መጣጥፎች




1. እርሱ የሰላም ባለቤት መሆኑን፡- ጌታችን "አስ-ሰላም" በመሆኑ ሰላም የሚገኘው ከሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡


" تَحِيَّتُهُمْ يَوْمَ يَلْقَوْنَهُ سَلَامٌ وَأَعَدَّ لَهُمْ أَجْرًا كَرِيمًا " سورة الأحزاب 44


"በሚገናኙት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም በመባባል ነው፤ ለነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል።" (ሱረቱል አሕዛብ 44)፡፡


" سَلَامٌ قَوْلًا مِنْ رَبٍّ رَحِيمٍ " سورة يس 58


"(ለነሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ ቃል በቃል ሰላምታ አላቸው።" (ሱረቱ ያሲን 58)፡፡


ሶላታችንን ሰግደን ስናጠናቅቅ ከሶስት ጊዜ "አስተግፊሩላህ" በኋላ የምንለው ዚክርም ይህን ያመላክታል፡-


عَنْ ثَوْبَانَ، قَالَ: كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِذَا انْصَرَفَ مِنْ صَلَاتِهِ اسْتَغْفَرَ ثَلَاثًا وَقَالَ: «اللهُمَّ أَنْتَ السَّلَامُ وَمِنْكَ السَّلَامُ، تَبَارَكْتَ ذَا الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ» مسلم.


ከሠውባን(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው፡- የአላህ መልክተኛ ሶላታቸውን እንዳጠናቀቁ ፡- "አስተግፊሩላህ(አላህ ሆይ ይቅርታህን እጠይቃለሁ) ሶስት ጊዜ ከዛም፡- አላሁምመ አንተ-ሰላም(አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ!) ወሚንከ-ሰላም(ሰላምም የሚገኘው ካንተው ነው)… ይሉ ነበር" (ሙስሊም)፡፡


2. አማኞች ሰላምን እንደሚያገኙ፡- ጌታችን አላህ "አስ-ሰላም" በመሆኑ በሱ ላመኑ ባሪያዎቹ ውስታዊና ውጫዊ ሰላም ያጎናጽፋቸዋል፡፡


" فَأْتِيَاهُ فَقُولَا إِنَّا رَسُولَا رَبِّكَ فَأَرْسِلْ مَعَنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَا تُعَذِّبْهُمْ قَدْ جِئْنَاكَ بِآيَةٍ مِنْ رَبِّكَ وَالسَّلَامُ عَلَى مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَى " طه 47


"ወደርሱም ኺዱ፤ በሉትም፦ እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፤ የእስራኤልንም ልጆች፣ ከኛ ጋር ልቀቅ፤ አታሰቃያቸውም፤ ከጌታህ በሆነው ታምር በእርግጥ መጥተንሃልና፤ ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይሁን።" (ሱረቱ ጣሀ 47)፡፡


" قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَامٌ عَلَى عِبَادِهِ الَّذِينَ اصْطَفَى آللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة النمل 59


"(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)፡፡" (ሱረቱ-ነምል 59)፡፡


" وَسَلَامٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ * وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة الصافات 182-181


"በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹን፤ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን" (ሱረቱ-ሷፍፋት 181-182)፡፡


3. ጀነት ለመግባት ሰበብ መሆኑን፡- ጌታችን አላህ "አስ-ሰላም" በመሆኑ በዚህ ምድር ላይ እኛ አማኝ ባሪያዎቹ ሰላምታን ማብዛት እንዳለብን ተነግሮናል፡፡ ይህንን የሚያደርግም ጀነት እንደሚገባ ተገልጻል፡፡ ቀጣዩ ሃዲስም ይህን ይገልጻል፡-


عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَا تَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّى تُؤْمِنُوا، وَلَا تُؤْمِنُوا حَتَّى تَحَابُّوا، أَوَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى شَيْءٍ إِذَا فَعَلْتُمُوهُ تَحَابَبْتُمْ؟ أَفْشُوا السَّلَامَ بَيْنَكُمْ» مسلم.


ከአቢ ሁረይራ(ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈው ሃዲስ የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- "እስካላመናችሁ ድረስ ጀነትን አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ድረስ አታምኑም፣ ከሰራችሁት ሊያዋድዳችሁ የሚችልን ነገር ላመላክታችሁን? ሰላምታን በመሐከላችሁ አብዙ" (ሙስሊም)፡፡


6. "አል-ሙእሚን"


ሀ. ትርጉሙ፡-


"አል-ሙእሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ለባሪያዎቹ ታማኝ ማለት ነው፡፡ አምላካችን አላህ ለምእመናን ባሪያዎቹ ታማኝና ጸጥታን ሰጪ የሆነ ጌታ ነው፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ሙእሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23


"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡


ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-


1. እሱን እያመለኩ ምንም ሳያጋሩበት በሱ የታመኑ ባሪያዎቹን በደኅነነቱ ከለላ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ወደ ቅኑ ጎዳናም ይመራቸዋል፡-


" الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ أُولَئِكَ لَهُمُ الْأَمْنُ وَهُمْ مُهْتَدُونَ " سورة الأنعام 82


"እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነሱም የተመሩ ናቸው" (ሱረቱል አንዓም 82)፡፡


2. አላህ ለባሪያዎቹ ታማኝ ጌታ በመሆኑ ማንንም የማይበድል መሆኑን፡-


" إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ وَإِنْ تَكُ حَسَنَةً يُضَاعِفْهَا وَيُؤْتِ مِنْ لَدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا " سورة النساء 40


"አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበደልም፤ መልካም ሥራ ብትኾንም ይደራርባታል፤ ከርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል።" (ሱረቱ ኒሳእ 40)፡፡


" إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَكِنَّ النَّاسَ أَنْفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ " سورة يونس 44


"አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 44)፡፡


" وَوُضِعَ الْكِتَابُ فَتَرَى الْمُجْرِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَا وَيْلَتَنَا مَالِ هَذَا الْكِتَابِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةً وَلَا كَبِيرَةً إِلَّا أَحْصَاهَا وَوَجَدُوا مَا عَمِلُوا حَاضِرًا وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا " سورة الكهف 49


"(ለሰው ሁሉ) መጽሐፉም ይቀርባል፤ ወዲያውም ከሐዲዎችን፥ በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ፤ ዋ ጥፋታችን! ለዚህ መጽሐፍ፥ (ከሥራ) ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው? ይላሉም፤ የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቀራቢ ሆኖ ያገኙታል፤ ጌታህም አንድንም አይበድልም" (ሱረቱል ከህፍ 49)፡፡


ይቀጥላል





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል አምስት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሃ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8





7. "አል-ሙሀይሚን"


ሀ. ትርጉም፡-


"አል-ሙሀይሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- የበላይ ተቆጣጣሪ እና ጠባቂ ማለት ነው፡፡ ፈጣሪ አምላካችን አላህ በፍጡራኑ ጉዳይ ፍጹም የበላይ ተቆጣጣሪ ነው፡፡ በንግስናው ስር ከሱ የሚሸሸግ ምንም ነገር የለም፡፡ ዛሬ በምድራችን የአምባገነኖች በደል በዝቶ እውነተኞች ደማቸው ያለ-አግባብ ፈስሶ ብንመለከትና ጌታችንም ያለ ምንም ምድራዊ ቅጣት ዝም ቢላቸው፡ እሱ ለሚያውቀውና ለሚፈልገው ጥበብ ቢፈልገው እንጂ ከግዛቱ መውጣት ችለው አይደለም፡፡ ይሄን እውነታ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡-


"አላህንም፤ በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው ዓይኖች በርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 42)፡፡


እርሱ ጌታ አላህ ዓለማትን በእውቀቱና በራሕመቱ የከበበ ነው፡፡ ፍጥረታቱን በመላ በችሎታው ስር ያደረገ ነው፡፡ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል፡፡ የፈለገውን ነገር "ሁን" ካለው ይሆናል፡፡


"ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም (ማስገኘት) በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 116)፡፡


"ጌታዬ ሆይ! ሰዉ ያልነካኝ ስሆን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፤ ነገሩ እንደዚህሽ ነዉ፤ አላህ የሚሻዉን የፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ሁን ይለዋል ወድያዉኑም ይሆናል፥ አላት።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 47)፡፡


"አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ፥ እንደ አዳም ብጤ ነዉ፤ ከዐፈር ፈጠረዉ፤ ከዚያም ለርሱ (ሰዉ) ሁን አለዉ ሆነም" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 59)፡፡


"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ እውነት ነው…." (ሱረቱል አንዓም 73)፡፡


"ለማንኛውም ነገር (መሆኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለርሱ ሁን ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።" (ሱረቱ-ነሕል 40)፡፡


"ነገሩም አንዳች ባሻ ጊዜ ሁን ማለት ነው ወዲያው ይሆናልም።" (ሱረቱ ያሲን 82)፡፡


"እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ፣ የሚያሞትም ነው፤ አንዳችን ነገር ባሻም ጊዜየሚለው ሁን ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።" (ሱረቱ ጋፊር 68)፡፡


እንዲሁም ይህ "አል-ሙሀይሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም ተመልካች የሚልም ትርጉም አለው፡፡ የባሪያዎቹን ንግግርና ስራ ተመልካችና አዋቂ ጌታ በመሆኑ በእውነት ይመሰክራል ይፈርድባቸውማል፡-


"እነዚያ ያመኑ፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ. አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና።" (ሱረቱል ሓጅ 17)፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ሙሀይሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23


"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡


የጌታችን ቃል የሆነው ቅዱስ ቁርኣንም ከሱ በፊት የነበሩትን ቀደምት መለኮታዊ መጽሓፍት የሚቆጣጠርና የሚመሰክር በመሆኑ "ሙሀይሚን" የሚል የባሕሪ ስም ተሰጥቶታል፡-


" وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ... " سورة المائدة 48


"ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲሆን በውነት አወረድን…" (ሱረቱል ማኢዳህ 48)፡፡


8. "አል-ዐዚዝ"


ሀ. ትርጉም፡-


"አል-ዐዚዝ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉም፡- አሸናፊና የላቀ ማለት ነው፡፡ አላህ በነገሮቹ ሁሉ የበላይ አሸናፊ ነው፡-


"ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ ፦ መኖሪያውን አክብሪ፤ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና፤ አላት፤ እንደዚሁም ለዩሱፍ (ገዥ ልናደርገውና) የሕልሞችንም ፍች፣ ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው፤ አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።" (ሱረቱ ዩሱፍ 21)፡፡


"እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩት እነዚያ በጣም በወራዶቹ ውስጥ ናቸው።አላህ ፦ እኔ በእርግጥ አሸንፋለሁ፤ መልክተኞቼም (ያሸንፋሉ ሲል)፤ ጽፏል። አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና።" (ሱረቱል ሙጃደላህ 21)፡፡


አሸናፊነት የጌታችን ባህሪ ነው፡፡


" الَّذِينَ يَتَّخِذُونَ الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِ الْمُؤْمِنِينَ أَيَبْتَغُونَ عِنْدَهُمُ الْعِزَّةَ فَإِنَّ الْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا " سورة النساء 139


"እነዚያ ከምእመናን ሌላ ከሐዲዎችን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ፣ እነሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን? ልቅናም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 139)፡፡


" وَلَا يَحْزُنْكَ قَوْلُهُمْ إِنَّ الْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ " سورة يونس 65


"ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 65)፡፡


" مَنْ كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ وَالَّذِينَ يَمْكُرُونَ السَّيِّئَاتِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَكْرُ أُولَئِكَ هُوَ يَبُورُ " سورة فاطر 10


"ማሸነፍን የሚፈልግ የሆነ ሰው፣ አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ (እርሱን በመግገዛት ይፈልገው)፤ መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል፤ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፤ እነዚያም መጥፎ ሥራዎችን የሚዶልቱ፣ ለነሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፤ የነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል።" (ሱረቱ ፋጢር 10)፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ዐዚዝ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 92 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡


" هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة آل عمران 6


"እርሱ ያ በማሕፀኖች ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነዉ። ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 6)፡፡


" وَالشَّمْسُ تَجْرِي لِمُسْتَقَرٍّ لَهَا ذَلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ " سورة يس 38


"ፀሐይም ለርሷ ወደሆነው መርጊያ ትሮጣለች ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው።" (ሱረቱ ያሲን 38)፡፡


" بِنَصْرِ اللَّهِ يَنْصُرُ مَنْ يَشَاءُ وَهُوَ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ " سورة الروم 5


"በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ) የሚሻውን ሰው ይረዳል፥ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው።" (ሱረቱ-ሩም 5)፡፡


ሐ. ከዚህ መለኮታዊ ስም የምንማረው፡-


1. አላህ የእልቅና ባለቤት መሆኑን፡-


" سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ " سورة الصافات 180


"የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ" (ሱረቱ-ሷፍፋት 180)፡፡


2. አማኝ ባሪያዎቹን እንደሚያልቅ፡-


" يَقُولُونَ لَئِنْ رَجَعْنَا إِلَى الْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ الْأَعَزُّ مِنْهَا الْأَذَلَّ وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ " سورة المنافقون 8


"ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከርሷ ያወጣል ይላሉ፤ አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና፣ ለምእምናን ነው፤ ግን መናፍቆች አያውቁም።" (ሱረቱል ሙናፊቁን 8)፡፡


" قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَنْ تَشَاءُ وَتَنْزِعُ الْمُلْكَ مِمَّنْ تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَنْ تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَنْ تَشَاءُ بِيَدِكَ الْخَيْرُ إِنَّكَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة آل عمران 26


"(ሙሐመድ ሆይ!) በል- የንግሥና ባለቤት የሆንክ አላህ ሆይ! ለምትሻዉ ሰዉ ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ ንግስናን ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 26)፡፡


3. በዚህ ስም አላህን መለመን እንደሚቻል፡-


" رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ إِنَّكَ أَنْتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة البقرة 129


"«ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከነሱው የኾነን መልክተኛ በነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን (ከክህደት) የሚያጠራቸውንም ላክ፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» " (ሱረቱል በቀራህ 129)፡፡


4. ቅዱስ ቁርኣን የአሸናፊው አላህ ቃል በመሆኑ ከፊቱም ሆነ ከኋላው ውሸት ሊቀርበው የማይችል አሸናፊ አድርጎታል፡-


" إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِالذِّكْرِ لَمَّا جَاءَهُمْ وَإِنَّهُ لَكِتَابٌ عَزِيزٌ * لَا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ تَنْزِيلٌ مِنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ " سورة فصلت 42-41


"እነዚያ በቁርአን፣ እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲሆን፣ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት (ጠፊዎች ናቸው)።ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።" (ሱረቱ ፉሲለት 41-42)፡፡


9. "አል-ጀባር"


ሀ. ትርጉም፡-


"አል-ጀባር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ኃያልና ጠጋኝ ማለት ነው፡፡ ሁሉም ነገር በኃያልነቱ ስር የተንበረከከ በመሆኑ አላህ "አል-ጀባር" ይባላል፡፡ ዳካማዎችን ጉልበት በመለገስ የሚጠግን፣ የተሰበረ ልብን ተስፋ በመሙላት የሚጠግን፣ ድኃን በማብቃቃት የሚጠግን፣ ህመምተኞችን በማዳን የሚጠግን፣አማኞችን በሚደርሰባቸው ሙሲባ ጽናትን በመለገስ የሚጠግን በመሆኑ አላህ "አል-ጀባር" ይባላል፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ጀባር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23


"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡


አላህ ኃያልና የባሮቹን ድክመት ጠጋኝ ጌታ በመሆኑ አንድ ሙስሊም በሩኩእና በሱጁድ ላይ ሲሆን ተከታዩን ዱዓ ያደርጋል፡-


"ሱብሓነ ዚል-ጀበሩቲ ወል-መለኩቲ ወል-ኪብሪያኢ ወል-ዐዘማህ" (አቡ ዳዉድ 873፣ ነሳኢይ 1131፣ አሕመድ 23980)፡፡


(የኃያልነት፣ የግዛት፣ የኩራትና የታላቅነት ባለቤት የሆነው አላህ ከጉድለት ሁሉ ጠራ) ማለት ነው፡፡


እንዲሁም በሁለቱ ሱጁዶች መሓል ሲቀመጥ እንዲህ ይላል፡-


"አላሁምመ ኢግፊር ሊ፣ ወርሐምኒ፣ ወጅቡርኒ፣ ወህዲኒ፣ ወርዙቅኒ" (ቲርሚዚይ)፡፡


(አላህ ሆይ! ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፣ እዘንልኝም፣ ጠግነኝ፣ ቅኑን ጎዳና ምራኝ፣ ሲሳይንም ለግሰኝ) ማለት ነው፡፡


ፍጹም ኃያልነት የጌታ አላህ ብቻ በመሆኑ በምድር ላይ ማንም በማንም ላይ የበላይ መሆንን ከፈለገ አላህ ያዋርደዋል፡፡ የሀቅንም መንገድ እንዳይቀበል ልቡ ይታሸጋል፡-


" الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِ اللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَانٍ أَتَاهُمْ كَبُرَ مَقْتًا عِنْدَ اللَّهِ وَعِنْدَ الَّذِينَ آمَنُوا كَذَلِكَ يَطْبَعُ اللَّهُ عَلَى كُلِّ قَلْبِ مُتَكَبِّرٍ جَبَّارٍ " سورة غافر 35


"እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር፣ በአላህ ታምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ፣ በጣም ተለቀ፤ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል።" (ሱረቱ ጋፊር 35)፡፡


ይቀጥላል





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል ስድስት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሃ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8





10. "አልሙተከቢር"


ሀ. ትርጉም፡-


"አልሙተከቢር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ኩራተኛ፡ የኩራት ባለቤት ማለት ነው፡፡ አላህ የሻውን ሰሪ፡ የፈለገውን አድራጊ፡ ፍጹም የበላይ አሸናፊ፡ ስልጣኑ ያልተገደበ ጌታ በመሆኑ "አልሙተከቢር" ይባላል፡፡ የፈለገውን እንደፈለገው ማድረግ ይችላል፡፡ ማንም ለምን? ብሎ ፈቃዱን መቃወም የሚችል ኃይል የለም፡፡ ኩራት በጌታ አላህ ባህሪ ውስጥ የክብርና የምሉእነት መገለጫ ሲሆን፡ በፍጡር ላይ ግን የበታችነትና የውድቀት ምክንያት ነው፡፡ የጠጣውን ውሃ ከሰዓታት በኋላ ሽንት ሆኖ እንዳይወጣ መቆጣጠር ያልቻለ፤ የበላው ምግብ ከሰዓታት በኋላ ቆሻሻ ሆኖ እንዳይወጣ መቆጣጠር የማይችል አካል እንዴት ሆኖ ይኮራል? እኮ እንዴት? ጌታ አላህ ግን በራሱ የተብቃቃ ኩሩ የሆነ ጌታ ስለሆነ ከስራ እንኳ በኢኽላስ የተሰራውን እንጂ ሪያእ(እዩልን ስሙልኝ) የተቀላቀለበትን አይቀበልም፡-


አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- "አላህ(በሃዲሱል ቁድሲይ ላይ) እንዲህ ይላል፡- እኔ ከተጋሪዎችና ከሚያጋሩብኝም ነገር የተብቃቃሁ ነኝ፡፡ በኔ ላይ ሌላን አካል አጋርቶ አንድን ስራ የሰራ ሰው (በስራው)ማጋራቱንም ሰውየውንም (ወዳጋራብኝ ሰው) እተወዋለሁ" (ሙስሊም)፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አልሙተከቢር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የመጣው፡-


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23


"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡


ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-


1. ጌታችን አላህ "አልሙተከቢር" ስለሆን ኩራት የርሱ መለኮታዊ ባሕሪ መሆኑን እንረዳለን፡-


" وَلَهُ الْكِبْرِيَاءُ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الجاثية 37


"ኩራትም በሰማያትም በምድርም ለርሱ ብቻ ነው፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱል ጃሢያህ 37)፡፡


2. ማንም ሰው ሊኮራ እንደማይገባና ይህንንም የሚፈጽም በዱንያ ውርደት በአኼራ ቅጣት እንደሚገጥመው እንረዳለን፡-


"እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር፣ በአላህ ታምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ፣ በጣም ተለቀ፤ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል።" (ሱረቱ-ጋፊር 35)፡፡


"በትንሣኤ ቀንም፣ እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን፣ ፊቶቻቸው የጠቆሩ ሆነው ታያቸዋለህ፤ በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?" (ሱረቱ-ዙመር 60)፡፡


"የገሀነምን በርሮች፣ በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ (ይባላሉ)፤ የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ!" (ሱረቱ ጋፊር 76)፡፡


"እነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡ ቀም ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳልፋችሁ በርሷም ተጣቀማችሁ ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጡ በነበራችሁት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ (ይባላል)።" (ሱረቱል አሕቃፍ 20)፡፡


እንድንኮራስ የሚያደርገን ምን አለንና? በመሬት ብንጓዝ የኛን ምልክት እንኳ ላዩዋ ላይ የማናሳርፍ፡ ብንዘል ደግሞ ተራራ የማንደርስ ነን፡-


"በምድርም ላይ የተንበጣረርክ ሆነህ አትኺድ፤ አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና፣ በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና።" (ሱረቱል ኢስራእ 37)፡፡


"ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፤ በምድርም ላይ ተንጠብርረህ አትኺድ፤ አላህ ተንበጥራሪን፣ ጉረኛን ሁሉ አይወድምና።" (ሱረቱ ሉቅማን 18)፡፡


አምሩ ኢብኑ ሹዐይብ ከአባቱ፡ አባቱ ደግሞ ከአያቱ፡ አያቱ ከነቢያችን(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰምቶ እንዳስተላለፈልን እንዲህ አሉ፡- "ኩራተኞች የቂያም እለት እንደ ቀይ ጉንዳን አናሳ ሁነው ይቀሰቀሳሉ፡፡ ውርደት ከየ-አቅጣጫው ይከባቸዋል፡፡ ቡለስ ወደተባለው ጀሐነም እስር ቤት ይነዳሉ…." (ቲርሚዚይ)፡፡


ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን ደግሞ የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- "በልቡ ላይ የጎመን ዘር ፍሬ ያህል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም፡፡ አንድ ሰውም መልክተኛውን፡- ሰውው ልብሱና ጫማው ጥሩ እንዲሆንለት ይፈልጋል(ይሄ ኩራት ነውን?) ሲል፡- እሳቸውም፡- አላህ ውብ ጌታ ነው ውበትንም ይወዳል፡፡ ኩራት ግን ሐቅን አለመቀበልና ሰውን በንቀት መመልከት ነው" (ሙስሊም)፡፡


3. አላህንም ስንገዛው በመተናነስና በመዋረድ ስሜት ዝቅ ብለን ከኩራት ርቀን መሆን እንዳለበት እንማራለን፡-


"እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ ያወድሱታልም፤ ለርሱም ብቻ ይሰግዳሉ።" (ሱረቱል አዕራፍ 206


"ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሻም በምድር ያለው ሁሉ መላክትም ይሰግዳሉ፤ እነርሱም አይኮሩም።" (ሱረቱ-ነሕል 49)፡፡


"በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የርሱ ነው፤ እርሱ ዘንድ ያሉትም (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ አይሰለቹምም።" (ሱረቱል አንቢያእ 19)፡፡


"ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያም እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።" (ሱረቱ ጋፊር 60)፡፡


11. "አል-ኻሊቅ"


ሀ. ትርጉም፡-


"አል-ኻሊቅ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፈጣሪ ማለት ነው፡፡ አላህ የዩኒቨርሱ(ፍጥረተ ዓለሙ) የምናየውንም ሆነ የማናየውንም ነገር ሁሉ ብቻውን የፈጠረ ነው፡፡


"(እርሱ) ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ ለእርሱ ሚስት የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 101)፡፡


"(እርሱ) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ የሆነ ልጅንም ያልያዘ፣ በንግሥናውም ተጋሪ የሌለው፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና፣ በትክክልም ያዘጋጀው ነው።" (ሱረቱል ፉርቃን 2)፡፡


"ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 102)፡፡


"አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።" (ሱረቱ-ዙመር 62)፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ኻሊቅ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 11 ጊዜ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الحشر 24


"እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱል ሐሽር 24)፡፡


" أَفَرَأَيْتُمْ مَا تُمْنُونَ * أَأَنْتُمْ تَخْلُقُونَهُ أَمْ نَحْنُ الْخَالِقُونَ " سورة الواقعة 59-58


"(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁትን? እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን።" (ሱረቱል ዋቂዓህ 58-59)፡፡


ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-


1. ከአላህ በስተቀር መፍጠር የሚችል እንደሌለ፡- የሌለ ነገርን መፍጠርና ማስገኘት የአላህ ባሕሪ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ባሕሪው ምንም ተጋሪ ለውም፡-


" يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ " سورة الحج 73


"እላንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምስሌ ተገለጸላችሁ ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝምብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፤ ለርሱ (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳ (አይችሉም) አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከርሱ አያስጥሉትም ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ። " (ሱረቱል ሐጅ 73)፡፡


2. የሚፈጥርና የማይፈጥር በምንም መልኩ እንደማይሰተካከሉ፡- አምልኮ የሚገባው መፍጠር የሚችለውን ብቻ እንደኾነ እንማራለን፡-


" أَفَمَنْ يَخْلُقُ كَمَنْ لَا يَخْلُقُ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ " سورة النحل 17


"የሚፈጥር፣ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሡጹምን ?" (ሱረቱ-ነሕል 17)፡፡


" يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ " سورة البقرة 21


"እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 21)፡፡


ይቀጥላል





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል ሰባት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሃ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


12. "አል-ባሪእ"


ሀ. ትርጉሙ፡-


"አል-ባሪእ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፈጣሪ፣ ከኢምንት አስገኚው ማለት ነው፡፡ በቁጥር 11 ላይ ካየነው "አል-ኻሊቅ" ከሚለው መለኮታዊ ስም ብዙም አይለያይም፡፡ አል-ኢማሙ-ዘመኽሸሪ ደግሞ "አል-ባሪእ" የሚለውን ሲተረጉሙት፡- ፍጥረቱን ከነውር ያጸዳ፣ በስራው እንከን አልባ የሆነ ብለውታል፡፡ ምክንያቱም የዚህ ስም ሐረግ(ስርወ-ግንዱ) "በረአ" የሚል ሲሆን፡ ትርጉሙም ነጻ ወጣ ዳነ የሚል ነው፡፡ ስለዚህ አላህ "አል-ባሪእ" ነው ስንል፡ ስራው ከነውርና ከጉድለት የጠራ ነው ለማለት ነው ይላሉ፡፡ ለዚህ አቋማቸውም ተከታዩን የቁርኣን አንቀጽ ያቀርባሉ፡-


" الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقًا مَا تَرَى فِي خَلْقِ الرَّحْمَنِ مِنْ تَفَاوُتٍ فَارْجِعِ الْبَصَرَ هَلْ تَرَى مِنْ فُطُورٍ " سورة الملك 3


"ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ሆነው የፈጠረ ነው። በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም። አይንህንም መልስ፤ ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?" (ሱረቱል ሙልክ 3)፡፡


ከፊል ሊቃውንቶች እንደሚገልጹት፡- "አል-ባሪእ" የሚለው መለኮታዊ ስም በአብዝኃኛው ግልጋሎት ላይ የሚውለው ሕያዋን ፍጥረታትን ለማመልከት ነው፡፡ ግዑዛን ፍጥረታትን ለመግለጽ አይደለም የሚል ነው ወላሁ አዕለም፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ባሪእ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ሶስት ጊዜ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الحشر 24


"እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱል ሐሽር 24)፡፡


" وَإِذْ قَالَ مُوسَى لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ إِنَّكُمْ ظَلَمْتُمْ أَنْفُسَكُمْ بِاتِّخَاذِكُمُ الْعِجْلَ فَتُوبُوا إِلَى بَارِئِكُمْ فَاقْتُلُوا أَنْفُسَكُمْ ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ عِنْدَ بَارِئِكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ " سورة البقرة 54


"ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን (አምላክ አድርጋችሁ) በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ፡፡ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ ይሃችሁ በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለናንተ በላጭ ነው» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 54)፡፡


13. "አል-ሙሰዊር"


ሀ. ትርጉም፡-


"አል-ሙሰዊር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ቅርጽን አሳማሪ፣ ሰዓሊ የሚል ነው፡፡ ፈጣሪ አምላካችን አላህ ፍጥረታቱን እሱ ብቻ በሚፈልገው ቅርጽ ያበጀና ያዘጋጀ ነው፡፡ በመልክም ሆነ በቅርጽ፤ በይዘትም ሆነ በአይነት የተለያዩ የሆኑ ስራዎቹን ገልጾዋል፡፡ በዚህ አለም ላይ ፍጹም ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት ነገሮችን ማግኘት አይቻልም፡፡ ይህ የችሎታውን ወሰን-የለሽነት፣ የጥበቡን ጥልቀት፣ የእውቀቱን ስፋት የሚገልጽ ነው፡፡ ከሰው፣ ከእንሰሳት፣ ከነፍሳት፣ ከእጽዋት፣ ከበራሪዎች እና ከመላእክት በቅርጽ የማይመሳሰሉ ስንትና ስንት ፍጥረታት አሉት፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አል-ሙሰዊር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الحشر 24


"እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱል ሐሽር 24)፡፡


ሐ. ከዚህ የምንወስደው ትምሕርት፡-


1. አላህ የፈለገውን ፍጥረት በፈለገው መልኩ መቅረጽ የሚችል ጌታ መሆኑን፡- መፍጠር የአምላካችን መለኮታዊ ባሕሪው መሆኑን ካመንን፡ የፈጠረውን ፍጥረት ደግሞ ምን አይነት ቅርጽ መያዝ እንዳለበት መወሰንም የሱ መብትና ችሎታ ብቻ ነው ማለት ነው፡-


" هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة آل عمران 6


"እርሱ ያ በማሕፀኖች ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነዉ። ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 6)፡፡


" يَا أَيُّهَا الْإِنْسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ * الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ * فِي أَيِّ صُورَةٍ مَا شَاءَ رَكَّبَكَ " سورة الإنفطار 8-6


"አንተ ሰው ሆይ በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ፣ ባስተካከለህም። በማንኛውም በሻው ቅርጽ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)።" (ሱረቱል ኢንፊጣር 6-8)፡፡


በሶላታችን ውስጥ በሱጁድ ስፍራ ላይ ሆነን ከምናደርጋቸው ዚክሮች አንዱ ይህንን የሚገልጽ ነው፡-


عن علي رضي الله عنه قال: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان إذا سجد قال : " اللهمَّ لَكَ سَجَدْتُ ، وَبِكَ آمَنْتُ ، وَلَكَ أَسْلَمْتُ ، سَجَدَ وَجْهِي للذِي خَلَقَهُ وَصَوَّرَهُ ، وَشَقَّ سَمْعَهُ وَبَصَرَهُ ، تَبَارَكَ الله أَحْسَنُ الخَالِقِينَ " رواه مسلم.


ዐሊይ ኢብኑ-አቢ ጧሊብ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ ሱጁድ ሲያደርጉ፡- ‹‹አላህ ሆይ! ላንተ ሰገድኩ፣ ባንተም አመንኩ፣ ላንተም ታዘዝኩ፣ ፊቴም ለዚያ ለፈጠረውና ቅርጽ ላስያዘው፣ መስሚያውንና መመልከቻውን ለከፈተለት ሰገደ" (ሙስሊም)፡፡


2. አላህ በፈለገው ቅርጽ የተሰራው ፍጥረት ደግሞ እጅጉኑ ያማረና የተዋበ የማያስቀይም መሆኑንም እንማራለን፡-


" اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ قَرَارًا وَالسَّمَاءَ بِنَاءً وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ وَرَزَقَكُمْ مِنَ الطَّيِّبَاتِ ذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَتَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ " سورة الغافر 64


"አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፤ የቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም ያሳመረ፣ ከጣፋጮችም ሲሳዮች የሰጣችሁ ነው፤ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ።" (ሱረቱል ጋፊር 64)፡፡


" خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ " سورة التغابن 3


"ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ፤ መመለሻችሁም ወደርሱ ነው።" (ሱረቱ-ተጋቡን 3)፡፡


" ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنْشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ " سورة المؤمنون 14


"ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 14)፡፡


" الَّذِي أَحْسَنَ كُلَّ شَيْءٍ خَلَقَهُ وَبَدَأَ خَلْقَ الْإِنْسَانِ مِنْ طِينٍ " سورة السجدة 7


"ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው፣ የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው፥ ነው።" (ሱረቱ-ሰጅዳህ 7)፡፡


" لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ فِي أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ " سورة التين 4


"ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው።" (ሱረቱ-ቲን 4)፡፡


3. ለሕያዋን ፍጥረታት ቅርጽን ማሳመር የአላህ ስራ ስለሆነ፡ ለኛ ሕይወት ያለውን(የሰውም ሆነ የእንሰሳት) ምስል መስራት፣ መቅረጽ እንደማይፈቀድልን እንማራለን፡፡ ምክንያቱም በውስጡ ሩህን በመንፋት ሕይወትን መለገስ አንችልምና፡-


عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: " أشد الناس عذابا يوم القيامة رجل قتل نبيا ، أو قتله نبي أو رجل يضل الناس بغير علم ، أو مصور يصور التماثيل " رواه الطبراني وحسنه الشيخ الألباني.


ዐብደላህ ኢብኑ-መስዑድ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ ነቢይ እንዲህ አሉ፡- "የቂያም ቀን ቅጣቱ እጅግ የሚበረታባቸው ሰዎች፡- ነቢይን የገደለ ወይም ነቢይ እሱን (በክህደቱ)የገደለው፣ ያለ እውቀት ሰዎችን ያጠመመ፣ (ህይወት ያላቸውን ነገሮች) አምሳል የሚቀርጽ ነው" (ጦበራኒ የዘገቡት፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 1000)፡፡


ይቀጥላል





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል ስምንት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሃ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


"አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


14-16 "አል-ገፋር"፣"አል-ገፉር"፣"አል-ጋፊር"


ሀ. ትርጉም፡-


"አል-ገፉር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉም፡- በጣም መሐሪ ማለት ነው፡፡ "አል-ገፋር" ደግሞ ፡- ትርጉሙ ተመሳሳይ ሆኖ ነገር ግን እጅግ በጣም መሐሪ የሚለውን የsuperlative degree form የሚገልጽ ነው፡፡ "አል-ጋፊር" የሚለውም ትርጉሙ ከመጀመሪያው አይለይም፡፡


ጌታችን አላህ ለባሪያዎቹ እጅግ በጣም ርኅሩህ፡ በጣም አዛኝ በመሆኑ፡ በኃጢአት ጊዜም መሐሪያቸው እሱ ብቻ ነው፡፡ ይሕ መሐሪነቱ ነው አማኞችን በልባቸው ተስፋን በመሙላት እሱን ለሚያስደስተው መልካም ስራ እንዲሽቀዳደሙ ከሚጠላው ነገር እንዲርቁ የሚያደርጋቸው፡፡ አማኝ የአላህ ባሪያዎች ሁሌም መልካም ተግባርን ጌታችን ይደስትበታል ብለው ሲሰሩ ሁለት ነገርን ከፊት-ለፊታቸው አድርገው ነው፡-


1. በዚህ መልካም ስራቸው ወደ አላህ በመቃረብ ከቸርነት ማዕዱ (ጀነትን) እንዲያቋድሳቸውና


2. በምድራዊ ሕይወታቸው ላጠፉት ጥፋት ምሕረቱን እንዲለግሳቸው በመሻት ነው፡፡


" إِنَّ الَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنْفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَارَةً لَنْ تَبُورَ * لِيُوَفِّيَهُمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدَهُمْ مِنْ فَضْلِهِ إِنَّهُ غَفُورٌ شَكُورٌ " سورة فاطر 30-29


"እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ, ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ፣ በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ። ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው፣ ከችሮታቸውም ሊጨምርላቸው፣ (ተስፋ ያደርጋሉ)፤ እርሱ በጣም መሐሪ አመስጋኝ ነውና።" (ሱረቱ ፋጢር 29-30)፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


-"አል-ገፉር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 91 ጊዜ ተጠቅሷል፡-


" تَكَادُ السَّمَاوَاتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْ فَوْقِهِنَّ وَالْمَلَائِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِمَنْ فِي الْأَرْضِ أَلَا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ " سورة الشورى 5


"(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፤ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፤ ንቁ አላህ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነው።" (ሱረቱ-ሹራ 5)፡፡


" إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ * إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ * وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ " سورة البروج 14-12


"የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው። እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም። እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው።" (ሱረቱል ቡሩጅ 12-14)፡፡





 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው ...

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው ...

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት