መጣጥፎች

ጾምህ


4


አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በአመት አንድ ወርን እንዲጾሙ ግዳጅ


አድርጎ ደንግጓል፡፡ እሱም የተባረከውን የረመዳንን ወር ነው፡


፡ አራተኛ የኢስላም ማዕዘንና ታላቅ መሰረት አድርጎታል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ)፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት


በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ ተፃፈ (ተደነገገ)


ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡›› ይላል፡፡ (አል በቀራ 183)


የምዕራፉ ማውጫ


የጾም ትርጉም


የረመዳን ወር ትሩፋት


የጾም ሚስጥር


የጾም ትሩፋት


ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች


እንዳይጾሙ አላህ ፍቃድ የሰጣቸው ሰዎች


ህመምተኛ


ደካማ


መንገደኛ


በወር አበባና በወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች


እርጉዝና አጥቢ ሴት


የውዴታ ጾም


የተባረከው የጾም ፍቺ በዓል (ዒዱል ፊጥር)


በጾም ፍቺ በዓል ቀን የሚፈቀዱ ነገሮች


ጾምህ


128


የረመዳን ጾም


የጾም ትርጉም


ጾም በኢስላም ያለው ትርጉም፡ ጎሕ ከቀደደበት ሰዓት ጀምሮ፣ ፀሐይ እስክትጠልቅ (የመግሪብ ሠላት አዛን የሚባልበት


ወቅት) ድረስ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነትና ከሌሎችም ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች እራስን በመቆጠብና


በማገድ አላህን መገዛት ነው፡፡


> የረመዳን ወር በላጭነት


የረመዳን ወር፣ በኢስላማዊው ቀመር ዘጠነኛው ወር


ነው፡፡ ረመዳን ከዓመቱ ወራት ሁሉ በላጩ ነው፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) ከተቀሩት ወራት በበርካታ ነገሮች አልቆታል፡፡


ከነዚህ ብልጫዎች መካከል የሚከለተሉት ይገኙበታል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) የተከበረውንና እጅግ የላቀውን


መጽሐፍ -ቁርኣንን- በውስጡ በማውረድ


የመረጠው ወር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡፡-‹‹(እንድትጾሙ የተፃፈባችሁ) ያ በርሱ


ውስጥ ለሰዎች መሪ፣ ከቅን መንገድና (ውነትን


ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲሆን


ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡


ከናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡›› (አል


በቀራ 185)


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ረመዳን


ሲገባ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የጀሀነም


በሮች ይዘጋሉ፤ ሰይጣናት ይታሰራሉ፡፡››


(አል ቡኻሪ 3103/ ሙስሊም 1079) አላህ


(ሱ.ወ) መልካምን በመሥራትና ከመጥፎ


በመራቅ ባሮቹ ወደርሱ የሚመለሱበትን ሁኔታ


አመቻችቷል፡፡


ቀኑን የጾመና ሌሊቱን በመስገድ ቆሞ ያሳለፈ ሰው


ያለፉት ወንጀሎቹ ይማሩለታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በእምነትና አላህ ዘንድ ያለውን


ምንዳ በማሰብ የረመዳንን ወር የጾመ፣ ቀደም ሲል


የሠራው ወንጀል ይማርለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ


1910 /ሙስሊም 760) ‹‹በእምነትና አላህ ዘንድ


ያለውን ምንዳ በማሰብ በረመዳን ወር (ተራዊሕና


ተሃጁድን በመስገድ) የቆመ ሰው ቀደም ሲል


የሰራው ወንጀል ይማርለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ


1905/ ሙስሊም 759)





> የረመዳን ወር በኢስላማዊው ቀመር ዘጠነኛው ወር ነው፡፡


በረመዳን ውስጥ የዓመቱ ትልቅ ሌሊት


ይገኛል፡፡


ይህች ሌሊት አላህ (ሱ.ወ) በመጽሐፉ፣ በዚች በርሷ


ውስጥ የሚሠራ መልካም ሥራ፣ ለረዥም ዓመታት


ከሚሠራ መልካም ሥራ እንደሚሻልና እንደሚበልጥ


የተናገረላት ነች፡፡ አላህ (ሱ.ወ):- ‹‹መወሰኛይቱ


ሌሊት ከሺህ ወር በላጭ ናት፡፡›› ብሏል (አል ቀድር


3) እናም ይህችን ሌሊት በእምነትና አላህ ዘንድ


ያለውን ምንዳ በማሰብ በመስገድ ቆሞ ያሳለፈ ሰው


ቀደም ሲል የሰራው ወንጀል ይማርለታል፡፡ እርሷ


በረመዳን ወር በመጨረሻዎቹ አስርት ሌሊቶች


ውስጥ የምትገኝ ነች፡፡ ይህችን ሌሊት፣ ማንም ሰው


በእርግጠኝነት በዚህ ዕለት ትሆናለች ብሎ መወሰንና


መናገር አይችልም፡፡


4


ጾምህ


129


> የጾም ሚስጥር


አላህ ሱ.ወ፣ በበርካታ ዓለማዊና መንፈሳዊ ምክንያቶች


ጾምን ግዴታ አድርጓል፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት


ይገኙበታል


1 የአላህን ፍራቻ ማጽናት


ጾም፣አንድ ባሪያ የሚወዳቸውን ነገሮች ወይም


ፍላጎቶቹን በመተው፣ ስሜቱን በመጫን፣ አላህን


የሚገዛበት አምልኮ በመሆኑ፣ በሁሉም ስፍራና ወቅት፣


በድብቅም ሆነ በይፋ ነፍሱን በአላህ ፍራቻ እንዲያንጽና


የአላህን ምርመራ እንዲያስተነትን ያደርገዋል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ)፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ


በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተጻፈ በናንተም ላይ


ተጻፈ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡›› ብሏል (አል በቀራ 183)


> ጾመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡- ጾሙን ሲፈታና


ፈጣሪውን ሲገናኝ ይደሰታል፡፡


2 ከወንጀልና ከሃጢኣት በመራቅ ላይ ስልጠና


ወይም ልምምድ መስጠት


አንድ ጾመኛ ሐላል ነገሮችን በመከልከል የአላህን


ትዕዛዝ ማክበር ከቻለ፣ የወንጀልና የሀጢኣት ስሜቱን


በመለጎሙና አላህ ከገደበው ወሰን በመጠበቁ፣ በስህተት


ላይ ባለመዘወተር የበለጠ ቻይ ይሆናል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የሐሰት ንግግርንና በሱም መሥራትን


ያልተወ ሰው፣ አላህ (ሱ.ወ) ምግብና መጠጡን ከመተዉ


ጉዳይ የለውም፡፡›› (አል ቡኻሪ 1804) ውሸት ማውራትና


በውሸት መሥራት ያልተወ ሰው፣ ለጾም የተደነገገለትን


ዓላማ በስራ ላይ አላዋለም ማለት ነው፡፡


3 ችግረኞችን ማስታወስና መደገፍ


ጾም፣ የተራቡና የተቸገሩ ሰዎችን ሕይወት


የሚካፈሉበትና ዓመቱን ሙሉ በችግርና በሰቆቃ


የሚያሳልፉትን ድሆች ሁኔታ የሚያስታውሱበት


የአምልኮ ዘርፍ ነው፡፡ ትክክለኛ የአላህ ባሪያ፣ ድሃ


ወንድሞቹ ምን ያህል በረሃብና በጥማት እንደሚቸገሩ


ያስታውሳል፤ በመሆኑም ለነርሱ የእርዳታ እጁን


በመዘርጋት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡


> የጾም ትሩፋት


ጾም በኢስላማዊው ሕግ የተደነገጉ በርካታ ትሩፋቶች


አሉት፡፡ ከነዚህም መካከል፡-


በአላህ አምኖ፣ ትዕዛዙንም አክብሮ፣ በረመዳን


ትሩፋት ዙሪያ የተላለፉ ጉዳዮችን እውነት ብሎ


ተቀብሎ እንዲሁም አላህ ዘንድ የሚያገኘውን


ምንዳ በመከጀል ረመዳንን የጾመ፣ ቀደም ሲል


የሰራው ወንጀሉ ይማርለታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ረመዳንን፣ በአላህ አምኖ


የሚያስገኝለትን ምንዳ አስቦና ከጅሎ የጾመ ሰው


ቀደም ሲል የሰራው ወንጀል ይማርለታል፡፡››


(አል ቡኻሪ 1910 / ሙስሊም 760)


ጾመኛ፣ ከአላህ ጋር ሲገናኝ በመጾሙ


ምክንያት በሚያገኘው ላቅ ያለ ምንዳና


ጸጋ ይደሰታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ


ብለዋል፡- ‹‹ጾመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡


በሚያፈጥርበት ጊዜ የሚደሰተውና ከጌታው


ጋር ሲገናኝ የሚደሰተው ደስታ ነው፡፡››


(አል ቡኻሪ 1805 /ሙስሊም 1151)


በጀነት ውስጥ ከጾመኞች በስተቀር ማንም


የማይገባበት የሆነ ረያን የሚባል በር አለ፡፡ ነብዩ


(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በጀነት ውስጥ


ረያን የሚባል በር አለ፡፡ የትንሳኤ ቀን ጾመኞች





ጾምህ


130


ይገቡበታል፡፡ ከነርሱ ሌላ ማንም በርሱ በኩል አይገባም፡፡ የት አሉ ጾመኞች? ይባላል፡፡ ወዲያውም እነሱ ወደርሱ


ይነሳሉ፡፡ ከነርሱ ሌላ ማንም በርሱ በኩል አይገባም፡፡ እነሱ ገብተው ሲያበቁ ይዘጋል፡፡ ማንም በሱ በኩል


አይገባም፡፡›› (አል ቡኻሪ 1797/ ሙስሊም 1152)


አላህ (ሱ.ወ) የጾምን ምንዳ ወደራሱ አስጠግቶታል፡፡ እናም ክፍያውና ምንዳው፣ ከቸሩ፣ ከለጋሱና ከኃያሉ


ጌታ ዘንድ የሆነለት ሰው ሊደሰት ይገባል፡፡ አላህ ባዘጋጀለትም ሽልማት ይበሰር፡፡ አላህ (ሰ.ወ) በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


አንደበት ሲነግረን፡- ‹‹ፆም ሲቀር ሁሉም የአደም ልጆች ስራ ለራሳቸው ነው፤ እርሱ ግን የኔ ነው ምንዳውን


የምከፍለው እኔው ነኝ፡፡›› ይላል፡፡ (አል ቡኻሪ 1805 /ሙስሊም 1151)


4


> ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች


ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች፣ አንድ ጾመኛ ሊከለከላቸውና


ሊቆጠባቸው የሚገቡ ነገሮች ናቸው፡፡ እነሱም


የሚከተሉት ናቸው፡፡


1 መብላትና መጠጣት፡- አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡- ‹‹ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር


(ከሌሊት ጨለማ) ለናንተ እስከሚገለጽላችሁ


ድረስ ብሉ ጠጡም ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ


ድረስ ሙሉ፡፡›› (አል በቀራ 187)


ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙ አይበላሽም፤


ወንጀልም የለበትም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹ጾመኛ መኾኑን


ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይቀጥል፡፡


ያበላውና ያጠጣው አላህ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ


1831/ሙስሊም 1155)


2 ምግብንና መጠጥን የሚተካ ነገር፡፡


• በሰውነት ውስጥ የተጓደለን የጨውና የምግብ መጠን


ለመጠገን የሚወሰዱ ምግብ ነክ የሆኑ መርፌዎችና


መድሃኒቶች ጾምን ያፈርሳሉ፡፡ ምክንያቱም የምግብና


የመጠጥን ቦታ ስለሚተኩ፣ በምግብና መጠጥ ላይ


ያለፈው ሕግ ይመለከታቸዋል፡፡


• ለህመምተኛ የሚሰጥ ደም፡፡ ምክንያቱም ደም


የምግብና የመጠጥ የመጨረሻው መዳረሻ በመሆኑ


ነው፡፡


• በማንኛውም መልክ ማጨስ፡፡ ጭስን ወደ ሰውነት


እያማጉ ማስገባት፣ ሰውነትን በመመረዝ እንዲጠናከር


ያደርገዋል፡፡


3 የፍቶት ጠብታ ቢፈስም ባይፈስም፣ የወንዱ


ብልት በሴቲቷ ብልት ውስጥ እንዲሰምጥ


በማድረግ የተፈፀመ ግብረ ስጋ ግንኙነት


4 በፍላጎትና በምርጫ በመተሻሸት ወይም በእጅ


በማባበልና በመሳሰሉት መንገዶች የፍቶት ጠብታን


(የዘር ፍሬ ፈሳሽን) ማፍሰስ


በእንቅልፍ ልብ የሚከሰት የዘር ፍሬ መፍሰስ ጾምን


አያበላሽም፡፡


አንድ ሰው ጾምን የሚያበላሹ ነገሮችን እንዳይፈጽም


መጠንቀቅና ስሜቱን መቆጣጠር የሚችል ከሆነ ሚስቱን


መሳም ይችላል፡፡


5 አውቆ ማስታወክ፡፡ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ


ትውከት በራሱ ከወጣ ጾምን አያፈርስም፡፡ ነብዩ


(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ትውከት ያሸነፈው


ጾመኛ፣ ጾሙን መክፈል አይጠበቅበትም፡፡


በፈቃዱ ያስታወከ ሰው ጾሙን ይክፈል፡፡›› (አል


ቲርሚዚ 720 /አቡ ዳውድ 2380)


6 አበባና የወሊድ ደም መፍሰስ፡፡


የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም በቀኑ የመጨረሻ


ክፍል ላይም ቢሆን ከፈሰሰ ሴቷ ጾሟ ይበላሻል፡፡


በሌላም በኩል፣ በወር አበባ ደም ላይ ቆይታ ጎሕ


ከፈነጠቀ በኋላ ብትጸዳና የዚያን ቀን ብትጾም፣


ጾሟ ትክክል አይሆንም፡፡ ያንን ቀን መጾም


የለባትም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-


‹‹የወር አበባ ላይ በምትሆንበት ጊዜ አትሰግድም


አትጾምም አይደል እንዴ?›› (አል ቡኻሪ 1850)


አንዲት ሴት ከተለመደው የወር አበባና የወሊድ ደም


ውጭ በበሽታ ምክንያት ደም የሚፈሳት ከሆነ ከመጾም


አትከለከልም፡፡


ጾምህ


131


> አላህ እንዳይጾሙ ፍቃድ የሰጣቸው ሰዎች


1 በመጾሙ የሚጎዳ ታማሚ፡- ለርሱ ማፍጠር ይፈቀድለታል፡፡ ከረመዳን በኋላ ሲሻለው ያፈጠረውን ይከፍላል፡፡


በሽምግልና ወይም ይድናል ተብሎ በማይከጀል በሽታ ምክንያት መጾም የማይችል ደካማ ማፍጠር


ይፈቀድለታል፡፡ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ያበላል፡፡ ይኸውም፣ በሀገሩ ከሚበላ የምግብ ዓይነት


አንድ ኪሎ ተኩል በመስጠት ይሆናል፡፡ 2


ተጓዥ መንገደኛ በጉዞው ላይ እያለ ከአራት ቀን ለማይበልጥ ጊዜ ሲያርፍ ማፍጠር ይችላል፡፡ ያንን ጾም


የፈታበትን ቀን ከረመዳን በኋላ ሀገሩ ሲመለስ ይከፍላል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በሺተኛ ወይም


በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በናንተ ገሩን (ይሻል)


በናንተም ችግሩን አይሻም፡፡›› (አል በቀራ 185)


3


የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች፡፡


በነኚህ ሁለት ሁኔታዎች ላይ ያሉ ሴቶች መጾም በነሱ ላይ እርም ነው፡፡ መጾማቸው ትክክለኛ አይደለም፡


፡ ከረመዳን በኋላ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ (ገጽ፣ 96 ተመልከት) 4


እርጉዝና አጥቢ፡፡


በራሳቸው፣ወይም በልጃቸው ላይ ጉዳትን ከሰጉ ወይም ከፈሩ፣ ማፍጠርና ቀኖቹን መክፈል ይችላሉ፡፡ 5


አላህ (ሱ.ወ) ከሰዎች መካከል ለተወሰኑ ሰዎች በረመዳን ወር አለመጾም እንዲችሉ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ ይህንንም


ያደረገው ለነርሱ ከማዘን፣ ከማግራትና ከማቅለል አንፃር ነው፡፡ እኚህ ሰዎች የሚከተሉት ናቸው:-


ጾምህ


132


በረመዳን ጾሙን ያበላሸ ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?


ማንኛውም ያለ በቂ ምክንያት ጾሙን ያበላሸ ሰው፣ ከባድ ወንጀል ፈጽሟል የፈጣሪውን ትዕዛዝ ጥሷል፡፡


ስለዚህም፣ በተውበት ወደ አላህ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ጾሙን ያበላሸው በግብረ ስጋ ግንኙነት ካልሆነ፣ ከዚህ


ከተውበቱ በተጨማሪ ያንን ጾም የፈታበትን ቀን መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ጾሙን የፈታው በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሆነ


ግን፣ ያንን ቀን መክፈል፣ እንዲሁም ለሠራው ወንጀል ማበሻ፣ ባሪያን ነፃ ማውጣት አለበት፡፡ ይህም፣ ሙስሊም ባሪያን


በመግዛትና ከባርነት በማላቀቅ ይተገበራል፡፡ እናስተውል! ኢስላም፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ልጅ ከባርነት


ቀንበር ነፃ መውጣት ትኩረት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ አሁን እንዳለንበት ዘመን ዓይነት ባሪያን ነፃ ማውጣት የማይቻል


ከሆነ፣ ሁለት ወሮችን በተከታታይ ይጾማል፡፡ ይህንንም ካልቻለ ስልሳ ሚስኪኖችን ያበላል፡፡


> የውዴታ ጾም


አላህ (ሱ.ወ) እንዲጾም ግዴታ ያደረገው በዓመት


አንድ ወርን ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቻለና ፍላጎት


ያለው፣ ከአላህ ተጨማሪ ምንዳን ለማግኘት የሚከጅል


ሰው፣ ሌሎች ቀናትንም እንዲጾም ያበረታታል፡፡ ከነኚህ


ቀናት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-


1 የዐሹራን ቀንና ከርሱ በፊት ወይም በኋላ ያለው


ቀን፡፡


የዐሹራ ዕለት የሚባለው በኢሰላማዊው


ቀመር መሰረት፣የወርሃ ሙሐረም አስረኛው


ቀን ነው፡፡ ይህ ዕለት፣ አላህ(ሰ.ወ) ነብዩላህ


ሙሳን(ዐ.ሰ) ከፈርዖን የገላገላቸውና፣


ፈርዖንን በባሕር ውስጥ ያሰጠመበት


ዕለት ነው፡፡ ሙስሊሞች አላህ (ሱ.ወ)


ነብዩላህ ሙሳን(ዐ.ሰ) ነፃ ስላወጣ፣ እርሱን


ለማመስገንና የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ


ለመከተል ሲሉ ይጾሙታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ቀን ከፊቱ ወይም


አንድ ቀን ከኋላው ጹሙ›› (አህመድ 2154)


ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ስለዚህ ዕለት ጾም ተጠይቀው፣


‹‹ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል፡፡››


ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 1162)


2 የዐረፋ ቀን፡


ዐረፋ፣ የወርሃ ዙልሒጃ ዘጠነኛው ቀን ነው፡


፡ ዙልሒጃ፣ በኢስላማዊ ቀመር መሰረት አስራ


ሁለተኛው ወር ነው፡፡ ይህ ቀን ሐጃጆች ዐረፋ


በሚባል ቦታ ላይ በመሰብሰብ አላህን ሲለምኑና


ሲማጸኑ የሚውሉበት ዕለት ነው፡፡ ከዓመቱ


ቀናት ሁሉ የላቀና የበለጠ ቀን ነው፡፡ ሐጅ ላይ


ላልተሳተፈ ሰው ይህን ቀን መጾም ይወደድለታል፡


፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ዕለት ጾም ተጠይቀው


ሲመልሱ፡- ‹‹ያለፈውንና የመጪውን ዓመት


ወንጀል ያስምራል፡፡›› ብለዋል (ሙስሊም 1162)


3 ስድስቱ የሸዋል ቀኖች፡


ሸዋል አስረኛው ወር ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ


ብለዋል፡- ‹‹ረመዳንን የጾመ፣ ከዚያም ከሸዋል


ስድስት ቀናትን አስከትሎ የጾመ ሰው፣ አንድ


ዓመት ሙሉውን እንደጾመ ይቆጠርለታል፡፡››


(ሙስሊም 1164)


ጾምህ


133


> የተባረከው የጾም ፍቺ በዓል


በዓላት፣ ከሃይማኖት መገለጫዎች ውስጥ ይመደባሉ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና በመጡበት ወቅት አንሣሮችን


ከዓመቱ ቀናት በሁለት ቀኖች ውስጥ ሲፈነጥዙ፣ ሲጫወቱና ሲደሰቱ አግኝተዋቸው ነበር፡፡ እናም፡ ‹‹እነዚህ ሁለት


ቀናት የምን ቀኖቻችሁ ናቸው?›› በማለት ጠየቋቸው፡፡ እነሱም፡ ‹‹ከኢስላም መምጣት በፊት- በጨለማው ዘመን


እንደሰትባቸው የነበሩ ቀኖች ናቸው፡፡›› በማለት መለሱ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹አላህ እነዚህን ቀናት ከነርሱ በተሻሉ


ሁለት ቀናት ተክቶላችኋል፡፡ የእርድ ዕለትና የፍስክ ዕለት›› አሏቸው፡፡ (አቡ ዳውድ 1134) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ በዓላት


የሃማኖቶች መገለጫ እንደሆኑ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹እያንዳንዱ ሕዝብ በዓል አለው፡፡ ይህ ደግሞ በዓላችን


ነው፡፡›› (አል ቡኻሪ 909 /ሙስሊም 892)


በዓል በኢስላም


በኢስላም ውስጥ፣ በዓል አንድ የአምልኮ ዘርፍን


ስላጠናቀቁ ደስታን የሚገልጹበትና አላህ(ሱ.ወ)


ለዚህ አምልኮ ስለመራቸውና ስለገጠማቸው እሱን


የሚያመሰግኑበት አጋጣሚ ነው፡፡ በዒድ ቀን፣ የሚያማምሩ


ልብሶችን በመልበስ፣ ለከጃዮች መልካም በመዋል በሰዎች


ልቦና ውስጥ ደስታን መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ኢስላም


ያስተምራል፡፡ በማንኛውም የተፈቀዱ መንገዶች፣


የሁሉም ልቦና የደስታ ስሜት እንዲሰማውና የአላህን ጸጋ


የሚያስታውስ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡


የሙስሊሞች በዓል


በዓመት ውስጥ ሙስሊሞች የሚያከብሯቸው ሁለት


በዓላት አሉ፡፡ ከሁለቱ ቀናት ውጪ ሰዎች እንደ


በዓል አድርገው የሚያከብሯቸውን ቀናቶች ማክበር


አይፈቀድም፡፡ እነኚህ በዓላት፡ የጾም ፍቺ በዓል (


የወርሃ ሸዋል የመጀመሪያ ቀን) እና የእርድ በዓል (የወርሃ


ዙልሒጃ አስረኛ ቀን) ናቸው፡፡


ጾምህ


134


የጾም ፍቺ በዓል


የጾም ፍቺ በዓል፣ የረመዳን የመጨረሻው ሌሊት ካለፈ በኋላ የሚከተለው የወርሃ ሸዋል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡


የጾም ፍቺ በዓል በመባል የሚጠራውም ለዚህ ነው፡፡ ይህ ቀን፣ ሰዎች ጾማቸውን በማጠናቀቃቸው፣ በጾማቸው አላህን


ይገዙበት እንደነበረው፣ በመደሰት አላህን የሚያመሰግኑበት ዕለት ነው፡፡ ሙስሊሞች ይህን በዓል የሚያከብሩት፣


አላህ ጸጋውን ስላሟላላቸውና የረመዳንን ወር በሙሉ ለመጾም ስላደላቸው፣ አላህን እያመሰገኑ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን


ደነገግንላችሁ)›› (አል በቀራ 185)


በኢስላማዊው ሕግ የተደነገጉና በዒዱ ዕለት የሚከናወኑ ነገሮች እንዴት ያሉት ናቸው?


1 የበዓል ሠላት (የዒድ ሠላት)፡ ኢስላም፣


ሙስሊሞች ከሴቶችና ሕፃናት ጋር


በመሆን በአንድነት ወጥተው ይህን


ሠላት እንዲሰግዱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ


አስተምሯል፡፡ የመስገጃ ጊዜው፣ ፀሐይ


ወጥታ የጦር ዘንግ ያክል ከፍ ካለችበት


ቅጽበት ጀምሮ ከሰማይ መሐከል


እስከምታዘነብልበት ጊዜ ይረዝማል፡፡


አፈፃፀሙ፡ የዒድ ሠላት ሁለት ረከዓ ነው፡፡


ኢማሙ ሲያሰግድ ቁርኣን የሚያነበው ድምፁን ከፍ


አድርጎ ሲሆን ከሠላቱ በኋላም ሁለት ኹጥባዎችን


ያደርጋል፡፡ በዒድ ሠላት ‹‹አላሁ አክበር›› የሚለውን


ቃል በእያንዳንዱ ረከዓ መጀመሪያ ላይ ደጋግሞ


ማለት ያስፈልጋል፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ላይ


ፋቲሓን ማንበብ ሳይጀምር በፊት፣ ከመጀመሪያው


የሠላት መግቢያ ተክቢራ ሌላ ስድስት ጊዜ ‹‹አላሁ


አክበር›› ይላል፡፡ በሁለተኛው ረከዓ ላይ ደግሞ


ከመጨረሻው ሱጁድ ሲነሳና ሲቆም ከሚለው


ተክቢራ ሌላ አምስት ጊዜ ‹‹አላሁ አክበር›› ይላል፡፡


2 የጾም ፍች ምጽዋት(ዘካተል ፊጥር)፡ አላህ


(ሱ.ወ) በዒድ ዕለት፣ ቀንና ሌሊቱን


ከሚበላው የሚተርፍ ነገር ያለው ሰው


አገሬው ከሚመገበው ሩዝ ወይም ስንዴ


ወይም ተምር አንድ ቁና ለሙስሊም


ድሆችና ችግረኞች እንዲሰጥ ግዴታ


አድርጓል፡፡ ይህም ድሆችና ችግረኞች


በዒድ ዕለት ተቸግረው እንዳይውሉ


ያደርጋቸዋል፡፡


የዘካተል ፊጥር መስጫ ጊዜ፡ የመጨረሻው


የረመዳን ቀን ፀሐይ ከጠለቀችበት ሰዓት ጀምሮ፣


የዒድ ሠላት እስከሚሰገድበት ወቅት ድረስ


ነው፡፡ ከዒዱ አንድ ወይም ሁለት ሌሊት ቀደም


ብሎ መስጠትም ይቻላል፡፡


ጾምህ


135


ዓይነትና መጠኑ፡ ከሀገሬው ምግብ የሆነ አንድ ቁና ሩዝ ወይም ተምርና የመሳሰሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ቁና የመስፈሪያ ልክ


ነው፡፡ ነገር ግን በዘመናዊ የሚዛን ልኬት መሆኑ የተሻለ ነው፡፡ በግምት ሦስት ኪሎግራም ይሆናል፡፡


ለራሱ፣ ለሚስቱ ልጆቹ፣ እንዲሁም ቀለብ ለሚሰፍርላቸውና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡


በእናቱ ማህፀን ውስጥ ላለ ፅንስ ማውጣትም ይወደዳል፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ካገሬው ምግብ አንድ ቁና ይወጣለታል፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ሲደነግጉ፣ ምጽዋቱ፣ ጾመኛ በማላገጥና በመጫወት ምክንያት የሚያገኘውን ወንጀል እንዲያብስለተና


ለችግረኞች ቀለብ ይሆን ዘንድ ነው፡፡ ከሠላት በፊት ላደረሳት፣ ተቀባይነት ያላት ምጽዋት ትሆናለች፡፡ ከሠላት በኋላ ላደረሳት


ደግሞ እንደማንኛውም ሠደቃ፣ ሠደቃ ነች ብለን እንወስደዋለን፡፡ (አቡ ዳውድ 1607)


3 በተፈቀዱ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም፣ በተቻለ መጠን፣ በቤተሰብ ውስጥ፣ ትልቁንም፣ ትንሹንም፣ ወንዱንም፣


ሴቱንም፣ እንዲደሰትና እንዲዝናና ማድረግ በኢስላም የተደነገገ ተወዳጅ ተግባር ነው፡፡ የሚያምር ልብስ


መልበስም እንዲሁ የተወደደ ነው፡፡ በዒድ ቀን መጾም ክልክል ነው፡፡ በዒድ ቀን የሚወደደው፣ በመብላትና


በማፍጠር አላህን መገዛት ነው፡፡


4 በኢድ ዋዜማ ሌሊቱን፣ እንዲሁም ወደ ዒድ ሠላት ሲወጣ፣ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት አላህን ማላቅ ኢስላም የደነገገው


ተግባር ነው፡፡ የዒድ አልፊጥር ሠላት ተሰግዶ ሲያበቃ የተክቢራው ጊዜ ይጠናቀቃል፡፡ ይህ የሚደረገው፣ አላህ(ሱ.ወ)


ወደ ጾም በመምራት፣ የተባረከውን የረመዳንን ወር ጾም ለማጠናቀቅ ስላበቃን፣ ለዋለልን ጸጋ እርሱን ለማመስገንና


ደስታችንን ለመግለጽ ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ቁጥሮችንም ልትሞሉ፣ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ


ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህንን ደነገግንላችሁ)›› (አል በቀራ 185)


የተክቢራ አባባል፡ ‹‹አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላኢላሃ ኢለላህ፤ አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ወሊላሂልሐምድ›› የሚል


ነው፡፡


እንዲሁም፡ ‹‹አላሁ አክበሩ ከቢራ ወልሐምዱሊላሂ ከሲራ ወሱብሓነላሂ ቡክረተን ወአሲላ›› ይባላል፡፡


ወንዶች፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፣ ሰዎችን በማይረብሽ ወይም በማያስቸግር መልኩ ተክቢራን መመላለሳቸው


የተደነገገ ተግባር ነው፡፡ ሴቶች ግን ድምፃቸውን ዝቅ ማድረግ አለባቸው፡፡


> ሙስሊሞች ከዒድ ሠላት ከወጡ በኋላ የሚያሳይ ምስል


ምጽዋትህ (ዘካህ)


 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ