መጣጥፎች

አላህን በእጅጉ የሚፈሩና ታማኞች


ናቸው፡፡ ወደ ትክክለኛው ጎዳና የተመሩና የሚመሩ


ናቸው፡፡ አላህ(ሱ.ወ) እነርሱን የላከበትን ነገር በሙሉ


አድርሰዋል፡፡ ከርሱ ምንም የደበቁትም ሆነ የቀየሩት


ነገር የለም፡፡ ከራሳቸው ዘንድ አንዲትም ፊደል በውስጡ


አልጨመሩም አልቀነሱምም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡- «በመልዕክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ


እንጂ ሌላ የለባቸውም፡፡» (አል ነሕል 35)


በመልዕክተኞች ማመን ምንን ያካትታል?


መልዕክታቸው በትክክልና በቀጥታ ከአላህ


ዘንድ ነው የተላለፈው ብሎ ማመን፡፡


የመልዕክተኞች ሁሉ ጥሪ፣ አላህን ያለአጋር


በብቸኝነት ወደ ማምለክ ነው፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «በየ ሕዝቡም


ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ


በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል::»


(አል ነህል 36)


በርግጥ የየነብያቱ ደንብና ስርዓት ንዑስ በሆኑ


ጉዳዮች ላይ ሊለያይ ይችላል፡፡ ከነኚያ ከተላኩባቸው


ሕዝቦች አንጻር የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች


ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


«ከናንተ ለሁሉም ህሕግና መንገድን አደረግን፡፡» (አል


ማኢዳ 48)


በነብያትና በመልክተኞች በሙሉ


ማመን፡፡


አላህ በስማቸው የነገረንን ከነስማቸው


እናምንባቸዋለን፡፡ ለምሳሌ ሙሐመድ፣


ኢብራሒም፣ ሙሳ፣ ዒሳ፣ ኑሕ (ዐለይሂሙ


ሰላም) …. ከነሱ መካከል ስማቸውን


የማናውቃቸውን ደግሞ በጥቁሉ


እናምንባቸዋለን፡፡ ከነሱ መካከል አንዱን


የካደ ሁሉንም ክዷል፡፡


በቁርኣንና በሐዲስ የተጠቀሱ


የመልዕክተኞችን ገድልና ተዓምራት


እውነት ነው ብሎ መቀበል፡፡ ለምሳሌ


ለነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) ባሕሩ


የተሰነጠቀላቸው መሆኑን ማመን፡፡


ወደ እኛ የተላኩትን መልዕክተኛ ህግና


ስርዓት መተግበር፡፡ እሳቸውም ከሁሉም


በላጩና መቋጫ የሆኑት ሙሐመድ


(ሰ.ዐ.ወ) ናቸው፡፡


አላህ (ሱ.ወ) መልዕክቱን በማስተላለፉ ለይቷቸዋል፡፡


ከሌላው ሰው ነጥሎ እነርሱን መለኮታዊ ራዕዩን እንዲረከቡ መርጧቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እኔ


አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ ቢጢያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡» (አል ካሕፍ 110)


የነብይነት ማዕረግም ሆነ መለኮታዊ መልዕክት፣ በመንፈሳዊ ምጥቀት ወይም በጮሌነት ወይም በአዕምሮ ብስለት


የሚያገኝ ነገር አይደለም፡፡


እሱ የአላህ መምረጥና ማጨት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከሰዎች መካከል መልዕክተኞችን መርጦ አጭቷቸዋል፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «አላህ መልክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ዐዋቂ ነው፡፡» (አል አንዓም 124)


የመልዕክተኞች መገለጫ


መልዕክተኞች የሰው ዘር ናቸው፡፡


በነሱና በሌላው ሰው መሐከል ያለው ልዩነት፣ አላህ (ሱ.ወ) በመለኮታዊ ራዕይና መልዕክት የመረጣቸው መሆኑ


ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከአንተም በፊት ወደ እነሱ የምናወርድላቸው የኾኑ ሰዎችን እንጂ ሌላን


አልላክንም፡፡» (አል አንቢያእ 7)


የጌትነትም ሆነ የአምላክነት ደረጃ የላቸውም፡፡


ነገር ግን በውጫዊ ተክለ ሰውነታቸው ምንም እንከን የሌላቸው፣ የሙሉዕነትን ደረጃ የደረሱ ሲሆን በስ-


ነምግባራቸውም በሙሉዕነት የመጨረሻውን ጣራ የነኩ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በጎሳቸውም የተከበረ ጎሳ አባል


ናቸው፡፡ እንዲሁም ብሩህ አዕምሮና ማራኪ ልሳን የተቸሩ ናቸው፡፡ ይህም የመልዕክቱን ውጣ ውረድ በአግባቡ


እንዲሸከሙ አድርጓቸዋል፡፡ የነብይነትን ፈተናም በብቃት እንዲወጡ አግዟቸዋል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) መልዕክተኞችን ከሰው ዘር ያደረገበት ምክንያቱ የሰዎች ተምሳሌቶች ከራሳቸው እንዲሆን ነው፡፡


በመሆኑም መልዕክተኞችን መከተልና እነርሱን በተምሳሌትነት መያዝ በሰዎች ሊከናወን የሚችልና በችሎታቸው


ስር ያለ ጉዳይ ነው፡፡


እነርሱ ከአላህ በሚያስተላልፉት መልዕክት ከስህተትና ከመርሳት የተጠበቁ ናቸው፡፡ ከአላህ በሚያስተላልፉት


መልዕክት አይሳሳቱም፡፡ አላህ ወደ እርነሱ የላከውንም በማስፈፀም አይሳሳቱም፡፡


እውነተኝነት፡


መልዕክተኞች በንግግራቸውም በተግባራቸውም እውነተኞች ናቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ይህ አዛኙ


ጌታ የቀጠረን፣ መልዕክተኛቹም እውነትን የነገሩን ነው፡፡» (ያሲን 52)


ትዕግስት፡


መል°ክተኞች ወደ አላህ ሃይማኖት አብሳሪና አስጠንቃቂ በመሆን በርግጥ ተጣርተዋል፡፡ በዚህም የተለያዩ ስቃዮችና


መከራዎች ደርሰውባቸዋል፡፡ ሁሉንም የሚደርስባቸውን መከራና ስቃይ የአላህን ቃል የበላይ በማድረግ ጉዞ ላይ


በትዕግስት ተሸክመው አልፈዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከመልዕክተኞችም የቆራጥነት ባለቤት የነበሩት


እንደታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡» (አል አሕቃፍ 35)


የመልዕክተኞች ምልክቶችና ታዓምራታቸው


አላህ (ሱ.ወ) መልዕክተኞቹን በማስረጃና ተያያዥነት ባላቸው የተለያዩ ነገሮች እውነተኝነታቸውንና ነብይነታቸውን በማረጋገጥ


ረድቷቸዋል፡፡ ከዚህም መካከል በሰው ልጅ ችሎታ የማይከሰቱ በሆኑ ታዓምራትና ግልጽ በሆኑ ምልክቶች ያደረገላቸው እገዛ


ወይም ድጋፍ አንዱ ነው፡፡ ይህም የሆነው እውነተኝነታቸውን ለማጽደቅና ነብይነታቸውን ለማጽናት ነው፡፡


ታዓምራት የሚባለው ተለምዶን ጥሰው የሚከሰቱ ነገሮችን ነው፡፡ ይኸውም አላህ (ሱ.ወ) በነብያቱና በመል°ክተኞቹ


አማካይነት ይፋ የሚያደርገው ሲሆን ሰዎች መሰሉን ሊያመጡ ወይም ሊያስከስቱ የማይችሉት እንደሆነ በመፎካከር መልክ


የሚከሰት ነው፡፡


ከነብያት ተዓምራት መካከል፡


• የነብዩላህ ሙሳ(ዐ.ሰ) በትር ወደ እባብነት መቀየር፡


• ነብዩላህ ዒሳ(ዐ.ሰ) ሕዝቦቻቸው በቤቶቻቸው ውስጥ ስለሚመገቡትና ስለሚያከማቹት ምግብ መናገራቸው፡


• ለነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጨረቃ መሰንጠቅ:


በዒሳ(ዐ.ሰ) ዙሪያ ያለው የሙስሊም እምነት


እርሱ ዒሳ(ዐ.ሰ) ከታላላቅ መልዕክተኞች አንዱና ስብዕናው እጅግ የላቀ ነው፡፡ እነኚህ ከመልዕክተኞች መካከል ስብዕናቸው እጅግ


የላቀ ነቢያት የቆራጥነት ባለተቤት በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነርሱም ሙሐመድ’ ኢብራሒም’ ኑሕ’ ሙሳና ዒሳ ናቸው (አለይሂሙ ሰላም)፡


፡ አላህ (ሱ.ወ) በሚከተለው ቃሉ ዘክሯቸዋል፡- «ከነብዮችም የጠበቀ ቃልኪዳናቸውን በያዝን ጊዜ (አስታውስ)፤ ከአንተም፣ ከኑሕም፣


ከኢብራሂምም፣ ከሙሳም፣ ከመርየም ልጅ ዒሳም(በያዝን ጊዜ አስታውስ)» (አል አሕዛብ 7) ይላል፡፡


ነብዩላህ ዒሳ(ዐ.ሰ) የኣደም ዝርያ ሰው ነው፡፡


አላህ (ሱ.ወ) ወደ ነገደ ኢስራኢል የላከው ሲሆን የተለያዩ ተዓምራት በርሱ እጅ እንዲፈፀሙ አድርጓል፡፡ ምንም ዓይነት


የጌትነትም ሆነ የአምላክነት ደረጃ የለውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለኢስራኢልም ልጆች ታምር


ያደረግነው የሆነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ » (አል ዙኽሩፍ 59)


ነብዩላህ ዒሳ(ዐ.ሰ) ሕዝቦቹን፣ እሱንም ሆነ እናቱን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው እንዲይዟቸው ፈፅሞ አላዘዘም፡፡ ለነርሱ


ያላቸው አላህ ያዘዘውን ብቻ ነበር፡፡ «ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ» (አል ማኢዳ 117)


እሱ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡


እናቱ መርየም፣ ፃድቅ፣ እውነተኛ፣ ለጌታዋ ፍፁም ታዛዥና ተገዢ፣ ጥብቅ፣ ጨዋና ድንግል ሴት ነች፡፡ ዒሳን(ዐ.ሰ)


የፀነሰችው ያለአባት በአላህ (ሱ.ወ) ችሎታ ነው፡፡ የእርሱ አፈጣጠር ዘልዓለማዊ ተዓምር ነው፡፡ ልክ ኣደምን ያለአባት እና ያለእናት


እንደፈጠረው ሁሉ እርሱንም ያለ አባት ፈጠረው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ


ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው ከዚያም ለርሱ (ሰው) ሁን አለው ሆነም፡፡» (አል ዒምራን 59)


በርሱ በዒሳ(ዐ.ሰ) እና በነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መሐከል የተላከ መልዕክተኛ የለም፡፡ ስለ ነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)


ትንቢት ተናግሮ አብስሯል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «የመርየም ልጅ ዒሳም፡ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ከበፊቴ ያለውን


ተውራትን የማረጋግጥና ከኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ (የተላክሁ) የአላህ


መልክተኛ ነኝ ባለ ጊዜ (አስታውስ) በግልጽ ታዕምራት በመጣቸውም ጊዜ ይህ ግልጽ ድግምት ነው አሉ፡፡» (አሥ ሠፍ 6)


አላህ (ሱ.ወ) በእርሱ እጅ እንዲፈፀሙ ባደረጋቸው ታዓምራት እናምናለን፡፡ ለምፃምን ማዳኑን፣ አይነ ስዉራን ማብራቱን፣


ሙታንን ማስነሳቱን፣ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ ስለሚበሉትና ስለሚያከማቹት መናገሩን እናምናለን፡፡ ሁሉም በአላህ ፍቃድ


የተፈፀሙ ናቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ይህንን ለነብይነቱና ለመልዕክተኝነቱ ትክክል ለመሆኑ ግልጽ የሆነ ማስረጃ አድርጎታል፡፡


ዒሳ(ዐ.ሰ) የአላህ ባሪያና መልክተኛ ነው ብሎ እስከሚያምን ድረስ የአንድም ሰው ኢማን የተሟላ ሊሆን አይችልም፡፡


አይሁዶች እርሱን ከገለጹበት የቅጥፈትና ፀያፍ ነገሮች ሁሉ የጸዳና የጠራ እንደሆነም እናምናለን፡፡


በዒሳ እውነተኛ ማንነት ዙሪያ የተሳሳቱትን የክርስቲያኖች አመለካከትም እናወግዛለን፡፡ ይኸውም እሱና እናቱን ከአላህ ሌላ


አማልክት ማድረጋቸው ነው፡፡ ከፊላቸው እርሱ የአላህ ልጅ ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ከስላሴዎች አንዱ ነው ብለዋል፡፡ አላህ


እነርሱ ከሚሉት ሁሉ የላቀ ነው፡፡


አላህ (ሱ.ወ) አይሁዶች ዒሳን(ዐ.ሰ) ሊገድሉት በፈለጉ ጊዜ ወደ ሰማይ ከፍ አደረገውና አሳረገው እንጂ እሱ አልተገደለም


አልተሰቀለምም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የእርሱ ምስል በሌላ ሰው ላይ እንዲሆን አደረገ እናም ያንን ሰው ዒሳ መስሏቸው ገደሉት ሰቀሉትም፡


፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸውም (ረገምናቸው)


አልገደሉትም አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት ከርሱ (መገደል) በመጠራጠር


ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ ይልቁንስ አላህ


ወደርሱ አነሳው አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በርሱ (በዒሳ) በእርግጥ የሚያምን እንጅ (አንድም)


የለም በትንሳኤም ቀን በነሱ ላይ መስካሪ ይኾናል፡፡ » (አል ኒሳእ 157-159)


አላህ (ሱ.ወ) እርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ እንዲያርግ በማድረግ ጥበቃ አድርጎለታል፡፡ በመጨረሻው ዘመን ወደ ምድር


ይወርዳል፡፡ በነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ሕግና ስርዓት ይዳኛል፡፡ ከዚያም በዚ‹ ምድር ይሞታል፤ በሷም ውስጥ ይቀበራል፡


፡ ሌሎች ሰዎች እንደሚቀሰቀሱት የትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ


በርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን ከርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡» (ጧሃ 55)


በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይነትና


መልዕክተኝነት ማመን


• ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአላህ ባሪያና መልዕክተኛ


መሆናቸውን እናምናለን፡፡ እርሳቸው የመጀመሪያዎችም


የኋለኞችም አለቃና የነብያት መቋጫ ናቸው፡፡


ከርሳቸው ብኋላ የሚነሳ ነብይ የለም፡፡ መልዕክታቸውን


አድርሰዋል፡፡ አደራቸውን ተወጥተዋል፡፡ ሕዝባቸውን


መክረዋል፡፡ በአላህ መንገድ መታገል የሚገባቸውን


ያክል ታግለዋል፡፡


• እርሳቸው የተናገሩትን በሙሉ እንቀበላለን፡፡ ያዘዙትን


እንተገብራለን፡፡ ከከለከሉትና ካስጠነቀቁት ነገር እንርቃለን፡


፡ እርሳቸው በዘረጉልን መስመር መሰረት አላህን እንገዛለን፡፡


ከርሳቸው ባሻገር ማንንም በአርዓያነት አንከተልም፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ለናንተ አላህንና የመጨረሻውን


ቀን የሚከጅል ለኾነ ሰው አላህንም በብዙ ለሚያወሳ


በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ፡፡» (አል


አሕዛብ 21)


• ለወላጅ፣ ለልጅ፣ በአጠቃላይ ለሰዎች ካለን ውዴታ


የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ውዴታ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል፡


፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «አንዳችሁም እኔ


እርሱ ዘንድ ከወላጆቹ፣ ከልጆቹና ከሰዎች በሙሉ የበለጠ


ተወዳጅ እስካልሆንኩ ድረስ አያምንም፡፡» (አል ቡኻሪ


15/ ሙስሊም 44) እርሳቸውን በትክክል መውደድ


ማለት ፈለጋቸውን መከተል፣ መመሪያቸውን መንገድ


ማድረግ ነው፡፡ ትክክለኛ ደስታም ሆነ ሙሉዕ መመራት


ሊረጋገጥ የሚችለው እርሳቸውን በመታዘዝ ብቻ ነው፡


፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ብትታዘዙትም


ትመራላችሁ፤ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ


ሌላ የለበትም፡፡» (አል ኑር 54)


• ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተላለፉትን በሙሉ መቀበል


አለብን፡፡ ለፈለጋቸውም ታዛዦች መሆን


ይኖርብናል፡፡ የእርሳቸውን መመሪያ ትልቅ ስፍራና


ክብር ልንቸረው ያስፈልጋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡- «በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው


በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ፣ ከዚያም


ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን


እስከማያገኙና ፍፁም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ


ድረስ አያምኑም፡፡» (አል ኒሳእ 65)


• የእርሳቸውን ትዕዛዝ ከመጻረርና ከመቃረን ልንጠቀቅ


ይገባል፡፡ ምክንያቱም የርሳቸውን ትዕዛዝ መቃረን ለፈተና፣


ለጥመትና ለአሳማሚ ቅጣት ይዳርጋል፡፡ አላህ(ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- «እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ


እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው


ይጠንቀቁ» (አል ኑር 63)


የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት ልዩ ይዘት


የነብዩ ሙሐመድ መልክት ከቀደምት መልዕክቶች


ለየት የሚያደርጉት በርካታ ይዘቶች አሉት፡፡ ከነዚህም


መካከል፡-


• የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት የቀደምት


መልዕክቶችን መልዕክት የሚቋጭ መሆኑ፡፡ አላህ (ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- «ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም


ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብዮች


መደምደሚያ ነው፡፡» (አል አሕዛብ 40)


• የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት ቀደምት


መልዕክቶችን የተካ መሆኑ፡፡ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)


ከተላኩ ብኋላ አላህ (ሱ.ወ) እርሳቸውን ከመከተል


ውጭ ምንም ዓይነት ሃይማኖትን አይቀበልም፡


፡ በርሳቸው ጎዳና እንጂ አንድም ሰው ወደ ጀነት


ጸጋ መድረስ አይችልም፡፡ እርሳቸው ከመልዕክተኞች


ሁሉ የተከበሩ ናቸው፡፡ ሕዝባቸውም ከሕዝቦች ሁሉ


ምርጥና በላጭ ሕዝብ ነው፡፡ ሕግጋታቸውም ከሕግጋት


ሁሉ የተሻለና የተሟላ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡- «ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው


ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም እርሱም በመጨረሻይቱ


ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡» (አል ዒምራን 85)


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ «የሙሐመድ ነፍስ በእጁ


በሆነችው ጌታ እምላለሁ፡ ከዚህ ሕዝብ ውስጥ የሁድም ሆነ


ክርስቲያን አንድም ሰው ስለኔ ሰምቶ በተላኩበት የማያምን


አይኖርም ከእሳት ጓዶች ቢሆን እንጂ» (ሙስሊም 153 /


አህመድ 8609)


• የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መልክት ሁለቱንም


ፍጡሮች ማለትም አጋንንትንም ሰውንም የሚመለከት


መሆኑ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ጅኖች ያሉትን ሲያወሳ እንዲህ


ብሏል፡- «ወገኖቻችን ሆይ የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡»


(አል አሕቃፍ 31) « አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ


አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢኾን እንጂ አልላክንህም ፡


፡» (ሰበእ 28)


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ «በስድስት ነገሮች


ከነብያት ተልቄያለሁ፡ ጥቅላዊ የንግገር ስልትን


ተሰጥቻለሁ፤ ጠላትን በማስፈራት ታግዣለሁ፣


ምርኮ ተፈቅዶልኛል፣ ምድር ንፁሕና የጸሎት ስፍራ


ተደርጋልኛለች፣ ወደ ፍጡራን በመሉ ተልኬያለሁ፣


ነብያት በእኔ ተደምድመዋል፡፡» (አል ቡኻሪ 2815 /


ሙስሊም 523)


> የአቅሷ መስጂድ ሙስሊሞች ልብ ውስጥ ልዩ ስፍራ አለው፡፡ በምድር ላይ ከሐረም መስጂድ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የተሰራ


መስጂድ ነው፡፡ ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) እና የተቀሩት ነብያትም በውስጡ ሰግደዋል፡፡


በመልዕክተኞች የማመን ጥቅም ወይም ፍሬ


በመልዕክተኞች ማመን ከባድ ጥቅም አለው ከነዚህም መካከል


አላህ(ሱ.ወ0 ለባሮቹ ያለውን ርህራሄና እንክብካቤ ማወቅ፡


ይኸውም መልዕክተኞቹን ወደ ነርሱ በመላክ ወደ ቀጥተኛው ጎዳና እንዲመሯቸውና በምን መልኩ


አላህን ማምለክ እንዳለባቸው እንዲያብራሩላቸው በማድረጉ ነው፡፡ የሰው ልጅ አዕምሮ ይህን


የማወቅ ችሎታ የለውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ስለ ነብያችን ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፡-


«(ሙሐመድ ሆይ) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም፡፡» (አል አንቢያእ 117)


በዚህ ታላቅ ጸጋው ላይ አላህን ማመስገን


መልዕክተኞችን መውደድ፣ ማላቅና ለነሱ በሚገባ መልኩ እነሱን ማድነቅና ማሞገስ፡፡ ምክንያቱም እነሱ


አላህን በመገዛት፣ መልዕክቱን በማድረስና ለባሮቹ መልካምን በማስተማር ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋልና


ነው፡፡


መልዕክተኞች ከአላህ ዘንድ የተላኩበትንና ይዘው የመጡትን መልዕክት መከተል፡


እሱም አላህን በብቸኝነት ማምለክና ለርሱ ተጋሪ አለማድረግ ነው፡፡ እርሱንም በተግባር መተርጎም


ነው፡፡ በዚህም ምእመናን በሁለቱም ዓለም መመራትን ስኬትንና መልካሙን ሁሉ ያገኛሉ፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም


አይቸገረምም፡፡ ከግሳጼዬም የዞረ ሰው ለርሱ ጠባብ ኑሮ አልለው፡፡» (ጧሃ 123-124)


ቁርኣን በመጨረሻው ቀን በማመን ላይ ትኩረት


ያደረገው ለምንድን ነው?


ቁርኣን በመጨረሻው ቀን በማመን ላይ ለየት ያለ


ትኩረት ሰጥቷል፡፡ በየአጋጣሚው ሁሉ ስለሱ አሳስቧል፡


፡ በተለያየ የዐረበኛ አገላለጾች የርሱን ተከሳችነት አጽንኦት


ሰጥቶታል፡፡ በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመጨረሻው


ቀን ማመንን በአላህ ከማመን ጋር አስተሳስሮታል፡፡


ምክንያቱም በአላህና በፍትሃዊነቱ ማመን በመጨረሻው


ቀን ማመንን ያስገድዳል፡፡ የዚህ ማብራሪያም


እንደሚከተለው ይሆናል፡-


አላህ (ሱ.ወ) በደልን አይቀበልም፡፡ በዳይን ሳይቀጣ፣


ተበዳይንም ሳይክስ አይተውም፡፡ መልካም ሰሪን


ሳይመነዳና ሳይከፍለው አይቀርም፡፡ ሁሉንም ባለ መብት


የሚገባውን መብት ይሰጠዋል፡፡ በዚች ዓለም ላይ በዳይ


ሆኖ የሚኖር፣ በዳይ ሆኖ የሚሞት፣ ነገር ግን ምንም


የማይቀጣ ሰው እንመለከታለን፡፡ በተቃራኒው ተበዳይ


ሆኖ የሚኖር ተበዳይ ሆኖ የሚሞት ግን አንድም መብቱ


የማይመለስለት ሰው እናያለን፡፡ ታዲያ አላህ በደልን


አይቀበልም የሚለው ትርጓሜ ምንድነው? ትርጓሜው


ከዚህ ሕይወት ሌላ እኛ ዳግም የምንኖርበት ሌላ


ሕይወት አለ ማለት ነው፡፡ የግድ ሌላ የምላሽ ሕይወት


ይኖራል፡፡ መልካም ሰሪ የሚመነዳበት፣ መጥፎ የሰራም


የሚቀጣበት፣ ሁሉም ባለ መብት የሚገባውን መብት


የሚያገኝበት ዓለም ይኖራል፡፡


> በመጨረሻው ቀን ማመን


በመጨረሻው ቀን የማመን ትርጓሜ


አላህ (ሱ.ወ) ሰዎችን ከቀብር ይቀሰቅሳል ከዚያም በስራዎቻቸው ይተሳሰባቸዋል በዚያም ይመነዳቸዋል፤ በዚህም


የጀነት ነዋሪዎች በማረፊያቸው ይረጋሉ፤ የእሳት ነዋሪዎችም በማረፊያቸው ይረጋሉ፤


ብሎ በቁርጠኝነት ማመን ነው፡፡


በመጨረሻው ቀን ማመን ከኢማን ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው፡፡ በርሱ ሳያምኑ ኢማን ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ግን መልካም ስራ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው ነው»» (አል በቀራ 177)


> ኢስላም ግማሽ የቴምር


ፍሬን በመለገስ


እንኳን ቢሆን ለሌሎች


መልካም በመዋል


ከእሳት እንድንርቅ


ያዘናል፡፡


በመጨረሻው ቀን ማመን ምንን ያካትታል?


አንድ ሙስሊም በመጨረሻው ቀን ማመኑ በርካታ


ጉዳዮችን በውስጡ ያካትታል፡፡ ከነዚህ ጉዳዮች


መካከል፡-


በመቀስቀስና በመሰብሰብ ማመን፡- ሙታን


ከመቃብራቸው ወጥተው ሕያው እንዲሆኑ ይደረጋሉ


፡፡ ሩሐቸውም ወደየገላዎቻቸው ይመለሳሉ፡፡


ሰዎች የዓለማት ጌታ ፊት ይቆማሉ፡፡ ከዚያም ጫማ


ሳይጫሙ እርቃናቸውን ልክ መጀመሪያ ሲፈጠሩ


እንደነበሩት ሆነው በአንድ ስፍራ ይሰበሰባሉ፡፡


በመቀስቀስ ማመን በቁርኣንና በሐዲስ የተነገረ ጉዳይ


ነው፡፡ ጤናማ አዕምሮና የተፈጥሮ ባህሪም ያጸደቁት


ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጠኝነት አላህ (ሱ.ወ) በቀብሮች


ውስጥ ያለን እንደሚቀሰቅስ፣ ነፍሶች ወደየገላዎቻቸው


እንደሚመለሱ፣ ሰዎች በጠቅላላ የዓለማት ጌታ ፊት


እንደሚቆሙ እናምናለን፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከዚያም እናንተ ከዚህ


በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ፡፡ ከዚያም እናንተ በትንሳኤ


ቀን ትቀሰቀሳላችሁ፡፡» (አልሙዕሚኑን 15-16)


መለኮታዊ መጽሐፍት በሙሉ በዚህ ጉዳይ ላይ


ይስማማሉ፡፡ የአላህ (ሱ.ወ) ጥበበኝነት በውስጡ ያዘለውም


ይህንኑ ነው፡፡ ይኸውም አላህ (ሱ.ወ) በተጣለባቸው


በእያንዳንዱ ኃላፍነት ፍጡራን የሚመነዱበት የሆነ


መመለሻ ዓለም እንዳዘጋጀ በመልክተኞቹ ልሳን መናገሩ


ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «የፈጠርናችሁ ለከንቱ


መኾኑን፣ እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን


ጠረጠራችሁን? (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)»


(አል ሙዕሚኑን 115)


መቀስቀስን የሚያረጋግጡ የቁርኣን ማስረጃዎች


• የሰው ልጅን ያለ አንዳች ቀዳሚ ምሳሌ የፈጠረው አላህ


ነው፡፡ ያለ አንዳች ቀዳሚ ምሳሌ የፈጠረ ደግሞ መልሶ


ማስገኘት፣ ወደነበረበት መመለስ አይሳነውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- «እርሱም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም


የሚመልሰው ነው፡፡» (አል ሩም 27)


አላህ (ሱ.ወ) አጥንቶች ከበሰበሱ በኋላ እንደነበሩ


መመለሳቸውን ለሚያስተባብል ሰው ምላሽ እንዲሰጥበት


ሲያዝ እንዲህ ብሏል፡- « ያ በመጀመሪያ ጊዜ ያስገኛት


ሕያው ያደርጋታል፤ እርሱም በፍጡሩ ሁሉ(ኹኔታ) ዐዋቂ


ነው በለው፡፡» (ያሲን 79)


• ምድር ምንም ዓይነት ዛፍም ሆነ አረንጓዴ ተክል


የማይታይባት ኾና ከደረቀችና ከሞተች በኋላ፣ አላህ


(ሱ.ወ) ዝናብ ያወርድባታል፡፡ እንደ አዲስ በአረንጓዴ


ትሸፈናለች፡፡ ከእያይነቱ ቡቃያን ታበቅላላች፡፡ እናም


ምድርን በዚህ መልኩ ሕያው ማድረግ የቻለ ጌታ


ሙታንንም ሕያው ማድረግ ይችላል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡- «ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን፤ በርሱም


አትክልቶችንና የሚታጨድን (አዝመራ) ፍሬ አበቀልን፡


፡ ዘምባባንም ረዣዥም ለርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት


ስትሆን (አበቀልን) ለባሮቹ ሲሳይ ትኾን ዘንድ (አዘጋጀናት)


በርሱም የሞተችን አገር ሕያው አደረግንበት (ከመቃብር)


መውጣትም እንደዚሁ ነው፡፡» (ቃፍ 9-11)


• ማንኛውም ማገናዘብ የሚችል ሰው የሚረዳው ነገር


ቢኖር አንድ ትልቅና ከባድን ነገር መከወን የቻለ ከሱ


በታች የሆነን ነገር በሚገባ መከወን እንደሚችል ጥርጥር


የሌለው መሆኑን ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እጅግ በጣም


ግዙፍ፣ ሰፋፊ፣ ውስብስብና ድንቅ ፍጥረቶች ከመሆናቸው


ጋር ሰማያትን፣ ምድርንና ከዋክብትን ያለ አንዳች ቀዳሚ


ናሙና ፈጥሯቸዋል፡፡ በመሆኑም የበሰበሱ አጥንቶችን


ሕያው በማድረግ ቻይ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ


ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? ነው እንጅ


እርሱም በብዙ ፈጣሪና ዐዋቂው ነው፡፡» (ያሲን 81)


በምርመራና በሚዛን ማመን፡ አላህ (ሱ.ወ)


ፍጡራኑን በዱንያ ሕይወት ሲሰሩት በነበረው


ስራቸው ይመረምራቸዋል፤ ይተሳሰባቸዋል፡፡


የአሃዳዊነት፣ የተውሂድ አራማጆች የሆኑ፣ አላህንና


መልክተኛውን የሚታዘዙ፣ ምርመራቸው እጅግ


በጣም ገር ነው፡፡ ከአጋሪያን የሆነ አመጸኛ ደግሞ


ምርመራው እጅግ በጣም ብርቱ ነው፡፡


ስራዎች ትልቅና ከባድ በሆነ ሚዛን ይመዘናሉ፡


፡ መልካም ስራዎች በአንድ ጎን፣ ክፉ ስራዎች ደግሞ


በሌላኛው ጎን ይደረጋሉ፡፡ የመልካም ስራው ክብደት


ከመጥፎው ስራው የበለጠና ሚዛን የደፋለት ከጀነት


ሰዎች ይሆናል፡፡ የመጥፎ ስራው ክብደት ከመልካም


ስራው የበለጠና ሚዛን የደፋበት ደግሞ ከእሳት ሰዎች


ይሆናል፡፡ ጌታህ ማንንም አይበድልም፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «በትንሳኤም ቀን


ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን ማንኛይቱም ነፍስ


ምንንም አትበደልም፡፡ (ስራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል


ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን ተቆጣጣሪዎችም በኛ


በቃ፡፡» (አል አንቢያእ 47)


ጀነትና እሳት፡ ጀነት የዘልዓለማዊ ጸጋዎች ዓለም


ናት፡፡ ጀነት አላህ (ሱ.ወ) እርሱን ለሚፈሩ፣ እሱና


መልክተኛውን ለሚታዘዙ ምዕመናን ያዘጋጃት


ናት፡፡ በውስጧ ነፍሶች የሚፈልጉት ዘውታሪ የሆኑ


የጸጋ ዓይነቶች በሙሉ አሉ፡፡ በሷ ውስጥ የሚወደዱ


ነገሮች ሁሉ የዓይን መርጊያዎች ሲሆኑ ይገኛሉ፡፡


አላህ (ሱ.ወ) የጎን ስፋቷ ብቻ የሰማያትና የምድርን


ያክል የሆነችውን ጀነት ለመግባት በታዛዥነት ላይ


ባሮቹ እንዲሸቀዳደሙ ሲያነሳሳና ሲያበረታታ እንዲህ


ብሏል፡- «ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ


እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ


የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡» (አለ ዒምራን 133)


እሳት ደግሞ ዘልዓለማዊ መቀጫ ዓለም ናት፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) ለካሃዲያን፤ ለነዚያ በአላህ ለካዱና መልክተኞች


ላይ ላመጹት መቀጫ ትሆን ዘንድ ያዘጋጃት ናት፡፡


በውስጧ በአዕምሮ ውልብ ብሎ የማያውቅ፣ እጅግ በጣም


አሳማሚ ቅጣት፣ ስቃይ፣ ሰቆቃና መከራ አለ፡፡


አላህ (ሱ.ወ) ባሮቹን ከዚች ለከሃዲያን መቀጫ


ካዘጋጃት እሳት በማስጠንቀቅ መልክ ሲናገር እንዲህ


ብሏል፡- «ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጊያዎች


የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፡ ለከሃዲዎች ተደግሳለች፡፡ »


(አል በቀራ 24)


አምላካችን ሆይ ጀነትንና ከንግግርም


ከስራም ወደርሷ የሚያቃርበውን እንድትለግሰን


እንጠይቅሃለን፡፡ ከእሳትና ወደርሷ ከሚያቃርብ


ንግግርና ስራም ባንተ እንጠበቃለን፡፡


4. የቀብር ስቃይና ድሎቱ፡ ሞት እውነት መሆኑን


እናምናለን፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


«በናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል


ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ፡፡» (አል


ሰጅዳ 11)


ይህ በተጨባጭ የሚመለከቱት፣ ጥርጥር


የሌለው እውነታ ነው፡፡ የሞተ ወይም የተገደለ ብቻ


በማንኛውም ሁኔታ ሕይወቱ ያለፈ ሰው፣ ይህ ቀነ


ገደቡ እንደሆነና የሞተበት ሁኔታ ከዕድሜው ላይ


ምንም እንደማያጎድል እናምናለን፡፡ አላህ (ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- «ለሕዝብም ሁሉ የተሰነ ጊዜ አላቸው፡


፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም


(ከጊዚያቱም) አይቀድሙም፡፡» (አል አዕራፍ 34)


• አንድ የሞተ ሰው ቂያማው ቆማበታለች፡፡ ወደ


ወዲያኛው ዓለምም ተሸጋግሯል፡፡


• ለከሃዲያንና ለአማጽያን በቀብር ውስጥ ቅጣት


እንደተዘጋጀ፣ ለምእመናንና ለጻድቅ ባሮች ደግሞ


የድሎት ጸጋዎች እንደተደገሱ የሚያረጋግጡ በርካታ


ሐዲሶች ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተዘግበዋል፡፡ በመሆኑም


በዚህ ጉዳይ እናምናለን፡፡ እንዴት እንደሆነ ለማወቅ


አንፈላፈልም፡፡ ምክንያቱም ይህ የስውሩ ዓለም


ክስተትና አዕምሮ ተጨባጭ ሁኔቴውንና በምን


ዓይነት እንደሚከሰት ሊደርስበት ስለማይችል ነው፡፡


ልክ እንደ ጀነትና እሳት የስዉሩ ዓለም ክስተት እንጂ


የይፋዊ ዓለም ክስተት አይደለም፡፡ አዕምሮ ሊቀይስ፣


ሊመረምርና ሊወስን የሚችለው በነባራዊው ዓለም


ተመሳሳይ ያለውንና የርሱን ስርዓት የሚከተልን ነገር


ብቻ ነው፡፡


• የቀብር ሕይወት በስሜት ሕዋሳት የሚደረስበት


አይደለም፡፡ ስውር ወይም ገይብ ሕይወት ነው፡፡ በሕዋስ


የሚደረስበት ቢሆን ኖሮ በስውር ወይም ከሕዋስ በራቀ


ነገር ማመንን ጥቅም አልባ ያደርገው ነበር፡፡ ኃላፊነት


የተጣለበትንም ሚስጥር ፉርሽ ያደርጋል፡፡ ሰዎችም


ባልተቀበሩ ነበር፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-


«አትቀባበሩም ማለትን ባልሰጋ ኖሮ አላህን እኔ የምሰማወን


የቀብር ቅጣት እንዲያሰማችሁ እለምነው ነበር፡፡»


(ሙሰሊም 2868 /አል ነሳኢ 2958)


ከላይ የጠቀስነው ምክንያቶች በእንሳሳት ላይ ሰለሌሉ


እነሱ ይህን እንዲሰሙ ተደርገዋል፡፡


በመጨረሻው ቀን የማመን ጥቅም ወይም ፍሬ


በመጨረሻው ቀን ማመን ሰዎችን በመልካም ስራ ላይ ስርዓት ይዘው እንዲዘወትሩ አቅጣጫ በማስያዝ


ረገድ እንዲሁም አላህን እንዲፈሩና ከሁሉ ለኔ ባህሪና ከይዩልኝ እንዲርቁ በማድረግ የጎላ ሚና አለው፡፡


አብዛኛውን ጊዜ መልካም ስራ በመጨረሻው ቀን ከማመን ጋር ተያይዞ የሚቀርበውም ለዚህ ነው ፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «የአላህን መስጂዶች የሚሰራው በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ነው፡፡»


(አል ተውባ 18) «እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የሚያምኑት እነርሱ በሶላታቸው ላይ የሚጠባበቁ ሲኾኑ


በርሱ ያምናሉ፡፡ » (አል አንዓም 92)


በሕይወት ውጣውረድ እራሳቸውን በመወጠር አላህን በመታዘዝ ላይ ከመሽቀዳደም ለተዘናጉ፣ ወደ አላህ


በመቃረብ ጊዜን ከመሻማት፣ እርሱን ከመታዘዝ፣ የዚችን ዓለም እውነተኛ ገጽታና አጭርነት ከማስተንተን፣


የወዲያኛውን ዓለም መርጊያነት ዘልዓለማዊነት ከማሰብ ለተዘናጉና ለረሱ ማሳሳቢያና ማስጠንቀቂያ አለበት፡፡


አላህ (ሱ.ወ)በቁርኣን ውስጥ መልዕክተኞችን ስራቸውን በመጥቀስ ሲያወሳ፣ እነዚያን ስራዎችና የላቁ ገድሎች


እንዲፈጽሙ ሰበብ የሆናቸውን ጉዳይ በማሞገስ ነበር ያወሳው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እኛ ጥሩ በኾነች


ጠባይ መረጥናቸው (እርሷም) የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት፡፡» ማለትም የነኚያ የተከበሩ ስራዎቻቸው


መንስኤ እነርሱ የመጨረሻይቱን አገር በማስታወስ ለየት ያሉ መሆናቸው ሲሆን ይህም ማስታወሳቸው እነዚያን


ስራዎችና አቋሞች እንዲኖራቸው ገፋፍቷቸዋል፡፡


እነርሱን ለማሳሰብና ለማስጠንቀቅ እንዲህ አለ፡- «የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ይበልጥ ወደዳችሁን?


የቅርቢቱ ሕይወት በመጨረሻይቱ (አንጻር) ጥቂት እንጂ አይደለም፡፡» (አል ተውባ 38)


የሰው ልጅ በመጨረሻው ቀን በትክክል በሚያምን ጊዜ ማንኛውም የዚች ዓለም ጸጋ ከመጨረሻው ዓለም


ጸጋ ጋር ሊነጻጸር እንደማይችል እርግጠኛ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል በወዲያኛው ዓለም ለአንዲት ቅጽበት


የሚያገነውን ቅጣት ምንም ሊያክለው አይችልም፡፡ በዚህም በዱንያ ላይ ያለ የቅጣት ዓይነትም ከመጨረሻው


ዓለም ቅጣት ጋር ሊነጻጸር እንደማይችል ይገነዘባል፡፡ በሌላ በኩል እዚህ ያለ ተድላና ደስታ በወዲያኛው


ዓለም ከሚያጋጥም የቅጽበት ጸጋ ወይም ድሎትና ደስታ ጋር አይስተካከልም፡፡


የሰው ልጅ በመጨረሻው ቀን ካመነ የስራውን ምንዳ ማግኘቱ አይቀሬ እንደሆነ እርግጠኛ ስለሚሆን


ይረጋጋል፡፡ ስለሆነም የሆነ የዚህች ዓለም ጥቅም ቢያመልጠው ወይም ቢያጣው ተስፋ በመቁረጥና


በመበሳጨት ነፍሱን በሐዘን አይገድልም፡፡ እንዳውም ታታሪ ሊሆንና አላህ (ሱ.ወ) የመልካም ሰሪን ምንዳ


በከንቱ እንደማያስቀር እርግጠኛ ሊሆን ይገባል፡፡ የጎመን ዘር ቅንጣትን የሚያህል ነገር ከርሱ በግፍ ወይም


ያለ አግባብ ቢወሰድበት ወይም ቢጭበረበር የትንሳኤ ቀን እሷ እጅግ በምታስፈልገው ወቅት ላይ ያገኛታል፡፡


ፈንታው ያለምንም ጥርጥር በጣም በሚያስፈልገው ወቅት ላይ እንደሚሰጠው ያወቀ ሰው እንዴትስ ያዝናል?


በእርሱና በሞጋቹ መሐከል የሚዳኝውና የሚፈርደው የፍትሃውያን ሁሉ ፍትሃዊ የሆነው ጥበበኛው ዳኛ


አላህ(ሰ.ወ) እንደሆነ ያወቀ እንዴትስ ይተክዛል?


በአላህ ውሳኔ የማመን ትርጓሜ


ማንኛውም መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የሚከሰተው


በአላህ ውሳኔና ፍርድ እንደሆነ በቁርጠኝነት ማረጋገጥ


ነው፡፡ እርሱ ያሻውን ሰሪ ነው፡፡ በእርሱ ፍላጎት እንጂ


የሚሆን አንድም ነገር የለም፡፡ ከሱ መሻት የሚወጣ ነገርም


የለም፡፡ በዓለም ውስጥ ከርሱ ውሳኔ የሚወጣ ነገር የለም፡


፡ ከርሱ ማዘጋጀት ወይም ማስተናበር ባሻገር የሚከሰትም


ነገር የለም፡፡ ከዚህም ጋር ትዕዛዛትን እንዲፈፅሙ ባሮቹን


አዟል፡፡ ክልከላዎችንም ከልክሏቸዋል፡፡ ለሚሰሯቸው


ስራዎቻቸውም የመምረጥ ነጻነት ሰጥቷቸዋል፡፡


አይገደዱም፡፡ ስራቸው የሚከሰተው እንደ ችሎታቸውና


እንደ ፍላጎታቸው ነው፡፡ አላህ እነሱንም ችሎታቸውንም


የፈጠረ እሱ ነው፡፡ በእዝነቱ ያሻውን ያቀናል፡፡ በጥበቡ


ያሻውን ያጠማል፡፡ እርሱ በሚሰራው አይጠየቅም እነርሱ


ተጠያቂ ናቸው፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን ምንን ያካትታል?


በአላህ ውሳኔ ማመን አራት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያካትታል


• አላህ (ሱ.ወ) በጥቅሉም ሆነ በዝርዝር ስለ ሁሉ


ነገር ያውቃል ብሎ ማመን፡፡ እነሆ እርሱ ፍጡራን


በሙሉ በርግጥ ከመፈጠራቸው በፊት ያውቃቸዋል፡፡


ሲሳያቸውን፣ ቆይታቸውን፣ ንግግራቸውንና ስራዎቻቸውን


አስቀድሞ አውቆታል፡፡ ሁሉንም እንቅስቃሲያቸውንና


መርጊያቸውን፣ ሚስጥራቸውንና ይፋቸውን ያውቃል፡


፡ ከነርሱ ውስጥ ማናቸው የጀነት ጓዶች እንደሆኑና


ማናቸው የእሳት ጓዶች እንደሆኑ አስቀድሞ ያውቃል፡


፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ


ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የኾነ


ነው፡፡» (አል ሐሽር 22)


• አላህ(ሱ.ወ) ተግባራትን ሁሉ አስቀድሞ በለውሕ አል-


መሕፉዝ ላይ አስፍሯቸዋል። ስለዚህ ማስረጃ የሚሆነው


የሚከተለው አላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው።‹‹ በምድርም


በነፍሳችሁም መከራ(ማንንም) አትነካም ስንፈጥራት


በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጂ።ይህ


በአላህ ላይ ገር ነው (አል ሐዲድ፡22) ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)


እንዲህ ብለዋል፦‹‹ አላህ የፍጡራንን ችሮታ ሰማያትንና


ምድርን ከመፍጠሩ ሃምሳ ሺህ አመታት በፊት


ጽፏል።››(ሙስሊም 2653)


• እርሷን የሚያስተጓጉላት ምንም ነገር በሌላት፣


ተፈጻሚ በሆነችው በአላህ መሻት እና ምንም


በማይሳነው በአላህ ችሎታ ማመን፡፡ ማናቸውም


ክስተት የሚከሰተው በአላህ መሻትና ችሎታ ነው፡፡


እርሱ የሻው ይሆናል እርሱ ያልሻው አይሆንም፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- « የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም


አትሹም፡፡» (አል ተክዊር 29)


• ማናቸውንም ነገር የሚያስገኘውና የሚያስከስተው


ወይም የሚፈጥረው አላህ (ሱ.ወ) መሆኑን ማመን፡


፡ እርሱ ብቸኛ ፈጣሪ ነው፡፡ ከርሱ ሌላ ያለ ነገር ሁሉ


ፍጡር ነው፡፡ እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ነገሩንም ሁሉ የፈጠረውና


በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡» (አል ፉርቃን 2)


> በአላህ ውሳኔ (በቀደር) ማመን


በአላህ ውሳኔ ማመን ከኢማን ማዕዘናት


መካከል አንዱ ማዕዘን ነው፡፡ ይኸው


እውነታ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጂብሪል ሰለ ኢማን


ጠይቋቸው በሰጡት ምላሽ ላይ ተዘክሯል፡


- « በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣


በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀንና በአላህ


ውሳኔ በክፉውም በደጉም ልታምን ነው፡፡»


(ሙስሊም 8)


> በዚህ ፍጥረተ-ዓለም ውስጥ አንድም ነገር ከአላህ


ውሳኔ ውጭ አይሆንም፡፡


የሰው ልጅ ምርጫ፣ ችሎታና ፍላጎት አለው፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን የሰው ልጅ በምርጫው


በሚፈጽማቸው ተግባሮቹ ላይ ፍላጎትና ችሎታ አለው


ከማለት ጋር አይቃረንም፤ አይጋጭም፡፡ ምክንያቱም


የእስላማዊ ድንጋጌና ነባራዊ ተጨባጭ ክስተት ይህንን


ለርሱ የሚያረጋግጡና የሚያጸድቁ ናቸው፡፡


ከእስላማዊ ድንጋጌ አንጻር አላህ (ሱ.ወ) መሻትን


አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፡- «ይህ የተረጋገጠው ቀን


ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡»


(አል ነበእ 39)


ችሎታን በማስመልከትም አላህ እንዲህ ብሏል፡- «አላህ


ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ


የሰራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራቺው (ኀጢኣት)


አለባት፡፡» (አል በቀራ 286)


ከነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ደግሞ ማንኛውም


ሰው ችሎታና መሻት እንዳለውና በነርሱም


የሚሰራውን እንደሚሰራ፣ የሚተወውንም


እንደሚተው ያውቃል፡፡ እንደመራመድና መሰል


እንቅስቃሴዎች ያሉ በፍላጎቱ የሚከሰቱትን፣


እንደመንቀጥቀጥና እንደ ድንገተኛ መውደቅ ያሉ


ያለፍላጎቱ ከሚፈጸሙት ለይቶ ያውቃል፡፡ ነገር


ግን የፍጡር መሻትና መቻል በአላህ መሻትና


ችሎታ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ


ብሏል፡- «ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው


(መገሰጫ ነው) ፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም


አትሹም፡፡» (አል ተክዊር 28-29)


በአንቀጹ ላይ እንደምንመለከተው መጀመሪያ የሰው


ልጅን መሻት አጸደቀ፤ ከዚያም በአላህ መሻት ውስጥ


የሚካተት እንደሆነ አሳሰበ፡፡ ምክንያቱም ፍጥረተ-


ዓለሙ በጠቅላላ የአላህ ይዞታ ነው፡፡ በርሱ ይዞታ


ውስጥ ደግሞ ከርሱ ዕወቀትና መሻት ውጭ የሚሆን


ነገር አይኖርም፡፡


> «እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሃዲ ሲኾን መንገዱን መራነው (ገለጽንለት)» (አል ደህር 3)


በአላህ ውሳኔ ማመካኘት


የግዳጅና ኃላፊነት፣ የትዕዛዝን የክልከላ ተያያዥነታቸው ከሰው ልጅ ችሎታና ምርጫው ጋር ነው፡፡ አንድ መልካም ሰሪ


ቀናውን ጎዳና የመረጠ በመሆኑ ይመነዳል፡፡ መጥፎ ሰሪ ደግሞ እኩይ የሆነን የጥመት መንገድ በመምረጡ ይቀጣል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) የምንችለውን እንጂ አላስገደደንም፡፡ በመሆኑም አላህ በርሱ ውሳኔ በማመካኘት እርሱን ማምለክ መተውን


ከአንድም ሰው አይቀበልም፡፡


ከዚህም በተጨማሪ የሰው ልጅ ከማመጹ በፊት አላህ አውቆ የወሰነው ምን እንደሆነ አያውቅም፡፡ አላህ ደግሞ ችሎታና


የመምረጥ ነጻነት ሰጥቶታል፡፡ የመልካምና የመጥፎን ጎዳና ነጣጥሎ አብራርቶለታል፡፡ በመሆኑም ካመጸ፣ አመጽን ለአላህ


ታዛዠ ከመሆን በላጭ አድርጎ የመረጠው እራሱ ነው፡፡ በአመጸኛነቱ የሚያገኘውን ቅጣት የመሸከም ግዴታ አለበት፡፡


> አንድ ሰው በአንተ ላይ ድንበር በማለፍ ንብረትህን ቢውስድብህና ቢያሰቃይህ፣ ከዚያም ለዚህ እኩይ ተግባሩ በርሱ ላይ አላህ የወሰነበት መሆኑን


እንደ ምክንያት ቢያቀርብ ምክንያቱ ተቀባይነት አይኖራትም፡፡ በፈጸመው በደል ትቀጣዋለህ፤ ንብረትህንም ታስመልሳለህ፡፡ ምክንያቱም


ሰውየው ይህን የፈጸመው በምርጫውና በፍላጎቱ ስለሆነ ነው፡፡


በአላህ ውሳኔ የማመን ጥቅም ወይም ፍሬ


በአላህ ውሳኔ ማመን በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን በዚህ የሕይወት ቆይታ ንቁ ሆኖ፣ አላህ የሚወደውን በመፈፀሙ እንዲጥርና እንዲተጋ


ከሚያደርጉ ነገሮች ዋነኛውና ትልቁ ነገር ነው፡፡


ምእመናን በአላህ ላይ ከመመካታቸው ጎን ለጎን የክስተት ሰበቦችን እንዲጠቀሙ ታዘዋል፡፡ ኢማን ማለት


ደግሞ በአላህ ፍቃድ እንጂ የክስተት ሰበቦች ውጤት ሊያስገኙ እንደማይችሉ እርግጠኛ መሆን ነው፡፡


ምክንያቱም የክስተት ሰበቦችን የፈጠረው አላህ ነው፡፡ ውጤታቸውንም የፈጠረውም እሱ ነው፡፡


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «በሚጠቅምህ ነገር ላይ ታታሪ ሁን፡፡ በአላህ ታገዝ፡፡ አትሳነፍ፡፡ የሆነ


(መሰናክል) ነገር ቢገጥምህ እንዲህ እንዲህ ባደረግ ኖሮ እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር አትበል፡፡ ነገር ግን አላህ


ወሰነ ያሻውንም ፈፀመ በል፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ማለት የሸይጣንን በር ትከፍታለች፡፡» (ሙስሊም 2664)


የሰው ልጅ የነፍሱን ልክ ማወቅ አለበት፡፡ ሊኮራም ሊኮፈስም አይገባም፡፡ ምክንያቱም እሱ በአላህ


የተወሰነውን ነገርና ወደፊት የሚከሰተውን ክስተት ማወቅ የማይችል ደካማ ፍጡር ነው፡፡ በመሆኑም የሰው


ልጅ ምንጊዜም በደካማነቱና ወደ ፈጣሪው ከጃይ መሆኑን ማመን አለበት፡፡


የሰው ልጅ በተፈጥሮው መልካም ነገር ሲገጥመው ይኮራል በርሱም ይታለላል፡፡ መጥፎ ነገርና አደጋ


ሲያጋጥመው ደግሞ ይበሳጫል፤ ይተክዛል፡፡ እናም የሰው ልጅን በአላህ ውሳኔ ከማመን በስተቀር መልካም ነገር


ሲገጥመው ከመኮፈስና ድንበር ከማለፍ፣ እንዲሁም መጥፎ ነገር ሲገጥመው ከማዘንና ከመተከዝ ሊታደገው


የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ ማናቸውም የተከሰቱና የሚከሰቱ ነገሮች የአላህ ውሳኔ የተላለፈባቸውና አላህ


አስቀድሞ ያወቃቸው ናቸው፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን ውግዝ ለሆነው ምቀኝነት እልባት ይሰጣል፡፡ አንድ ሙእሚን አላህ ከችሮታው


በሰጣቸው ነገር ሰዎችን አይመቀኝም፡፡ ለነርሱ የለገሳቸውና ይህንን ነገር የወሰነላቸው አላህ (ሱ.ወ) ነው፡፡


እናም ሙእሚን ሌሎችን ሲመቀኝ በአላህ ውሳኔና ፍርድ ላይ እያመጸ መሆኑን ወይም ውሳኔውን እየተቃወመ


እንደሆነ ያውቃል፤ ስለሆነም አይመቀኝም፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን በልብ ውስጥ ችግሮችን ለመጋፈጥ ጀግንነትን ይፈጥራል፡፡ ቁርጠኝነትንም


ያጠናክራል፡፡ ምክንያቱ፣ በአላህ ውሳኔ ማመን የዱንያ ቆይታ (አጀል) ሲሳይ በአላህ የተወሰነ እንደሆነና


የሰው ልጅን የሚያጋጥመው የተጻፈው ነገር ብቻ መሆኑን እርግጠኛ እንዲሆኑ ስለሚያደርግ ነው፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን በሙእሚን ነፍስ ውስጥ የተለያዩ የኢማን ጭብጦችን ይተክላል፡፡ እርሱ ምንጊዜም


እገዛ የሚሻው ከአላህ ብቻ ነው፡፡ የክስተት ሰበቦችን ከመፈፀሙም ጋር የሚንተራሰውና የሚመካው በአላህ


ላይ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም ምንጊዜም ጌታውን ከጃይ ይሆናል፡፡ በጽናት ላይ እንዲያበረታው ከርሱ እገዛን


ይፈልጋል፡፡


በአላህ ውሳኔ ማመን የመንፈስ እርጋታን ይፈጥራል፡፡ ሙእሚን፣፣ የደረሰበት ነገር መጀመሪያውኑ ሊስተው


እንዳልነበረ፣ የሳተውም ነገር መጀመሪያውኑ ሊያገኘው እንዳልነበረ ያውቃል፡፡



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ