መጣጥፎች




በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


መቅድም


ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ይሁን፡፡ ሰላትና ሰላም የነቢያት ሁሉ መደሚደሚያ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድና በቤተሰባቸው፣ እንዲሁም በባልደረቦቻቸው ((በሰሀቦቻቸው) ) እና እስከ ዕለተ ትንሳኤ ድረስ ፈለጋቸውን በተከተሉት ላይ ይውረድ፡፡


ከዚህ በመቀጠል ለክርስቲያን ወገኖቻችን በነቢዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)) በወረደውና የአላህ ((ሱ..ወ) ) የመጨረሻው ቃል ኪዳን በሆነው ቅዱስ ቁርአን ላይ በመንተራስ ወደ አላህ አንድነት ጥሪ ማድረግ እንፈልጋለን፡፡ ይህም በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተጣለ ኃላፊነት ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ይህንን ኃላፊነት ችላ ከማለታችን የተነሳ ““ወንጌልን ለሙስሊሞች ለማዳረስ” ” የሚለውን አጀንዳ አንግበው ሰፈር ለሰፈር የሚንቀሳቀሱት ወንጌላዉያን ሙስሊሙን በማክፈር ረገድ እያደረሱት ያለው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ይህንን አደጋ ለመመከት የሚታገሉት አንዳንድ የዳዕዋ ሰዎችም ወቅታዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታን ያገናዘበ የአጠራር ስልት ስለሚያንሳቸው ጥሪውን በተገቢው መንገድ በጥበብ ለማድረግ ብዙ ይጠበቅባቸዋል፡፡


ወንጌላዉያን ‹‹‹‹የኢየሱስን ጌትነት›› ›› ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንዲቀበልላቸው የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ዳር ዳሩን ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ በተለያዩ ዘዴዎች ለማሳመን ይሞክራሉ እንጂ ቁርጥ አድርገው በልበ ሙሉነት እንኳን ለመግለፅ ይቸገራሉ፡፡ አንዴ ‹‹‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው›› ›› ይላሉ፡፡ ጌታ አለመሆኑን እራሱ ኢየሱስ የተናገረውን መሠረት በማድረግ ሲጠየቁ ደግሞ ‹‹‹‹የእግዚአብሔር


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


6


ልጅ ነው›› ›› በማለት አቋማቸውን ከአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይለዋውጣሉ፡፡ በማያሻማ መልኩም አያስተምሩም፡፡


ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር ‹‹‹‹የሰው ልጅ›› ›› እያለ እንዴትስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል ተብለው ሲጠየቁ ደግሞ ‹‹‹‹ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ›› ›› በሚለው ይደመድማሉ፡፡


በዚህ ዘመን ከቁርአንም አንዳንድ አንቀጾችን አጣሞ በመጠቃቀስ ሙስሊሙ ሃይማኖቱን እንዲለቅ ለማድረግ ይታገላሉ፡፡ በዚህ ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይፈለግበታል፡፡ ይህ ሁኔታ እንደሚከሰት አላህ አስቀድሞ በቁርአን ውስጥ አስጠንቅቆናል፡፡


‹‹


‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ! ከነዚያ መጽሐፉን ከተሰጡት ሰዎች ከፊሉን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ይመልሷችኋል፡፡›››› ((ኣለ ዒምራን 33÷÷100100) )


ስለሆነም እየተደረገ ያለው ነገር በቁርአን ውስጥ አስቀድሞ የተተነበየ በመሆኑ ሙስሊሙ ተግቶና ነቅቶ ሃይማኖቱን መጠበቅ አለበት፡፡


ለሙስሊሙ ህብረተሰብ በጣም የተጨነቁ በመምሰል በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የኢየሱስን ጌትነት እንዲቀበል በሰብዓዊ ዕርዳታ ስም የሚንቀሰቀሱት ወንጌላዉያን ሊገነዘቡት የሚገባ ሀቅ ((እውነታ) ) አለ፡፡ ይኸውም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተዘረዘሩት የታሪክ ማስረጃዎች በአብዛኛው ከክርስቲያናዊ መፅሐፍት የተወሰዱ በመሆናቸው እንደመስታወት ከፊት ለፊታችሁ አስቀምጣችሁ በጽሞና ልትመለከቱት ይገባል፡፡ የዛሬው ትውልድ ደግሞ ያለፉት ትውልዶች የፈፀሟቸውን ስህተቶች ማረም ይገባዋል


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


7


እንጂ እነርሱ በደነገጉት መንገድ መጓዝ ለዘለዓለማዊው ህይወት የሚሰጠው ዋስትና አስተመማኝ ባለመሆኑ ይህንንም ለማወቅ ዕድሉ አሁን ነውና ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ በመጨረሻም የሚከተለውን የቁርአን አንቀጽ ከዚህ መጽሐፍ ጋር አስተያዩ፡--


‹‹


‹‹እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ! በኃይማኖታችሁ ከዕውነት ሌላ የሆነን ((ማለፍ) ) ወሰንን አትለፉ፤ በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱና ብዙዎችን ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም ((አሁን) ) የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ በላቸው፡፡›› ›› ((አል--ማኢዳህ 55÷÷7777) )


የዛሬው ትውልድ የተባለውን ብቻ ሰምቶ ከመቀበል ይልቅ በሚዛን ላይ በማስቀመጥ አጣርቶ የሃይማኖት ምርጫውን ማስተካከል ይኖርበታል፡


የመጽሐፉ ርዕስም ‹‹‹‹ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ›› ›› የተባለበት ዋናው ምክንያት በማስረጃ የተደገፈ የሃይማኖት ምርጫ ለአዲሱ ትውልድ የሚያስፈልግ ከመሆኑም በላይ ያለንበት ክፍለ ዘመንም ለማስረጃ ልውውጥ የተመቻቸ ስለሆነ ይህንኑ ዕድል አዲሱም ትውልድ ይጠቀምበት ዘንድ ለማሳሰብ ነው፡፡


አላህ ወደ ቀጥተኛው ኃይማኖት ይምራን!!


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


8


መግቢያ


ዛሬ በዓለማችን ላይ የብዙ ኃይማኖቶች መኖርና በተለያዩም ጊዜያት የአዳዲስ ሃይማኖቶች መፈጠር የሰውን ልጅ ፈጣሪውን ከመገዛት ከሚያግዱት ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳም ሰዎች የትኛውን ሀይማኖት መያዝ እንደሚገባቸው ግራ ስለሚጋቡ በሁሉም እምነቶች ላይ ጥርጣሬ ማሳደርና ሁሉንም ሀይማኖት በአንድ መንጽር ማየት ይጀምራሉ፡፡ በሌላ በኩል ሰው በተፈጥሮው ዘንጊ የሆነ ፍጡር በመሆኑ የወደፊት ህይወቱን በመርሳት ምድራዊ ፍላጎቱን ብቻ በማሟላት ላይ የተመሰረተ አላማ አንግቦ ሲጓዝ ማየቱ ለሀይማኖተኛ ሰው በጣም ዘግናኝ ነው፡፡ ነገ ምን እንደሚገጥም አይታወቅምና ዛሬ በልቼ ልሙት ባዩ ወገን በሚያስደንቅ አኳኋን ሞት በድንገት ሲነጥቀው ከሁለቱም ዓለም ተጠቃሚ ሳይሆን ይቀራል፡፡ ያጠራቀመውንም ሀብት በልቶና ጠጥቶ፣ ለብሶና ሥጋዊ ፍላጎቱን እንኳ ሳያሟላ ከማያውቀው አቅጣጫ የተፈጥሮአዊው ሞት አደጋ በላዩ ላይ እያንዣበበ ቀሪ ህይወቱን የአልጋ ቁረኛ በመሆን ካሳለፈ በኋላ በመጨረሻ አይቀሬ የሆነችው ሞት ትወስደዋለች፡፡ አሊያም ጤናኛና ብርቱ ሆኖ ሳለ ድንገተኛ ሞት ሊይዘው ይችላል፡፡


‹‹


‹‹እነዚያ የካዱት ከነዚያ ካመኑት የሚሳለቁ ሲሆኑ ቅርቢቱ ሕይወት ተሸለመችላቸው፤ እነዚያም የተጠነቀቁት በትንሣኤ ቀን ከበላያቸው ናቸው፤ አላህም ለሚሻው ሰው ያለ ግምት ይሰጣል፡፡›››› ((አል--በቀራህ 22÷÷212212))


ከዚያስ? ? ከዚያ በኋላማ ከወዲያኛው አለም ድርሻ ምንም አልፈልግም በማለት የራሱን ውሳኔ በራሱ ስላፀደቀና ፈጣሪውን ሳይገዛ ሕይወቱ ያለፈች ስለሆነ ብርቱ ቅጣት እንደሚጠብቀውም


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


9


በመጽሐፍት የተደነገገ በመሆኑ የጀሀነም--እሳት ውስጥ ይገባል፡፡


‹‹በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፤ አንጐሉን ያፈርሰዋልም፤ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፤ ለናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ አለው በማለት) ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፣ (ወዮላችሁ)፡፡›› (አል-አንቢያ 21÷18)


ከዚህ ዓይነቱ ቅጣት ለማምለጥ የፈጣሪን አንድነት መመስከርና በመንገዱም ላይ ቀጥ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በቅድሚያ የፈጣሪ መኖርን በሙሉ ልብ አምኖ መቀበል የሚጠበቅብን ሲሆን ይህም አብዛኛው ፍጡር የሚያምነው ነው፡፡ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ፈጣሪውን ለመገዛት መንገዱ የትኛው ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ መሠረታዊ ዕዉቀት ከሁሉም ኃይማኖቶች መገብየት ያስፈልጋል፡፡ በወገንተኝነት ስሜት ተሞልተን ‹‹‹‹የኛ ይሻላል›› ›› በማለት የዕውቀት አድማሳችንን ማጥበብ በራሳችን ላይ መጋረድ ስለሆነ የሁሉንም ወገኖች የኃይማኖት መመሪያ በጥንቃቄ መፈተን የዕውቀትን በር ለመክፈት ያስችላል፡፡


‹‹


‹‹ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉንም ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፡፡›› ›› ((11ኛ ተሰሎንቄ 55÷÷2121) )


ስለዚህ በአላህ አንድነትና በሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ) ነቢይነት ያላመኑት ወገኖች የእስልምናን ትንቢት ሳይንቁ ከክርስትና ኃይማኖት ጋር ጎን ለጎን በማጤን ተገቢ ዕውቀት አግኝተው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመለሱ ዘንድ አላህ አዕምሮአቸውን ለማወቅ እንዲጠቀሙበት ይክፈትላቸው በማለት ይህንን መጽሐፍ ‹‹‹‹ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ›› ›› በሚል ርዕስ አዘጋጅተን ‹‹‹‹ለማወቅ ያለህን ዕድል ላለማወቅ አትጠቀምበት›› ››


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


10


በሚል መሪ ርዕስ ስር አቅርበነዋል፡፡


‹‹


‹‹አላህ ለነሱ ብርቱን ቅጣት አዘጋጀ፣ እናንተም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ አላህን ፍሩ፤ አላህ ወደናንተ ግሣጼን በእርግጥ አወረደ፤ መልክተኛን ((ላከ))፡፡›››› ((አጥ--ጠላቅ 6565÷÷1010))


ዛሬ በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል ያለው የተዛባ አመለካከት መወገድ አለበት፡፡ ስለሆነም መቀራረብ፣ መመካከር፣ መማማር፣ ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጥና መወያየት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በጥንታዊ የኃይማኖት ትምህርትም ሆነ በዘመናችን የፍልስፍና ትምህርት ውስጥ የአንድ ነገር ሦስትነትና አንድነት ወይንም ደግሞ የሦስት ነገሮች ድምር አንድ መሆን በፍጹም አይታወቅም፡፡ ሚስጥረ ሥላሴ ከኢየሱስ በፊት በነበሩት ነቢያት ወቅት አልነበረም፡፡ በአይሁድ ኃይማኖት ውስጥም ጥንትም ሆነ ዛሬ አይታወቅም፡፡ በኢየሱስ ዘመንና ከኢየሱስ በኋላ እስከ የመጀመሪያዎቹ ሦስት መቶ ዓመታት ድረስ አይታወቅም ነበር፡፡ ታሪካዊ አመጣጡን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት የምናተኩርበት ሲሆን ለመንደርደሪያ ግን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብቻ በመውሰድ ሚስጥረ ሥላሴ የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑንና ይልቁንም ቤተ--ክርስቲያናዊ መሆኑን እንረዳለን፡፡


‹‹


‹‹የማይገለጥ የተከደነ፤ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና›› ›› ((የማቴዎስ ወንጌል 1010÷÷2626) )


ይህ አባባል ኢየሱስ አስቀድሞ ሚስጥረ ሥላሴን እንዳንቀበል የሰጠው ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ የክርስትና ኃይማኖት አስተማሪዎች የፈጣሪን አንድነት የሚገልጹት በሚስጥር ሲሆን ይህንን ሚስጥር ማንም ሰው ለመግለጽ እንደማይችል ያስጠነቅቃሉ፡፡ ይህንን ጉዳይ


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


11


አስመልክቶ ብዙ ተመራማሪዎች ለመረዳትና ለማስረዳት አልቻሉም፡፡ አይቻልምም፡፡ ምክንያቱም ፈጣሪ አንድ ብቻ ነውና፡፡ ሥላሴያዊ ባህሪው ማስረጃ የለውም፡፡


ቲኦሎጂን በተመለከተ አንድ ምሁር የሚከተለውን ብለው ነበር፡--


‹‹


‹‹ቲኦሎጂ ለራሳቸው ያልተረዱትን ትምህርት ለሌላው ለማስረዳት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ዓላማውም እውነትን ለመንገር ሳይሆን ጠያቂውን ለማስደሰት ነው፡፡›› ›› ((አልቤርት ሁበርድ፣ ከኢትዮጵያ ሄራልድ፣ ዓርብ ጁን 16/200016/2000 የተወሰደ))


እዚህ ጋ የአልቤርት ሁበርድ አስተያየት ሊጠቀስ የቻለውም ያለ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ አፃፃፍ፣ የክርስትናን ታሪካዊ አመሰራረት፣ የአንዳንድ ወንጌሎችን በቤተክርስቲያን ጉባኤ መመረጥና የሌሎች መወገድ፣ በሥላሴ ዙሪያ ያለውን የዓለም ውዝግብና የትንቢቶችን አፈፃፀም አያውቁም፡፡ ስለዚህ ሌላውን ከማስረደት ይልቅ ለራስ መረዳት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ‹‹‹‹ታላቅ ምክር››››ን ማንበብ መልካም ዕድል ይሁንልዎ እያልን የአልቤርት ሁበርድንም አባባል አስታዉሱ እንላለን፡፡


‹‹


‹‹በእርግጥ በአላህ ዘንድ ያለው ኃይማኖት እስላም ብቻ ነው፡፡ እነዚያ መፅሐፉን የተሰጡት ((ክርስቲያኖችና አይሁዶች) ) ዕውቀቱ ከመጠላቸው በኋላ በመካከላቸው ስላለው ምቀኝነት እንጂ ለሌላ አልተለያዩም ነበር፡፡›››› ((ኣለ ዒምራን 3÷19)3÷19)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


12


ኃይማኖትን በንጽጽር


አንዳንድ ሰዎች በክርስትና ኃይማኖት ውስጥ የዲኖሚኔሽኖች ((የሀይማኖት ወገኖች) ) መብዛት የተነሳ የኃይማኖት ነገር በግልጽ አይታወቅም ብለው ያምናሉ፡፡ ለምን እስልምናን ለማወቅ አትሞክሩም በሚባሉበት ጊዜ ደግሞ መልሳቸው ‹‹‹‹የዓረብኛን ቋንቋ አንችልም›› ›› ነው፡፡ የዚህም ጽሑፍ ዋና ዓላማ ‹‹‹‹ዓረብኛን አናውቅም›› ›› የሚለውን ሲንድሮምን ((የበሽታ ምልክት) ) መዋጋት ነው፡፡ የምንዋጋበት መንገድም እውነታው የት እንዳለ በመጠቆም ለእውነት ፈላጊው መረጃን በመስጠት ይሆናል፡፡ ከዚህ ጽሑፍም ባሻገር በእስልምና ላይ ትኩረት በመስጠት በብዙ የዓለም ህብረተሰብ ቋንቋዎች ተተርጉሞ እየተሰራጨ ያለውን መረጃ ((ኢንፎርሜሽን) ) ለማግኘት የወቅቱ የመረጃ ልውውጥ ከምንጊዜውም በበለጠ አመቺ በመሆኑ የዓረብኛን ቋንቋ አላውቅም ማለት ለመጨረሻው ዓለም ጥያቄ በቂ መልስ አይሆንም፡፡ ዓረብኛውም ቢሆን ከየትኛውም ቋንቋ የተለየ ክብደት ያለው ባለመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተምሮ ስለእስልምና ኃይማኖት በቂ ግንዛቤ ለማግኘት ይቻላል፡፡ ለስራ ፍለጋስ ቢሆን ይጠና የለም? ?


ሌላው የዘወትር ጥያቄ ሆኖ በሰዎች አዕምሮ የሚኖረው ጉዳይ የሃይማኖት መመሪያዎቹ ምንጭ በተለይም የክርስትናና የእስልምና መጽሐፍት ምንጫቸው መለኮታዊ ((ሰማያዊ) ) መሆናቸው ነው፡፡ የእስልምና ኃይማኖት መመሪያ የሆነው ቅዱስ ቁርአን ንጽሕናው የተጠበቀና ከውሸትም የጠራ መሆኑን ቁርአኑ በሚገባ ያስተምራል፡፡ ትልቁ ችግር ያለው የመነበብ ትኩረት ((ፍላጎት) ) ማጣት ነው፡፡


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


13


‹‹


‹‹ከኋላም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፣ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡›››› ((ፉሲለት 4141÷÷4242))


‹‹


‹‹ቁርአንን አያስተነትኑትምን? ? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡›› ›› ((አን--ኒሳእ 44፡8282))


ነገር ግን የክርስትና ኃይማኖት መመሪያ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት ያለበት መሆኑን በክርስቲያናዊ መፅሐፍ አንደበት የተነገረውን እንደሚከተለው እናንብብ፡--


‹‹


‹‹በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ በእጅ በተገለበጠባቸው በ3,000 3,000 ዓመታት የጊዜ ገደብ ውሰጥ ሰርገው የገቡትን ማናቸውንም የመገልበጥ ስህተቶች ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማጥራት ላለፉት 100 100 ዓመታት እጅግ ተግተው ሰርተዋል፡፡ ምንም ያህል ጥንቃቄ ቢደረግና ተደጋግሞ የማረጋገጫ ምንባብ ቢደረግም እንኳ ታትመው የሚወጡ መፃሕፍት ሁልጊዜም ስህተት እንደሚኖርባቸው መጽሐፉን የደረሰው ሁሉ ይረዳል፡፡›› ›› ((ለሙስሊሞች ጥያቄዎች የክርስቲያኖች መልሶች፤ ገጽ 1111፤ በጌርሃርድ ኔልስ ከተፃፈው መፅሐፍ ላይ የተወሰደ))


የቅዱስ ቁርአንን ተዓምራዊነትና ጥበባዊ ልቅና በሚገባ አለማወቅ ብዙዎችን ሰዎች ከእስልምና ውጪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በተጨማሪም እውነተኛውን ኃይማኖት ለማወቅ የሚደረገው ጥረትም የሚያበረታታ አይደለም፡፡ በተለይም አንዳንድ ግለሰቦች ቁርአን የመጽሐፍ ቅዱስ ግልባጭ ነው እንጂ በራሱ ምሉዕ አይደለም ብለው ይገምታሉ፡፡ በእርግጥ ለዚህ አባባላቸው የሚያቀርቡት ማስረጃ አሳማኝ አይደለም፡፡ ቁርኣን ከፈጣሪ በጅብሪል ((ዓለይሂ ሰላም) ) አማካይነት ለነቢዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


14


ዓለይሂ ወሰለም) ) ቃል በቃል የወረደ ስለመሆኑ ታሪክን ሳያጣምሙ በትክክል የፃፉት የታሪክ ተመራማሪዎች በብዙ መልኩ አረጋግጠውታል፡፡ ከታሪክም ባሻገር ዛሬ ዘመናዊ ሳይንስም በቁርአን ውስጥ ያሉትን አንቀጾች በቅርብ ጊዜ ከተገኙት ሳይንሳዊ ግኝቶች ጋር በመጣጣማቸው ቁርአን ማለት በሰው ጭንቅላት የተደረሰ ወይንም ከሌላ የሰው ልጅ የምርምር ውጤት የተገለበጠ አለመሆኑን አረጋግጠዋል፡፡


ለምሳሌ ያህል በቅርቡ በተለይም በ2020ኛና በ2121ኛ ክ//ዘመናት በዘመናዊ መሣሪያዎች በቤተ ሙከራ ተጠንተው የተገኙት ግኝቶች በ77ኛው ክ//ዘመን በዓረቡ ምድር ሳይንሳዊ ዕውቀት ባልጎለበተበት ወቅት በቁርአን ውስጥ በተለያዩ አንቀፆች ተጠቅሰው መገኘታቸው ለቁርአን ትክክለኛነት ዋቢ ይሆናሉ፡፡ ከነዚህ የቁርአን አንቀጾች መሀከል አንዳንዶቹ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡--


1) ‹‹በእርግጥ ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡›› (አል-ሙእሚኑን 23÷12-14)


(ይህ ከዘመናዊ የኢምብሪዎሎጂ (ሥነ-ጽንስ) ጥናትና ግኝት ጋር ፍጹም አንድ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ማረጋገጫም አግኝቷል፡፡)


2) “በምድርም ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት፤ ጅረቶችንም መንገዶችንም ትመሩ ዘንድ፡- (አደረገ)፡፡›› (አን-ነሕል 16÷15)


(ይህ ከዘመናዊው የጂኦሎጂ (ሥነ-ምድር) ጥናትና ግኝት ጋር ይስማማል፡፡)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


15


3) ‹‹አላህ ደመናን የሚነዳ መሆኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፤ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፤ ዝናሙንም ከመካከሉ የሚወጣ ሆኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና) በውስጧ ካሉ ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፣በርሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነከል፤ ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፤ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡›› (አን-ኑር 24÷43)


(ይህ ከሜትሪኦሎጂ ግኝ ጋር ይስማማል፡፡)


4) ‹‹እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ሕያው የሆነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን አያምኑምን?›› (አል-አንቢያ 21÷30)


(ይህ ከኒውክለር ፊዚክስና ከባዮሎጂ ጋር ይስማማል)፡፡


በመሆኑም እነዚህን እውነታዎች ስናነብ አንዳች ለአዕምሮአችን የሚጎረብጥ ጉዳይ አለ፡፡ ይኸውም ነቢዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)) እንደተባለውም ቁርአንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ከገለበጡ እነዚህ ሳይንሳዊ ግኝቶች ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው የተገለበጡት? ? የሚለው ነው፡፡


አሁን ለውሳኔ አሰጣጥ ያመች ዘንድ ከግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት እውነታ አለ፡፡ ይኸውም የነቢዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)) የትምህርት ደረጃ ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ነው፡፡ እንደተባለውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ካልገለበጡ ምናልባት የራሳቸውን ፍልስፍና አክለውበት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠረጠር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ነቢዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)) እንኳንስ ሳይንሳዊ ዕውቀት ይቅርና የራሳቸውን ስም እንኳን የማንበብና


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


16


የመፃፍ ችሎታ የላቸውም፡፡ ቁርአኑን በቃላቸው ለተከታዮቻቸው በማስተማር የቆዩ ሲሆን ቁርአኑ ወርዶ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው ለጽሕፈት የበቃው እንጂ ለዓለም ብርሃን ሆኖ የቀረበው በግልበጣ አይደለም፡፡


ነብዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)) የሌላ ፈላስፋ ሥራን ወስደው ቁርአን ውስጥ አስገቡ ተብሎም ሊታሰብ ይችላል፡፡ ለዚህ ዓይነቱ አመለካከትም መልሱ ቀላል ነው፡፡ ያ ፈላስፋ ስሙ፣ ልዩ ሙያውና የትውልድ አገሩ መጠቀስ አለበት፡፡ በግምት ብቻ የአንድ ሰው ሥራ ተወስዶ ነው የሚባለው ሐሳብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተለይም የዘመኑ የኢምብሪዮሎጂ ((ሥነ--ጽንስ) ) ጥናት በቁርአንና በሐዲሥ ላይ የተመሠረተ ጥናት ለማካሄድ ከላይ የተጠቀሰው የሰው ልጅ አፈጣጠር በጣም ጥሩ ዕድል መሆኑን ተመራማሪዎቹ በሳይንሳዊ ማስረጃቸው በማስደገፍ ያደንቁታል፡፡ እኛስ ሳይንቲስት ያልሆን ሰዎች አምነን ለመቀበል ለምን ቸገረን? ?


አላህ ((ሱብሓነሁ ወተዓላ)) የሰውን ልጅ በሙሉ በእስልምና ላይ መፍጠሩን ቁርአን ያስተምራል፡፡ ይህንን አባበል አብዛኞቹ ክርስቲያኖች አይቀበሉትም፡፡ ምናልባት ይህንን ሲሰሙ የሚስቁም አይጠፉም፡፡ ነገር ግን አንድ ጥያቄ ቢቀርብላቸው ለመመለስ አይችሉም፡፡ እርሱም አላህ ሰውን በእስልምና ኃይማኖት ላይ ካልፈጠረ ለመሆኑ በክርስትና ላይ ነውን? ? ለሚለው መልሱ አዎን ከሆነ በማስከተል ክርስቲያኖች ልጆቻቸውን ለምን ያጠምቃሉ? ? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ሙስሊሞች ልጆቻቸው በተፈጥሮ በእስልምና ላይ ስለሚወለዱ ምንም ዓይነት የኃይማኖት ጠመቃ ሳያደርጉ በተወለዱበት በእስልምና ላይ ያሳድጋሉ፡፡ ይህስ የሰው ልጅ


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


17


በእስልምና ላይ መወለዱን ግልጽ አያደርገውምን??


በነገራችን ላይ ከክርስቶስ እርጋት በፊት የክርስትና ኃይማኖት በዓለም ላይ እንዳልነበረ ያውቃሉን? ? ይህንን ሀሳብ በሚገባ ግልጽ የሚያደርገው ቅዱስ ቁርአን ብቻ ነው፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ በሙሉ በእስልምና ላይ ስለመፈጠሩ በግልጽ ያስተምራልና፡፡


‹‹


‹‹ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለኃይማኖት ቀጥ አድርግ፤ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርስዋ ላይ የፈጠረባትን ((ሃይማኖት ያዙዋት) ) የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፤ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፤ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡›› ›› ((አር--ሩም 3030÷÷3030))


የክርስትና ኃይማኖት መመሪያ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የሚስጥረ ሥላሴ መስራችዋ ቤተ--ክርስቲያን ደግሞ የሰው ልጅ በሙሉ በክርስትና ላይ ስለመፈጠሩ አያስተምሩም፡፡ በመሰረቱ ኢስላም ማለት ትርጉሙ እራስህን ለአላህ ማስገዛት፣ ለአላህ መልካም ፍቃድ እራስን አሳልፎ መስጠትና ከሺርክና ከባዕድ አምልኮ ሙሉ በሙሉ በመጥራት እርሱን ብቻ ማምለክ ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ስማቸው የተጠቀሱት ነቢያት፣ ኢየሱስን ጨምሮ ሁሉም ያስተማሩት የሰው ልጅ ፈጣሪውን ብቻ እንዲገዛ ነው፡፡ ፈጣሪን መገዛት ማለት ኢስላም ከሆነ የቱ ላይ ነው ልዩነቱ? ? ማለትም ሁሉም ነቢያት ኢየሱስን ጨምሮ የሰውን ልጅ ያስተማሩት በእስልምና መንገድ ነው እንጂ በክርስትና መንገድ አይደለም፡፡ አሁንም ይህንን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ከቁርአን ሌላን ማስረጃ መመልከት ይቻላል፡፡


‹‹


‹‹ዒሳ ከነርሱ ክሕደት በተሰማውም ጊዜ ፡-- ወደ አላህ


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


18


(


(ተጨምረው) ) ረዳቶቼ እነማን ናቸው? ? አለ፡፡ ሐዋርያትም እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህ አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር አሉ፡፡›››› ((ኣለ ዒምራን 33÷÷5252))


‹‹


‹‹እርሱ ወደ እስልምና በሚጠራበት ጊዜ በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰውም ይበልጥ በደለኛ ማነው? ? አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡›››› ((አስ--ሰፍ 6161÷÷77))


ስለሆነም ለሰው ልጅ ሁሉ በዚህ አጋጣሚ የምናስተላላፈው መንፈሳዊ ጥሪ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ንጽጽራዊ ኃይማኖት መከተል እንጂ በስሜት ወይንም በጥላቻ ብቻ ፊትን ማዞር ግቡ የማያምር በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡ አላህ ((ሱብሓነሁ ወተዓላ) ) በቅዱስ ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡--


‹‹


‹‹ይህች መንገዴ ናት፤ ወደ አላህ እጠራለሁ፤ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፤ ጥራትም ለአላህ ይገባው፤ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም፡፡› › በል፡፡›››› ((ዩሱፍ 12÷108) 12÷108)


ይህንን የቁርአን አንቀጽ ወስደን የክርስትና ሃይማኖታዊ ዶግማ ከሆነው ሚስጥረ ሥላሴ ጋር በማመዛዘን የትኛው ግልጽና በእውቀት ላይ የተመሠረተ መሆኑን መገንዘብ እንችላለን፡፡


የእስልምና ሃይማኖት የዕምነት መሠረቱ የፈጣሪ አንድነት ነው፡፡ ‹‹‹‹ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም›› ›› ወይም ((ላ ኢላሀ ኢለላህ) ) በሚለው መርሆ ላይ በመመርኮዝ ነው ሁሉንም የሰዉ ልጆች ወደ አንድ መንገድ ብቻ እንዲመለሱ ጥሪ የሚያደርግላቸው፡፡ ነገር ግን ቤተ--ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን በመፃረር የክርስትና ሃይማኖት የእምነት መሰረቱ ሚስጥረ ሥላሴ እንደሆን ደነገገች፡፡


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


19


ሃይማኖትን በንጽጽር ለመቀበል የሚፈልግ ሰው ከሁለቱ የትኛውን ይመርጣል? ? ምርጫዎቹ ሁለት ናቸው፡፡


1/


1/ የእስልምና ሀይማኖታዊ ዶግማ ((ዐቂዳ) ) መሰረት የሆነውን የተዉሒድ //የአላህ አንድነት// እምነት ጥሪን በግልጽ ማስረጃ፣ ማለትም ከላይ በቁርአኑ በተገለጸው መሠረት መቀበል፤ አሊያም


2/


2/ የቤተ--ክርስቲያን አስተምህሮት ቀመር የሆነውን የሥላሴ እምነት ማለትም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመንፈስ ወይም በአምላካዊ ሥራዎቻቸው ((በመለኮት ወይም በአምላካዊ ሥልጣናቸው) ) ደግሞ አንድ ናቸው፤ የሚለውን እምነት መቀበል ነው፡፡ ሦስት የተለያዩ አካላት እንዴት አንድ ሊሆኑ ቻሉ? ? ከተባለ ከቤተ--ክርስቲያን የሚሰጠው ምላሽ ይህ ጉዳይ ሚስጥር ስለሆነ ሳይመራመሩ በየዋህነት//በገራገሪነት ማለፍና መቀበል ነው፤ ይሉናል፡፡ በመሆኑም እውነታው ይህ ከሆነ እርስዎ የትኛውን ይመርጣሉ? ?


ኢየሱስ ክርስቶስ /ዐ.ሰ/ ነቢይና መልዕክተኛ ስለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች


1. “ኢየሱስ አላቸው፡- እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና እሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁም፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 8÷42)


2. “ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኳችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?” (የዮሐንስ ወንጌል 8÷40)


3. “እኔ ከራሴ አልተናገርኩምና ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የሚለውን የሚናገረውንም ትዕዛዝ ሰጠኝ፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 12÷49)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


20


4. “የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የኔ አይደለም፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 14÷24)


5. “ከኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 14÷28)


6. “እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም ጠላታቸው ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 17÷14)


7. “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ አርጋለሁ፡፡” /ኢየሱስ ከአንደበቱ/ (የዮሐንስ ወንጌል 20÷17)


8. “አንተ እንደላከኝ ዓለም ያምን ዘንድ፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 17÷20)


9. “ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህም አላቸው፡- እውነት እውነት እላችኋለሁ፡፡ አብ ሲያደርግ ያየውን እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 5÷19)


10. “እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፡፡ እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፡፡ ፍርዴም ቅን ነው፡፡ የላከኝ ፍቃድ እንጂ ፍቃዴን አልሻምና፡፡ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 5÷30-32)


11. “አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ ይህን የማደርገው ሥራ እንደላከኝ ስለእኔ ይመሰክራልና፡፡ የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 5÷39)


12. “ኢየሱስ መልሶ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 6÷29)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


21


13. “እኔም በራሴ አልመጣሁም፤ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፡፡ እኔ ግን ከርሱ ዘንድ ነኝ፤ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ ብሎ ጮኸ፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 7÷28-30)


14. “በሰማያት ያለውን ያባቴን ፍቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (የማቴዎስ ወንጌል 7÷21)


15. “ኢየሱስም ጌታህን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው፡፡” (የማቴዎሰ ወንጌል 4÷7)


16. “ኢየሱስ ሂድ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎዋልና አለው፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 4÷10)


17. “እኔ ግን እላችኋለሁ፡- በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 5÷45)


18. “እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍፁም እንደሆነ እናንተም ፍፁማን ሁኑ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 5÷48)


19. “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፡፡ አባት ሆይ፣ የሰማይና የምድር ጌታ ሆይ፣ ይህንን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለገለጽህላቸው አመሰግንሀለሁ፡፡” (ማቴዎስ 11÷25)


20. “ኢየሱስም አይኖቹን ወደ ላይ አንስቶ፣ አባት ሆይ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡” (ዮሐንስ 11÷41)


21. “ሕዝቡንም አሰናብቶ ይፀልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 14÷23)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


22


22. “አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 23÷19)


23. “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 24÷36)


24. “ኢየሱስም ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው፡፡” (የማርቆስ ወንጌል 11÷22)


25. “በእግዚአብሔር በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለነበረው ስለኢየሱስ እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደሰቀሉት ነው፡፡” (የሉቃስ ወንጌል 24÷19-21)


ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎች የምንገነዘበው መሠረታዊ ጉዳይ በማያሻማ መልኩ ያለንዳች መቃረን ላኪው አላህ ((ሱብሓነሁ ወተዓላ) ) ተላኪውም ደግሞ ኢሳ //ዓለይሂ ሰላም// ወይንም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ፤ አይን ያለውም ይመልከት፤ ልብ ያለውም ይገንዘብ፡፡


ስለ ዒሳ //ዓለይሂ ሰላም// ሊተኮርበት የሚገባ አብይ ጉዳይ የዓለም ታላላቅ የሃይማኖት መሪዎች ምን አስተማሩ ሳይሆን መንፈሳዊ መፃሕፍት ምን አሉ? ? የሚለውን ጥያቄ አንግበን ለዘላለማዊ ሕይወታችን የሚበጀውን ሐቀኛና ቀጥተኛ መስመር ይዘን መጓዝ ስለሚገባን ብርቱ ጥንቃቄ ወስደን ያለ ማንም ሰው ተፅዕኖ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ተማሪም ብቻ ሳንሆን አስተማሪ ሆነን


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


23


እውነታዉን ጨብጠን ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት መመለስ አለብን፡፡


ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሚሰጡት ትምህርቶች ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሳሉ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ጥቅሶች ለምን ትኩረት እንደተነፈጋቸው አይገባንም፡፡ ወንጌላዉያንም የመጽሐፍ ቅዱስን የአሓዳዊ እምነት አስተምህሮት ገሸሽ አድርገውና የቤተ--ክርስቲያንን ተልዕኮ ብቻ ከመሸከም ተቆጥበው ወንጌልን በጥሞና ከመረመሩ በኋላ ሐቁን ቢገነዘቡ ለሕይወታቸው ትክክለኛ አማራጭ መንገድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በሌላም በኩል የእስልምና ሃይማኖት እውቀት ሳይኖራቸው እስልምናን የሚያጥላሉት፣ በቂ የክርስትና ሃይማኖት እውቀት ሳይኖራቸው ደግሞ ሳይድኑ ድነናል የሚሉት ሰባኪዎች ኃይማኖትን በንጽጽር ቢማሩ መልካም ይሆናል፡፡ ድንቁርና የክህደት ዋነኛ መንስኤ ነው፡፡


ስለሆነም ወንጌላዉያንና ሰባኪዎች የቤተ--ክርስቲያንን አስተምህሮት ለሙስሊሞች ለማዳረስ የእያንዳንዱን ሙስሊም ቤት በር ከማንኳኳት ይልቅ አስቀድመው በመጽሐፋቸው ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ቢያጤኑ መልካም ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ቁርኣን ሁሉ ስለአሓዳዊ እምነት ብቻ ሲያስተምር ቤተ--ክርስቲያን ደግሞ የእምነት መሰረቷን የገነባችው በሥላሴ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ሙስሊሙም ሆነ ሌላው ሕዝብ ይህን እውነታ በሚገባ ማወቅ አለበት፡፡


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


24


ስለ ኢየሱስ እስራኤላዊ ነቢይነት መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?


1. “አንቺ ቤቴልሔም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዥዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 2÷5-6)


2. “እነዚህን አስራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፡፡ አዘዛቸውም፡- በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፣ወደ ሳምራዉያንም ከተማ አትግቡ፡፡ ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 10÷5-6)


3. “እርሱም መልሶ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላኩም አለ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 15÷24)


4. “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡-እውነት እውነት እላችኋለሁኝ፡፡ እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 19÷28)


5. “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፡- እስራኤል ሆይ ስማ፤ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፡፡” (የማርቆስ ወንጌል 12÷29)


6. “እርሱ ታላቅ ይሆናል፡፡ የልዑል ልጅም ይባላል፡፡ ጌታ አምላክም ያባቱን የዳዊትንም ዙፋን ይሰጠዋል፡፡ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሣል፡፡” (የሉቃስ ወንጌል 1÷32)


7. “ለአባቶቻችን እንደተነገረ ለአብራሃም እና ለዘሩ ለዘለዓለም ምህረት ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናው ረድቶአል፡፡” (የሉቃስ ወንጌል 1÷54-55)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


25


8. “እነሆም በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር፡፡” (የሉቃስ ወንጌል 2÷25)


9. “ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው፡፡” (ባዩ ማነው? ኢየሱስ) (የዮሐንስ ወንጌል 17÷6)


10. “(ኢየሱስም) እኔ እለምንሃለሁ፡፡ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 17÷9)


11. “ይህን እግዚአብሔር ለእስራኤል ንስሐን የኃጢዓትንም ስሪየት ይሰጥ ዘንድ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው፡፡” (የሐዋርያት ሥራ 5÷31)


12. “ከዚህም ሰው ዘር /ከዳዊት/ እግዚአብሔር እንደተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ፡፡” (የሐዋርያት ሥራ 13÷23)


ለምን እስራኤላዊ ነቢይ?


ስለ እስራኤል የተነገሩ በቂ ምክንያቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ከትንቢተ ሕዝቅኤል፣ ኢሳይያስ፣ እግዚአብሔር ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ ስሜ ከአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናል፤ ይላል፡፡


1. “እናንተም እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ፤ እናንተ ስሙን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ!” (ሚልክያስ 1÷5-6)


2. “ስሜ በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና ይላል፤ እግዚአብሔር” (ሚልኪያስ 1÷14)


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


26


3. “ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቷል ትውልድ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፡፡” (ኤርሚያስ 2÷30)


4. “በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፡፡” (ኤርሚያስ 33÷17)


5. “እስራኤል ሆይ ከአምላክ ተለይተህ አመንዝረሃልና እንደአሕዛብ ደስ አይበልህ፡፡ ይህ የሚያስረዳው አሕዛብ ከእግዚአብሔር መንገድ አልጠፋም ማለት ነው፡፡ እስራኤል ግን የጠፋ ሕዝብ በመሆኑ ከጥፋት ይገስጽ ዘንድ ኢየሱስ ተላከባቸው፡፡” (ሆሲህ 9÷1)


ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ፍሬ ሃሳቦች በመጠኑም ቢሆን ስለኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክት ለእስራኤል ወገን ብቻ መላክ እንዲሁም ደግሞ እስራኤላዉያን የተረገሙና በኃጢዓታቸው ወሰን ያለፉ፣ በዓለም ላይ ካሉት ሕዝቦች የተጣመሙ፣ በተዓምራዊ አፈጣጠር የተወለደው ኢየሱስ ቢላክባቸውም የኢየሱስን ነቢይነት ያልተቀበሉ መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡


ይህ በመሆኑም አላህ ((ሱብሓነሁ ወተዓላ) ) ከእስራኤል ሕዝቦች ፊቱን በማዞር ቃል ኪዳኑን ከእስማኤላዊ ዝርያ ጋር ለማድረግ በመወሰኑ ነቢዩ ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)) ከዓረቡ ምድር ሊነሱ ችለዋል፡፡ ይህንኑ የሚያረጋግጡ መልዕክቶችና ጥቅሶችን ወደ ፊት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት የምንመለከት ሆኖ አሁን እስራኤላዉያን በአላህ ((ሱብሓነሁ ወተዓላ) ) ዘንድ ምን እንደሚመስሉ ማወቁ ጠቃሚ ስለሆነ ይህንኑ እንመለከታለን፡፡





“እግዚአብሔር እንዲህ ይለል፡-- ‹‹ይህ ሕግ ከበፊቴ ቢወገድ


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


27


ይላል እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-- ሰማይ በላይ ቢከነዳ የምድርም መሠረት በታች ቢመረመር በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እጥላለሁ፡፡” ” ((ትንብተ ኤርምያስ 3131÷÷3636--3737) )


እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ከእስማኤላዉያን ጋር በሚጀምርበት ጊዜ እስራኤላዉያን የነቢዩ ዒሳንና የነቢዩ ሙሐመድን ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ) መልዕክቶች ተራ በተራ ስላልተቀበሉ ቀጥሎ የአላህ ሕግ ነቢያችን ሙሐመድ ((ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ) ከተላኩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘላለም ይቆያል ማለት ነው፡፡ እስራኤል ግን ዛሬም የሁለቱንም ነቢያት መልዕክቶች ያልተቀበለ ሕዝብ በመሆኑ ለዘላዓለም የተጣለ ሕዝብ መሆኑን በግልጽ ያስረዳል፡፡ የትንቢቱን ተግባራዊነት በእስራኤል የሁለት ነቢያትን መልዕክት አለመቀበል ይፋ ያደርገዋል፡፡





“ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፡-- ‹‹ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዓይናችንም ድንቅ ነው፡፡ የሚለውን ከቶ ከመጽሐፍ አላነበባችሁምን? ? ስለዚህ እላችኋለሁኝ፤ የእግዚአብሔር መንግስት ከናንተ ትወሰዳለች፤ ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች፤ በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፡፡” ” ((የማቴዎስ ወንጌል 2121÷÷4242) )


ይህም የሚያመለክተው የእግዚአብሔር መንግስት ከእስራኤል እጅ ተወስዶ ፍሬዋን ለሚያደርግ ለዓረብ ((ለእስማኤላዉያን ወገን) ) እንደሚሰጥ የሚያረጋግጥ ሲሆን ተገቢውን ትኩረት የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ ክርስቲያን ወገኖቻችን በሞት


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


28


ከመያዛቸው በፊት በተቻለ መጠን ጥናታቸውን ማስተካከል አለባቸው፡፡ አንዳንድ ሰባኪዎች ስብከታቸውን ሲያቀርቡ እራሱን እስራኤል አድርገዉ ያመነ ሰዉ በሙሉ መንፈሳዊ እስራኤል ሆኗል በማለት ነው፡፡ ዘሩ በሙሉ የተጣለና ለዘለዓለም የማይድን ከሆነ ወደ መንፈሳዊ እስራኤል የመለወጥ ትርፉ ምንድነው? ? ሀያሉ አምላክ ከእስራኤል ጋር ምን ጊዜም አልታረቅም፤ እስከዘላለም ድረስ እጥላቸለዋሁ እያለ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲያስተምር የኢስላም ትምህርትን ለመማር ልባቸው ስላልፈቀደ በያዙት መንገድ የሚገፉ ብዙዎች ናቸው፡፡


መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእስራኤልን ዘር ሁሉ ለዘለዓለም እጥላለሁ እያለ በሌላ መልኩ ደግሞ እዚያው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንግስተ ሰማያት ለ144,000 144,000 እስራኤላዉያን ብቻ ተዘጋጅቶ ሌሎች የሰው ዘሮች በሙሉ የሚቃጠሉ መሆኑን የሚገልጽ ከሆነ የመረጥነው ጎዳና ምን ያህል ቀጥተኛ ነው ብለን ህሊናችንን መጠየቅ አለብን፡፡


የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 77፡11--8 8 እና ምዕራፍ 9 9 በምናይበት ጊዜ በጣም ያስደነግጣል፤ ተስፋም ያስቆርጣል፡፡ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ አገላለፅ መሠረት ለመንግስት ሰማያት የታጩት አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ /144,000/ /144,000/ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ እነርሱም ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች //ነገዶች// ከእያንዳንዳቸው ደግሞ አሥራ ሁለት ሺህ //12,00012,000// ቁጥር ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡


ይኸውም ከእስራኤል ከመጀመሪያው ከአይሁዳ ነገድ 12,000 12,000 እስከ ብኒያም ነገድ 12,000 12,000 ሲሆን ስሌቱም 12 12 ነገድ x x 12,000 = 144,000 12,000 = 144,000 የእግዚአብሔር ማህተም በግንባራቸው


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ


29


ይታተምባቸውና ሌሎች የሰዉ ዘሮች በሙሉ ይቃጠላሉ ይባላል፡፡ ይህንን የሚተነትነው የዮሐንስ ራዕይ 99 ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡


1/


1/ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ለመንግስተ ሰማያት የሚመረጡት ከ12,000 12,000 ሊበልጡና ሊያንሱ ያለመቻላቸው 12,000+1 12,000+1 ወይንም 12,00012,000--1 1 አለመሆናቸው እራሱ ሌላ ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ኮታው ቀድሞ ከታወቀና ለ1212ቱ የእስራኤል ነገዶች በእኩል ከተከፋፈለ የሌላው ድካም ሁሉ ያለ ውጤት መና ይቀራል ለማለት ያስደፍራል፡፡


2/


2/ እስራኤላዉያን እስከ ዛሬ የሚተዳደሩት በሙሴ //ዓለይሂ ሰላም// ሕግጋቶች ሆኖ የኢየሱስን ነቢይነት እንኳን ሳይቀበሉ እንዴት መንግስተ ሰማያት እንደሚገቡ ፍፁም አጠያያቂ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ምናልባት መንግስተ ሰማያት መጀመሪያውኑ ለእስራኤል ልጆች ሽልማት የተዘጋጀች ይመስላል፡፡ ሚስጥሩን የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባኪዎች ይፍቱት እንጂ መልሱ እንዲያው ዝም ነው፡፡ ትውልድ በሙሉ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡


ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው ሁሉ አይሁዶችና ነሳራዎች መንግስተ ሰማያትን በግላቸው የተቆጣጠሩ ይመስላል፡፡ ፈጣሪ በግል የሚያዝ ሳይሆን የዓለማት ጌታ ነዉ፡፡


መንግስተ ሰማያት ደግሞ የንጹሃን ናት እንጂ የአንድ ጎሳ ብቻ አይደለችም፡፡ ሁለቱም እንዲህ ሲሉ ራሳቸውን እንደሚያሞካሹ ቁርአን ግልፅ አድርጎታል፡፡ አላህ ((ሱብሃነሁ ወተዓላ)) እንዲህ ይላል፡--





“እኛ የአላህ ልጆቹና ምርጦቹ ነን” ” አሉ፡፡ በል፡-- ““ለምንስ በወንጀላችሁ ይቀጣችኋል??” ” ((አል--ማኢዳህ 55÷÷1818) )


ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ

ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ...

ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ማስገባት እና የፈጠራዉ አደጋ