መጣጥፎች

የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል አንድ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሃ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


አምላካችን አላህ እሱ የሚጠራበትና የሚመለክበት የኾኑ ብዙ መልካም ስሞች አሉት፡፡ የእነዚህ ስሞች መብዛት ደግሞ የሚያመላክተው፡- በባሕሪያቱ እንከን አልባ የሆነ፣ችሎታው ፍጹም የተሟላ፣ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል….. መሆኑን ነው፡፡ጌታችን አላህ በስሞቹ የሚጠራ፣በባሕሪያቱ የሚገለጽ፣በስራዎቹ የሚታወቅ አምላክ ነው፡፡ስሞቹም የሱን ማንነት፡ ባሕሪያቱንና ስራዎቹን ገላጭ ናቸው፡፡ እሱ እራሱን የሰየመባቸው ብዙ መለኮታዊ ስሞች አሉት፡፡


" وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى فَادْعُوهُ بِهَا وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ " سورة الأعراف 180


" ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤ (ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ።" ሱረቱል አዕራፍ 180


" قُلِ ادْعُوا اللَّهَ أَوِ ادْعُوا الرَّحْمَنَ أَيًّا مَا تَدْعُوا فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى وَلَا تَجْهَرْ بِصَلَاتِكَ وَلَا تُخَافِتْ بِهَا وَابْتَغِ بَيْنَ ذَلِكَ سَبِيلًا " سورة الإسراء 110


" አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤(ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ፣(መልካም ነው)፤ ለርሱ መልካም ስሞች አሉትና በላቸው፤ በስግደትህም (ስታነብ) አትጩህ፤ በርሷም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ፤ በዚህም መካከል መንገድን ፈልግ።" ሱረቱል ኢስራእ 110


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


" هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الحشر 24


" እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" ሱረቱል ሐሽር 24


ከነዚህ አራት አንቀጾች የምንረዳው፡- አላህ ብዙ መለኮታዊ ስሞች እንዳሉትና እነዚህም መለኮታዊ ስሞች " አል-ሑስና " (እጅግ ያማሩ) መሆናቸውን ነው፡፡ በነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሃዲስ ውስጥም ጌታችን መለኮታዊ የሆኑ ስሞች እንዳሉት ተነግሮናል፡፡


عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «إِنَّ لِلَّهِ تِسْعَةً وَتِسْعِينَ اسْمًا مِائَةً إِلَّا وَاحِدًا، مَنْ أَحْصَاهَا دَخَلَ الجَنَّةَ» رواه البخاري


عَنْ أَبِى هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِىِّ -صلى الله عليه وسلم- قَالَ « لِلَّهِ تِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ اسْمًا مَنْ حَفِظَهَا دَخَلَ الْجَنَّةَ وَإِنَّ اللَّهَ وِتْرٌ يُحِبُّ الْوِتْرَ » رواه مسلم


ከአቢ ሁረይራህ በተላለፈው ሃዲስ የአላህ ነቢይ እንዲህ አሉ፡- " አላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህን ስሞች የሀፈዘ (በቃሉ ያጠና) ጀነት ገባ፡፡ አላህ ዊትር(አንድ) ነውና ዊትር ነገርንም ይወዳል " ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡


በዚህ ሃዲስ መሰረት ጌታችን ዘጠና ዘጠኝ መለኮታዊ ስሞች እንዳሉት መረዳት እንችላለን፡፡ ያ ማለት ደግሞ ከዛ በላይ ሌሎች ስሞች የሉትም ማለት አይደለም፡፡ የተነገረንን በደንብ እናስተውል፡፡ ሃዲሱ የሚለው " አላህ 99 ስሞች አሉት " ነው እንጂ " የአላህ ስሞች 99 ናቸው " አይደለም፡፡ ተግባባን ወንድሞችና እህቶች? ወይስ በሁለቱ መሐል ያለውን ልዩነት ላስረዳቹ? መርሐባ፡፡ " አላህ 99 ስሞች አሉት " ማለት ማንም ሰው መረዳት እንደሚችለው እሱ ጌታችን አላህ 99 ስሞች እንዳሉት ነው፡፡ ነገር ግን ከዛ በላይ ሌሎች ስሞች የሉትም የሚለውን ከዚህ ቃል መረዳት አይችልም፡፡ በተቃራኒው ደግሞ፡- " የአላህ ስሞች 99 ናቸው " ማለት ደግሞ የስሞቹን ብዛት በ 99 ገድበን እነዚህ ስሞች ብቻ እንዳሉት ነው የምንረዳው፡፡ አሁንም ግልጽ ካልሆነላቹ ሌላ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ " እኔ መቶ ብር አለኝ " ብላችሁ እናንተ የምትረዱት በኪሴ ውስጥ መቶ ብር እንደያዝኩ እንጂ ከዛ በላይ እንዳልያዝኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን እኔ መቶ ብር አለኝ ከማለት ይልቅ " እኔ ያለኝ መቶ ብር ነው " ብላችሁ ደግሞ ከዛ በላይ ሌላ ብር እንደሌለኝ ትረዳላችሁ ማለት ነው፡፡አረብኛውም ላይ የተቀመጠው አገላለጽ لِلَّهِ تِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ اسْمًا የሚል እንጂ إن أسماء الله تسعة وتسعون የሚል አይደለም፡፡ የሃዲሱም መልእክት በቦታው ላይ ለነበሩ ሰዎች አላህ ዘጠና ዘጠኝ መለኮታዊ ስሞች እንዳሉትና በነዚህም ስሞች አላህን እንዲለምኑና ወደ አላህ እንዲቃረቡባቸው ለማስተማር እንጂ የአላህን ስሞች በቁጥር ለመገደብ አይደለም፡፡ ይበልጥ ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክረው ሌላ ነቢያዊ ሃዲስ ደግሞ መኖሩ ነው፡፡


عَنْ عَبْدِ اللهِ ابن مسعود رضي الله عنه، قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " مَا قَالَ عَبْدٌ قَطُّ إِذَا أَصَابَهُ هَمٌّ وَحَزَنٌ : اللَّهُمَّ إِنِّي عَبْدُكَ ، وَابْنُ عَبْدِكَ ، ابْنُ أَمَتِكَ ، نَاصِيَتِي بِيَدِكَ ، مَاضٍ فِيَّ حُكْمُكَ ، عَدْلٌ فِيَّ قَضَاؤُكَ ، أَسْأَلُكَ بِكُلِّ اسْمٍ هُوَ لَكَ ، سَمَّيْتَ بِهِ نَفْسَكَ ، أَوْ أَنْزَلْتَهُ فِي كِتَابِكَ ، أَوْ عَلَّمْتَهُ أَحَدًا مِنْ خَلْقِكَ ، أَوِ اسْتَأْثَرْتَ بِهِ فِي عِلْمِ الْغَيْبِ عِنْدَكَ ،.... إِلاَّ أَذْهَبَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَمَّهُ ، وَأَبْدَلَهُ مَكَانَ حُزْنِهِ فَرَحًا ، قَالُوا : يَا رَسُولَ اللهِ يَنْبَغِي لَنَا أَنْ نَتَعَلَّمَ هَؤُلاَءِ الْكَلِمَاتِ ؟ قَالَ : أَجَلْ ، يَنْبَغِي لِمَنْ سَمِعَهُنَّ أَنْ يَتَعَلَّمَهُنَّ. " رواه أحمد 267/5


ከዐብደላህ ኢብን መስዑድ በተላለፈው ሃዲስ የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- " አንድ የአላህ ባሪያ ጭንቀትና ሃዘን ሲገጥመው ፡- አላህ ሆይ! እኔ ባሪያህ፣የባሪያህ ልጅ ነኝ፡ እኔነቴም ባንተ ቁጥጥር ስር ነው፡ ውሳኔህ በኔ ላይ ተፈጻሚ ነው፡ ፍርድህም ፍትሀዊ ነው፡ እኔም ያንተ በሆኑት ስሞችህ ኹሉ፡ ራስህን በሰየምክበት፡ በመጽሐፍህም ውስጥ በጠቀስከው፡ ከፍጡሮችህም ለማንኛውም ባሳወቅከው፡ አንተ ዘንድም ብቻህን ባወቅከው ስሞችህ እለምንሀለሁ …..አይልም አላህ ጭንቀቱንና ሃዘኑን ቢያስወግድለት፡ በምትኩም ደስታን ቢለግሰው እንጂ " ኢማሙ አህመድ የዘገቡት፡፡


በዚህ ሃዲስ ውስጥ أَوِ اسْتَأْثَرْتَ بِهِ فِي عِلْمِ الْغَيْبِ عِنْدَكَ "አንተ ዘንድም ብቻህን ባወቅከው ስሞችህ" የሚለው የሚያመላክተን ጌታችን ራሱ ብቻ የሚያውቀው ከፍጡራን የተሰወረ መለኮታዊ ስሞች እንዳሉት ነው፡፡


ለምን አስፈለገ?


የአላህን ስሞችና ባሕሪያትን ስናጠና አላማ ሊኖረን ይገባል፡፡ ከፊት ለፊታችን ጥቅምን አስቀምጠን መሆን አለበት፡፡የአላህ ስሞችንና ባሕሪያትን ስንማር ብዙ ጥቅሞችን እናገኛለን፡፡ ከነዚህም መሐከል፡-


1. ጌታችንን ማወቅ


ከጌታ አላህ ስሞች እና ባሕሪያት ጋር በተዋውቅን ቁጥር ስለ አላህ ያለንም እውቀት በዛው መልኩ እያደገ ይመጣል፡፡ ምክንያቱም አላህ ባወረደው ቅዱስ ቁርኣኑ ላይ እራሱን ያስተዋወቀን፡ በስሞቹ፣ በባሕሪያቱና በስራዎቹ አማካይነት ነው፡፡ እነዚህን ስሞችና ባሕሪያትን ማወቅ ደግሞ ለአላህ ያለን ክብር ከፍ እንዲልና እንድንፈራው እንድናከብረውም ይረዳናል፡፡


2. ወደሱ መቃረብ


ሌላው ጥቅም ደግሞ፡- አላህን ለመለመንና በስሞቹም ወደሱ ለመቃረብ ይረዳናል፡፡ ተከታዩ የቁርኣን አንቀጽ ይህንን ያስረዳል፡፡


" وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى فَادْعُوهُ بِهَا.... " سورة الأعراف 180


" ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤ (ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት …." ሱረቱል አዕራፍ 180


3. ጀነት መግባት


የመጨረሻውና ትልቁ ግብም ይኸው ነው፡፡ የአላህን ስሞች (ዘጠና ዘጠኙን) የሐፈዘ ጀነት ይገባል፡፡


عَنْ أَبِى هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِىِّ -صلى الله عليه وسلم- قَالَ « لِلَّهِ تِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ اسْمًا مَنْ حَفِظَهَا دَخَلَ الْجَنَّةَ وَإِنَّ اللَّهَ وِتْرٌ يُحِبُّ الْوِتْرَ » رواه مسلم


ከአቢ ሁረይራህ በተላለፈው ሃዲስ የአላህ ነቢይ እንዲህ አሉ፡- " አላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህን ስሞች የሀፈዘ (በቃሉ ያጠና) ጀነት ገባ፡፡ አላህ ዊትር(አንድ) ነውና ዊትር ነገርንም ይወዳል " ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡


እዚህ ላይ " مَنْ حَفِظَهَا ( የሀፈዘ"በቃሉ ያጠና" ) የሚለው ላይ የኢስላም ሊቃውንት (ዑለማእ) የሰጡትን ማብራሪያ መመልከት ይኖርብናል፡፡


قال ابن القيم: " مراتب إحصاء أسمائه التي من أحصاها دخل الجنة وهذا هو قطب السعادة ومدار النجاة والفلاح:


• المرتبة الأولى إحصاء ألفاظها وعددها.


• المرتبة الثانية فهم معانيها ومدلولها، والإحاطة بجميع معانيها.


• المرتبة الثالثة دعاؤه بها كما قال تعالى" وَلِلَّهِ الأَسْمَاءُ الْحُسْنَى فَادْعُوهُ بِهَا "الأعراف:180، وهو مرتبتان: إحداهما: دعاء ثناء وعبادة والثاني: دعاء طلب ومسألة، فلا يثنى عليه إلا بأسمائه الحسنى وصفاته العلى . " بدائع الفوائد 171 باختصار


ኢማም ኢብኑል-ቀይም 691-751 ሒጅሪያ (ረሒመሁላህ) ሲያብራሩት፡- የአላህን ስሞች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የሐፈዘ ጀነት ይገባል የሚለው የደስታ ሁሉ ቁንጮ እና የመዳን ዕምብርት ነው፡፡


ሀ. ስሞቹን ቃላቱን ከነ-ብዛታቸው መሐፈዝ (በቃል መያዝ)


ለ. የእነዚህን ስሞች ትርጓሜና መልክታቸውን በአግባቡ መረዳት


ሐ. በነዚህ ስሞች አላህን መለመንና እሱን ብቻ መገዛት፡፡ አላህ ራሱ እንደተናገረው፡- " ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤ (ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት …." ሱረቱል አዕራፍ 180 እሱን ስንጠራውም፡-


1. የምስጋናና የውዳሴ ጥርሪዎችን በመጠቀም


2. የልመናና የአምልኮ ጥርሪዎችን በመጠቀም መሆን አለበት " በዳኢዑል-ፈዋኢድ ገጽ 171 በአጭሩ፡፡


የምንከተለው መርሆ


የአላህን ስሞችና ባህሪያትን አምነን የምንቀበለው ከዚህ በታች በተቀመጡት መስፈርቶች ሊሆን ይገባል፡፡


1. ((إثباتُ ما أثبته الله لنفسه في كتابه ، أو أثبته له رسوله صلى الله عليه وسلم ؛ من غير تحريف ولا تعطيل ، ومن غير تكييف ولا تمثيل)).


1. አላህ ለራሱ በቁርኣኑ ላይ ያጸደቀውን ወይም መልከተኛው በሃዲሳቸው ላይ ያጸደቁትን ስም ቃላቱን ሳንቀይር፣ትርጉም ሳናሳጣው፣ እንዲሕ ይመስላል ሳንልና ከፍጡሩም ጋር ሳናመሳስለው ማጽደቅ፡፡


አላህ ስለ-ራሱ ከማንም በላይ ዐዋቂ ነው፡፡ መልክተኛው ደግሞ ከሁሉም በላይ ስል-ጌታቸው የበለጠ ዐዋቂ ናቸው፡፡ የኛ ድርሻ በቁርአንም ሆነ በሶሒሕ ሃዲስ የተነገረንን የአላህን ስሞችና ባሕሪያት እንዳመጣጡ መቀበልና ማጽደቅ ብቻ ነው፡፡


2. ((نفـيُ ما نفاه الله عن نفسه في كتابه ، أو نفاه عنه رسوله صلى الله عليه وسلم ، مع اعتقاد ثبوت كمال ضده لله تعالى)).


2. አላህ በቁርኣኑ ከራሱ ላይ ውድቅ ያደረገውን ወይም መልከተኛው በሃዲሳቸው ላይ ውድቅ ያደረጉትን ባህሪያት እኛም ውድቅ ማድረግ፡፡


ለጌታችን ተገቢ ያልሆኑ ባሕሪያትን በሙሉ በቅዱስ ቁርኣን ላይ እና በሃዲስ በተነገረን መሰረት እኛም ጌታችንን ከነዚህ ባህሪያት ማጽዳት ፡፡ ለምሳሌ፡-ዕንቅልፍ፣ልጅን መያዝ፣ጅህልና…..በተቃራኒው ሕያውነቱን፣አዋቂነቱን፣ከልጅ የጠራ መሆኑን ከማመን ጋር፡፡


3. ((صفات الله عَزَّ وجَلَّ توقيفية ؛ فلا يُثبت منها إلا ما أثبته الله لنفسه ، أو أثبته له رسوله صلى الله عليه وسلم ، ولا يُنفى عن الله عَزَّ وجَلَّ إلا ما نفاه عن نفسه ، أو نفاه عنه رسوله صلى الله عليه وسلم)).


3. የአላህን ስሞችና ባሕሪያት ማወቅ የሚቻለው በቁርኣንና ሃዲስ ላይ በመጣው መልኩ ብቻ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ከሌላ ምንጭ በመጠቀም ቁርኣን ውስጥና ሃዲስ ውስጥ የሌለን ስም እንደ ስሙ መያዝ፣ቁርኣንና ሃዲስ ያልተቃወሙትንም ስምና ባሕሪ እኛም ልንቃወም አይገባንም፡፡


አንድን ስም ወይም ባሕሪ የአላህ ነው ብሎ ለመቀበል የግድ ያ ስም በቁርኣን ወይም በሶሒሕ ሃዲስ ውስጥ መሰረት ሊኖረው ይገባል፡፡ በይሆናልና በግምት ወይም ከሌላ ምንጭ በመውሰድ አላህን መሰየም የተሳሳተ አካሄድ ነው፡፡ ውድቅም ስናደርግ እንደዛው በቁርኣንና ሃዲስ ላይ መገደብ ያስፈልገናል፡፡


4. ((صفات الله تعالى كلها صفات كمال ، لا نقص فيها بوجهٍ من الوجوه)).


4. የአላህ ስሞችና ባህሪያት በጠቅላላ ፍጹም ምሉእነትን የተላበሱ ናቸው፡፡ በምንም አይነት መልኩ ጉድለት አይጠጋቸውም፡፡


ኡለማዎች ብዙ መርሆችን አስቀምጠዋል፡፡ ለመግቢያ ያክል እነዚህ በቂ ናቸው፡፡ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአላህ ፈቃድ የምንመለከታቸው የአላህ ስሞች ተራ አቀማመጥ ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ መሰረት ስልሆነ እናንተም ያን በማየት እንድትዘጋጁ፡፡ ዘጠና ዘጠኙን ስሞች የሚጠቅሰው ሃዲስ ላይ የሃዲስ ሊቃውንት ሰነዱ ላይ ድክመት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ከውስጡም ስሞች ያልሆኑ ግን ባህሪ ውስጥ የሚካተቱም እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ሁሉንም በአላህ ፈቃድ በቦታው እናየዋለን ኢንሻአላህ፡፡





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል ሁለት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሃ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


1.አር-ራሕማን


ሀ.ትርጓሜው


የዚህ መለኮታዊ ስም "አር-ራሕማን" ትርጉም፡- እጅግ በጣም ሩኅሩህ ማለት ነው፡፡ ርህራሄው ፍጥረቱን በመላ ያካለለ ለአማኙም ሆነ ለከሐዲው የተረፈ ነው፡፡


"አር-ራሕማን" የሚለው መለኮታዊ ሰም አላህ ብቻ ሚጠራበት ነው፡፡ ከሱ ውጪ ማንንም በዚህ ስም መጥራት አይፈቀድም፡፡ ከራህመቱ መገለጫዎችም፡- ባሬያዎቹን ፈጥሮ ለሲሳያቸውም ኃላፊነቱን ራሱ መውሰዱ፣የመኖሪያ ስፍራቸውን ዱንያን ያለ-ምንም ሽያጭና ኪራይ በነጻ መስጠቱ፣ነቢያትን ከመሐከላቸው መርጦ፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን አውርዶ ወደ ቅን ጎዳና ማመላከቱና ማገዙ....ከፊሎቹ ናቸው፡፡የአላህ ራህመት ለባሪያዎቹ የተስፋ በርን የሚከፍት፤ ወደ መልካም ስራ የሚያነሳሳ እንዲሁም ፍርሐትና ተስፋ መቁረጥን የሚያርቅ ነው፡፡ ስለሆነም ነው ነቢያችን እንዲህ የተናገሩት፡- "ሙእሚን አላህ ለኃጢአተኞች ያዘጋጀውን ቅጣት ታላቅነት ቢረዳ ኖሮ ጀነቱን ተስፋ አያደርግም ነበር፤ ካፊር ደግሞ አላህ ለተመላሽ ባሪያዎቹ የደገሰውን የራህመቱን ታላቅነት ቢረዳ ከጀነቱ ተስፋ አይቆርጥም ነበር" (ሙስሊም የዘገበው)፡፡ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ቂያማ እስከሚቆም ድረስ ጌታችን በምድራችን ላይ ያወረደው ራህመት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን? ከፈለግን ቀጣዩን ነቢያዊ ሃዲስ እንመልከት፡- -


ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለ፡- "አላህ ራህመትን ከፈጠረው በኋላ ወደ መቶ ቦታ ከፈለው፡፡ ከዛም አንድ እጁን ወደ ምድር በማውረድ ዘጠና ዘጠኙን እሱ ዘንድ አኖረ፡፡ በዚህ አንድ ክፋይ ነው ፍጥረተት የሚተዛዘኑት፡ ፈረስ እነኳ ሳትቀር እግሯን ከልጇ ላይ እንዳትጎዳው በማሰብ የምታነሳው የዚሁ ራህመት ውጤት ነው" (ቡኻሪ የዘገበው)፡፡ በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ፡- የቂያም ዕለት መቶውንም የራህመት ክፍሎች ለአማኝ ባሪያዎቹ እንደሚለግሳቸው ተገልጻል፡፡ ጌታችን አላህ ከቁጣው ራህመቱ የቀደመ አምላክ ነው፡፡


ለ. አመጣጡ


"አር-ራሕማን" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 57(ሃምሳ ሰባት) ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለናሙና ያክል፡-


« قَالَتْ إِنِّي أَعُوذُ بِالرَّحْمَنِ مِنْكَ إِنْ كُنْتَ تَقِيًّا » سورة مريم 18


"፦ እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፤ ጌታህን ፈሪ እንደ ኾንክ፣ (አትቅረበኝ) አለች።" ሱረቱ መርየም 18


« إِذَا تُتْلَى عَلَيْهِمْ آيَاتُ الرَّحْمَنِ خَرُّوا سُجَّدًا وَبُكِيًّا » سورة مريم 58


"የአልረሕማን አንቀጾች በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ፣ ሰጋጆችና አልቃሾች ኾነዉ ይወድቃሉ።" ሱረቱ መርየም 58


« وَلَقَدْ قَالَ لَهُمْ هَارُونُ مِنْ قَبْلُ يَا قَوْمِ إِنَّمَا فُتِنْتُمْ بِهِ وَإِنَّ رَبَّكُمُ الرَّحْمَنُ فَاتَّبِعُونِي وَأَطِيعُوا أَمْرِي » سورة طه 90


"ሃሩንም ከዚያ በፊት በእርግጥ አላቸው፦ ሕዝቦቼ ሆይ! (ይህ) በርሱ የተሞከራችሁበት ብቻ ነው ጌታችሁም አልረህማን ነው ተከተሉኝም፤ ትእዛዜንም ስሙ።" ሱረቱ ጣሀ 90


ይህ "አር-ራሕማን" የሚለው መለኮታዊ ስም ስምነትን ብቻ ሳይሆን ባሕሪንም ጭምር ያዘለ ነው፡፡ እሱም ጌታችን አላህ የራህመት ባሕሪ ባለቤት መሆኑን ያሳየናል፡፡ ለመለኮታዊ ክብሩ ተገቢ በሆነ መልኩ ከፍጡራን የርህራሄ ባሕሪ ጋር ምንም ባልተመሳሰለ መልኩ አላህ የራህመት ባለቤት ነው፡፡


« فَإِنْ كَذَّبُوكَ فَقُلْ رَبُّكُمْ ذُو رَحْمَةٍ وَاسِعَةٍ وَلَا يُرَدُّ بَأْسُهُ عَنِ الْقَوْمِ الْمُجْرِمِينَ » سورة العنعام 147


"ቢያስተባብሉህም፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ሕዝቦች ላይ አይመለስም» በላቸው፡፡" ሱረቱል አንዓም 147


ችሮታ ማለት እዝነት ቸርነት የሚለውን የሚገልጽ ነው፡፡ ከፍጡራን ጋር ምንም የሚያመሳስለው ነገር የለም፡- "ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፤ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም" (ሱረቱ-ነሕል 74)፡፡ እንዲሁም፡- "(እርሱ) የሰማያትና የምድር፣ በሁለቱም መካካል ላለዉ ሁሉ ጌታ ነዉና ተገዛዉ፤ እርሱን በመግገዛትም ላይ ታገሥ፤ ለርሱ ሞክሼን ታዉቃለህን ?" (ሱረቱ መርየም 65)፡፡ እንዲሁም፡- "…የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው" (ሱረቱ-ሹራ 11)፡፡ እንዲሁም፡-"ለርሱም አንድም ብጤ የለውም" (ሱረቱል-ኢኽላስ 4) የሚሉትን ተመልከት፡፡


ሐ. የምንወስደው ትምሕርት


ከዚህ "አር-ራሕማን" ከሚለው መለኮታዊ ስሞች ብዙ ጠቀሚ ነገሮችን እንወስዳለን፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-


1. "አር-ራሕማን" የሚል ስም እንዳለው፡- ፈጣሪ አምላካችን አላህ እርሱ "አር-ራሕማን" መሆኑን እንረዳለን፡፡አምነንም እንቀበላለን፡፡


« قُلْ هُوَ الرَّحْمَنُ آمَنَّا بِهِ وَعَلَيْهِ تَوَكَّلْنَا فَسَتَعْلَمُونَ مَنْ هُوَ فِي ضَلَالٍ مُبِينٍ » سورة الملك 29


"እርሱ (እመኑበት የምላችሁ) አልረሕማን ነው፤ (እኛ) በርሱ አመንን፤ በርሱም ላይ ተጠጋን፤ ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የሆነው እርሱ ማን እንደ ሆነ በእርግጥ ታውቃላችሁ በላቸው።" ሱረቱል ሙልክ 29


2. ይህ ስም የ ራህመት ባሕሪን እንዳቀፈ፡- ጌታችን በርህራሄና በቸርነቱ የሚታወቅ በዚህም ባህሪ የሚገለጽ እንደሆነ እንረዳለን፡፡


« وَرَبُّكَ الْغَنِيُّ ذُو الرَّحْمَةِ إِنْ يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَسْتَخْلِفْ مِنْ بَعْدِكُمْ مَا يَشَاءُ كَمَا أَنْشَأَكُمْ مِنْ ذُرِّيَّةِ قَوْمٍ آخَرِينَ » سورة الأنعام 133


"ጌታህም ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው፡፡ ቢሻ ያስወግዳችኋል፤ (ያጠፋችኋል)፡፡ ከሌሎች ሕዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ከበኋላችሁ የሚሻውን ይተካል፡፡" ሱረቱል አንዓም 133


3. ማመስገን እንዳለብን፡- "አር-ራሕማን" የሆነው አምላካችን አላህ ከራህመቱ ስፋት የተነሳ ቀኑን እንድንሰራበትና ሲሳያችንን እንድንፈልግበት ብርሐን፡ ሌሊቱን ደግሞ እንድናርፍበት ጨለማ አድርጎልናል፡፡ በዚህ ራህመቱም እንድናመሰግነው ይፈልጋል፡፡ አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን፡፡


« وَمِنْ رَحْمَتِهِ جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَلِتَبْتَغُوا مِنْ فَضْلِهِ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ » سورة القصص 73


"ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት፣ አመስገኞችም ልትኾኑ አደረገላችሁ፡፡" ሱረቱል ቀሰስ 73


4. በዚህ ስም እንድንለምነው፡- ጌታችን አላህን ስንለምነውና ስንማጸነው "ያ አላህ" እንደምንለው ሁሉ "ያ ራህማን" ብለንም መማጸንና መለመን እንችላለን፡፡


« قُلِ ادْعُوا اللَّهَ أَوِ ادْعُوا الرَّحْمَنَ أَيًّا مَا تَدْعُوا فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى » سورة الإسراء 110


"፦አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤(ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ፣(መልካም ነው)፤ ለርሱ መልካም ስሞች አሉትና በላቸው…" ሱረቱል ኢስራእ 110


5. ባርነትን ወደዚህ ስም ማስጠጋትን፡- "አር-ራሕማን" የጌታችን ስም እስከሆነ ድረስ እኛም ባርነታችንን ወደዚህ ስም በማስጠጋት "ዐብዱ-ራሕማን" "አመቱ-ራሕማን" ብለን መሰየም፡ ስም ማውጣት እንችላለን፡፡


« إِنْ كُلُّ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ إِلَّا آتِي الرَّحْمَنِ عَبْدًا » سورة مريم 93


"በሰማያትና በምድር ያለዉ ሁሉ (በትንሣኤ ቀን)፣ ለአልረሕማን ባሪያ ኾነዉ የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም።" ሱረቱ መርየም 93


« وَعِبَادُ الرَّحْمَنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا » سورة الفرقان 63


"የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ ሰላም የሚሉት ናቸው።" ሱረቱል ፉርቃን 63


ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-"አላህ ዘንድ ከተወደዱት ስሞቻችሁ ውስጥ "ዐብደላህ" እና "አብዱ-ራሕማን" ናቸው" (ሙስሊም 2132)


በዚህ ስም ከተጠሩት የዚህ ኡመት ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ታላቁ ሶሐቢይ "ዐብዱ-ራህማን ኢብኑ ዐውፍ" ነው፡፡ በሒጅራ አቆጣጠር 32ኛው አመት ላይ የሞተ፤ ጀነት ከተበሰሩት አስሩ ሰሐባዎች አንዱ ነው ረዲየላሁ ዐንሁ፡፡


6. ይህን ባህሪ መላበስ እንዳለብን፡- "አር-ራሕማን" የሆነው አምላካችን አላህ በመለኮታዊ ባህሪው ለባሪያዎቹ ርኅሩህ እንደሆነው እኛም በፍጥረታዊና ደካማ ባህሪያችን ለመሰል ወንድሞቻችንና ለእንሰሳት ርኅሩህ መሆን እንዳለብን እንማራለን፡፡


ዐብደላህ ኢብኑ አምር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-"አዛኞችን አር-ራሕማን ያዝንላቸዋል፡፡ የምድር ነዋሪዎች ሆይ! እዘኑ፤ ከሰማይ በላይ ያለው ያዝንላችኃልና" ( ቲርሚዚ 1924





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል ሶስት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሃ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


ባለፈው ክፍል ሁለት ዓምዳችን ላይ በቁጥር 1 ስር የመጀመሪያውን መለኮታዊ ስም "አር-ራሕማን" የሚለውን በተወሰነ መልኩ ትርጓሜውን ቃኝተን ነበር፡፡ ዛሬ ቀጣይ ክፍሉ ይቀርባል ኢንሻአላህ፡፡


2. አር-ረሒም


ሀ.ትርጓሜው


የዚህ መለኮታዊ ስም "አር-ረሒም" ትርጉም፡- እጅግ በጣም አዛኝ ማለት ነው፡፡ እዝነቱ ምእመናን ባሮቹንና በተውበት የሚመለሱትን ያካለለ ስም ነው፡፡


"አር-ረሒም" የሚለው ስም "አር-ራሕማን" ከሚለው ስም ጋር ያለውን ልዩነት ሊቃውንት ካስቀመጡት ነጥቦች ውስጥ ሁለቱን እንመልከት፡-


- "አር-ራሕማን" የሚለው ስም የሚያመለክተው የጌታችንን የህልውናው (የዛቱ) መጠሪያ ስም ሲሆን "አር-ረሒም" ደግሞ በስራና በተግባር የሚገለጸውን የባሕሪ ስም አመልካች ነው፡፡


- "አር-ራሕማን" የሚለው ስም በዚህ አለም ላይ ለፍጡራኑ በጠቅላላ ለሙስሊሙም ለካፊሩም አዛኝነቱን የሚያመላክት ስም ነው፡፡ ጸሐይ ቢወጣ፣ ዝናብ ቢዘንብ፣ ምድር ብታበቅል የሚዳረሰው ለሁሉም ነውና፡፡ "አር-ረሒም" ግን ለአማኞች ብቻ የሚገለጽ የራህመት አይነት ነው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃነት የሚቀርበው ተከታዩ አንቀጽ ነው፡-


« هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ لِيُخْرِجَكُمْ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ وَكَانَ بِالْمُؤْمِنِينَ رَحِيمًا» سورة الأحزاب 43


"እነሱ ያ በናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው፤ መላእክቶችም ፥ ( እንደዚሁ ምሕረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው) ፣ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያመጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል)፤ ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው።" ሱረቱል አሕዛብ 43


« يَوْمَ لا يُغْنِي مَوْلًى عَن مَّوْلًى شَيْئاً وَلا هُمْ يُنصَرُونَ * إِلا مَن رَّحِمَ اللهُ إِنَّهُ هُوَ العَزِيزُ الرَّحِيمُ » سورة الدخان 42-41


"ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት፣ እነሱም የማይርረዱበት ቀን ነው።አላህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር፤ (እርሱስ ይርረዳል)፤ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና።" ሱረቱ-ዱኻን 41-42


ለ. አመጣጡ


"አር-ረሒም" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 114 ጊዜ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-


" وَإِذْ قَالَ مُوسَى لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ إِنَّكُمْ ظَلَمْتُمْ أَنْفُسَكُمْ بِاتِّخَاذِكُمُ الْعِجْلَ فَتُوبُوا إِلَى بَارِئِكُمْ فَاقْتُلُوا أَنْفُسَكُمْ ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ عِنْدَ بَارِئِكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ " سورة البقرة 54


"ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን (አምላክ አድርጋችሁ) በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ፡፡ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ*** ይሃችሁ በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለናንተ በላጭ ነው» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡" ሱረቱል በቀራህ 54


" وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ يَغْفِرُ لِمَنْ يَشَاءُ وَيُعَذِّبُ مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة آل عمران 129


"በሰማያት ያለዉ፣ በምድርም ያለዉ፣ ሁሉ፣ የአላህ ነዉ፤ ለሚሻዉ ሰዉ ይምራል፤ የሚሻዉንም ሰዉ ይቀጣል፤ አላህም ማሐሪ አዛኝ ነዉ።" ሱረቱ አለ ዒምራን 129


" فَمَنْ تَابَ مِنْ بَعْدِ ظُلْمِهِ وَأَصْلَحَ فَإِنَّ اللَّهَ يَتُوبُ عَلَيْهِ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة المائدة 39


"ከመበደሉም በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ አላህ ጸጸቱን ከርሱ ይቀበለዋል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" ሱረቱል ማኢዳህ 39


ሐ. የምንማረው ትምሕርት


"አር-ረሒም" ከሚለው መለኮታዊ ስም ብዙ ትምሕርት እናገኛለን፡፡ ከነዚህም መካከል፡-


1. ጌታችን "አር-ረሒም" የሚል መለኮታዊ ስም እንዳለው እንረዳለን፡፡ አምነንም እንቀበላለን፡፡


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ هُوَ الرَّحْمَنُ الرَّحِيمُ " سورة الحشر 22


"እርሱ አላህ ነው፤ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የሆነው፤ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ ነው።" ሱረቱል ሐሽር 22


2. በዚህ ስም እንድንለምነው፡- ጌታችን አላህን ስንለምነውና ስንማጸነው "ያ አላህ" እንደምንለው ሁሉ "ያ ረሒም" ብለንም መማጸንና መለመን እንችላለን፡፡


" قَالَ رَبِّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي فَاغْفِرْ لِي فَغَفَرَ لَهُ إِنَّهُ هُوَ الغَفُورُ الرَّحِيمُ " [القصص:16]


"«ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ለእኔም ማር አለ፡፡» ለእርሱም ምሕረት አደረገለት እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡" ሱረቱል ቀሶስ 16


3. ባሕሪውን መላበስን፡- ጌታችን አላህ በባሕሪውም ሆነ በስሞቹ ከፍጡራን ጋር አይመሳሰልም(ሹራ 11)፡፡ ለፍጡር ባሪያው ግን ከማንነቱ ጋር ተስማሚ የሆነ ባህሪ ለግሶታል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ እዝነት ነው፡፡ እርሱ ጌታችን "አር-ረሒም" ነውና ለባሪያውም እዝነትን ለገሰ፡፡ በተለይ ለነቢያችን የተለገሰው ባሕሪ ነው፡፡ ተከታዮቹ አንቀጾች ይህን ይገልጻሉ፡-


" لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِنْ أَنْفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُمْ بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ " سورة التوبة 128


"ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በርሱ ላይ ጥኑ የሆነ፣ በናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ርኅሩህ አዛኝ የሆነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ።" ሱረቱ-ተውባህ 128


" وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِلْعَالَمِينَ " سورة الأنبياء 107


" (ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም።" ሱረቱል አንቢያእ 107


3. አል-መሊክ


ሀ. ትርጓሜው


የዚህ መለኮታዊ ስም "አል-መሊክ" ትርጉም፡- ንጉስ እና ባለቤት(ማሊክ) ማለት ነው፡፡ ፍጥረተ ዓለሙ በጠቅላላ የተገኘው በጌታችን አላህ ጥበብና ችሎታ በመሆኑ እሱ የዓለሙ ሁሉ ባለቤት ነው ማለት ነው፡፡ ፈጥሮና አስገኝቶም በተግባር ዓለሙን ሲመራና ሲያስተናብር ደግሞ "ንጉስ" ይሰኛል ማለት ነው፡፡


ጌታችን አላህ ብቻውን ንጉስ ነው፡፡ በንግስናው ተጋሪ የለውም፡፡


" الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُنْ لَهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا " سورة الفرقان 2


" (እርሱ) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ የሆነ ልጅንም ያልያዘ፣ በንግሥናውም ተጋሪ የሌለው፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና፣ በትክክልም ያዘጋጀው ነው።" ሱረቱል ፉርቃን 2


" وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُنْ لَهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ وَلِيٌّ مِنَ الذُّلِّ وَكَبِّرْهُ تَكْبِيرًا " سورة الإسراء 111


"፦ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዝነው ለርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው ለርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይግባው፣ በልም ማክበርን አክብረው።" ሱረቱል ኢስራእ 111


ለ. አመጣጡ


"አል-መሊክ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 5 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡


" فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ... " سورة طه 114


"እውነተኛው ንጉስ አላህም(ከሃዲዎች ከሚሉት)ላቀ …" ሱረቱ ጣሀ 114


" إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَهَرٍ * فِي مَقْعَدِ صِدْقٍ عِنْدَ مَلِيكٍ مُقْتَدِرٍ " سورة القمر 55-54


"አላህን ፈሪዎች በአትክልቶችና በወንዞች ዉስጥ ናቸው፤(እነሱም ውድቅ ቃልና መወንጀል በሌለበት) በውነት መቀመጫ ዉስጥ ቻይ እሆነው ንጉስ ዘንድ ናቸው" ሱረቱል ቀመር 54-55


" فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ " سورة المؤمنون 116


"የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡" ሱረቱል ሙእሚኑን 116


ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-


1. ጌታችን "አል መሊክ" የሚል መለኮታዊ ስም እንዳለው እንረዳለን፡፡ አምነንም እንቀበላለን፡፡


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23





"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" ሱረቱል ሐሽር 23


" يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ الْمَلِكِ الْقُدُّوسِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ " سورة الجمعة 1


"በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ ቅዱስ፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለሆነው ያሞግሳል።" ሱረቱል ጁሙዓህ 1


2. ንግስና የሱ ብቻ መሆኑን፡- -በዚህ በምድረ ዓለም ላይ የነገሰ ዓለሙን የሚገዛ ብቸኛ ንጉስ አላህ ብቻ ነው፡፡


"... يَخْلُقُكُمْ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ خَلْقًا مِنْ بَعْدِ خَلْقٍ فِي ظُلُمَاتٍ ثَلَاثٍ ذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ الْمُلْكُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ فَأَنَّى تُصْرَفُونَ " سورة الزمر 6


"...በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ፣ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ፣ ከመፍጠር በኋላ፣ (ሙሉ) መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው። ሥልጣኑ የርሱ ብቻ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ።" ሱረቱ-ዙመር 6


" يُولِجُ اللَّيْلَ فِي النَّهَارِ وَيُولِجُ النَّهَارَ فِي اللَّيْلِ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِي لِأَجَلٍ مُسَمًّى ذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ الْمُلْكُ وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِنْ قِطْمِيرٍ " سورة فاطر 13


"ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፤ ሁሉም እተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፤ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፤ እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሺፋን እንኳ አይኖራቸውም።" ሱረቱ ፋጢር 13


" يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة التغابن 1


"በሰማያት ውስጥ ያለው በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፤ ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፤ ምስጋናም ለርሱ ነው፤ እርሱም በነገሩ ቻይ ነው።" ሱረቱ-ተጋቡን 1


" تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الملك 1


"ያ ንግሥና በእጁ የሆነው አምላክ ችሮታው በዛ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።" ሱረቱል ሙልክ 1


3. ንጉስን የሚሾም የሚሽር እሱ ብቻ መሆኑን፡-


" رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِنْ تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنْتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ " سورة يوسف 101


"ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ፤ ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፤ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፤ ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ፤ በመልካሞቹም አስጠጋኝ፤ (አለ)።" ሱረቱ ዩሱፍ 101


" قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَنْ تَشَاءُ وَتَنْزِعُ الْمُلْكَ مِمَّنْ تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَنْ تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَنْ تَشَاءُ بِيَدِكَ الْخَيْرُ إِنَّكَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة آل عمران 26


" (ሙሐመድ ሆይ!) በል- የንግሥና ባለቤት የሆንክ አላህ ሆይ! ለምትሻዉ ሰዉ ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ ንግስናን ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።" ሱረቱ አለ-ዒምራን 26


4. በመጨረሻው ዓለምም ብቸኛ ንጉስ እሱ ብቻ መሆኑን፡-


" مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ " سورة الفاتحة 4


" የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው (ምስጋና ይገባው)" ሱረቱል ፋቲሐ 4


"...وَيَوْمَ يَقُولُ كُنْ فَيَكُونُ قَوْلُهُ الْحَقُّ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنْفَخُ فِي الصُّورِ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ " سورة الأنعام 73


"…«ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡" ሱረቱል አንዓም 73


" الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ لِلَّهِ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ " سورة الحج 56


"በዚያ ቀን፣ ንግሥናው የአላህ ብቻ ነው፣ በመካከላቸው ይፈርዳል፤ እነዚያም ያመኑት፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት፣ በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው።" ሱረቱል ሐጅ 56


" الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَنِ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا " سورة الفرقان 26


"እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልረሕማን ብቻ ነው፤ በከሐዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው። " ሱረቱል ፉርቃን 26


" يَوْمَ هُمْ بَارِزُونَ لَا يَخْفَى عَلَى اللَّهِ مِنْهُمْ شَيْءٌ لِمَنِ الْمُلْكُ الْيَوْمَ لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ " سورة غافر 16


"እነርሱ ከመቃብር (በሚወጡበት) ቀን፣ በአላህ ላይ ከነሱ ምንም ነገር አይደበቅም፤ ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው? (ይባላል)፤ ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው (ይባላል)።" ሱረቱ ጋፊር 16


ይቀጥላል





የአላህ ስሞችና ባሕሪያት


በ አቡ ሃይደር


ክፍል አራት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሃ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሀቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡


ይህ ዓምድ ከጌታችን አላህ ስሞችና ባሕሪያት ጋር የምንተዋወቅበት ዓምድ ነው፡፡


" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8


" አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8


4. "አል-ቁዱስ"


ሀ. ትርጉሙ


የዚህ መለኮታዊ ስም "አል-ቁዱስ" ትርጉም፡- ከነውር የጸዳ የምሉዕ ባሕሪያት ባለቤት ማለት ነው፡፡


ለ. አመጣጡ


"አል-ቁዱስ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23


"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡


" يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ الْمَلِكِ الْقُدُّوسِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ " سورة الجمعة 1


"በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ ቅዱስ አሸናፊ ጥበበኛ ለሆነው ያሞግሳል።" (ሱረቱል ጁሙዓህ 1)፡፡


وعند مسلم من حديث عائشة رضي الله عنها أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان يقول في ركوعه وسجوده : ( سُبُّوحٌ قُدُّوسٌ رَبُّ المَلاَئِكَةِ وَالرُّوحِ )


አዒሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- የአላህ መልክተኛ በሩኩዕ ላይ ሁነው፡- "ሱቡሕ፣ቁዱስ፣ረቡል መላኢከቲ ወር-ሩሕ" ይሉ ነበር፡፡ (ሙስሊም)፡፡


ሐ. የምንወስደው ትምሕርት


-ጌታችን ከጉድለት የጠራ ንጹህ መሆኑን፡-


" وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَنْ يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ " سورة البقرة 30


"(ሙሐመድ ሆይ) ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ፤ እነርሱም) «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ (አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 30)፡፡


5. "አስ-ሰላም"


ሀ. ትርጉሙ፡-


"አስ-ሰላም" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- የሰላም ባለቤት፤ ነውር አልባ የሚል ነው፡፡


ለ. አመጣጡ፡-


"አስ-ሰላም" የሚለው ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-


" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23


"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡


ሐ. የምንማረው



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው ...

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው ...

ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት