መጣጥፎች

ምግብህና መጠጥህ


8 ሐላል ምግብ በኢስላም ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ዱዓ ተቀባይነት


እንዲያገኝ፤ ገንዘብና ቤተሰብ የተባረኩ እንዲሆኑ ሐላል መመገብ


የግድ ነው፡፡


ሐላል ምግብ በሚለው ቃል የተፈለገው ትርጓሜ፣ የተፈቀደ፣


በተፈቀደ መንገድ የተዘጋጀ፣ በሌሎች መብት ላይ ድንበር


ሳይታለፍ፣ ግፍ ሳይፈፀም የተገኘና በንፁሕ ገንዘብ የተዘጋጀ


ምግብ ለማለት ነው፡፡


የምዕራፉ ማውጫ


በምግብና መጠጥ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መመሪያዎች


አዝርዕቶችና ፍሬዎች


አስካሪ መጠጦችና አልኮል


አደንዛዥ እጽ


የባሕር ምግቦች


የየብስ እንሰሳት


ኢስላማዊ አስተራረድ


በካሃዲያን ምግብ ቤትና ማዘጋጂያ የሚገኝ ስጋ ብያኔ


ኢስላማዊ አደን


የምግብና የመጠጥ ስነ ስርዓቶች


ምግብህና መጠጥህ


174


ምግብህና መጠጥህ


በምግብና መጠጥ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መመሪያዎች


ምግቦችንና መጠጦችን በተመለከት ያለው መሰረታዊ መመሪያ፡ የሰው ልጅን በጤናው፣ በስነ ምግባሩና


በሃይማኖቱ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የሆኑ፣ በክልክለነታቸው ለብቻ ተነጥለው የተጠቀሱት ነገሮች ሲቀሩ ሌሎቹ


ሁሉ የተፈቀዱ መሆናቸውን የሚናገር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እርም ካደረጋቸው ነገሮች በስተቀር በምድር ላይ ያሉ


ነገሮችን ሁሉ ለሰው ልጆች የፈጠረላቸው መሆኑ አላህ በሰው ልጅ ላይ ከዋለው ውለታ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለናንተ የፈጠረ ነው፡፡›› (አል በቀራ 29)


>አዝርዕቶችና ፍሬዎች


እንደ አስካሪ መጠጥ ወይም


አደንዛዥ ዕጽ ዓይነት አካልና


ጤንነት ላይ አደጋ የሚያደርሱ


ወይም አዕምሮን የሚሸፍኑና


የሚያስቱ ካለሆኑ በስተቀር፣


ከበረሃና ከጫካ ዛፎች፣ ስራ


ስሮችና በተፈጥሮ የበቀሉ፣


እንዲሁም ሰዎች የሚዘሯቸው


ተክሎች ሁሉም በዓይነታቸው


ሊበሉ የሚፈቀዱ ናቸው፡፡ አስካሪ


መጠጥ ወይም አደንዛዥ ዕጽ ግን


ለአደጋና ለአዕምሮ መመረዝ ሰበብ


ስለሆኑ እርም ናቸው፡፡


ምግብህና መጠጥህ


175


> አስካሪ መጠጥና አልኮል


ማንኛውም አዕምሮን የጋረደ ወይም ከርሱ ተቀላቅሎ


ያሸነፈው ወይም ሸፍኖት ተጽእኖ ያሳደረበት ነገር


በሙሉ ኸምር ወይም አስካሪ መጠጥ ነው፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማንኛውም አስካሪ


ነገር ኸምር ነው፡፡ ማንኛውም ኸምር ደግሞ ሐራም


ነው፡፡›› (ሙስሊም 2003) አስካሪ መጠጡ፣ እንደ


ወይን፣ የቴምር እሸት፣ በለስና ዘቢብ ባሉ ፍራፍሬዎች፣


አለያም እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ ወይም ሩዝ ባሉ


አዝርዕቶች፣ ወይም እንደ ማር ባሉ ጣፋጭ ነገሮች


የተሰራ ቢሆንም ፍርዱ አንድ ዓይነት ነው፡፡


ማንኛውም አዕምሮን የጋረደ ነገር፣ በየትኛውም


ስም ቢጠራም በየትኛውም መንገድ ቢዘጋጅም ኸምር


ነው፡፡ ከጭማቂዎች ጋር ወይም ከጣፋጮችና ቸኮሌቶች


ጋር ተቀላቅሎ የተዘጋጀ ቢሆንም እንኳኸምር ነው፡፡


አዕምሮን መጠበቅ


ይህ ታላቅ ሃይማኖት፣ በቅርቢቱም ሆነ በወዲያኛው


ዓለም የባሮችን ጥቅም በማረጋገጥና በማስጠበቅ ላይ


ትኩረት የሰጠ ሃይማኖት ነው፡፡ ከነዚህም ጥቅሞች


መካከል እጅግ አንገብጋቢና አስፈላጊ ለሆኑ አምስት


ነገሮች ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ አድርጎላቸዋል፡፡ እነሱም


ሃይማኖት፤ ነፍስ፤ አዕምሮ፤ንብረትና ዘር ናቸው፡፡


አዕምሮ የኃላፊነት መሰረት ነው፡፡ የሰው ልጅ


መለኮታዊ ክብርና ምርጫን የተጎናጸፈበት አካል ነው፡፡


በመሆኑም ኢስላማዊው ድንጋጌ እርሱን ከሚያበላሽና


ከሚያዳክም ማናቸውም ነገር ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ


አድርጎለታል፡፡


የኸምር ፍርድ


ኸምር መጠጣት ከከባባድ ወንጀሎች መካከል የሆነ


ወንጀል ነው፡፡ በቁርኣንና በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች


ላይ የኸምርን እርምነት የሚያውጁና የእሷን ጉዳይ


አጥብቀው የሚያወግዙ መልክቶች ተላልፈዋል፡፡


ከነኚህም መካከል፡


• አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ


ሆይ የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማርም፣ ጣኦትም፣


አዝላምም፣ ከሰይጣን ስራ የኾኑ እርኩስ ብቻ


ናቸው፡፡ (እርኩስን) ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡


፡›› (አልማኢዳ 90)


አላህ (ሱ.ወ) ኸምርን የገለጻት በነጃሳነቷ ነው፡፡


የሰይጣን ተግባር መሆኗን ከገለጸም በኋላ መዳን


የምንፈልግ ከሆነ ከእርሷ እንድንርቅም አዞናል፡፡


• ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማንኛውም


አስካሪ መጠጥ ኸምር ነው፡፡ ማንኛውም ኸምር


ደግሞ ሐራም ነው፡፡ በዱንያ ላይ ኸምርን የጠጣና


እሱን አዘውታሪ ሆኖ የሞተ በአኼራ አይጠጣም፡፡››


(ሙስሊም 2003)


• ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኸምር መጠጣት ከኢማን ጋር


የሚቃረንና እሱን የሚያጓድል እንደሆነ ሲገልጹ


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድም ሰው በሚጠጣበት


ቅጽበት ላይ ሙእሚን ኾኖ ኸምርን አይጠጣም፡፡››


(አል ቡኻሪ 5256 / ሙስሊም 57)


> ኢስላም አዕምሮን ከሚረብሹትና ከሚጎዱት ነገሮች ሁሉ


ጠብቆታል፡፡


ምግብህና መጠጥህ


176


• ኢስላም ኸምርን በሚጠጣ ሰው ላይ ቅጣትን


በይኗል፡፡ ኸምርን የሚጠጣ ሰው ክብሩ


ይጎድፋል፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ ታማኝነቱ


ይወገዳል፡፡


• በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ) እስከሚሞት ድረስ


ኸምርን በመጠጣት ላይ የዘወተረንና በመሰል


ተግባር ላይ የተሰማራን ሰው አሳማሚ ቅጣት


እንደሚጠብቀው ዝቷል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ


ብለዋል፡- ‹‹አላህ (ሱ.ወ) የሚያሰክርን ነገር


የሚጠጣ ሰውን የመግል እንጥፍጣፊን ሊያጠጣው


ቀጠሮ ዝቶበታል፡፡›› (ሙስሊም 2002) ይህ መግል


የጀሀነም ሰዎች ቁስል እዥ ነው፡፡


• ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ኸምርን በመጠጣት ላይ


የተሳተፈም ሆነ የረዳ ሰው በዛቻው ውስጥ


ይካተታል፡፡


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኸምር ዙሪያ ተሳታፊና ተያያዥነት


ያላቸውን አስር ሰዎች ረግመዋል፡፡ ጠማቂውን፣


አስጠማቂውን፣ ጠጪውን፣ ተሸካሚውን፣


አሸካሚውን፣ ቀጂውን፣ ሻጩን፣ ዋጋውን


የሚበላውን፣ እሱን ገዝቶ ጋባዡን፣ እና የሚገዛለትን


ወይም ተጋባዡን ረግመዋል፡፡ (አል ቲርሚዚ 1295)


> አደንዛዥ እጽ


የሚበቅልም ይሁን በፋብሪካ የተመረተ አደንዛዥ


እጽን በአፍንጫ በመሳብም ሆነ በመዋጥ፣ ወይም


በመርፌ መልክ በመወጋት መጠቀም ወይም መውሰድ


ከታላላቅ ወንጀሎችና ሃጢኣቶች መካከል ነው፡፡ እሱ


አዕምሮን የሚጋርድ ከመሆኑም በተጨማሪ የሰው


ልጅን ነርቮች ያበላሻል፡፡ አደንዛዥ እጽን የሚያዘወትር


ሰው በተለያዩ የነርቭና የመንፈስ በሽታዎች ይጠቃል፡፡


ምናልባትም ለሞቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ነፍሶቻችሁንም አትግደሉ


አላህ ለናንተ አዘኝ ነውና፡፡›› (አል ኒሳእ 29)


> የባሕር ምግቦች


የባሕር ምግቦች ሲባል የሚጠቁመው በውሃ ውስጥ


እንጂ የማይኖሩትን እንስሳት ነው፡፡


ባሕር ደግሞ ብዙ ውሃ ያለው ሲሆን እንደ ሐይቅና


የመሳሰሉት ብዙ ውሃ ያለባቸው የውሃ ዓይነቶችም


በዚሁ ስር ይካተታሉ፡፡


እነኚህ የባሕር ምግቦች፣ እንሰሳት ወይም እጽዋቶች


ቢሆኑም የታደኑ ወይም ሞተው የተገኙ ሆነው በጤንነት


ላይ ጉዳት የማያስከትሉ ከሆነ እነሱን መመገብ የተፈቀደ


ነው፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የባሕር ታዳኝና ምግቡ


ለናንተም ለመንገደኞችም ተፈቀደ፡፡›› (አልማኢዳ 96)


ታዳኝ ማለት ከነነፍሱ የተያዘ ማለት ነው፡፡ ምግቡ


የተባለው ደግሞ ከሞተ በኋላ ባሕር የተፋው ማለት


ነው፡፡


ምግብህና መጠጥህ


177


> የየብስ እንሰሳት


የየብስ እንሰሳትን መብላት የሚፈቀደው ሁለት


መስፈርቶች ከተሟሉ ነው፡፡


እነሱን መመገብ የተፈቀደ


መሆናቸውና


አደናቸው ወይም


እርዳቸው ኢስላማዊውን


ሕግ በተከተለ መልኩ


የተከናወነ መሆኑ ነው፡፡


1 2


የሚፈቀዱ እንሰሳት የትኞቹ ናቸው?


ሐራምነታቸው ከቁርኣንና ከሱና ማስረጃ ከተገኘላቸው


ውጭ ያሉ ሁሉም እንሰሳት መሰረታቸው የተፈቀደ ነው፡፡


የተከለከሉት የሚከተሉት ናቸው፡


አሳማ፡


በኢስላም ውስጥ አሳማ እርም የተደረገና


እርኩስ ነው፡፡ እያንዳንዱ ገላውና አካሉ


ከርሱም የሚወጣ ማንኛውም ነገር እርምና


ነጃሳ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


‹‹በክት፣ ፈሳሽ ደምም፣ የእሪያ (አሳማ) ስጋም


… በናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡››


(አል ማኢዳ 3)


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የአሳም ስጋ አሱ


እርኩስ ነውና፡፡›› (አል አንዓም 145) እርኩስ


ማለት ነጃሳ ማለት ነው፡፡


ማንኛውም አዳኝ ጥርሶች ያሉት አውሬ፡


ይህ ማለት ማንኛውም ስጋ በሊታ አውሬ


ለማለት ነው፡፡ እንደ አንበሳና ነብር ያሉ


ትላልቆችና ግዙፎች ቢሆኑም አለያም እንደ


ድመትና የመሳሰሉ ትናንሾችም ቢሆኑ ፍርዱ


ልዩነት የለውም፡፡ ውሻም በዚሁ ስር የሚካተት


ነው፡፡


ማደኛ ያላቸው በራሪ አዕዋፍ፡


ይህ ስጋ በሊታ የሆኑ አዕዋፍን በሙሉ


የሚመለከት ነው፡፡ ቁራ፣ ንስር አሞራንና


የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡





ነፍሳት፡


ማንኛውም በየብስ የሚኖሩ ነፍሳትን


መብላት አይፈቀድም ምክንያቱም እነርሱ


ለመታረድ አይመቹም፡፡ ከነሱ መካከል


አንበጣ ለብቻው ተነጥሎ ይወጣል፡፡


እሱን መብላት ይፈቀዳል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት ሙት ነገሮች


ተፈቅደውልናል፤ አሳና አንበጣ፡፡›› (ኢብኑ


ማጃህ 3228)


እባብ፣ ዘንዶና አይጥ፡


እነኚህን መብላት ክልክል ነው፡፡ እንድንገላቸው


ታዘናል፡፡ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል፡


- ‹‹አምስት ነገሮች አጥፊዎች ናቸው፡፡ በሐጅ


ትጥቅ ላይ ሆኖም፣ ተፈቶም እነሱን መግደል


ይፈቀዳል፡፡ እነሱም፡ እባብ፣ ጥቁር አሞራ፣


አይጥ፣ ተናካሽ ውሻና ቀርጮ፡፡›› (አል ቡኻሪ


3136 / ሙስሊም 1198)


የቤት አህያ፡


ዕቃን ከቦታ ቦታ ለመጓጓዝና ለመጫን


የሚገለገሉበት አህያ ነው፡፡





> በቁርኣንና በሱና ለብቻቸው ተነጥለው የተነገሩት ሲቀሩ


እንሰሳትን ካረዱ በኋላ መመገብ ይፈቀዳል፡፡


ምግብህና መጠጥህ


178


የተፈቀዱ እንሰሳት ዓይነት


ከነዚህ መካከል አላህ የፈቀዳቸው በሁለት ይከፈላሉ፡፡


• በበረሃ የሚኖሩ፣ ከሰው ልጅ የሚሸሹ፣ ሰዎች


ይዘውት ለማረድ የማይችሉትን የዱር እንስሳ


ሕጋዊ በሆነ መንገድ ልናድነው ይፈቀድልናል፡፡


• ሌላው ዓይነት ደግሞ ለማዳና በቀላሉ ሊያዝ


የሚችል ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ደግሞ በኢስላማዊ


አስተራረድ ካልታረደ በስተቀር መመገቡ


አይፈቀድም፡፡


ኢስላማዊ አስተራረድ


ኢስላማዊ መስፈርቶችን ያሟላ እርድ ማለት ነው፡፡


የኢስላማዊው አስተራረድ መስፈርቶች


የሚያርደው ግለሰብ ለማረድ ብቃት ያለው መሆን


አለበት፡፡ እሱም ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት


ባለቤቶችን፣ ክርስቲያንና አይሁዳውያንን የሚያካትት


ሲሆን እርዱን መምረጥ የሚችልና ስለ እርድ


የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡


የሚያርድበት መሳሪያ እንደ ቢላዋ ያለ የሚቆርጥ፣


ደም የሚያፈስና ለማረድ ብቃት ያለው መሆን


አለበት፡፡ እንሰሳቱን በክብደቱ በሚጫን መሳሪያ፣


ወይም የእንሰሳቱን ጭንቅላት በመግጨት ወይም


በኤሌክትሪክ ንዝረት በማቃጠል መግደል እርም


ነው፤ አይፈቀድም፡፡


እጁን ለማረድ በሚያንቀሳቅ ጊዜ ‹‹ቢስሚላህ››


በማለት የአላህን ስም ማውሳት፡፡


በእርድ ላይ መቆረጥ ያለባቸውን ክፍሎች መቁረጥ፡


፡ እነርሱም የአየር ቧንቧ፣ ጉሮሮና ሁለቱ የደም ጋኖች


ናቸው፡፡ እነኚህ፣ በአንገት ግራና ቀኝ ያሉ የደም


ስሮች ናቸው፡፡ ከነኚህ አራት አካላት መካከል ሦስቱን


ቢቆርጥ በቂ ነው፡፡


እነኚህ ጉዳዮች ከተሟሉ እርዱን መብላት ይበቃል፡፡ ነገር


ግን ከእነኚህ መስፈርቶች መካከል አንዱ ከተጓደለ እርሱን


መብላት አይፈቀድም፡፡





የስጋ ዓይነቶች በምግብ ቤትና በልኳንዳዎች


የሚገኝ ስጋ


ሙስሊም ወይም የመጽሐፍቱ ባለቤቶች


ያላረዷቸው፣ ቡዲሂስቶች፣ ሂንዶዎች፣


እንዲሁም ሃይማኖት የለሾች ያረዷቸው፣


ያልተፈቀዱና እርም የተደረጉም ናቸው፡፡


ብዙሃኑ ነዋሪቿ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍ


ባለቤቶች ባልሆነች ሀገር ውስጥ የሚገኙ ምግብ


ቤቶችና ልኳንዳዎችም በዚህ ስር ይካተታሉ፡፡


ተቃራኒ የሆነ ብይን እስካልተረጋገጠለት ድረስ


ይህ ዓይነቱ ሐራም ነው፡፡


ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት ባለቤት የሆነ


አራጅ ኢስላማዊውን ሕግ በተከተለ መልኩ


ያረደውን መብላት በአንድ ድምፅ የሚፈቀድ


ወይም ሐላል መሆኑ የጸደቀ ነው፡፡


አንድ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት ባለቤት


የሆነ ሰው ኢስላማዊውን ሕግ ባልተከተለ


መንገድ እንስሳው እራሱን ስቶ እንዲሞት፣


ወይም ውሃ ውስጥ ሰጥሞ እንዲሞት የተደረገ


እንስሳ ስጋ፡፡ ይህን ዓይነቱን መብላት ክልክል


ነው፡፡


አንድ አስተራረድ በማያውቅ የመጽሐፍት ባለቤት


በሆነ ግለሰብ ወይም ምግብ ቤትና ልኳንዳ


ውስጥ የታረደ፡፡ በመሰረቱ ይህ ዓይነቱም ከነሱ


እርድ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ እናም ምንም


እንኳ ሐላል መሆኑ ግልጽ የሆነን ስጋ ፈልጎ


መመገቡ በላጭ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለውን


እርድ መመገብ የተፈቀደ መሆኑን የሚያጸድቅ


አስተያየት ትክክል ነው፡፡ ሲመገቡት ግን የአላህን


ስም ማውሳት መዘንጋት የለበትም፡፡





> የመጽሐፍቱ ባለቤቶች፡ አይሁድና ነሣራ፣ ኢስላማዊውን


አስተራረድ ተከትለው ያረዱት ከሆነ፣ አላህ(ሱ.ወ) እርዱን


እንድንበላ ፈቅዶልናል፡፡


ምግብህና መጠጥህ


179


> ሸሪዓዊው አደን


ሸሪዓዊው አደን የሚፈቅደው፣ ስጋቸው የሚፈቀድ፣ ነገር ግን እነርሱን በቁጥጥር ስር አውሎ መባረክና ማረድ


የማይመች የሆኑ እንስሳትን ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ስጋ በሊታ ከሆኑት በጫካና በዱር የሚገኙ አዕዋፍ፣ እንዲሁም ሚዳቋ፣


ጥንቸልና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡


ለአደን መስፈርቶች አሉት፡፡ ከነርሱም መካከል፡


አዳኙ፣ ጤናማ አዕምሮ ያለው፣ አደንን አስቦ የወጣ፣ ሙስሊም አለያም ከመጽሐፍት ባለቤት የሆነ መሆን አለበት፡፡ ጣዖት


አምላኪ ወይም አዕምሮን የሳተ ሰው ያደነው አይፈቀድም፡፡


እንሰሳው በመበርገግና ከሰው በመራቁ ምክንያት ተባሮ ሊያዝና ሊታረድ የማይችል መሆን አለበት፡፡ እንደ ዶሮ፣ ፍየልና


በግ፣ እንዲሁም ከብት አይነት ከሆነ ማደን አይቻልም፡፡


እንሰሳው የሚገደልበት መሳሪያ እንደ ቀስት፣ ጥይትና የመሳሰሉ መሳሪያዎች ዓይነት በስለቱ የሚገድል መሆን አለበት፡፡


እንደ ድንጋይና መሰል በክብደቱየሚገድል ዓይነት፣ ሰውዬው እንሰሳው ከመሞቱ በፊት ደርሶ የሚባርከውና የሚያርደው


ካልሆነ በስተቀር መመገቡ አይፈቀድም፡፡


ማደኛ መሳሪያውን ከመተኮሱ ወይም ከመልቀቁ በፊት፣ ‹‹ቢስሚላህ›› በማለት የአላህን ስም ማውሳት አለበት፡፡


እንሰሳውን ወይንም በራሪውን ካደነው በኋላ ሳይሞት በሕይወት ካገኘው በማረድ ሐላል ሊያደርገው ይገባል፡፡


ለመብላት ካልሆነ በስተቀር እንሰሳትን ማደን እርም ነው፡፡ ያደኑትን ላይበሉ፣ ለመዝናናትና ለሌላ ጥቅማ ጥቅም


እንሰሳትን ማደን ክልክል ነው፡፡





ምግብህና መጠጥህ


180


> የመብላትና የመጠጣት ስርዓት


በወርቅና ብር ዕቃዎች፣ ወይም የሁለቱ ቅብ በሆኑ


ዕቃዎች ላይ መመገብ ክልክል ነው፡፡ ይህ የሆነበት


ምክንያት፣ በዚህ ውስጥ ብክነት፣ ድንበር ማለፍ፣


አና የድሆችን ቀልብ መስበር ስላለበት ነው፡፡ ነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በወርቅና ብር ዋንጫዎች


አትጠጡ፤ በነርሱም ትሪዎች ላይ አትመገቡ፤ እርሷ


በዚህች ዓለም የነርሱ (የከሃዲያን)፣ በወዲያኛው


ዓለም ደግሞ የኛ ነች፡፡›› (አል ቡኻሪ 5110 / ሙስሊም


2067)


ከምግብ በፊትና በኋላ እጅን መታጠብ፡፡ በእጅ


ላይ ቆሻሻና የምግብ ቅሪት ካለበት ደግሞ መታጠቡ


የጠበቀ ይሆናል፡፡


መብላት መጠጣት ከመጀመሩ በፊት፣ ‹‹ቢስሚላህ››


ማለት፡፡ ትርጉሟ፡ በአላህ ስም በረከትን እፈልጋለሁ፣


በርሱም እታገዛለሁ፤ ማለት ነው፡፡ ከረሳና በምግቡ


መሐከል ካስታወሰ፣ ‹‹ቢስሚላሂ ፊ አወሊሂ


ወኣኺሪሂ›› (መጀመሪያውንም መጨረሻውንም


በአላህ ስም) ይላል፡፡





ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመመገብ ስርዓትን የማያውቅና


የማያሰምርን አንድ ትንሽ ሕፃን ልጅ አይተው


ሊያስተምሩት እንዲህ አሉት፡- ‹‹አንተ ልጅ ሆይ!


የአላህን ስም አውሳ፤ በቀኝ እጅህ ብላ፤ ከአጠገብህም


ብላ፡፡›› ( አል ቡኻሪ 5061 / ሙስሊም 2022)


በቀኝ እጅ መብላትና መጠጣት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በግራ እጃችሁ አትብሉ፤ ሸይጣን


የሚበላው በግራ እጁ ነው፡፡›› ( ሙስሊም 2019)


ቆሞ ባይበላና ባይጠጣ ይወደድለታል፡፡


አንድ ሰው እርሱ አጠገብ ካለ ምግብ መብላትና


ሰዎች ፊት ለፊት ካለው አለመብላት ከአደብ ነው፡፡


ከሰዎች ፊት እያነሱ መብላት፣ ስርዓት ማጣት ነው፡


፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለልጁ፣ ‹‹ከአጠገብህም ብላ፡፡››


ብለውታል፡፡





አላህ ለሰው ልጆች የዋለውን ጸጋ


ለማስታወስ፣ ከበሽታዎች ለመጠበቅ፣


ማባከንን እና፣ ድንበር ከማለፍ መጠበቅን


ይመስል ዓላማንና አምላካዊ ጥበብን


ለማረጋገጥ፣ አላህ (ሱ.ወ) በምግብና


መጠጥ ውስጥ ብዙ ስርዓቶችን ደንግጓል፡፡


ከነኚህ ስርዓቶች መካከል የሚከተሉት


ይገኙበታል፡፡


ምግብህና መጠጥህ


181


ጉርሻ ከወደቀ ማንሳትና ያለባትን ቆሻሻ ማስወገድ እስከተቻለ ድረስ ማበስና መብላት ይወደዳል፡፡ በዚህ ውስጥ ጸጋንና


ምግብን መጠበቅ አለበት፡፡


የምግብን ነውር አለመናገር፣ አለማዋደቅና አለመናቅ፡፡ ከተቻለ ያድንቅ፤ አለበለዚያ፣ ይተወውና ዝም ይበል፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንዴም ምግብን አነውረው አያውቁም፡፡ ከፈለጉት ይበሉታል፤ ከጠሉት ደግሞ ይተውታል፡፡ (አል


ቡኻሪ 5093/ሙስሊም 2064)


ምግብን አለማብዛትና በርሱም አለመወጠር፡፡ ይህ የበሽታና የድብርት ምንጭ ነው፡፡ መሐከለኛ መሆን የነገሮች


ሁሉ ያማረው ገጽታ ነው፡፡ ጉዳዩ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት ነው፡፡ ‹‹የሰው ልጅ ከሆድ የከፋን ዕቃ አልሞላም፡፡


ለኣደም ልጅ፣ ወገቡን ቀና የሚያደርግበት ጥቂት ጉርሳዎች ይበቁታል፡፡ መብላት የግድ ከሆነ ግን፣ አንድ ሦስተኛውን


ለምግቡ፣ ሌላ አንድ ሦስተኛውን ለመጠጡ፣ ሌላ አንድ ሦስተኛውን ደግሞ ለአየር ያድርገው፡፡›› (አትቲርሚዚ


2380/ ኢብኑ ማጃህ 3349)


ሲያበቃ ‹‹ አልሐምዱሊላህ ›› በማለት ከሰዎች ብዙዎችን ሳያካትት እርሱን በመመገብ ያበለጸገውን አላህን ያመሰግናል፡፡ በዚህም


ላይ አክሎ፣ ((አልሐምዱ ሊላሂ አለዚ አጥዐመኒ ሓዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚኒ ወላ ቁዋህ)) -‹‹የኔ ብልሃትና ኃይል


ሳይኖርበት ይህንን የመገበኝና የሰጠን አላህ ይመስገን›› ማለት ይችላል፡፡





ልብስህ



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ

ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ...

ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ማስገባት እና የፈጠራዉ አደጋ