መጣጥፎች

 ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረው ማን ነው?


 እኔንስ የፈጠረኝ ማን ነው?


 ለምንስ ፈጠረኝ?





 በመስጂደል ሐረም እና በመስጂድ አን-ነበዊይ


 በሃይማኖት ዘርፍ የዕውቀት ነክ ጉዳዮች ርዕሰ


 መስተዳድር ኮሚቴ ያዘጋጀው





 ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረው ማን


ነው? እኔንስ የፈጠረኝ ማን ነው?


ለምንስ ፈጠረኝ?





 በመስጂደል ሐረም እና በመስጂድ አን-ነበዊይ


በሃይማኖት ዘርፍ የዕውቀት ነክ ጉዳዮች ርዕሰ


መስተዳድር ኮሚቴ ያዘጋጀው





ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረው ማን ነው?


እኔንስ የፈጠረኝ ማን ነው? ለምንስ ፈጠረኝ?


በትክክለኛ መንገድ ላይ ነኝን?


ሰማያትንና ምድርን፣ በውስጣቸውም ያለውን ማንም


ሊያካብባቸው የማይቻሉ የሆኑትን ትላልቅ ፍጡራንን


የፈጠራቸው ማን ነው?


ይህን በሰማያትና ምድር ውስጥ ያለውን የረቀቀና


አስተማማኝ የሆነውን ስርዓት የዘረጋው ማን ነው?


የሰው ልጅን የፈጠረው ማን ነው፤ መስሚያ፣


መመልከቻና አይምሮ ለግሶ፤ እውቀትን በመፈለግ እውነታ


ላይ እንዲደርስ ያስቻለውስ ማን ነው?


የሰውነት ክፍሎችህን በዚህ ረቂቅ በሆነ አሰራር የፈጠረና


አሳምሮ የቀረፀህ ማን ነው?


ህያው ፍጥረታት ከመለያየታቸውና ከመበርከታቸውም


ጋር እስኪ አፈጣጠራቸውን አስተውል! ገደብ የለሽ በሆነ


መገለጫዎቻቸው የፈጠራቸው ማን ነው?


ይህ ታላቅ አጽናፈ ዓለም በረቀቀ ስርዓት በሚቆጣጠረው


መርህ ስር እንዴት ለዚህ ሁሉ ዓመታት ወጥ እና የተረጋጋ


ሊሆን ቻለ?


ይህን ዓለም የሚገዙትን ሥርዓቶች (ሕይወትና ሞትን፣


2


የሕያዋን መባዛት፣ ቀንና ሌሊት፣ የወቅት ለውጥ ወዘተ) ማን


ነው ያቋቋመው?


ይህ አጽናፈ አለም ራሱን ፈጥሮ ነው? ወይስ ካለመኖር


ወደ መኖር የመጣ ነገር ነው? ወይስ በአጋጣሚ የተገኘ ነው?


አላህ እንዲህ ብሏል:-





 {ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነሱ


ፈጣሪዎች ናቸውን?


ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም


አያረጋግጡም።}


[አጥጡር: 35 - 36]


ራሳችንን በራሳችን ካልፈጠርን ካለመኖር ወይም


በአጋጣሚ ያለፈጣሪ መጥተናል ማለትም ከቶ የማይሆን


ነገር ነው። ስለዚህ ጥርጥር የሌለው እውነታ:- ይህ አጽናፈ


ዐለም የግድ ታላቅና ቻይ የሆነ ፈጣሪ አለው የሚለው ነው።


ምክንያቱም ይህ አጽናፈ አለም ራሱን በራሱ ፈጥሯል


ወይም ካለመኖር (ከምንምነት) ነው ዝም ብሎ የመጣው


ወይም በአጋጣሚ ነው የመጣው ማለት ከቶ የማይሆን


ስለሆነ ነው።


የሰው ልጅ የማያያቸው ነገሮች መኖራቸውን


የሚያምነው ለምንድን ነው? ለምሳሌ:- (ማወቅ፣ አይምሮ፣


ነፍስ፣ ስሜት፣ ፍቅር) ተፅእኗቸውን ስለሚያይ አይደለምን?


3


ታዲያ እንዴት የሰው ልጅ የፍጡራኑን፣ የስራዎቹንና


የእዝነቱን ተጽእኖ ምድር ላይ እያየ የዚህን ታላቅ አጽናፈ


ዐለም ፈጣሪ መኖርን ይክዳል?


አንድም ጤነኛ ሰው "ይህ ቤት የመጣው በራሱ


ያለምንም ገንቢ ነው" ቢባል ወይም "ይህንን ቤት ህልውና


የሰጠው ህልውና የሌለው ነገር ነው" ቢባል


እንደማይቀበለው ሁሉ ታዲያ እንዴት አንዳንድ ሰዎች "ይህ


ታላቅ አጽናፈ ዐለም ያለፈጣሪ ነው የመጣው" የሚልን ሰው


ያምናሉ? እንዴትስ አንድ ጤነኛ ሰው "የዚህ አጽናፈ አለም


የረቀቀ ስርዓት በአጋጣሚ ነው የመጣው" ሲባል ይቀበላል?


ይህ ሁሉ ወደ አንድ ውጤት ይመራናል። እርሱም ይህ


አጽናፈ ዐለም ታላቅ ጌታ፣ ቻይና አስተናባሪ እንዳለው፤


እርሱም ብቻውን ለአምልኮ የተገባ እንደሆነ፤ ከርሱ ውጪ


የሚመለኩ ሁሉ አምልኳቸው ከንቱ መሆኑንና


ለመመለክም የማይገባቸው እንደሆኑ ነው።


ታላቁ ጌታና ፈጣሪ


አንድ ፈጣሪና ጌታ ነው ያለው። ለሁሉም ንጉሱ፣


አስተናባሪው፣ ሲሳይን ሰጪው፣ ህያው የሚያደርገውም


የሚገድለውም እርሱ ነው። ምድርን የፈጠረና ያገራት፣


ለፍጡራኑም ምቹ ያደረጋት እርሱ ነው። እርሱም


ሰማያትንና በውስጧ ያሉትን ትላልቅ ፍጡራን የፈጠረ ነው፤


ፀሃይን፣ ጨረቃን፣ ምሽትና ቀንንም በዚህ ወጥና ረቂቅ


ስርዓት መሰረት ማድረጉም የርሱን ታላቅነት የሚጠቁም


4


ነው።


እርሱም ለኛ ያለርሱ ህይወት የሌለንን አየርን ያገራልን፤


በኛ ላይ ዝናቦችን ያወረደልን፤ ወንዞችና ውቅያኖሶችን


ያገራልን፤ ለኛ ምንም አቅም ባልነበረን በናቶቻችን ሆድ


ውስጥ ፅንስ በነበርን ወቅት የሚጠብቀን፣ የሚቀልበንና


ከውልደታችን ጀምሮ እስከምንሞት ድረስ በደም ስሮቻችን


ደምን ያዘዋወረልን ነው።


ይሀው ጌታ፣ ፈጣሪና ሲሳይ ሰጪ አላህ ሱብሓነሁ


ወተዓላ ነው።


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ


የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም (ለክብሩ በሚስማማ መልኩ)


በዐርሹ ላይ ከፍ አለ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ


የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም


ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ!


መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ


(ክብሩ) ላቀ፡፡}


[አልአዕራፍ:54]


በአጽናፈ አለም ውስጥ የሚገኙ የምናያቸውንም ሆነ


5


የማናያቸውን ነገሮች ሁሉ የፈጠራቸው ጌታችን አሏህ ነው።


ከርሱ ውጪ ያሉት ነገሮች ባጠቃላይ የርሱ ፍጡሮች ናቸው።


እርሱ ብቻ ነው አምልኮ የሚገባው። ከርሱ ጋርም ከርሱ


ውጪ ያለን አንድንም አካል ማምለክ አይፈቀድም።


በንግስናው ወይም በመፍጠሩ ወይም በማስተናበሩ ወይም


በመመለክ ለርሱ አጋር የለውም።


እንዲሁ ለሙግት ያህል ግርማው ከላቀው ጌታችን ውጪ


ሌሎች አማልክቶች አሉ ብለን ብንወስድ እንኳ አጽናፈ


አለሙ ይበላሽ ነበር። ምክንያቱም ሁለት አማልክቶች


የአጽናፈ አለምን ጉዳይ በአንድ ጊዜ ማስተናበራቸው


የማይሆን ነገር ነውና። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ


ብሏል:





 {በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ


አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር።}


አልአንቢያእ: 22


የጌታችን አሏህ ባህሪያት


ጥራት የተገባው ጌታ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ውብ ስሞች


አሉት፤ ለርሱም ምሉእነቱን የሚጠቁሙ ትላልቅና በርካታ


የላቁ ባህሪያት አሉት። ከስሞቹም መካከል:- "አልኻሊቅ"


(ትርጉሙም: ፈጣሪ)፣ "አላህ" ትርጉሙም አምልኮ ለርሱ


ብቻ የተገባው አምላክ፣ አጋርም የሌለው ማለት ነው፤


"አልሐይ" (ህያው)፣ "አልቀይዩም" (በራሱ የቆመ)፣


6


"አርረሒም" (አዛኝ)፣ "አርራዚቅ" (ሲሳይ ሰጪ)፣ "አልከሪም"


(ቸር) የሚሉት ይገኙበታል።


የላቀው አላህ በተከበረው ቁርኣን እንዲህ ብሏል:


 َ


 {አላህ ከእርሱ በቀር እውንተኛ አምላክ የለም፡፡ ሕያው


ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አይዘውም፡፡


በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ


ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ


ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው


ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ


በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ


ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡


እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡}


[ሱረቱል በቀራህ: 255]


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡


"አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡





«አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡


«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»}


[አልኢኽላስ 1-4]


ተመላኪው ጌታ በምሉዕ ባህሪያት የሚገለፅ


ነው።


ከባህሪያቶቹ መካከልም እርሱ የሚመለክና የሚገዙት


ነው። ከርሱ ውጪ ያሉ ፍጡራን፣ ታዛዦች፣ የበታቾችና


ትእዛዙን ለመፈፀም ያጎበደዱ ናቸው።


ከባህሪያቶቹ መካከልም እርሱ ህያውና በራሱ የቆመ


መሆኑ ተጠቃሽ ነው። በአለም ላይ የሚገኙትን ሁሉም


ህይወት ያላቸውን ነገሮች ህይወት የሰጣቸውና ከምንም


ያስገኛቸው አላህ ነው።   


እንዲኖር በማድረግ፣ ሲሳዩን በመስጠትና እርሱን


በመጠበቅ ላይ የቆመውም እርሱ ነው። ጌታ ህያውና


የማይሞት ነው። የእርሱ መጥፋትም ፈፅሞ የማይታሰብ


ነገር ነው። በራሱ የቆመና የማይተኛም ነው። ማንቀላፋትና


እንቅልፍም አይዘውም።


ከባህሪያቶቹ መካከልም በምድርም ሆነ በሰማይ ውስጥ


አንዳችም የማይደበቅበት ሁሉን አዋቂ ነው።


ከባህሪያቶቹ መካከልም አላህ ሁሉንም ነገር የሚሰማና


ሁሉን ፍጡር የሚመለከት ሰሚና ተመልካች ነው። ነፍሶች


የሚጎተጉቱትን ነገርና ልብ የምትደብቀውንም ያውቃል።


8


በምድርም ሆነ በሰማይ ውስጥ አንዳችም ነገር ከርሱ


አይደበቅም።


ከአላህ ባህሪያቶች መካከል እርሱ አንዳችም


የማያቅተው፣ አንድም አካል ፈቃዱን የማይመልስበት ቻይ


ነው። በወሰን የለሽ ጥበቡ የሻውን ይፈፅማል የሻውን


ይከለክላል፤ ያስቀድማል ወደኋላ ያስቀራል።


ከአላህ ባህሪያቶች መካከልም እርሱ ፍጡራንን ፈጥሮ


የሚያስተናብር ፈጣሪ፣ ሲሳይ ሰጪና አስተናባሪ ነው።


ፍጡራንም በርሱ ቁጥጥርና በስልጣኑ ስር ናቸው።


ከአላህ ባህሪያቶች መካከልም እርሱ የባለ ከባድ ጭንቀት


ልመናን የሚቀበል፣ ተበዳይን የሚረዳ፣ ችግርን የሚገላግል


ነው። ሁሉም ፍጡር ችግር ውስጥ የወደቀ ወይም ነገሮች


የጠበቡበት ጊዜ ወደርሱ ተገዶ የሚጠጋው ወደርሱ ነው።


አምልኮ ለአላህ ካልሆነ በቀር ለማንም አትሆንም። አላህ


ብቻ ነው ሙሉ ለሙሉ ለአምልኮ የተገባው፤ ከርሱ ውጪ


የተመለከ ነገር ባጠቃላይ በከንቱ የተመለከ፣ ለሞትና


ለመጥፋትም የተጋለጠ ጎዶሎ ነው።


አላህ የርሱን ታላቅነት የምናውቅበትን አይምሮ


ሰጥቶናል፤ መልካምን እንድንወድና ክፋትን እንድንጠላ


የምታደርግና ወደ አለማቱ ጌታ አላህ የተጠጋች ጊዜ


የምትረጋጋን ተፈጥሮ በኛ ውስጥ አስርጿል። ይህቺ ተፈጥሮ


የርሱን ምሉዕነት ትጠቁማለች። አላህ በጉድለት ሊገለፅ


ፈፅሞ አይቻልም።


9


አንድ ጤነኛ አይምሮ ያለው ሰው ምሉዕ ከሆነው አምላክ


ውጪ ማምለክ አይገባውም። እንዴት እንደርሱ አምሳያ


ጉድለት ያለበትን ወይም ከርሱ በታች የሆነን ፍጡር


ያመልካል?


ሰው፣ ጣዖት፣ ዛፍና እንስሳ በፍፁም አምላክ ሊሆኑ


አይችሉም።


ጌታ ከሰማያቱ በላይ ነው። ከዐርሹ በላይም ከፍ ብሏል፤


ከፍጡራኑ ተነጥሏል። በርሱ ዛት ላይ አንዳችም ፍጡር


የለም፤ በፍጡራኖቹ ላይም የርሱ ዛት ምንም የለም።


በአንድም ፍጡሩ ላይ አይሰፍርም አይሰርፅምም።


ጌታ እርሱን የሚመስል አንዳችም የለም ፤ እርሱም


ሰሚና ተመልካች ነው። ለርሱም አንድም ቢጤ የለውም፤


እርሱም ከፍጡራኑ የተብቃቃ ነው፤ አይተኛምም ምግብም


አይመገብም፤ አላህ ሚስት ወይም ልጅ ሊኖረው የማይገባ


የላቀ ነው፤ ፈጣሪ በፈላጊነት ወይም በጉድለት ባህሪ ፈፅሞ


በማይገለፅበት ሁኔታ ለርሱ የልቅና ባህርያት አሉት።


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለፀላችሁ።


ለእርሱም አድምጡት። እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው


(ጣዖታት) ዝንብን ፈፅሞ አይፈጥሩም። እርሱን  


10


(ለመፍጠር)  ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም)። አንዳችንም


ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም። ፈላጊውም


ተፈላጊውም ደከሙ።


አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም። አላህ በጣም ኀያል


አሸናፊ ነው።}


[አልሐጅ: 73-74]


ይህ ታላቅ ፈጣሪ ለምንድን ነው የፈጠረን? ከኛስ


ምንድን ነው የሚፈልገው?


አላህ ይህን ሁሉ ፍጡራን ያለአላማ ነው የፈጠረው


ተብሎ ይታመናልን? እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ሆኖ ሳለ


ለጨዋታ ይፈጥራቸዋልን?


እንዲህ ባለ ወጥና ፍፁምነት የፈጠረን በሰማያትና


በምድር ያለውን ሁሉ ያስገዛልን ያለ ዓላማ ሊፈጥረን


ይችላል ተብሎ ይታሰባልን? ወይስ እኛን የጠመዱንን


አንገብጋቢ ጥያቄዎች ሳይመልስ ሊተወን ይችላልን?


ለምሳሌ: እኛ ለምንድነው እዚህ አለም ላይ ያለነው? ከሞት


በኋላ ምንድነው ያለው? የመፈጠራችን አላማስ ምንድን


ነው?


ለግፈኛ ቅጣት የለም ለበጎ ሰሪም ምንዳ የለውም ማለት


ያስኬዳልን?


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





{«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ


የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ


የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)}


[አል-ሙእሚኑን: 115]


እንደውም አላህ የመኖራችንን አላማ እንድናውቅ


መልክተኞችን ልኳል፤ እንዴት እንደምናመልከውና ወደርሱ


እንዴት እንደምንቃረብ፤ ከኛ ምንድነው የሚፈልገው?


እንዴት ነው ውዴታውን የምናገኘው? የሚለውን


ጠቁሞናል። ከሞት በኋላ ስላለው መመለሻችንም ነግሮናል።


አላህ ብቻ ለአምልኮ የተገባ እንደሆነ ሊነግሩን፣ እንዴት


እንደምናመልከው እንድናውቅ፣ ትእዛዙንና ክልከላውንም


ሊያደርሱን፣ እርሷን ከያዝን ህይወታችን ምርጥ


የምትሆንበትን መልካምና በረከት የሚያካብበንን በላጭና


ቀጥ ያለ እውቀት እንዲያስተምሩን መልክተኞችን ልኳል።


አላህ በርካታ መልክተኞችን ልኳል፤ ለምሳሌ (ኑሕ፣


ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳ) ፣ እውነተኝነታቸውንና እነርሱ


ከአላህ ዘንድ የተላኩ መሆናቸውን በሚጠቁሙ ተአምራትና


ምልክቶችም አጠናክሯቸዋል። የመጨረሻው መልክተኛም


ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም


በእርሳቸው ላይ ይስፈን ናቸው።


መልክተኞች ፍንትው ባለ መልኩ ይህ ህይወት የፈተና


ህይወት መሆኑንና ትክክለኛውም ህይወት ከሞት በኋላ


መሆኑን ነግረውናል።


12


በመጪው አለምም አላህ ላይ ምንንም ሳያጋሩ


በብቸኝነት ላመለኩ በሁሉም መልክተኞችም ላመኑ


አማኞች ጀነት እንዳለ፤ እንዲሁም ከአላህ ጋር ሌላ


አማልክትን ላመለኩ ወይም ከአላህ መልክተኞች መካከል


በማንኛውም መልክተኛ ለካዱ ከሀዲያንም አላህ እሳትን


እንዳዘጋጀ ነግረውናል።


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {የአዳም ልጆች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ በናንተ ላይ


አንቀጾቼን የሚያነቡ መልክተኞች ቢመጧችሁ ከእናንተ


ክሕደትን የተጠነቀቁና መልካምንም የሠሩ በነሱ ላይ ፍርሃት


የለባቸውም፡፡ እነሱም አያዝኑም፡፡ (35)


እነዚያም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ


እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች


ናቸው፡፡}


[አል-አዕራፍ፡ 35-36]


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ


በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን)


ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (21)


(እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ


ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም


ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም


(ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን


አታድርጉ፡፡ (22)


በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ


ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ፡፡


እውነተኞችም እንደኾናችሁ ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን


ጥሩ፡፡ (23)


(ይህንን) ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን


መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤


ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡ (24)


እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ


ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው


14


መኾኑን አብስራቸው፡፡ ከርሷ ከፍሬ (ዓይነት) ሲሳይን


በተመገቡ ቁጥር (ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ) «ይህ ያ ከአሁን


በፊት የተመገብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ


ተሰጡት፡፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች


አሏቸው፡፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡}


[አልበቀራህ: 21-25]


መልክተኞች የበዙበት ምክንያት ምንድን ነው?


በርግጥም አላህ ወደ ሁሉም ህዝቦች መልክተኞችን


ልኳል። እያንዳንዱ ህዝብ ጌታቸውን ወደማምለክ


የሚጠሯቸው፣ ትእዛዙንና ክልከላውን የሚያደርሷቸው


አላህ መልክተኞችን የላከላቸው ናቸው። የመልክተኞች


ባጠቃላይ ጥሪ አላማም አላህን በብቸኝነት ወደ ማምለክ


ነበር። የሆነ ህዝብ መልክተኛቸው ይዞት የመጣውን ወደ


አላህ አሃዳዊነት ማዘዝን መተው ወይም ማጥላላት ሲጀምር


አላህ መንገዱን እንዲያርሙላቸው፣ አላህን በመነጠልና


በመታዘዝ ሰዎች ወደ ንፁህ ተፈጥሮ እንዲመለሱ ሌላ


መልክተኛን ይልካል።


ይህም የተሟላ ሃይማኖትና እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ


ለሁሉም የሰው ዘር የሚያዳርስና ዘውታሪ፣ ያለፈውን ሸሪዓ


የሚሽርና የሚያሟላ ሸሪዓ ይዘው በመጡት በሙሐመድ


(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው


ላይ ይስፈንና መልክተኞችን እስኪደመድም ድረስ ቀጥሏል።


ግርማው የላቀው ጌታ አላህ ይህ ሃይማኖት እስከ ትንሳኤ ቀን


15


እንደሚቆይና እንደሚዘወትር ቃል ገብቷል።


አንድ ግለሰብ በሁሉም መልክተኞች ካላመነ


አማኝ አይሆንም።


መልክተኞችን የላከው፣ ፍጡራኑንም ባጠቃላይ እነሱን


እንዲታዘዙ ያዘዘው አሏህ ነው። ከነዚህ መልክተኞች መካከል


በአንዱ መልክተኝነት የካደ ሰው በሁሉም ክዷል። ሰው


የአላህን ራዕይ ከመመለስ የባሰ ወንጀል የለውም። ስለሆነም


ጀነት ለመግባት በመልክተኞች ባጠቃላይ ማመን ግዴታ


ነው።


በዚህ ዘመን በያንዳንዱ ሰው ላይ ያለበት ግዴታ በሁሉም


የአላህ መልክተኞችና በመጨረሻው ቀን ማመን ነው። ይህም


የመጨረሻውና መደምደሚያ በሆኑት፣ ዘውታሪ በሆነው


ተአምር በታገዙት ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)


የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በማመንና


በመከተል ካልሆነ በቀር አይረጋገጥም። ለርሳቸው የተሰጠው


ተአምርም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም መፅሀፍ አላህ


ምድርንና በውስጧ ያለውን እስኪወርስ ድረስ


እንደሚጠብቀው ቃል ገብቷል።


አላህ በተከበረው ቁርአን ውስጥ ከመልክተኞቹ መካከል


በማንኛውም መልክተኛ ከማመን እምቢተኛ የሆነ ሰው


በአላህ የካደ፣ ራዕዩንም ያስተባበለ መሆኑን ጠቅሷል። አላህ


ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:-





 {እነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ የሚክዱ፣ በአላህና


በመልክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉ፣ «በከፊሉም


እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን» የሚሉ፣ በዚህም መካከል


መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፤ (150)


እነዚያ በውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ ለከሓዲዎችም


አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል፡፡}


[አን-ኒሳእ: 150-151]


ስለዚህም እኛ ሙስሊሞች አላህ ባዘዘው መልኩ በአላህና


በመጨረሻው ቀን እናምናለን። በሁሉም መልክተኞችና


ባለፉት መፅሀፍቶችም እናምናለን። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ


እንዲህ ብሏል:





 5


 {መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡


ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣


በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም


መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤


ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡


መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም፡}


17


[አልበቀራህ: 285]


የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?


የተከበረው ቁርአን አላህ በመጨረሻው መልክተኛ


ሙሐመድ ላይ ያወረደው የአላህ ንግግርና ራዕዩ ነው።  


ቁርአን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና


ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነቢይነት የሚጠቁም ትልቁ


ተዐምር ነው። የተከበረው ቁርአን በህግጋቶቹ እውነተኛ


በሚናገራቸው ንግግሮችም ታማኝ የሆነ መፅሀፍ ነው።


አላህ ከሓዲዎችን የቁርአንን ብጤ አንዲት ምዕራፍ እንኳ


እንዲያመጡ ተገዳደራቸው። ግን አልቻሉም። ይህም በዚህ


ህይወትም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ከሰው ጋር ተያያዥ


የሆኑን ነገሮች ሁሉ ያካተተ ታላቅ እና ይዘቱ አካታች ስለሆነ


ነው። ሊታመኑባቸው ግዴታ የሆኑን የእምነት እውነቶችን


ሁሉ አካትቷል።


በተጨማሪም አንድ ሰው በራሱ እና በጌታው መካከል


ወይም በእሱ እና በራሱ መካከል ወይም በእሱ እና በሌሎች


ፍጥረታት መካከል ሊከተላቸው የሚገቡትን ትእዛዛት እና


ክልከላዎች አካትቷል። ይህ ሁሉ ደግሞ በከፍተኛ


የማብራራት እና የመግለፅ ዘይቤ ነው።


ቁርአን በሰዎች ሊፈጠር እንደማይችል ይልቁንም የሰው


ልጅ ጌታ ከሆነው አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የተወረደ ቃል


መሆኑን የሚያሳዩ በርካታ ሎጂካዊ ማስረጃዎችን እና


ሳይንሳዊ እውነታዎችን አካትቷል።


18


እስልምና ምንድን ነው?


እስልምና ማለት በተውሒድ ለአላህ እጅ መስጠት፣ ለርሱ


በትእዛዙ መመራት፣ በውዴታና በመቀበል ሸሪዓውን


መተግበር፣ ከአላህ ውጭ በሚመለኩ ነገሮችም ሁሉ መካድ


ማለት ነው።


በርግጥም አላህ መልክተኞችን በአንድ መልዕክት ላከ


እርሱም፡ ያለ አጋር አላህን በብቸኝነት አምልኩ በሚል እና


ከአላህ ሌላ የሚመለኩትን ሁሉ እንዲክዱ ጥሪ አድርጉ


የሚል መልዕክት ነው።


እስልምና የነቢያቶች ባጠቃላይ ሃይማኖት ነው።


ነቢያቶች ጥሪያቸው አንድ ሲሆን ድንጋጌያቸው ግን የተለያየ


ነው። ዛሬ ላይ ያሉ ሙስሊሞች ነቢያቶች ባጠቃላይ ይዘውት


የመጡትን ትክክለኛውን ሃይማኖት የሚከተሉ ብቸኞች


ናቸው። በዚህ ዘመን ያለው የኢስላም መልዕክት ትክክለኛና


ከሰው ዘር ፈጣሪ የወረደ መደምደሚያ መለኮታዊ


መልዕክት ነው።


ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳን የላከዉ ጌታ


የመጨረሻውን መልእክተኛ ሙሐመድንም (ሶለላሁ ዓለይሂ


ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና


የላከዉ እርሱው ነው። የእስልምና ሸሪዓ የመጣውም ከሱ


በፊት የነበሩትን ሸሪዓዎች የሚሽር ሆኖ ነው።


በአሁኑ ጊዜ ከእስልምና በቀር ሰዎች የሚከተሏቸው


ሃይማኖቶች ሁሉ በሰዎች የተፈበረኩ ሃይማኖቶች ወይም


19


መለኮታዊ የነበሩና ከዚያም የሰው እጅ የተጫወተባቸው


የአፈ ታሪክ ጥርቅም፣ የተወራረሱ ታሪኮች እና የሰው ልጅ


አመለካከት ድብልቅ የሆኑ ሃይማኖቶች ናቸው።


የሙስሊሞች ሀይማኖት ግን አላህን የሚያመልኩበት


አምልኮ አንድ እንደሆነ ሁሉ ሃይማኖታቸውም የማይለወጥ


ግልፅና አንድ ሀይማኖት ነው። ሁሉም አምስቱን ሰላት


ይሰግዳሉ ፣በሀብታቸው ዘካን ይሰጣሉ ፣ የረመዳንን ወር


ይፆማሉ። ስለሚከተሉት ህግ ስታስተነትንም የተከበረው


ቁርኣን ነው። ቁርአንም በሁሉም ሀገራት አንድ አይነት


መጽሃፍ ነው። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም


በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት


በኩል ወደድኩ። በረሀብ ወቅት ወደ ሀጢዐት ያዘነበለ


ሳይሆን (እርም የሆኑትን ለመብላት) የተገደደ ሰውም


(ይብላ)። አላህ መሀሪ አዛኝ ነውና።}


[አል-ማኢዳህ: 3]


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ብሏል:





 {"በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም (በቁርኣን)፣


በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣


በነገዶችም ላይ በተወረደው፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም


ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው (አመንን)፡፡ ከእነርሱ መካከል


አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ (84)


{ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ


ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም


ከከሳሪዎቹ ነው፡፡}


[አሊ-ዒምራን፡ 84-85]


የእስልምና ሀይማኖት የህይወት መስክን ጠቅልሎ


ያቀፈን መንገድ የያዘ፤ ከጤናማ አስተሳሰብ እና


ምክንያታዊነት ጋር የሚጣጣም፤ የተስተካከሉ ነፍሶች ዘንድ


ተቀባይነት ያለው ነው። ይህም ታላቁ ፈጣሪ ለፍጥረታቱ


የደነገገው ሃይማኖት ሲሆን ለሰዎች ባጠቃላይ በዚህ አለም


ላይም ይሁን ለመጪው አለም የመልካም እና የደስታ


ምንጭ የሆነ ሀይማኖት ነው። እስልምና አንዱን ዘር ከሌላው


አይለይም፤ አንዱንም ቀለም ከሌላው አይለይም፤


በውስጧም ሰዎች እኩል ናቸው፤ በእስልምና አንድን ሰው


ከሌላው በመልካም ሥራው መጠን ልክ ካልሆነ በቀር


አያበላልጥም።


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 7


 {ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ


መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት


ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡}


[አንነህል:97]


እስልምና የደስታ ጎዳና ነው።


እስልምና የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው። ለሁሉም ሰው


የተደነገገ የአላህ ሃይማኖት እንጂ አረቦች ለብቻቸው


የሚለዩበት ሀይማኖት አይደለም።


እስልምና በዚህ ዓለም ውስጥ እውነተኛ ደስታን


የሚያመጣ እና ከሞት በኋላ ባለው ዓለም ደግሞ ዘላለማዊ


ፀጋን የሚያመጣ መንገድ ነው።


እስልምና የነፍስንና የሥጋን ፍላጎቶች የሚያሟላና


ሁሉንም የሰው ልጅ ችግሮች የሚፈታ ብቸኛ ሃይማኖት


ነው። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል





 {አላቸው «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ሁላችሁም


ከእርሷ ውረዱ ከእኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪዬን


የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡ (123)


ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው።


22


በትንሣኤም ቀን ዕውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን።"}


[ጣሀ: 123-124]


አንድ ሙስሊም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም


ምን ይጠቀማል?


እስልምና ትላልቅ ጥቅሞች አሉት? ከነዚህም መካከል:


የአሏህ ባርያ በመሆኑ በዚህ ዓለም ውስጥ ስኬት እና


ክብርን ያጎናፅፈዋል። የአላህ ባሪያ ካልሆነ ግን


የስሜታዊነት፣ የሰይጣን እና የፍላጎቱ ባሪያ ነው የሚሆነው።


በመጪው ዓለምም የአላህን ምህረት በማግኘት፣ የአላህ


ውዴታ ይሰፍርበታል፣ አላህ ጀነት ውስጥ ያስገባዋል፣


ዘላለማዊ ውዴታ እና ፀጋን ያገኝበታል፣ ሰውዬውም


ከጀሀነም ስቃይ ድኖ ስኬታማ ይሆናል።


ሙእሚን በትንሣኤ ቀን ከነቢያት፣ ከእውነተኞች፣


ከሰማዕታትና ከጻድቃን ጋር ይሆናል። ምንኛ ጣፋጭ


አጋርነት ነው! ያላመነ ሰው ደግሞ ከጣዖቶች፣ ከክፉዎች እና


ከወንጀለኞች ጋር ነው የሚሆነው።


አላህ ጀነት ያስገባቸው ሰዎች ደግሞ ሞት፣ ህመም፣


ስቃይ፣ እርጅና እና ሀዘን በሌለበት ዘላለማዊ ደስታ ይኖራሉ፤


የፈለጉትን ምኞታቸውንም ሁሉ ይሰጣቸዋል። ጀሀነም


የሚገቡት ደግሞ በማይቋረጥ ዘላለማዊ ስቃይ ውስጥ


ይሆናሉ።


በጀነት ውስጥ ዓይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ የሰው





 ልጅ አይምሮ ውል ብሎ የማያውቅ ተድላ አለ። የዚህም


ማስረጃ ይህ የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ንግግር ነው:





 {ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ


መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት


ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡}


(አንነህል 97)


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል:





 {ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ


ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ


አታውቅም፡፡}


[አስ-ሰጅዳህ: 17]


ሙስሊም ያልሆነ ሰው ምን ይከስራል?


ሰው እስልምናን ካልተቀበለ ትልቁን እውቀት ይከስራል።


ይህም አላህን ማወቅ እና ስለርሱ መገንዘብ ነው።  በዚህ


ዓለም ውስጥ ደህንነት እና መረጋጋትን የሚሰጠውንና


በመጪው አለም ውስጥ ደግሞ ዘላለማዊ ደስታን


የሚሰጠውን በአላህ ማመንንም ይከስራል።


አላህ ለሰዎች ያወረደውን ታላቁን መጽሐፍ ከማንበብ


እና በዚህ ታላቅ መጽሐፍ ላይ ያለውን ከማመንም


24


ይከስራል።


በትላልቅ ነቢያት ማመንንም ይከስራል። ልክ እንደዚሁ


በትንሳኤ ቀን ጀነት ውስጥ ትላልቅ ነቢያቶችን መጎዳኘትንም


ይከስራል። ከሰይጣናት፣ ከወንጀለኞች እና ከጣዖቶች ጋር


በመጎዳኘት በገሀነም እሳት ውስጥ ይሆናል። መኖሪያውና


ማረፊያውም ምን የከፋ ነው!


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {"ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሳኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና


ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልፅ ኪሳራ


ነው።" በላቸው። (15)


ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የኾኑ (ድርብርብ) ጥላዎች


አልሏቸው፡፡ ከበታቻቸውም ጥላዎች አልሏቸው። ይህ አላህ


ባሮቹን (እንዲጠነቀቁ) በእርሱ ያስፈራራበታል፡፡ «ባሮቼ


ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ፡፡»}


[አዝ-ዙመር፡ 15-16]


በመጪው አለም ለመዳን የሚፈልግ ሰው


እስልምናን ተቀብሎ ለአላህ ታዛዥ መሆንና ነቢዩ


ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ


ይስፈንና) መከተል ይኖርበታል።


25


ነብያትና መልእክተኞች (ዐለይሂም ሶላት ወሰለም) የአላህ


ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና  ከተስማሙባቸው


እውነታዎች አንዱ በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ያመኑ፣


ማንንም በርሱ ላይ በአምልኮ ያላጋሩ፣ በነቢያትና


በመልእክተኞች ሁሉ ያመኑ ሙስሊሞች ካልሆኑ በቀር


ማንም በመጪው አለም የማይድን መሆኑን ነው።


የመልክተኞች ተከታዮች፣ በነርሱ ያመኑና የነርሱን መልዕክት


እውነት ያሉ በሙሉ ጀነት ይገባሉ ከጀሀነም ይድናሉ።


በነብዩ ሙሳ ጊዜ የነበሩት እና በእርሱ ያመኑ እና


አስተምህሮቱንም የተከተሉ እነርሱ ደጋግ ሙስሊሞች እና


አማኞች ናቸው። ነገር ግን አላህ ዒሳን ከላከ በኋላ የሙሳ


ተከታዮች በዒሳ አምነው ዒሳን የመከተል ግዴታ አለባቸው።


በዒሳ ያመኑም ደጋግ ሙስሊሞች ሲባሉ በዒሳ ማመንን


ሳይቀበል በሙሳ ሃይማኖት ውስጥ እቆያለሁ የሚል ሰው


ግን አማኝ አይደለም። ምክንያቱም ከአላህ በተላከ ነቢይ


ማመንን ስላልተቀበለ ነው።


ከዚያም አላህ የመልክተኞችን መጨረሻ ሙሐመድን


(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው


ላይ ይስፈንና ከላከ በኋላ ሁሉም በርሳቸው የማመን ግዴታ


አለባቸው። ሙሳንና ዒሳን የላካቸው ጌታ  የመጨረሻውን


መልዕክተኛ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ


ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የላከውም ራሱ


ነው። ስለዚህ በሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ


ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መልእክት ክዶ እና


26


"ሙሳን ወይም ዒሳን በመከተል እቀጥላለሁ" የሚል ሰውም


አማኝ አይደለም።


አንድ ሰው ሙስሊሞችን አከብራለሁ ማለቱ ብቻውን


በቂ አይደለም። በመጪው አለም ለመዳንም ምጽዋት


መስጠትና ድሆችን መርዳት በቂ አይደለም። ይልቁንም አላህ


ከርሱ ይህን ስራውን እንዲቀበለው በአላህ፣ በመፃሕፍቱ፣


በመልክተኞቹ እና በመጨረሻው ቀን ማመን ግድ ይለዋል።


ከሽርክ፣ በአላህ ከመካድ ፣ አላህ ያወረደውን ራዕይ


ካለመቀበልና የመጨረሻውን ነቢይ የመሐመድን (ሶለላሁ


ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ


ይስፈንና ነቢይነት ካለመቀበል የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለም።


የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድን (ሶለሏሁ ዐለይሂ


ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና


ተልእኮ የሰሙ አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች እና ሌሎችም


በእርሳቸው ማመንንና ወደ እስልምና ሀይማኖት መግባትን


ካልተቀበሉ በጀሀነም እሳት ውስጥ ይሆናሉ። በውስጧም


ይዘወትራሉ። ይህም የአላህ ፍርድ እንጂ የማንም ሰው


ፍርድ አይደለም። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል:





 {እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም


እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ


እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡}





[አል_በይናህ፡ 6]


ለመላ የሰው ልጆች የተላለፈው የመጨረሻው ተልዕኮ


ከአላህ ዘንድ የወረደ በመሆኑ ስለ እስልምናና  


ስለመጨረሻው ነብይ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)


የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተልዕኮ


የሰማ ሰው ሁሉ በርሳቸው የማመን፣ ሸሪዓቸውን የመከተል


እና በትእዛዛቸውና ክልከላቸው እርሳቸውን የመታዘዝ


ግዴታ አለበት። ስለዚህም የመጨረሻውን ተልዕኮ ሰምቶ


የሚክድ አላህ ከእርሱ ምንንም አይቀበልም በመጪው


ዓለምም ይቀጣዋል።


የዚህ ማስረጃውም የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ንግግር


ነው:





 {ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ


ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም


ከከሳሪዎቹ ነው፡፡}


[አሊ-ዒምራን፡ 85]


አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል:





{"የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል


ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን


ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን


ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤" በላቸው፡፡


እምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ"


በሏቸው፡፡}


[አሊ-ዒምራን፡ 64]


አንድን ሙስሊም ምን ምን ነገሮች ግዴታ


ይሆኑበታል?


አንድ ሙስሊም በነዚህ ስድስት ማዕዘናት ማመን ግዴታ


ይሆንበታል።


በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ማመን፤ እርሱ ፈጣሪ፣ ሲሳይ


ሰጪ፣ አስተናባሪና የሁሉም ነገር ባለቤት መሆኑን ማመን፤


እርሱን የሚመስለውም ምን ም ነገር የለም፣ ለርሱም


ሚስትም ልጅም የለውም፣ እርሱ ብቻም ነው መመለክ


የሚገባው፣ ከርሱ ጋርም ሌላ መመለክ እንደሌለበት፤ ከሱ


ሌላ የሚመለኩትን ሁሉ ማምለክ ከንቱ ነው ብሎ ማመን


ነው።


በመላእክት ማመን፤ እነርሱ የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ


ባሪያዎች መሆናቸውን ማመን፤ ከብርሃን እንደፈጠራቸው፤


ከሥራቸውም መካከል አንዱ እነርሱ በነቢያቶች ላይ ራዕይ


ይዘው እንደሚወርዱ ማመን ነው።


አላህ ለነቢያቱ ባወረደላቸው መጽሐፍት ባጠቃላይ


29


(ከመጣመማቸው በፊት እንደ ተውራት እና ኢንጅል -) እና


በመጨረሻው መጽሐፍ በተከበረው ቁርኣን ማመን፤


በሁሉም መልክተኞች ማመን፤ እንደ ኑሕ፣ ኢብራሂም፣


ሙሳ፣ ዒሳ እና የመጨረሻው ነቢይ በሆኑት በሙሐመድ


ማመን፤ መልክተኞቹም ሰው ናቸው። አላህ በራዕይ


አግዟቸዋል፤ እውነተኝነታቸውን የሚጠቁሙ ምልክቶችንና


ተአምራትንም ሰጥቷቸዋል።


በመጨረሻው ቀን ማመን፤ ይህም አላህ


የመጀመሪያውንና የመጨረሻውን የሚቀሰቅስበት፣ አላህም


በፍጡራኑ መካከል የሚፈርድበት፣ ምእመናኑንም ጀነት፣


ከሓዲዎችንም ጀሀነም የሚያስገባበት ጊዜ ነው።


በቀደር ማመን፤ ይህም አላህ ያለፈውን እና ወደፊት


የሚሆነውን ሁሉንም ነገር እንደሚያውቅ፣  አላህ ሁሉንም


ነገር አውቆት ይህንንም እንደጻፈ፣ እንደሻው እና ሁሉን


ነገርም እንደፈጠረ ማመን ማለት ነው።


አላህ በደነገጋቸው አምልኮዎች አላህን ማምለክ


ይኖርብሃል። ሶላት፣ ዘካ፣ ጾም፣ ወደርሱ መጓዝ ከቻልክም


ሐጅ ማድረግ ይኖርብሃል። በመቀጠል የዱንያን ደስታ


የሚያገኝበትና ከመጪውም አለም መዳኛ ምንጭ የሆነውን


ሃይማኖቱን መማር ይኖርበታል።


***


 30


 


31


ማውጫ


ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረው ማን ነው? እኔንስ የፈጠረኝ ማን


ነው? ለምንስ ፈጠረኝ? .................................................................. 2


ታላቁ ጌታና ፈጣሪ .................................................................... 4


ይሀው ጌታ፣ ፈጣሪና ሲሳይ ሰጪ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ


ነው። ................................................................................................ 5


የጌታችን አሏህ ባህሪያት ........................................................... 6


ተመላኪው ጌታ በምሉዕ ባህሪያት የሚገለፅ ነው። ................ 8


ይህ ታላቅ ፈጣሪ ለምንድን ነው የፈጠረን? ከኛስ ምንድን ነው


የሚፈልገው? ................................................................................. 11


መልክተኞች የበዙበት ምክንያት ምንድን ነው? ................... 15


አንድ ግለሰብ በሁሉም መልክተኞች ካላመነ አማኝ


አይሆንም። .................................................................................... 16


የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ......................................... 18


እስልምና ምንድን ነው? ......................................................... 19


እስልምና የደስታ ጎዳና ነው።.................................................. 22


አንድ ሙስሊም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ምን


ይጠቀማል? ................................................................................... 23


ሙስሊም ያልሆነ ሰው ምን ይከስራል? ................................ 24


በመጪው አለም ለመዳን የሚፈልግ ሰው እስልምናን


ተቀብሎ ለአላህ ታዛዥ መሆንና ነቢዩ ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና


ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መከተል ይኖርበታል። ........... 25


አንድን ሙስሊም ምን ምን ነገሮች ግዴታ ይሆኑበታል? .... 29


***



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረው ማን ነ ...

ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረው ማን ነው? እኔንስ የፈጠረኝ ማን ነው? ለምንስ ፈጠረኝ?

እኔ እስልምን እንደ ሃይማኖት አሸ ...

እኔ እስልምን እንደ ሃይማኖት አሸንፌ አገኘሁ፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ (ሰላም በላዑ) ወይም በእግዚአብሔር ነቢያት ማንኛውንም እምነት አልጠፋም

አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ ...

አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ 2

አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ ...

አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ 1