መጣጥፎች




Amharic





1 ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አሏህ እንመለስ 11


2


ረዥም እድሜ እኖራለን ብለን ተስፋ ከማድረግ


እንጠንቀቅ 13


3 ተውባን ማዘግየት የሚያስከትለው ውጤት 17


4 አሏህን በመታዘዝ ላይ ሆኖ ያደገ ወጣት 19


5 ነብያዊ ምክር 21


6 በመጨረሻ ወጣቶች ሆይ! እነዚህን ነገሮች


አስታውሱ! 25


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


7


إن الحمد لله نحمده، ونستعينه، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات


أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له


ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው፡፡ እናመሰግነዋለን፤ እርዳታም ከሱ


እንጠይቃለን፡፡ ከነፍሳችን ክፋትና ከስራዎቻችን ጥፋት በአላህ


እንጠበቃለን፡፡ አላህ የመራውን ሰው የሚያጠመው ነገር የለም፤ አላህ


ያጠመመውን ደግሞ የሚመራው የለም፡፡ ከአላህ ሌላ በሐቅ የሚመለክ


አምላክ እንደ ሌለ፤ እሱ ብቸኛ ነው አምሳያ የለውም፡፡ ሙሐመድም


(ሰዐወ) የአላህ ባርያና መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡


ወጣቶች ደስታን ለማጣጣም ወይም ከጎደኞቻቸው ጋር ላለመለያየት


ወይም ደግሞ ዱንያዊ ኑሯቸውን ለማቃናት ሲሉ ከአሏህ ጋር


ያላቸውን ግኑኝነት ያቋርጣሉ። አሉ የተባሉ ሃራም ነገሮችንም


ይሰራሉ። የሚፈልጉትን ነገር በሃላል መንገድ ማግኘት ሲችሉ አሏህን


በማመፅ ላይ ይፈልጋሉ።


ወቅቱ ወጣቱ ክፍል ለወጣትነት ጊዜው ትኩረት የማይሰጥበት፣


ለዲኑ ግዴለሽ የሆነበት፣ ከእውቀት ይልቅ አሉቧልታን ያስቀደመበት፣


ከመስጊድ የራቀበት፣ አዋዋሉ የማያምርበት፣ ለጊዜ ዋጋ የማይሰጥበት


የድንቁርና ጊዜ በመሆኑ ይችን ፅሁፍ ልፅፍ ወደድኩ ያንብቧት!


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


9


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አሏህ


እንመለስ


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው አሏህ ይገባው። ከአሏህ ውጭ በሐቅ


ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)


የአሏህ መልዕክተኛና ባሪያ መሆናቸውን እንመሰክራለን። የአሏህ


ሰላትና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በሱሃቦቻቸው


ላይ ሁሉ ይሁን።


ጀርባው የጎበጠ፣ ፀጉሩ የሸበተ፣ ጥርሶቹን ያጣ፣ አይኑም ጆሮውም


የደከመ፣ ቀስ እያለ የሚራመድ ሽማግሌ ሰው ገጥሟችሁ አያቅም?


መስገድ፣ መፆም፣ መብላት፣ መጠጣት አይችልም። አንድ ወቅት


ግን እንደኛው ወጣት ነበር። የወጣቶችን ህይወት ኑሯል። ወጣቶች


እንደሚያደርጉት ተጫውቶና ተዝናንቶ የወጣትነቱን ጊዜ አሳልፏል።


የወጣትነት ጊዜው ረዥም እንደሚሆንና የወጣትነት ጥንካሬው


እድሜ ልኩን አብሮት እንደሚዘልቅ ነበር ያሰበው።


ዛሬ ሸምግሎ ደካማ ከሆነ ቡኋላ በሽታው በርትቶበት ባሳለፈው


ህይወቱ ላይ ያለቅሳል። ባረባ ጨዋታና ስራ ባሳለፈው ጊዜ ላይ


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


10 11


ረዥም እድሜ እኖራለን ብለን ተስፋ


ከማድረግ እንጠንቀቅ


ወጣቶች ሆይ! ይህን ያህል ደካማ እስክሆን ድረስ ምን እጠብቃለሁ?


ልትሉ ትችሉ ይሆናል። ምናልባት እድሜየ አርባ ሲሆን ወይም ከዛ


በፊት በተውበት ወደ አሏህ እመለሳለሁ ልትሉ ትችሉ ይሆናል። ያኔ


የወጣትነት ጊዜየን ተደስቸበት ከዚያ ብኋላ አሏህን እገዛለሁ። አሏህ


ርህሩህ አዛኝ ነው። የአሏህ ባሪያ ነፍሱ በጉሮሮው እስካልወጣች


ድረስ ስልሳዎቹም ሆነ ሰባዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ በተውበት ወደ


እሱ ከተመለሰ ይምረዋል። ታዲያ ለምንድነው የምትጨቀጭቁን


ልትሉ ትችላላችሁ።





ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ


ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡





ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች


ያለቅሳል። ምነው የወጣትነት ጊዜ በተመለሰልኝና አሏህን በመገዛት ላይ


በተጠቀምኩበት ሲል ይመኛል። ነግርግን ጊዜው እረፈደ። እንያንዳንዷ


አዲስ ቀን የአደም ልጅ ሆይ! እኔ አዲስ ቀን ነኝ። ለምትሰሩት ነገር


ምስክር እሆናለሁና ተጠቀሙብኝ። ምክኒያቱም አንዴ ከሄድኩ እስከ


እለተ ቂያማ ድረስ በፍፁም አልመለስምና ሲል ይጣራል።


ይህ ሰው የሃዘንና የፀፀት ህይወት መኖሩን ቀጥሏል። እድሜው


በመግፋቱና በጣም በመድከሙ አሏህን የመገዛት አቅሙ ተሟጧል።


መስገድ ይፈልጋል ነገርግን አስቸጋሪ ሆነበት። መፆም ይፈልጋል


ነገርግን አልቻለም። በሽታ አዳክሞት እድሜው ገፍቶ የፀፀት ባህርን


እየቀዘፈ ቀሪ ህይወቱን እንዲሁ መግፈቱን ተያይዞታል።


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


12 13


ምንያህል ወጣቶች እንደሚሞቱ አላያችሁም? በተውበት ወደ አሏህ


የመመለስ እድል የገጠማቸው ወይም እስኪቶብቱ ድረስ ሞታቸው


የዘገየላቸው ስንቶቹ ይሆኑ? አሏህን በማመፅ ላይ ያባከኑት ጊዜ


መቃብሮቻቸው ውስጥ ይጠቅማቸው ይሆን? እንቶብታለን ብለን


ካሰብነው የእድሜ ክልል እነሱ ደርሰው ይሆን? ታዲያ ለምን ረዥም


እድሜ እንደምንኖር ተስፋ እናደርጋለን? ዛሬ ብሞትስ ብልን ብናስብና


ለመጭው አለም ህይወት ስንቅ የሚሆነንን ነገር ብናዘጋጅ የሚሻል


አይመስላችሁም? ሞት ባልተጠበቀ መልኩ በድንገት ሊመጣባችሁ


እንደሚችል እያወቃችሁ ለምን ወደ አሏህ ከመመለስ ነገ ዛሬ ትላላችሁ?





እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም በተውበት ወደ


አሏህ ተመለሱ።


{አል-ቁርአን 24:31} ወጣቶች ሆይ! እድሜያችሁ አርባ አመት ሲሆን


የወጣትነት ጥንካሬያችሁ ከእናንተ ጋር እንደሚሆንና አሏህን በተሻለ


መንገድ የምትገዙበት አቅም እንደሚኖራችሁ ምንድነው ዋስትናችሁ?


እድሜው 30 ወይም 40 የሆነ ወጣት በሽታ አጥቅቶት ቀሪ ህይወቱን


የአልጋ ቁራኛ ሊያደርገው እንደሚችል አታስቡም?


ወጣቶች ሆይ! በተውባ ወደ አሏህ እንመለስ ይህ ከቅጣት ያድነን


ይሆናል። ሃጢያት ነገሮችን እንጠንቀቅ ምክኒያቱም በአሏህ ላይ


ማመፅ ትልቅና ዘላለማዊ ጥፋት በራሳችን ላይ ማምጣት ነውና።


ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ


ሠሪዎችን ይወዳል፡፡





ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ


አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ


ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡


(በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ


ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡





እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች


ሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው፡፡


የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች!፡፡


ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ! ይህ የማይረባ እቅድ መሆኑን ትገነዘብ


ዘንድ እንዲህ ስል ልጠይቃችሁ ወደድኩ። እስከ ሰላሳ ወይም አርባ


አመት የእድሜ ክልል ውስጥ በህይወት መኖራችሁን ያረጋገጠላችሁ


ማነው? ነገ በህይወት እንደምትኖሩ ያረጋገጠላችሁ ማነው? በእርግጥ


አሁን ከተቀመጣችሁበት ወይም ከቆማችሁበት ወይም ደግሞ ተኝታችሁ


ከሆነ ከተኛችሁበት ቦታ ላይ እንደምትሆኑ ያረጋገጠላችሁ ማነው?


ሞት በድንገት ሊመጣብን እንደሚችልና አረጋውያንን እንደሚያጠቃው


ወጣቶችን ሊያጠቃ እንደሚችል ትንሽ አናስብም?


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


15


ተውባን ማዘግየት የሚያስከትለው


ውጤት


ወጣቶች ሆይ! ልብ ያላልነው ጉዳይ ቢኖር ቸልተኝነትና ማዘግየት


የመጥፎ ፍፃሜያችን ምክኒያት ሊሆን እንደሚችል አለማሰባችን ነው።


በቸልተኝነት ነገዛሬ የምንል ከሆነ ምናልባት የመቃብራችን ጉድጎድ


እስኪ ቆፈርልን ድረስ ተውበቱን ልናዘገይ እንችላለን። እያንዳንዱን


ቀን በቸልተኝነት ነገዛሬ የምንል ከሆነ የበለጠ ከአሏህ እየራቅን


ከተውበት እየራቅን ነው የምንሄደው። ወዲያውኑ በተውበት ወደ


አሏህ የሚመለስና ከሃጢያት የሚጠነቀቀው ቆራጥ ሰው ብቻ ነው።


ወጣቶች ሆይ! ተውበትን ከማዘግየትና ሃጢያት ውስጥ ተዘፍቀን


አሏህ ይምረኛል እያልን ከመኩራራት እንጠንቀቅ። በእርግጥ አሏህ


ሁሉን መሃሪ ነው። ነገርግን ቅጣቱም ከባድና አሳማሚ ነው።





በእርግጥ የጌታህ ቅጣት ከባድ ነው። {አል-ቁርአን 85:12}





የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


16 17


አሏህን በመታዘዝ ላይ ሆኖ ያደገ ወጣት


አቡ ኹረይራ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ)


ምንም ጥላ በማይኖርበት በዕለተ ትንሳኤ ሰባት ሰዎች ከአሏህ ዙፋን


ጥላ ስር ይሆናሉ ካሏቸው መካከል አንዱ አሏህን በመታዘዝ ላይ ሆኖ


ያደገ ወጣት ነው ብለዋል።


ወጣቶች ሆይ! አሏህ በአርሹ ጥላ ስር እንዲጠብቃችሁ አትፈልጉም?


ኪታባችሁንስ በቀኝ እጃችሁ መቀበል አትሹም?





ኪታቡ በቀኝ እጁ የሚሰጠው ሲሆን ይኸውና አንብቡት ይላል።


በእርግጥ ሒሳቤን እንደማገኝ አምን ነበር (ይላል)። =<({አል-ቁርአን


69:19-20})>=


ጀነት ውስጥ የጌታችሁን ፊት ማየት፣ ነብያቶችንና መልዕክተኞችን


መገናኘት አትፈልጉም? የጀነት ድንግልና ንፁህ ሚስቶች እንዲኖሯችሁስ


አትፈልጉም? እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑላችሁ የምትፈልጉ ከሆነ ወደ


አሏህ ተመለሱ! ወደ ፊት እጣፈንታችሁ ምን ሊሆን እንደ ሚችል


አስቡ? ህይወት አጭር መሆኗን አትዘንጉ!


ጊዜ እንዲህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው። =<({አል-


ቁርአን 11:102})>=


የአሏህን ቅጣት የምንዘነጋባቸው ሶስት ምክኒያቶች


በዱንያ ደስታና ብልጭልጭ ነገሮች መታወር


ተውበትን ማዘግየት


ወንጀል ላይ ተዘፍቀን በአሏህ መሃሪነት መኩራራት


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


19


ነብያዊ ምክር


عن بن عباس رضي الله عنهما قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم


اغتنم خمسا قبل خمس شبابك قبل هرمك وصحتك « : لرجل وهو يعظه


.» قبل سقمك وغناءك قبل فقرك وفراغك قبل شغلك وحياتك قبل موتك


341 وقال : هذا حديث صحيح على شرط الشيخين / 4 ) أخرجه الحاكم في المستدرك رقم ) 7846


ኢብን አባስ ባስተላለፈው ሐዲስ መሰረት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አንድን


ሰው ሲመክሩ አምስት ነገሮች ከመከሰታቸው በፊት አምስት ነገሮችን


ተጠቀም አሉ።


ሽማግሌ ከመሆንህ በፊት ወጣትነትህን


ከመታመምህ በፊት ጤናህን


ድሃ ከመሆንህ በፊት ሃብት ንብረትክን


ከመጨናነቅህ በፊት ትርፍ ጊዜህን


ከመሞትህ በፊት ህይወትክን


ወጣቶች ሆይ! ኢስላም መጫወት ወይም መደሰት ይከለክላል ብሎ


ማሰብ ስህተት ነው። በእርግጥ ኢስላም መጫወትንም ሆነ መደሰትን


ይፈቅዳል። ነገርግን የሰው ልጅ የስሜቱ ባሪያ እንዳይሆን የራሱ


የሆነ ገደብ አስቀምጧል። ኢስላም ከፈቀዳቸው ነገሮች መካከል


የሚከተሉት ይገኙበታል።


ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


20 21


{{ሰዎች ሆይ! በምድር ውስጥ መልካምና የተፈቀደ ምግብ ብሉ።


የሰይጣንንም የእግር ኮቴ አትከተሉ በእርግጥ እሱ ለእናንተ ግልፅ


ጠላት ነው።}} {አል-ቁርአን 2:168}


ሳቅና ቀልድ: ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ይስቁም ይቀልዱም ነበር። ነገርግን


ለመዝናናት ወይም ለመቀለድ እውነተኛ ንግግርን ብቻ ነበር


የሚጠቀሙት። ምክኒያቱም ኢስላም መዋሸትን አይፈቅድም።


ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሰዎች እንዲስቁለት ብሎ ሲያወራ የሚዋሽ ሰው


ወየውለት፣ ወየውለት፣ ወየውለት ብለዋል።


ጉዞና ጉብኝት: ይህ ሌላኛው የተፈቀደ ነገር ነው። ወንጀል ነገሮች


የሚሰሩበት፣ ወንዱና ሴቱ የሚቀላቀልበት፣ ሐራም ነገሮች


የሚታይበት፣ ሙዚቃ ነክ ነገሮች ያሉበት እስካልሆነ ድረስ


ይፈቀዳል።


ስፓርትና የአካል እንውስቃሴ: ጠንካራ አማኝ ከአሏህ ዘንድ


ከደካማ አማኝ የበለጠ የተወደደ ነው። ኡመር(ረ.ዐ) ልጆቻችሁን


ውሃ ዋና፣ ቀስት(ጦር) ውርወራና ፈረስ ግልቢያ አስተምሩ


ይሉ ነበር። ሆኖም ወጣቶች እነዚህን ነገሮች ሲማሩ ንያቸውን


ማስተካከል ይኖርባቸዋል።


ወጣቶች ሆይ! ታዲያ ለምን አሁን ተውበት አድርገን ወደ


አሏህ አንመለስም? ይህን ጥያቄ ስትመልሱ ምክኒያት አታብዙ


እራሳችሁን ነው የምታታልሉት! ቆራጦች ሁኑ! ህይወታችሁን


የምትቀይሩበትን ውሳኔ ወስኑ! ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሰዎች ተገቢ ምስጋና


ያልቸራቸው(በአግባቡ ያልተጠቀሙባቸው) ሁለት ሲሳዮች አሉ።


ትዳር: ኢስላም ትዳርን የሚያበረታታ ሲሆን ጠንካራ የስሜት


ልጓም ነው። በባልና በሚስት መካከል ፍቅርና መተሳሰብ


የሚጎለብትበት ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፦





ከምልክቶቹ መካከል፤ በነሱ ውስጥ ሰላም ታገኙ ዘንድ ለእናንተ


ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ፈጠረ፤ በመካከላችሁም ፍቅርን እና


እዝነትን አደረገ። በእርግጥ በዚህ ላይ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች


(ሰዎች) ምልክቶች አሉ። =<({አል-ቁርአን 30:21} )>=


የትዳር ብዙ ጥቅሞች አሉት


የአሏህን ትዕዛዝ መፈፀምና የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ መከተል


ነው።


በባልና በሚስት መካከል ፍቅርናን፣ መተሳሰብን፣ አጋርነትን


ይፈጥራል።


ጥብቅ ለመሆንና ስሜትን ለመቆጣጠር ይረዳል


የሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲበዛና እንዲጠነክር ያደርጋል።


ከአባላዘር በሽታ ይከላከላል


መብላትና መጠጣት: አሏህ ንፁህና ሐላል የሆነ ምግብ


እንድንመገብ ፈቅዶልናል። አሏህ እንዲህ ይላል፦





ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አላህ እንመለስ


22 23


በመጨረሻ ወጣቶች ሆይ! እነዚህን


ነገሮች አስታውሱ!


ያላችሁ ሃብት ህይወታችሁ ነውና በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ


አታባክኑት።


ጎድኛ የምታደርጉትን ሰው ማንነት እወቁ። ከማጥፎ ሰው ጋር


አትጎዳኙ።


ሶላቶቻችሁን ተጠባበቁ


ውዱ ማድረግ የሚከብዳችሁ ጊዜ እንኳ ቢሆን ቀድማችሁ ውዱ


ከማድረግ አታመንቱ፤ የጀመአ ሶላት ላይ ተበራቱ።


የሱና ፆሞችን ፁሙ! በወጣትነት ጊዜያችሁ ከመጥፎ ነገሮች


መጠበቂያችሁ ናቸውና።


ቀን በቀን ከቁርአን የተወሰነ ምዕራፍ እንብቡ


አሏህን አብዝታችሁ ለምኑት አውሱትም ምክኒያቱም አሏህ


የሚያወሳውንና የሚለምነውን ይወዳልና።


የነብያቶችንና የሰሃቦችን ታሪክ አጥኑ


እወቀትን መሻት በኢስላም ግዴታ ነውና ለእውቀት ልዩ ትኩረት


ይኑራችሁ


ለሰዎች ትሁት ሁኑ


ወላጆቻችሁን በቅንነት አገልግሉ


ሃያዕን ተላበሱ


ጤናና ትርፍ ጊዜ ናቸው ብለዋልና ከወዲሁ አሏህን በመገዛት ላይ


ልትጠቀሙባቸው ይገባል።


ወጣትነታችን ጥንካሬንና ትርፍ ጊዜን የያዘ ነውና ታዲያ ለምን


ይህን ጊዜ ወደ አሏህ የምንቃረብበትና ለአሂራ የሚጠቅመንን ነገሮች


በመስራት አንጠቀምበትም?


አብዱሏህ ኢብን መስኡድ(ረ.ዐ) ለዱንያና ለአሂራ ህይወቱ


በሚጠቅመው ነገር ላይ ትርፍ ጊዜውን የማይጠቀም ሰው ማየቱ


ያስጠላኛል ይል ነበር።



 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ