መጣጥፎች

ምጽዋትህ (ዘካህ)


5


አላህ (ሱ.ወ) ምጽዋትን ግዴታ አድርጎ ደንግጓል፡፡ ከኢስላም


ማዕዘናት መካከል ሦስተኛ አድርጎታል፡፡ እሷን የማይፈፅም


ሰውን ብርቱ በሆነ ቅጣት ዝቶበታል፡፡ ኢስላም፣ ንስሃ


መግባትን፣ ሠላት ማቋቋምንና ምጽዋት መስጠትን ከሙስሊሞች


የወንድማማችነት ትስስር ጋር አቆራኝቶታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ቢፀፀቱም፣ ሠላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም


ቢሰጡ፣ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡›› (አል ተውባ 11)


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹ኢስላም በአምስት መሰረታዊ ጉዳዮች


ላይ ተገነባ፡፡›› ‹‹…..ሠላትን ማቋቋም፣ ምጽዋትን መስጠት››


ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 8 / ሙስሊም 16)


የምዕራፉ ማውጫ


የምጽዋት ድንጋጌ ዓላማዎች


ምጽዋት ማውጣት ግዴታ የሚሆንባቸው ጉዳዮች


ወርቅና ብር


ንብረትና ተቀማጭ ገንዘብ


ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች


የምድር በቆልቶች


የእንሰሳት ሀብት


ምጽዋት የሚሰጠው ለነማን ነው?


ምጽዋትህ (ዘካህ)


138


ምጽዋት


ዘካ ማለት አላህ በሙስሊሞች ላይ


ግዴታ ያደረገው ቀለል ያለ ገንዘብ


መጠን ነው። የድሆችንና የምስኪኖችን


ችግር ለማቅለልና ለሌሎች ዓላማዎች


ባለሀብቶች የሚሰጡት ነው።


የምጽዋት ዓላማዎች


አላህ (ሱ.ወ) ምጽዋትን በሙስሊሞች ላይ ግዴታ


ያደረገበት ከባባድ ዓላማዎች አሉት፡፡ ከፊሎቹን


እንደሚከተለው እንጠቅሳለን፡


ገንዘብን መውደድ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ


ባህሪ ሲሆን፣ ይህ ባህሪው ገንዘቡን በመያዝና


በመጠበቅ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት እንዲኖረው


ያደርገዋል፡፡ ኢስላማዊው ሕግ ነፍስ ከዘቀጡ


የስስታምነትና ልክ የለሽ የገንዘብ ጥማት ባህሪዎች


እንድትጸዳና እንዲሁም ከቁሳቁስ ፍቅርና


እንድትላቀቅ ምጽዋትን በግዴታነት ደነገገ፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከገንዘቦቻቸው


ስትኾን፣ በርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው


የኾነች ምጽዋትን ያዝ፡፡›› (አልተውባ 103)


ምዕዋት መስጠት በማኅበረሰቡ መካከል


የመደጋገፍና የመዋደድ መሰረትን ይጥላል፡፡ የሰው


ልጅ ነፍስ ውለታ የዋለላትን አካል በመውደድ


ላይ የተገራች ናት፡፡ በምጽዋት አማካይነት


የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ልክ እንደ


አንድ ግንብ ከፊሉ ከፊሉን የሚደግፍና እርስ


በርሳቸው የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ሆነው


ይኖራሉ፡፡ በመሐከላቸው ስርቆት፣ ዘረፋና


ማጭበርበር በብዛት የማይታየውም በዚሁ


ምክንያት ነው፡፡


በምጽዋት፣ ለዓለማት ጌታ ሙሉ ለሙሉ መማረክና


ፍጹም ታዛዥ መሆን ይረጋገጣል፡፡ አንድ ባለ


ሃብት፣ ከንብረቱ ላይ ምጽዋትን በሚያወጣ ጊዜ


የአላህን ሕግጋት በመተግበርና ትዕዛዙን በመፈፀም


ላይ ሲሆን በተሰጠው ጸጋ ላይ የጸጋውን ባለቤት


እያመሰገነም ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹ብታመሰግኑም


እጨምርላችኋለሁ፡፡›› ይለናን፡፡ (ኢብራሂም 7)





ምጽዋትን በመተግበር ማኅበራዊ ዋስትና


ይረጋገጣል፣ እንዲሁም በተለያዩ የማኅበረሰቡ


ክፍሎች መካከል አንጻራዊ የሆነ የኢኮኖሚ


መመጣጠን ይከሰታል፡፡ በተጨማሪም


ምጽዋትን ለሚገባቸው የማኅበረሰቡ ክፍሎች


መስጠት፣ ሀብት በተወሰኑ የማኅበረሰቡ


ክፍሎች ውስጥ የተገደበና የተከማቸ እንዳይሆን


ያደርጋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹ከናንተ ውስጥ


በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይሆን፡፡››


ይላል፡፡


4


> ገንዘብን መውደድ ከሰው ልጅ የተቀረፀ ተፈጥሮአዊ


መለያ ሲሆን ኢስላም ነፍስን ወደ ማንጻትና በገንዘብ ላይ


የተንጠለጠሉ ወደ አለመሆን ተጣርቷል።


ምጽዋትህ (ዘካህ)


139


ምጽዋት ሊወጣለት ግዴታ የሚሆን ንብረት የትኛው ነው?


አንድ ሰው ለራሱ በሚጠቀምበት ንብረቱ ላይ ምጽዋት የማውጣት ግዳጅ የለበትም፡፡ ለምሳሌ፣ ዋጋው ምንም ያህል


ቢወደድም የሚኖሪያ ቤቱ፣ እንዴትም ያለ ዘመናዊና የቅንጦት ቢሆንም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስበት መኪናው ላይ፣


ምጽዋት የማውጣት ግዴታ የለበትም፡፡ በሚለብሰው፣ በሚበላውና በሚጠጣውም ነገር ላይ እንዲሁ የግዴታ ምጽዋት


የለበትም፡፡


አላህ (ሱ.ወ) ምጽዋትን ግዴታ ያደረገው በግል ጉዳይ ላይ ግልጋሎት የማይሰጡ በሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ሲሆን


እነኚህ ንብረቶች በባሕሪያቸው እየጨመሩና እየፋፉ የሚሄዱ ናቸው፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡-


1 ለጌጥነትና ለውበት የማይለበስ የሆነ ወርቅና ብር


የወርቅና የብር ክምችትም ሆነ ማንኛውም ንብረት፣ ኢስላማዊው ሕግ የገደበውን


መጠን (ሂሣብ) ካልሞላ፣ እንዲሁም ሳይቀንስ አንድ የጨረቃ ዓመት ማለትም


354 ቀናቶች ካልዞረበት በስተቀር ምጽዋት(ዘካ) ሊወጣበት ግዳጅ አይሆንም፡፡


በሁለቱ ማዕድናት ምጽዋት የማውጪያ መጠን (ሂሣብ)


ሂሣብ፣ ለወርቅ 85 ግራምና ከዚያ በላይ ለብር ደግሞ 595 ግራምና ከዚያ


በላይ ነው፡፡


አንድ ሙስሊም ይህን መጠን የሚደርስ ወርቅ ወይም ብር ካለውና አንድ ዓመት


ከዞረበት፣ ከንብረቱ 2.5 ፐርሰንቱን ይመጸውታል(ዘካ ያወጣል)፡፡


2 ተቀማጭ ገንዘብና የተለያዩ የመገበያያ ኖቶች እንደ ዓይነታቸው


በካሽ በእጁ ያለ ወይም በባንክ አካውንት ውስጥ የሚገኝ ገንዘብ ዘካ


ይወጣለታል፡፡


የግዴታ ምጽዋት(ዘካ) አወጣጥ፡


የገንዘቡንና የመገበያያውን ነገር ሊገዛ ከሚችለው የወርቅ መጠን ጋር በማስላት፣


መጠኑ ወርቅ ዘካ ከሚወጣበት ሂሣብ ጋር እኩል ከሆነና ከዚያም ከበለጠ ዘካ


ያወጣለታል፡፡ ገንዘቡ ከ85 ግራም ወርቅ ጋር ከተስተካከለ ወይም ከበለጠ፣


እንዲሁም በሰውዬው ይዞታ ስር ኾኖ ሳይቀንስ አንድ የጨረቃ ዓመት ካለፈበት፣


የንብረቱን 2.5 ፐርሰንት ዘካ ያወጣል፡፡


የወርቅ ዋጋ ከፍ፣ ዝቅ ሊል፣ ሊወዋወጥ ይችላል፡፡ በአንድ ሰው ላይ ዘካ


ማውጣት ግዳጅ በሚሆንበት ወቅት የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ 25 ዶላር ነው


ብለን ብናስብ፣ በዚያ ወቅት የዘካ ማውጫ መጠን ወይም ሂሣብ የሚከተለው


ይሆናል፡፡


25 ዶላር/ግ.ም X 85ግ.ም = 2125 ዶላር ይሆናል፡፡ 85ግ.ም- ምጽዋት


ማውጣት ግዳጅ የሚሆንበት የወርቅ መጠን ሲሆን ይህ ቋሚና የማይለወጥ


ነው፡፡ 2125 ዶላር-በቀረበው ምሳሌ መሰረት ዘካ ግዳጅ የሚሆንበት የገንዘብ


መጠን(ሂሣብ) ነው፡፡ ስለዚህ የዘካው መጠን- 2.5% X 2125 ዶላር = 53.125


ዶላር ይሆናል፡፡


ምጽዋትህ (ዘካህ)


140


3 ለንግድ የቀረቡ ዕቃዎች


ለንግድ የተዘጋጁ፣ እንደ ሪል ኢስቴቶች፣ ቤቶች፣ ሕንፃዎች ያሉ


የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡ ወይንም ምግብ ነክ አና አላቂ ሸቀጦች በዚህ


ስር ይገባሉ፡፡


የዘካው አወጠጥ፡ ነጋዴው ለንግድ ዕቃዎቹን በሙሉ ዓመት


ዞሮባቸው ከሆነ ዋጋቸውን ያሰላል፡፡ የሚያሰላበት ዋጋም ዘካውን


ሊያወጣ በተነሳበት ዕለት ባለው የገበያ ዋጋ መሰረት ነው፡፡ የቃዎቹ


ዋጋ የዘካ ማውጫ መጠን (ሂሣብ) ከደረሰ፣ ከሱ ላይ 2.5 ፐርሰንት


ዘካ ያወጣለታል፡፡


4 ከምድር የሚበቅሉ፡ አዝመራ፣ ፍራፎዎችና የእህል አይነቶች


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ


ካፈራችሁትና ከዚያም ለናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ


ለግሱ፡፡›› (አል በቀራ 267)


ዘካ ማውጣት ግዴታ የሚሆነው በተወሰኑ የአዝርዕት ዓይነቶች


ላይ እንጂ በሁሉም አይደለም፡፡ ይህም በኢስላማዊው ድንጋጌ


መሰረት ዘካ የሚወጣለትን መጠን ከደረሰ ብቻ ነው፡፡


የሰዎችን ልፋትና ድካም ከግምት ውስጥ ከማስገባት አንጻር፣ ዘካ


የሚወጣው ብዛት በዝናብና በወንዝ ውሃ በለሙና በሰው ኃይል


ወይም መስኖ በለሙት መካከል ልዩነት አለው፡፡


5 እንደ ላም፣ ግመልና ፍየል ያሉ የእንሰሳት ሃብት፡ ባለሃብቱ፣


እነሱን በመቀለብ የማይቸገርና የማይለፋ ከሆነ እንዲሁም በግጦሽ


ላይ ተሰማርተው ውለው የሚገቡ ከሆነ ዘካ ይወጣላቸዋል፡፡


የሚወጣበትን መጠን (ኒሣብ) የሚወጣለትን መጠንና የመሳሰሉትን


ዝርዝር መረጃዎች ከፊቂህ መጽሐፍት ላይ የምናገኘው ይሆናል፡፡


ምጽዋትህ (ዘካህ)


141


ምጽዋት የሚሰጠው ለነማን ነው?


ኢስላም ዘካ የሚሰጣቸውን ክፍሎች ገድቦ አስቀምጧል፡፡ አንድ ሙስሊም ከነኚህ ክፍሎች መካከል ለአንዱ ብቻ


ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ አካሎች ዘካውን መስጠት ይችላል፡፡ ለሚገባቸው ክፍሎች ሊያከፋፍሉለት ለሚችሉ በጎ


አድራጎት ድርጅቶችና ማህበሮች መስጠትም ይችላል፡፡ ዘካን በሀገር ውስጥ ማከፋፈሉ በላጭ ነው፡፡


ዘካ የሚገባቸው ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡


ድሆችና ችግረኞች፡ አንገብጋቢና መሰረታዊ


ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላትና ለመሸፈን በቂ


አቅም የሌላቸው ናቸው፡፡


ዘካን በመሰብሰብና በማከፋፈል ሰራ ላይ


የተሰማሩ የዘካ ሰራተኞች


ከአሳዳሪው እራሱን በመግዛት ነፃ ለመውጣት


ለሚጥር ባሪያ፡፡ ይህ ሰው ዘካን በመውሰድ


ነፃነቱን ያውጃል፡፡


ብድር ተበድሮ መክፈል ያቃተው ሰው፡


የተበደረው ብድር ለሰዎች በጎ ለመዋልና


ለሕዝባዊ ጥቅም ወይም ለግል ጉዳይ ቢሆንም


ልዩነት አይኖረውም፡፡


በጦር ግንባር በአላህ መንገድ ላይ ለሚፋለም ጀግና፡


እነኚህ ደግሞ ከሃይማኖታቸውና ከአገራቸው


ጠላትን በመመከትና በመጋፈጥ ላይ ያሉ ተዋጊዎች


ሲሆኑ ማንኛውም ኢስላምን ለማስፋፋትና


ለማሰራጨት፣ የአላህን ቃል ከፍ ለማድረግ የሚሰራ


ስራም በዚሁ ስር የሚካተት ነው፡፡





> ድሆች ማት ለአስፈላጊና መሠረታዊ ፍላጐቶችን የሚያሟሉበት አቅም የሌላቸው ማለት ነው።


ልቦናቸው ከኢስላም ጋር በመላመድ ላይ ላሉ


አዲስ ሙስሊሞች፡ እነኚህ፣ ከሃዲያን የነበሩ፣


በቅርቡ ኢስላምን የተቀበሉ፣ ወይም ይሰልማሉ


ተብሎ የሚከጀሉና ተስፋ የሚጣልባቸው ሰዎች


ናቸው፡፡ ለእነኚህ ዘካ የሚሰጧቸው ግለሰቦች


ሳይሆኑ፣ መንግሳታዊ ክፍሎችና ጠቃሚነቱን


ሊያገናዝቡና ሊመረምሩ የሚችሉ የበጎ አድራጎት


ድርጅቶች ናቸው፡፡


ስንቅ ያለቀበት መንገደኛ፡ ይህ ሰው በአገሩ


ከፍተኛ ካፒታል ወይም ንብረት ያለው ቢሆንም


ባለበት ሁኔታ፣ ስንቅ ካለቀበት፣ ከተቋረጠበትና


ገንዘብ ካስፈለገው ዘካ ይሰጠዋል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) ዘካ የሚገባቻን ክፍሎች ሲያብራራ


እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት)


ለድሆች፣ ለሚስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ


ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በኢስላም) ለሚለማመዱት፣


ጫንቃዎችንም ነፃ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ


መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኞችም ብቻ ነው፡፡›› (አል


ተውባ 60)





የእንሰሳት ሃብት ዘካ


የእንሰሳት ሃብት፣ሰዎች የሚገለገሉባቸው የቤት እንሰሳት ማለት ነው፡፡ እነሱም ግመል፣ ላምና ፍየል ወይንም በግ


ናቸው፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እነኚህን እንሰሳት በመፍጠር ለሰዎች ትልቅ ውለታ ውሎላቸዋል፡፡ ሰዎች ስጋዎቻቸውን ይመገባሉ፤


ከቆዳዎቻቸው ልብስን ይለብሳሉ፤ በመንገድ ሲጓዙና ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ እነሱንና ጓዛቸውን ይሸከሙላቸዋል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ግመልን፣ ከብትን፣ ፍየልንም፣ በርሷ (ብርድን መከላከያ) ሙቀት፣ ጥቅሞችም ያሉባት ስትኾን


ለናንተ ፈጠረላችሁ ከርሷም ትበላላችሁ፡፡ ለናንተም በርሷ ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜ፣ በምታሰማሩዋትም ጊዜ


ውበት አላችሁ፡፡ ጓዞቻችሁንም በነፍሶች ችግር እንጂ ወደማትደርሱባት አገር ትሸከማለች ጌታችሁ በእርግጥ ርኀሩኅ


አዛኝ ነውና፡፡ (አል ነሕል 5-7)


የእንሰሳት ዘካ ጥቅላዊ መስፈርቶች


በእነኚህ እንሰሳት ላይ ዘካ ግዴታ የሚሆነው


የሚከተሉት መስፈርቶች ሲሟሉ ነው፡


ብዛታቸው የኢስላማዊውን ዘካ የማወጫ


መጠን(ሂሣብ) መድረስ፡ ምክንያቱም


ዘካ በባለሃብቶች ላይ እንጂ በሌላው


ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ለግል ጉዳያቸው


የሚጠቁሙባቸው ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ


እንሰሳት ያሉት ሰው የዘካ ግዴታ የለበትም፡


፡ ከግመል ዘካ የሚወጣው ቁጥራቸው


አምስት ሲደርስ ነው፡፡ ለፍየል አርባ፣ ለላም


ደግሞ ሰላሳ ነው፡፡ ቁጥራቸው ከዚህ ቁጥር


በታች ከሆነ የዘካ ግዴታ የለበትም፡፡


በይዞታነት ባለሀብቱ ዘንድ አንድ ሙሉዕ


የጨረቃ ዓመት ሊዞርባቸው ወይም


ሊያስቆጥሩ ይገባል፡፡


በግጦሽ ላይ ተሰማርተው የሚበሉ መሆን


አለባቸው፡ እንሰሰዎቹ በግጦሽ ላይ የሚኖሩ፣


ድርቆሽና ግጦሽ በማቅረብ ባለንብረቱ ወጪ


የማያደርግባቸው መሆን አለበት፡፡


እንሰሳቱ በስራ የተጠመዱ መሆን


የለበትም፡፡ ባለቤቱ ማሳውን የሚያርስበት


ወይም ዕቃ የሚያጓጉዝበት ወይም እራሱ


የሚጓጓዝበት መሆን የለበትም፡፡ ይህ ከሆነ


ዘካ የማውጣት ግዳጅ የለበትም፡፡





ምጽዋትህ (ዘካህ)


143


የጋማ ከብቶች የዘካ አወጣጥ


ግመል


ሁሉም የግመል ዓይነቶች ባለ አንድ ሻኛ ወይም ባለ ሁለት ሻኛ ቢሆኑም ብዛታቸው አምስት ከደረሰ ዘካ ማውጣት


ግዴታ ነው፡፡


ብዛት


ግዴታ የሚሆንበት መጠን


ብዛት


ግዴታ የሚሆንበት መጠን


ከ እስከ ከ እስከ


5 9 አንድ ሴት ፍየል 46 60 ሒቃህ (የሦስት ዓመት እድሜዋን ጨርሳ


አራተኛ እድሜዋን የጀመረች ሴት ግመል)


10 14 ሁለት ሴት ፍየሎች 61 75


ጀዝዐህ (የአራት ዓመት እድሜዋን ጨርሳ


አምስተኛ እድሜዋን የጀመረች ሴት


ግመል)


15 19 ሦስት ሴት ፍየሎች 76 90


ሁለት ቢንት ለቡን (የሁለት ዓመት


እድሜያቸውን ጨርሰው የሦስተኛ ዓመት


እድሜያቸውን የጀመሩ ሴት ግመሎች)


20 24 አራት ሴት ፍየሎች 91 120


ሁለት ሒቃህ (የሦስተኛ ዓመት


እድሜያቸውን ጨርሰው የአራተኛ ዓመት


እድሜያቸውን የጀመሩ ሴት ግመሎች)


25 35


ቢንት መኻድ (የአንድ ዓመት እድሜዋን


ጨርሳ ሁለተኛ ዓመት እድሜዋን


የጀመረች ሴት ግመል)


ብዛታቸው


ከ120 በላይ


ሲሆን በየ40ዎቹ


ተጨማሪ ግመሎች


አንድ ቢንት ለቡን (የሁለት ዓመት


እድሜዋን ጨርሳ የሦስተኛ ዓመት


እድሜዋን የጀመረች ሴት ግመል) ከላይ


ከተቀመጠው ቁጥር ላይ ይጨመራል፡፡


36 45


ቢንት ለቡን (የሁለት ዓመት እድሜዋን


ጨርሳ ሦስተኛ እድሜዋን የጀመረች


ሴት ግመል)


በየ50ዎቹ


ተጨማሪ ግመሎች


አንድ ሒቃህ የሦስተኛ ዓመት


እድሜዋን ጨርሳ የአራተኛ ዓመት


እድሜዋን የጀመረች ሴት ግመል ከበላይ


ከተቀመጠው ቁጥር ላይ ይጨመራል


1


ምጽዋትህ (ዘካህ)


144


ከብት


ከከብት ላይ ዘካ ግዴታ የሚሆነው የከብቶቹ ቁጥር ከ30 በላይ ሲሆን ነው


ብዛት


ግዴታ የሚሆንበት መጠን


ከ እስከ


30 39 አንድ ጥጃ (አንድ ዓመት የሞላው ጥጃ)


40 49 አንድ ሙሲናህ (የሁለት ዓመት እድሜዋን


የጨረሰች ላም)


60 69 ሁለት ጥጆች (ሁለት ዓመት የሞላቸው)


70 79 አንድ መሲናህ (ሁለት ዓመት የሞላት ላም) እና


ተቢዕ (አንድ ዓመት የሞላው ጥጃ)


80እና ከዚያ በላይ


በየ30ዎቹ


አንድ ተቢዕ (አንድ ዓመት የሞላው ጥጃ) ከላይ


ከተጠቀሰው ቁጥር ላይ ይጨመራል፡፡


በየ40ዎቹ


ሙሲናህ (ሁለት ዓመት የሞላት ላም) ከላይ


ከተጠቀሰው ቁጥር ላይ ይጨመራል፡፡


በግና ፍየል


የበጎችና የፍየሎች ቁጥር ከ40 በላይ ሲሆን ዘካ ማውጣት ግዴታ ይሆናል


 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎ ...

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች።

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የ ...

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ...

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት