መጣጥፎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች። 


﴿الٓمٓ١ ذَٰلِكَ ٱلۡكِتَٰبُ لَا رَيۡبَۛ فِيهِۛ هُدٗى لِّلۡمُتَّقِينَ٢ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡغَيۡبِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ٣ وَٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبۡلِكَ وَبِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ ٤ أُوْلَٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدٗى مِّن رَّبِّهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ٥﴾ [البقرة: 1-5]


(አሊፍ ላም ሚም* ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመሆኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡ * ለነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለሆኑት፤ * ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው የሚያምኑ በመጨረሻይቱም (ዓለም) እነርሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት (መሪ ነው)፡፡ * እነዚያ ከጌታቸው በመመራት ላይ ናቸው፤ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡) (አል በቀራህ፡ 1-5)


﴿ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡحَيُّ ٱلۡقَيُّومُۚ لَا تَأۡخُذُهُۥ سِنَةٞ وَلَا نَوۡمٞۚ لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ مَن ذَا ٱلَّذِي يَشۡفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦۚ يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيۡءٖ مِّنۡ عِلۡمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَۚ وَسِعَ كُرۡسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَۖ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفۡظُهُمَاۚ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡعَظِيمُ٢٥٥﴾ [البقرة: 255]


(አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡)


(አያቱል ኩርሲይ አል በቀራህ፡ 255)


﴿ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّن رُّسُلِهِۦۚ وَقَالُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۖ غُفۡرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيۡكَ ٱلۡمَصِيرُ٢٨٥ لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ لَهَا مَا كَسَبَتۡ وَعَلَيۡهَا مَا ٱكۡتَسَبَتۡۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذۡنَآ إِن نَّسِينَآ أَوۡ أَخۡطَأۡنَاۚ رَبَّنَا وَلَا تَحۡمِلۡ عَلَيۡنَآ إِصۡرٗا كَمَا حَمَلۡتَهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِنَاۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلۡنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِۦۖ وَٱعۡفُ عَنَّا وَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَآۚ أَنتَ مَوۡلَىٰنَا فَٱنصُرۡنَا عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ٢٨٦﴾ [البقرة: 285-286]


(መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲሆኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም። *


አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡ ከእኛም ይቅርታ አድርግ ለእኛም ምሕረት አድርግ፡፡ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፡፡ በከሓዲዎች ሕዝቦች ላይም እርዳን፡፡) (አል በቀራህ 285 - 286)


﴿حمٓ١ تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ٢ غَافِرِ ٱلذَّنۢبِ وَقَابِلِ ٱلتَّوۡبِ شَدِيدِ ٱلۡعِقَابِ ذِي ٱلطَّوۡلِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ إِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ٣﴾ [غافر: 1-3]


(ሓ ሚም * የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ዐዋቂ ከሆነው አላህ ነው፡፡ * ኀጢአትን መሓሪ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣ ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከሖነው (አላህ የወረደ ነው)፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው፡፡) (አል ጋፊር፡ 1 - 3)


﴿هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِۖ هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ٢٢ هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡقُدُّوسُ ٱلسَّلَٰمُ ٱلۡمُؤۡمِنُ ٱلۡمُهَيۡمِنُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡجَبَّارُ ٱلۡمُتَكَبِّرُۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يُشۡرِكُونَ٢٣ هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡخَٰلِقُ ٱلۡبَارِئُ ٱلۡمُصَوِّرُۖ لَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ٢٤﴾ [الحشر: 22-24]


(እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የሆነ ነው፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ ነው፡፡ * እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ * እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።) (አል'ሐሽር 22 - 24)


﴿قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ١ ﴾ [الإخلاص: 1]


(በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡)


﴿قُلۡ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلۡفَلَقِ١ ﴾ [الفلق: 1]


(በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡)


﴿قُلۡ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ١ ﴾ [الناس: 1]


(በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ፡፡)


ሙሉ ምዕራፉን (አል'ኢኽላስን፣ አል'ፈለቅን እና አንናስን) ሦስት ጊዜ ይነበባሉ።


«أعوذ بكلمات الله التامات من شر ما خلق»


«አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ» (ምሉዕ በሆኑት የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ነገሮች ክፋት እጠበቃለሁ።)


(ሦስት ጊዜ) ይባላል።


«بِسْمِ اللهِ الَّذِي لاَ يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيْءٌ فِي الأْرْضِ وَلاَ فِي السَّمَاءِ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ»


«ቢስሚላሂ ለዚ ላ የዹሩ መዐ_ስሚሂ ሸይኡን ፊል አርዺ ወላ ፊ ስሰማኢ ወሁወ አስ'ሰሚዑል ዐሊም።» (በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና ዐዋቂ በሆነው አላህ ስም።)


(ሦስት ጊዜ) ይባላል።


«رضيت بالله ربًّا وبالإسلام دينًا وبمحمد صلى الله عليه وسلم نبيًّا»


«ረዺቱ ቢልላሂ ረበን ወቢል ኢስላሚ ዲነን ወቢ ሙሐመዲን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነቢየን» (የአላህን ጌትነት ፣ የእስልምናን ሃይማኖትነት፣ የሙሐመድን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነብይነት ወደድኩ (ተቀበልኩ)።)


(ሦስት ጊዜ) ይባላል።


«أصبحنا وأصبح الملك لله والحمد لله لا إله إلا الله وحدة لا شريك له. له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير. رب أسألك خير ما في هذا اليوم وخير ما بعده. وأعوذ بك من شر ما في هذا اليوم ومن شر ما بعده. ربِّ أعوذ بك من الكسل والهرم وسوء الكِبَر. وأعوذ بك من عذاب النار وعذاب القبر»


«አስበሕና ወአስበሐል ሙልኩ ሊላሂ፤ ወልሐምዱ ሊላሂ፤ ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር፤ ረብቢ አስአሉከ ኸይረ ማ ፊ ሀዘል የውሚ ወኸይረ ማ በዕደሁ፤ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ማ ፊ ሀዘል የውሚ ወሚን ሸሪ ማ በዕደሁ፤ ረብቢ አዑዙ ቢከ ሚነል ከሰሊ ወል ሀረሚ ወሱኢል ኪበር፤ ወአዑዙ ቢከ ሚን ዐዛቢ አንናሪ ወዐዛቢል ቀብር።» (እኛም አነጋን፤ ንግስናም የአላህ ሆኖ አነጋ። ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። ከአላህ ውጭ (በእውነት) የሚመለክ አምላክ የለም ፤ ብቸኛና አጋር የሌለው ነው ፤ ንግስና እና ምስጋና ለርሱ ነው ፤ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። ጌታዬ ሆይ! በዚህ ቀን ውስጥም ከዚህ ቀንም በኋላ ያለን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ። በዚህ ቀን ውስጥም ከዚህ ቀንም በኋላ ካለው ክፉ ነገርም በአንተ እጠበቃለሁ። ጌታዬ ሆይ! ከስንፍና ፣ ከመጃጀትና ከመጥፎ እርጅና በአንተ እጠበቃለሁ። ጌታዬ ሆይ! ከእሳት ቅጣት እና ከቀብር ቅጣት በአንተ እጠበቃለሁ።)


«أمسينا وأمسى الملك لله»


ምሽት ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ እኛም ንግስናም የአላህ ሆነን አመሸን። … እንዲህም ይላል፦ (ጌታዬ ሆይ የዚህንም ሌሊት እና ከዚህ ሌሊት በኋላም ያለን መልካም ነገር እማፀንሀለሁ... እስከመጨረሻው አዝካር ድረስ፡ (እኛም ንግስናም የአላህ ሆኖ አነጋን።) እና (በዚህ ቀን ውስጥ) በሚለው ፈንታ።


«اللهم بك أصبحنا وبك أمسينا وبك نحيا وبك نموت واليك النشور»


«አልላሁምመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ_ንኑሹር።» (ጌታዬ ሆይ! በአንተ (ጥበቃ) አነጋን ፤ በአንተ (ጥበቃም) አመሸን ፤ በአንተ (ስም) ህያው እንሆናለን ፤ በአንተ (ስምም) እንሞታለን ፤ መቀስቀስም ወደ አንተ ብቻ ነው።)


«اللهم بك أمسينا وبك أصبحنا وبك نموت وبك نحيا وإليك المصير»


ምሽት ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ «አልላሁምመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሙቱ ወቢከ ነሕያ ወኢለይከል መሲር።» (ጌታዬ ሆይ! በአንተ (ጥበቃ) አመሸን በአንተ (ጥበቃም) አነጋን ፤ በአንተ (ስም) ህያው እንሆናለን በአንተ (ስም) እንሞታለን። መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው።)


«اللهم ما أصبح بي من نعمة أو بأحد من خلقك فمنك وحدك لا شريك لك فلك الحمد ولك الشكر»


«አልላሁምመ ማ አስበሐ ቢ ሚን ኒዕመቲን አው ቢአሐዲን ሚን ኸልቂከ ፈሚንከ ወሕደከ ላ ሸሪከ ለከ ፈለከል ሐምዱ ወለከ አሽሹክሩ።» (አላህ ሆይ! በኔ ወይም ከፍጡራንህ በአንዱ ላይ ያነጋው ፀጋ ከአንተው ብቻና ብቻ ነው። ለአንተ አጋር የለህም ምስጋናና ውዳሴም ይገባሀል።


«ما أمسى بي»


ምሽት ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ (በኔ ላይ ያነጋው በሚለው ፈንታ) በኔ ላይ ያመሸው።


«اللهم إني أصبحت في نعمة وعافية وستر. فأتم نعمتك عليّ وعافيتك وسترك في الدنيا والآخرة»


«አሏሁመ ኢኒ አስበሕቱ ፊ ኒዕመቲን ወዓፊየቲን ወሲትሪን ፈአቲም ኒዕመተከ ዓለየ ወዓፊየተከ ወሲትረከ ፊዱኒያ ወልአኺራህ» (አላህ ሆይ! በጸጋ፣ በጤና እና በጥበቃህ ስር ሆኜ አንግቻለሁ፤ ስለዚህ በረከትህን፣ ደህንነትህን እና ጥበቃህን በዚህ ዓለም እና በመጨረሻው ዓለም አሟላልኝ።)


«اللهم إني أمسيت…»


(ሦስት ጊዜ።) ምሽት ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ "አሏሁመ ኢኒ አምሰይቱ… " (አላህ ሆይ … አምሽቻለሁ) እስከመጨረሻው።


«اللهم إني أعوذ بك من الهم والحزن. وأعوذ بك من العجز والكسل. وأعوذ بك من الجبن والبخل. وأعوذ بك من غلبة الديْنِ ومن قهْر الرجال»


«አልላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ሀምሚ ወል ሑዝኒ፤ ወአዑዙ ቢከ ሚነል ዐጅዚ ወል ከሰል፤ ወአዑዙ ቢከ ሚነል ጁብኒ ወል ቡኽል፤ ወአዑዙ ቢከ ሚን ጘለበቲ አድ‐ደይኒ ወሚን ቀህሪ አርሪጃል» አላህ ሆይ! ከጭንቀትና ከሀዘን ከደካማነትና ከስንፍና ከስስት እና ከፍርሃት ከእዳ መደራረብ እና ከሽንፈት በአንተ እጠበቃለሁ።


«اللهم إني أسألك العافية في الدنيا والآخرة. اللهم إني أسألك العفو والعافية في ديني ودنياي وأهلي ومالي. اللهم استر عوراتي وآمن روعاتي. اللهم احفظني مِن بين يديَّ ومِن خلفي وعن يميني وعن شمالي ومن فوقي. وأعوذ بعظمتك أن أُغتال من تحتي»


«አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከል ዓፊየተ ፊድዱኒያ ወል አኺረቲ፤ አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከል ዐፍወ ወል ዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፤ አልላሁምመ ስቱር ዐውራቲ ወአሚን ረውዓቲ፤ አልላሁምመ ኢሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደይየ ወሚን ኸልፊ ወዐን የሚኒ ወዐን ሺማሊ ወሚን ፈውቂ፤ ወአዑዙ ቢዐዞመቲከ አን ኡጝታለ ሚን ተሕቲ።» (አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ጤናን እጠይቅሀለሁ። አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም በሃይማኖቴ እና በቅርቢቱ ዓለም ህይወቴ በቤተሰቦቼም በንብረቴም ይቅርታህንና ጤናን እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ። ለስጋቴ (ለፍርሃቴ) ደህንነትን ለግሰኝ። አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ ከኋላዬም ከበስተቀኜም ከበሰተግራዬም ከበላዬም ጠብቀኝ። ከበታቼም እንዳልጠቃ በልቅናህ  እጠበቃለሁ።)


«اللهم أنت ربي لا إله إلا أنت. خلقتني وأنا عبدك. وأنا على عهدك ووعدك ما استطعت. أعوذ بك من شر ما صنعت. أبوء لك بنعمتك علي. وأبوء بذنبي. فاغفر لي. فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت»


«አልላሁምመ አንተ ረቢ ላኢላሀ ኢልላ አንተ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መስተጠዕቱ፤ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማሰነዕቱ፤ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዓለይየ፤ ወአቡኡ ቢዘንቢ፤ ፈግፊር ሊ ፈኢነሁ ላ የግፊሩ አዝ‐ዙኑበ ኢልላ አንተ።» (አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ። ከአንተ በስተቀር ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ፈጥረኸኛል። እኔም ባርያህ ነኝ። ላንተ የገባሁትን ቃል ኪዳን ለመሙላት የቻልኩትን ያህል እጥራለሁ። (የገባህልኝንም) ቀጠሮ አምናለሁ። ከሰራሁት ነገር ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ።በኔ ላይ ለዋልከው ፀጋም እውቅናን እሰጣለሁ። ኃጢአት መስራቴንም አምናለሁ። ምህረትህን ለግሰኝ። እነሆ ካንተ በስተቀር ኃጢአትን የሚምር ማንም የለምና።)


«اللهم فاطر السماوات والأرض. عالم الغيب والشهادة. ربَّ كل شيء ومَلِيكه. أشهد أن لا إله إلا أنت. أعوذ بك من شر نفسي ومن شر الشيطان وشركه وأن أقترف على نفسي سوءاً أو أجُرَّه إلى مسلم»


«አልላሁምመ ፋጢረስ_ ሰማዋቲ ወል አርዲ፤ ዐሊመል ገይቢ ወሽ_ሸሃደቲ፤ ረብበ ኩሊ ሸይኢን  ወመሊከሁ፤ አሽሀዱ አን ላኢላሀ ኢልላ አንተ፤ አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ነፍሲ ወሚን ሸርሪሽ_ሸይጧኒ ወሺርኪሂ ወአን አቅተሪፈ ዐላ ነፍሲ ሱአን አው አጁረሁ ኢላ ሙስሊም።» (የሰማያትና የምድሩ ፈጣሪ የሆንከው፣ የሩቁን እና የቅርቡን አዋቂ ፤ የሁሉም ነገር ጌታ እና ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ከአንተ በስተቀር ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ። ከነፍሴ ተንኮል እንዲሁም ከሸይጧን ተንኮል እና የሽርክ ጥሪው (ውትወታው)፣ በነፍሴ ላይ መጥፎ ከመስራትም ይሁን ሙስሊም በሆነ ሰው ላይ መጥፎን ከመፈፀም በአንተ እጠበቃለሁ።)


«اللهم إني أصبحت أُشهدُك وأشهد حملة عرشك وملائكتك وأنبياءك وجميع خلقك بأنك أنت الله لا إله إلا أنت وأن محمدًا عبدك ورسولك»


«አልላሁምመ ኢንኒ አስበሕቱ ኡሽሂዱከ ወኡሽሂዱ ሐመለተ ዐርሺከ ወመላኢከቲከ ወአንቢያአከ ወጀሚዐ ኸልቂከ ቢአንነከ አንተ አልላሁ ላ ኢላሀ ኢልላ አንተ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱከ ወረሱሉከ» (አላህ ሆይ! አንተ አምላክ መሆንህን ከአንተ በስተቀርም በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድም ባርያህና መልዕክተኛህ መሆናቸውን አንተን፣ የዐርሽህን ተሸካሚዎች፣ መላእክትህን፣ አንቢያኦችህን (ነብያቶችህን) እንዲሁም ሁሉንም ፍጡራኖችህን ምስክር አድርጌ አነጋሁ።)


«اللهم إني أمسيت…»


በምሽት ደግሞ «አሏሁመ ኢኒ አምሰይቱ» ( ... አስመስክሬ አመሸሁ።) እስከመጨረሻው (አራት ጊዜ)።


«لا إله إلا الله وحده لا شريك له. له الملك وله الحمد. وهو على كل شيء قدير»


«ላኢላሀ ኢለላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር።» (ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ተጋሪም የለውም። ንግስናም ምስጋናም የሚገባው ለእርሱ ብቻ ነው። እርሱ በነገሮች ላይ ሁሉ ቻይ ነው።)


(መቶ ጊዜ) ንጋት ወይም ምሽት ላይ።


«حسبي الله لا إله إلا هو عليه توكلت وهو رب العرش العظيم»


«ሐስቢየልላሁ ላ ኢላሀ ኢላ ሁው፤ ዐለይሂ ተወከልቱ፤ ወሁወ ረቡል ዐርሺል ዐዚም።» (አላህ በቂዬ ነው፤ ከእርሱ በቀር ሌላ በእውነት የሚመለክ የለም፤ በእርሱ ተመካሁ፤ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።)


(ሰባት ጊዜ)


«حسبي الله وكفى. سمع الله لمن دعاء ليس وراء الله مرمى»


«ሐስቢየላሁ ወከፋ፤ ሰሚዐልላሁ ሊመን ደዓ፤ ለይሰ ወራአ -ልላሂ መርማ።» (አላህ በቂዬ ነው። አላህ በዱዓ የሚጠራውን (የሚለምነውን) ሁሉ ይሰማል። ከአላህ በኋላ ግብ የለም /ከአላህ ሌላ የሚፈለግ ነገር የለም/ ።)


«سبحان الله وبحمده»


«ሱብሓነ'ላሂ ወቢሐምዲሂ።» (ጥራት እና ምስጋና ለአላህ ተገባው።)


(መቶ ጊዜ) ሲነጋ እና ሲመሽ። ወይም በሁለቱም ወቅት።


«أستغفر الله وأتوب إليه»


«አስተግፊሩላሀ ወአቱቡ ኢለይሂ» (አላህን ምህረቱን እጠይቀዋለሁ፤ ወደ እርሱም በፀፀት እመለሳለሁ።)


(መቶ ጊዜ።)


ለመጻፍ የገራልኝ ይህን ያክል ነው፤  ሌሎች የሚጠቀሙበት እንዲያደርገው አላህን እማጸነዋለሁ።


ጸሐፊ ሙሐመድ አስ'ሷሊሕ አል'ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው) ቀን 20-1-1418 ሂ



 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎ ...

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች።

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የ ...

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ...

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት