የአዘጋጁ መቅድም
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
የዓለማት ፈጣሪ ለሆነው አላህ ምስጋና ይገባው የአላህ እዝነትና ሰላም የነቢያት መደምደሚያ በሆኑት በታላቁ መልእክተኛ በሙሐመድ እና በተከታዮቻቸው ላይ ይስፈን።
በመቀጠልም:- አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ፍጹም ለእርሱ ብቻ የተሰራን መልካም ስራ እንጂ አይቀበልም በመሆኑም፦
ይህ መጽሐፍ የተውሂድን ምንነትና ወሳኝነት እንደዚሁም የሽርክን(በአላህ የማጋራትን) አደገኝነትና ዓይነቶቹን በሚገባ የሚያብራራ እና የተውሂድን መሰረታዊ ነጥቦች በቀላሉ ለአንባቢያን የሚያስጨብጥ እጥር ምጥን ያለ ወሳኝ መጽሐፍ ነው።
በዚህም መጽሐፍ ተጠቃሚዎች ያደርገን ዘንድ አላህን እለምናለሁ
አዘጋጅ/ አብዱሏህ አል--ሁይል
የተርጓሚው ማስታወሻ:-
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፦
4
ሰዎች ስለ ፈጣሪያቸው ማወቅና እርሱን ብቻ መገዛት ከምግብና ከመጠጥ እንደዚሁም ከሌሎች እውቀቶች ሁሉ ይበልጥ ለእነርሱ ወሳኝና አንገብጋቢ ጉዳይ ነው በዚህም መሰረት ይህ መጽሐፍ ከአርብኛ ወደ አማርኛ ቋንቋ ቢተረጎም አረበኛውን የማይረዱ ወንድሞች የተፈጠሩለትን አላማ ከትርጉሙ መረዳት እንደሚችሉ ተስፋ በማድረግ በአላህ ፍቃድ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተርጉሜ ለወገኖቼ ሳቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ይሁን እንጂ ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይቀርምና በትርጉሙ ዙሪያ የሚገኙ ስህተቶችንና አስተያየቶቻችሁን በ(abuabdelah787@gmail.com )ወይም በ 0503655174 ሞባይል አድራሻችን ስታደርሱልን በታላቅ ክብርና ደስታ እንቀበላለን
ተርጓሚ/አብዱረሂም ሙሳ ሐሰን
-
-ትርጉም፡ የተውሂድ
5
ተውሂድ ማለት በቋንቋ አንድን ነገር ብቸኛ ማድረግና መነጠል ሲሆን ሃይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ አላህን በሶስቱ የተውሂድ አይነቶች ማለትም፡- በጌትነቱ፤ በአምላክነቱ ፤ በስሞቹና በባህሪያቱ አጋርና አምሳያ የሌለው ብቸኛ አምላክ መሆኑን ማመን ማለት ነው።
የተውሂድ ዓይነቶች፦
ተውሂድ በሦስት ይከፈላል እነሱም፦
1ኛ- ተውሂዱል - ሩቡቢያ እሱም፦ አላህ ሰማያትንና ምድርን፤ ሰዎችንና ጅኖችን፤ እንደዚሁም ማንኛውንም ፍጥረታት ሲፈጥርና ሲያስገኝ አማካሪና ተባባሪ ሳይኖረው ሳያስፈልገውም በብቸኝነት የፈጠረና ያስገኘ መሆኑን ማወቅና ማመን ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ አስተውሉ! የመፍጠርና የማዘዝ ስልጣን የእርሱ(የአላህ) ብቻ ነው። የዓለማት ፈጣሪ የሆነው አላህ ክብሩ የላቀ ነው ” (አል-አዕራፍ፡54)
አላህ በሌላ አንቀፅ ላይም እንዲህ ይላል፡-
“ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው ” (አልማኢዳ፡17)
2ኛ- ተውሂዱል- ኡሉሂያ እሱም አላህ በአምላክነቱ ብቸኛ መሆኑን ማወቅና ማመን ነው። ይህም ሊረጋገጥ የሚችለው አማኞች የሚሰሯቸውን መልካም ስራዎች ለምሳሌ፦ ሶላትን፤ ፆምን፤ ሐጅን፤ ፀሎትን፤ ስለትን፤ ውዴታንና
6
የመሳሰሉትን መልካም ስራዎች ሲያከናውኑ ፍጹም ለአላህ ብቻ አድርገው ሲሠሩ ብቻ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ አላህንም ተገዙ በእርሱም ምንንም አታጋሩ ” (አል-ኒሳእ፡ 36)
አላህ በሌላ አንቀፅ ላይም እንዲህ ይላል፡-
“ ከአንተ በፊት ማንኛውንም መልእክተኛ አላክንም እነሆ ከእኔ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም። ስለዚህ እኔን ብቻ ተገዙ የሚል መለኮታዊ ራዕይ ወደ እርሱ ያወረድን ቢሆን እንጂ ” (አል-አንቢያእ፡25)
3ኛ- ተውሂዱል- አስማኢ ወሲፋት እሱም አላህ በስሞቹና በባህሪያቱ ብቸኛ መሆኑን ማወቅና ማመን ማለት ነው። ይህም የሚረጋገጠው አላህ እርሱ ለራሱ ያፀደቃቸውን ስሞቹንና መልካም መገለጫ ባህሪያቱን እንደዚሁም በመልእክተኛው አማካኝነት የፀደቁትን ስሞቹንና ባህሪያቱን በፍጡራን ስሞችና ባህሪያት ሳናመሳስል ወይም ትርጉሙን ሳናዛባ ወይም ትርጉም አልባ ሳናደርግ በቀጥታ ቃሉ በሚሰጠው ትርጉም መሰረት ስናምን ብቻ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ እርሱን (አላህን) የሚመስል አንድም የለም እርሱም ሰሚና ተመልካች ነው ”(አሹራ፡11)
አላህ በሌላ አንቀፅ ላይም እንዲህ ይላል፡-
“ አላህም መልካም ስሞች አሉት። በነዚያም መልካም ስሞቹ ለምኑት። እነዚያንም ስሞቹን የሚያጋድሉና የሚያጣሙ ሰዎችን ተዋቸው ይሰሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ ”(አል-አዕራፍ፡ 180)
ወሳኝና ጠቃሚ ነጥቦች፡-
1- እነዚህ ሦስት የተውሂድ ክፍሎች ከፍተኛ ትስስርና ተዛምዶ ያላቸው በመሆኑ በአንዱ አምኖ በሌላው መካድ በሁሉም እንደመካድ ይቆጠራል።
2- በአላህ መልዕእክተኛ // ወቅት የነበሩት ከሃዲያን የሁሉ ነገር ፈጣሪ ፤ ሲሳይን ሰጪ ፤ ሕይወት የሚሰጠውና የሚነሳው አላህ ብቻ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁና ያምኑ ነበር። ይሁን እንጂ ከአላህ ውጭ የሆነን አካል ያመልኩ ስለነበር ይህ እምነታቸው ሙስሊሞች ሊያሰኛቸው አልቻለም።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ከደመና ባወረደው ዝናብ አዝርእቶችን ከምድር በማብቀል ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? መስሚያዎችንና መመልከቻዎችን የፈጠረላችሁስ ማነው?፤ ሕይወት ያለውን ሕይወት ከሌለው የሚያወጣና ሕይወት የሌለውንም ሕይወት ካለው የሚያወጣስ ማነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብረውስ ማነው? በላቸው በእርግጥም አላህ ነው ይላሉ። (ታዲያ
8
ይህን ሁሉ ማድረግ የሚችለው አላህ ብቻ መሆኑን እያወቃችሁ ሌላን አካል በእርሱ እንዴት ታጋራላችሁ? ) አላህን አትፈሩምን? በላቸው ” (ዩኑስ፣ 31)
3-የመልእክተኞች የመጀመሪያ ጥሪ ተውሂዱል ኡሉሂያ(አላህን ብቻ ተገዙ) የሚለው ቁም ነገር ነው። ምክንያቱም ማንኛውም አምልኮ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ተውሂዱል ኡሉሂያ ዋና መሰረት ስለሆነና እሱ ካልተረጋገጠ ተቃራኒው/ ሺርክ/ መኖሩ አይቀሬ ስለሆነ ነው።
4- በመልእክተኞችና በወገኖቻቸው መካከል አለመግባባትና ጭቅጭቅ የተፈጠረውም በዚሁ የተውሂድ ክፍል ነበር። ስለዚህ ይህን የተውሂድ ክፍል ማወቅና በሚገባ መረዳት የማንኛውም ሰው ግዴታ ነው ።
የተውሂድ ወሳኝነትና ደረጃው፡--
1- ተውሂድ ከእስልምና መሰረቶች የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዝ ዋና መሰረት ነው። በመሆኑም አንድ ሰው ወደ እስልምና ሃይማኖት መግባት የሚችለው፡-
ላኢላሀ ኢለላህ ወይም ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን ሲመሰክርና አላህን ብቻ መገዛት እንዳለበት አምኖ ሲቀበል ነው ።
የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-
“ ኢስላም በአምስት ነጥቦች ላይ ተመሰረተ፡- ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፤ ሶላትን መስገድ፤ ዘካን መክፈል፤ የተከበረውን የአላህን ቤት ሓጅ (ጉብኝት) ማድረግና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው ”ብለዋል።
2- ተውሂድ ከማንኛውም አምልኮ በፊት መታወቅ ያለበትና ወደ እርሱ ጥሪ ሊደረግለት የሚገባው ወሳኝ ነጥብ ነው ።
9
የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ሙዓዝ የተባለውን ሱሃቢ "የመን" ወደ ተባለ አገር ላስተማሪነት ሲልኩት፦
“ መጽሐፍ የተሰጣቸውን ሰዎች ታገኛለህ ስለዚህ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት ጌታ አለመኖሩንና እኔ የአላህ መልእክተኛ መሆኔን አስተምራቸው ” አሉት።
3- አንድ አምልኮ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ተውሂድ ዋና መስፈርትና መሰረት ነው ለምሳሌ፦ ሶላት ያለ ውዱእ ተቀባይነት እንደማያገኝ ሁሉ ማንኛውም አምልኮ ያለ ተውሂድ ተቀባይነት አያገኝም።
4- ተውሂድ በዚችም ሆነ በመጪዋ ዓለም የተቃና እድልና ሰላም ለማግኘት ዋና ምክንያት ነው።
አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-
“ እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ወይም በሽርክ ያልቀላቀሉና ያልበከሉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ሰላምን(መረጋጋትን) ያገኛሉ ። እነሱም ለጥሩ እድል ሁሉ የበቁ ናቸው ” (አል-አንዓም፡82)
እዚህ አንቀፅ ላይ ዙልም ወይም በደል በማለት የተፈለገው በሐዲስ እንደተብራራ ሁሉ ሺርክ ማለት ነው ። ኢብኑ ከሲር የተባሉት ታላቅ አሊም ይህችን አንቀፅ ሲያብራሩ ፦
“ እነዚያ በአላህ ምንንም ሳያጋሩ አምልኮትን ለእርሱ ብቻ ያደረጉ የቂያማ ቀን ሰላምን ያገኛሉ። በቅረቢቱ ሕይወትና በመጪዋም ዓለም እድለኞች ናቸው” ብለዋል።
10
ስለዚህ የተሟላ ተውሂድ ለተሟላ ሰላምና እድል ያበቃል ። ብሎም ያለምንም ቅጣት ጀነትን ለመግባት ያስችላል።
5- በአላህ ማጋራት የመጨረሻ አድሎና በደል ሲሆን አላህን ብቻ መገዛት ደግሞ የመጨረሻ ፍትህ ነው ።
6- ተውሂድ ከእሳት ለመዳንንና ጀነት ለመግባት ዋና ምክንያት ነው። ነብዩ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-
“ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ እና አገልጋይ መሆናቸውን የመሰከረ፤ እንደዚሁም ኢሳ(ኢየሱስ) የአላህ መልእክተኛና አገልጋይ መሆኑንና አላህ ወደ መርየም ያስተላለፋት በሆነች ቃል የፈጠረውና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች አንዱ መሆኑን የመሰከረ ፤ ጀነትና እሳትም እውነት መሆናቸውን ያመነና የመሰከረ ሰው ባለው ስራ አላህ ጀነት እንዲገባ ያደርገዋል” ብለዋል።
የአላህ መልእክተኛ// ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሳቸውም፡-
“ የአላህን ፊት ፈልጎ (በፍጹምነት) ላኢላሀ ኢለላህ ወይም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም ያለ ሰው አላህ ከእሳት እርም ያደርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
7- ተውሂድ በዚህችም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ሊያጋጥም ከሚችል አደጋና መከራ ለመዳን ዋና ምክንያት ነው።
8- ተውሂድ ለአላህ ጠላቶችም ሆነ ለወዳጆቹ ዋና መሸሻና መጠጊያ ነው።
11
- ጠላቶቹ ከዚህች ዓለም ጭንቀትና መከራ እንደሚድኑበት አላህ እንዲህ ሲል ይናገራል፡
“በመርከቧም ላይ በተሳፈሩ ጊዜ ፀሎትን ለእርሱ(ለአላህ) ብቻ አድርገው ይለምኑታል። ወደ የብስ በማውጣት ሲያድናቸውም ወዲያውኑ እነርሱ ያጋራሉ”(አል-ዐንከቡት፡65)
- ወዳጆቹ ደግሞ በተውሂዳቸውና በእምነታቸው ምክኒያት በዚህችም ሆነ በመጪዋ ዓለም ሊያጋጥሟቸው ከሚችሉ ችግሮችና ጭንቀቶች ይድኑበታል ።
ለዚህ ነው የአሣው ባለቤት ነቢዩላህ ዩኑስ/ዐለይሂ አሰላሙ/ካጋጠማቸው ጭንቀትና መከራ ለመውጣት አላህን የተማፀኑትና የለመኑት የተውሂድን ቃል በማንሳት የነበረው ።
- ሽርክ ለተለያዩ አደጋዎችና ችግሮች ያጋልጣል። ተውሂድ ከተለያዩ ችግሮች ለመዳን ይረዳል ።
በጠቅላላ ተውሂድ የፉጡራን መሸሻና አስተማማኝ ምሽግ ነው።
9 -ተውሂድ ሰዎችና ጅኖች የተፈጠሩበት ዋና አላማና ግብ ነው።
አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል
“ አጋንንትንና ሰዎችንም እኔን ብቻ ሊገዙ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም ” (አዛሪያት፡56)
ሰዎች የተፈጠሩት፤ መልዕክተኞች የተላኩት ፤ መጻሕፍት የወረዱት፤ ህግጋት የተደነገጉት አላህ ብቸኛና ፍፁም አምላክ መሆኑ ታውቆ እሱ ብቻ ይመለክ ዘንድ ነው ።
12
ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው የምስክርነ ቃል ማስረጃና ትርጉም፣
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ በፍትህና በማስተካከል ቋሚ የሆነው አላህ እነሆ ከእርሱ ሌላ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ መሰከረ። መላእክትና የእውቀት ባለቤቶችም መሰከሩ። አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ሌላ በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም ” (አሊ-ዒምራን፡18)
አላህ በሌላ አንቀጽ ላይ እንዲህ ይላል፡-
“እነሆ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን እወቅ(ተረዳ) ”(ሙሐመድ፡19)
የላኢላሀ ኢለላህ ትክክለኛ ትርጉም፡-
ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም የሚለው ትክክለኛ
የላ-ኢላሀ ኢለላህ ትርጉም ሲሆን የሚከተሉት ትርጉሞች ግን ትክክለኛውን ትርጉም አይወክሉም ፦
1ኛ-ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም የሚለው ትርጉም ሲሆን ይህ ትርጉም በእውነትም ሆነ በሀሰት የሚመለክ ነገር ሁሉ አላህ ነው ማለትን ስለሚያስረዳ ትክክለኛ የላኢላሀ ኢለላህ ትርጉም አይደለም።
2ኛ- ከአላህ በስተቀር ፈጣሪ የለም የሚለው ትርጉም ደግሞ ከትርጉሞቹ አንዱ ቢሆንም እንኳን የተፈለገው እሱ አይደለም ምክንያቱም ትርጉሙ ይህ ቢሆን ኖሮ በመልእክተኛውና በአጋሪዎች መካከል ጭቅጭቅና አለመግባባት
13
ባልተፈጠረ ነበር። ምክንያቱም እነርሱ በዚህ ነጥብ ወይም ከአላህ በስተቀር ፈጣሪ የለም በሚለው እውነታ ያምኑ ስለነበሩ ነው ።
3ኛ- ፍርድ የአላህ ብቻ ነው የሚለው ትርጉም ደግሞ ከትርጉሞቹ አንዱ ቢሆንም ነገር ግን እሱ ብቻ በቂ አይደለም።
ምክንያቱም አንድ ሰው አላህ በፍርድና በውሳኔ ብቸኛ መሆኑን ቢያምንም በሌሎቹ የአምልኮት ዘርፎች ሌላን አካል የሚገዛ ከሆነ ተውሂዱ ሊረጋገጥ ስለማይችል ነው።
ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው የምስክርነት ቃል ሁለት ክፍሎች አሉት እነሱም ፦
1ኛ-"ላኢላሀ" የሚለው ቃል ከአላህ ውጭ የሆነ አካል አምልኮ እንደማይገባው በግልፅ የሚያስረዳ ሲሆን
2ኛ- "ኢለላህ" የሚለው ቃል ደግሞ አምልኮ ለአላህ ብቻ የሚገባ መሆኑን ያረጋግጣል።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ በጣዖትም የካደና በአላህ ያመነ ሰው የማትበጠስ አስተማማኝ ገመድን በእርግጥ ጨበጠ/ያዘ/ አላህ ሰሚና አዋቂ ነው”(አልበቀረህ: 256)
የካደ የሚለው አምልኮን ከአላህ ውጭ ከሚመለኩ ነገሮች ያነሳና ያስወገደ ማለት ሲሆን ያመነ የሚለው ደግሞ አምልኮን ለአላህ ብቻ ያፀደቀና ያረጋገጠ ማለት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
14
“ኢብራሂምም ለአባቱና ለወገኖቹ እኔ እናንተ ከምትገዙት ነገር ሁሉ የፀዳሁና የራቅኩ ነኝ ያ የፈጠረኝ ሲቀር እሱም ቀናውን መንገድ በእርግጥ ይመራኛል" ባለጊዜ አስታውስ”(አዙኽሩፍ፡ 27)
አንድ ሰው ላኢላሀ ኢለላህ በሚለው የተውሂድ የምስክርነት ቃል ሊጠቀም የሚችለው ምን ሲያሟላ ነው?
የቃሉን ትርጉም አውቆ በመልእክቱ ሲሰራ ነው። ትርጉሙና መልእክቱም ከአላህ ውጭ ከሆነ አካል የአምላክነትን ባህሪ አንስቶ ለአላህ ማፅደቅና እርሱን ብቻ መገዛት ነው።
ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው የምስክርነት ቃል ስምንት መስፈርቶች አሉት። እነሱም፡-
1- ማወቅ፤
2- እርግጠኝነት፤
3- ፍጹምነት፣
4- እውነተኝነት፤
5- መውደድ፤
6- መታዘዝ፣
7- መቀበልና
8- ከአላህ ውጭ በሚመለኩ ነገሮች መካድ ናቸው።
የእነዚህ መስፈርቶች ዝርዝርና ማብራሪያ፦
15
1-ማወቅ የሚለው መስፈርት፡- ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው የምስክርነት ቃል የሚያስረዳውን የማንሳትና የማፅደቅ(አሉታዊና አዎንታዊን) ትርጉም አውቆ በተግባር ላይ ማዋል ማለት ነው አላህ እንዲህ ይላል፡-
“እነሆ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን እወቅ”( ሙሐመድ፡19)
2- እርግጠኝነት የሚለው መስፈርት፦ ከአላህ ሌላ በሀቅ የሚገዙት አምላክ የለም የሚለውን የተውሒድን ቃል በእርግጠኝነት መናገር ማለት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ ትክክለኛ አማኞች እነዚያ በአላህ እና በመልእክተኛው ያመኑና ከዚያም በእምነታቸው ያልተጠራጠሩ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ ላይ የሚታገሉ ናቸው። እነዚያ እነርሱ እውነተኛ አማኞች ናቸው” (አል-ሁጁራት፡15)
3-ፍፁምነት የሚለው መስፈርት ሊረጋገጥ የሚችለው የአምልኮ ዓይነቶች በሙሉ ለአላህ ብቻ ሲውሉ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ቀጥተኞች እና ኃይማኖትን ፍፁም ለአላህ ብቻ አድርገው ሊገዙት እንጂ አልታዘዙም” ( አል-በይነህ: 5)
4- እውነተኝነት ማለት የተውሂድን የምስክርነት ቃል( ላኢላሀ ኢለላህን) በምላሱ ሲናገር በልቡ አምኖ መናገር ማለት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል :
16
“ሰዎች ሳይፈተኑ (ሳይሞከሩ) አምነናል በማለታቸው ብቻ የሚተዉ መሰላቸውን? ከእነሱ በፊት የነበሩትን በእርግጥ ፈትነናቸዋል አላህ እነዚያን እውነተኞችንና ሀሰተኞችን ለይቶ ያውቃል” ( አል-ዐንከቡት: 1-3 )።
5- መውደድ የሚለው መስፈርት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ሲናገር አላህንና መልእክተኛውን፤ የቃሏን መልእክትና ትርጉም በልቡ ወዶ መናገር ማለት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ከሰዎችም እንደ አላህ አድርገው የሚወዷቸው የሆኑ ጥዖታትን የሚገዙ አሉ እነዚያ ያመኑትም አላህን ከማንኛውም በላይ ይወዳሉ” (አልበቀረህ- 175)።
6- መታዘዝ የሚለው መስፈርት፦ አላህን ብቻ መገዛትና ለሕጉ ታዛዥ መሆን ማለት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል.፡-
“ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ ለእሱም እጅ ስጡ” ( አዙመር: 54)
7- መቀበል የሚለው መስፈርት፦ የምስክርነት ቃሏንና መልእክቷን ከልቡ አምኖ መቀበል ማለት ነው ይህም የሚረጋገጠው ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ነገሮችን ትቶ አላህን ብቻ በመገዛት ነው ።
8- ከአላህ ውጭ በሚመለኩ ነገሮች መካድ የሚለው መስፈርት ደግሞ ከአላህ ሌላ የሚመለኩ ነገሮች በሙሉ የውሸት አማልክት መሆናቸውን አውቆና አምኖ እነሱን ከመገዛት መፅዳትና መራቅ ማለት ነው።
17
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ በጣዖትም የካደና በአላህ ያመነ ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ(ያዘ)። አላህም ሰሚና አዋቂ ነው” (አል-በቀረህ: 256) ።
ማሳሰቢያ
አንድ ሰው እነኝህን መስፈርቶች ሳያረጋግጥና ሳያሟላ በአንደበቱ ብቻ ላኢላሀ ኢለላህ ማለቱ ተጠቃሚ አያደርገውም።
ሙሀመድ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመንና መመስከር፡-
ይህ ማለት እሳቸው የአላህ ባሪያ መሆናቸውን እና ለሁለት ከባድ ፍጡራን ( ለሰዎችና ለጅኖች) የተላኩ መሆናቸውን ከልብ ማመን እና በአንደበት መመስከር ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ አላህም አንተ የእርሱ መልእክተኛ መሆንህን ያውቃል”(አል-ሙናፊቁን: 1)
በሌላም አንቀፅ አላህ እንደዚህ ይላል፡-
18
“ በእርግጥ ከራሳችሁ ጎሳ የሆነ መልእክተኛ መጣላችሁ (ተላከላችሁ) ይህ መልዕክተኛ ችግራችሁ የሚያስጨንቀው ለናንተ መልካምና ጥሩ እድል የሚጥርና የሚጓጓ ለምእምናንም እጅግ በጣም አዛኝና ሩኅሩኅ የሆነ መልዕክተኛ ነው” (አተውበህ- 128)
ይህች የምስክርነት ቃል ሁለት ክፍሎች አሏት እነሱም፡-
እሳቸው የአላህ መልእክተኛ እና ባሪያው መሆናቸውን አምኖ መቀበል ናቸው።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ ነው” ( ሙሐመድ: 29)
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“እነሆ የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ አላህን) ለመገዛት በተነሳ ጊዜ (አጋንንት)( በመማረክ )በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊሆኑ ቀረቡ” (አል-ጅን፡ 19)
ከዚህ የምንረዳው ዋና ቁም ነገር እሳቸው የማይስተባበሉ መልእክተኛ እና የማይመለኩ የአላህ ባሪያ መሆናቸውን ነው።
እሳቸው የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ስንመሰክር ወሳኝ የሆኑ አራት ነጥቦችን ማሟላት ይኖርብናል እነሱም፡- 1-የተናገሩትን እውነት ብለን መቀበል።
2- ትእዛዛቸውን ማክበር ።
3- የከለከሉትንና ያስጠነቀቁትን ሙሉ ለሙሉ መራቅና
4-አላህን ስንገዛ በፈጠራና በዘፈቀደ ሳይሆን በእሳሣቸው አስተምህሮት ብቻ በመወሰን መገዛት ናቸው።
ሽርክ እና ዓይነቶቹ፡--
19
ሽርክ በቋንቋ ደረጃ ማጋራትና ማወዳደር ማለት ሲሆን ሀይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ ከአምልኮት ዘርፎች የተወሰነ እንኳን ቢሆን ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል አሳልፎ በመስጠት በአላህ ማጋራት ማለት ነው።
እርሱም ከፍተኛውና መለስተኛው ማጋራት ተብሎ በሁለት ይከፈላል ፦
1- ማንኛውም ከእስልምና ኃይማኖት የሚያስወጣ ወንጀል ሁሉ ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ሲባል ፣
2- ማንኛውም በቃልም ሆነ በተግባር የሚሰራ ወንጀል ማጋራት ወይም ክህደት የሚል ስያሜ ቢሰጠውም ከእስልምና ኃይማኖት የማያስወጣ ከሆነ መለስተኛው የማጋራት ወንጀል ይባላል።
የትልቁ ማጋራት ዓይነቶች፡-
ትልቁ ማጋራት በአራት መልኩ ሊገለፅ ይችላል እሱም ፡-
1- ከአላህ ሌላ የሆነን አካል በመለመንና በመፀለይ የሚፈፀም የማጋራት ወንጀል ፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“በመርከቧም ላይ በተሳፈሩ ጊዜ አላህን ብቻ ይጸልያሉ። ወደ የብስ በማውጣት ሲያድናቸውም ወዲያውኑ እነርሱ ያጋራሉ”(አል-አንከቡት- 65)።
2- በአስተሳሰብ የሚፈፀም የማጋራት ወንጀል ፡-
አላህ እንዲህ ይላል፡-
20
“ ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ ሰዎች የሥራዎቻቸውን (ምንዳ) በእርሷ ውስጥ እንሰጣቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ አይጎድልባቸውም ፤
(15) እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከእሳት በቀር የላቸውም (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩት በጎ ሥራም ተበላሸ ” (ሁድ፡ 16)
3- ከአላህ ውጭ የሆነ አካል አላህ የከለከለውን ሲፈቅድ ወይም የፈቀደውን ሲከለክል አቤት ብሎ በመታዘዝ የሚፈፀም የሽርክ አይነት፦
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“አላህን ብቻ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሆነው እያለ ሊቃውንቶቻቸውን፤ መነኮሳቶቻቸውንና አልመሲህንም የመርየምን ልጅ ከአላህ ውጭ አማልክት አድርገው ያዙ ። ከእርሱ(ከአላህ) በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም እነሱም ከሚያጋሩት ነገር የፀዳ ነው” (አተውበህ: 31)።
አንቀፁም በአጭሩ እና በቀላሉ ሲተረጎም ለሊቃውንቶችና ለመነኮሳቶች በቀጥታ ባይሰገድ እና ባይፆምም አላህ የከለከለውን ሲፈቅዱ ወይም የፈቀደውን ሲከለክሉ ያለምንም ተቃውሞ አቤት ብሎ መቀበልና መታዘዝ እነሱን እንደመገዛት ይቆጠራል። ነቢዩ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ ዐዲይ ኢብኑ ሃቲም ለተባለው ሰሀቢይ ይህን አንቀፅ ሲያነቡለት እኛ ሊቃውንቶችን አልተገዛንም ሲላቸው የሰጡት ምላሽ ይህን ነበር ።
4- ከአላህ ውጭ የሆነን አካል እንደ አላህ አድርጎ በመውደድ የሚፈፀም የማጋራት ወንጀል አይነት ፤ አላህ እንዲህ ይላል፡-
21
نخدَادًا يُ َ
“ ከሰዎችም እንደ አላህ የሚወዷቸውን ጣዖታት ከአላህ ሌላ የሚገዙ አ” አል-በቀረህ: 16)።
የከፍተኛው ማጋራት ምሣሌዎች፡-
1-ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል ቁርባን ማቅረብ፤ መሣልና አላህ እንጂ ማንም መስጠት የማይችለውን ነገር ከአላህ ሌላ ከሆነ አካል መጠየቅ ከፍተኛና ግልፅ የማጋራት ወንጀል ሲሆን ፣
2- አላህ እንጂ ማንም ሊያደርሰው የማይችለውን ችግር ከአላህ ውጭ የሆነ አካል ያደርስብኛል ብሎ መፍራት ደግሞ ከፍተኛና ስውር የማጋራት ወንጀል ይባላል።
የመለስተኛው ማጋራት ምሣሌዎች፡-
1- ከአላህ ሌላ በሆነ አካል መማል፤ አላህ እና አንተ እያላችሁ፤ እገሌና አላህ ባይኖሩ ኖሮ ማለት እና የመሳሰሉት ግልፅና መለስተኛ ማጋራት ሲሆኑ ለይስሙላ መስራት፤በገድ ማመን እና የመሣሠሉት ደግሞ ስውርና መለስተኛ የማጋራት ወንጀል ናቸው።
በከፍተኛውና በመለስተኛው የማጋራት ወንጀል መካከል ያለው ልዩነት፡-
1- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ከእስልምና ኃይማኖት ሲያስወጣ ፣መለስተኛው የማጋራት ወንጀል አለማስወጣቱ፤
2- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ያለበት ሰው ከዚህ ወንጀሉ ሳይመለስ(ንስሓ ሳያደርግ) ከሞተ በጀሐነም ውስጥ በቋሚነት የሚቀጣ ሲሆን፣ መለስተኛው የማጋራት ወንጀል ያለበት ግን የወንጀሉን ያህል ተቀጥቶ ጀነት የመግባት እድል መኖሩ፤
22
3- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል መልካም ስራዎችን በሙሉ ሲያወድም፣ መለስተኛው የማጋራት ወንጀል ግን ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያለውን ስራ ብቻ ማውደሙና
4- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ያለበት ግለሰብ ደሙም ሆነ ንብረቱ የተፈቀደ መሆኑ ናቸው።
የማጋራትን ወንጀል ለመከላከል ጠቃሚ ዱዓ( ፀሎት)፡-
አቡሙሳ የተባሉ ታላቅ ሰሀቢ አንድ ቀን የአላህ መልዕክተኛ // ሲመክሩን ፦
“ እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህን የማጋራት ወንጀል ተጠንቀቁት እርሱ ከጉንዳን ኮቴና እንቅስቃሴ ይበልጥ ስውር ነው" ከጉንዳን እንቅስቃሴና ኮቴ ይበልጥ ስውር ከሆነ እንዴት መጠንቀቅ እንችላለን ? ሲሏቸው፡- " አላህ ሆይ! እያወቅን ባንተ ከማጋራት ባንተው እንጠበቃለን ለማናውቀው ደግሞ ምህረትህን እንጠይቃለን በማለት አላህን ለምኑ አሉ”።
በአላህ የማጋራት ወንጀል አመጣጥ፡-
አላህ ብቸኛ ፈጣሪና አምላክ መሆኑን ማመን የሰው ልጆች ጥንታዊና ነባሩ እምነት ነው በአላህ የማጋራት ወንጀል ደግሞ ከግዜ በኋላ የመጣ ጣልቃ ገብ እምነት ነው። ኢብኑ አባስ የተባሉ ታላቅ ሶሀቢ በአደምና በኑህ መካከል አስር ክፍለ-ዘመናት ነበሩ በነዚህ ክፍለ-ዘመናት የነበሩት ሕዝቦች በሙሉ እምነታቸው ተውሂድ (አላህን ብቻ ማምለክ) ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
23
የማጋራት ወንጀል እንዴት መጣ?
በአላህ የማጋራት ወንጀል ለመጀመሪያ ግዜ በምድር ላይ የተከሰተበት ዋና ምክንያት በአላህ ወዳጆችና በደጋግ ሰዎች ድንበር ማለፍ ነው። ለዚህም አደገኛ ለሆነው ወንጀል የመጀመሪያ ተዋናይና ምክንያት የሆኑት የነቢዩላህ ኑህ ወገኖች ናቸው። ይኽውም የሚወዷቸውና የሚያከብሯቸው የነበሩት ደጋግ ሰዎች ሲሞቱ ለታሳቢነት በሚል በሰይጣን አደገኛ አስተያየት ተነሳስተው ሀውልቶቻቸውን በመስራትና ምስሎቻቸውን በመሳል ድንበር አለፉ። ከዚያም ጊዜው እየረዘመ ሲመጣና ስለነዚህ ደጋግ ሰዎች ማንነት የሚያውቁት ሰዎች ሲጠፉና ሲሞቱ ተተኪው ትውልድ በሰይጣን ግፊትና ተባባሪነት በቀጥታ አመለኳቸው። ከዚያም አላህ ኑህን ወደ ተውሂድ ይጠራቸው ዘንድ ላከላቸው ።
-የሙሳ ወገኖች ጥጃውን(ወይፈኑን) ከአላህ ውጭ አምላክ አድርገው በመያዝ የማጋራት ወንጀልን ለሁለተኛ ጊዜ አደሱት ።
-ክርስቲያኖች ደግሞ በተራቸው የአላህ ባሪያ የሆነውን ኢሳን ወይም ኢየሱስን ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ለተንኮልና ለማታለል በየኢሱስ አመንኩ ያለ አንድ ጳውሎስ የተባለ ግለሰብ መጥቶ የስላሴንና የመስቀልን እምነት በማስተማር ይህን የማጋራትን ወንጀል እንዲቀጥል አደረገው ።
-አንድ ዐምር ብኑ ሉሀይ የተባለ ግለሰብ ከሻም ሀገር ወደ ሂጃዝ ወይም ዐረብ አገር ጣዖታትን በመውሰድ ሰዎች በትክክለኛው በኢብራሂም ኃይማኖት ፈንታ ጣዖታትን እንዲያመልኩ በማድረግ ይህ የማጋራት ቫይረስ ወደ ዐረብ ሀገራት እንዲተላለፍ አደረገ ።
በአላህ የማጋራት ወንጀል በነቢዩ ሙሐመድ ሕዝቦች ውስጥ እንዴት ሊከሰት ቻለ?
እንደ ዓመተ-ሒጅራ አቆጣጠር ከአራት መቶ ክፍለ-ዘመን በኋላ የመልእክተኛውን // ልጅ ፋጢማን እንወዳለን የሚሉ ግለሰቦች በመቃብር ላይ የተለያዩ ቁባዎችን በመስራት የእስልምና ኃይማኖት የማያውቀውን ልደት
24
ወይም መውሊድ የሚባል ፈጠራን በመፍጠርና በጠቅላላ በሷሊሆች ድንበር በማለፍ ይኽው የማጋራት ወንጀል በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ እንዲስፋፋና እንዲቀጥል አደረጉት ።
በአላህ ማጋራት የሚያስከትለው መዘዝ፡-
1-በአላህ ማጋራት በተውበት (ንስሓ) እንጂ የማይማር ከባድ ወንጀል ነው
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“አላህ በእርሱ የማጋራትን ወንጀል በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ የሆነን (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ” (አኒሳእ: 48)፡፡
2- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ከእስልምና ኃይማኖት ያስወጣል፦ አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ የተከበሩት የሓጅ ወራት ሲያልፉ(የሚዋጓችሁን) ጣኦታዊያን በተገኙበት ሥፍራና አጋጣሚ ግደሏቸው፤ ያዟቸውም ክበቧቸውም”(አተውበህ: 5)
3- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ያለበት ሰው የሚሰራው መልካም ስራ ሁሉ ተቀባይነት አያገኝም የሰራውም መልካም ስራ በአየር ላይ እንደተበተነ አመድ ይሆናል፦
አላህ እንዲህ ይላል፡-
25
" ወደ ሰሩት ስራም አሰብን እንደተበተነ ገለባም አደረግነው" (አልፉርቃን: 23)
አላህ በሌላም አንቀፅ ላይ እንዲህ ይላል፡-
“ በእርግጥም ወደ አንተና ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ነቢያት ወህይ(ራእይ) ወረደ ካጋራህ በእርግጥ ስራህ ይወድማል ከከሳሪዎችም ትሆናለህ”( አዙመር: 65) ።
4- ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ያለበት ሰው ጀነት የመግባት እድሉ የጨለመና የተቃጠለ ነው የዘላለም መኖሪያውም በጀሀነም ወይም በሲኦል ውስጥ ይሆናል ። አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው በእርግጥ አላህ በሱ ላይ ጀነትን እርም አድርጓል መኖሪያውም እሳት ናት። ለግፈኞች(ለአጋሪዎችም) ማንም ከአላህ ቅጣት ሊረዳቸው የሚችል ሀይል የለም ” (አልማኢዳ: 72)።
የእስልምናን እምነት የሚያበላሹ ነገሮች፡--
እስልምናን የሚያበላሹ ብዙ ነገሮች አሉ ይሁን እንጂ በጣም አደገኛ እና ብዙ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉት በአስር ነጥቦች ይካተታሉ እነሱም፣-
26
1- ከአላህ ሌላ የሆነን አካል በእርሱ ማጋራት ለምሳሌ ለጅን፤ ለመቃብር እና ለመሳሰሉት የውሸት አማልክቶች ማረድ።
2- ወደ አላህ የሚያማልዱና የሚያቃርቡ ግለሰቦች አሉ ብሎ ማመን። ይህም በዑለሞች መካከል ልዩነት ሳይኖር ከእስልምና ሃይማኖት የሚያስወጣ ወንጀል ነው።
3- የአጋሪዎችን ከሃዲነት መጠራጠር እና ሃይማኖታቸውም ትክክለኛ ነው ብሎ ማመን።
4- ከነብዩ ሙሀመድ // ኃይማኖት (መንገድ) ውጭ ሌላ የተሻለ ኃይማኖት አለ ብሎ ማመን ወይም ከእሳቸው ፍርድ የበለጠና የተሻለ ፍርድ አለ ብሎ ማመን ፤
5- መልእክተኛው የተላኩበትን ህግና ስርዓት መጥላት ።
6- በአላህ ፤ በመልዕክተኛውና በቁርኣን ማሾፍ። በጠቅላላ በእስልምና ሐይማኖት አስተምህሮ ማሾፍና መሳለቅ፤ አላህ እንዲህ ይላል፡-
“በአላህ፤በአንቀጾቹ እና በመልእክተኛው ታሾፋላችሁን? ምክንያት አታቅርቡ ካመናችሁ በኋላ በእርግጥ ክዳችኋልና በላቸው”( አተውበህ: 65-66) ።
7- ድግምት ማድረግም ሆነ ማስደረግ። እንደዚሁም አንድ ሰው ሌላውን እንዲጠላ ወይም እንዲወድ ማድረግ።
8- ከአጋሪዎች ጋር በመተባበርና በመወገን ሙስሊሞችን መውጋት፤ አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ከእናንተ እነሱን (አጋሪዎችን) ወዳጅ አድርጎ የሚይዝ እሱ ከእነሱ
ይመደባል ። አላህ አጋሪ ሰዎችን አይመራም ” (አል-ማኢዳ: 51)።
27
9- ከእስልምና ኃይማኖት ውጭ ሌላ ትክክለኛና የተሻለ ኃይማኖት አለ ብሎ ማመን፤ አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ ከእስልምና ኃይማኖት ውጭ ሌላ ኃይማኖትን የሚሻ ከእሱ ተቀባይነት አያገኝም እሱም በመጪዋ ዓለም ከከሳሪዎች ይሆናል”(ኣሊዒምራን: 85)።
10- የእስልምናን ኃይማኖት ተምሮ በስራ ላይ ማዋል ሲገባው ቸል ማለት አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ በአላህ አንቀጾች ተመክሮ እርሷን ቸል ያለ ወይም ዘወር ካለ ሰው የበለጠ በደለኛ የለም እኛ ጠማሞችን ተበቃዮች ነን ” (አስ-ሰጅዳ: 22)
ማሳሰቢያ፡-
1- እነዚህን የተጠቀሱትን የኢስላም አፍራሾች ተገዶ ካልሆነ በስተቀር ሆን ብሎም ሆነ በግደለሽነት መፈፀም ልዩነት የለውም።
2- እነኝህ አፍራሾች በጣም አደገኛና ብዙ ግዜ የሚከሰቱ ስለሆኑ ማንኛውም ሙስሊም አውቆ ሊጠነቀቃቸው ይገባል ።
ጣዖት፡--
28
ከአላህ ውጭ የሆነን አካል በመገዛት ፤በመታዘዝ እና በመከተል ድንበር የታለፈበት ነገር ሁሉ ጣዖት ይባላል።
በጣዖት መካድ ግዴታ ሰለ-መሆኑ፡-
በሰው ልጆች ላይ የተጣለው የመጀመሪያው ግዴታ በጣዖት መካድ እና በአላህ ማመን ነው ። አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ በማንኛውም ሕዝብ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት
የሚያስተምር መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል”( አል-ነህል: 36)
በጣዖት መካድ፡-
በጣዖት መካድ ማለት፦ ከአላህ ውጭ የሚገዙት ነገር ሁሉ ከንቱ መሆኑን አምኖ መተውና ጣዖት አምላኪዎች ከሃዲያን መሆናቸውን አውቆ ከእነሱም ሆነ ከተግባራቸው ነፃ መሆንና መራቅ ማለት ነው።
የጣዖት አለቃዎች፡-
1- የአላህ እርግማን የተረጋገጠበት ሰይጣን፤
2- ከአላህ ውጭ በፍቃዱ የሚመለክ፤
3- ሰዎች እሱን ያመልኩት ዘንድ ጥሪ የሚያደርግ እና
4- የሩቅ ወይም የሚስጥር እውቀት አውቃለሁ የሚል ሰው ናቸው።
ማንኛውም ሰው በሕይወት እያለ ማወቅ ያለበትና በቀብር ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ እነሱም፡-
29
1ኛ- ስለ ፈጣሪው ማወቅ፤
2ኛ- ስለነቢዩ ሙሀመድ // መልእክተኝነት ማወቅና
3ኛ- የእስልምና ኃይማኖትን በሚገባ መረዳት ናቸው።
የእነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች ዝርዝርና ማብራሪያ፡-
* የመጀመሪያው መሰረታዊ ጥያቄ ስለፈጣሪ ማወቅና መረዳት ሲሆን በውስጡ የሚከተሉትን ወሳኝ ነጥቦች ያካትታል። እነሱም፦
1- ያ እኛንም ሆነ ዓለማትን የፈጠረና በተለያዩ ፀጋዎቹ የሚንከባከበን አላህ ብቻ መሆኑን ማወቅ።
2- ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን ማወቅና ማመን።
3- ፈጣሪያችንን በተለያዩ ምልክቶች እና ታላላቅ በሆኑ ፍጥረታት ማወቅ እንደሚቻል መገንዘብ። ለምሣሌ የእሱን ፈጣሪነት እና ብቸኛ አምላክ መሆኑን ከሚጠቁሙ ምልክቶች፡-
ሀ- ሁለት ተፈራራቂ የሆኑ ሌሊትና ቀን፤
ለ- ፀሐይና ጨረቃ፤
መ- ሰባት ሰማያትና ሰባት ምድሮች፤ እንደዚሁም በውስጣቸውና በመካከላቸው ያለ ነገር ሁሉ አላህ ብቸኛ ፈጣሪና አምላክ መሆኑን ይጠቁማል።
*-ሁለተኛው መሰረታዊ ጥያቄ ስለ እስልምና ሃይማኖት ማወቅና መረዳት ሲሆን በውስጡ ሶስት ነጥቦችን ያካትታል።
1- አላህ የወደደውና የመረጠው ሃይማኖት እስልምና ብቻ መሆኑን ማወቅ፣
2- ኢስላም ማለት ለአላህ እጅ መስጠት፤ ለእሱም መታዘዝ፤ ከሽርክና ከሽርክ ባለቤቶች ነፃ መሆንና መራቅ ነው።
3- ኢስላም፤ ኢማን እና ኢህሳን የሀይማኖቱ ደረጃዎች መሆናቸውን ማወቅና መረዳት ናቸው።
30
*- ሦስተኛው መሰረታዊ ጥያቄ ስለነቢዩ ሙሀመድ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለመ/ ማወቅ ሲሆን በውስጡ ብዙ ወሳኝ ነጥቦች ይካተታሉ፡-
1- ስማቸውን ከነዘር ሀረጋቸው ማወቅ ሲሆን ስማቸውም፦ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላህ ኢብኑ አብዲል ሙጦሊብ ኢብኑ ሃሺም ይባላል። ሐሺም የቁረይሾች ተወላጅ ነው። ቁረይሾች ደግሞ የዐረብ ተወላጆች ናቸው ዐረቦች ከኢስማዒል የዘር ሀረግ ሲወርዱ ሲዋረዱ የመጡ ናቸው።
2- የእድሜ ክልላቸው ስልሳ ሦስት አመታት መሆኑንና አርባዎቹን ከመላካቸው በፊት ሲያሳልፏቸው ሃያ ሶስቶቹን ደግሞ ነቢይና መልእክተኛ ሆነው እንዳሳለፏቸው ማወቅ፤
3- አንብብ በመባል የነቢይነትን መኣረግ ሲያገኙ ተከናናቢው ሆይ! .በሚለው ደግሞ መልእክተኛ መሆናቸው እንደታወጀ ማወቅ፤
4 -የትውልድ አገራቸው መካ ሲሆን የተሰደዱበት ሀገር ደግሞ መዲና መሆኑን ማወቅ፤
5 -የዳዕዋ( የጥሪ) ዋና ርእሳቸው ከሽርክ ማስጠንቀቅና ወደ ተውሂድ ጥሪ ማድረግ መሆኑን ማወቅ ናቸው።
ክህደት፡--
ክህደት ማለት የኢስላም ተቃራኒ ሲሆን እሱም ከፍተኛውና መለስተኛው ክህደት ተብሎ በሁለት ይከፈላል፤
ከፍተኛው ክህደት የሚከተሉትን ነጥቦች ያካትታል።
1- ከአላህ የመጣውን እውነት በማስተባበል የሚፈፀም የክህደት አይነት ። አላህ እንዲህ ይላል፡-
31
“ በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም እውነቱ ሲመጣለት ካስተባበለ ሰው የበለጠ በደለኛ የለም። በገሀነም ውስጥ ለከሃዲያን መኖሪያ ተዘጋጅቷል” (አል-ዐንከቡት: 78)።
2- ከአላህ የመጣው መመሪያ እውነት መሆኑን እያወቀ በኩራትና ሀቅን ባለመቀበል የሚፈፀም የክህደት አይነት።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልን ግዜ ወዲያውኑ ሰገዱ። ዲያቢሎስ ግን እምቢ አለ ኮራም ከከሃዲያንም ሆነ ” (አበቀረህ: 34)።
3- ከእውነት በመዞርና ቸል በማለት የሚፈፀም የክህደት አይነት። አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ እነዚያ የካዱት ሰዎች ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ነገር ቸል ይላሉ”(አል-አህቃፍ: 3)
4- በመጪው ዓለም መጠራጠር ለምሳሌ፦ ከሞት በኋላ በመነሳት፤ ጀነትና እሳት የሚባሉ ሁለት ቋሚ አገሮች በመኖራቸውና በመሳሰሉት የአኺራ ጉዳዮች ላይ በመጠራጠር የሚፈጸም ክህደት ነው።
5- በንፍቅና ምክንያት የሚመጣ የክህደት አይነት ። አላህ እንዲህ ይላል፡-
32
“ እነሱ ካመኑ በኋላ በመካዳቸው በልቦቻቸው ላይ ታሸገ ስለዚህ እነሱ የሚሰሙትን ምክር መረዳት አይችሉም”(አል-ሙናፊቁን: 3)።
መለስተኛው ክህደት፡-
ማንኛውም ወንጀል በቁርኣንና በሐዲስ ክህደት የሚል ስያሜ ከተሰጠው እና እንደ ከፍተኛው ክህደት ከእስልምና ሃይማኖት የማያስወጣ ከሆነ መለስተኛው ክህደት ይባላል። እሱም ተውበት የሚያሻው ታላቅ ወንጀል ነው። ምሳሌዎቹም፡-
1- አላህም ሆነ ሰዎች በዋሉለት ውለታ ማመስገን ሲገባው መካድ።
2- አንድ ሙስሊም ሌላ ሙስሊም ወንድሙን መግደል።
የአላህ መልእክተኛ// ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-
“ አንድን ሙስሊም መሳደብ አመጽ ሲሆን መግደሉ ደግሞ ክህደት ነው ” ብለዋል።
3- የሰዎችን የዘር ሀረግ ማንቋሸሽና ማነወር፤
4- በሞተ ሰው ላይ ሙሾ መደርደርና ጮሆ ማልቀስ። የአላህ መልእክተኛ // ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-
“ ሁለት ነገሮች በሰዎች ዘንድ ክህደት ናቸው የሰዎችን የዘር ሀረግ ማጉደፍና በሞተ ሰው ላይ ሙሾ መደርደር ወይም ጮሆ ማልቀስ” ብለዋል።
ንፍቅና//አስመሳይነት//፡--
33
በእንቅስቃሴውና በተግባሩ ሙስሊሞችን መስሎ በልቡ ውስጥ ክህደትን ማሳደር ንፍቅና ይባላል።
ንፍቅና በሁለት ይከፈላል እነሱም፡-
1ኛ- ከፍተኛና እምነታዊ ንፍቅና፤
2ኛ- መለስተኛና ተግባራዊ ንፍቅና ናቸው።
እምነታዊ ንፍቅና ያለበት ግለሰብ ሳይቶብት በንፍቅናው ላይ እያለ ከሞተ የመጨረሻ አዘቅጥ በሆነው የጀሐነም ክፍል እንዲቀጣ ይደረጋል። ይህም እምነት ስድስት መገለጫዎች አሉት። እነሱም፡-
1- መልእክተኛውን ማስተባበል፤
2- ወይም መልእክተኛው ያመጡትን መመሪያ ማስተባበል፣
3- ወይም መልእክተኛውን መጥላት፤
4- ወይም መልእክተኛው ያመጡትን ህግና ስርዓት መጥላት፣
5- ወይም የእስልምና ሃይማኖት የበታች ሲሆን እና ሲረገጥ መደሰትና
6- ኢስላም የበላይነት ሲያገኝ ቅር መሰኘት ናቸው።
ተግባራዊ ንፍቅና ማለት በአላህ ላይ ያለው እምነት በልቡ ውስጥ እያለ የሙናፊቆችን ተግባር ማከናወን ነው። እሱም ከሃይማኖት ባያስወጣም ወንጀልነቱ ከታላላቅ ወንጀሎች ይቆጠራል። ባለቤቱም የእምነትና የንፍቅና ባህሪያትን አስተናጋጅ ይባላል። የሙናፊቆችንም ተግባር ባበዛ ቁጥር ሙናፍቅነቱ እያመዘነ እና ኢማኑ እየተዳከመ ይመጣል። ከዚያም የለየለት ሙናፊቅ ሊሆን ይችላል።
የመለስተኛው ንፍቅና ምሳሌዎች፡-
1- ሲናገር መዋሸት፤
2- ቀጠሮን አለማክበር፣
34
3- የተሰጠውን አደራ መካድ፤
4- ሲከራከር በውሸት ማሸነፍ(መርታት)፤
5- ቃልኪዳኑን ማፍረስ፤
6- ወደ መስጂድ ሄዶ በህብረት(በጀማዓ) አለመስገድ እና መልካም ስራዎችን ለእዩልኝ መስራት ናቸው ።
ወላእና በራእ ((መውደድና መጥላት) ) በኢስላም ፡--
ወላእ በቋንቋ ደረጃ መውደድ ማለት ሲሆን በራእ የሚለው ደግሞ መቁረጥና መራቅ ማለት ነው።
የወላእ ሃይማኖታዊ ትርጉም ፡- ሙስሊሞችን መውደድ፤ መርዳት፤ ማክበርና ከነሱ ጋር መቀራረብ ሲሆን በራእ ደግሞ ከሃዲያንን መጥላትና ከነሱ መራቅ በሃይማኖት ጉዳይም ከእነሱ ጋር አለመተባበር ማለት ነው።
የመውደድና የመጥላት ወሳኝነት፡-
1-ከእስላማዊ እምነት መሰረቶች አንዱ መሆኑ፤
2- አስተማማኝ የእምነት ገመድ መሆኑ፤
3- የነቢዩ ኢብራሂምና የነቢዩ ሙሀመድ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ መንገድና እምነት መሆኑ ናቸው።
ከሃዲያንን መውደድ በሁለት ይከፈላል፡-
አንደኛው- እነሱን መውደድና በኃይማኖታቸው ጉዳይ መተባበር ሲሆን
ሁለተኛው - ትብብር የሌለው ውዴታ ነው።
35
ምሣሌዎቹም፦
1-ማጋራትንና ክህደትን መውደድ፤
2- አጋሪንና ከሃዲያንን መውደድ፤
3- ከከሃዲያን ጋር ወግኖ አማኞችን መውጋትና የመሳሰሉት ናቸው።
ይህ የውዴታ ክፍል ከኃይማኖት የሚያስወጣ ትልቅ ክህደት ነው።
መውደድ፡-
ከሃዲያንና አጋሪዎችን ለግል ጥቅም ብሎ መውደድና ወዳጅ አድርጎ መያዝ የተከለከለና ከታላላቅ ወንጀሎች የሚመደብ ተግባር ነው።
ከሃዲያንን የመውደድ ምልክቶች፣-
1- በአለባበስና በአነጋገር እነሱን ለመምሰል መሞከር፤
2- ለመዝናናት እና ለመደሰት ብሎ ወደ እነሱ ሀገር መሄድ፤
3- ለሃይማኖቱ ሲል ወደ እስላም ሀገር መሄድ ሲገባው ያለ ምንም ችግር እና ምክንያት በሀገራቸው መኖርን መምረጥ፤
4- በእነሱ አቆጣጠር መቁጠር በተለይም ዓመት ባዓላቸውን የሚገልጽ በሆነው እንደ-ልደት አይነት፤
5-በባዓላቸው መገኘትና መሳተፍ ወይም ለባዓሉ ዝግጅት ትብብር ማድረግና እንኳን ለባዓሉ አደረሳችሁ ማለት፤
6 ከእስልምና ኃይማኖት ጋር የማይጣጣም በሆነው ስማቸው መጠራትና የመሳሰሉት ናቸው።
ከመውደድና ከመጥላት አንፃር ሰዎች በሶስት ይከፈላሉ።
1- ያለምንም ጥላቻ በንፁህ ልቦና የሚዎደዱ ሰዎች አሉ እነሱም ንፁሃን አማኞች ናቸው።