ነው ።


በከዋክብት ዝናብን መለመን፡-


በከዋክብት ዝናብን መለመን በሁለት ይከፈላል፡-


አንደኛው ፦ ከፍተኛ የማጋራት ወንጀል ሲሆን ይህም በሁለት መልኩ ይገለፃል፡-


1- ከዋክብትን ዝናብ ያዘንቡ ዘንድ በቀጥታ መለመን ለምሳሌ፦ እገሌ የተባልክ ኮከብ ሆይ! ዝናብ ስጠን፤ አዝንብልን ፤አጠጣንና የመሳሰሉትን ቃል በመጠቀም መለመንና፣


2- ከዋክብት በራሳቸው ጊዜ ዝናብን የማዝነብ ችሎታ አላቸው ብሎ ማመን ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፡-


70





“ በሲሳያችሁ(በዘነበላችሁ ዝናብ)አላህን ማመስገን ሲገባችሁ ታስተባብላላችሁን ? ” (አል-ዋቂዓ: 82)


ሙጃሂድ የተባሉ ዐሊም ይህችን አንቀፅ ሲያብራሩ እገሌ የተባለው ኮከብ አዘነበልን በማለት የአላህን ጸጋ የሚያስተባብሉ ሰዎችን የሚያወግዝ አንቀጽ ነው ብለዋል ።


የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን ? ሲሉ ሱሃቦችን ጠየቁ እነሱም አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ ሲሉ መለሱ። እርሳቸውም እርሱ (አላህ) እንዲህ አለ፡- ከባሮቼ ከፊሉ በእኔ አማኝ ሆኖ ሲያድር ከፊሉ ከሃዲ ሆነ። በአላህ ችሮታና እዝነት ዘነበልን ያለ በእኔ አማኝ ሲሆን በከዋክብት ከሃዲ ሆነ። እገሌ በተባለው ኮከብ ዘነበልን ያለ ደግሞ በእኔ ከሃዲ ሲሆን በከዋክብት አማኝ ሆነ ” አሉ ።


2- ዝናብ ለመዝነብ ከዋክብት ምክንያት ናቸው ብሎ ማመን መለስተኛ የማጋራት ኃጢአት ሲሆን ዝናብ የሚዘንብበትን ወቅትና ጊዜ በከዋክብት አማካኝነት ማወቅ ግን የተፈቀደ ነው።


ይስሙላ፡--


አንድን መልካም ስራ ሰዎች አይተው ወይም ሰምተው ያመሰግኑት ዘንድ ይፋ


ማድረግና አሳምሮ መስራት ይስሙላ ይባላል እሱም በሁለት ይከፈላል።


71


1ኛ- ለይስሙላ የሚሰራው አንዳንድ ጊዜና በተወሰኑ አምልኮዎች ብቻ ከሆነ መለስተኛው የማጋራት ወንጀል ሲሆን ፣


2ኛ- ተግባሩ በሙሉ ወይም አብዛኛው ለይዩልኝ (ለዩስሙላ) ከሆነ ግን ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ይሆናል። ይህም የሙናፊቅ ባህሪና ምልክት እንጂ የአማኝ ባህሪ አይደለም ።


የይስሙላ አደገኝነት፡-


1-ከማጋራት ወንጀሎች አንዱ መሆኑ፦ የአላህ መልእክተኛ //አል-ኢማሙ አህመድ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ በናንተ ላይ ከሚያሰጋኝ ነገር ሁሉ በእጅጉ የሚያሰጋኝ መለስተኛው የማጋራት ወንጀል ነው ” ብለዋል። እሱም ምን እንደሆነ ሲጠየቁ“ ለይስሙላ መስራት ነው ” አሉ።


2- ይስሙላ በተውበት(በንስሓ) እንጂ የማይማር ወንጀል መሆኑ፦ አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ አላህ በእርሱ የማጋራትን ወንጀል በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለን (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ”(አኒሳእ: 48)፡፡


72


ይህ የቁርዓን አንቀፅ የሚያስረዳው ማንኛውም የማጋራት ወንጀል ከፍተኛውም ሆነ መለስተኛው በተውበት/በንስሓ/እንጂ የማይማር መሆኑን ነው።


3- ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያለውን መልካም ስራ ማውደሙ፦


የአላህ መልእክተኛ // ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ አላህ እንዲህ ብሏል ሲሉ ተናግረዋል፡-





“ እኔ ከአጋር የተብቃቃሁ ነኝ። ስለዚህ አምልኮውን ከኔ ጋር ሌላን አካል በማጋራት የፈፀመ ሰው ከነሽርኩ እተወዋለሁ።”


4- የይስሙላ አደገኝነት ሐሰተኛ ከሆነው አልመሲህ አደጋ የከፋና የበለጠ መሆኑ ናቸው፦


የአላህ መልእክተኛ // አሊማሙ አህመድ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ከደጃል አደጋ ይበልጥ በናንተ ላይ የሚያሰጋኝን ነገር ልንገራችሁን?” አሉ እንዴታ ይንገሩን እንጂ ሲሏቸው፡- “ስውር የሆነው የማጋራት ወንጀል ነው እርሱም አንድ ሰው ሶላት በሚሰግድበት ወቅት ሰዎች ወደ እርሱ የሚመለከቱ መሆናቸውን ሲያውቅ ሶላቱን አሳምሮ መስገድ ነው” አሉ ።


ይስሙላ ከሥራ ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር በሶስት ይከፈላል፡-


73


1-መልካም ስራውን ለመስራት ያነሳሳው ይስሙላ ከሆነ ይህ አስተሳሰቡ(ኒያው) የማጋራት ወንጀል ሲሆን አምልኮውም ተቀባይነት አያገኝም።


2- ስራውን ለአላህ ብሎ ከጀመረው በኋላ የይስሙላ በሽታ ከተከሰተበት ይህ ጉዳይ በሁለት መልኩ ይታያል፡-


ሀ- ራሱን ከታገለና በይስሙላ ላይ ካልቀጠለ በስራው ላይ ምንም ዓይነት ችግር አያሳድርበትም።


ለ- በይስሙላው ደስተኛ ሆኖ በዚያው ላይ ከቀጠለ ደግሞ የሚያደርገውን አምልኮ በሁለት መልኩ ማየት ያሻል፡-


1- በመጨረሻ ያደረገው አምልኮ ከመጀመሪያው ጋር ተያያዥነት ካለው ለምሳሌ፦ ፍጹም ለአላህ አጥርቶ አንድ ረከዓ ከሰገደ በኋላ የሚቀጥለውን ሁለተኛ ረከዓ ለይስሙላ ከሰገደው ሁለቱም ረከዓዎች ይበላሻሉ ።


2- ለይስሙላ የፈፀመው የመጨረሻው መልካም ስራ ከመጀመሪያው ጋር ተያያዥነት ከሌለው ደግሞ ለምሳሌ ፦ፍጹም ለአላህ ብቻ አጥርቶ አንድ መቶ ብር ለሰደቃ ከሰጠ በኋላ ሰዎች ያመሰግኑት ዘንድ ሌላ አንድ መቶ ብርን ቢሰጥ የመጀመሪያው ሶደቃ ተቀባይነት ሲኖረው የሁለተኛው መቶ ብር ሶደቃ ግን ተቀባይነት አያገኝም።


3- የይስሙላ ስሜት የተሰማው መልካም ስራው ከተፈፀመ በኋላ ከሆነ በአምልኮው ላይ ምንም አይነት ችግር አያሳድርበትም ።


ማሳሰቢያ፡-


አንድ ሰው በሚሰራው መልካም ስራ ሰዎች ሲያሞግሱትና ሲያመሰግኑት መደሰቱ በሃይማኖቱ ላይ ምንም ዓይነት ችግር አያሳድርበትም። እንዲያውም ሙስሊም እንደዘገቡት ይህ በዚህች ዓለም ቀድሞ የመጣ የአማኙ ብስራት ነው ።


ማሳሰቢያ፡-


ሰዎች ያዩኛል ወይም ይሰሙኛል በሚል ስጋት መልካም ስራን (አምልኮን) መተውና ማቋረጥ መለስተኛ የማጋራት ወንጀል ይሆናል ።


74


- የይስሙላን በሽታ ሊከላከሉ የሚችሉ ወሳኝ ነጥቦች፡-


1- ፍፁምነት(ለአላህ ብቻ አጥረቶ መስራት) የሚያስገኘውን ደረጃ ማወቅና ማስታወስ፣


2- ለይስሙላ መስራት የሚያስከትለውን የአኺራ ኪሳራ መረዳትና ከልብ መገንዘብ፣


3- ሰዎች መጥቀምም ሆነ መጉዳት እንደማይችሉ ጠንቅቆ ማወቅና


4- በሚከተለው ዱዓ አላህን መማፀን ናቸው እሱም፡-


" اللهم إنِّ أعوذ بك من أن أشَك بك شيئاً أعلمه وأستغفرك لما لا أعلمه ".


“ አላህ ሆይ ! እያወቅኩ ባንተ ከማጋራት ባንተው እጠበቃለሁ በማላውቀው ደግሞ ምህረትህን እጠይቃለሁ።”


አንድ ሰው በሚሰራው መልካም ስራ/ የቅርቢቱን ህይወት መሻት፡-


ገንዘብ ለማግኘት ብቻ አስቦ ሐጅ ማድረግ፤ ለምርኮ ገንዘብ ብሎ መዝመት እና የመሳሰሉትን ንጹህ አምልኮዎች ለግዚያዊ ጥቅም ብቻ አስቦ መፈፀም በሁለት መልኩ ይታያል፡-


1- የሚፈፅመው አምልኮ በሙሉ ወይም አብዛኛው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም ለማግኘት ከሆነ ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ሲሆን ፣


2- ዓለማዊ ጥቅም ለማግኘት የሚያከናውነው አምልኮ የተወሰነ እና ጥቂት ከሆነ ደግሞ መለስተኛ የማጋራት ወንጀል ይሆናል። ለዚሁ ዓላማ ያደረገውም አምልኮ ተቀባይነት አያገኝም።


አንድ ሰው በሚሰራው የአምልኮ ተግባር የዓለማዊ ጥቅምን ብቻ ማሰብ እንደሌለበት የሚያስጠነቅቁ ብዙ ቁርኣናዊ አንቀፆችና ነቢያዊ ሐዲሶች አሉ፡-አላህ እንዲህ ይላል፡-


 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎ ...

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች።

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የ ...

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ...

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት