ልብስ በኢስላም
አንድ ሙእሚን ከሰዎች ጋር ለመደባለቅና ሠላትን ለመስገድ የሚለብሰው ልብስ፣ የሚያምርና ንጹህ መሆን አለበት፡፡
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹የአደም ልጆች ሆይ (ሃፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ
ያዙ፡፡›› (አል አዕራፍ 31)
አላህ (ሱ.ወ)፣ የሰው ልጅ በአለባበሱና በይፋዊ መገለጫው እንዲቆነጃጅ የሚያዘው ሕግን ደንግጓል፡፡ ይህ በራሱ
የአላህን ጸጋ ይፋ ማድረግ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የአላህን ጌጥ ያችን ለባሮቹ የፈጠራትን ከሲሳይም
ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው? በላቸው እርሷ በትንሳኤ ቀን ለነዚያ ላመኑት ብቻ ስትኾን በቅርቢቱ ሕይወት
ተገቢያቸው ናት፡፡ በላቸው እንደዚሁ ለሚያውቁ ሕዝቦቹ አንቀጾችን እናብራራለን፡፡›› (አል አዕራፍ 32)
ልብስ ብዙ ጉዳዮች ይፈጸሙበታል፡
የተወሰኑ የሰውነት ክፍሎችን ከእይታ ይሸፍናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የአደም ልጆች ሆይ ሃፍረተ ገላችሁን
የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፡፡›› (አል አዕራፍ 26)
ገላን ከሙቀትና ከውርጭ፣ እንዲሁም ከጎጂ ነገሮች ይጠብቃል፡፡
ብርድና ሙቀት ተለዋዋጭ የአየር ንብረቶች ናቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ የልብስን ገጽታ በማስመልከት እንዲህ
ብሏል፡- ‹‹ሐሩርንም (ብርድንም) የሚጠብቋችሁን ልብሶች፣ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች
ለናንተ አደረገላችሁ፡፡እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በናንተ ላይ ይሞላል፡፡›› (አል ነሕል 81)
ልብስህ
185
> በልብስ ዙሪያ
ኢስላም ተፈጥሯዊ ሃይማኖት ነው፡፡ በመሆኑም
የሰዎችን አኗኗር አስመልክቶ የተደነገጉት ሕጎች በሙሉ
ከተፈጥሮ ጋር የሚስማሙና ከጤናማ አዕምሮ ጋር
የሚጣጣሙ ናቸው፡፡
የሙስሊም አለባበስና የተፈቀዱ መቆነጃጃዎች
ኢስላም የሰው ልጅን አለባበሰ የተገደበ
አላደረገውም፡፡ ድንበር ማለፍ የሌለባቸው ከሆነና
ለተፈለጉበት ዓላማ መዋል የሚችሉ እስከሆኑ
ድረስ፣ ሁሉም የልብስ ዓይነቶች ሕጋዊ መሆናቸውን
ያጸድቃል፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ በዘመኑ የነበሩ አልባሳትን
ለብሰዋል፡፡ ሰዎች የተወሰኑ ልብሶች ብቻ እንዲለበሱ
አላዘዙም፡፡ እንዳይለበሱ የከለከሉት ውስን ልብስም
የለም፡፡ የከለከሉት በአለባበስ ዙሪያ ያሉ የተወሰኑ
ገጽታዎችን ነው፡፡
በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ የሁሉም ነገር መሰረቱ
የተፈቀደ ነው፡፡ በማስረጃ ካልሆነ በስተቀር እርም
ነው ማለት አይቻልም፡፡ ልብስ ደግሞ ከነዚህ ጉዳዮች
መካከል አንዱ ነው፡፡ አምልኮ ግን የዚህ ተቃራኒ
ነው፡፡ ማንኛውም ዓይነት አምልኮ መሰረቱ የተከለከለ
ነው፡፡ በማስረጃ ካልሆነ በስተቀር የተፈቀደ ወይም
ሕጋዊ አይሆንም፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ያለማባከንና
ያለኩራት ብሉ፣ መጽውቱ፣ ልበሱ፡፡›› (አል ነሳኢ
2559)
> ኢስላም ልብስን በተመለከተ፣
መለበስ አለበት ብሎ የገደበው
ወይም የወሰነው ልብስ የለም፡
፡ በላጩና የተሻለው፣ በኢስላም
የተፈቀደና የሀገሬው ነዋሪዎች
የሚለብሱት የልብስ ዓይነት ነው፡፡
የተከለከሉ አልባሳት
አንድ ሙስሊም ሀፍረተ ገላውን በልብስ የመሸፈን
ግዴታ አለበት፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡
- ‹‹ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም
በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፡፡›› (አል አዕራፍ 26)
ኢስላም ለወንዶችም ለሴቶችም የሀፍረተ ገላን ገደብ
አስቀምጧል፡፡ የወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ ከእንብርቱ እስከ
ጉልበቱ ሲሆን፣ ትልቁ ሀፍረተ ገላው ሁለት ብልቶቹ
ናቸው፡፡ እነኚህ ሁለት ብልቶች፣ ለሚስት ወይም እንደ
ሕክምና እና መሰል ጉዳዮች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ
ካልሆነ በስተቀር ለማንም ማሳየት አይፈቀድም፡፡ አንድ
ሠሓቢይ፣ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ሀፍረተ ገላ በጠየቃቸው ጊዜ
እንዲህ ብለውታል፡- ‹‹ሀፍረተ ገላህን፣ ለባለቤትህ ወይም
በቁጥጥርህ ስር ላሉ ባሮች ካልሆነ በስተቀር ከማጋለጥ
ጠብቅ፡፡››
ሠሓቢዩም፡ «አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ፣ ሰዎች
ከፊሉ ከከፊሉ ጋር ተደበላልቀውና ተቀላቅለው የሚኖሩ
ከሆነስ?» አላቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
አሉት፡- ‹‹አንድም ሰው እንዳያይብህ ማድረግ እስከቻልክ
አይይብህ፡፡›› አሉት
ሠሓቢዩም በማስከተል፡- «እሺ አንዳችን ብቻውን
ከሆነስ?(እርቃኑን ቢሆንስ)» በማለት ጠየቀ፡፡ ነቢዩም
(ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹አላህ ከሰዎች የበለጠ ሊታፈር ይገባል፡፡›› አሉት
(አቡ ዳውድ 4017)
1
ልብስህ
186
ሴት ልጅ፣ ለወንዶች እይታ በምትጋለጥበት ወይም
ወንዶች ፊት ለፊት ስትሆን፣ ከመዳፎቿና ከፊቷ በስተቀር
ሰውነቷ በጠቅላላ ሀፍረተ ገላዋ ነው፡፡ ይህ ሴቶችን
ከማናቸውም ክብራቸውን ከሚያጎድፍና በነርሱ ላይ
አደጋን ከሚጋርጥ ነገር የሚጠብቅ ነው፡፡
ኢስላም፣ በፈቀደበት አጋጣሚ ላይ ካልሆነ በስተቀር
ለባዕድ (አጅነቢ) ወንዶች ምንም ዓይነት የገላዋን ክፍል
መግለጥና ለእይታ ማጋለጥ አይፈቀድላትም፡፡ ነገር ግን
የቅርብ ተጠሪዎቿ (መሓሪሞቿ) ፊት ለፊት በተለምዶ
መገለጥ ወይም መታየት ያለበት የሆነን ገላዋን ተገልጣ
መታየት ትችላለች፡፡ ባሏ ግን ለርሱም ሆነ ለርሷ የፈለጉትን
መመልከትና በሱም መርካትና መደሰት ይችላሉ፡፡ አላህ
(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤
እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡›› (አል በቀራ 187)
የገላን ቅርጽ የሚያወጣ የተወጣጠረ ልብስም ሆነ
ከስሩ ያለን ገላ ገልጦ በሚያሳይ ስስ ልብስ መሸፈን
አይቻልም፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ ሀፍረተ ገላውን የሚያሳይ
ስስ ልብስ በሚለብስ ሰው ላይ የዛተው ለዚህ ነው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹ሁለት ዓይነት ሰዎች የእሳት ጓዶች
ናቸው፡፡›› ካሉ በኋላ ‹‹ለብሰው የተራቆቱ ሴቶች፡፡››
በማለት አንደኛውን ጠቅሰዋል፡፡
በሁለቱ ጾታዎች መሐል መመሳሰልን የሚፈጥር
ይሀህ ሴቶች ብቻ የሚለብሷቸውን አልባሳት
በመልበስ ወንዶች ከሴቶች ጋር መመሳሰላቸውንና
እንዲሁም ሴቶች በወንዶች መመሳሰላቸውን የሚገልፅ
ነው፡፡ ይህ ከከባባድ ወንጀሎች ውስጥ የሚፈረጅ
እርም ወይም ክልክል ነው፡፡ በአካሄድ፣ በንግግርና
በመሳሰሉት መመሳሰልም በዚሁ ስር የሚካተት
ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሴቶችን ልብስ የሚለብስን
ወንድ እንዲሁም የወንዶችን ልብስ የምትለብስ ሴትን
ተራግመዋል፡፡ (አቡ ዳውድ 4098)
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከወንዶች
መካከል በሴቶች የሚመመሳሰሉትን፣ ከሴቶች
መካከልም በወንዶች የሚመሳሰሉትን
ተራግመዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 5546)
እርግማን ማለት ከአላህ እዝነት መባረርና
መራቅ ነው፡፡ ኢስላም የወንድ ባህሪና ውጫዊ
መገለጫዎቹ፣ የርሱ ብቻና ከሴቶች የሚለዩት
እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ ሴቶችም እንዲሁ፡፡
ካልተበረዘ ተፈጥሯዊ ስርዓትና ጤናማ አዕምሯዊ
እይታ ጋር የሚስማማውም ይሄው ነው፡፡
ከካሃዲያን ልዩ መገለጫ ጋር የሚመሳሰለል ልብስ
እንደ ባሕታውያንና ካህናት ልብሶች ዓይነት የተወሰነ
ሃይማኖት መገለጫ ወይም አርማ የተደረጉ አልባሳትና
የመሳሰሉት የተከለከሉ ናቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከሕዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ
ከነርሱ ነው፡፡›› (አቡ ዳውድ 4031) የሃይማኖት
ማንጸባረቂያ አርማ ያለባቸው አልባሳትም በዚሁ
ስር የሚካተቱ ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ መመሳሰል፡
የአቋም ድክመት፣ በራስ አለመተማመንና እርሱ
በእምነት እርግጠኛ አለመሆንን የሚያስረዳ ነው፡፡
አንድ ሙስሊም፣ ከከሃዲያን መካከል አብዛኞቹ
የሚለብሱትና የሚያዘወትሩት ቢሆንም፣ በሀገሩ ላይ
በሰፊው ሕዝብ የሚለበስን ልብስ መልበሱ መመሳሰል
አይባልም፡፡ ምክንያቱም፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኢስላማዊው
ድንጋጌ ከተከለከለው ውጭ የቁረይሽ አጋሪያን ይለብሱት
የነበረውን የልብስ ዓይነት ይለብሱ ነበር፡፡
> ከካሃዲያን ጋር የሚያመሳስልን ወይም ከኢስላም ውጭ ያሉ
ሃይማኖቶችን አርማ በላዩ ላይ ያዘለን ልብስ መልበስ ክልክል
ነው፡፡
ልብስህ
187
ኩራትና መኮፈስን የሚያንጸባርቅ አለባበስ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በቀልቡ ውስጥ
የቅንጣትን ክብደት ያክል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት
አይገባም፡፡›› (ሙስሊም 91)
ኢስላም ኩራትና መኮፈስን የሚፈጥር ከሆነ ወንዶች
ልብሳቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች በመልቀቅ
እንዳይጎትቱ ከልክሏል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
ብለዋል፡- ‹‹በትዕቢት ተሞልቶ ልብሱን የጎተተ ሰው
የትንሳኤ ቀን አላህ አይመለከተውም፡፡›› (አል ቡኻሪ
3465 ሙስሊም 2085)
ለታዋቂነት የሚጋብዝ ልብስም ተከልክሏል፡፡
አንድ ሰው በመልበሱ ሰዎች የሚገረሙበትና
የሚደነቁበት፣ ስለሱ የሚያወሩለት ፣በይዘቱ ወይም
በመልኩ ወይም እሱን የለበሰ ሰው በሚያሳየው የኩራትና
የትዕቢት ስሜት ምክንያት የሚሸማቀቁበት የአለባበስ
ዓይነት ወይም ልብስ የተከለከለ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በዱንያ ላይ የታዋቂነት ልብስን የለበሰ
ሰው፣ አላህ (ሱ.ወ) በትንሳኤ ቀን የውርደት ልብስን
ያለብሰዋል፡፡›› (አህመድ 5664 ኢብኑ ማጃህ 3607)
ሐርነት ወይም ወርቅነት ያለው ከሆነ ለወንዶች
የተከለከለ ነው፡፡
ኢስላም ሁለቱንም በወንዶች ላይ እርም
አድርጓል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹እነኚህ ሁለቱ በወንድ ሕዝቦቼ ላይ እርሞች ናቸው፤
ለሴቶቻቸው ደግሞ የተፈቀዱ ናቸው፡፡›› (ኢብኑ
ማጃህ 3595 / አቡ ዳውድ 4057)
በወንዶች ላይ እርም የተደረገው፣ በሐር ትል የሚመረተው
የተፈጥሮ ሐር ነው፡፡
ማባከንና ማዝረክረክ ያለበት፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማባከንና ኩራት
በሌለበት ሁኔታ ብሉ መጽውቱ ልበሱ፡፡›› (አል ነሳኢ
2559)
ይህ እንደሁኔታው ይለያያል፡፡ ባለሃብት፣ ድሃ ሊገዛው
የማይገባውንና የማይችለውን የልብስ ዓይነት የመግዛት
መብት አለው፡፡ ይህም ካለው ሃብትና ገቢ፣ እንዲሁም
ኢኮኖሚያዊ ደረጃ አንጻር የሚታይ ይሆናል፡፡ አንድ ልብስ
ለድሃ ሰው ማባከን ተብሎ ለሃብታም ግን ማባከን ላይባል
ይችላል፡፡
> ማባከን በአለባበስም የተከለከለ ነው፡፡ ይሁን እንጂ
እንደየግለሰቡ የቀን ገቢና የተገቢነት ደረጃ ይለያያል፡፡
ቤተሰብህ
10
ኢስላም ቤተሰባዊ ሕይወት እንዲጸናና እንዲረጋ፣ እንዲሁም
ቤተሰብን ከሚያበላሹና ከሚያፈርሱ ነገሮች በመጠበቅና
በመከላከል ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባጠቃላይ፣ አንድ
ቤተሰብ ካማረና ከተስተካከለ የተቀናጀ ግለሰባዊና ማህበረሰባዊ
ዋስትናዎችን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
የምዕራፉ ማውጫ
ቤተሰብ በኢስላም ውስጥ ያለው ስፍራ
ሴት በኢስላም ውስጥ ያላት ክብርና ደረጃ
ኢስላም ልዩ ትኩረት የሰጣቸው ሴቶች
በሁለቱ ፆታዎች መሐከል መጣረስ የለም
ከወንድ አንጻር የሴት ዓይነቶች
በባዕድ ወንዶችና ሴቶች መሐከል ለሚኖር ግንኙነት የተቀመጠ መመሪያ
የሂጃብ -የሴቶችኢስላማዊ አለባበስ- ገደብ
ጋብቻ በኢስላም
የባልና የሚስት መብቶች
ከአንድ በላይ ሚስቶች ማግባት
ፍቺ
የወላጆች መብት
የልጆች መብት
ቤተሰብህ
190
> ቁርኣን በባልና በሚስት መሐከል ያለን እርካታ፣ ፍቅርና
መተዛዘን ከታላላቅ ጸጋዎች መድቦታል፡፡
የሚከተሉት ጉዳዮች ኢስላም ለቤተሰብ ልዩ እንክብካቤና
እገዛ ማድረጉን በግልጽ ያሳያሉ፡-
ኢስላም በጋብቻ ጅማሬና በቤተሰብ ምስረታ
ላይ ልዩ እይታ አለው፡፡ በመሆኑም ከስራዎች
ሁሉ የላቀ ተግባር ከመሆኑም ባሻገር፣
የመልክተኞች ፈለግ እንዲሆንም አድርጎታል፡
፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነገር
ግን እኔ እጾማለሁ እፈታለሁም፤ እሰግዳለሁ
አሸልባለሁም፤ ሴትም አገባለሁ፡፡ ከኔ ፈለግ
የወጣ ከኔ አይደለም፡፡››
(አል ቡኻሪ 4776 /ሙስሊም 1401)
• ቁርኣን ከታላላቅ ተዓምራትና ጸጋዎች ጎራ
ከቆጠራቸው ነገሮች አንዱ አላህ (ሱ.ወ) በባልና
ሚስት መሐከል ፍቅርን እዝነትንና እርካታን
ማድረጉን ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
‹‹ለናንተም ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ
ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን
ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ
ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አልሉ፡፡›› (አል
ሩም 21)
• ጋብቻን ገር ማድረግ፣ ለማግባት የሚፈልግም ሰው
ነፍሱን ከዝሙት እንዲጠብቅ መረዳትና መታገዝ
እንዳለበት ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አላህ ሦስት ዓይነት ሰዎችን
ለመርዳትና ለማገዝ በራሱ ላይ ግዴታ አድርጓል፡፡
›› አሉና ከነሱ መካከል፣ ‹‹ጥብቅነትን ፈልጎ ጋብቻን
የፈፀመን ሰው›› ጠቅሰዋል፡፡ (አል ቲርሚዚ 1655)
• ወጣቶችን ገና በአፍላ ዕድሚያቸውና ባልተነካ
ጉልበታቸው ላይ ሳሉ ጋብቻን እንዲፈፅሙ አዟል፡፡
ምክንያቱም ጋብቻ ለነሱ መርጊያቸውና መርኪያቸው
ስለሆነ ነው፡፡ ለፍቶት ስሜታቸውና ፍላጎታቸው
ትክክለኛ መፍትሄም ነው፡፡
1
ኢስላም ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ወንድም
ሆነ ሴት ልዩ ክብር ሰጥቷል፡፡
ኢስላም ልጆችን የመንከባከብና በማሳዳግ ጉዳይ
በእናትና በአባት ላይ ከባድ ኃላፊነት ጥሏል፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር፣ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ
ሰምቻቸዋለሁ ማለታቸው ተላልፏል፡- ‹‹ሁላችሁም
እረኞች ናችሁ፤ ማናችሁም ከሚጠብቀው ይጠየቃል፡
፡ አንድ መሪ እረኛ ነው፤ በጥበቃው ስር ስላሉት
ሁሉ ተጠያቂ ነው፡፡ አባወራ በቤተሰቡ ላይ እረኛ
ነው፤ በርሱ ስር ስላሉት ሁሉ ተጠያቂ ነው፡፡ ሴትም
በባሏ ቤት ውስጥ እረኛ ነች፤ በርሷ ስር ስላሉት ሁሉ
ተጠያቂ ነች፡፡ ባሪያ በአሳዳሪው ንብረት ላይ እረኛ
ነው፡፡ በርሱ ስር ስላሉት ሁሉ ተጠያቂ ነው፡፡›› (አል
ቡኻሪ 853 /ሙስሊም 1829)
ኢስላም ለአባቶችና ለእናቶች ክብር በመስጠትና
ደረጃቸውን በመጠበቅ፣ እንዲሁም እስከ ህልፈተ
ሕይወታቸው ድረስ እነርሱን መንከባከብና
ትዕዛዛቸውን መፈፀምን አስመልክቶ ልዩ ትኩረት
ቸሯል፡፡
ወንድ ወይም ሴት ልጅ፣ ምንም ያህል ትልቅ ሰው
ቢሆኑም ለወላጆቻቸው ታዛዥ የመሆንና ለነሱ በጎ
የመዋል ግዴታ አለባቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ይህንን
ጉዳይ ከርሱ አምልኮ ጋር አቆራኝቶ ጠቅሶታል፡
፡ እነርሱ ላይ በንግግርና በተግባር ድንበር ማለፍን
ከልክሏል፡፡ በነሱ መናደዱን የሚመለክትን ቃል ወይም
ድምፅ ማሰማትንም ሳይቀር ከልክሏል፡፡ ‹‹ጌታህም
(እንዲህ ሲል) አዘዘ፤ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤
በወላጆቻችሁም መልካምን ስሩ፤ በአንተ ዘንድ ኾነው
2
3
> ቤተሰብ በኢስላም ውስጥ ያለው ስፍራ
ቤተሰብህ
191
> ኢስላም ለእናትና ለአባት ክብር የመስጠትን መሰረት ጥሏል፡፡
> ሴት በኢስላም ውስጥ ያላት ስፍራ
ኢስላም ሴት ልጅን እጅግ በጣም አክብሯታል፡፡
ለወንዶች ባሪያ ከመሆንም ነፃ አውጥቷል፡፡ ክብርና
ደረጃ የሌላት ውዳቂና ርካሽ ከመሆንም አድኗታል፡፡
ከሴት ልጅ ክብር ጋር ተያያዥነት ካላቸው ኢስላማዊ
ድንጋጌዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ
አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም፤ ለነርሱም መልካምን
ቃል ተናገራቸው፡፡›› (አል ኢስራእ 23)
ኢስላም የወንድም ሆነ የሴት ልጆችን መብት
እንድንጠብቅ አዟል፡፡ በመካከላቸው በወጪም
ሆነ በይፋ በሚታዩ ጉዳዮች ላይ ፍትሃዊ መሆንም
ግዴታ ነው፡፡
ኢስላም በአንድ ሙስሊም ላይ ዘመድናን
የመቀጠል ግዴታ ጥሎበታል፡፡ ይህ ማለት
በእናቱም ሆነ በአባቱ በኩል ያሉትን ዘመዶቹን
ዝምድና በመቀጠልና ለነርሱ በጎ በመዋል
ይገለፃል፡፡
ወንድሞቹ፣ እህቶቹ፣ አጎቶቹ፣ አክስቶቹና ልጆቻቸው
እዚህ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ለነርሱ መልካም መስራት፣
ከታላላቅ ወደ አላህ መቃረቢያዎችና ታዛዥነትን
መግለጫ መንገዶች መካከል ቆጥሮታል፡፡ ዝምድናቸውን
ከመቁረጥ፣ ወይም ክፉ ነገር በነርሱ ላይ ከመፈፀም
እንድንርቅ አስጠንቅቋል፡፡ ይህን ማድረግን ከከባባድ
ወንጀሎች ፈርጆታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
- ‹‹ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም፡፡›› (አል ቡኻሪ
5638 /ሙስሊም 2556)
4
5 • ኢስላም ለሴት ልጅ ፍትሃዊ በሆነ ክፍፍሎሽ የውርስ
ድርሻዋን ሰጥቷል፡፡ በአንዳንድ ስፍራ ከወንድ ጋር
እኩል ታገኛለች፡፡ በአንዳንድ ስፍራ ደግሞ ድርሻዋ
ከወንዱ ይለያል፡፡ ይኸውም ለሟች ባላት ቅርበት፣
እንዲሁም ካለባት ኃላፊነትና ወጪ አንጻር የሚወሰን
ነው፡፡
• በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ወንድና ሴትን እኩል
አድርጓቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ማንኛውም ገንዘብ
ነክ እንቅስቃሴ አንዱ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
ብለዋል፡- ‹‹ሴቶች የወንዶች ክፋይ ናቸው፡፡›› (አቡ
ዳውድ 236)
• ኢስላም ለሴት ልጅ ባሏን የመምረጥ ነፃነት ሰጥቷል፡፡
ልጆችን የማሳደግ ትልቅ ኃላፊነት ደግሞ ጥሎባታል፡
፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሴት ልጅ በባሏ
ቤት ውስጥ ጠባቂ ነች፤ ከምትጠብቀው ነገር ተጠያቂ
ነች፡፡›› (አል ቡኻሪ 853 / ሙስሊም 1829)
• ስሟና በአባት የመጠራት ክብሯ እንዲቆይ
አድርጎላታል፡፡ ከጋብቻ በኋላም በአባት መጠራቷ
ይቀጥላል፡፡ ምን ጊዜም በአባቷና በቤተሰቦቿ
መጠራቷም ይዘልቃል፡፡
• ወጪያቸውን መሸፈን ከሚኖርበት ሴቶች መካከል
ከሆነች ማለትም ሚስቱ እናቱ ወይም ሴት ልጁ
ከሆነች፣ ኢስላም በወንዱ ላይ እሷን የመጠበቅና
ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ ጥሎበታል፡፡
• የቅርብ ዘመድ ባትሆንም፣ ረዳት የሌላትን ደካማ
ሴት መርዳትና ማገዝ ልዩ ክብርና ደረጃ የሚሰጠው
መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶታል፡፡ እሷን ለመርዳትና
ለማገዝ መሯሯጥ አላህ ዘንድ ትልቅ ክብር ያለው
ተግባር መሆኑን በመግለጽ አነሳስቷል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና
የችግረኞችን ጉዳይ ለመፈፀም የሚሯሯጥ ሰው፣ ልክ
በአላህ መንገድ ላይ ትግል እንደሚያደርግ፣ ሌሊት
ተነስቶ ሳይታክት እንደሚሰግድና፤ ጾሞ እንደማያፈጥር
ሰው ነው፡፡›› (አልቡኻሪ 5661 / ሙስሊም 2982)
ቤተሰብህ
192
ኢስላም ልዩ ትኩረት እንዲቸራቸው ያደረጋቸው
ሴቶች
እናት፡ አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ) የሚከተለውን ሐዲስ
አስተላልፈዋል፡፡ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ
መጣና፣ አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ ከሰዎች ሁሉ
በበለጠ ጓደኝነቱን ወይም ግንኙነቱን ልጠብቅለት የሚገባ
ማን ነው? አላቸው፡፡ እሳቸውም፡ ‹‹እናትህ›› አሉት፤
ከዚያስ? አላቸው፤ ‹‹ከዚያም እናትህ›› አሉት፤ ከዚያስ?
አላቸው፤ ‹‹አሁንም እናትህ›› አሉት፡፡ ለአራተኛ ጊዜ፡
ከዚያስ? አላቸው፣ ‹‹ከዚያማ አባትህ ነው፡፡›› አሉት፡፡
(አል ቡኻሪ 5626 / ሙስሊም 2548)
ሴት ልጅ፡ ዑቅበቱ ኢብኑ ዓሚር(ረ.ዐ) ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡ ‹‹ሦስት ሴት ልጆች
ኖረውት፤ ስለነርሱ ትዕግስት አድርጎ፣ ጥሮ ግሮ ከላቡ
ውጤት ያበላቸው፣ ያጠጣቸውና፣ ያለበሳቸው ሰው፣
የትንሳኤ ቀን ከእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል፡፡›› (ኢብኑ
ማጃህ 3669)
ሚስት፡ እመት ዓኢሻ(ረ.ዐ)፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡- ‹‹በላጫችሁ ለቤተሰቦቹ
መልካም የሆነው ነው፡፡ እኔ ለቤተሰቦቼ መልካማችሁ
ነኝ፡፡›› (አል ቲርሚዚ 3895)
በኢስላም የወንድና የሴት ግንኙነት የመደጋገፊያ
ግንኙነት ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ሙስሊም
ማህበረሰብን በመገንባት ላይ የሚዘጉት ክፍተት
ወይም ቀዳዳ አላቸው፡፡
በሁለቱ ፆታዎች መካከል ሽኩቻ የሚፈጥር ነገር
የለም፡፡
በአንዳንድ ያልሰለጠኑ ማህበረሰቡች ውስጥ እንደታየው፣
በወንድና በሴት መካከል የተደረጉት ሽኩቻዎች፣ በወንዱ
በሴት ላይ ፈላጭ ቆራጭ መሆን፣ አለያም ደግሞ በሴቷ
ከተፈጥሯዊ ባህሪ ማፈንገጥና ከአላህ ሕግጋት ውጭ
መሆን ይጠናቀቃል፡፡
ይህ ደግሞ ከአላህ ሕግጋት ፍፁም በመራቅ እንጂ
ሊከሰት አይችልም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-
‹‹አላህም ከፊላችሁን በከፊላችሁ ላይ በርሱ ያበለጠበትን
ጸጋ አትመኙ፤ ለወንዶች ከሰሩት ስራ ዕድል አላቸው፤
ለሴቶችም ከሰሩት ስራ ዕድል አላቸው፤ አላህንም
ከችሮታው ለምኑት አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡››
(አል ኒሳእ 32)
በኢስላም ሁለቱም ፆታዎች እራሱን የቻለ ልዩ ተሰጥኦ፣
ኃላፊነትና ክብር አላቸው፡፡ ሁሉም የአላህን ችሮታና
ውዴታ ለማግኘት ይጥራል፡፡ ኢስላማዊው ድንጋጌ፣
ለሙስሊም ማህበረሰብ ብሎም ለሰው ዘር በሙሉ እንጂ
ለወንዶች ወይም ለሴቶች ሲባል የተደነገገ አይደለም፡፡
በኢስላም እይታ መሰረት፣ በሁለቱ ፆታዎች መሐከል
ያ ለሽኩቻ ቦታ የለውም፡፡ በዓለማዊ ጥቅም መፎካከር
ትርጉም አልባ ነው፡፡ በሴቶች ላይ ማሴር ወይም በወንዶች ላይ
ማመጽ የሚባል ነገር ጣዕም ወይም ስሜት አይኖረውም፡
፡ አንዱ ሌላኛውን በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ፣ ድክመቱን
ችግሩንና ጉድለቱን ለማጋለጥ የሚካሄድ ሙከራ በኢስላም
ቦታ የለውም፡፡
ይህ ሁሉ በአንድ በኩል ስንመለከተው ጫወታ ነው፡
፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢስላምንና የሁለቱን ፆታዎች
ትክክለኛ የስራ ዘርፍ አላግባብ ከመረዳት የመነጨም
ነው፡፡ ሁላቸውም አላህን ከችሮታው ሊለምኑት ይገባል፡፡
ከወንድ አንጻር ሴቶች ያላቸው ስፍራ
ሴት ለወንድ ከምትሆንለት አንጻር በብዙ ክፍል
ትመደባለች፡
ሴቷ ለወንዱ ሚስት መሆኗ
አንድ ወንድ ሚስቱን በፈለገው መልኩ
ማየትና በሷ መርካት ይፈቀድለታል፡፡ ሴትም ከባሏ
ጋር እንዲሁው ይፈቀድላታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የመንፈስ
ትስስራቸውን፣ የስሜት ውህደታቸውንና የአካል
ቅርርባቸውን ሲገልጽ፣ ባልን የሚስት ልብስ ሚስትንም
የባል ልብስ በማለት ይገልጻቸዋል፡፡ ‹‹እነርሱ ለናንተ
ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡››
(አል በቀራ 187) (ገጽ፣ 204 ተመልከት)
1
ቤተሰብህ
193
የቅርብ ዘመዱ (መሕረም) ከሆነች
ከሴቶች መሕረም የሚባሉት፣ አንድ ወንድ ፈፅሞ ሊያገባቸው የማይችሉ የሆኑ ሴቶች ናቸው፡፡ እነሱም
የሚከተሉት ናቸው፡
1 ወላጅ እናትና አያት፤ አያትነቱ ቢረዝምም ቢያጥርም አንድ ነው፡፡
2 የራሱን ሴት ልጅ፣ የወንድ ልጁ ሴት ልጅ፣ የሴት ልጁ ሴት ልጅ፤ የልጅ ልጅነታቸው ምንም ያክል
ቢወርድም እርምነቱ ያው ነው፡፡
3 የእናት አባቱ ልጅ እህቱ፣ በአባት የሚገናኙ እህቱ፣ ወይም በእናት የሚገናኙ እህቱ፤
4 የአባቱ እህት አክስቱ፤ ለአባቱ እህትነቷ በአባትም በእናትም ቢሆንም በአባት ብቻ ወይም በእናት
ብቻም ቢሆንም ልዩነት የለውም፡፡ የአባት አክስትና የእናት አክስትም በዚሁ ስር የሚካተቱ ናቸው፡፡
5 የእናቱ እህት የሹሜው፤ ለእናቱ እህትነቷ በአባትም ሆነ በእናትም ቢሆን፣ በአባት ወይም በእናት ብቻም
ቢሆን ልዩነት የለውም፡፡ የአባት አክስትና የእናት አክስትም በዚሁ ስር የሚካተቱ ናቸው፡፡
6 የወንድሙ ሴት ልጅ፤ ወንድምነቱ በእናትም በአባትም፣ ወይም በእናት ብቻ፣ ወይም በአባት ብቻ
ቢሆንም ልዩነት የለውም፡፡
7 የወንድም ወንድ ልጅ ሴት ልጅን ይመስል የልጅነት ሐረጓ ቢወርድም ፍርዱ ያው ነው፡፡
8 የሚስቱ እናት፡ ሚስቱ አብራው ብትሆንም ወይም ቢፈታትም እናቷ እስከመጨረሻው መሕረምነቷ
ይቆያል፡፡ ልክ እንዲሁ የሚስት እናት እናት ወይም የሚስት አያትም ከዚሁ ትመደባለች፡፡
9 ከርሱ የማትወለድ የሚስቱ ሴት ልጅ
10 የልጅ ሚስት ወደ ታች የሚወለድ ቢሆንም ለምሳሌ እንደ ልጅ ልጅ ሚስት
11 ወደ ላይ ከፍ ቢልም የአባት ሚስት ወይም ልክ እንደ የልጅ ሚስት በአባት በኩል
12 የጡት እናቱ፡ የጡት እናት ማለት በሁለቱ የመጀመሪያ የአራስነት ዓመታት ወቅት ውስጥ አምስት ጊዜ
ጠግቦ የጠባት ሴት ናት፡፡ እርሱን በማጥባቷ ምክንያት ኢስላም ለርሷ በርሱ ላይ መብት ደንግጎላታል፡፡
13
የጡት እህቱ፡ ይህች ደግሞ እርሱን ያጠባችው ሴት ልጅ ናት፡፡ በዚሁ መልክ፣የጡት አክስት የጡት
ወንድም ልጅ የጡት እህት ልጅና የመሳሰሉት ሁሉም የጡት ዘመዶች ልክ የደም ትስስር እንዳላቸው
ዘመዶች እርም ይሆናሉ፡፡
የዝምድና ደረጃ ከፍ የማለትና
ወደታች የመውረድ ምልክት
በእነዚህ ክልክል በሆኑ ወንዶች ፊት እንደ ባህሉ መሠረት መውጣት ይችላሉ። ነገር ግን ድንበሩን
ማለፍ የለበትም እጆች፣ ትከሻ፣ፀጉር፣ የመሳሰሉት ግልፅ መሆን ይችላሉ።
ቤተሰብህ
195
> አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ዓይንን ሰበር ማድረግ ጨዋነትንና
ክብርን ማስጠበቂያ መንገድ ነው፡፡
ሴቷ ለርሱ ባዕድ ከሆነች
ባዕድ ሴት የምትባለው ከተጠቀሱት መሓሪሞች
ውጭ ያለች ሴት ሁሉ ነች፡፡ ከርሱ ጋር ዝምድና ያላቸው
ቢሆኑም፣ እንደ አጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ፣ የወንድሙ
ሚስት፣ ወይም ከርሱ ጋር ዝምድና የሌላቸው ቢሆንም
ከርሱ ጋር የሚያስተሳስራቸው የዘር ሐረግ ወይም
የአማችነት ትስስር ባይኖርም በኢስላም እይታ አጅነቢ
ወይም ባዕድ ናቸው፡፡
በእርግጥ ኢስላም አንድ ሙስሊም ከባዕድ ሴት
ጋር ሊኖረው የሚገባን ግንኙነት ሥርዓትና መመሪያ
አድርጎለታል፡፡ ይህ ደግሞ ክብርን የሚጠብቅና የሰይጣን
በሮችን የሚዘጋ ነው፡፡ የሰው ልጅን የፈጠረው አላህ(ሱ.ወ)፣
ለርሱ የሚበጀውን ከማንም በላይ ያውቃል፡፡ አላህ
(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹የፈጠረ አምላክ እርሱ
ዕውቀተ ረቂቁ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን (ሚስጥርን ሁሉ)
አያውቅምን?›› (አል ሙልክ 14)
3 በወንድና በባዕድ ሴት መካከል የሚኖር ግንኙነት
ስርዓት
ዓይንን መስበር
አንድ ሙስሊም የሌላ ሰውን ሀፍረተ ገላ ማየት
አይፈቀድለትም፡፡ የፍቶት ስሜቱን የሚቀሰቅሱ ነገሮችንም
መመልከትም የተከለከለ ነው፡፡ ያለ ጉዳይ አንዲትን ሴት
አተኩሮ ማየት የለበትም፡፡
አላህ ሱ.ወ) ሁለቱንም ጾታዎች ዓይናቸውን ሰበር
እንዲያደርጉ አዟቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ የጥብቅነትና
የጨዋነት ጎዳና በመሆኑ ነው፡፡ ዓይንን ያለ ገደብ እንደፈለጉ
መልቀቅ የዝሙትና የወንጀል መንገድ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)
እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለምዕመናን ንገራቸው ዓይኖቻቸውን
ያልተፈቀደን ከማየት ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ
ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ
ነው፡፡ ለምእመናትም ንገራቸው ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ
ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡›› (አል ኑር 30-31)
በድንገት የተከለከለን ነገር ለማየት የተጋለጠ ሰው
ወዲያው ከዚያ እይታ ዓይኑን ሰበር ማድረግ አለበት፡፡
ዓይንን መስበር በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና በኢንተርኔት
ከሚሰራጩ የተከለከሉ ነገሮችንም ያካትታል፤ የፍትወት
ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮችን መመልከት ክልክል ነው፡፡
በስርዓትና በመልካም ስነምግባር አብሮ መኖር
ስርዓትን በጠበቀና መልካም ስነ ምግባርን በተላበሰ
መልክ፣ ከማንኛውም ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች ርቀው
አንዲት ባዕድ ሴትን ቢያናግር፣ እሷም ብታናግረው፣
ማሕበራዊ ሕይወታቸውን ቢመሩ አይከለከልም፡፡
1
2
> ኢስላም በሴቶችና በወንዶች መካከል የሚኖርን ግንኙነት
ስርዓት የሚያሲዝ ደንብና መመሪያ አስቀምጧል፡፡
በየዕለቱ የሚወጡ መረጃዎች
እንደሚያመለክቱት ከእምነት አስተምህሮ
በራቁ ቤተሰቦችና ማህበረሰብ ውስጥ
የአስገድዶ መድፈርና ፀያፍ የወንጀል ስራዎች
በሰፊው ተስፋፍተዋል፡፡
ቤተሰብህ
196
• አላህ(ሰ.ወ) ሴቶች ባዕድ ወንዶችን ሲያናግሩ
ድምፃቸውን እንዳያስለመልሙ ከልክሏል፡፡
ግልጽ የሆነ ንግግርን እንዲናገሩም አዟል፡፡ አላህ
(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ያ በልቡ በሽታ ያለበት
እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም መልካምንም
ንግግር ተናገሩ፡፡›› (አል አሕዛብ 32)
• ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ አረማመዶች፣ እንቅስቃሴዎችና
ከጌጦችም ከፊሎቹን ግልጽ ማድረግ የተከለከሉ ናቸው፡
፡ አላህ (ሱ.ወ) ሴቶችን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡-
‹‹ከጌጦቻቸው የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው
አይምቱ፡፡›› (አል ኑር 31)
የኸልዋ (ለብቻ መነጠል) እርምነት
ኸልዋ ማለት አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ማንም
በማያያቸው ስፍራ ላይ ለብቻቸው መገኘት ሲሆን
ይህንን ኢስላም እርም አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም፣ ይህ
ዓይነቱ አጋጣሚ፣ ዝሙትና ፀያፍ ተግባራት እንዲፈፀሙ
የሚያደርግበት የሸይጣን መግቢያ በር በመሆኑ ነው፡፡
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አድምጡ! ከእይታ
በራቀ ቦታ ላይ አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር
አይነጠልም ሦስተኛቸው ሰይጣን ቢሆን እንጂ፡፡›› (አል
ቲርሚዚ 2165)
አል ሒጃብ (የሴቶች ኢስላማዊ አለባበስ)
አላህ (ሱ.ወ) በሴቶች ላይ ሂጃብን ግዳጅ ያደረገው
ማራኪ ውበትና አታላይ ተክለ ሰውነት ያላበሳቸው
በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሯቸው ደግሞ ለወንዶች
ፈታኝነቱ፣ ወንዶች ለሴቶች ካላቸው ተፈጥሯዊ ፈታኝ
ገጽታ በእጅጉ የላቀ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ) ሂጃብን የደነገገው ለብዙ ዓላማ ነው፡
• ሴት የተፈጠረችለትን ዓላማና የተጣለባትን
ማህበረሰባዊ ኃላፊነት፣ በዕውቀትም በተግባርም
በብቃትና በጥራት እንድትወጣ እንዲሁም ክብሯንና
ጨዋነቷን ጠብቃ እንድትኖር ለማድረግ ነው፡፡
• የዋልጌነትና የጋጠወጥነት መንስኤዎችን በመቀነስና
በማዳከም በአንድ በኩል የማህበረሰቡን ጽዱዕነት
በሌላም በኩል የሴትን ክብር ለማስጠበቅ ነው፡፡
• ወደሴቶች ለሚመለከቱ ወንዶች በጥብቅነትና ስሜትን
በመቆጣጠር ላይ ማገዝ፤ ይኸውም እንደማንኛውም
የእድገትና የልማት አጋር ከሴቶች ጋር እንዲረዳዱና
እንዲተጋገዙ ያደርጋል፡፡ የቅጽበታዊ ስሜት ማርኪያ
የፍቶት ስሜት ቀስቃሽ ብቻ አድርገው እንዳይመለከቷት
ለማድረግ ያስችላል፡፡
3
4
የሂጃብ ይዘት
አላህ (ሱ.ወ) ሴት ልጅ በባዕድ ወንዶች ፊት ከፊቷና
ከመዳፎቿ በስተቀር ሰውነቷን በሙሉ እንድትሸፍን
ግዴታ አድርጓል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡
- ‹‹ጌጣቸውንም ከርሷ ግልጽ የኾነውን በስተቀር
አይግለጡ፡፡›› (አል ኑር 31)
ግለጽ የኾነ የሚባለው ፊትና መዳፍን ነው፤ እሱም
ቢሆን፣ ፊትና መዳፍን በመገለጥ የሚከሰት ፈተና ወይም
ችግር ካለ መሸፈናቸው ግድ ይሆናል፡፡
የሒጃብ ስርዓተ ደንብ
አንዲት ሴት የሚከተሉትን ቅድመ መስፈርቶች
በጠበቀ መልክ የፈለገችውን ዓይነት መልክና ይዘት
ያለው ሒጃብ ወይም ልብስ መልበስ ይፈቀድላታል፡፡
1 ሒጃቡ የግድ መሸፈን ያለበትን የሰውነት ክፍል
በጠቅላላ የሚሸፍን መሆን አለበት
2 ሰፊ መሆን አለበት፤ የሚያጣብቅ፣ ጠባብ፣ የሰውነትን
ቅርጽ የሚያወጣና የሚያሳይ መሆን የለበትም፡፡
3 ወፍራም መሆን አለበት፡፡ ስስነቱ በስሩ ያለን
የሰውነት ክፍል የሚያጋልጥና የሚያሳይ መሆን
የለበትም፡፡
> ሒጃብ ሴት ልጅን በማህበረሰቡ ውስጥ ሊኖራት የሚገባውን
ሚና በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከሚታወቁት ስርዓቶች ሁሉ
በጥራትና በብቃት እንድትወጣ አመቻችቷታል፡፡
ቤተሰብህ
197
ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸውና
ካበረታታቸው ማህበራዊ ጉዳዮች መካከል
አንዱ ነው፡፡ የነብያት ፈለግም ነው፡፡ (ገጽ፣
196 ተመልከት)
ኢስላም ለጋብቻ ዝርዝር ድንጋጌና ስርዓትን
በመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶታል፡፡ የባለ
ትዳሮች መብት መከበር የጋብቻው ግንኙነት
እንዲጎለብትና እንዲረጋ ያደርጋል፡፡ በመንፈስ
የተረጋጋ፣ በእምነቱ የጸና፣ በሁሉም የማሕበራዊ
ጉዳዮች ላይ የመጠቀ፣ ሕፃናት በውስጡ
የሚያድጉበት የሆነን ስኬታማ ቤተሰብ
ለመመስረት ያስችላል፡፡
ከነኚህ ኢስላማዊ ድንጋጌዎች መካከል፡
ኢስላም ለአንድ ጋብቻ ትክክለኛነት
በባልም ሆነ በሚስት በኩል የግድ ሊሟሉ የሚገባቸው
መስፈርቶችን አስቀምጧል፡፡ እነሱም የሚከተሉት
ናቸው፡፡
ኢስላም ለሚስትነት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች፡
ሙስሊም፣ ወይም የመጽሐፍት ባለቤት
ማለትም አይሁድ ወይም ክርስቲያን መሆን
አለባት፡፡ ይሁን እንጂ ኢስላም ከሙስሊሟም
ቢሆን በሃይማኖቷ ጠንካራዋን እንድንመርጥ
ይመክራል፡፡ ምክንያቱም ወደፊት ለልጆችህ
እናትና ተንከባካቢ፣ ለአንተ ደግሞ በመልካም
ነገር ላይ የምታግዝህና የምታጸናህ እሷ በመሆኗ
ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ባለ
ሃይማኖቷን ምረጥ አለያ እጅህ አመድ አፋሸ
ትሆናለች›› (አል ቡኻሪ 4802 / ሙስሊም
1466)
ጥብቅና ጨዋ መሆን አለባት፡፡ በዝሙትና
በእንዝላልነት የምትታወቅ ሴትን ማግባት
ክልክል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡
- ‹‹ከምእመናት ጥብቆቹም ከነዚያ ከናንተ
በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም
(ተፈቀዱላችሁ)›› (አል ማኢዳ 5)
1
2
> ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ ነው
> ጋብቻ በኢስላም
ለዘላለሙ ሊያገባቸው እርም ከተደረጉ
መሐሪሞቹ መካከል መሆን የለባትም፡፡ የዚህን
ዝርዝር ማብራሪያ ከዚህ በፊት አሳልፈናል፡
፡ በጋብቻው አንዲት ሴትን ከእህቷ ወይም
ከአክስቶቿ ማለትም ከአባቷ እህት ወይም
ከእናቷ እህት ጋር በአንድ ላይ ማግባት
አይፈቀድለትም፡፡ (ገጽ፣ 200 ተመልከት)
ኢስላም ለባልነት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች፡
ባል ሙስሊም መሆን አለበት፡፡ በኢስላም፣ ሙስሊም
ሴትን ሃይማኖቱ የመጽሐፍ ተከታይ (አህለል ኪታብ)
ወይም መጽሐፍ የለሽ ቢሆንም ለካሃዲ መዳር የተከለከለ
ነው፡፡ ኢስላም አንድን ወንድ በባልነት ለመቀበል ወንዱ
ሁለት ባህሪዎችን የተላበሰ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡
• በሃይማኖቱ ጽኑ መሆኑና
• መልካም ስነ ምግባር የተላበሰ በሆኑ ናቸው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሃይማኖቱንና
ስነምግባሩን የምትወዱለት ልጃችሁን ከጠያቃችሁ
አጋቡት፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1084 / ኢብኑ ማጃህ 1967)
3
ቤተሰብህ
198
> የባልና የሚስት መብቶች
> አንድ ሰው በአካባቢው ተለምዶ መሰረት የባለቤቱንና የልጆቹን
ወጪ የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡
አላህ (ሱ.ወ) በባልም በሚስትም ላይ ሊጠብቁት የሚገባ የሆነ መብት ሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም የጋብቻን ሕይወት
የሚያሳምሩና የሚጠብቁ ነገሮችን በሙሉ እንዲፈፅሙ አነሳስቷል፡፡ እነኚህን ጉዳዮች የመጠበቅ ኃላፊነት በሁለቱም ወገን
ላይ የተጣለ ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት አንዳቸው ከሌላኛው የማይቻልን ነገር እንዲፈፅም መጠየቅ የለባቸውም፡፡ አላህ
(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ለነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኗኗር (በባሎቻቸው
ላይ መብት) አላቸው፡፡›› (አል በቀራ 228)
የሕይወት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው አና የተከበረው
ቤተሰብ እንዲጸና ነገርን ማግራራትና ጉድለትን ማለፍ
እንዲሁም መለገስ ያስፈልጋል፡፡
የሚስት መብቶች
1 ቀለብና መጠለያ
• ሚስት ባለ ሃብት ብትሆንም እንኳ፣ ባል ለሚስቱ
የምግቧን፣ የመጠጧን፣ የልብሷንና የአስፈላጊ ጉዳዮች
ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም
ለሰረሷ ተመጣጣኝ የሆነን መኖሪያ ወይም ማረፊያም
ሊያዘጋጅላት ይገባል፡፡
• የወጪ መጠን፡ ወጪ የሚለካው እንደ ባልየው
የገቢ መጠንና እንደየ አገሩ የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣
ማባከንም ሆነ መጨናነቅ የሌለበት ሊሆን ይገባል፡፡
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የችሎታ ባለቤት
ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበት
ሰው፣ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድዳትም፡፡››
(አል ጠላቅ 7)
• ይህን ወጪ ሲሸፍን መመጻደቅ፣ እንዲሁም
በመጨናነቅ እሷንም ሆነ እራሱን ማዋረድ የለበትም፡
፡ ገንዘብ ሲያወጣ፣ አላህ (ሱ.ወ) በገለጸው መልኩ
በመልካም እሳቤ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ
ሚስት በባሏ ላይ ያላት መብት እንጂ እርሱ በቸርነቱ
የለገሳት አይደለም፤ እናም መብቷን በአግባቡ
ሊጠብቅላትና ሊሰጣት ይገባል፡፡
• በኢስላም፣ በሚስትና በቤተሰብ ላይ የሚወጣ ወጪ
ከባድ ምንዳን ያጎናጽፋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ
ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሙስሊም ከአላህ እመነዳበታለሁ
በሚል እሳቤ በሚስቱ ላይ ወጪ ሲያወጣ ለርሱ
ምጽዋት ይሆንለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 5036 /
ሙስሊም 1002)
በሌላም ዘገባ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በርሷ
ብትመነዳባት እንጂ አንተ የአላህን ፊት ከጃይ ሆነህ
አንድም ወጪን አታወጣም፤ በሚስት አፍ ውስጥ
የምታስቀምጣት ጉርሻ እንኳን ብትሆን፡፡›› (አል
ቡኻሪ 56 /ሙስሊም 1628)
ወጪ አልሰጥም ያለ ሰው፣ ወይም እየቻለ ማውጣት
ካለበት የቀነሰ ሰው፣ በርግጥ ከባድ ወንጀል ውስጥ
ተዘፍቋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ለአንድ ሰው ወንጀለኛነት፣ የሚያስተዳድረውን ሰው
ማንገላታቱ ይበቃዋል፡፡›› (አቡ ዳውድ 1692)
2 መልካም አኗኗር ወይም ግንኙነት
መልካም አኗኗር በሚለው የተፈለገው መልዕክት
መልካም ስነ ምግባር የሚለው ነው፡፡ ልበ ለስላሳነት፤
ለብ ያለ ንግግርን መናገር፤ አንድም የሰው ልጅ
ሊርቃቸው የማይችሉ ስህተቶችንና ድክመቶችን ችሎ
ማለፍና የመሳሰሉትን ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ብሏል፡
- ‹‹በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፤ ብትጠሉዋቸውም
(ታገሱ)፤ አንዳችን ነገር ልትጠሉ፣ አላህም በርሱ ብዙ ደግ
ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡›› (አል ኒሳእ 19)
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡