መጣጥፎች




*^* የፍቺ መብት *^*


ከሴቶች መሰረታዊ መብቶች ውስጥ ፍቺ


ይገኝበታል፡፡ ለዘላቂ ህይወት ሴት ከአንድ


ወንድ ጋር በጋብቻ ስትጣመር እና ጋብቻው


ሊሰምር ካልቻለ የመጨረሻው አማራጭ


መፍታት እና ከሚሆናት ሌላ ወንድ ጋር ዳግም


ጋብቻ መመስረት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን


ይህንን የማይቀበል ሲሆን ሴትም ብትፈታ


የተሰጣት አማራጭ ሳታገባ መኖር ነው፡፡


ስለፍቺ በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ መልኩ ትእዛዝ


ተላልፏል ፡-


‹‹ሚስትም ከባልዋ አትለያይ ብትለያይ ግን


ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፡፡››(1ኛ


ቆሮንቶስ 7፡10-11 )


ይህን ጥቅስ የእምነቱ አስተማሪዎች እንዲህ


በማለት ያብራራሉ፡- ‹‹በጠቅላላው ሰዎች


እንዲፈቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሆንም


አንዳንድ ጊዜ በራሳቸው ፍቃድ የሚፋቱ


ሰዎች ይኖራሉ ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚፋቱ


ከሆነ ማድረግ ያለባቸው ሳያገቡ መኖር


ወይም መታረቅ ነው፡፡(ወርቁወልደ ዮሐንስ


ክርስቲያናዊ ጋብቻ፤ ገጽ 123)


በሌላ ምዕራፍ ላይ መጽሐፍ‹‹ቅዱስ››


በዝሙት ምክኒያት ብቻ መፋታት (ፍቺ)


እንደሚቻልና ከዚህ ሌላ ምክንያት ተቀባይነት


እንደሌለው ደንግጓል፡፡


‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ ያለዝሙት ምክኒያት


ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሁሉ


ያመነዝራል የተፈታችውንም የሚያገባ


ያመነዝራል አላቸው፡፡(የማቴዎስ ወንጌል 19፡


‹‹ሴት በቧላ ህይወት የታሰረች ናት ››(1ኛ


ቆሮንቶስ 7፡39)


*^* ምንም እንኳ ኢስላም ለስኬታማ


ጋብቻና ጠንካራ ቤተሰብ ምስረታ የሚረዱ


መርሆች ያስቀመጠ ቢሆንም የሰው ልጅ ግን


ሁል ጊዜ በተወሰነላቸው ገደብና በተቀረጸላቸው


ተምሳሌት ይጓዛል የሚል እምነት የለም ፡


፡ ያለ መግባባት ሁከትና ግጭት ሊፈጠር


የሚችልበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ በባልና


ሚስት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አብረው


እንዲኖሩ የማያስችልና መለያየትን የተሻለ


አማራጭ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ለሁለቱም


ጾታዎች ደህንነት መለያየታቸው ባይወደድም


በመጨረሻ አማራጭነት ፍች አስፈላጊ ሆኖ


ይገኛል፡፡


ነገር ግን የክርስቲያን ሚሽነሪዎች እና


ኦሬንታሊስቶች ኢስላም በሴቶች ላይ ካለው


አቋም ጋር በተያያዘ የከፈቱትን ዘመቻ ከቅርብ


ጊዜ ወዲህ በሁለት ነጥቦች ማለትም በፍችና


ከአንድ በላይ ማግባት ላይ አተኩሯል፡፡


የሚገርመው ሁለቱም ኢስላም የሚኮራባቸው


አቋሞች ናቸው፡፡ አንዳንድ ሙስሊሞች


የነርሱን ተቀብለው በማስተጋባት እነዚህን


አጀንዳዎች ከቤተሰብና ከማህበረሰብ ችግሮች


ፈርጀው ያስተጋቧቸዋል ፡፡ አሁን አሁን


ደግሞ የታላቁን ኢስላምና የአንጸባራቂውን


ሸሪዓውን ልዕልና ለማጉደፍ ይጠቀሙባቸው


ይዘዋል፡፡ እውነታው ግን ኢስላም የደነገጋቸው


በሁለቱም ጾታዎች እንዲሁም በቤተሰብና


3


በኅብረተሰብ ሕይወት ውስጥ ለሚከሰቱ እጅግ


በርካታ ችግሮች መፍትሄ ይሆን ዘንድ ነው፡


፡ እውነተኛው ችግር የአላህን ሕግና ድንጋጌ


ካለመረዳት ወይም በአግባቡ ካለመተግበር


የሚመነጭ ነው፡፡ አንድን ነገር በተገቢው


መንገድ ጥቅም ላይ አለማዋል የከፋ ጉዳት


ሊያስከትል ይችላል፡፡


*^* ፍች ለምን? *^*


በኢስላም የሚደገፉት ፍቺዎች ሁሉም


አይደሉም ፡፡ እንዳንዱን ፍች ኢስላም


ይጠላዋል፡፡ ሌላኛውን ደግሞ እርም ያደርገዋል፡


፡ ፍችን ኢስላም እንዲታነጽ የሚጓጓለትን


ከታነፀም በኋላ እንዳይናጋ የሚንከባከበውና


ቤተሰባዊ ሕይወት መናድ ነውና፤ ያለጥንቃቄ


በዘፈቀደ እንዲፈጸም አይሻም ፡፡ ለዚህም


ነው በአቡዳውድ በተዘገበው በተከታዩ ሐዲስ


የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ያሉት፡-


‹‹ከአላህ ዘንድ የሚጠላ ሐላል ነገር ፍች


ነው፡፡››


ይህ ከመሆኑ አኳያ ቁርአን ባልንና ሚስትን


ማለያየትንና ማፋጀትን ከከሐዲያን ደጋሚዎች


እኩይ አድራጎት መፈረጁ አያስገርምም፡፡ አላህ


እንዲህ ይላል፡-


‹‹ከሁለቱም (ሰዎች) ባልንና ሚስትን


የሚለያዩትን (የድግምት ዕውቀት) ይማራሉ፡፡


››(ሱረቱ አል-በቃራህ 2፡102)


ኢስላም የደነገገው የፍች ሥርዓት በአካል


ላይ እንደሚደረግ አሳማሚ ቀዶ ጥገና ሊወሰድ


ይችላል፡፡ አካሉ ሲቀደድና ሲሰፋ፤ ከዚህም


አልፎ ተቆርጦ ሲጣል ቀሪውን የአካሉን ክፍል


ከበሽታ ለመፈወስ ሲል ማንም ጤነኛ ሰው


ሕመሙን መሸከም አይከብደውም ፡፡


እንደዚሁም በሁለት ተጋቢዎች መካከል


ጥልና አለመግባባት ሲነግስ፤ ለማስማማት


የተደረጉ ጥረቶች ሁሉ ሲከሽፉ፤ በዚህ ጊዜ


ፍች ብቸኛ አማራጭ ይሆናል፡፡ መድኃኒቱ


እርሱም ብቻ ነውና ቢመርም ይወሰዳል፡፡


‹‹ስምምነት ከጠፋ መለያየት ደግ ነው›› ይበላል


፡፡ ታላቁ ቁርአን እንዲህ ይላል፡-‹‹ከተለያዩም


(ከተፋቱ) አላህ ለሁሉም ከሲሳዩ ይለግሳል፡፡


አላህ (ችሮታው) ሰፊ፤ ጥበበኛ ነውና፡፡››(ሱረቱ


አል-ኒሳእ፤ 130)


የኢስላምን አቋም አዕምሮ ያጸድቀዋል፡


፡ ጥበብም ያፀድቀዋል፡፡ ከጥቅምም አኳያ


አወንታዊ ነው፡፡ በአንድ የሽርክና ተግብር


ላይ የተስማሙ ሁለት ሰዎች እርስ በርስ


የማይስማሙ፤ የማይጣጣሙና የማይተማመኑ


ሆነው እያለ ዘልዓለም ‹‹አንድ ላይ


ተቆራኝታችሁ ኑሩ›› ብሎ ማስገደድ ጤነኛ


አስተሳሰብ አይቀበለውም፡፡


4


እንዲህ ዓይነት ሰዎችን በሕግ ማስተሳሰር


ትልቅ ቅጣት ነው፡፡ ትልቅ ወንጀል ለፈፀመ


ሰው ካልሆነ ተገቢ ያልሆነ ቅጣት፡፡ ከዕድሜ


ይፍታህ እስራት የሚተናነስ አይደልም፡፡


የሚያሰቃይ የገሃነም ኑሮ ነው፡፡ በቀድሞው


ዘመን አንድ ጠቢብ እንዲህ ብለዋል፡-


‹‹ከመከራዎች ሁሉ ትልቁ መካራ


ከማትጣጣመውና ሁሌም ከማይለየህ ሰው ጋር


አብሮ መኖር ነው፡፡››


አቡ ጦዩብ አል-ሙተንቢ የተባለ ገጣሚ


የሚከተለውን ስንኝ ቋጥሯል፡-


ለጨዋ መከራና ጭንቁ፣


ከስቀይ ሁሉ ትልቁ ፣


ጠላቱ አብሮት እንደሚኖር ማወቁ።


ይህ ገጣሚ ‹‹ጭንቅ›› ያለው ከሳምንት


አንድ ቀን ወይም ለቀናት በቀን ውስጥም


ለሰዓት ወይም ለሰዓታት ብቻ ሊያገኘው


የሚችለውን ጓደኛውን በማስመልከት ከሆነ


ሁሌም ከአጠገቡ የማትጠፋ የትዳር ጓደኛ፤


የጎጆው ተጋሪስ ምን ልትሰኝ ነው?


*^* ቅድሚያ መስኩን ማጥበብ *^*


ኢስላም የፍቺን መጠን በከፍታ ሁኔታ


ሊቀንሱት የሚችሉ መርሆችን ድንጋጌዎችን


ያስቀመጠ ሲሆን፤ ከነዚህም መርሆችዎች


ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-


1) በትዳር ጓደኛ አመራረጥ ላይ ጥንቃቄ


ማድረግ፤ ከገንዘብ፤ ከስልጣንና ከውበት


ይልቅ ለዲንና ለስነምግባሩ ትኩረት መስጠት፡፡


ቡኻሪና ሙስሊም ባሰፈሩት ዘገባ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡-


‹‹ሴት ለአራት ነገሮች ሲባል ለጋብቻ


ትመረጣለች ፡፡ ለገንዘቧ፤ ለዘሯ፤ ለውበቷና


ለዲኗ፡፡ አደራ የዲን ባለቤት የሆነችዋን ምረጥ፡


፡››


2)ጋብቻ ከመፈጸሙ በፊት እጮኛን ማየት


ተገቢ ነው ፡፡ የትዳር ጓዳኛ ውበት አይቶ


ልብ መፍቀዱን ለማረጋገጥ ፡፡ ከጋብቻ በፊት


መተያየት መግባባትንና ፍቅርን ይጠነስሳል፡፡


ይህም በመሆኑ ነው የአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ)


ሴት ላጨ አንድ ባልደረባቸው ፡- ሂድና


እያት፡፡ በመካከላችሁ መግባባት እንዲፈጠር


ይጠቅማችኋል›› ያሉት፡፡(አህመድ፤ ዳረል


ቁጥኒ፤ ሐኪምና በይሃቂ ዘግበውታል)


ነብዩ ‹‹እያት›› በማለት የሰጡት ትእዛዝ


ማየት ግዴታ መሆኑን ባያመለክትም


እንደሚወደድ ግን ያስተምራል፡፡ ተመሳሳይ


መልእክት ያዘሉ ሌሎች ሀዲሶችም ተላልፈዋል፡


፡ ጃቢር ስላገቧት ባለቤታቸው ሁኔታ ሲናገሩ፡


- ‹‹እርሷን እንዳገባ የሚያስችለኝ እና የሚስበኝ


ነገር እስከማይ ድረስ በዛፍ እየተደበቅኩ አያት


ነበር፡፡


5


3) ሴቷና የቅርብ ዘመዶች (ወልዮች)


የሚመርጡት ባል መልካም ፤ ዲኑና ባህሪው


ያማረ እንዲሆን የሚያደርጉት ጥረትም ፍቺን


ለመቀነስ ይረዳል፡፡


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን አስመልክቶ እንዲህ


ብለዋል፡- ‹‹ዲኑና እና ስነምግባሩን የምትወዱት


ወንድ ልጃችሁን ከጠየቃችሁ ስጡት››


ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡


ቀደምት የሙስሊም ሊቃውንቶች እንዲህ


በማለት ይመክራሉ፡-


‹‹ልጅህን ዲኑና ስነ-ምግባሩ መልካም ለሆነ


ሰው ስጥ፡፡ ምክኒያቱም ከወደዳት ያከብራታል፤


ይንከባከባታል፡፡ ካልወደዳትም አይበድላትም፡


፡››


4) ለሴቷ ባሏን የመምረጥ መብት መሰጠቱም


ፍቺን ለመቀነስ አስተዋጽኦ አለው፡፡ከዚህ


ቀደም እንዳየነው ሴት ልጅ የማትፈልገውን


ወንድ እንድታገባ ማስገደድ ፈጽሞ አይፈቀድም


፡፡ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላልወደደችውና


ላልፈቀድችው ባል የተሰጠ ችን ልጅ ጋብቻ


ማፍረሳቸው ይታወቃል፡፡


5) የቅርብ ቤተሰቦቿም በጋብቻው


መስማማታቸው የሚወደድ መሆኑ


በመስፈርትነት ተቀምጧል ፡፡ ይህም ፍቺን


ይቀንሳል ፡፡ ሴት ልጅ ቤተሰቦቿ ያልወደዱትና


ያፈቀዱትን ጋብቻ እንድተፈጽም ለመከላከል


ይህ መስፈርት ጠቃሚ ነው፡፡ ከነርሱም ሐሳብና


ፈቃድ ከወጣች ይቆጡባታል፤ ያኮርፏታል፡


፡ እርሷም ከቤተሰቦቿ ትነጠላለች ፡፡ ጥሉ


በጋብቻ ሕይወቷ ውስጥ ያንጸባረቃል፡፡ መጥፎ


ተጽእኖም ያሳርፋል፡፡


6)በሴት ልጅ የጋብቻ ጉዳይ እናቷን


ማማከር ተገቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡


ጋብቻው በሁለቱም ወገኖች ፈቃድና ይሁንታ


እንዲጠነሰስ ከጠንካራ መሰረት ላይ እንዲታነጽ


፡፡


ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ሴቶቻችሁን በሴት


ልጆቻችሁ ጋብቻ ጉዳይ አማክሯቸው››


ማለታቸው ተዘግቧል።


7) ሚስትን በመልካም መተዳደርና


መንከባከብ ግዴት መሆኑ፤ የተጋቢዎች


መብቶችና ግዴታዎች በግልጽ መቀመጣቸው፤


የአማኝ ልቦናና ሕሊና የአላህን ሕግ ላለመጣስ


ጥንቃቄና የአላህ ፍራቻ ለጋብቻ ትልቅ


ዋስታናዎች ናቸው፡፡ ከእያንዳንዱ መብት


ተጓዳኝ ግዴታ አለ ፡፡ ሙዕሚን(አማኝ)


መብቱን ከመጠየቁ በፊት ግዴታዎቹን


መወጣት እንዳለበት ኢስላም ያስተምራል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) አንጸባራቂ በሆነው ቃሉ በሱረቱ


አል-በቀራህ 2፡228 እንዲህ ይላል፡-


‹‹(ከባሎቻቸው ሸሪዓው የሚፈቅደውን)


መልካም አያያዝና እንክብካቤ የማግኘት መብት


አላቸው፡፡››(ሱቱ አል-በቀራህ 2፡228)


(የአላህ ሱ.ወ ፍቃዱ ከሆነ የባል እና


ሚስት መብት በኢስላምና በክርስትና በሚል


ርዕስ ጊዜውን ጠብቆ በሰፊው የምንዳስሰው


ይሆናል!!! )


6


ባል ምንጊዜም ተጨባጩን መዘንጋት


እንደሌለበት ኢስላም አጽኖት ሰጥቶ


ያስተምራል፡፡ ከሚስቱ ምሉዕነትን


እንዳይጠብቅ ፤ ከድክመቶች በተጓዳኝ ጠንካራ


ጎኗን እንዲያስታውስ ይመክረዋል፡፡ እንዱ


ባህሪዋ ቢያስከፋው ሌላው ያስደስተዋል፡፡


በሀዲስም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸው


ተላልፏል፡-


‹‹አማኝ ወንድ አማንኝ ሴት ሙሉ


በሙሉ አይጥላ፡፡ አንድ ባህሪዋ ቢያስከፋው


ሌላኛው ያስደስተዋል፡፡››(አህመድና ሙስሊም


ዘግበውታል)


9) ባል ሚስቱን የመጥላት ስሜት


ሲያድርበት ለዚህ ስሜቱ ቶሎ እጅ እንዳይሰጥ


፤ እንዲያመዛዝን፤ ወደፊት ሁኔታዎች ወደ


ተሸለ ደረጃ ሊቀየሩና ሊስተካከሉ እንደሚችሉ


ተስፋ እንዲያደርግ እምነቱ ይመክረዋል ፡፡


ይህን አስመልክቶ አላህ ሱ.ወ በተከበረው ቃሉ


እንዲህ ይላል፡-


‹‹በመልካም ሁኔታ ያዟቸው ፡፡


ብትጠሏቸውም(በትእግስ አብራችኋቸው


ለመኖር ሞክሩ)፡፡ አላህ የጠላችሁትን ነገር


በርካታ መልካም ነገሮች ያደርግበት ይሆናልና፡


፡››(ሱረቱ አል-ኒሳእ 4፡19)


10) በተጋቢዎች መካከል አለመግባባት


ሲያይል እና የመለያየት አዝማሚያ ሲታይ


ኅብረተሰቡ ከባልም ከሚስትም ዘመዶች


በተውጣጡ ታማኝ የቤተሰብ ዳኞች


አማካኝነት ጣልቃ እንዲገባ እና የጠፈጠረውን


ችግር በጥበብ ለመፍታት እንዲጥር ኢስላም


ያስተምራል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


‹‹በመካከላችሁ አለመግባባት እንዳለ


ከተረዳችሁ ከርሱ ቤተሰብ የሆነነ ከርሷ ቤተሰብ


የሆነን ቤተሰብ ዳኞች ሰይሙ፡፡ እርቅን የሚሹ


ከሆነ አላህ ያስማማቸዋል፡፡››(ሱረቱ አል-ኒሳእ


4፡35)


*^*^ የኢስላም አስተምሮ ይህንን ይመስላል፡


፡ ኢስላም ቅድሚያ ፍቺ እንዳይከሰት መስኩን


አጥብቦታል ሙስሊሞች እነዚህን አስተምሮዎች


ቢተገብሯቸው ኖሮ ፍቺ በከፍተኛ ደረጃ በቀነሰ


ነበር *^*^


*^በኢስላም አስተምሮ መሰረት ፍች መቼ


እና እንዴት ይፈጸም ?*^*


**ኢስላም በተገኘ ወቅትና ሁኔታ ፍች


እንዲፈፀም አልፈቀደም፡፡ በቁርአንና በአዲስ


የተጠቀሰው ህጋዊ የፍች ስርዓት ወቅትንና


ሁኔታና ማገናዘብን ይጠይቃል፡፡ ሚስት


በወር አበባ ወቅት፣ ከወር አበባ ብትፀዳም


ግንኙነት ከፈፀመ በኃላ መፍታት ያልተፈቀደና


ያልተደነገገ /ቢድዓ/ እና ሐራም የፍች አፈፃፀም


7


ነው፡፡ በዚህ መልኩ የተፈፀመ ፍች ተቀባይነት


እና ተፈፃሚነት እንደሌለው ከፊል የህገ – ሸሪዓ


ጠበብት ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም አፈፃፀሙ


የአላሀንና የመልዕክተኛውን ፍቃድ የተከተለ


አይደለምና፡፡ በሀዲስ የሚከተለው ተላልፏል፡፡


“የኛ ፍቃድ ያልታከለበትን አንድ ተግባር


የፈፀመ ስራው ውድቅ ነው፡፡” ሙስሊም/


** አንድ ወንድ ፍች በሚፈጽምበት ወቅት


አዕምሮውን ያልሳተና በምርጫው መሆን


አለበት፡፡ አዕምሮውን ስቶ፣ ተገዶ ወይም


ህሊናውን የሚሸፍንና የማመዛዘመን ክህሎቱ


የሚያጠፋ ቁጣ ተቆጥቶ እያለ ፍች ቢፈጽም፣


ፍችው ተቀባይነት እንዳሌለው ተመራጭ


የሆነው የፊቅህ ጠበብት አቋም ይገልፃል፡፡


በሀዲስ የሚከተለው ተላልፏል፡፡


“በቁጣ ወቅት ወይም ተገዶ የተፈፀመ ፍች


ውድቅ ነው፡፡” /አቡ ዳውድና ኢብን ማጃህ/


“ኢግላቅ” የሚለውን የሐዲስ ቃል አቡ


ዳውድ “ቁጣ” ሲሉ ተርጉመውታል፡፡ ሌሎች


ደግሞ


“መገደድ” እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱም


ትርጉሞች ያስኬዳሉ፡፡


** ፍችውን የፈፀመው ከሚስቱ ጋር


ለመለያየት አስቦና ወስኖ መሆን አለበት፡፡


ፍችን መሐላ ማድረጉ በርሱ ዛቻ መስንዘሩና


ማስፈራራቱ ግን ተፈፃሚነትን ያሳጣዋል፡


፡ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው የህገ- ሸረዓ


ምሁራን ዕይታ ይህን ያመለክታል፡፡ ከፊል


የሰለፍ ምሁራን ይህን ዕይታ አራምደዋል፡፡


ኢማም ኢብነል ቀይም እና ሸይኻቸው ኢብን


ተይሚያህም ሚዛን የሚደፋው ሀሳብ ይህ


እንዳሆነ ተናግረዋል፡፡


** ከላይ የተዘረዘሩት የፍች አፈፃፀም


ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የሚቀረው ሰውየው


አስቦና ተጨንቆ ጉዳዩን በሚገባ አጥንቶና


አጢኖ ሊታገሰው ካልቻለው የጋብቻ ህይወት


ለመውጣት ብቸኛውና የተሻለው መንገድ


ፍች መሆኑን ካመነበት በኃላ የሚፈጽመው


ፍች ነው፡፡ ተከታዩ የኢብን ዐባስ ቃል ይህን


ያመለክታል፡-


“ፍች ተቀባይነት የሚኖረው ታስቦበት


ሲፈፀም ብቻ ነው፡፡” /ቡኸሪ/


*^ ከፍች በኋላ ያለው ሁኔታ በኢስላም


አስተምሮ ምን ይመስላል? *^*


** ፍች መፈፀም የጋብቻን ገመድ መልሶ


እንዳይቀጠል አድርጐ ከነጭራሹ አየበጥሰውም፡


፡ ቁርአን ፍች ለፈፀመ ሰው ሁለት የማሰቢያና


የማስተንተኛ ጊዜዎችን ይሰጣል፡፡ ተጋቢዎት


እየተፋቱ እንደገና የመጋባት ሁለት ዕድል


አላቸዉ፡፡ ከዚያ በኃላ ግን ሶስተኛ ፍች


ከተፈፀመ የመጨረሻና የመቆራረጫ ይሆናል፡፡


ሚስት ሌላ ወንድ አግብታ እስካልፈታች ድረስ


ዳግም በትዳር መኖር አይፈቀድላቸውም፡፡


ከዚህ ድንጋጌ አንፃር ሲታይ በአንድ


ቅጽበትና ቃል ሶስት ጊዜ መፍታትን መናገር


የቁርአንን አስተምህሮ የሚፃረረ ነው፡፡ ኢማም


ኢብን ተይሚያህ እና ተማሪያቸው ኢብነል


ቀይም ይህን አቋም በመረጃ አስደግፈው


አብራርተዋል፡፡ የበርካታ ዐረብ ሀገሮች የሸርዓ


8


ፍርድ ቤቶችም በዚህ አቋም በመስራት ላይ


ይገኛሉ፡፡


** ፍች ሴት ከባሏ የምታገኘውን ቀለብ


አያሳጣትም፡፡ በ”ዒዳ” ወቅት ሊቀልባት


ግድ ይላል፡፡ ባልም ከቤቷ ሊያስወጣት


አይፈቀድለትም፡፡ ከርሱ ቀረብ ብላ እንደትቆይ


ሸርዓው ያስገድደዋል፡፡ ይህ የሆነበት የፍቅር


ስሜት ዳግም እንዲያንሰራራ፣ ጥልና ብዥታ


ተገፎ ትዳርን የማደስ ሀሳብ ህያው እንዲሆን


ዕድል ለመስጠት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-


“አላህ ከዚህ /ፍች/ በኋላ አዲስ ሁኔታን /


ዳግም የመጣመርን ጉጉት ይፈጥር እንደሆነ


የምታውቀው ነገር የለምና፡፡” (ሱረቱ አል –


ጦላቅ፡ 1)


** ፍች ወንዱ የሴቷን የጥሎሽ ገንዘብ /


መህር/ እንዲያስቀር ወይም ያበረከተላትን


ስጦታ እንዲያስመልስ ዕድል ወይም ፍቃድ


የሚሰጥ አይደለም፡፡ አላህ(ሱ.ወ) ይህን


አስመልክቶ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡-


“እናንተ ባሎች፣ ለሚስቶቻችሁ


ከሰጣቸኃቸው ጥሎሽ /መህር/ ቅንጣት


ልትቀበሉ አይፈቀድላችሁም፡፡” (አል – በቀራህ


2:229)


** ቁሳዊ ድጋፍ የማግኘት መብት አላት፡


፡ የባልን አቅምና የህብረተሰቡን ተጨባጭ


ባገናዘበ መልኩ፡፡ አላህ(ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-


“የተፈቱ ሴቶች በ”መዕሩፍ” /የባልን


አቅም ግምት ውስጥ የከተተ/ የገንዘብ ድጐማ


ተደንግጐላቸዋል፡፡ ይህ /ድጐማ/ አላህን


በሚፈሩ ሰዎት ላይ በገዴታነት ፀና፡፡” (አል –


በቀራህ፡ 2:241)


ይህ ቁሳዊ ድጋፍ ሁሉንም በፍች ከባላቸው


የተለዩ ሴቶችን ያጠቃልላል፡፡ ድንጋግጌው


ሴቷ በፍች የሚደርስባትን የቀልብ ስብራት


ለመጠገን የታለመ ነው፡፡


** ባልም የፈታትን ሚስቱን ስም ማጥፋት፣


እርሷንም ሆነ ቤተሰቧን ማወክ አይፈቀድለትም፡


- አላህ(ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-


“ከዚያ በኋላ /ባል ሚስቱን/ በመልካም


ሁኔታ መያዝ ወይም በበጐ አኳኋን /


ሳይበድላትና መብቷን ቅንጣት ሳይደፈር


ማሰናበት ግድ ይሆንበታል፡፡” (አል – በቀራህ፡


2:229)


“በመካከላችሁ /ባለ ግንኙነት/ ችሮታን /


ከግዴታ በላይ መስጠት፣ ለሌሎች ጥቅም ሲሉ


የራስን ድርሻ መተውን/ አትዘንጉ፡፡”(አል –


በቀራህ፡ 2: 237)


*^* የኢስላም የፍች ስርዓት ይህን


ይመስላል፡፡ በሚፈለገው ጊዜ፣ ቦታ፣


መጠን፣ ጥሩ በሆነ የአፈፃፀም ስልትና


ለበጐ ዓላማ ብቻ የሚፈፀም ስርዓት ነው፡


፡*^*


9


** ከዚህ በፊት እንዳየነው በክርስትናው


ዓለም ካቶሊኮች ፍችን ከነጭራሹ እርም


አድርገዋል፡፡ ኦርቶዶክሶች ደግሞ ከዝሙት


ውጭ ባለ የትኛውም ምክንያት ፍች


እንዳይፈፀም አቅበዋል፡፡ መነሻቸውም፡-


“እግዚአብሔር ያጣመረውን የሰው ልጅ


አይፈታም” የሚል ነው፡፡


በአንፃሩ ሙስሊሞች፡- “አላህ በህጋዊ


ድንጋጌዎች መቁጠርም መምታትም ይችላል፡፡


” ድንጋጌዎቹም የሰውን ልጅ ጥቅም፣ ደህንነትና


ምቾት ያገናዘቡ ናቸዉ፡፡ የሰው ልጆችን ጥቅም


ከነርሱ ይበልጥ እርሱ ያውቃልና” የሚል ነው፡፡


** ክርስትና በፍች ላይ ያለውን አቋም


በርካታ ክርስቲያኖችን በህጉ ላይ እንዲያምፁ


አድርጓል፡፡ በመሆኑም አብዛኛዎቹ ክርስቲያን


ሀገሮች ፍችን በተመለከተ ሰው ሰራሽ ህጐችን


ለማጽደቅ ተገደዋል፡፡ እነዚህ ህጐቻቸው ፍችን


ኢስላም ያስቀጠመጣቸዉ አይነት ገደቦች፣


ግዴታዎችና የሞራል ደንቦች ሳይደረግባቸዉ


እንዳሻቸው እንዲፈጽሙ መብት ይሰጧቸዋል፡


፡ እናም ለተራና መናኛ ምክንያት ፍች ቢፈጽሙ


አያስገርምም፡፡ የጋብቻ ህይወታቸው ምንጊዜም


የመንኮታኮት አደጋ እንዳንዣበበበት ነው፡፡


*^* ፍቺ ለምን በወንዶች እጅ ሆነ ?*^*


** ምላሻችን፣ ወንዱ የቤተሰቡ ተንከባካቢና


የመጀመሪያ ተጠሪ ስለሆነ ነው፡፡ ጥሎሽ /


መህር/ የከፈለው እርሱ ነው፡፡ ከዚያ በኃላ


ያሉትን ኃላፊነቶች የሚወጣውም እርሱ ነው፡


፡ ቤተሰባዊዉ ህይወት በርሱ ትከሻ ላይ


ተገንብቷል፡፡ እናም ይህን ያህል ከፍተኛ ዋጋ


የከፈለበት ቤተሰብ እጅግ ፈታኝ እና አስቸጋሪ


ሁኔታ ካልተከሰተ በቀር እንዲሀም በቀላሉ


እንዲፈርስ አይፈቅድም፡፡


** የፍች ስልጣን ለፍርድ ቤት መስጠቱም


አግባብ አይደለም፡፡ ከጓዳ መውጣት፣ አደባባይ


መስማት የሌለባቸዉ የፍች ምክንያቶች


አሉ፡፡ ችሎት ቀርበው ዳኞች ሊሰማቸው፣


ፀሐይ ሊሞቋቸው፣ ጠበቆች ሊቀባበሏቸው፣


ጋዜጦችም የዓምድ ማድመቂያ ሊያደርጓቸው


የማይገቡ የጓዳ ጉዳዮች አሉ፡፡


በተጨማሪ ምዕራባዊያን የፍችን ስልጣን


ለፍርድ ቤት የሰጡ ቢሆንም ፍች አልቀነሰም፡፡


ፍች የሚፈልጉ ተጋቢዎችን ፍላጐት መገደብና


ፍችውን ማስቀረት አልሆነላቸውም፡፡


*^ * ታዲያ ሴቷ እንዴት ትገላገል?*^*


** ብዙ ሰዎችን የሚያሳስብ ጥያቄ አለ፡፡


ይኸውም፣ ፍች ከላይ ለተሰጡት ምክንያቶች


ሲባል – በወንድ እጅ ከተደረገ ሸረዓው ለሴቱ


ምን ዋስትና ሰጥቷል? ባሏ ፀባየ ከርዳዳ፣


ወይም ስነ ምግባር የሌለው ወይም መብቷን


በግልጽ የሚጋፋ ቢሆን፣ ኃላፊነቱን መወጣት


የሚያስችል አካላዊና ቁሳዊ አቅም ባይኖረው፣


ወይም በሌላ ምክንያት ከባሏ ጋር መኖር


ባትፈልግ በምን መንገድ መገላገል ትችላለች?


10


** የዚህ ጥያቄ ምላሹ ሸሪዓዉን የደነገገው


ጥበበኛ አምላክ ለሴት ልጅ በርካታ መውጫ


መንገዶችን አመቻችቶላታል፡፡ አንዱን ተጠቅማ


ጋብቻዋን ማፍረስ ትችላለች፡፡ እነርሱም፡-


1. በጋብቻ ውል ወቅት ፍች በእጂ ይሆን


ዘንድ መዋዋል ትችላለች፡፡ በአቡ ሐኒፋና


በኢማም አህመድ መዝህቦች ይህን ማድረግ


የተፈቀደ ነው፡፡ በሶሒሕ የሀዲስ ዘገባ


የሚከተለው ተላልፏል፡-


“ከውሎች ሁሉ ልትፈጽሙት ይበልጥ


የተገባው የጋብቻ ውል ነው፡፡” /ቡኸሪና


ሙስሊም/


2. “ኹልዕ” ሌላው መንገድ ነው፡፡ ይኸውም


ባሏን ያልወደደችና መፍታታ የፈለገች ሴት


ለርሷ የሰጠውን ጥሎሽና ሌላ ነገር ለባሏ


መልሳ ፍች ማስፈፀም ትችላለች፡፡ ፍችውን


የጠየቀችው፣ የጋብቻ ህይወቷን ማፍረስ


የከጀለችው እርሷ ሆና እያለ ኪሳራውን ባል


ብቻ እንዲሸከም መፍረድ ፍትሃዊ አይደለም፡


፡ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


“ሁለቱም ወገኖች የአላህን ህግጋት


ወሰኖች እንጥሳለን የሚል ስጋት ካደረባቸዉ


በቀር፣ እናንተ /ባሎች/ጥሎሽ /መህር ቅንጦት


ልትቅበሉ አይፈቀድላችሁም፡፡”(ሱረቱ አል –


በቀራህ 229)


* በሀዲስ እንዳተላለፈውም የሳቢት ቢንት


ቀይስ ሚስት ከነቢዩ ዘንድ ቀረበችና ባሏን እጅግ


እንደምትጠላው ነገረቻቸው፡፡ የአትክልት


ስፍራውን ትመልሽለታለሽን? አሏት፡፡ በጥሎሽ


/መህር/ ተቀብላው ነበር፡፡ “አዎ” አለች፡፡


መልዕክተኛውም ሳቢትን የአትክልት ቦታውን


እንዲረከብና ተጨማሪ ነገር እንዳይጠይቅ


አዘዙት፡፡ /ብኸሪ/


3. የቤተሰብ ዳኞች ጋብቻውን ማፍረስ


ይችላሉ፡፡ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


“በመካከላቸው አለመግባባት እንዳለ


ከተረዳችሁ ከርሱ ቤተሰብ የሆነን ከርሷም


ቤተሰብ የሆነን የቤተሰብ ዳኞች ሰይሙ፡


፡ እርቅን የሚሹ ከሆነ አላህ ያስማማቸዋል፡


፡” (ሱረቱ አን -ኒሳእ፡ 35)ቁርአን የቤተሰብ


ሽማግሌዎችን “ዳኞች” በማለት መሰየሙ


የመፍረድ ስልጣን እንዳላቸው ያመለክታል፡


፡ ከሶሐቦች አንዱ ለቤተሰብ ዳኞች እንዲህ


ብሏቸዋል፡- “ማስማማት ከፈለጋችሁ


አስማሟቸው ካልፈለጋችሁም አለያዩዋቸው፡፡”


4. ባል ወሲብ መፈፀም የሚያስችለው


አካላዊ ነውርና ድክመት ካለበትም ሚስት


ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ዳኛው ጋብቻውን


እንዲያፈርስ ማድረግ ።



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎ ...

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች።

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የ ...

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ...

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት