
8 - የጦሃራ መበላሸት (መፍረስ) .
አስራ ሁለተኛ ትምህርት: የዉዹእ ቅድመ
መስፈርቶች (ሸርጦች)
እነርሱም፡- አስር ናቸው።
ሙስሊም መሆን፣ የአይምሮ ጤናማ መሆን፣ ነገሮችን
መለየት የሚያስችል እድሜ ላይ መድረስ፣ ኒያ ማድረግ (በልብ
ማሰብ)፣ የዉዹእን ብይን ማጎዳኘት ይህም ዉዹእን
እስከሚያጠናቅቅ ድረስ ላለማቋረጥ መነየት (መወሰን)፣
ውዱዕ ማድረግን ግዴታ ከሚያደርጉ ነገሮች መራቅ፣ አስቀድሞ
በውሃ ኢስቲንጃ ማድረግ (ማጠብ) ወይም በደረቅና በሚፈቀዱ
ነገሮች ማደራረቅ፣ ውሃው ንፁህና የተፈቀደ መሆን አለበት፣
ውሃ ወደ ሰውነት ቆዳ እንዳይገባ የሚከለክሉ ነገሮችን
ማስወገድ፣ ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ውዱእ የማጥፋት ችግር
ላለበት ሰው ደሞ የሶላቱ ወቅት መግባቱ ናቸው።
አስራ ሶስተኛ ትምህርት: የዉዹእ ግዴታዎች
ስድስት ናቸው። እነርሱም፡-
ፊትን መታጠብ፣ ይህም ሲባል መጉመጥመጥና በአፍንጫ
ውሃን ስቦ መመለስን ያካትታል ፤ ሁለቱ እጆችን ከክርን ጋር
መታጠብ ፤ ራስን (የራስ ቅልን) ሙሉ በሙሉ በውሃ ማበስ፤
ይህም ሁለቱ ጆሮዎችን ማበስንም ያካትታል። ሁለቱ እግሮችን
ከቁርጭምጭሚት ጋር መታጠብ ፤ ቅደም ተከተልን መጠበቅ
20
፤ ለውዱእ የሚታጠቡ አካሎችን በመሀከላቸው የጊዜ ክፍተት
ሳይኖር አከታትሎ ማጠብ ናቸው። ፊትን፣ ሁለት እጆችንና
እግሮችን በሚያጥቡበት ጊዜ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ማጠብ
ይወደዳል። እንዲሁ በሚግሞጠሞጥበት እና በአፍንጫው ውሃ
በሚያስገባበት ጊዜ ሶስት ሶስት ቢያደርግ ይወደዳል። ። ይህን
ማድረግ ካልቻለ ግን ግዴታ የሚሆንበት አንድ ጊዜ ብቻ
ማድረጉ ነው። የራስ ቅልን ማበስ በተመለከተ ግን ትክክለኛ
ሀዲሶች እንደሚያመላክቱት ከአንድ በላይ መደጋገሙ
አይወደድም።
አስራ አራተኛ ትምህርት: ዉዹእን የሚያበላሹ
ነገሮች
ስድስት ናቸው። እነርሱም፡-
ከሁለቱ የቆሻሻ መውጫ ክፍሎች የወጣ ሁሉ፤ ከሰውነት
ነጃሳና የሚያስጠላ የሆነ ነገር መውጣቱ ፤ በእንቅልፍና በሌሎች
አእምሮን ሊያስቱ በሚችሉ ነገሮች አእምሮን መሳት ፤ ከፊት
ወይም ከኋላ ያለውን ሀፍረተ ገላ ያለምንም ግርዶሽ በቀጥታ
በእጅ መንካት ፤ የግመል ስጋ መብላት፤ እኛንም መላውንም
ሙስሊም አላህ ይጠብቀንና ‐ ከእስልምና መውጣት ናቸው።
አንገብጋቢ ማሳሰቢያ፦ ሬሳን ማጠብ (ውዱእ ያበላሻል
ወይስ አያበላሽም የሚለውን) አስመልክቶ ትክክለኛው
አስተያየት ዉዱእ አያበላሽም የሚለው ነው። ይህ አስተያየት
ደግሞ የአብዛኛዎቹ ሊቃውንት አቋም ነው። ምክንያቱም
ያበላሻል የሚለው ምንም ማስረጃ የለውምና። ነገር ግን
21
የሟቹን ሀፍረተ ገላ ያለምንም ግርዶሽ የነካ ሰው ዉዱኡ
ይበላሻልና ዉዱእ የማድረግ ግዴታ አለበት።
የሬሳውን ሀፍረተ ገላ ያለምንም ከለላ መንካትም
ይከለከላል። እንዲሁም ትክክለኛ በሆነው የዑለማዎች አቋም
መሰረት ሴትን በስሜትም ሆነ ያለ ስሜት መንካትም ከብልቱ
ፈሳሽ እስካልወጣ ድረስ ውዱእ አያበላሽም የሚለው ነው።
ምክንያቱም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሚስቶቻቸው
አንዷን ስመው ውዱእ ሳያደርጉ ሰግደዋልና።
በሱረቱ አን-ኒሳእ እና በሱረቱል ማኢዳህ ምዕራፍ ውስጥ
የተጠቀሰው ተከታዩን የአላህን ቃል በተመለከተ፦
በእነዚህ አንቀጾች ማስተላለፍ የተፈለገው መልዕክት
በትክክለኛው የዑለማዎች አቋም መሰረት የግብረ ስጋ
ግንኙነት ነው። ይህም አቋም የዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ -
ረዺየሏሁ ዐንሁማ - እና የብዙ ሰለፎች (ቀደምት
ዑለማዎች) እንዲሁም የመልካም ሰለፎች ምትክ
ዑለማዎች አቋማቸው ይህ ነው። ተውፊቅን
የሚሰጠው አላህ ነው(ና አላህ ይወፍቀን)።
22
አስራ አምስተኛ ትምህርት: ለሁሉም
ሙስሊም የተደነገጉ መልካም ስነምግባሮችን
መላበስ
ከእነዚህም ውስጥ፡- እውነተኛነት፣ ታማኝነት፣ ጥብቅነት፣
አይነአፋርነት (ሐያእ)፣ ጀግንነት፣ ለጋሽነት፣ በቃል መገኘት፣
አላህ ከከለከለው ነገር ሁሉ መራቅ፣ ጉርብትናን ማሳመር፣
በተቻለ አቅም ሁሉ የተቸገረን መርዳት እና ሌሎችም ቁርኣን
እና ሐዲሥ ውስጥ የተደነገጉ እና የተወሱ ስነምግባራት
ይገኙበታል።
አስራ ስድስተኛ ትምህርት: በኢስላማዊ
ስነስርአቶች መታነጽ
ከነርሱም መካከል: እስላማዊ ሰላምታን መለዋወጥ
(አሰላሙዐለይኩም ማለት እና ምላሹን መስጠት)፤ ለሰዎች
ጥሩ ፈገግታ ማሳየት፤ በቀኝ መብላትና መጠጣት፤ ሲጀምሩ
ቢስሚላህ ብሎ መጀመር ሲጨርሱ ደግሞ “አልሐምዱሊላህ”
ማለት፤ በምናስነጥስበት ጊዜም አልሓምዱሊላህ ማለት፤
አስነጥሶ “አልሀምዱሊላህ” ላለ ሰው “የርሐሙከላህ” ማለት፤
የታመመን መጠየቅ፤ የሙስሊም አስክሬን ላይ ለመስገድና
ለመቅበር ሲባል አስክሬኑን መከተል፤ መስጂድ ወይም ቤት
ሲገባ እና ሲወጣ፣ ጉዞ ላይ፣ ከወላጆች፣ ከዘመዶች፣ ከጐረቤቶች
በዕድሜ ከሚበልጡን ሰዎች ከታናናሾቻችን ጋር ኢስላማዊ
ስርዓቶችን መጠበቅ፤ እንዲሁም የወለደን እንኳን ደስ አለህ
ማለት፤ ላገባ ሰው በረካን መለመን (ባረከላሁ ለኩማ … ማለት)
23
፤ ችግር የደረሰበትን ሰው ማፅናናት፤ እንዲሁም ልብስ እና
ጫማ በምንለብስበትና በምናወልቅበት ጊዜ ኢስላማዊ
ስርዓቶችን መጠበቅ ይገባል።
አስራ ሰባተኛ ትምህርት: ከሺርክና ከወንጀል
አይነቶች ሁሉ ማስጠንቀቅ
ከእነርሱም መካከል: ሰባቱ አጥፊ ወንጀሎች ይገኙበታል።
እነርሱም፦ በአላህ ማጋራት፤ ድግምት፤ በሐቅና በፍትህ ካልሆነ
በቀር አላህ መግደል ክልክል ያደረገውን ነፍስ መግደል፤ ወለድ
ወይም አራጣ መብላት፤ የየቲምን ንብረት መብላት፤ በጂሀድ
ጦርነት ወቅት ከጠላት ፊት ለፊት ገጥሞ ጦርነቱ ከተፋፋመ
በኃላ መሸሽ፤ ከወንጀል የራቁ ጥብቅ ምዕመናትን በዝሙት
መወንጀል ናቸው።
ከእነርሱም መካከል፡- ወላጅን መበደል (መጨቆን)፤
ዝምድናን መቁረጥ፤ በውሸት መመስከርና መማል፤ ጐረቤትን
ማስቸገር፤ ሰዎችን በደማቸው፣ በንብረታቸውና በክብራቸው
ላይ በደል ማድረስ፤ አስካሪ መጠጥ መጠጣት፤ ቁማር
መጫወት፤ ሀሜት፤ ነገር ማሳበቅ እና ሌሎችም አላህ ዐዘ ወጀል
ወይም መልዕክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና
ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የከለከሉትን በሙሉ መራቅ
ናቸው።
24
አስራ ስምንተኛ ትምህርት: ሟችን ለቀብር
ማሰናዳት፣ በርሱ ላይ መስገድና መቅበር
ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፦
በቅድሚያ ጣዕረ ሞት ላይ የደረሰን ሰው
"ላኢላሃ ኢለሏህ" እንዲል ማስታወስ ነው፤
ጣዕረ ሞት ላይ የደረሰን ሰው “ላ ኢላሃ ኢለላህ” የሚለውን
አርፍተ ነገር ደጋግሞ ማስባል በሸሪዓችን ተደንግጓል።
ምክንያቱም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና
ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ፦
{ሙታኖቻችሁን ላኢላሃ ኢለላህ አስብሏቸው።}1.
ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል። በዚህ ሐዲሥ ውስጥ
"ሙታኖችን" በሚለው ቃል የተፈለገበት የሞት ምልክት
የታየባቸው በጣዕረ ሞት ላይ ያሉ ሰዎችን ለማለት ነው።
ሁለተኛ: መሞቱ በተረጋገጠ ጊዜ
መሞቱ በተረጋገጠ ጊዜ ሁለት ዓይኖቹ ይጨፈናሉ፤
መንጋጭሎቹም እንዲጋጠሙ ይደረጋሉ። ምክንያቱም ይህ
ተግባር በሱና ስለተረጋገጠ ነው።
1ሙስሊም በጀናኢዝ (916)፣ ቲርሚዚይ በጀናኢዝ (976)፣ ነሳኢይ በጀናኢዝ (1826)፣
አቡዳውድ በጀናኢዝ (3117)፣ ኢብኑማጀህ በጀናኢዝ (1445)፣ አሕመድ በ(3/3) ላይ
ዘግበውታል።
25
ሶስተኛ: ሬሳ ማጠብ
በጦር ሜዳ ፍልሚያ ላይ ሰማዕት (ሸሂድ) ከሆነ ሰው
በስተቀር የሙስሊምን ሬሳ ማጠብ ግዴታ ይሆናል። ሰማዕት
የሆነ ሰው አይታጠብም፤ ሰላትም አይሰገድበትም፤
የሚቀበረውም ከነልብሱ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ
ይስፈንና) የኡሑድ ዘመቻ ላይ የተገደሉትን ሰማዕታት
አላጠቡምም አልሰገዱባቸውምም።
አራተኛ: የሬሳ አስተጣጠቡ፡
ሀፍረተ ገላው ይሸፈንና ከእራሱ በኩል ትንሽ ቀና ተደርጎ
ሆዱን በቀስታ ጫን ይደረጋል። ቀጥሎ አጣቢው እጁን በጨርቅ
ወይም በመሰል ነገር ይጠቀልልና ኢስቲንጃእ ያስደርገዋል።
ቀጥሎ ለሶላት እንደሚያደርገው ዉዹእ ያደርገዋል። ቀጥሎ
ጭንቅላቱንና ፂሙን በውሃና በቁርቁራ ቅጠል ወይም በመሰል
ነገር ያጥበዋል። ቀጥሎ ቀኝ ጎኑን ከዚያም ግራ ጎኑን ያጥባል።
በዚህ መልኩ ለሁለተኛና ለሶስተኛ ጊዜ ያጥበዋል። በየሁሉም
ትጥበት እጁን በሆዱ ላይ ጫን እያደረገ ያሳልፋል። ከሆዱም
አንዳች ነገር ከወጣ ያጥበውና ቀዳዳውን በጥጥ ወይም በመሰል
ነገር ይዘጋዋል። ይህም ሳይገድበው ከቀረ በስሚንቶ ነገር ወይም
ፋሻና ፕላስተርን በመሰሉ የዘመናዊ ህክምና መሳሪያ
ያስቆመዋል።
ዉዹኡንም ድጋሚ ያደርገዋል። በሶስት ትጥበት ካልፀዳ እስከ
አምስት ወይም እስከ ሰባት ትጥበት ይጨምራል። ከዚያም
26
በልብስ ያደራርቀዋል። መተጣጠፊያ እና የሱጁድ አካላቶቹ ላይ
ሽቶ ያድርግለት። ሙሉ ሰውነቱን ሽቶ ከቀባውም ጥሩ ነው።
ከፈኑ ላይ ዕጣን ያጭስበት። ቀድሞ ቀመሱ ወይም ጥፍሩ
ከረዘሙ ይቁረጥለት። ሳይቆርጥ ቢተወውም ግን ችግር
የለውም። ምንም ማስረጃ ስላልመጣበት ፀጉሩ አይበጠርም፣
የብልት ፀጉሩም አይላጭም፣ አይገረዝምም። ሴት ልጅ ፀጉሯ
ለሶስት ተጎንጉኖ ወደ ኋላዋ ይለቀቃል።
አምስተኛ: ሟችን መከፈን
ወንድ ከሆነ ልክ ለነብያችን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
እንደተደረገው ቀሚስና ጥምጣም በሌላቸው ሶስት ነጫጭ
ጨርቆች መሆኑ በላጭ ነው። ተራ በተራ ይጠቀለልበታል።
በቀሚስ፣ በሽርጥና ብትን በሆነ ጨርቅ ቢጠቀለልም ችግር
የለውም።
ሴት ከሆነች ደግሞ በአምስት ጨርቆች ትጠቀለላለች፤
ማለትም በቀሚስ፣ በሻሽ፣ በአንድ ሽርጥና በሁለት ብትን
ጨርቆች ነው። ወንድ ህጻን ከሆነ ከአንድ እስከ ሦስት ባሉ ብትን
ጨርቆች ይጠቀለላል፤ ትንሽ ሴት ህጻን ከሆነች በቀሚስ እና
በሁለት ብትን ጨርቆች ትጠቀለላለች።
ወንድም ሆነ ሴት ሲገነዙ መላ ሰውነትን ሊሸፍን በሚችል
አንድ ብትን ጨርቅ መጠቅለላቸው ግዴታ ነው። ነገር ግን ሟች
ሙሕሪም ሆኖ የሐጅና የዑምራ ተግባራትን እያከናወነ ባለበት
ወቅት የሞተ ከሆነ በውሃና በቁርቁራ ይታጠብና እርሱ በነበረው
ሽርጥና ኩታ ወይም ከዛ ውጭ ባለ ጨርቅ ይከፈናል። ሆኖም
27
ግን ራሱንና ፊቱን አይሸፈንም፤ ሸቶም አይደረግለትም።
ምክንያቱም ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ
ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመጣው ትክክለኛ
ዘገባ የቂያማ ቀን ተልቢያ (ለብበይከ-ል-ላሁምመ ለበይክ ...)
እያለ ይቀሰቀሳልና። በሐጅ ስነስርአት ላይ የሞተችው ሴት
ከሆነች ደግሞ እንደሌሎች ሰዎች ትከፈናለች ነገር ግን ሽቶ
አትቀባም፤ ፊቷም ኒቃብ አይሸፈንም፤ እጇም ጓንት
አይለብስም፤ ነገር ግን የሚሸፈነው ከላይ ባሳለፍነው የሴት
አገናነዝ መሰረት ፊቷም እጇም በተመሳሳይ ከፈን ይሆናል።
ስድስተኛ: ማን ይከፍን
ሬሳውን ለማጠብ በእርሱ ላይም ሊሰግዱበትና ሊቀብሩት
ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰዎች
ሬሳውን ለማጠብ በእርሱ ላይ ለመስገድና እርሱንም
ለመቅበር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰዎች በመጀመርያ ሟቹ
የተናዘዘለት ሰው ነው። ከዚያም አባት፣ ከዚያም አያት፣ ከዚያም
ጠቅላይ ቅርብ ወራሽ (ወንድም፣ አጐት፣ የወንድም ልጅ)
ለሰውዬው እንዳላቸው ቅርበት መብት ይኖራቸዋል።
ሴትን በማጠብ ላይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ደግሞ፦
በመጀመርያ የተናዘዘችላት ሴት፤ ከዚያም እናቷ ከዚያም ሴት
አያቷ ከዚያም ሴት ዘመዶቿ እንደየቅርበታቸው ደረጃ ቅድሚያ
ይሰጣቸዋል። ባልና ሚስት አንዱ ሌላውን ሊያጥብ ይችላል።
ምክንያቱም አቡበከር ሲዲቅንም ባለቤታቸው ነች
28
ያጠበቻቸው፤ እንዲሁም ዐሊይም ባለቤታቸው ፋጢማን
አጥበዋልና።
ሰባተኛ: የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ
አራት ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፡ ከመጀመሪያ ተክቢራ በኋላ አል
ፋቲሓ (የመክፈቻው ምዕራፍን) ያነባል፤ ከዚህም በተጨማሪ
አጠር ያለ የቁርአን ምዕራፍ ወይም አንድ ወይም ሁለት አንቀፅ
ቢቀራም ጥሩ ነው። ይህንን የተመለከተ ከዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ
የተዘገበ ትክክለኛ ሐዲሥ ስላለ ነው። ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ
ተክቢራ ያደርጋል፤ ተሸሁድ ላይ ባለው መልኩ በነብዩ ሶለሏሁ
ዓለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት ያወርዳል። ከዚያም ሦስተኛውን
ተክቢራ ካደረገ በኃላ እንዲህ ይላል፦
{"አልላሁምመ‐ጝፊር ሊሐዪና ወመዪቲና ወሻሂዲና
ወጛኢቢና ወሶጚሪና ወከቢሪና ወዘከሪና ወኡንሣና፤
አልላሁምመ መን አሕየይተሁ ሚንና ፈአሕዪሂ ዐለል ኢስላም
29
ወመን ተወፈይተሁ ሚንና ፈተወፈሁ ዐለል ኢማን፤
አልላሁምመ‐ጝፊር ለሁ ወርሓምሁ ወዓፊሂ ወዕፉ ዓንሁ
ወአክሪም ኑዙለሁ ወወሲዕ ሙድኸለሁ ወጝሲልሁ ቢልማኢ
ወሠልጂ ወልበረዲ ወነቂሂ ሚነልኸጣያ ከማ ዩነቀ አሥ
ሠውቡል አብየዹ ሚነ‐ድደነሲ፤ ወአብዲልሁ ዳረን ኸይረን ሚን
ዳሪህ ወአህለን ኸይረን ሚን አህሊህ ወአድኺሉሁል‐ጀነተ
ወአዒዝሁ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወዓዛቢ ናር ወፍሰሕ ለሁ ፊ
ቀብሪሂ ወነዊር ለሁ ፊህ አልላሁምመ ላተሕሪምና አጅረሁ
ወላቱዲለና በዕደሁ።"}.
{ትርጉሙም፡ አላህ ሆይ! በህይወት ያለነውንም፣ የሞቱብንም፣
በቅርብ ያለነውንም ሩቅ ያሉትንም፣ ትልልቆቻችንንም፣
ትንንሾቻችንንም፣ ወንዶቻችንንም፣ ሴቶቻችንንም ማርልን።
አላህ ሆይ! ከመካከላችን የምታኖረውንም ኑሮውን በኢስላም
አድርግለት፤ የምትገለውንም በእምነት ላይ እንዲሞት አድርገው።
አላህ ሆይ! (ለሟቹ) ምህረት አድርግለት፤ እዘንለትም፤ (ከእሳት)
ጠብቀው፤ ይቅርም በለውም፤ መስተንግዶውንም አሳምርለት፤
መግቢያውንም አስፋለት፤ ሀጢአቱንም በውሃ፤ በበረዶና
በቀዝቃዛ ውሃ እጠብለት፤ ነጭ ልብስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው
የእርሱንም ወንጀል አፅዳለት፤ ከቤቱ የተሻለ ቤት ከቤተሰቡ
የተሻለ ቤተሰብን ተካለት። ወደ ጀነት አስገባው፣ ከቀብር
ቅጣትና ከእሳት ቅጣትም ጠብቀው፤ ቀብሩንም አስፋለት
አብራለትም። አላህ ሆይ! ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱም በኋላ
እጣችንን ጥመት አታድርግብን።}.
30
ከዚያም አራተኛውን ተክቢራ ካደረገ በኋላ በቀኝ በኩል ብቻ
“አስሰላሙ ዐለይኩም” በማለት ያጠናቅቃል።
ከየሁሉም ተክቢራ ጋር ሁለት እጆቹን ከፍ ማድረጉ
ይወደድለታል። ሟቿ ሴት ከሆነች "አላሁመ‐ጝፊር ለሃ…"
(አላህ ሆይ ለርሷ ማራት..) ይባላል። ሬሳዎቹ ሁለት ከሆኑ ደግሞ
"አላሁመ‐ጝፊር ለሁማ… " (አላህ ሆይ ለነርሱ ማራቸው ...)
ይባላል። ከዚህም የበዙ ከሆነ ደግሞ "አላሁመ‐ጝፊር ለሁም…
" (አላህ ሆይ ለነርሱ ማራቸው ...) ይባላል። ሟቹ ህፃን ልጅ ከሆነ
ለርሱ ዱዓ ከማድረግ ይልቅ እንዲህ ይባላል: "አልላሁምመ
ኢጅዐልሁ ፈረጠን ወዙኽረን ሊዋሊደይሂ ወሸፊዓን ሙጃበን
አልላሁምመ ሠቂል ቢሂ መዋዚነሁማ ወአዕዚም ቢሂ
ኡጁረሁማ ወአልሒቁሁ ቢሷሊሒ ሰለፊል ሙእሚኒን
ወጅዐልሁ ፊ ከፋለቲ ኢብራሂመ ዐለይሂ አስሰላቱ ወስሰላም፤
ወቂሂ ቢራሕመቲከ ዓዛበል ጀሒም።" (ትርጉሙም፦ “አላህ
ሆይ (አኼራ ላይ) ቀድሞ ሄዶ ለወላጆቹ የሚያመቻች፤ ለችግር
ቀን አለኝታቸው፤ ተሰሚነት ያለው አማላጅ አድርግላቸው።
አላህ ሆይ! የመልካም ስራቸው ሚዛን ማክበጃና የምንዳቸው
ማጎልበቻ አድርግላቸው። ከደጋግ ምእመናን ጋርም አስጠጋው፤
ከነብዩ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም እንክብካቤ ስርም አድርገው፤
በችሮታህም ከጀሐነም እሳት ጠብቀው።) .
ኢማሙ ሲያሰግድ ሟች ወንድ ከሆነ በጭንቅላቱ በኩል ሴት
ከሆነች ደሞ በወገቧ ትይዩ መቆሙ ሱና ነው። ጀናዛዎች የበዙ
ጊዜ ደግሞ ወንዱ ሬሳ በኢማሙ በኩል ሲሆን ሴቷ ሬሳ ደግሞ
በቂብላው በኩል ትሆናለች። ከሬሳዎቹ መካከል ህፃን ካለ ደግሞ
31
የህፃኑ ልጅ ሬሳ ከሴት ሬሳ (በሰውዬውና በሴትዮዋ መካከል)
ይቀደማል። ከዚያም የሴቷ ሬሳ ትቀጥላለች ከዚያም የሴት ህፃን
ሬሳ ትቀጥላለች። የወንድ ህፃን ሬሳ ጭንቅላቱም በትልቁ ወንድ
ሬሳ ጭንቅላት ትይዩ ይደረጋል። የሴቷ ሬሳ ወገብም በወንዱ ሬሳ
ጭንቅላት ትይዩ ይደረጋል።የሴቷ ህፃን ሬሳም በትልቋ ሴት ሬሳ
ትይዩ ይደረጋል። የህፃኗም ወገብ በወንዱ ጭንቅላት ትይዩ
ይደረጋል። ሰጋጆች ባጠቃላይ ከኢማሙ ኋላ ይሆናሉ። ነገር ግን
ከኢማሙ ኋላ ቦታ ያላገኘ ሰው ከኢማሙ በቀኝ በኩል
ይቆማል።
ስምንተኛ: የአስክሬን አቀባበር
በሸሪዓ የተደነገገው ቀብሩ ሲቆፈር የአንድ ሰው ግማሽ አካል
ቁመት ያህል ወደታች ስምጥ ተደርጐ መቆፈር፤ መቃብሩ
ውስጥም በቂብላ አቅጣጫ ገባ ብሎ የሚቆፈር ("ለሕድ")
ማድረግ፤ ጀናዛውን (አስክሬኑን) ለሕድ ውስጥ በምናስገባበት
ጊዜ በቀኝ ጐኑ አስተኝቶ የከፈኑን ቋጠሮ መፍታት፤ ከፈኑን
ማውለቅ አይፈቀድም ይልቁንም በዛው ይተዋል። ሬሳው
ወንድም ሆነ ሴት ፊቱ አይገለፅም፤ ከዚያም በጀርባው በኩል
ብሎኬት ይደረደርና በጭቃ ተመርጎ አፈሩ እንዳይደረመስበት
ይደረጋል። ብሎኬት ማግኘት ካልተቻለ የአፈር መደርመስን
የሚከላከልለት ከርሱ ውጪ ባሉ እንደጣውላ ወይም ድንጋይ
ወይም እንጨት ይደረግበታል። ከዚያም በላዩ ላይ አፈሩ
ይመለስበታል። በዚህ ጊዜም.
{ቢስሚላህ ወዓላ ሚለቲ ረሱሊላህ} ይባላል። ትርጉሙም
(በአላህ ስም በአላህ መልክተኛ መንገድ ላይ) ማለት ነው።
ቀብሩ የስንዝር ያህል ከፍ ይደረጋል። ከተቻለ ቀብሩ ላይ
ጠጠሮች ይደረግበትና ውሃ ማርከፍከፍ።
ለሸኚዎች መቃብሩ ዘንድ ቆመው ለሟቹ ዱዓ ማድረጋቸው
በሸሪዓ የተደነገገ ነው። ይህም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
(የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሟችን ከቀበሩ
በኋላ እርሱ ዘንድ ቆመው እንዲህ ይሉ ስለነበር ነው:-
{ለወንድማችሁ ምህረትን ጠይቁለት! እርሱ አሁን
ይጠየቃልና ፅናትን ለምኑለት።}1.
ዘጠነኛ: ያልሰገደበት ካለስ?
ያልሰገደበት ሰው ካለ ከተቀበረም በኋላ በርሱ ላይ መስገዱ
በሸሪዓ የተደነገገ ነው። ይህም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
(የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለተገበሩት
ነው። ይህ ግን ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ መሆን አለበት። ጊዜው
ከወር በላይ ከሆነ ቀብሩ ላይ መስገድ አይፈቀድም።
ምክንያቱም ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና
ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሟች ከተቀበረ ከወር በኋላ
ለሟች መስገዳቸው አልመጣምና።
1አቡዳውድ በጀናኢዝ (3221) ውስጥ ዘግበውታል።
33
አስረኛ፡ ታዕዚያ
የሟች ቤተሰቦች ሊያፅናኗቸው ለመጡ ሰዎች ምግብ
ማዘጋጀት አይፈቀድላቸውም። ይህም ታላቁ ሶሐባ ጀሪር ቢን
ዐብደላህ አልበጀሊይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም
ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ስላሉ ነው:-
(ከቀብር በኋላ ሟች ቤተሰብ ዘንድ መሰብሰብና ምግብ
ማዘገጀትን ሙሾ እንደማውረድ አድርገን እንቆጥረው
ነበር።).
ኢማሙ አሕመድ በጥሩ ሰነድ ዘግበውታል። ነገር ግን ሌላ
ሰው ለሟች ቤተሰቦች ወይም ለእንግዶቻቸው ምግብ
ማዘጋጀቱ ችግር የለውም። የሟች ቅርብ ዘመዶችና ጎረቤቶች
ለሟች ቤተሰቦች ምግብ ማዘጋጀታቸው በሸሪዓ የተደነገገ ነው።
ይህም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም
በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀዕፈር ቢን አቢጧሊብ ረዺየሏሁ
ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሻም ላይ
እንደሞቱ ዜናው የደረሳቸው ጊዜ ቤተሰባቸው ለጀዕፈር
ቤተሰቦች ምግብ እንዲያዘጋጁ እንዲህ ብለው አዘዋል:-
{እነርሱ ምግብ ከማዘጋጀት ጊዜያቸውን የሚያጣብብ
ነገር አጋጥሟቸዋል።}1.
የሟች ቤተሰቦች ከሌሎች የመጣላቸውን ምግብ
ጎረቤታቸውን ወይም ሌላን ሰው ጠርተው ማብላታቸው ችግር
1ቲርሚዚ በጀናኢዝ (998)፣ አቡዳውድ በጀናኢዝ (3132)፣ ኢብኑ ማጃህ በጀናኢዝ (1610)
ውስጥ ዘግበውታል።
34
የለውም። ለዚህም እስከምናውቀው ድረስ በሸሪዓ
የተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የለውም።
አስራ አንደኛ: ሴት ልጅ
ባሏ ከሞተ ወይም እርጉዝ የሆነች ጊዜ ካልሆነ በቀር ለሟች
ከሶስት ቀን በላይ ለቅሶ መቀመጥ አይፈቀድላትም። ሴት ልጅ
ከባሏ ውጪ ለሟች ከሶስት ቀን በላይ ለቅሶ መቀመጥ
አይፈቀድላትም። በባሏ ለቅሶ ላይ ግን አራት ወር ከአስር ቀን
የመቀመጥ ግዴታ አለባት። እርጉዝ ከሆነች ግን ፅንሷን
በመውለዷ የለቅሶ ጊዜዋ ይጠናቀቃል። ይህም ሶሒሕ ሐዲሥ
ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም
በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለተዘገበ ነው። ወንዶች ግን ለቅርብ
ዘመድም ይሁን ለሌላ አካል ሞት ብለው ለቅሶ መቀመጥ
አይፈቀድላቸውም።
አስራ ሁለተኛ: ወንዶች
በፈለጉበት ወቅት መቃብር መዘየር፣ ለነርሱ ዱዓእ ማድረግ፣
ለነርሱ እዝነትን መለመንና ቀብርን በመዘየር ሞትንና ከሞት
በኋላ ያለውን ህይወት ማስታወስ በሸሪዓ ተደንግጎላቸዋል።
ይህም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም
በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ ነው:
{ቃብርን ዘይሩ! እርሷ መጪውን አለም
ታስታውሳችኋለችና። }1.
1ሙስሊም በጀናኢዝ (976)፣ ነሳኢይ በጀናኢዝ (2034)፣ አቡዳውድ በጀናኢዝ (3234)፣
ኢብኑ ማጀህ በጀናኢዝ (1569)፣ አሕመድ በ(2/441) ዘግበውታል።
35
ኢማም ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል። ነቢዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ
ይስፈንና) ሶሐቦቻቸው ቀብርን በዘየሩ ወቅት እንዲህ እንዲሉ
ያስተምሯቸው ነበር:-
{አሰላሙ ዐለይኩም ያ አህለ ዲያር ሚነል ሙእሚኒነ
ወልሙስሊሚን ወኢና ኢንሻአላሁ ቢኩም ላሒቁን ነስአሉላሀ
ለኩም ወለና አል ዓፊያ የርሐሙላሁ አልሙተቀዲሚነ ሚና
ወልሙስተእኺሪን} .
{ትርጉሙም፦ በዚህ መቃብር ውሰጥ የምትገኙ
ሙእሚኖችና ሙስሊሞች ሆይ ሰላም ይስፈንባችሁ!
እኛም በአላህ ፈቃድ እንከተላችኋለን፤ ለእኛም
ለእናንተም ከአላህ ዘንድ ደህንነትን እንጠይቃለን፤
ከመካከላችን ለተቀደሙትም ወደ ኋላ ለቀሩትም አላህ
ምህረትን ይለግሳቸው።}1.
ሴቶች ግን ቀብርን ሊዘይሩ አይፈቀድላቸውም። ምክንያቱም
የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና
ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብርን የሚጐበኙ ሴቶችን
ረግመዋልና፤ የዚህም ሰበብ ቀብር በሚጐበኙበት ጊዜ ፈተናና
ትግስት ማጣት ስለሚፈራላቸው ነው። እንደዚሁም እስከ ቀብር
1ሙስሊም በጀናኢዝ (975)፣ ነሳኢይ በጀናኢዝ (2040)፣ ኢብኑ ማጀህ በጀናኢዝ (1547)፣
አሕመድ በ(5/353) ዘግበውታል።
36
ድረስ ሬሳን መሸኘትም አይፈቀድላቸውም። ይህም የአላህ
መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም
በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ተግባር ስለከለከሉ ነው።
መስጂድ ውስጥ ወይም በሚሰገድበት ቦታ ተገኝቶ ሟች ላየ
መስገድ ግን ለወንድም ሆነ ለሴት የተፈቀደ ነው።
ይህ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለማካተት ለተሞከረው
ማጠናቀቂያ ነው። የአላህ ውዳሴና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ
በቤተሰባቸው እና በባልደረቦቹም ላይ ሁሉ ይስፈን።