بِسْمِ اللَِّ الرَّحَْنِ الرَّحِيمِ
ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም ( በአላህ ስም
እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
እጀምራለሁ )
ምስጋና ለአሏህ ለዓለማት ጌታ ለሆነው
ይገባው ፡ ሰላምና እዝነት ከነቢያት ሁሉ
በላጭ በሆኑት በነቢያችን ሙሐመድ ላይ
ይስፈን ።
ከዚህ በመቀጠል ፡ -
አሏህ ከለገሰን ታላላቅ ፀጋዎች አንዱ ምላስ
ነው ፡፡ ምላስ ትንሽ አካል ነው ግን በእርሱ
የሚፈፀሙ አምልኮ እና ወንጀሎች ታላላቅ
ናቸው ፡፡ ምክንያቱም በምላስ ክህደት እና
እምነት ይገለፃልና ፡ ምላስ ዘርፉ ሰፊ ነው
፡ እንደዚሁም መንገዱም ሰፊ ነው ፡ እሱም
የልቦች እና የሃሳቦች መግለጫ ትርጓሜ ነው
፡ የመግለጫ ዋና መሳሪያ ነው የንግግርም
መንገድ ነው ፡ በኸይር ጉዳይ ታላቅ ቦታ
አለው ፡ በመጥፎ ጉዳይ ረጅም እቅፍ
የሚያክል ስፋት አለው ። ለጥበብ እና
ጠቃሚ ለሆነ ንግግር ጉዳዮችን ለመፈፀም
የተጠቀመበት እንደዚሁም በሸሪዓው ልጓም
ያሰረው በእርግጥም የአሏህን ፀጋ አረጋገጠ
፡ ነገሩንም በቦታው አስቀመጠ ፡ እርሱም
ከአሏህ ቅጣት ለመዳን የተገባ ነው ።
ምላሱንም መጥፎ ንግግር በመናገር ልቅ
ያደረገ እና መልካም ንግግር በመናገር
ያልተጠቀመበት ሰይጣን በራሱ መጥፎ
መንገድ ያስገባዋል ፡ በሃዲስ (እንደተዘገበው)
ሰዎችን በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው ላይ
የሚገለበጡት በምላሳቸው ሳቢያ ነው ።
እንዲያውም የሰው ልጅ አካላት በሙሉ
በኢስቲቃማ /ቀጥ በማለት/ እና በመጣመም
አኳያ ከሰውየው ምላስ ጋር ተያያዥነት
አላቸው ።
ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) በሀዲሳቸው
እንዲህ ይላሉ ፡-
صْبَحَ ابْنُ آدَمَ كَفَرَتْ جَوَارِحُهُ لِلِسَانِهِ،
َ
إِذَا أ «
فَقَالَتِ: اتَّقِ الله فِينَا، فَإِنَّكَ إِذَا اسْتَقَمْتَ
» اسْتَقَمْنَا، وَإِنِ اعْوَجَجْتَ اعْوَجَجْنَا
- “የአደም ልጅ ባነጋ ጊዜ ሁሉም አካሎች
ምላስን ያስጠነቅቃሉ ፡ እንዲህም ይላሉ ፦
በኛ ጉዳይ ላይ አሏህን ፍራ ፡ እኛ ስራችን
ባንተ ነው የሚለካው ፡ አንተ ቀጥ ካልክ
እኛም ቀጥ እንላለን ፡ አንተ ከተጣመምክ
እኛም እንጣመማለን ” ይላሉ ። ቲርሚዚ
ዘግበውታል ፡ አልባኒ ሐሰን (መልካም
ሐዲስ) ብለውታል።
ንግግርን ጥሩ በሆነ ጥበብ መጠቀም
በኢስላም ታላቅ ቦታ አለው፦
ኢስላም የንግግርን አርዕስትና ያጠቃቀም
ዘዴዎችን(ስልቶችን) አስመልክቶ ታላቅ የሆነ
ማሳሰቢያ ሰጥቷል ፡ ምክንያቱም ማንኛውም
ሰው ትክክለኛ አዕምሮ እና ትክክለኛ ስነ-
3
ምግባር ያለው መሆኑን የሚያመለክተው
ንግግሩ ነው ፡፡
ማንኛውም ማህበረሰብ የተለያዩ የንግግር
ጥበብ እና ስልቶችን መጠቀማቸው ታላቅ
በሆነ ደረጃ ላይ እና በጣም ስር የሰደደ ስነ-
ምግባር ያላቸው መሆኑን ያመለክታል ።
በመጀመሪያ ማንኛውም ሰው ሌሎችን
ከማናገሩ በፊት እዚህ ቦታ ላይ ለመናገር
የሚያስፈልግ ነገር አለ ወይ ብሎ እራሱን
መጠየቅ አለበት ፡ መናገሩ አስፈላጊ ከሆነ
ይናገር አልያም ዝም ይበል ። አስፈላጊ ካልሆነ
ንግግር መራቅ ታላቅ የሆነ ምንዳ ያለው ዒባዳ
ነው ። ዓብደሏህ ኢብን መስዑድ (ረድየ አላህ
ዐንሁ ) እንዲህ ይላሉ ፡ - “በዚያ ከርሱ ሌላ
የሚገዙት (የሚያመልኩት) አምላክ በሌለው
እምላለሁ በምድር ላይ ከምላስ ይበልጥ
ለረዥም ጊዜ እስር ቤት የሚያስፈልገው ነገር
ምንም የለም ። ”
ኢብኑ ዓባስም (ረድየ አላህ ዐንሁ ) እንዲህ
ይላሉ ፡ -“ አምስት ነገሮችን መተግበር
ጥሩ ግመሎችን ሰጥቶ ከሚያስገኘው ምንዳ
ይበልጣል ፦
1/ የማያስፈልግህን ነገር አትናገር ፣
ምክንያቱም ትርፍ ነገር ነውና ። በአንተም
ላይ ወንጀልን አልተማመንልህም ።
2/ የሚመለከትህንም ነገር ቦታ
እስከምታገኝለት ድረስ አትናገር ፡ ምክንያቱም
ብዙዎች የሚመለከታቸውን ነገር የሚናገሩ
ሰዎች አሉ ፡ በቦታው ግን ላይሆን ይችላል፣
በንግግሩም ይነወርበታል ፡፡
3/ ትሁት እና ቂል/ ሞኝ ሰውን አትከራከር
፡ ምክንያቱም ትሁተኛው ይጠላሀል፣ ቂሉ
ደግሞ ይጎዳሃልና ፡፡
4/ ወንድምህን ከአንተ ከራቀ አንተን
ሊያስታውስህ በምትወደው ጥሩ ነገር
አስታውሰው ፡፡
5/ አንተን ይቅር ሊልህ እምትወደውን ሁሉ
እሱንም ይቅር በለው ፣ስራንም ስትሰራ በጥሩ
ነገር በጎ ምንዳ አገኛለው ፣ በወንጀል ደግሞ
መጥፎ ቅጣት ያገኘኛል ብሎ እንደሚያስበው
ሰው ሆነህ ስራ ። ”
ማንኛውም ሙስሊም ምላሱን የተቆጣጠረና
የምላሱንም ልጓም /ገመድ/ በኃይል ያሸነፈ
ሰው ሲቀር እነዚህ አምስት ነገሮችን መስራት
አይችልም ፡ ከዚያም ዝም በሚባልበት
ጊዜ ይገታዋል ፡ መናገር በሚፈልግበት ጊዜ
ይናገራል ፡ እነዚያ ምላሳቸው እንዳስፈለገ
የሚመራቸው ሰዎችም ወደ መጥፊያቸው
ነው የሚመራቸው ።
የምላስ አደገኝነት
ይህን ታላቅ ሃዲስ ልብ እንበል / እናስተውል
!! ቡኻሪና ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ (ረድየ
አላህ ዐንሁ) ከነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ
ወሰለም) ይዘው እንዳስተላለፉት ፡ -
إنّ العبد ليتكلم بالكلمة من رضوان الله لا يلقي «
لها بالاًيرفعه الله بها درجات وإن العبد ليتكلم
بالكلمة من سخط الله لا يلقي لها بالاً يهوي
رواه البخارى ومسلم » بهافى جهنم
4
“ ማንኛውም የአሏህ ባሪያ /አገልጋይ/ ትልቅ
ደረጃ ያላት መሆኗን ሳያስብ ከአሏህ ዘንድ
የሚያስወድድን ቃላት ይናገራል አሏህም
በርሷ ደረጃዉን ከፍ ያደርገዋል ። ማንኛውም
የአሏህ ባሪያ ከአሏህ ዘንድ መጥፎ መሆኗን
ሳያስብ ከአሏህ ዘንድ የሚያስቆጣን ንግግር
/ቃላት/ ይናገራል በእርሷም ወደ ጀሀነም
ይወረወራል ።”
ምላስን መጠበቅን በማስመለከት ታላቅ የሆነ
ማረጋገጫ በቁርኣን መጥቷል ፡፡
“ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ መላእክት
የሚመዘግቡ ቢሆን እንጅ ምንም አይናገርም
” (ቃፍ ፡ 18 )
እንደዚሁም ታላቅ የሆነ ትእዛዝ በሐዲስ
መጥቷል ፡፡ ነቢዩም (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም)
ምላሳቸውን በመያዝ እንዲህ አሉ ፡- “
ሙዓዝ ሆይ ይህን ምላስክን ከመጥፎ ንግግር
ጠብቅ . . . . ። ሰዎች የምላሳቸው ወንጀል
(ጣጣ) እንጅ በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው
ላይ ይደፋሉን ? ”( ቲርሚዚ ዘግበውታል )
ይህ የምላስ ጉዳይ አሳሳቢና አደጋ ያለው
ለመሆኑ የተከበሩት ሰሐቦች አስገራሚ የሆነን
ምሳሌ አስቀምጠዋል ፡ -
አቡበክር አሲዲቅ (ረድየ አላሁ ዐንሁ )
ምላሱን ይይዝና እንዲህ ይል ነበር ፡ -“ ይህ
ነው ወደ ጥፋት ቦታ የመራኝ ፡፡” (ማሊክ
ዘግበዉታል )
ቢን ቡረይዳህ እንዲህ ይላሉ ፡ -“ ቢን
ዓባስን (ረድየ አላህ ዐንሁ ) ምላሱን ይዞ
እንዲህ ሲል አየሁት ፡ - “ወየውልህ ጥሩን
ንግግር /ኸይርን/ ተናገር ታተርፋለህና ወይም
ከመጥፎ ንግግር ዝም በል ነፃ ትሆናለህና
ያለበለዝያ አንተ የምትፀፀት መሆኑን እወቅ
። ”
ኢብኑ ዓባስም እንዲህ ተባሉ ፡ - ቢን
ዓባስ ሆይ ይህን ለምን ትላለህ ? ሲባሉ ፡
እሳቸውም እንዲህ አሉ ፡፡ - “ ምክንያቱም
የሰው ልጅ በምላሱ ጥሩ ነገር የተናገረበት
ወይም ያስመዘገበበት ሲቀር የውመልቂያማ
(የትንሳኤ) ቀን በአካሎቹ ውስጥ ካሉት
ነገሮች ሁሉ ከምላስ ይበልጥ በጣም
የሚበሳጭበት ነገር የለም ። ”
ቢን መስዑድ እንደዚህ በማለት ይምሉ
ነበር ፦ “በዚያ ከርሱ ሌላ የሚገዙት አምላክ
በሌለው እምላለሁ በምድር ላይ ከምላስ
ይበልጥ ረዥም የሆነ እስር ቤት ምንም
የሚያስፈልገው ነገር የለም፡፡”
ንግግርህ ምርኮኛህ ነው
ንግግርህ ምርኮኛህ ነው ፡ ካፍህ ከወጣ
ደግም አንተ ምርኮኛው ትሆናለህ ። አሏህ
(ሱብሃነሁ ወተዓላ ) እንዲህ ይላል ፡ -
“ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ መላእክት
የሚመዘግቡ ቢሆን እንጅ ምንም አይናገርም
” (ቃፍ ፡ 18 )
በልብም ውስጥ ላለው ነገር ጠቋሚ
ከፈለግክ የምላሱን የንግግር እንቅስቃሴ
ማመሳከሪያ አድርግ ። ምክንያቱም ምላስ
ባለቤቱ ቢፈልግም ባይፈልግም በልቡ ውስጥ
ያለውን ያስረዳሃል
የንግግር ወንጀሎች ስንል ሺርክን ያካትታል
፡ እርሱም ከአሏህ (ዓዘወጀል) ዘንድ ታላቅ
ወንጀል ነው ፡ እንደዚሁም በአሏህ ላይ ያለ
እውቀት መናገርን ያካትታል ፡ እርሱም የሺርክ
ጓድ ነው ። ስለዚህ ምላስ ባለ ሁለት ስለት
መሳሪያ ነው ፡ ብልጥ እና የተመራ ለሆነ ሰው
የበጎ እና መልካም ከሆኑ መሳሪያዎች አንዱ
መሳሪያ ነው ፣ ወደ ጥሩ ነገር ለመድረስና
ለስኬትም ከሆኑ መርከቦችም አንዱ መርከብ
ነው ። ምላስ ደረቅና ቂል ለሆነ ሰው ደግሞ
መጥፎ የሆነ ጊንጥ ነው ፣ የማይላቀቅ መጥፎ
ትል ነው ባገኘው ስጋ ሁሉ ላይ ይላከክበታል
።
ከምላስ ጣጣዎች መካከል ፦
1ኛ- በአሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) ማሻረክ
(ማጋራት) ፡ -
አል ሓፊዝ ቢን ረጀብ እንዲህ ይላሉ
፡ - “በአሏህ ማሻረክ(ማጋራት)ከንግግር
ወንጀሎች ውስጥ ይገባል ፡ እርሱም ከአሏህ
(ሱብሃነሁ ወተዓላ ) ዘንድ ከወንጀሎች
ሁሉ ታላቅ ወንጀል ነው ፡ በአሏህ ላይ ያለ
እውቀት መናገርም እንደዚሁ ይካተታል ። ”
2ኛው/ በአሏህ ላይ ያለ እውቀት መናገር
፡ -
በአሏህ ላይ ያለ እውቀት መናገር በጣም ታላቅ
ከሆኑት ወንጀሎች አንዱ ነው ፡ እንዲያውም
ኢብኑል-ቀይም እንደሚሉት ከሽርክ የበለጠ
ወንጀል ነው ።የሽርክ ምክንያት ስለሆነ እንጅ
እንደዚህ /ከሽርክ የበለጠ /ወንጀል አይሆንም
ነበር ፣ እርሱ የሺርክ ሰበብ ደግሞ በአሏህ
ላይ ያለ እውቀት መናገር ነው ።
3ኛው የምላስ ጣጣ / ሀሜት ነው፡ -
ሀሜት ማለት ወንድምህን በሚጠላው
ነገር ማውሳት ሲሆን አንተ የምትለው ነገር
ይኑርበትም አይኑርበትም ሀሜት ይባላል ።
ነቢዩም (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) በዚሁ
መልኩ ነው ሀሜትን የገለፁት።
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) ጥበብ በተሞላ
ቁርኣኑ ውስጥ እንደዚህ ይላል ፡ -
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን
ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡
ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን
አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ
ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን)
ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት) ፡፡
6
አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ
ነውና፡፡” (አልሁጁራት ፡ 12)
ሀሜት ሶስት ስሞች አሉት ፦
አል ጊባህ (ሀሜት)
አል ኢፍክ(ቅጥፈት)
አል ቡህታን (ሰውየው የሌለበትን ነገር
መጫን )
_ የምትለው መጥፎ ነገር በወንድምህ ላይ
ያለ ነገር ከሆነ ሀሜት ይባላል።
_ ስለሱ የነገሩህ ነገር በውሸት የምትናገር
ከሆነ ኢፍክ (ቅጥፈት)ይባላል ።
_ በሱ የሌለበትን ነገር ከተናገርክ ደግሞ
ቡህታን (የሌለበትን መጫን) ይባላል ።
የዕውቀት ባለቤቶች በዚህ መልክ ሀሜትን
ገልፀዋል ፡ ሰውየውን ለማዋረድ የሚደረጉ
ነገሮች ሁሉ ሀሜት ውስጥ ይገባሉ ፡ነገሩ
በንግግርም ይሁን በፁሁፍም ይሁን ሀሜት
ይባላል ብለዋል ።
4ኛው የምላስ ወለምታ ውሸት ነው ፡ -
በሶሒሕ አል ቡኻሪ እንደተዘገበው ነቢዩ
(ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) (በኢስራእ ሌሊት
) ከእሳት ሰዎች የቅጣት አይነት ያየሁት ነገር
አንዱ አሉና እንደዚህ ብለው ገለፁ ፡ -
أماالذي رأيته يشق شدقه فكذاب يحدث «
بالكذبة فتحمل عنه حتى تبلغ الآفاق فيصنع به
»... إلى يوم القيامة
“......... የአፉን አገጭ ጎንና ጎን ሲቀድ ያየሁት
ውሸትን የሚዋሽ ውሸታም ሰው ነው ፡ ወደ
ሰማይ አጥናፍ እስከሚደርስ ድረስ (ሰዎች
ከሱ ይዘው) ያሰራጩታል ፡ እስከ ትንሳኤ
ዕለት እንደዚሁ( አሁን እንዳየሁት)እየተደረገ
ይቀጣል ። ”
ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ
ይላሉ ፡ -
إياكم والكذب، فإن الكذب يهدي إلى «
الفجور، وإن الفجور يهدي إلى النار، وإن الرجل
ليكذب، ويتحرى الكذب حتى يكتب عند
متفق عليه( ( » الله كذابا
“ ውሸትን ተጠንቀቁ ፣ ውሸት በእርግጥ ወደ
ጥመት ይመራል ። ጥመት ደግሞ ወደ እሳት
ይመራል ፡፡ ሰውየው የሚዋሽና ውሸትንም
የሚያስብ ከሆነ አሏህ ዘንድ ውሸታም
ተብሎ ይመዘገባል ። ”(ቡኻሪና ሙስሊም
ዘግበዉታል )
5ኛው የምላስ ወለምታ / ንፁሃን የሆኑ
ምዕመናን ሴቶችን በዝሙት መሳደብ ፦
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ብሏል ፡ -
እነዚያ ንፁሃን ምዕመናትን በዝሙት “
የሚሳደቡ ከዚያም አራት ምስክሮችን
ያላመጡ ሰማንያ ግርፋቶችን ግረፏቸው ፡
7
ምስክርን ለነርሱ በፍፁም አትቀበሏቸው
)እነዚያ እነሱ አመፀኞች ናቸው ። (አኑር : 4
አሏህ የገጠመው ሰው ሲቀር ይህ ስድብ
በአሁኑ ዘመን ብዙ ሙስሊሞች ነፃ
የማይሆኑበት ነው ፡ ፡ ምክንያቱም ይህ ስድብ
የሚዳፈረው ሰው ብዙ ስለሆነ ።
ምዕመናንና ምዕመናትን በክብረ ንፅህናቸውም
ይሁን በሃየማኖታቸው ወይም እነሱ ነፃ
ከሆኑበት ነገር መጠራጠር ይህ ሁሉ ታላቅ
የሆነ ወንጀል ነው ፡ (ከባኢር /ታላላቅ/
ከሚባሉ ወንጀሎች ውስጥ ይቆጠራል) ።
6ኛው የምላስ ወለምታ፡ በውሸት
መመስከር ፡ -
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የሱን ባሮች
ሲያሞግስ እንደዚህ ይላል ፡ -
“እነዚያ በውሸት የማይመሰክሩ ፡ በመጥፎ
ነገር ላይ ባለፉም ጊዜ የተከበሩ ሆነው
የሚያልፉ ናቸው ( መጥፎን የማያዳምጡ)
(ትክክለኛ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው) ።” (አል
ፉርቃን )
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል ፡ -
“ምስክርን አትደብቁ ፡ ምስክርን የሚደብቃት
እርሱ ልቡ ሀጤአተኛ ነው ።” (አል በቀራህ)
7ኛው የምላስ ወለምታ / ሙዕሚኖችን
መሳደብና መዘለፍ ፡ እንደዚሁም በነሱ ላይ
መሳለቅ /ማላገጥ/ ፦
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል ፡ -
“ እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ሰዎች በሰዎች
ላይ አይሳለቁ ፡ ምናልባት (የሚሳለቁባቸው
ሰዎች) ከነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይችላልና ፡
ሴቶችም በሴቶች ላይ አይሳለቁ ምናልባት
(የሚሳለቁባቸው ሴቶች ) ከነርሱ በላጭ
ሊሆኑ ይችላልና ፡ እራሳችሁንም አትውቀሱ
በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ ፡ ከእምነትም
በኋላ መጥፎ የሆነ ስም ምንኛ ከፋ ፡
ወደ አሏህ ያልተመለሰ ሰው እነዚያ እነሱ
ነፍሶቻቸውን በደለኞች ናቸው ” (አል
ሑጁራት 11)
8
8ኛው የምላስ ወለምታ / ከአሏህ
(ሱብሃነሁ ወተዓላ) ውጭ ባለ ነገር
መማል ፡ -
ለምሳሌ ፡ በአማና / በአደራ / ፤ በቃል ኪዳን
፤ በወላጆች ፡ በልጅ ፤ በክብር (በልቅና ) ፤
በጎሳ ፤ በዕድሜ ፤ በነቢዩም ዕድሜ መማል
፡ (በእነዚህ ነገሮች መማል በአረቦች ባህል
የተለመደ ነው ኢስላም ግን ከልክሏል)
ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ
-
رواه أحمد وصححه » من حلف بغير الله فقد أشرك «
الألباني
“ ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር የሚምል በእርግጥ
አጋራ ። ”(አሕመድ ዘግበዉታል ፡ አልባኒ
ትክክለኛ ሐዲስ ብለዉታል ።)
ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህም
ብለዋል ፡ -
» من كان حالفا فليحلف بالله أو ليصمت «
متفق عليه
“ መማል የፈለገ በአሏህ ይማል ወይም ዝም
ይበል ።” ( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል )
9ኛው የምላስ ወለምታ / መጥፎ ንግግርን
መናገር ወይም ሐቅ ነገርን ዝም ማለት ፦
ኢብኑል ቀይም( ረሂመሁ ላሁ ) እንዲህ ይላሉ
፡ - “ በምላስ ላይ ሁለት ታላላቅ የምላስ
ወለምታዎች አሉ ፡ ሰውየው ከአንደኛው ነጻ
ቢሆንም ከአንደኛው ነጻ ላይሆን ይችላል ፡
፡ የመናገር ወለምታ እና ዝም የማለት
ወለምታ አለው ፡፡ ሁሉም እያንዳንዱ ወንጀሉ
ከሌላው በራሱ ጊዜ በላጭ ይሆናል። ይህም
ማለት ፡ ሐቅን ከመናገር ዝም የሚል ሰው
ዱዳ የሆነ ሰይጣን ነው ፡ አሏህን አመፀኛ
ለእዩልኝ ሰሪ አስመሳይ ነው ፣ በነፍሱ ላይም
ካልፈራ ይሄን ስራ ይሰራል ። መጥፎ ነገርን
የሚናገር ፡ ተናጋሪ ሰይጣን ነው ። አሏህን
አመፀኛ ነው ፡ አብዛኛው ፍጡር በንግግሩም
በዝምታውም የጠመመ ነው ።እነሱም
በእነዚህ ሁለት ዓይነት ባህሪ ውስጥ ነው
የሚሆኑት ። የሁለት አማካኝ(የሚዛናዊነት)
ባለቤቶች እነሱ የቀጥተኛ መንገድ ባለቤቶች
ናቸው ፡ ምላሳቸውን ከመጥፎ ይከለክላሉ ፡
በአኼራ ለሚጠቅማቸው ጉዳይ ይጠቀማሉ
። ”
10ኛው የምላስ ወለምታ እርግማን ነው፡
-
አቡ ደርዳእ (ረድየ አላህ ዐንሁ ) እንደዘገቡት
፡ ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ
ብለዋል ፡ -
لا يكون اللعانون شفعاء ولا شهداء يوم «
رواه مسلم. » القيامة
“ ተራጋሚዎች በትንሳኤ ቀን አማላጆችም
ምስክሮችም አይሆኑም ፡፡” (ሙስሊም
ዘግበዉታል)
እንደዚሁም ከአቡደርዳእ (ረድየ አላህ ዐንሁ
) ከነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) ይዘው
እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል ፡ -
9
إن العبد إذا لعن شيئا صعدت اللعنة إلى «
السماء فتغلق أبواب السماء دونها، ثم تهبط
إلى الأرض فتغلق أبوابها دونها، ثم تأخذ يمينا
وشمالا فإذا لم تجد مساغا رجعت إلى الذي لعن،
رواه » فإن كان لذلك أهلا وإلا رجعت إلى قائلها
أبوداود وحسنه الألباني
“ ማንኛውም የአሏህ ባሪያ አንድን ነገር ከረገመ
እርግማኑ ወደ ሰማይ ይወጣል የሰማይም በር
በርሱ ላይ ትዘጋበታለች ፡ ከዚያም ወደ ምድር
ይወርዳል ፡ በርሱ ላይ በሯ ትዘጋለች ከዚያም ወደ
ቀኝም ወደ ግራም ይሄዳል መግቢያ ካጣ ወደዚያ
ወደ ተረገመው ሰውዬ ይመለሳል ፡ እርሱ ለዚህ /
እርግማን/ ተገቢ ከሆነ በርሱ ላይ ያርፋል ፡ እርሱ
/ለእርግማን/ ተገቢ ካልሆነ ግን ወደ ተራጋሚው
ሰውዬ ይመለሳል ። ”( አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል
፡ አልባኒ መልካም ሐዲስ ብለውታል )
መቀለድ (ማፌዝ)
ባአሁን ጊዜ በሰዎች መካከል ከውሸት
ዓይነቶች ( ቀልድ/ ጆክ ) በማለት የሚታቀው
ተሰራጭቷል ፡ እሱም አንዳንድ ሰዎች መሰረት
የሌለው አባባሎችን ከልብ ወለድ በመፍጠር
ከተለያዩ ጎሳዎችና ዝርያዎች ወይም የሰዎችን
አገር በማንሳትና ቀልዶችን በመፍጠር
የሚፈጸም ተግባር ነው። ይህም ሰዎችን
ለማሳቅ ሲባል የሚደረግ ሲሆን እርሱም
ሐራም ነው ፡(በሸሪዐው በጥብቅ የተከለከለ
ጸያፍ ተግባር ነው) ሀሜትንና ውሸትንም
በአንድ ላይ መቀላቀልና መሰብሰብ ነው
ሚሆነው ። (የሀሜትና የውሸት ወንጀልም
አለበት) ። በእርግጥም በዚህ ላይ ከነቢዩ
(ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) ታላቅ የሆነ ዛቻ
መጥቷል ፡ ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም)
እንዲህ ይላሉ ፡ -
ويل للذي يحدث بالحديث ليضحك به القوم «
رواه أبوداود وحسنه الألباني. » فيكذب ويل له ويل له
“ ለዚያ ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ ውሸት
ለሚያወራው ሰው ለርሱ ወየውለት
ወየውለት ። ” (አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል
አልባኒ መልካም ሐዲስ ብለዉታል)
ወይል ማለት ፡ ገሀነም ውስጥ ያለ ሸለቆ ነው
።
ምላስህን መልካም የሆነ ንግግር
አለማምድ
ሰውየው መልካም የሆነን ንግግር ምላሱን
ማለማመድ በጣም ተገቢና ያማረ ነው
፡ በተናገረም ጊዜ መልካምን እንጅ ሌላን
አይናገርም ፡ መልካም /ንፁህ/ የሆነ ንግግር
ከወዳጆችና ከጠላቶችም ጋር ከሁሉም
ጋር ያምራል ፡ ጣፋጭ የሆነ ፍሬ አለው
፡ ከወዳጆች ጋር ውዴታቸውን ይጠብቃል
፡ ጓደኝነታቸውን ያዘወትራል የሰይጣንን
ተንኮል በመከላከላቸው ያለውን ግንኙነት
ከመበላሸት እና ከመዳከም ይከላከላል ።
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) እንዲህ ይላል ፡ -
“ለባሮቼ ያችን መልካም የሆነችን ንግግር
10
እንዲናገሩ ንገራቸው ፡ ሰይጣን በመካከላቸው
ይወተውታል ፡ ምክንያቱም ሸይጣን ለሰው
ልጅ ግልፅ የሆነ ጠላት ነውና ።” (አልኢስራእ
፡ 53) ከጠላቶች ጋር መልካም ንግግር
ክርክራቸውን ያጠፋል ፡ ቁጣቸውንም
ይሰብራል ፡ መጥፎውን ነገር እንዳይቀጥልና
መጥፎው ነገር እንዳይሰራጭ ያስቆመዋል ።
አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) እንዲህ ብሏል
“መልካም እና መጥፎ አይስተካከሉም ፡ በዛች
እርሷ መልካም በሆነችው ነገር (የመጥፎውን
አጠፋ) መልስ ፣ ወዲያውኑ ያ ባንተና በሱ
መካከል ጥላቻ ያለበት ሰው ልክ ቅርብ የሆነ
ወዳጅ ይሆናል ።” (ፉሲለት ፡34)
የዑለማዎችን /የመሻይኾችን/
ክብር መዳፈርን ተጠንቀቅ
በጣም መጥፎ አስቀያሚ ከሚባሉት የንግግር
ዓይነቶችና የምላስ አደጋዎች መካከል
ጥሩ ናቸው ተብለው በሚታሰቡ ሰዎች
መሰባሰቢያ ላይ አሉባልታን ማሰራጨትና
የሆነ ያልሆነውን ወሬ መዘባረቅ ነው ።
የወሬው መጨረሻና ውጤትም የታላላቅ
ዑለማዎች ( ሊቃውንቶችን ) ክብር
መዝለፍና እንዲሁም በኡሉል አምር (ስልጣን
ባለቤቶች ) ላይ ያለን ትዕዛዝን ማንሳት
ነው ። መልካምና ጥሩ በሆኑ ወንድማማቾች
እንዲዚሁም ወደ አላህ ተጣሪዎች በሆኑት
መካከል ማጣላትና ማለያየት ነው ።
መደምደምያ ፦
ሁላችንም ልናውቀው የሚገባው ነገር ቢኖር
ለማንኛውም ቃላት ሃላፊነት ልንወስድ
እንደሚገባ እና ከማንኛውም ቃላት ጋር
እንዴት ማድረግ እንዳለንብን ማወቅ
ይኖርብናል ። ምክንያቱም ትንሽ መጥፎ
ቃላት ወደ ጠብ ታደርሳለች ፡ ትንሽዬ
ደረቅ መጥፎ ቃልም የቤተሰብን ልትበትን
ትችላለች ።
ትንሽ ወሰን ያለፈች ቃል ሰውዬውን
ከሀይማኖቱ ( ከኢስላም ) ልታስወጣው
ትችላለች ። እንደዚሁም ደግሞ ትንሽ ምርጥ
የሆነች ቃላት የሰውዬውን ህይወት ልታድን
ትችላለች ። ትንሽዬ መልካም ቃላትም
የሰውዬውን ፕሮግራም ትሰበስባለች ።
እናንተንም እኛንም ባለ መልካም ንግግር
አሏህ ያድርገንና የምንናገረው ንግግር ቃላት
አሳሳቢና ተፅእኖ አሳዳሪ ስለመሆኑ ነቢዩ
(ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ፡ -
من كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليقل خيراً أو «
متفق عليه » ليصمت
“ በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን
ንግግር ይናገር አልያም ዝም ይበል” (ቡኻሪና
ሙስሊም ዘግበዉታል)
11
ይህንን ሐዲስ ሰዎች ቢረዱት ኑሮ ምርጥና
የተከበረ ሐዲስ ነው ፡ ሰዎች በዚህም ሐዲስ
ለመስራት ሀሳባቸው እውነተኛ ቢሆን ኑሮ
ብዙን መጥፎ ንግግር ይርቁ ነበር ፡፡ ብዙ ጊዜ
በሰው መካከል ያለውን ፍቅር የሚያበላሸው
ነገር ቢኖር አደገኛ ጎጂ የሆኑ በቦታው ላይ
ተገቢ ያልሆኑ ቃላቶችን መጠቀም ነው ።
ምክንያቱም መጥፎ ቃል መርዛማ የሆነው
ጦር ሰርፆ እንደሚገባ ሁሉ ቃላቶችም ሰርፀው
ይገባሉ ። አንድ የነበረውንም ማህበረሰብም
ይለያያል፣ ጥሩ መልካም የሆነውንም ነገር
ያበላሻል ።
የተከበሩ አሸይኽ ቢን ባዝ (ረሒመሁሏህ)
እንዲህ ይላሉ ፡ - “ሰውየውን በሚወደውና
በሚያፈቅረው ነገር ማውሳት ይህ ሀሜት
አይባልም ። ለምሳሌ ፡ እርሱ መልካም ሰው
ነው ፣ እርሱም ሶላቶቹን ጠብቆ ይሰግዳል
፣ ምርጥ ከሆኑት ሰዎች ነው ማለት ይህ
ሀሜት አይባልም ፡፡ ይህ ሰውየውን ማሞገስ
ነው ሚባለው በዚህም ችግር የለውም ።
ሀሜት የሚባለው ወንድምህ በሚጠላው
ነገር ማውሳት ነው ። ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ
ወሰለም) እንዳሉት ፦
» الغيبة ذكرك أخاك بما يكره «
“ሀሜት ማለት ወንድምህን በሚጠላው ነገር
ማውሳት ነው ። ”
ሀሜት ማለት ፡ ለምሳሌ ፡ ስስታም ፤ ፈሪ
፤ ምላሱ አስቀያሚ፣ የመሳሰሉት ናቸው
።ሲሰማ የሚጠላው ነገር ከሆነ ይህ ነው
ሀሜት የሚባለው ።
ሰውዬው ወንድሙን ካማ በሱ ላይ ግዳጅ
የሚሆንበት ወደሱ ሄዶ ይቅርታ መጠየቅ
ነው ።ጀዛከሏሁ ኸይር እኔ ያንተን ክብር
ነክቼያለሁ ይቅርታ አድርግልኝ ይበለው ፡
መጥፎን ነገር ከፈራ (ጉዳት ያደርስብኛል)
ካለ ወይም ይቅርታን በመጠየቁ መጥፎን
የሚያስከትል ከሆነ አሏህን ማርታ
ይጠይቅለት ፡ ዱዓ (ፀሎት) ያድርግለት ፡
ሰለእሱ የሚያውቃቸው መልካም ነገርንም
ባማበት ቦታ ያውሳው ፡ ለአሏህ ምስጋና
ይገባውና ይህም በቂ ነው ፡፡
በምላሱ ከተሳለቀ /ከቀለደ/ እርሱ ተሳላቂ
/ቀላጅ/ ይባላል ፡፡ በሃይማኖት /በዲን
በኢስላም/ ከተሳለቀ /ካላገጠ/ ከሐዲ /ካፊር/
ይባላል ፡፡ ከሱ ጋር አንድም የሚሳለቅ /
የሚያላግጥ/ ባይኖርም እንኳ ካፊር /ከሐዲ/
ይባላል ። በርሱም ላይ ወደ አሏህ መፀፀትና
ወደ ሓቅ መመለስ አለበት ፡ ለአሏህ የተፀፀተ
አሏህ ፀፀቱን ይቀበለዋል ። ”
ሰላት እና ሰላም በነቢዩ ላይ ይስፈንባቸው
እንደዚሁም በቤተሰቦቻቻው እና
በባልደረቦቻቻው ላይ ይሁን ::
ተፈጸመ