ሠላትህ
3
ሠላት የሃይማኖት መሰረት ነው፡፡ ባሪያውን ከጌታው ጋር
የሚያገናኝ መስመር ነው፡፡ ስለሆነም ከአምልኮዎች ሁሉ ታላቁና
ደረጃውም እጅግ የላቀ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ አንድ ሙስሊም
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እርሷን እንዲጠብቅ አዟል፡፡
ነዋሪም ሆነ መንገደኛ፣ ጤነኛም ሆነ ህመምተኛ፣እንዲተገብራት
አዟል፡፡
የምዕራፉ ማውጫ
የሠላት ደረጃና ትሩፋት
የሠላት ትሩፋት
አምስቱ የግዴታ ሠላቶችና ወቅቶቻቸው
የሠላት ቦታ
የሠላት አፈፃፀም
የምሰግደው እንዴት ነው?
የሸላት ማዕዘናትና ግዴታዎች
ሠላትን የሚያበላሹ ነገሮች
በሠላት ውስጥ የሚጠሉ ነገሮች
የመቃረቢያ ስግደቶች የትኞቹ ናቸው?
የህብረት(ጀመዐህ) ሠላት
አዛን (ጥሪ)
በሠላት ውስጥ መመሰጥ
የጁምዓ ሠላት
የመንገደኛ ሠላት
የታማሚ ሰው ሠላት
ሠላት
የሠላት መሰረታዊ ትርጉሙ፡ መማፀን
ወይም መለመን ሲሆን፣ ባሪያን ከፈጣሪው ጋር
የምታገናኝ መስመር ነች፡፡ በውስጧ ወሳኝ የሆኑ
የባርነት መገለጫዎችን አቅፋለች፡፡ ወደ አላህ
መሸሽና በርሱ መታገዝን አዝላለች፡፡ በሠላት
ውስጥ ባሪያው ጌታውን ይለምናል፣ በሚስጥር
ያወራል፣ ያወሳዋል፣ ነፍሱ ትጸዳለች፣ ባሪያው
እውነተኛ ማንነቱን ያስታውስበታል፣በውስጧ
እየኖረባት ያለችውን የዱንያን ትክክለኛ
ገጽታ ይገነዘባል፡፡ የዚህች ዓይነቷ ሠላት፣
በሪያው በአላህ ህግጋትና ድንጋጌ ላይ ጽናት
እንዲኖረው፣ ከግፍ፣ ከዝሙትና ከአመፀኝነት
እንዲርቅ ታደርገዋለች፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡
- «ሠላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፤ ሠላት
ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡»
ይላል፡፡ (አል አንከቡት 45)
>የሠላት ደረጃና ትሩፋት
ሠላት ከአካላዊ አምልኮዎች ታላቋና ደረጇም
የላቅ ነው፡፡ ቀልብን፣ አዕምሮንና ምላስን በአንድነት
የሚያሳትፍ አምልኮ ነው፡፡ የሠላት አንገብጋቢነትን
ከብዙ አቅጣጫ መመልከት ይቻላል፡፡
ሠላት ከፍ ያሉ ደረጃዎች አሉት
1 ከኢስላም ማዕዘናት መካከል ሁለተኛው
ማዕዘን ነው፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)፡- «ኢስላም
በአምስት መሰረታዊ ማዕዘናት ላይ ተገነባ፡፡
-ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ
የለም፣ ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ ናቸው ብሎ
መመስከር፣ ሠላትን ማቋቋም፣….» ብለዋል፡፡
(አል ቡኻሪ 8 /ሙስሊም 16) የአንድ ግንባታ
ማዕዘን ወይም ምሰሶ፣ ያለርሱ ግንባታው
የማይቆምበት መሰረቱ ማለት ነው፡፡
2 ሸሪዓዊ መረጃዎች፣ በሙስሊሞችና በካሃዲያን
መካከል መለያ ነጥብ ያደረጉት ሠላትን ማቋቋምን
ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «በአንድ ሰውና በክህደት
መሐከል ያለው ነገር ሠላትን መተው ነው፡፡
» ብለዋል፡፡(ሙስሊም 82) «በእኛና በእነርሱ
መሐከል ያለው ኪዳን ሠላት ነው፡፡ እርሷን
የተወ በርግጥ ክዷል፡፡» ብለዋል፡፡ (አል ቲርሚዚ
2621/ አል ነሳኢ 463)
3 አላህ (ሱ.ወ) ሠላትን በማንኛውም ሁኔታ
ላይ ሆኖ እንዲተገበር አዟል፡፡ በመንገደኛነት፣
በነዋሪነት፣ በሰላም፣ በጦርነት፣ በጤንነት፣
በህመምም ላይ ሆኖም በሚቻለው መጠን
ሁሉ ይተገበራል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «በሰላቶች
ተጠባበቁ» ይላል፡፡ (አልበቀራ 238)
ምዕመናን ባሮቹን ደግሞ፡- «እነዚያም እነሱ
በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኾኑት፡፡
»በማለት ይገልጻቸዋል፡ (አል ሙእሚኑን 9)
95
> አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጅ፣ በጦርነትና በአደጋ ጊዜ እንኳን
ቢሆን፣ ብቻ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆኖ ሠላትን
እንዲተገብር አዟል፡፡
የሠላት ትሩፋት
የሠላትን ትሩፋት በማስመልከት በርካታ የቁርኣንና
የሐዲስ ማስረጃዎች ተላልፈዋል፡፡ ከነሱም መካከል
የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
1 ሠላት ወንጀሎችን ታብሳለች፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡
- «አምስት ሠላቶችና ከጁምዓ እስከ ጁምዓ ትላልቅ
ወንጀሎች እስካልተጣሱ ድረስ በመካከላቸው
የሚፈፀሙትን ወንጀሎች ያብሳሉ፡፡» ብለዋል፡፡
(ሙስሊም 233/ አል ቲርሚዚ 214)
2 ሠላት፣ለአንድ ሙስሊም በመላው ሕይወቱ
የምታበራለት ብርሃኑ ናት፡፡ በመልካም ነገር ላይ
ታግዘዋለች፡፡ ከመጥፎ ነገሮች ታርቃዋለች፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡
- «ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡»
ይላል፡፡ (አል አንከቡት 45) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «ሠላት ብርሃን
ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 223)
3 ሠላት፣ የትንሳኤ ቀን ባሪያው በመጀመሪያ የሚገመገምባት
ጉዳይ ናት፡፡ እርሷ ካማረችና ተቀባይነት ካገኘች፣ የተቀረው
ስራ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ እርሷ ተመላሽ ከሆነች የተቀሩት
ስራዎችም ተመላሽ ይሆናሉ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «የትንሳኤ
ቀን ባሪያው በመጀመሪያ የሚገመገምበት ነገር ሠላት
ነው፡፡ እርሷ ካማረች የተቀሩት ስራዎቹ ያምራሉ፡፡ እርሷ
ከተበላሸች የተቀሩት ስራዎችም ይበላሻሉ፡፡» ብለዋል፡፡
(አል ሙዕጀሙል አውሰጥ ሊጠበራኒ 1859)
ሙእሚን በጣም የሚረካበት ቆይታ፣ በሠላት ውስጥ
ጌታውን ሲያናግር ነው፡፡
በዚህን ጊዜ፣ መንፈሳዊ እረፍትን፣ መረጋጋትናና አጫዋችን
ያገኛል፡፡
ሠላት ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታላቋ የዓይን ማረፊያ ነበረች፡፡
ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) የህንኑ ሲገልጹ፡-«የዓይኔ መርጊያ በሰላት ውስጥ
ተደርጎልኛል፡፡»ይላሉ፡፡ (አል ነሳኢ 3940)
ወደ ሠላት ለሚጣራው ሙኣዚናቸው ቢላል፡- «ቢላል ሆይ
በርሷ አሳርፈን» ይሉ ነበር፡፡ (አቡ ዳውድ 4985)
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ የሆነ ጉዳይ ካሳሰባቸው ወይም ካጨናነቃቸው
ወደ ሰላት ይሸሹ ነበር፡፡ (አቡ ዳውድ 1319)
ሠላት ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው?
ሠላት፣ በወር አበባና በወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች
ሲቀሩ በማንኛውም ጤናማ አዕምሮ ባለው፣ ሃላፊነትን
ለመሸከም በደረሰ ሙስሊም ሁሉ ላይ ግዴታ ነው፡፡
ሴቶች በወር አበባ ወይም በወሊድ ደም ላይ ሆነው
አይሰግዱም፡፡ ከጸዱና ደሙ ከተቋረጠ በኋላም ሠላትን
አይከፍሉም፡፡ (ገጽ 96 ተመልከት)
ለአቅመ አዳምና ሄዋን መድረስ የሚወሰነው
ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱ ሲሟላ ነው፡፡
አስራ አምስት ዓመት መድረስ
በፊት ለፊት ወይም በኋላ ብልቶች ዙሪያ ከርደድ
ያለ ጸጉር ማብቀል
በሕልም ወይም በንቃተ ሕሊና የፍቶት ፈሳሸን
ማፍሰስ
ለሴት፣ የወር አበባ መታየት ወይም ማርገዝ
96
> ለሠላት ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች ምንድን ናቸው?
1 ከሐደስና ከነጃሳ መጥራት፡፡ ዝርዝር ገለፃውን አሳልፈናል (ገጽ፣ 91 ተመልከት)
2 ሀፍረተ ገላን መሸፈን
ሀፍረተ ገላን በአጭርነትና ወይም በስስነት የሰውነት ክፍሎችን የማያጋልጥና የማያሳይ በሆነ ልብስ መሸፈን
የግድ ነው፡፡
ሀፍረተ ገላ ሦስት ዓይነት ነው፡፡
ለሴት፡ ሰላት ለመስገድ የደረሰች ሴት ሀፍረተ ገላ ከፊቷና ከመዳፎቿ በስተቀር ሰውነቷ በሙሉ ነው፡፡
ለሕፃን፡ ትንሽ ሕፃን ልጅ ሀፍረተ ገላው ሁለቱ ብልቶቹ ብቻ ናቸው፡፡
ወንድ፡ የደረሰ ወንድ ሀፍረተ ገላ ከእምብርቱ እስከ ጉልበቱ ድረስ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ)፡- «የአደም ልጆች ሆይ (ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡»
ይላል፡፡ (አል አዕራፍ 31) ሀፍረተ ገላን መሸፈን ከመጌጥ ትንሹ ደረጃ ነው፡፡ ‹‹በመስገጃው ሁሉ›› ማለት በየሠላቱ
ማለት ነው፡፡
> ሙስሊም ሴት፣ በሠላት ውስጥ ከፊቷና ከመዳፎቿ በስተቀር ሌላውን ሰውነቷን በሙሉ መሸፈን አለባት፡፡
97
3 ወደ ቂብላ መቅጣጨት ወይም መዞር
አላህ (ሱ.ወ)፡- «ከየትም (ለጉዞ) ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አቅጣጫ አዙር፡፡» ብሏል፡፡
(አል በቀራ 149)
• የሙስሊሞች የስግደት አቅጣጫ የተከበረው ካዕባ ነው፡፡ እሷን የገነባት የነብያት አባት የሆነው ኢብራሂም(ዐ.ሰ)
ነው ፡፡ ነብያት ወደርሷ የአምልኮ ጉዞ (ሐጅ) አድርገዋል፡፡ እርሷ የማትጠቅም የማትጎዳም ድንጋይ እንደሆነች
እናውቃለን፡፡ ግን አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በሙሉ ወደ አንድ አቅጣጫ በመዞር አንድ እንዲሆኑ፣ ስንሰግድ ወደርሷ
እንድንዞር ወይም እንድንቅጣጭ አዞናል፡፡ ስለሆነም፣ ወደ ካዕባ በመዞራችን የአላህ ብርነታችንን እንገልፅበታለን፡፡
• አንድ ሙስሊም ሲሰግድ ካዕባን ፊት ለፊት የሚመለከታት ከሆነ ወደርሷ ፊቱን ማዞር ግድ ነው፡፡ ከርሷ በርቀት
የሚገኝ ሰው ደግሞ ወደ መካ አቅጣጫ መዞሩ በቂ ነው፡፡ በሚቅጣጭ ጊዜ ከካዕባ አቅጣጫ ትንሽ ማዘንበሉ
ወይም መዞሩ ችግር የለውም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «በምስራቅና በምዕራብ መሐከል ያለ በሙሉ የሠላት አቅጣጫ
(ቂብላ) ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (አል ቲርሚዚ 342)
• ልክ የተቀሩት ግዴታዎች በመቸገር ምክንያት ግዴታነታቸው እንደሚነሳ ሁሉ፣ በበሽታ ወይም በሌላ ምክንያት ወደ
ካዕባ መዞር ላልቻለም ግዴታነቱ ይነሳለታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፡፡» ይላል፡፡
(አል ተጋቡን 16)
4 የሠላት ወቅት መግባት
ይህ ለሠላት ትክክለኛነት መስፈርት ነው፡፡ ወቅቷ ከመግባቱ በፊት የተሰገደች ሠላት ትክክለኛ አትሆንም፡
፡ ከወቅቷ ማዘግየትም የተከለከለ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «ሶላት በምእመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ
ናትና፡፡» ይላል፡፡ (አል ኒሳእ 103)
ወቅት በመግባት ዙሪያ በተወሰኑ ነገሮች ላይ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡
• ሠላትን በመጀመሪያው ወቅት ላይ መስገዱ በላጭ ነው፡፡
• ሠላትን በወቅቷ መስገድ ግዴታ ነው፡፡ በማንኛውም ምክንያት ቢሆንም ሠላትን ማዘግየት ክልክል ነው፡፡
• በእንቅልፍ ወይም በመርሳት
ምክንያት ሠላት ያለፈው
ሰው ባስታወሰ ጊዜ ፈጥኖ
መስገድ አለበት፡፡
> አላህ (ሱ.ወ)፡- «ሶላት በምእመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡» ይላል፡፡ (አል ኒሳእ 103)
98
> አምስቱ የግዴታ ሠላቶችና ወቅቶቻቸው
አላህ (ሱ.ወ) በሙስሊሞች ላይ በቀንና በሌሊት ውስጥ አምስት ሠላቶችን ግዴታ አደርጓል፡፡ እነኚህ ሠላቶች
የሃይማኖት ምሶሶዎች ናቸው፡፡ ግዴታነታቸውም እጅግ አጽንዖት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ለነርሱም የሚከተሉትን
ወቅቶች አድርጎላቸዋል፡፡
የፈጅር ሠላት፡ ሁለት ረካዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ጎሕ ከሚወጣበት
ጊዜ ሲሆን፣ በአድማስ ላይ ብርሃን ሲፈነጥቅ ወይም ጨለማ መገፈፍ ሲጀምር
ይከሰታል፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ፀሐይ ስትወጣ ነው፡፡
የዐሥር ሠላት፡ አራት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው የዙህር ወቅት
ካበቃበት ጊዜ ጀምረ ሲሆን ይኸውም የእያንዳንዱ ነገር ጥላ ከራሱ ቁመት
ጋር ሲስተካከል ነው፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ፀሐይ ስትጠልቅ ነው፡፡ አንድ
ሙሰሊም ይህችን ሠላት፣ የፀሐይ ብርሃን ጮራ መድከምና መገርጣት
ሳይጀምር ፈጠን ብሎ ሊሰግድ ይገባዋል፡፡
የዒሻእ ሠላት፡ አራት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ቀዩ ብርሃን ከጠፋበት
ቅጽበት ነው፡፡ የሚያበቃው እኩለ ሌሊት ላይ ነው፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታ
በሚገጥምበት ጊዜ ጎህ እስኪ ቀድ ባሉት ሰዓቶችም ውስጥ ሊሰገድ ይችላል፡፡
የዙህር ሰላት፡ አራት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ፀሐይ ከመሐል አናት
በምታዘነብልበት ጊዜ ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ የእያንዳንዱ ነገር ጥላ ከራሱ
ቁመት ጋር ሲስተካከል ነው፡፡
የመግሪብ ሠላት፡ ሦስት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ፀሐይ
ከጠለቀችበትና ፍንጣቂዋ ከአድማስ ላይ ሲወገድ ወይም ሲደበቅ ነው፡፡
የሚያበቃው ደግሞ ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ የሚታየው ቀዩ ወጋገን ሲጠፋ
ነው፡፡
አንድ ሙስሊም የሰላትን ወቅቶች በተመለከተ በወቅቶች ሰሌዳ መጠቀም ይችላል ነገር
ግን ወደ ሰላት ለመግባት እሱን የመመልከት ግዴታ የለበትም
99
ኢስላም ሠላት በህብረት ወይም በጀመዓ
እንዲፈፀም አዟል፡፡ ለሙስሊሞች መገናኛና
መሰባሰቢያ መንገድ ይሆን ዘንድም በመስጂድ
ውስጥ እንዲፈፀም አበረታቷል፡፡ ይህን
በማድረግ፣በመካከላቸው ወንድማማችነትና
ፍቅር ይጨምራል፡፡ ኢስላም የጀመዓ ሠላትን
አንድ ሰው ለብቻው ከሚሰግደው ሰላት በብዙ
ደረጃዎች የሚበልጥ አድርጎታል፡፡ ነብዩ
(ሰ.ዐ.ወ)፡- «አንድ ሰው በጀመዓ የሚሰግደው
ሠላት በነጠላ ለብቻ ከሚሰገደው ሠላት በሃያ
ሰባት ደረጃ ይበልጣል፡፡» ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ
619/ ሙስሊም 650/ አህመድ 5921)
ሠላት በማንኛውም ስፍራ ቢሰገድ ትክክለኛ
ነው፡፡ ይህም የአላህ እዝነት መገለጫ ነው፡
፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «ምድር መስገጃና ንጹህ
ተደርጋልኛለች፤ከህዝቦቼ፣ ማንም ሰው ሠላት
ከደረሰበት፣ በደረሰበት ስፍራ ይስገድ» ብለዋል፡
፡ (አል ቡኻሪ 328/ ሙስሊም 521)
የሠላት ቦታ ይዘት
ኢስላም፣ ሠላት የሚሰገድበት ቦታ ንጹህ እንዲሆን
በመስፈርትነት አስቀምጧል። አላህ (ሱ.ወ)፡- «ወደ
ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና
ለተቀማጮቹም፣ ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል
ቃል ኪዳን ያዝን፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 125) የነገሮች
መስረት ንጹህ ነው፤ ነጃሳ ደግሞ ባዕድ/መጤ ነው፡፡
ስለሆነም፣ ነጃሳ ያለበት መሆኑን እርግጠኛ ባልሆንክበት
ነገር ላይ ንጹህነትን ትወስናለህ፡፡ በመስገጃ ወይም ሰሌን
ላይ እንጂ አለመስገድ የሚወደድ ተግባር አይደለም፡፡
ልንከተላቸው የሚገቡ በርካታ ስርዓተ ደንቡች
አሉ፡፡ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
1 በመስገጃ ስፍራ ላይ ሰዎችን አለማስቸገር፡፡ ለምሳሌ፡
የመተላለፊያ መንገድ ላይ መስገድ፣ እንዲሁም
ግፊያና መጨናነቅን በሰዎች ላይ የሚፈጥር ስፍራ
ላይ መቆም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሰዎችን ማስቸገርና
በነሱ ላይ ጉዳት ማድረስን ሲከለክሉ፡- «መጉዳትም
መጎዳትም (በኢስላም) ቦታ የለውም፡፡» ብለዋል፡፡
(ኢብኑ ማጃህ 2340/ አህመድ 2865)
2 በመስገጃ ቦታ ላይ፣እንደ ስዕል፣ ከፍ ያለ ድምጽና
ሙዚቃ ያለ፣ ሰጋጅን የሚረብሽና ትኩረቱን
የሚበትን ነገር መኖር የለበትም፡፡
3 የመስገጃው ስፍራ ለሹፈትና ለፊዝ የሚያጋልጥ
መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ፡ ሰካራሞች
በተሰበሰቡበት ወይም ጽንፈኞች በሚያዘወትሩበት
ስፍራና በመሳሰሉት ቦታዎች፣መስገጃ መሆን
የለባቸውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የካሃዲያንን አማልክት
መሳደብን የከለከለው እነሱ ባለማወቅ አላህን
እንዳይሰድቡ ለመከላከል ሲል ነው፡፡ እንዲህም
ይላል፡- «እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውን
(ጣዖታት)አትስደቡ፤ ድንበርን በማለፍ ያለ
ዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡» (አል አንዓም 108)
የመስገጃ ቦታ፣ እንደ ዳንስና ጭፈራ ቤት ያለ፣
አላህን ለማመፅ የተዘጋጀ መሆን የለበትም፡፡
በዚህ መሰሉ ስፍራ ሠላት መስገድ የተጠላ ነው፡፡
4
> የሠላት ቦታ (ስፍራ)
100
ይህ ህዝብ (የነቢዩ ኡማህ)
ከተቸረው ልዩ ነገር መሐከል
በምድር ላይ በየትም ስፍራ
ቢሰገድ ሠላቱ ተቀባይነት ያለው
መሆኑ ነው፡፡
በመስጂድ ውስጥ ከጀመዓ ጋር መስገድ ትችላለህን?
ቦታው ነጃሳ ባይሆንም ሰዎችን የሚያስቸግር ቦታ ላይ መስገድ ይፈቀዳል? ለምሳሌ
መተላለፊያ መንገዳቸው ቢሆን?
እንደ ፎቶና ከፍተኛ ድምፅ የመሰሉ ከ የሚያስተጓጉሉ ነገሮች ባሉበት
ቡታስ?
በመስጂድ ውስጥ መስገድ ካልቻልክ ከሱ ሌላ ያሉ ቦታዎች ነጃሳ ናቸውን?
አዎ፡ ሠላትን በጀመዓ መስገድ በወንድ ላይ የጠበቀ
ግዴታ ነው፡፡ ከስራዎች ሁሉ ትልቁና አላህ ዘንድ እጅግ
የላቀ ነው፡፡ በጀመዓ መስገድ ለሴቶችም ይፈቀዳል፡፡
ሰዎችን ማስቸገርና ለመስገድ እንኳን ቢሆን በነርሱ
ላይ መጨናነቅን መፍጠር ክልክል ነው፡፡ ሌላ ቦታ
ልትመርጥና ልትቀይር ይገባል፡፡
ሰጋጅን ከሚረብሹና ሠላቱን ከሚያስተጓጉሉ ነገሮች ሁሉ
መራቅ ያስፈልጋል፡፡
በነጃሳ ቦታ ላይ መስገድ የተከለከለ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)
ለሠላት ጽዱዕ እንድንሆን አዞናል፡፡
101
> የሠላት ገጽታ
1 ማሰብ (ኒያ)
ኒያ ለሠላት ትክክለኛነት መስፈርት ነው፡፡ ለምሰሌ፡
የመግሪብ ወይም የዒሻእ ሠላት መሆኑን ለይቶ፣
በልቦናው በሠላት አላህን መገዛት ማለም፣የሠላት ኒያን
ይገልፃል፡፡ ድምፅን ከፍ በማድረግ ሐሳቡን በንግግር
መግለጽ አይፈቀድም፡፡ የሚፈለገው በልቦናውና
በሕሊናው ማለም ብቻ ነው፡፡ ይህን ድምፅ
በማውጣት መግለጽ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም፣ ኒያን
በንግግር መግለጽ ከነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ሆነ ከተከበሩት
ባልደረቦቻቸው ስላልተላለፈ ነው፡፡
2 ለሠላት እንደቆመ አላሁ አክበር (አላህ ትልቅ
ነው፡፡) ይላል፡፡ በዚህን ጊዜ፣ የውስጥ መዳፉን ወደ
ቂብላ አቅጣጫ በማዞር፣ እጁን በትከሻው ልክ ወይም
የበለጠ ከፍ ያደርጋል፡፡
አላሁ አክበር ከሚለው ቃል ውጭ ሌላ ዓይነት ቃልን
መጠቀም አይቻልም፡፡ ትርጉሙም፡ ክብር፣ የበላይነትና
ኃያልነት ለአላህ የተገባ ነው ማለት ነው፡፡ አላህ ከርሱ
ሌላ ካሉ አካሎች ሁሉ ታላቅ ነው፡፡ ከዱንያና በውስጧ
ካሉ ፍላጎቶችና መርኪያዎች ሁሉ የበለጠ ነው፡፡
ስለሆነም ስንሰግድ በልቦናችንና በሕሊናችን ተመስጠን
ሁሉን ነገር ወደ ጎን በመተው ወደ ታላቁ አላህ እንዙር፡፡
3 አላሁ አክበር ካለ በኋላ፣ ቀኝ እጁን በግራ እጁ ላይ
በማነባበር በደረቱ ላይ ያስቀምጣል፡፡ ምንጊዜም ሲቆም
ማድረግ ያለበት ይህንን ነው፡፡
4 የመክፈቺያ ዱዓ ቢል የተወደደ
ነው፡፡ እሱም፡- «ሱብሓነከላሁመ
ወቢሐምዲከ፣ ወተባረከስሙከ፣
ወተዓላ ጀዱከ፣ ወላ ኢላሃ
ገይሩከ»- የሚለው ሲሆን፣
ትርጉሙ፣ «አምላካችን ሆይ
ከምስጋና ጋር ጥራት ይገባህ
፡፡ ስምህ የተባረከ ነው፡፡
ልዕልናህ የላቀ ነው፡፡ ካንተ
ሌላ አምላክ የለም፡፡» ማለት
ነው፡፡
5 አዑዙ ቢላሂ ሚነ
ሸይጧኒ ረጂም (ከእርጉሙ
ሰይጣን በአላህ እጠበቃለሁ)
ይላል፡፡ ጥበቃን መፈለግ ይህ ነው ፡፡ ትርጉሙ፣ ‹‹ወደ
አላህ በመጠጋት ከሴጣን ተንኮል እጠበቃለሁ›› ማለት
ነው፡፡
6 በስመላህን፣(ቢስሚላሂ ራሕማኒ ረሒም) -
(በአላህ ስም እጅግ ርኀሩኀ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
) የሚለውን ሐረግ ያነባል፡፡ የበስመላህ መልዕክቱ፣
በአላህ ስም የምታገዝና የምባረክ ስሆን
እጀምራለሁ ማለት ነው፡፡
7 የፋቲሓን ምዕራፍ ያነባል፡፡
ፋቲሓ በአላህ መፅሐፍ ውስጥ ባለው
ክብርና ደረጃ ታላቁ ምዕራፍ ነው፡፡
• አላህ (ሱ.ወ) ይህን ምዕራፍ
ማውረዱን በረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ላይ ውለታ አድርጎ ቆጥሮታል፡
፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «ከሚደጋገሙ
የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም
ቁርኣን (በሙሉ) በርግጥ
ሰጠንህ፡፡» ይላል፡፡ (አል
ሂጅር 87) «ከሚደጋገሙ
የኾኑን ሰባትን» የተባለው
ፋቲሓን ነው፡፡ በዚህ ስያሜ
የተሰየመችው የአንቀጾቿ
ብዛት ሰባት ስለሆነ ነው፡፡
102
• ሙስሊም ሁሉ ይህንን ምዕራፍ መማር አለበት፡
፡ ምክንያቱም፣ ብቻውን ወይም ኢማሙ ድምጹን
ከፍ አድርጎ በማያነብባቸው ሠላቶች ውስጥ
ተከታይ ሆኖ የሚሰግድ ሰው፣ በሠላቱ ውስጥ እሷን
ማነብነቡ ከሠላት ማዕዘናት መካከል አንዱ በመሆኑ
ነው፡፡
8 ፋቲሓን ካነበበ ወይም ኢማሙ ሲያነብ
እያዳመጠ ከቆየ በኋላ፣ ኣሚን ማለት ይወደድለታል፡፡
ትርጉሙም አምላካችን ሆይ ተቀበለን ማለት ነው፡፡
9 በመጀመሪያዎቹ ሁለት ረከዓዎች ላይ ከፋቲሓ
አስከትሎ ሌላ ምዕራፍን ወይም አንቀጾችን ያነባል፡፡
ሦስተኛና አራተኛ ረከዓ ላይ ግን ፋቲሓን ብቻ በማንበብ
ይገደባል፡፡
ፋቲሐን፣ የሠላት ውስጥ ውዳሴዎችንና
ሙገሳዎችን በቃሉ ያልያዘ ወይም ያልሸመደደ
ሰው ምን ማድረግ አለበት?
በቅርቡ የሰለመና ፋቲሐን፣ የሠላት ውስጥ
ውዳሴዎችንና ሙገሳዎችን በቃሉ ያልያዘ ወይም
ያልሸመደደ ሰው የሚከተለውን መፈፀም ይኖርበታል፡
• ግዴታ የሆኑ የሠላት ውስጥ ውዳሴዎችንና
ሙገሳዎችን በቃሉ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት
ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉት ውዳሴዎች
በዐረብኛ ቋንቋ መሆን አለባቸው፡፡
ፋቲሐና ተክቢር፤ ሱብሐነ ረቢየል ዐዚም፤
ሰሚዐላሁ ሊመን ሐመዲሁ፤ ረበና ወለከል
ሐምድ፤ ሱብሐነ ረቢየል አዕላ፤ ረቢግፊርሊ፤
ተሸሑድ፤ ሠላት ዐለ ነቢይ፤ አሰላሙዐለይኩም
ወራሕመቱላህ፡፡
• አንድ ሙስሊም እነኚህን ውዳሴዎችንና ሙገሳዎችን
በቃሉ እስከሚይዝ ወይም እስከሚሸመድድ ድረስ
በሠላት ውስጥ የሚችለውን ተስቢሕ (ሱብሓነላህ)፣
ተሕሚድ(አልሐምዱሊላህ) እና ተክቢር(አላሁ
አክበር) ደጋግሞ ማለት፣ ወይም በቃሉ የያዘውን
የቁርኣን አንቀፅ እየደጋገመ ማንበብ አለበት፡፡
ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏልና ነው፡
- ‹‹አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፡፡›› (አል
ተጋቡን 16)
• ይህ ሰው በዚህ ቆይታው ሠላቱን በተሟላ
መልኩ ለመካናወን ይረዳው ዘንድ በጀመዓ
መስገድን ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡
፡ ይህም ኢማሙ በተከታዩ ሰው በኩል የሚከሰቱ
ክፍተቶችን ስለሚያሟላ ነው፡፡
• በፈጅር፣ በመግሪብና በዒሻእ ሠላቶች ላይ፡
በመጀመሪያዎቹ ሁለት ረከዓዎች፣ ፋቲሓንም ከሱ
ቀጥሎ የሚነበበውንም ክፍል፣ ድምጽ ከፍ ተደርጎ
ይነበባል፡፡ በዙህርና በዐሥር ሠላት ላይ ግን
ድምጽ ከፍ አይደረግም፡፡ የተቀሩት በሠላት ውስጥ
የሚባሉ ውዳሴዎችና ሙገሳዎችም ሲነበቡ ድምፅ
ከፍ አይደረግም፡፡
• ሌሎች የሶላት ዚክሮች በልቦና ይባላሉ።
103
ይገየለፋፃቲልሓ፡ ትርጓሜ በሚከተለው መልኩ
‹‹ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው››፡
አላህን በባሕሪያቱ፤በተግባራቱ፣ በግልጽና ስውር
ፀጋዎቹ በሙሉ ከውዴታና ከማላቅ በመነጨ መልኩ
አመሰግነዋለሁ ማለት ነው፡፡
ጌታ(ረብ)፡ የሁሉ ፈጣሪ፤ ባለቤት፤ አስተናባሪና ባለ
ጸጋ የሆነ አካል ማለት ነው፡፡ ዓለማት፡ የሚባለው ደግሞ
ማንኛውም ከአላህ ባሻገር ያለ፣ የሰው፣ የጅን፣ የመላእክት፣
የእንሰሳትና የተቀሩት ፍጡራንን የሚገልጽ ቃል ነው፡፡
‹‹እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ፡›› እነኚህ ከአላህ
የተዋቡ ስሞች መካከል ሁለት ስሞቹ ናቸው፡፡ ‹‹ርኅሩኅ››
ማለት ሁሉን ነገር የሚያዳርስ የሆነ ርኅራኄ ባለቤት
ማለት ነው፡፡ ‹‹አዛኝ›› የሚለው ቃለል ደግሞ ምእመናን
ባሮቹን ብቻ የሚደርስ በሆነ የርኅራኄ ባህሪ የሚገለፅ
ማለት ነው፡፡
‹‹የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው››፡ የፍርዱና የግምገማው
ቀን ባለቤትና አስተናባሪ ማለት ነው፡፡ ይህ አንቀጽ
የመጨረሻውን ቀን ያስታውሳል፤ በመልካም ስራ ላይም
ያበረታታል፡፡
‹‹አንተን ብቻ እንገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን
እንለምናለን፤›› ጌታችን ሆይ! እኛ አምልኮን ላንተ ብቻ
እንሰጣለን፤ በየትኛውም የአምልኮ ዓይነት ካንተ ጋር ሌላን
አካል አናጋራም፤ በማንኛውም ጉዳያችን ላይ ካንተ ብቻ
እርዳታና እገዛን እንፈልጋለን፤ እያንዳንዱ ጉዳያችን በአንተ
እጅ ነው፤ ከርሱ የቅንጣት ታክልም ሌላ አካል ባለቤትነት
የለውም፡፡ ማለት ነው፡፡
‹‹ቀጥተኛውን መንገድ ምራን››፡ ቀጥተኛውን መንገድ
አመላክተን፤ አቅጣጨን፤ ግጠመን፤ ካንተ እስከምንገናኝ
ድረስ በርሱ ላይም አጽናን ማለት ነው፡፡ ቀጥተኛው
መንገድ ኢስላም ነው፡፡ እርሱም ግልጽ፣ ወደ አላህ
ውዴታና ወደ ጀነት የሚያደርስ ወይም የሚወስድ መንገድ
ነው፡፡ እርሱ ያ የነብያትና የመልዕክተኞች መደምደሚያ
የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የጠቆሙት መንገድ
ነው፡፡ በርሱ ላይ በመጽናት እንጂ ለሰው ልጅ ስኬትና
ደስታ ሊገኝ አይችልም፡፡
‹‹የነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን መንገድ››፡
የእነዚያን ቀጥተኛውን መመሪያ ያደልካቸውንና በሱም
ላይ ያጸናሃቸውን ሰዎች፣ ማለትም የነብያትንና የፃድቃንን
መንገድ ምራን ማለት ነው፡፡ እነሱ በርግጥ እውነትን
አውቀው የተከተሉ ናቸው፡፡
‹‹በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች
መንገድ››፡ አንተ ከተቆጣህባቸውና ከተናደድክባቸው
ሰዎች መንገድ አርቀን፤ ሰውረን፤ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም
እነርሱ ሐቅን አውቀው አልተገበሩትም፡፡ እነኚህ የሁዶችና
መሰሎቻቸው ናቸው፡፡ ከተሳሳቱት ሰዎችም መንገድ
ሰውረን፤ አርቀን፤ ማለት ደግሞ፣ ካለማወቃቸው የተነሳ
ወደ እውነት ያልተመሩ ሰዎችን፣ ክርስቲያኖችንና
መሰሎቻቸው የሚጠቁም ነው፡፡
104
10 ከዚያም፣ ልክ በመጀመሪያው ተክቢራ
ላይ እንዳደረገው እጆቹን በትከሻዎቹ
ትክክል ወይም ትንሽ ከፍ አድርጎ
በማንሳትና የመዳፎቹን ውስጣዊ ክፍልዳ
ቂብላ በማቅጣጨት ለሩኩዕ ‹‹አላሁ
አክበር›› ይላል፡፡
11 በመዳፎቹ ጉልበቶቹን በመያዝ ወደ ቂብላ
እንደተቅጣጨ ከወገቡ ጎንበስ በማለት ሩኩዕ ያደርጋል፤
ጭንቅላቱና ወገቡ ወጣ ገባ መሆን የለበትም፤ እንዲህም ይላል፡
- ‹‹ሱብሓነ ረቢየል ዐዚም›› (ታላቁ ጌታዬ ከእንከንና ከጉድለት
ጠራ፡፡) ይህን ውዳሴ ሦስት ጊዜ መደጋገም የተወደደ ነው፤ ግዴታው
ግን አንድ ጊዜ ብቻ ማለት ነው፡፡ ሩኩዕ አላህን የሚያልቁበትና
የሚያወድሱበት ዒባዳ ነው፡፡
‹‹ሱብሓነ ረቢየል ዐዚም›› - ‹‹ታላቁን አላህ ከእንከንና ከጉድለት አጠረዋለሁ፤
እቀድሰዋለሁ፤›› ማለት ሲሆን፣ አንድ ሰጋጅ ይህንን የሚለው ከወገቡ ጎንበስ
በማለት ለአላህ ያጎበደደና የተዋረደ ሆኖ ነው፡፡
12 ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ እጆቹን በትከሻዎቹ ትክክል ከፍ
በማድረግና የመዳፎቹን ውስጠኛ ክፍል ወደ ቂብላ በማቅጣጨት
ካጎነበሰበት ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ ኢማም ወይም ብቻውን የሚሰግድ
ከሆነ ደግሞ፣ ‹‹ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደሁ›› - (አላህ ያመሰገነውን
ሰው ሰማው) ይላል፡፡ ከዚያም ሁሉም ፡ ‹‹ሐምደን ከሲረን ጠይበን
ሙባረከን ፊሂ ሚልኣሰማኢ ወል አርዲ ወሚልአ ማሺእተ ሚን
ሸይኢን በዕድ›› - (በርካታ፣ መልካምና በውስጡ በረከት ያለው፣
በሰማያት ሙሉ፣ በምደር ሙሉ፣ ከነዚህም ሌላ አንተ በምትሻው
ነገሮች ሙሉ የሆነ ምስጋና ይድረስህ) ይላሉ፡፡
105
13 በማስከተል፣ በሰባት የሰውነት ክፍሎቹ መሬት ላይ በመደፋት
ሱጁድ ያደርጋል፡፡ እነኚህም የሰውነት ክፍሎች ግንባር ከአፍንጫ
ጋር፤ ሁለት መዳፎች፤ ሁለት ጉልበቶች እና ሁለት እግሮች
ናቸው፡፡ ሱጁድ ሲያደርግ እጆቹን ከጎኖቹ ማራራቅ፣
ሁዱንና ጭኖቹን አለማጣበቅና እንዲሁም ጭኖቹንና
ባቶቹን አለማገናኘት ይወደድለታል፡፡
14 በሱጁድ ውስጥ፡ ‹‹ሱብሐነ ረቢየል አዕላ››
- (ከፍ ያለው ጌታዬ ከእንከንና ከጉድለት ጠራ)
ይላል፡፡ ) ይህንን አንድ ጊዜ ማለት ግዴታ ሲሆን ሦስት ጊዜ
መደጋገም ደግሞ ተወዳጅ ተግባር ነው፡፡
ሱጁድ፣ አላህን ከመለመኛ ስፍራዎች ሁሉ በላጩ ነው፡፡ ሰጋጆች በሱጁድ ውስጥ መባል ያለባቸውን ውዳሴዎችን
ካሉ በኋላ የሚፈልጉትን የዱንያም ሆነ የኣኺራ ጉዳዮችን መለመን ይችላሉ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
- ‹‹አንድ ባሪያ ለጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆንበት ስፍራ ሱጁድ ነው፤ ስለሆነም በርሱ ውስጥ ዱዓን አብዙ፡፡››
(ሙስሊም 482)
‹‹ሱብሐነ ረቢየልአዕላ›› የሚለው ሐረግ ትርጓሜ፡- ‹‹የላቀው አላህ፣ በትልቅነቱና በችሎታው የተቀደሰና ከሰማያት
በላይ የላቀ ነው፤ ከማንኛውም ጉድለትና እንከንም የጠራ ነው›› ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ ቃል እራሱን ዝቅ
በማድረግና በመመሰጥ፣ በመሬት ላይ በመደፋት ሱጁድ ለሚያደርግ ሰው ሁሉ፣ በርሱና በጌታው መሐከል ያለን
የማይነፃፀር ልዩነት እንዲያስታውስ የሚያደርግ የሆነ ማሳሰቢያ ነው፡፡ በመሆኑም ለጌታው በተመስጦና በመተናነስ
ይሰግዳል፡፡
15 ከዚያም ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት ከመጀመሪያው ሱጁድ ቀና ብሎ
ይቀመጣል፡፡ አቀማመጡም ግራ እግሩን በማንጠፍና ቀኝ እግሩን በመቸከል ቢሆን
ተወዳጅ ነው፡፡ መዳፎቹን ከጉልበቱ ቀጥሎ ባለው የጭኑ ጠረፍ ወይም ጫፍ ላይ
ማድረግ ይኖርበታል፡፡
• ሰጋጆች በሠላት ውስጥ በሚቀመጡበት በየትኛውም ጊዜ ከላይ
በተጠቀሰው መልኩ መቀመጣቸው የተወደደ ነው፡፡ ግን ለመጨረሻው
ተሸሁድ በሚቀመጡበት ጊዜ በተጠቀሰው መልኩ ቀኝ እግርን
በመቸከል፣ ግራ እግርን በማሾለክ፣ በእግር ላይ ሳይሆን በመሬት ላይ
ተመቻችተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
• ጉልበቱ ህመም የሚሰማው ወይም ልምድ በማጣት ምክንያት
ለመጀመሪያው ተሸሁድ ወይም ለሁለተኛው ተሸሁድ በተነገረው
መሰረት መቀመጥ ያልቻለ ሰው ሳይጨናነቅ ለተጠቀሰው አቀማመጥ
የቀረበ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይችላል፡፡
16 በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሲቀመጥ፡ ‹‹ረቢ ኢግፊር ሊ፣ ወርሓምኒ፣
ወህዲኒ፣ ወርዙቅኒ፣ ወጅቡርኒ፣ ወዓፊኒ፣›› - (ጌታዬ ሆይ ምሕረትህን
ስጠኝ፤ እዘንልኝ፤ ምራኝ፤ ሲሳይህን ለግሰኝ፤ ጠግነኝ፤ ጤናማ አድርገኝ፡፡)
ማለት ይኖርበታል፡፡
17 ከዚያም ልክ በመጀመሪያው ሱጁድ መልኩ ለሁለተኛ ጊዜ ሱጁድ
ያደርጋል፡፡
106
18 በመቀጠልም ከሁለተኛው ሱጁድ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት ተነስቶ ይቆማል፤
19 ልክ እንዲሁ የመጀመሪያውን ረከዓ በሰገደው መልኩ ሁለተኛውንም ረከዓ ይሰግዳል ወይም ያስከትላል፡፡
20 ከዚያም በሁለተኛው ረከዓ፣ ከሁለተኛው ሱጁድ ቀና ካለ በኋላ ለመጀመሪያው
ተሸሁድ ይቀመጣል፡፡ ቁጭ ባለበት እንዲህ ይላል፡- ‹‹አትተሒይያቱ ሊልላሂ፣
ወሥሠለዋቱ፣ ወጥጠይባቱ፣ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀ ንነቢይዩ ወረሕመቱልላሂ
ወበረካቱሁ፣ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አሣሊሒነ አሽሐዱ አን ላ
ኢላሃ ኢልለ ላህ ወአሽሃዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡››
21 ከዚህ ቡሃላ እንደ ሰላቱ ዓይነት ባለ ሶስት ወይም አራት ረከዓ ሰላት
ከሆነ የቀረውን የሰላት ክፍል ለመሙላት ይቆማል፤ ነገር ግን በሶስተኛም
ሆነ በአራተኛ ረከዓዎች ላይ የሚነበነበው ፋቲሓ ብቻ መሆን አለበት፡፡
• የሚሰገደው የሰላት ዓይነት እንደ ፈጅር ሰላት ባለ ሁለት ረከዓ
ከሆነ ከዚህ በታች በተጠቀሰው መልኩ የመጨረሻውን ተሸሁድ
ይከውናል፡፡
22 ከዚህ በኋላ በመጨረሻው ረከዓ፣ ከሁለተኛው ሱጁድ በኋላ፣
ለማጠናቀቂያ ተሸሁድ ይቀመጣል፡፡ በመጀመሪያው ተሸሁድ የሚባለውን
በሙሉ ካለ በኋላ በሚከተለው መልኩ ለነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዱዓ ያደርጋል፡
‹‹አላሁምመ ሠሊ ዐላ ሙሐመድ ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ሠልለይተ
ዓላ ኢብራሂመ ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፤ ወባሪክ
ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ባረክተ ዓላ ኢብራሂም
ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡››
በማስከተልም፡ ‹‹አዑዙ ቢላሂ ሚን ዐዛቢ ጀሐነመ ወሚን ዐዛቢል
ቀብር ወሚን ፊትነቲል ማሕያ ወል መማት ወሚን ፊትነቲል መሲሒ
ደጅጃል፡፡›› በማለት ዱዓ ማድረግ ይወደድለታል፡፡ በተጨማሪም
የሚሻውን ነገር መለመን ይችላል፡፡