መጣጥፎች




23 በመጨረሻም ወደ ቀኙ በመዞር ‹‹አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ›› ይላል፤ ወደ ግራውም በመዞር ይህንኑ


ይደግማል፡፡


አንድ ሰጋጅ በዚህ መልክ በማሰላመት ስግደቱን ያጠናቅቃል፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሠላትን አስመልክተው፡ ‹‹በተክቢር


ይታሰራል፤ በተስሊም ይፈታል›› ብለዋል፡፡ (አቡ ዳውድ 61/ አቲርሚዚ 3)


ከሐዲሱ እንደምንረዳው ወደ ሠላት የሚገባው በመጀመሪው ተክቢራ ሲሆን ከርሱ የሚወጣው ወይም እርሱ


የሚጠናቀቀው ደግሞ በተስሊም ወይም በሰላምታ መሆኑን ነው፡፡


24 አንድ ሙስሊም የግዴታን ሠላቶች ከሰገደ በኋላ የሚከተሉትን ውዳሴና የሙገሳ ቃላትን ማለት ይወደድለታል፡፡


1. ሦስት ጊዜ ‹‹አስተግፊሩላህ›› (የአላህን ምሕረት እማፀናለሁ)


2. ‹‹አላሁምመ አንተ ስሰላም ወሚንከ ስሰላም ተባረክተ ያ ዘል ጀላሊ ወል ኢክራም›› - (አምላካችን ሆይ አንተ ሰላም


ነህ፤ ሰላምም ካንተ ነው፤ አንተ የልቅናና የልግስና ባለቤት ሆይ ከሁሉ በላይ ነህ፡፡)


‹‹አላሁምመ ላ ማኒዐ ሊማ አዕጠይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ ዘል ጀድዲ ሚንከል ጀድዱ›› - (አምላካችን


ሆይ! አንተ ለሰጠኸው ከልካይ፣ ለከለከልከውም ሰጪ የለም፤ የዝምድና ባልተቤትም ዝምድናው ካንተ የሚያብቃቃው


አይደለም) ይላል፡፡


3. ሰላሳ ሦስት ጊዜ ‹‹ሱብሓነላህ››፣ ሰላሳ ሦስት ጊዜ


‹‹አልሐምዱሊላሂ››፣ሰላሳ ሦስት ጊዜ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት


ለመቶኛው ማሟያ ‹‹ላ ኢላሃ ኢለላሁ፣ ወሕደሁ ላ ሸሪ…ከ ለሁ


ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓለ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲ…ር››


- (ከአላህ ባሻገር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ በአምላክነቱ


ብቸኛ ነው፤ አጋር የለውም፤ ንግሠና ሁሉ የርሱ ነው፤ ምስጋናም


ሁሉ የርሱ ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡) ይላል፡፡





ከሩኩዕ ቀና በማለት ቀጥ


ብሎ ይቆማል፤ በዚህን


ጊዜ እጁን በተክቢራ ላይ


እንደሚያደርገው ከፍ


ያደርጋል፤ ኢማም ሆኖ ወይም


ብቻውን የሚሰግድ ሰው ከሆነ


ደግሞ ‹‹ሰሚዐላሁ ሊመን


ሐሚደሁ›› ይላል፤ ከዚህ


በኋላ ሁሉም ‹‹ረበና ወለከል


ሐምድ›› ይላሉ፡፡


በሁለቱ ሱጁዶች መካከል፣ ቀኝ


እግሩን በመቸከል፣ በግራ እግሩ


ላይ ይቀመጣል፤ እጁን በጭኖቹ


መጀመሪያ ላይ ያስቀምጣል፤


ከዚያም ‹‹ረቢግፊርሊ ወርሐምኒ››


ይላል፤ ቀጥሎ ቀደም ሲል


እንዳደረገው ለሁለተኛ ጊዜ ሱጁድ


ያደርጋል፡፡


‹‹አላሁ አክበር›› እያለ


ወደ ሱጁድ ይወርዳል፤


እጁን ግን ከፍ


አያደርግም፤ ሱጁድ


የሚያደርገው በሰባት


የሰውነት ክፍሎቹ ነው፤


እነርሱም፡ ግንባሩና


አፍንጫው፤ እጆቹ፤


ጉልበቶቹና እግሮቹ


ናቸው፤ በሱጁድ ላይ


ሆኖ ሦስት ጊዜ ‹‹ሱብሐነ


ረቢየል ዐዚም›› ይላል፡፡





110


7


ከሱጁድ ቀና በማለት ወደ


ሁለተኛ ረከዓ ይቆማል፤


ከዚያም በመጀመሪያ ረከዓ


ላይ ያከናወነውን ደግሞ


ያከናውናል፤ ይኸውም


መቆም፤ ቁርኣን ማንበብ፤


ሩኩዕ ማድረግ፣ ከሩኩዕ


ቀና ማለትና ሱጁድ


ማድረግ ነው፡፡


8


9


ከሁለተኛው ረከዓ ሁለተኛ


ሱጁድ ቀና ካለ በኋላ


ለመጀመሪያው ተሸሁድ


ይቀመጣል፤ አቀማመጡም


በሁለቱ ሱጁዶች መካከል


በሚቀመጠው መልኩ


ነው፤ እንዲህም ይላል፡


‹‹አትተሒይያቱ ሊልላሂ፣


ወሥሠለዋቱ፣ ወጥጠይባቱ፣


አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀ


ንነቢይዩ ወረሕመቱልላሂ


ወበረካቱሁ፣ አስሰላሙ ዐለይና


ወዓላ ዒባዲልላሂ ሠሣሊሒ..ነ


አሽሐዱ አን ላ ኢላሃ ኢልለ


ላህ ወአሽሃዱ አንነ ሙሐመደን


ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡››


የሚሰግደው ሠላት ባለ ሦስት ወይም ባለ አራት


ረከዓዎች ከሆነ ወደ ሦስተኛ ረከዓ ይቆማል፤


ከዚያም በመጀመሪያውና በሁለተኛው ረከዓ


ላይ የሰራቸውን ስራዎች በሙሉ ደግሞ


ይሰራል፡፡ ግን ከፋቲሓ በኋላ ሌላ ምዕራፍ


አያነብም፡፡ የተቀሩት ስራዎችና ንግግሮች


ካለፉት ረከዓዎች ጋር አንድ ዓይነቶች ናቸው፡፡


> እንዴት ነው የምሰግደው? (ሁለተኛ ረከዓ፤ ተሸሁድ፤ ሰላምታ)








በመጨረሻው ረከዓ ከሱጁድ በኋላ ቁጭ ብሎ


የመጀመሪያውን ተሸሁድ ይላል፤ በተጨማሪም


በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሠለዋት ያወርዳል፤ አባባሉም


በሚከተለው መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡


‹‹አላሁምመ ሠሊ ዐላ ሙሐመድ ወዓላ ኣሊ


ሙሐመድ ከማ ሠልለይተ ዓላ ኢብራሂመ ወዓላ


ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፤ ወባሪክ


ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ባረክተ


ዓላ ኢብራሂም ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ


ሐሚዱን መጂድ፡፡››


ከዚያም ‹‹አሰላሙዐለይኩም


ወረሕመቱላህ›› በማለት ወደ አንገቱን


ቀኝ አቅጣጫ ያዞራል፤ ከዚያም ወደ


ግራውም በመዞር ‹‹አሰላሙዐለይኩም


ወራሕመቱላህ›› ይላል፡፡ በዚህ መልክ


ሠላቱን ያጠናቅቃል፡፡





112


> የሠላት ማዕዘናት ግዴታዎች


የሠላት ማዕዘናት የሚባሉት የሠላት ዋና ዋና


ክፍሎች ሲሆኑ ታውቆም ሆነ በመርሳት ከተተዉ ሠላት


የሚበላሽባቸው ነገሮች ናቸው፡፡


እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡


• ተክቢረቱል ኢሕራም (የመግቢያ ተክቢራ ወይም


‹‹አላሁ አክበር‹‹) • መቆም ለሚችል ሰው መቆም •


ከተከታይ ወይም ማእሙም በስተቀር ፋቲሐን ማንበብ፤


• ሩኩዕ፤ • ከሩኩዕ ቀና ማለት፤ • ሱጁድ፤ • በሁለት


ሱጁዶች መሐከል መቀመጥ፤ • የመጨረሻው


ተሸሁድ፤ • ለመጨረሻው ተሸሁድ መቀመጥ፤ •


መረጋጋት ወይም ጡመእኒና እና ማሰላመት ናቸው


የሰላት ግዴታዎች ማለት በሰላት ውስጥ ግዴታ የሆኑ


አካላት ማለት ሲሆን እነዚህ ግዴታዎች ቢሆን ተብሎ


ከተተው ሰላቱ ይበላሻል። ነገር ግን አንድ ሰው ረስቶ


ወይም ዘንግቶ ከተዋቸው የጐደለውን ለመሙላት


የመርሳት ሱጁድ የመውረድ ግዴታ አለበት። ይህም


ወደፊት በሚወጣው ርዕስ የምንመለከተው ይሆናል።


የሰላት ግዴታዎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡


• ከተክቢረተል ኢሕራም ውጭ ያሉት ሁሉም


ተክቢራዎች፤ • ሩኩዕ ላይ እያሉ አንድ ጊዜ


‹‹ሱብሐነረቢየል ዐዚም›› ማለት፤ • ብቻውን


ለሚሰግድና ኢማም ሆኖ ለሚያሰግድ ‹‹ሰሚዐላሁ


ሊመን ሐሚደሁ›› ማለት፤ • ለሁሉም ሰጋጅ ‹‹ረበና


ወለከልሐምዱ›› ማለት፤ • ሱጁድ ውስጥ አንድ ጊዜ


‹‹ሱብሐነ ረቢየል አዕላ›› ማለት፤ • በሁለቱ ሱጁዶች


መሐከል ሲቀመጡ አንድ ጊዜ ‹‹ረቢግፊርሊ›› ማለት፤


እና • የመጀመሪያው ተሸሁድ፤ ናቸው፡፡ እነኚህ


ግዴታዎች በመርሳት ምክንያት ከተተዉ ግዴታነታቸው


ይቀራል፡፡ እነርሱም የእርሳና ሱጁድ ወይም ሱጁደ


ሰህው በማድረግ ይጠገናሉ፡፡


የሠላት ውስጥ ሱናዎች፡ ማንኛውም የሠላት ማዕዘን


ወይም ግዴታ ውስጥ የማይመደብ ንግግርም ሆነ ተግባር


የሠላት ውስጥ ሱና ይባላል፡፡ ሠላትን የሚያስውብና


የሚያሟላ ነው፡፡ በመሆኑም እርሱን በዘውታሪነት


መፈፀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እርሱን በመተዉ ሠላት


አይበላሽም፡፡


ሱጁደ ሰህው


ሱጁደ ሰህው፣ ሁለት ሱጁዶችን ማድረግ ሲሆን በሠላት


ውስጥ ለሚከሰቱ ጉድለቶችና ክፍተቶች ማካካሻና መጠገኛነት


የተደነገገ ነው፡፡


ሱጁደ ሰህው ማድረግ የሚፈቀደው መቼ ነው?


በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ሱጁደ ሰህው ይደረጋል፡


1 አንድ ሰጋጅ በመርሳትና በስህተት ምክንያት በሠላቱ


ውስጥ ተጨማሪ ሩኩዕን ወይም ሱጁዱን ወይም መቆም ወይም


መቀመጥን ከጨመረ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡


2 ከሠላት ማዕዘናት መካከል አንዱን ማዕዘን ካጎደላ፣ ያንን


ያጎደለውን ማዕዘን ያሟላና በሠላቱ ማብቂያ ላይ ሰጅደተ ሰህው


ይሰግዳል፡፡


3 እንደ ተሸሁደል አወል(የመጀመሪያው መቀመጥ) ዓይነት


ከሠላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ረስቶ ከተወ ሰጅደተ ሰህው


ይሰግዳል፡፡


4 የሰገዳቸውን የረከዓት ቁጥር ከተጠራጠረ፣ መጀመሪያ


እርግጠኛ የሆነውን፣አነስተኛውን ቁጥር ይይዝና ካሟላ በኋላ


ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡


የአሰጋገዱ ዓይነት፡ በመደበኛ ሠላቱ ውስጥ እንዳለው


ሱጁድና መቀመጥ ዓይነት፣ በሱጁዶቹ መሐከል የሚቀመጥ ሆኖ


ሁለት ሱጁዶችን ይሰግዳል፡፡


ሱጁድ የማድረጊያው ጊዜ፡ ሱጁደ ሰህው ሁለት ጊዜዎች


አሉት፤ ሰጋጁ ከሁለቱ በአንዱ በፈለግው ጊዜ ሊሰግደው


ይችላል፡፡


• ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ይሰግዳትና ከዚያም


ያሰላምታል፡፡


• ሠላቱን በሰላምታ ካሰናበተ በኋላ ሁለት ሱጁዶችን ስግዶ፣


ለሁለተኛ ጊዜ በሰላምታ ያሰናብታል፡፡





113


ሠላትን የሚያበላሹ ነገሮች


1 ሠላት፣ አንድ ሰጋጅ መተግበር የሚችለው ሆኖ፣


ሲታወቀውም ይሁን በስህተት ማዕዘንን ወይም


የሠላት መስፈርትን ከተወ ሠላቱ ትበላሻለች፡፡


2 ሲታወቀው ከሠላት ግዴታዎች መካከል አንዱን


ግዴታ ከተወ ትበላሻለች፡፡


3 ሲታወቀው ከተናገረ ትበላሻለች፡፡


4 ሠላት ድምጽ ባለው ሳቅ፣ በማሽካከት ትበላሻለች፡፡


5 በማያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ በሚደረጉ


ተከታታይና በርካት በሆኑ እንቅስቃሴዎች


ትበላሻለች፡፡


> የአንድ ሰጋጅ ሰላት በሚኖረው የአላህ ፍራቻና ከሰላት


ከሚያዘናጉ ነገሮች መራቁ ምንዳውና ደረጃዎቹ ላቀ እንዲሆን


ያደርገዋል።


> ሰላት ውስጥ ፊትን ወይም እጅን እያነካኩ መጫወት


ይጠላል።


በሠላት ውስጥ የተጠሉ ነገሮች፡፡


እነኚህ ነገሮች፣ የሠላትን ምንዳ የሚቀንሱ፣ ለሠላት


መተናነስን የሚያጠፉ፣ እና የሠላትን ግርማ ሞገስ


የሚሰልቡ ናቸው፡፡ እነርስሩም እንደሚከተሉት ናቸው፡፡


1 በሰላት ውስጥ መዞር የተጠላ ተግባር ነው


ምክንያቱም ነቢዩ(ሰ∙ዐ∙ወ) በሰላት ውስጥ


መዞርን (እየዞረ መመልከትን) አስመልክቶ


ጥያቄ ሲቀርብላቸው ‹‹እርሱ ሰርቆት


ነው(ሸይጧ የአላህ ባሪያ ከሰላቱ ይሰርቀዋል››


ብለዋል።(ቡኻሪ፡ 718)


2 በሠላት ውስጥ በእጆች፣ በፊት፣ ጣቶችን


በማጣመርና በማንጫጫት መጫወት ይጠላል፡፡


3 አንድ ሰው፣ ልቡ በሽንት ሐሳብና በምግብ


ክጃሎት ሐሳብ ልቡ ተጠምዶ ወደ ሠላት


መግባቱ ይጠላል፡፡ ነገሩ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዳሉት ነው፡፡ ‹‹ምግብ ቀርቦ፣ ሁለቱ ቀሻሾች


እየገፈተሩትም ሠላት የለም›› (ሙስሊም 560)





114


> የተወደዱ ሠላቶች የሚባሉት ምንድን ናቸው?


በሙስሊም ላይ፣በቀንና በሌሊት ግዴታ የሚሆኑት


ሠላቶች አምስት ናቸው፡


እንዲህ ከመሆኑ ጋር፣ ኢስላማዊው ድንጋጌ ለአንድ


ሙስሊም ከነኚህ አምስት ሠላቶች በተጨማሪ የውዴታ


ሠላትን እንዲሰግድ ደንግጎለታል፡፡


እነኚህ ሠላቶች የአላህን ውዴታ የማግኚያ ሰበቦች


ናቸው፡፡ ከግዴታ ሠላቶችም የጎደለውን የሚያሟሉ


ናቸው፡፡


የውዴታ ሠላቶች ብዙ ናቸው፤ ከነርሱ መካከል


ዋንኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡


1 የተዘወተሩ ሱናዎች( አር ረዋቲብ)፤ይሄንን ስያሜ


ያገኙት ከግዴታ ሠላቶች ጋር ተቆራኝተው


ስለሚመጡ፣ እንዲሁም አንድ ሙስሊም


የማይዘነጋቸው በመሆኑ ነው፡፡


ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማንም ሙስሊም


ግዴታ ሳይሆን በውዴታ የሆኑ አስራ ሁለት ረከዓዎችን


አይሰግድም አላህ በጀነት ቤትን ቢገነባለት እንጂ››


(ሙስሊም 728)


እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡


1 ከፈጅር ( ከጎሕ መቅደድ) ሠላት በፈት ሁለት ረከዓ፡


ከዙሁር ሠላት በፈት አራት ረከዓ፤ በየሁለት ረከዓው


ያሰናብታል፡፡ ከዚያን ደግሞ ከዙሁር በኋላ ሁለት


ረከዓዎችን ይሰግዳል፡፡


2


3 ከመግሪብ ሠላት በኋላ ሁለት ረከዓ


4 ከዒሻእ በኋላ ሁለት ረከዓ


2 የዊትር ሠላት፡ በዚህ ስያሜ የተጠራችው


የረከዓዎቿ ቁጥር ኢ-ተጋማሽ ስለሆነ ነው፡፡


ከውዴታ ሠላቶች ሁሉ በላጯ ነች፡፡ ነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹እናንተ የቁርኣን ባለቤቶች ሆይ


ዊትርን ስገዱ›› ብለዋል፡፡ (አቲርሚዚ 453/


ኢብኑ ማጃህ 1170)


የዊትር ሠላት ተመራጩ ጊዜ በሌሊቱ ማብቂያ አካባቢ


ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ከዒሻእ ሠላት በኋላ ጎሕ እስኪቀድ


ድረስ በየትኛውም የሌሊት ክፍል ሊሰግዳት ይችላል፡፡


የዊትር ሠላት የረከዓዎች ቁጥር ገደብ የለውም፡፡ ትንሹ


ቁጥር አንድ ረከዓ ነው፡፡ ተመራጩ ቁጥር ሦስት ረከዓ


ነው፡፡ በዚህ ላይ የፈለገውን መጨመር ይችላል፡፡ የኣላህ


መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስራ አንድ ረከዓ አድርገው


ይሰግዷት ነበር፡፡


የውዴታ ሠላቶች መሰረታዊ ፈለግ ባለ ሁለት ረከዓ


ሠላት መሆኗ ነው፡፡ ሁለት ረከዓዎችን ይሰግድና


ያሰላምታል፤ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡ የዊትር ሠላትም


እንደዚሁ ነች፡፡ ግን ሠላቱን ማገባደድ ሲፈልግ አንድ


ረከዓ ይሰግድና በርሷ ያጠናቅቃል፡፡ በዊትር ሠላት


ውስጥ፣ ከሩኩዕ ቀና ካለ በኋላ፣ ሱጁድ ከማድረጉ


በፊት በሐዲስ የተወረዱትን ውዳሴዎች ማነብነብ


ይወደድለታል፡፡ ከዚህም በኋላ፣ ሁለት መዳፎቹን ወደ


ላይ በመዘርጋት አላህን ይለምናል፡፡ ይህ ዱዓ፣ ዱዓኡል


ቁኑት በመባል ይታወቃል፡፡





115


በፈቃደኝነት የሚሰገዱ ሠላቶች የሚከለከሉበት ወቅት፡


ኢስላም ሠላት በውስጣቸው እንዳይሰገድ ነጥሎ ከጠቀሳቸው ወቅቶች በስተቀር የተቀሩት ወቅቶች በሙሉ አንድ


ሰው የውዴታ ሠላቶችን ያለ ገደብ ሊሰግድ ይችላል፡፡ እነኚህ የተከለከሉት ወቅቶች የከሃዲያን ማምለኪያ ሰዓታት


ስለሆኑ ያለፈን የግዴታ ሠላት አለያም እንደ ተሒየተል መስጂድ ያሉ ሰበብ ያላቸውን ሠላቶች ካልሆነ በስተቀር


የውዴታ ሠላቶችን መስገድ አይቻልም፡፡ ይህ ሠላትን በተመለከተ ያለው ፍርድ ሲሆን አላህን ማወደስና(ዚክር) እና


አላህን መለመን(ዱዓእ) ግን በየትኛውም ሰዓት ሊተገበር ይችላል፡፡


የተከለከሉት ወቅቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡


ጎሕ ከቀደደበት ጊዜ ጀምሮ ፀሐይ ወጥታ የጦር ዘንግን ያህል ትንሽ ከፍ እስከምትል ድረስ ያለው ወቅት፤


የምድር ወገብ አካባቢ ላሉ አገሮች ከ20 ደቂቃ በኋላ ይህ ወቅት ይደርሳል፡፡ 1


ፀሐይ በሰማይ መሐከል ሆና ወደ መጥለቂያዋ እስክትዘነበል ድረስ መስገድ አይቻልም፡፡ ይህ የዙሁር


ሰላት ወቅት ከመግባቱ በፊት ያለ ትንሽ ጊዜ ነው፡፡ 2


3 ከዐሥር ሠላት በኋላ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ያለው ጊዜ፡


> ከዐሥር ሠላት በኋላ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ባለው ጊዜ ሠላት መስገድ ሐራም ነው፡፡





116


> ሠላተል ጀማዓ (በሕብረት መስገድ)


አላህ(ሱ.ወ) ወንዶችን በሕብረት እንዲሰግዱ


አዟቸዋል፡፡ ሠላተል ጀማዓ ትልቅ ምንዳ እንዳለውና


ልቅናውን የሚናገሩ ሐዲሶች ወርደዋል፡፡


ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹የሕብረት ሠላት ከነጠላ ሠላት በሃያ


ሰባት ደረጃ ይበልጣል፡፡›› ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 619


/ ሙስሊም 650)


የሠላተል ጀማዓ ትንሹ ቁጥር ኢማምና አንድ ተከታይ


ነው፡፡ የጀመዓው ቁጥር በበዛው ልክ አላህ ዘንድ


ያለውም ተወዳጅነት ይጨምራል፡፡


የመከተል ትርጉም፡


መከተል ማለት፣ አንድ ተከትሎ የሚሰግድ ሰው


ሠላቱን በኢማሙ ማሰሩ ነው፡፡ ተከትሎ የሚሰግደው


ሰው ኢማሙን በሩኩዑ፣ በሱጁዱ ይከተለዋል፡፡ የቁርኣን


ንባቡን ደግሞ ያዳምጠዋል፡፡ ኢማሙን ሊቀድመው


ወይም ከርሱ ወደ ኋላ መቅረት አይገባውም፤ ይልቁንም


ኢማሙ የሚሰራውን ነገር በቶሎ እየተከተለ ይተገብራል፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ እነሆ ኢማም


የተደረገው ሊከተሉት ነው፡፡ አላሁ አክበር ሲል አላሁ


አክበር በሉ፤ አላሁ አክበር እስኪልም ቀድማችሁ አላሁ


አክበር አትበሉ፤ ሲያጎነብስ አጎንብሱ፣ እስኪያጎነብስ


ድረስም አታጎንብሱ፤ ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደሁ


ሲል፣ ረበና ወለከል ሐምዱ በሉ፤ ሲሰግድም ስገዱ፤


እስኪሰግድ ድረስም አትስገዱ…..›› (አል ቡኻሪ 701/


ሙስሊም 414 / አቡዳውድ 603)


ለኢማምነት የሚቀደመው ማን ነው?


የአላህን መጽሐፍ በቃሉ የሸመደደ ሰው ለኢማምነት


ይቀደማል፡፡ ከርሱ በመለስ ያለው ይከተለዋል


እንዲህም እያለ ይቀጥላል፡፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ


ብለዋል፡- ‹‹የአላህን መጽሐፍ ይበልጥ አሳምሮ


የሚያነብ ሰው ለኢማምነት ይቀደማል፡፡ በንባብም


የሚስተካከሉ ከሆነ ደግሞ ይበልጥ ፈለጌን(ሱናን)


የሚያውቀው ይቀደማል፡፡….›› (ሙስሊም 673)


ኢማሙና ተከታዮቹ የሙቆሙት የት ነው?


ኢማሙ ከፊታቸው መሆን አለበት፡፡ ተከታዮቹ


ደግሞ፣ የመጀመሪያውን ሠፍ ብሎ የሚቀጥለውን


እያሟሉ ተስተካክለው መቆም አለባቸው፡፡ ተከታዩ


አንድ ከሆነ ደግሞ ከኢማሙ በስተቀኝ በኩል ይቆማል፡፡





117


ኢማም ተከትሎ ሲሰግድ ያመለጠውን ሠላት


እንዴት ይሞላዋል?


ከሠላት የተወሰነ ክፍል አምልጦት ኢማሙን የተከተለ


ሰው፣ ኢማሙ ኢስኪያሰናብት ተከትሎ ይሰግድና


ከዚያም ቀሪዉን ይሞላል፡፡


ከኢማሙ ጋር ያገኘውን የሠላት ክፍል እንደ ሠላቱ


መጀመሪያ፣ቀጥሎ የሚሰራውን ደግሞ እንደ ሠላቱ


መጨረሻ አድርጎ ይቆጥረዋል፡፡


ረከዓ በምን ትገኛለች?


ሠላትን የምንቆጥረው በረከዓዎች ቁጥር ነው፡፡


ከኢማሙ ጋር ሩኩዕ ላይ የደረሰ ሰው ሙሉ ረከዓን


አግኝቷል፡፡ ሩኩዕ ያመለጠው ሰው ደግሞ ኢማሙን


ተከትሎ ወደ ሠላት ይገባል ነግር ግን ከዚያች ረከዓ


ያመለጠው ስራና ንግግር ከረከዓዎቹ አይቆጠሩም፡፡


ከፈጅር ሠላት፣ ከኢማሙ ጋር ሁለተኛዋን ረከዓ


ያገኘ ሰው፣ ኢማሙ ካሰላመተ በኋላ ቆሞ ያለፈችውን


አንድ ረከዓ ማሟላት አለበት፡፡ አጠናቆ እስኪሰግድ


ድረስ ማሰላመት የለበትም፤ ምክንያቱም የፈጅር ሠላት


ረከዓ ቁጥር ሁለት ነው፤ እርሱ ደግሞ ያገኘው አንዷን


በመሆኑ የተቀረውን ማሟላት


አለበት፡፡


የዙሁር ሠላት ላይ፣ በሦስተኛዋ


ረከዓ፣ ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ያገኘው


ሰው፣ ከኢማሙ ጋር ሁለት ረከዓዎችን


አግኝቷል፡፡ ይህ ማለት


ለተከትሎ ሰጋጁ ከዙሁር


ሠላት የመጀመሪያዎቹን ሁለት


ረከዓዎች ሰገደ ማለት ነው፡


፡ ኢማሙ ካሰናበተ በኋላ ቆሞ


የተቀረውን ማሟላት አለበት፡፡


ዙሁር ባለ አራት ረከዓ ስለሆነ፣


ቆሞ የሚሞላቸው ረከዓዎች


ሦስተኛዋንና አራተኛዋን ይሆናል ማለት


ነው፡፡


ኢማሙ ከመግሪብ ሠላት


በመጨረሻው ተሸሁድ ላይ ሆኖ ያገኘው ሰው፣


ኢማሙ ካሰላመተ በኋላ ሦስት ሙሉ ረከዓዎችን


መስገድ አለበት፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት፣ እርሱ


ኢማሙን ያገኘው በመጨረሻው ተሸሁድ ላይ ነው፤


ረከዓን ማግኘት የሚቻለው ግን ከኢማሙ ጋር ሩኩዕ


ላይ በመድረስ ስለሆነ ነው፡፡


ከኢማሙ የመጀመሪያው


የሠላት ክፍል ያመለጠው ሰው


ምሳሌ፡


> ተከትሎ የሚሰግድ ሰው (መእሙም)፣ ኢማሙን ባገኘበት


በማንኛውም የሠላት ክፍል ውስጥ ተከትሎ መግባት አለበት፡፡





1 አላ…ሁ አክበር፣ አላ…ሁ አክበር፤ አላ…ሁ


አክበር አ…ላሁ አክበር!


2 አሽሐዱ አን ላ..ኢላ..ሃ ኢለላ…ህ፤አሽሐዱ


አን ላ..ኢላ..ሃ ኢለላ...ህ!


3 አሽሐዱ አነ ሙሐመደን ረሱ…ሉላ…ህ፤


አሽሐዱ አነ ሙሐመደን ረሱ…ሉላ…ህ!


4 ሐይየ ዐለ ሠላ…ህ፤ ሐይየ ዐለ ሠላ…ህ!


5 ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ፤ ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ!


6 አላ…ሁ አክበር አላ…ሁ አክበር


7 ላ..ኢላ…ሃ ኢለላ….ህ!


> አዛን በአላህ ዘንድ ከላቁ ተግባራት


መካከል እንድ ነው።


አላህ ለሙስሊሞች አዛን ያደረገው ሰዎችን ወደ ሰላት ለመጥራትና የሰላት ወቅት መግባቱን እንዲሁም የሰላቱን


መጀመር ማሳወቂያ ይሆን ዘንድ ነው። ሙስሊሞች ለሰላት እየተጠራሩ ይሰባሰቡ ነበር። ግን አንድ ለሁሉ የሚጠራ


አልነበረም አንዳንዶች የክርስቲያኖችን መሰል ደውል አድርጉ ሲሉ ተወሰኑት ደግሞ


እንደ አይሁዳዊያን ቀንድ ይሁን አለ ዑመር ወይም ለሰላት የሚጣራ ሰው አድርጉ አሉ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)


እንደህ አሉ፦‹‹ ቢላል ሆይ! ተነስና ለሰላት ጥሪ አድርግ።››(ቡኻሪ 579 ሙስሊም377)


የአዛንና የኢቃም መገለጫ


• በአዛንና በኢቃም ስነ- ስርዓት በግለሰብ ሳይሆን


በቡድን ላይ ግዴታ ነው። አውቀው የተውት ከሆነ


ሃጢአት ኖሮባቸውም ቢሆን ሰላታቸው ትክክል


ነው።


• አዛን ለማድረግ በመልካምና በሚሰማ ድምጽ ሆኖ


ሰዎች ሰላት እንዲመጡ የሚጣራ መሆን አለበት


• ለአዛንና ለኢቃም የተለያዩና የተረጋገጡ አኳኋኖች


ከነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ተዘግበዋል።





119


ኢቃም (የሠላት መጀመሪያ ጥሪ)


1 አላ…ሁ አክበር፣ አላ…ሁ አክበር!


2 አሽሐዱ አን ላ..ኢላ..ሃ ኢለላ...ህ!


3 አሽሐዱ አነ ሙሐመደን ረሱ…ሉላ…ህ!


4 ሐይየ ዐለ ሠላ…ህ!


5 ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ!


6 ቀድ ቃመቲ ሠላ…ህ ቀድ ቃመቲ ሠላ…ህ!


7 አላ…ሁ አክበር፣ አላ…ሁ አክበር!


8 ላ..ኢላ…ሃ ኢለላ….ህ!


> አንድ ሙስሊም ወደ መስጂድ በተራመደው እርምጃ ልክ አላህ


(ሱ.ወ) ምንዳን ይከፍለዋል፡፡


ሙኣዚኑን ተከትሎ መድገም


አዛን ለሰማ ሰው፣ ሙኣዚኑን ተከትሎ


እርሱ የሚለውን በሙሉ መልሶ ማለት


ይወደዳል፡፡ ሙኣዚኑ ‹‹ሐይየ ዐለሠላ..ህ››


እና ‹‹ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ›› በሚል ጊዜ ግን፣


‹‹ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐሊዪል


ዐዚም›› ማለት አለበት፡፡


በመቀጠልም፣ ‹‹አላሁም ረበ ሃዚሂ ዳዕወቲታማ


ወሠላቲል ቃኢማ ኣቲ ሙሐመደኒል ወሲ..ለተ ወል


ፈዲ..ለተ ወብዐስሁል መቃመል መሕሙደኒ ለዚ


ወዐድተሁ›› ይላል፡፡





120


> በሠላት ውስጥ መመሰጥ


በሠላት ውስጥ መመሰጥ የሠላት እውነተኛ


መገለጫና አንኳሩ ነው፡፡ መመሰጥ ማለት፡


አንድ ሰጋጅ፣ በሠላት ውስጥ የተናነሰና እራሱን


ዝቅ ያደረገ ሆኖ፣ የሚያነበውን የቁርኣን


አንቀጽ፣ ጸሎቱንና ውዳሴን በሕሊናው


እያስተነተነ አላህ(ሱ.ወ) ፊት መቆሙ ነው፡፡


መመሰጥ፣ ከአምልኮዎች ሁሉ በላጩና የላቀ


የታዛዥነት መገለጫ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣


በመፅሐፉ ውስጥ መመሰጥ የምእመናን ባህሪ


መሆኑን ትኩረት ሰጥቶ የተናገረው ለዚህ ነው


፡፡አላህ (ሱ.ወ)፡- #ምእመናን ፍላጎታቸውን


ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ) እነዚያ እነሱ


በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች


(የሆኑት); ይላል፡፡ (አል ሙእሚኑን 1-2)


በሠላት ውስጥ መመሰጥ የቻለ ሰው፣


የኢማንና የአምልኮን ጣዕም ማጣጣም ይችላል፡


፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹የዓይን መርጊያዬ በሠላት


ውስጥ ተደርጋልኛለች›› ያሉት ለዚህ ነው፡፡ (አል ነሳኢ 3940)


የዐይን መርጊያ ማለት፣ ከዳር የደረሰ ደስታ፣ ስኬትና እርካታን ማግኘት ነው፡፡


በሠላት ውስጥ ለመመሰጥ የሚረዱ መንገዶች


በሠላት ውስጥ ለመመሰጥ የሚረዱ መንገዶች


አሉ፡፡ ከነሱም፡-


1 አስቀድሞ ለሠላት መዘጋጀት


ዝግጅት ማለት፡ ወንዶች፣ የሚያምር ልብስ በመልበስና


ወደ ሠላት በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ በመራመድ


አስቀድሞ ወደ መስጂድ በመምጣት፣ ከሠላት በፊት


የሚከናወኑ ነብያዊ ፈለጎችን በማከናወን የሚረጋገጥ


ነው፡፡


> ባሪያው ለጌታው በጣም ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሆኖ ነው፡፡


2 አዕምሮን የሚያጠምዱ፣ አዘናጊና እንቅፋት


የሆኑ ነገሮችን በቅድሚያ ማስወገድ


አንድ ሰው፣ ከፊት ለፊቱ ሐሳቡን የሚሰርቁ ምስሎች፣


ልብ የሚያንጠለጥሉ ጨዋታዎችና ሐሳቡን የሚሰርቁ


ድምፆች ባሉበት መስገድ የለበትም፡፡ እንዲሁም፣ ሽንት


ቤት መግባት እያስፈለገው፣ ተርቦ ወይም ተጠምቶ፣


ምግብና መጠጥ በቀረበበት ቅጽበት ሠላት መጀመር


የለበትም፡፡ ይህ ሁሉ ያስፈለገው ሰጋጁ አዕምሮው ነፃ


እንዲሆንና ከባድ ጉዳይን በማስተናገድ እንዲጠመድ


ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ሲሆን ከፊት ለፊቱ የሚያገኘው


ሠላቱን ይሆናል፡፡ ሠላት ደግሞ ከጌታው ጋር


የሚነጋገርበት ወሳኝ ነገር ነው፡፡





121


3 በሠላት ውስጥ መረጋጋት


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሠላትን ሲሰግዱ፣ በሩኩዓቸውም


በሱጁዳቸውም ውስጥ፣ እያንዳንዱ መገጣጠሚያቸው


ወደ ቦታው እስኪመለስ ድረስ በመረጋጋት ነበር፡፡


ሠላቱን ማሳማር ያልቻለውን ሰውዬ፣ በሠላቱ ውስጥ


በሚፈፅማቸው ተግባሮችን በሙሉ በእርጋታና በዝግታ


እንዲፈፅም አዘውታል፡፡ መቻኮልን ከልክለዋል፤ችኮላን


ከአሞራ ውሃ አጠጣጥ ጋር አመሳስለውታል፡፡


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- #በስርቆት አደገኛው ሰው ማለት


ከሠላቱ ላይ የሚሰርቅ ነው፡፡; ሲሉ፣ ሠሓቦች፡ «ከሰላቱ


ላይ የሚሰርቀው እንዴት ነው?» በማለት ጠየቁ፡፡


እሳቸውም፡ #ሩኩዓንም ሱጁዷንም በማጓደል ነው; በማለት


መለሱላቸው (አህመድ 22642)


በሠላት ውስጥ የማይረጋጋ ሰው፣ በሠላቱ ሊመሰጥ


አይችልም፡፡ ምክንያቱም መፍጠን መመሰጥን ስለሚጻረር


ነው፡፡ እንደ አሞራ ጎንበስ ቀና ማለት ምንዳን ያሳጣል፡፡


4 ፊት ለፊቱ የሚቆመውን አካል ኃያልነት


ማሰብ


በሠላት ውስጥ ሆኖ የፈጣሪን ኃያልነትና ልቅና፣


የነፍሱን ደካማነትና ወራዳነት፣እንዲሁም ጌታው ፊት


በመቆም እየተማፀነውና እያናገረው እንደሆነ ያስብ፣


ለርሱ በመዋደቅና በመዋረድ ፈጣሪውን ይለምን፡፡


ከዚህም ባሻገር፣ አላህ (ሱ.ወ) በወዲያኛው ዓለም


ለምእመናን ያዘጋጀውንና የደገሰውን፣ እንዲሁም


አጋሪያን የሚጠብቃቸውን ቅጣትና ውርደት


ያስተንትን፡፡ በወዲያኛው ዓለም ጌታው ፊት


የሚቆምበትን ጊዜ ያስታውስ፡፡


አንድ ሙእሚን በሠላት ውስጥ ሆኖ ይህን በአዕምሮው


መሳል ከቻለ፣ አላህ በመፀሐፉ ውስጥ፣ ‹‹ጌታቸውን


እንደሚገናኙ እርግጠኞች ናቸው›› ብሎ ከዘከራቸው


ሰዎች ይሆናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- #(ሠላት) በፈሪዎች


ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ እነዚያ


እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ እነሱም ወደርሱ ተመላሾች


መኾናቸውን የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ እንጅ ከባድ


ናት; ይላል፡፡ (አል በቀራ 45-46)


አንድ ሰጋጅ በሠላቱ ውስጥ መመሰጥን የሚያገኘው፣


አላህ (ሱ.ወ) እንደሚሰማው፣ የጠየቀውን


እንደሚሰጠውና ለልመናው ምላሽ እንደማይነፍገው


በሕሊናው መሳል በሚችለው ደረጃ ልክ ነው፡፡


5 የሚነበቡ አንቀጾችን፣ የሠላት ውዳሴና


ሙገሳዎችን ማስተንተንና ከነሱ ጋር በሕሊና


መጓዝ


ቁርኣን የተወረደው ሊያስተነትኑት ዘንድ ነው፡፡ #ይህ


ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሀፍ ነው አንቀጾቹን


እንዲያስተነትኑና የአዕምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ


አወረድነው፡፡; አንድ ሰው የሚያነባቸውን አንቀጾች፣


የሚላቸውን ውዳሴዎችና ዱዓዎች ትርጉም ካላወቀ


ሊያስተነትን አይችልም፡፡ ትርጉሙን መረዳት ሲችል፣


በአንድ በኩል እርሱ ያለበትን ሁኔታና ተጨባጭ


ነገር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአንቀጾቹን፣ የውዳሴና


ልመናዎቹን ትርጉም ማስተንተን ይችላል፡፡ ከዚህም፡


መመሰጥ፣እንዲሁም ለጌታው መዋረድና መዋደቅ


ይገኝለታል፡፡ ጥልቅ ስሜት ይሰማዋል፡፡ ምናልባትም


ዓይኖቹ ሊያነቡ ይችላሉ፡፡ አንድም አንቀጽ ጫና


ሳያሳድርበት አያልፍም፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- #እነዚያም


በጌታቸው አንቀጾች በተገሰጹ ጊዜ (የተረዱ ተቀባዮች


ኾነው እንጅ ) ደንቆሮችና ዕውሮች ኾነው በርሷ ላይ


የማይደፉት ናቸው፡፡; ይላል፡፡ (አል ፉርቃን 73)





122


> የጁምዓ ሠላት


አላህ (ሱ.ወ) በጁምዓ ዕለት፣


በዙህር ሠላት ወቅት እጅግ


በጣም የላቀ የኢስላም መገለጫና


ከግዴታዎቹ ሁሉ የጠበቀ ሠላትን


ደንግጓል፡፡ ይህ ሙስሊሞች


በሳምንት አንዴ የሚሰባሰቡበት


ዕለት ነው፡፡በዚሁ ዕለት የጁምዐው


ኢማም የሚያቀርብላቸውን


ምክርና ተግሳጽ ያዳምጣሉ ከዚያም


የጁምዐን ሠላት ይሰግዳሉ፡፡


የጁምዓ ዕለት ትሩፋት


የጁምዓ ዕለት ከሳምንቱ ቀናቶች


ትልቁና የላቀ ክብር ያለው ዕለት


ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከቀናቶች


መካከል መርጦታል፡፡ ከተቀሩት


ወቅቶች በበርካታ ልዩ ነገሮች


አብልጦታል፡፡ ከነኚህም መካከል፡-


ጁምዓ ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው?


የጁምዓ ሠላት የሚከተለውን መገለጫ ባሟላ ሰው ላይ


ግዴታ ነች፡፡


1 ወንድ፡ በሴት ላይ ግዴታ አይደለም


2 ለአቅመ አዳም የደረሰ፡ በባሪያና ባልደረሰ ሕፃን


ላይ ግዴታ አይደለም፡፡


3 ነዋሪ፡ በመንገደኛ፣ እንዲሁም ከከተማና ከመንደር


ርቆ በዱር በሚኖር ሰው ላይ ግዴታ አይደለችም፡፡


> ሰጋጆች የጁምዓን ኹጥባ በጥሞና ማዳመጥ ከርሱ ከሚያስተጓጉለቸውን ነገር መራቅ አለ


ባቸው፡፡


• አላህ (ሱ.ወ)፡ ይህን ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች


ነጥሎ በዚህ ዕለት አልቆታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡


- ‹‹አላህ (ሱ.ወ) ከኛ በፊት ያሉትን የጁምዓን


ዕለት አስቷቸዋል፡፡ ለአይሁዶች የቅዳሜን ዕለት፣


ለክርስቲያኖችም የእሁድን ዕለት አደረገላቸው፡፡


አላህ እኛን አመጣንና ለጁምዓ ዕለትም መራን፡፡››


ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 856)


• አደም የተፈጠረው በዚሁ ዕለት ነው፡፡ የምፅዓት


ዕለትም የምትከሰተው በጁምዓ ዕለት ነው፡፡ ነብዩ


(ሰ.ዐ.ወ)፡- #ፀሐይ ከምትወጣባቸው ቀናቶች


በላጩ የጁምዐ ቀን ነው፡፡ኣደም የተፈጠረው በሱ


ውስጥ ነው፡፡ ጀነት እንዲገባ የተደረገውም በሱ


ውስጥ ነው፡፡ ከሷም እንዲወጣ የተደረገው በዚሁ


ዕለት ውስጥ ነው፡፡ ሰዓቲቱም በጁምዓ ዕለት እንጂ


አትከሰትም፡፡; ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 854)





123


የጁምዓ ሠላት አፈፃፀምና ድንጋጌዎች


1 ከጀሙዓ ሠላት በፊት ገላን መታጠብ፤ኹጥባ


ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በጊዜ ወደ መስጂድ


መምጣትና ጥሩ ልብስ መልበስ የተወደደ ነው፡፡


2 ሙስሊሞች ጁምዓ በሚሰገድበት ትልቅ መስጂድ


ወይም መስጂድ ጃሚዕ ውስጥ ይሰባሰቡና፣


ኢማሙ በመድረክ ላይ በመውጣት ፊቱን ወደ


ሰጋጆቹ በማዞር በሁለት ክፍል የተከፈለ ኹጥባ/


ዲስኩር ያደርግላቸዋል፡፡ በሁለቱ ኹጥባዎች


መሐከል፣ ለመለያ ያክል ትንሽ ጊዜ በመቀመጥ


እረፍት ያደርጋል፡፡ በኹጥባው ውስጥ፣ አላህን


እንዲፈሩ ያስታውሳል፡፡ የቁርኣን አንቀጾችን


እያጣቀሰ የተለያዩ ምክሮችና ተግሳጾችን


ያስተላልፋል፡፡


3 ሰጋጆቹ ኹጥባውን በጥሞና ማዳመጥ


አለባቸው፡፡ መነጋገር ወይም ከኹጥባው


ተጠቃሚ እንዳይሆኑ በሚያደርጉ ነገሮች


እራስን ማጥመድ ክልክል ነው፡፡ መስገጃ


መነካካት ወይም አሸዋና አፈር እያነሱ መበተን


እንኳን ክልክል ነው፡፡


4 ከዚህ ቀጥሎ፣ ኢማሙ ኹጥባውን ሲጨርስ


ከመድረኩ ይወርዳል፡፡ ኢቃም ይደረግና በቁርኣን


ንባቡ ድምፁን ከፍ በማድረግ ሁለት ረክዐዎችን


ያሰግዳቸዋል፡፡


5 የጁምዓ ሠላት የተደነገገው የተወሰነ ያክል ሰው


ለሚገኝበት ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ፣ የጁምዓ ሠላት


ያመለጠው ወይም በሆነ ምክንያት ከጁምዓ ሠላት


የቀረ ሰው፣ በሱ ምትክ መስገድ ያለበት ዙህርን


ነው፡፡ ብቻውን የሚሰግደው ጁምዓ ተቀባይነት


የለውም፡፡


6 ከጁምዓ ሠላት የዘገየና ከኢማሙ ጋር ከረከዓ


ያነሰውን ክፍል እንጂ ያልደረሰ ወይም ያላገኘ


ሰው የሚሞላው ሠላት በዙህር መልክ ነው፡፡


7 ጁምዓ ግዴታ የማይሆንባቸው፣ ሴቶችና መንገደኛ


የመሳሰሉት በሙሉ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን


ቢሰግዱ ሠላታቸው ተቀባይነት ያገኛል፡፡ በዚህም


የዙህር ሰላት ግዴታ ይወርድለታል፡፡


ከጁምዓ ለመቅረት የሚፈቀድለት ማን ነው?


ኢስላማዊው ድንጋጌ፣ የጁምዓ ሠላት ላይ መገኘቱ


ግዴታ በሆነባቸው ሰዎች ላይ ሁሉ በቦታው መጣድ


ግዴታ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል፡፡ በዓለማዊ ጉዳይ


ከርሱ መዘናጋትን አጥብቆ አስጥንቅቋል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ)፡- #እናንተ ያመናችሁ ሆይ በዐርብ ቀን ለስግደት


ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ መሸጥንም


ተዉ፤ ይሃችሁ የምታውቁ ብትኾኑ ለናንተ በጣም


የተሻለ ነው፡፡›› ይላል፡፡ (አል ጁምዓ 9)


ያለ ህጋዊ ምክንያት ከርሱ የሚቀርን ሰው በልቦናው ላይ


መናፍቅነት መታተምን አስጥንቅቋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡


- ‹‹ያለ ምንም ምክንያት በመዘናጋት ሦስት ጁምዓን የተወ


ሰው፣ አላህ (ሱ.ወ) በቀልቡ ላይ ያትምበታል፡፡›› ብለዋል፡


፡ (አቡ ዳውድ 1052 አህመድ 15498) ‹‹በቀልቡ ላይ


ያትምበታል›› ማለት ይጋርደዋል፣ ይሸፍነዋል፣ በውስጡ


እንደ መናፍቃንና አመጸኞች ልብ መሃይምነትንና ድርቀትን


ያበቅልበታል ማለት ነው፡፡


ከጁምዓ ለመቅረት የሚያስችል ምክንያት፡ ድንገተኛና


ያልተለመደ፣ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ወይም በኑሮ


አለያም በጤና ላይ አስጊና አደገኛ ሁኔታ መከሰት ነው፡፡





124


በስራና ሃላፊነት ላይ ለመገኘት


ሲባል ከጁምዓ መቅረት እንደ ህጋዊ


ምክንያት ይታያልን?


በመሰረቱ፣ በስራና ሃላፊነት ላይ


ለመገኘት ሲባል ከጁምዓ ሠላት


መቅረት ህጋዊነት ወይም ተቀባይነት


ያለው አይደለም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በዚህ


ወቅት ስራችንን ትተን ለሠላት ዝግጁ


እንድንሆን፣ #እናንተ ያመናችሁ ሆይ


በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ


ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ መሸጥንም


ተዉ ይሃችሁ የምታውቁ ብትኾኑ


ለናንተ በጣም የተሻለ ነው፡፡›› በማለት


አዞናል፡ (አል ጁምዓ 9)


አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹አላህንም የሚፈራ


ሰው ለርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡


ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፡


፡በአላህ ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው


ነው፡፡›› ይላል፡፡ (አጠላቅ 2-3)


> አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡


ስራ፣ ከጁምዓ ሠላት ለመቅረት ህጋዊ ምክንያት የሚሆነው ምን ጊዜ ነው?


ቀጥለው ከተጠቀሱት፣ ከሁለቱ በአንዱ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር ተደጋጋሚና ዘውታሪ ስራ ከጁምዓ ሠላት ለመቅረት


እንደ ምክንያት ሊቆጠር አይችልም፡፡


1 እርሱ በቦታው ላይ በመኖሩና ከጁምዓ በመቅረቱ እንጂ ሊከሰት የማይችል ትልቅ ህዝባዊ ጥቅም ካለና ይህን


ስራ እርሱ ከተወው ከፍተኛ ጉዳትና አደጋ የሚደርስ ከሆነ እርሱን ሊተካው የሚችል ማንም ከሌለ፡፡


2 ስራው ብቸኛ የገቢ ምንጩ ከሆነ አስፈላጊ የዕለት ወጪዎቹን ምግቡን መጠጡንና ወሳኝ ጉዳዮችን ለራሱና


ለቤተሰቦቹ የሚያስፈፅምበት ከዚያ ስራ ውጭ ምንም ከሌለው ሌላ ስራ እስከሚያገኝና ያለበት ችግር


እስኪወገድለት ድረስ በዚያ ስራ ላይ በመቆየት ጁምዓ ሳይሰግድ ቢቀር ይፈቅድለታል፡፡ወይም ምግቡን


መጠጡንና አስፈላጊ ጉዳዮችን ለራሱና ለቤተሰቦቹ የሚያስፈጽምበት እስከሚያገኝ ድረስ ይፈቀድለታል፡፡


ይሁን እንጂ ሌላ ስራና የገቢ ምንጭ ማስገኛ መንገድ የማፈላለግ ግዴታ አለበት፡፡


• በድንገተኛ ክፍል የሚሰራ ዶክተር ድንገተኛ አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞችንና በሽተኞች


የሚያክም ከሆነ


• ዘበኛና ፖሊስ የሰዎች ንብረት በሌቦችና በወሮበሎች እንዳይዘረፍ በመጠብቅና በመከላከል


ላይ ከተሰማሩ


• በትላልቅ ኢንዳስትሪ ውስጥ የማሽኖችና መሳሪያዎችን ሂደት የሚከታተልና የሚቆጣር


ቴክኒሻን ከሆነ ክትትል ለሴኮንዶች መቋረጥ የማይችል ከሆነ


ምሳሌ





125


> የመንገደኛ ሰላት


• መንገደኛ ከቦታ ቦታ በሚዘዋወርበት ወይም ከአራት


ቀን ላነሰ ወቅት ጊዚያዊ ቆይታ በሚያደርግበት ስፍራ


ሆኖ ባለ አራት ረከዓ ሰላቶቹን ሁለት ረከዓ አድርጎ


መስገድ ይወደድለታል፡፡ዙህር ዐሱርና ዒሻን የአገሬ


ነዋሪ የሆነ ኢማምን ተከትሎ ካልሰገደ በስተቀር


በአራት አራት ረከዓ ምትክ ሁለት ሁለት አድርጎ


ይሰግዳል፡፡ እንዲያ ከሆነ ግን ኢማሙን ሊከተልና


እንደሱ አራት ረከዓ ሊሰግድ ይገባል፡፡


• ከፈጅር ሱና በስተቀር የተቀሩትን ተቀጥላ ሱና


ሰላቶችን ቢተው ወይም ባይሰግድ ይችላል፡፡


• ዙህርና ዐስሩን በአንድነት መግሪብና ዒሻን በአንድነት


አቆራኝቶ መስገድ ይችላል፡፡ በተለይ በሚዘዋወርበትና


በሚሳፈርበት ወቅትና ሁናቴ ላይ ከሆነ የአላህን


ህግ ገራገርነት እዝነትና ማጨናነቅ የሌለው መሆኑን


የሚያሳይ ነው፡፡


> የታማሚ ሰው ሰላት


አዕምሮውን እስካልሳተና እራሱን እስካወቀ ድረስ


በፈለገው ሁናቴ ላይ ቢሆንም ሰላት በሙስሊም ላይ


ግዴታ ነው፡፡ ነገር ግን እስልምና የሰዎችን ሁኔታና


ያለባቸውን ጉዳይ ከግምት አስገብቷል፡፡ ከነዚህ


ሁኔታዎች አንዱ ህመም ነው፡፡


ይህን ለማብራራት ያክል፡


• መቆም የማይችል ወይም መቆም የሚያስቸግረው


ወይም ለመቆም የሚያስችለው ፈውሱ የሚዘገይበት


የሆነ ህመምተኛ ቆሞ መስገድ ይሻርለታል፡፡ እርሱ


የሚሰግደው ቁጭ ብሎ ነው፡፡ቁጭ ማለትም ካልቻለ


በጎኑ እንደተጋደመ ይሰግዳል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፡ ቁመህ ስገድ፡፡ ካልቻልክ ቁጭ


ብለህ ስገድ፡፡ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ


አል ቡኻሪ 1066


• ማጎንበስ (ሩኩዕ) ወይም ሱጁድ ማድረግ ያልቻለ


ሰው በሚችለው ልክ ምልክት በማድረግ ይሰግዳል፡፡


• በመሬት ላይ ቁጭ ማለት የሚቸገር ሰው በወንበርና


በመሰል ነገሮች ላይ ቁጭ ብሎ መስገድ ይችላል፡፡


• በህመም ምክንያት ለእያንዳንዱ ሰላት መጥራራት


ወይም ዉዱእ ማድረግ የሚቸገር ሰው ዙህራና ዐሱርን


በአንድነት መግሪብና ዒሻን በአንድነት በማቆራኘት


መስገድ ይችላል፡፡


• ሰላት ለመስገድ በህመም ምክንያት ውሃን መጠቀም


የማይችል ሰው በአፈር ተየሙም ማድረግ ይችላል፡፡


ጾምህ



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎ ...

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች።

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የ ...

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ...

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት