መጣጥፎች




የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይገባው፡፡ እዝነትና ሰላም በአላህ


መልእክተኛ የነቢያቶች መደምደሚያ በሆኑት፣ በቤተሰቦቻቸው፣


በባልደረቦቻቸውና እስከቂያማ ድረስ እሳቸውን በተከተሉ ላይ


ይስፈን፡፡


በመቀጠል፡- አብዛኛው የአህለሱና ወልጀማዓ ዓሊሞች ተወሱል


እንደሚፈቀድ ተስማምተዋል፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከቁርኣንና ሰሒሕ


ከሆነ ሐዲስ አቀረቡ፡፡ ግን የተወሰኑ ሙስሊሞች በቁርኣንና ሐዲስ፣


እንደዚሁም የዚህ ኡማ ቀደምቶች ስራ ዉስጥ የመጣ የተወሱል


ስርዓት ግንዛቤ አስቸገራቸው፡፡ ከኢስላም መሰረታዊ መርሆዎችና


የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መመሪያ ጋር የሚቃረን የተሳሳተ ግናዛቤ


ያዙ፡፡ ለዚህ ግንዛቤያቸው ደዒፍ እና መውዱዕ (የተፈበረከ) ሐዲስ


ማስረጃ አቀረቡ፡፡ እንደውም ከዚህ ራቅ ብለው ሄዱና ተወሱልን


አስመልክተው የመጡትን የቁርኣን አንቀፆችን ከተሳሳተ ግንዛቤያቸው


ጋር እንዲስማማ አጣመው ተረጎሙ፡፡


ሁላችንም የሚንስማማበት ነጥብ አለ፡፡ እሱም እኛ የቁርኣንና የሐዲስ


ግንዛቤ ዉስጥ ካልተስማማን ወደ ደጋግ ሰለፎች የሰሓቦችና ታቢዖች


ግንዛቤ እንመለሳለን የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም እነሱ ከሁሉም በተሻለ


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


8 9


የተወሱል ትርጉም


ተወሱል በቋንቋ ደረጃ ወደ ግብ የሚያደርስ ምክንያትና ወደ ሚፈለገው


ነገር መቃረብ ነው፡፡ በተስፋ ወደሱ መድረስ ነው፡፡ ሌላ ትርጉምም


አለው፡፡ እሱም ንጉስ ዘንድ ደረጃና ቀረቤታ ማግኘት ነው፡፡


በሸሪዓዊ አተረጋጎም ደግሞ ወደ አላህ የሚያቃርብ የተፈቀደ


ምክንያትን መተግበር፣ ወደ አላህ ዉዴታ የሚያደርስ ዒባዳና


በመልእክተኛው አንደበት የተፈቀደን ነገር መስራት፣ ይህም አላህ


ዘንድ የላቀ ደረጃ ለማግኘት፣ ወይም ጥቅም በማምጣትና ጉዳትን


በመከላከል ጉዳይን ለማስፈፀም ወይም በአዱንያና በአኽራ


የሚጠቅሙ ነገሮችን ለማግኘት የሚሰሩ ስራዎች ናቸው፡፡ ተወሱል


(ወደ አላህ መቃረብ) እሱ በፈቀደ ነገር እንጅ አይሆንም፡፡


ተወሱል በሶስት ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡


የሚንቃረበውም ወደ አላህ (ሱወ) ነው፡፡


ለመቃረብ የሚፈልግ፣ እሱም ደካማ የሆነ ጉዳዩ እንዲፈፀምለት


የሚፈልግ ባርያ ነው፡፡


መቃረቢያ፡- እሱም ወደ አላህ (ሱወ) የሚያቃርብ መልካም


ስራ ነው፡፡ እሱም “ወሲላ” (መቃረቢያ) ይባላል፡፡


ወደ ሁለቱ ወሕዮች ቅርብ ናቸውና፡፡ እነሱ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምስክር


የሶስቱ በላጭ ክፍለ ዘመን ሰዎች ናቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ


“በላጭ ሰዎች የኔ ክፍለ ዘመን ናቸው፡፡ ከዚያም እነሱን የሚከተሉ


ናቸው፤ ቀጥሎም እነሱን የሚከተሉ ናቸው፡፡” ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡


ከዚሁ በመነሳት ማንኛውም በአላህና በመጨረሻ ቀን ያመነ ሰው


ስሜትን ከመከተል መራቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም እሱ ከአላህ (ሱወ)


መንገድ ያጠማልና፡፡ ቀደምት ሰለፎቻችን የነበሩበትን መንገድ


መከተል አለበት፡፡ ከዚህ መሰረታዊ መርህ በመነሳት ይህችህ ጭቅጭቅ


የበዛባት፣ የቢድዓና ስሜት ተከታይ ሰዎች ዘንድ እንደሚንመለከተው


ብዙ ሰዎች የተሳሳቱበትን ጉዳይ ማብራራት ፈለግኩኝ፡፡ ከአላህ


(ሱወ) እርዳታን ጠየኩኝና ተወሱልን አስመልክተው ቁርኣንና


ሐዲስ ዉስጥ የመጡ ማስረጃዎችን ሰበሰብኩኝ፡፡ ኒያዬ እኽላስ


እንዲኖረውና ራዕዬም ትክክል እንዲሆን አላህን ለምናለውኝ፡፡ እሱ


ቸርና ለጋሽ ነውና፡፡


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


10 11


የተወሱል አይነቶች


የሱና ዓሊሞች ተወሱልን በሁለት ከፍለውታል፡፡ እነሱም፡


የተፈቀደ ተወሱል እና የተከለከለ ተወሱል ናቸው፡፡


የተፈቀደ ተወሱል እና አይነቶቹ


የተፈቀደ ተወሱል የሚባለው ዋጅብ ወይም ሱና በሆኑ ዒባዳዎች


በንግግር፣ በድርጊት ወይም በልብ በማመን አላህ በሚወደው ነገር


ወደርሱ መቃረብ ነው፡፡


በጥሩ ስሞቹና በተከበሩ ባህርያቶቹ ወደ አላህ መቃረብ፡-


በአላህ ስሞችና በተከበሩ ባህርያቶቹ ወደርሱ መቃረብ ካሉት


የተወሱል አይነቶች መካከል በላጩ፣ አንጋፋውና ለባርያ


የሚጠቅም ነው፡፡ ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ለአላህ መልካም ስሞች አሉት፡፡ (ስትለምኑ) በእርሷም ጥሩት፡፡”


አል-አዕራፍ፡180


በመልካም ስሞቹ ወደ አላህ ተቃርባችሁ እሱን ለምኑ ማለት


ነው፡፡ ይህ አንቀጽ ከአላህ ስሞች ወይም ከርሱ ባህርያቶች ዉስጥ


ይህች መቃረቢያ (ወሲላ) ወደ አላህ የሚታቃርብና ጉዳይን


የሚታስፈፅም ጠቃሚ እንዲትሆን ቀጣዩን መስፈርት መጠበቅና


የሚቃረበው ሰው ዘንድ መኖሯ ግዴታ ይሆናል፡፡ እነሱም፡-


ወደ አላህ ለመቃረብ የሚፈልግ ባርያ ደግ ሙእሚን መሆንና


በስራው የአላህን ፊት መፈለግ አለበት፡፡


የሚያቃርበውም ስራ በሱ ወደርሱ እንዲንቃረብበት በአላህ


የተፈቀደ መሆን አለበት፡፡


ስራው የተፈቀደና ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጋር የሚስማማ


መሆን አለበት፡፡ በሱ ላይ አይጨምርም ከሱም አይቀንስም፡፡


ከተቀመጠለት ጊዜና ቦታ ውጭም አይሰራውም፡፡


ከዚህ በመነሳት ከሙእሚን ውጭ ያሉ ሰዎች የሚሰሩት ስራ


ወደ አላህ መቃረቢያ አይሆንም፡፡ እንዲሁም ቢድዓም ወደ አላህ


መቃረቢያ አይሆንም፡፡


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


12 13


በደጋግ ሰዎች ዱዓእ ወደ አላህ መቃረብ፡- ለምሳሌ አንድ


ሙስሊም ችግር ዉስጥ ይገባል፡፡ ለራሱ የአላህን ሐቅ እንዳጎደለ


ያውቃል፡፡ ወደ አላህ የሚያቃርበውን ጠንካራ ምክንያት ፈልጎ


ወደ አንድ ደግ ሰው ተቅዋና እውቀት አለው ብሎ ወደ ሚገምተው


ሰው ሄዶ ችግሩን እንዲያስወግድለት አላህን እንዲለምንለት


ይጠይቀዋል፡፡ ይህ የተወሱል አይነት የተፈቀደ ተወሱል ነው፡፡


ሸሪዓውም ይህንኑ ያመላክታል፡፡ አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡-





“ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን


ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ፡፡” አል-ሐሽር፡ 10


ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ሙእሚን ወንድሙ በሌለበት


ዱዓእ ካደረገለት ተቀባይነት አለው፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል፡፡


ሌላ ሐዲስ አነስ ቢን ማሊክ ከዑመር ቢን አልኸጣብ የዘገበው


ሐዲስ ነው፡፡ እሱም፡- “ዑመር ቢን አልኸጣብ ዝናብ ሲጠፋ


በዐባስ ቢን ዐብዱል ሙጠሊብ ዝናብን ይፈልግ ነበር፡፡


እንዲህም ይል ነበር “እኛ በነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ወዳንተ እንቃረብ


ነበር፤ ታዘንብልናለህም፡፡ አሁን ደግሞ በነቢያችን አጎት ወዳንተ


እንቃረባለን፤ ስለዚህ አዝንብልን፡፡ ይዘንብላቸውም ነበር፡፡”


ቡኸሪ ዘግበውታል፡፡ የዑመር ቃል ትርጉምም እንደሚከተለው


ይሆናል፡- እኛ ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄደን ዱዓእ እንዲያደርጉልን


ጠይቀን በዱዓቸው ወደ አላህ እንቃረብ ነበር፤ አሁን ደግሞ ስለ


ሞቱ ዱዓእ ሊያደርጉልን አይችሉም፡፡ ስለዚህ ወደ ነቢያችን አጎት


ዐባስ ሄዴን ዱዓእ እንዲያደርግልን እንጠይቀዋለን ማለት ነው፡፡


በአንዱ ወደ አላህ መቃረብ እንደሚቻል ያሳያል፡፡ ይህን ስራ


አላህ ይወዳል፡፡ ለዚህም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህንን ይጠቀሙ ነበር፡፡


መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) በለመኑት እኛም መለመን ይፈቀድልናል፡፡


ሰሓቦች፣ ታቢዖችና የነሱ ተከታዮች በዚህ መልኩ ለምነዋል፡፡


ለማኙ በሰራው መልካም ስራ ወደ አላህ መቃረብ ይችላል፡፡


ለምሳሌ አንድ ሙስሊም “አላህ ሆይ! ባንተ ባመንኩኝ እምነቴ፣


በሚወድህ ዉዴታ፣ መልእክተኛህን በመከተሌና በርሱ በማመኔ


ያለብኝን ችግር አስወግድልኝ” ማለት ይችላል፡፡ እንደዚሁም


የሚለምን ሰው ለአላህ ብሎ የሰራውን መልካም ስራ ጠቅሰው


አላህን ልለምንበት ይችላል፡፡ ለምሳሌ በአላህ ባመነው እምነት፣


በሰላት፣ በፆም፣ በጅሃድ፣ ቁርኣንን በመቅራት፣በዚክር፣ ነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት በማውረዱ፣ በሰራው መልካም ስራና


በራቃቸው ወንጀሎች ሁሉ ወደ አላህ መቃረብ ይችላል፡፡


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“እነዚያ፡- «ጌታችን ሆይ! እኛ አመንን ኀጢአቶቻችንንም ለእኛ


ማር፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡” ኣሊ ዒምራን፡ 16


ከሐዲስ ደግሞ ከኛ በፊት የነበሩ ሶስቱ የዋሻ ሰዎች ታሪክ ነው፡፡


ሶስት ሰዎች ዋሻ ገቡ፡፡ ቋጥኝ ዋሻውን ዘጋችባቸው፡፡ ያላቸውን


ትልቅ ስራን ፈለጉና በሱ አላህን ለመኑ፡፡ አላህም ከፈታላቸውና


ከችግር አስወጣቸው፡፡ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘገበውታል፡፡


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


14 15


የተከለከለ ተወሱል እና አይነቶቹ


የተከለከለ ተወሱል የሚባለው አላህ በማይወደው ንግግር፣ ድርጊት


ወይም እምነት ወደሱ መቃረብ ነው፡፡ ይህ የተወሱል አይነት ብዙ ሰዎችን


ከሚፈቀደውና አላህ ካዘዘን የተወሱል አይነት አዘናግቷል፡፡ በሚከለከለው


ተወሱል ተይዘው የታዘዙትን ዘነጉ፡፡ በዚህም ስራቸው ከሰሩ፡፡


አሁን ደግሞ ለኡማው መልካም በማሰብ፣ የኢስላም መልእክትን


ለማድረስና ለማሳወቅ ከተከለከሉ የተወሱል አይነቶች ጥቂቶቹን


እናብራራለን፡፡ እነሱም፡-


በግለሰቦች ሐቅ፣ በክብራቸውና በደረጃቸው ተወሱል ማድረግ፡


- ቢድዓ ከሆኑ የተወሱል ዐይነቶች መካከል አንዱ ከፍጡራኑ


በአንዱ ክብር ተወሱል ማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው “አላህ


ሆይ! በነቢይህ ክብር ወይም በእገሌ ክብር እለምንሃለው” ይላል፡፡


ወይም በነቢዩ ሐቅ ወይም በአንድ ባርያው ሐቅ አላህን ይለምናል፡፡


ይህን የተወሱል አይነት ኢስላም አያውቀውም፡፡ ሁሉንም ነገር


ባጠቃለለው በአላህ ቁርኣን ዉስጥም አልተጠቀሰም፡-





“በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም፡፡” አል-አንዓም፡38


እነዚህ ሶስቱ የሚፈቀዱ የተወሱል አይነቶች ናቸው፡፡ ከነሱ ውጭ


ያሉት ማስረጃ የላቸውም፡፡ እነዚህ ያለፉት ሶስቱ ብይናቸው


ይለያያል፡፡ ከነሱ ዉስጥ ግዴታ የሚሆኑ አሉ፡፡ ለምሳሌ በአላህ


ስሞች፣ በባህርያቶቹ፣ በኢማንና በተውሒድ ወደ አላህ መቃረብ


ግዴታ ነው፡፡ ሱና የሚሆኑም አሉ፡፡ ለምሳሌ በመልካም ስራና


በደጋግ ሰዎች ዱዓእ ተወሱል ማድረግ ሱና ነው፡፡


ስለዚህ ሁሉም ሙስሊሞች በችግር ጊዜ በተፈቀዱ የተወሱል


አይነቶች ብቻ ወደ አላህ መቃረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አላህን አፍረውና


ለሱ ታዘው ቢድዓና ወንጀልን መተው አለባቸው፡፡


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


16 17


ለዚህም ሰሓቦች ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሞቱ በኋላ እሳቸውን ትተው


ዐባስ ዱዓእ እንዲያደርግላቸው ጠየቁ፡፡ እነርሱ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


በሕይወት እያሉ “አላህ ሆይ! ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ክብር ስትል


አዝንብልን” እያሉ ቆይተው እሳቸው ሲሞቱ “አላህ ሆይ! ለዐባስ


ክብር ስትል አዝንብልን” ወደ ሚለው ቀየሩ ማለት አይደለም፡፡


ምክንያቱም ሰሓቦች እንደዚህ አይነት ቢድዓ የሆነ ተወሱል ከነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) አልተማሩምና፡፡ ከቁርኣን ዉስጥም ምንም አይነት


መሰረት የለውም፡፡ ለዚህም ነው ያልሰሩት፡፡ አንድ ሰው ከሞተ


በኋላ በሱ ተወሱል ማድረግ የሚቻል ቢሆን ኖሮ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ከሁሉም ይበልጥ ነበር፡፡ ይህ የተወሱል አይነት በመካ ዘመን


ከነበረ ሽርክ ጋር አንድ ነው፡፡ አላህ (ሱወ) ሲለነሱ እንዲህ ይላል፡-





“ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም»


(ይላሉ)፡፡” አዝ-ዙመር፡3


በፍጡር ወይም በክብሩ ተወሱል ማድረግ ከተጀመረ፣ ደረጃው


የፈለገ ያህል ቢሆንም ጥቅም ማምጣት ወይም ጉዳት መከላከል


ይችላል የሚል እምነት ዉስጥ በጥቂቱም ቢሆን ከተገባ ከእስላም


የሚያስወጣ ትልቁ ሽርክ መሆኑን እወቅ፡፡


ወሊዮችንና ደጋግ ሰዎችን መለመን፣ ለነሱ መሳልና እርዳታ


መጠየቅ፡- ደጋግ ሰዎችን መለመን፣ በክብራቸው መቃረብን


መፈለግና ለነሱ መሳል በአላህ ኀይማኖት ዉስጥ ፈፅሞ


የለም፡፡ይልቁንም እሱ ከትልቁ ሽርክ ነው፡፡ ተውሒድንም


እንዲሁም በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ዉስጥም አልመጣም፡፡


አቡ ሁረይራ እንደዘገበው ደግሞ “ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሽንት ቤት


አጠቃቀም ሳይ ቀር ሁሉንም ነገር አስተምረውናል፡፡” በነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ስራ ዉስጥም አልመጣም፡፡ እስላም ያዘዘን


በስሞቹና በባህርያቶቹ አላህን መለመን ነው፡፡ ይህ ቢድዓ የሆነው


ተወሱል ወደ ትልቁ ሽርክ ሊያደርስ ይችላል፡፡ እሱም አላህ (ሱወ)


እንደ ዱንያ መሪዎች ወይም ነገስታት ጣልቃ ገብ ያስፈልገዋል


ብሎ የሚያምን ከሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም እሱ ፈጣሪን ከፍጡር


ጋር ማመሳሰል ነውና፡፡ አላህ ከፍጡራን ጋር አይነፃፀርም፡፡ አላህ


ከባርያው ለመውደድ ጣልቃ ገብ አይፈልግም፡፡ ከተቆጣበትም


ጣልቃ ገብ አይጠቅመውም፡፡


አንድ ፍጡር ደረጃው የፈለገ ያህል ቢሆንም መለይካ፣ ነቢይ ወይም


መልእክተኛ ቢሆንም አላህን በሱ ማነፃፀር አይፈቀድልህም፡፡


ምክንያቱም ፍጡር ከፈጣሪ ከጃይ ነው፡፡ አላህ ደግሞ ከፍጡር


የተብቃቃ ነውና ምንም ጣልቃ ገብ አይፈልግም፡፡ አላህ (ሱወ)


እንዲህ ይላል፡-





“ከአላህም ሌላ ከሰማያትም ከምድርም ምንንም ሲሳይ


የማይሰጧቸውን (ምንንም) የማይችሉትንም ይግገዛሉ፡፡ ለአላህም


አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፡፡


እናንተ ግን አታውቁም፡፡ ” አን-ነሕል፡73-74


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


18 19


ከአላህ ሌላ ወዳሉት ነገሮች መዞርና እነሱን መለመን፣ በነሱ ላይ


ድንኳን መስራት፣ ወይም መቃብራቸው ላይ ማብራት ማስገባትና


ሌሎችም መኀይማን የሚሰሩትን ስራ መስራት የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣


የሰሓቦችና የታቢዖች ስራ አይደለም፡፡ እነሱ የሚለመነው አላህ


ብቻ እንደሆነ ያምናሉና፡፡ አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡-





“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ


ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ


ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡” አልበቀራ፡186


የተውሒድ ሰዎች ኢማም የሆኑት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ዒባዳ ማለት


ዱዓእ ነው” ብለው አስተምሯቸዋል፡፡ ታዲያ ዱዓእ የአላህ ሐቅ


ሆኖ ሳለ እንዴት ለሌላ አካል ይደረጋል?


በተጨማሪ እነኚህ ስራዎች ሁላቸውም ነቢያቶችና መልእክተኞች


የተላኩበት የተውሒድ ቃልን ይፃረራሉ፡፡ የተውሒድ ቃል


አምልኮትን ከሁሉም አካል አስወግዶ ለአላህ ብቻ ያረጋግጣል፡፡


ነቢያቶች አላህ ከስራዎች መልካሙና ከሱ ሸሪዓ ጋር የሚስማማን


እንጅ አይቀበልም የሚለውን አብራርተዋል፡፡ አላህ ሁሉንም


ወንጀል ይምራል፤ ሽርክ ብቻ ሲቀር፡፡ አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡





ይፃረራል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው “ሰይዲ ሆይ! እገሌ ሆይ! እጄን


ያዘኝ፤ እንዲህ አድርግልኝ፡፡ ወይም እኔ ባንተ ጥበቃ ዉስጥ ነኝ፤


ወይም ባንተና በአላህ ነው የሚኖረው” ማለት ከሽርክ ይመደባል፡፡


እንዲሁም ለሞተ ሰው መሳል የተፈቀደ ተወሱል አይደለም፡፡


ለምሳሌ አንድ ሰው “ሰይዲ እገሌ ሆይ! አላህ ስሳይ ከሰጠኝ


ላንተ እንዲህ አደርግልሃለው፤ ሰይዲ እገሌ ሆይ! ላንተ


እንዲህ አደርግልሃለው፡፡ ወይም እንዲህ አይነት ነገር


ካገኘውኝ ላንተ እንዲ አይነት ነገር አደርግልሃለው” ይላል፡፡


እነዚህን የመሳሰሉት ስለቶች ሁሉ ከአላህ ሌላ ባለ ነገር መሳል


ነው፡፡ ከአላህ ሌላ ላለው አካል አምልኮትን መስጠትም ነው፡፡


ኢስላም ከእንዲህ አይነቱ ተግባር የጠራ ነው፡፡ አላህ (ሱወ)


እንዲህ ይላል፡-





“ለአላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም


ድርሻን አደረጉ፡፡ በሐሳባቸውም «ይህ ለአላህ ነው፡፡ ይህም


ለተጋሪዎቻችን ነው፡፡» ለተጋሪዎቻቸውም «(ለጣዖታት) የኾነው


ነገር ወደ አላህ አይደርስም፡፡ ለአላህም የኾነው እርሱ ወደ


ተጋሪዎቻቸው ይደርሳል» አሉ፡፡ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ!”


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


20 21


ወደ ኢስላም የሚጠጉ ብዙ መኃይማን ይህን ቢድዓ የሆነ ተወሱል


ይዘው በቁርኣን፣ በሐዲስና በኡማው ስምምነት ተረጋግጦ


የተፈቀደውን ተወሱል ትተው ምንም ሳይጠቀሙበት ሲቀሩ


ስታይ ትገረማለህ፡፡ በሱ ፋንታ እራሳቸው የፈጠሩትን ዱዓእ


ስያደርጉና አላህ ያልፈቀደውን፣ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ያልተገበሩትንና


ከዚህ ኡማ ቀደምት ያልተገኘ ቢድዓ የሆነን ተወሱል ሲጠቀሙ


ታያለህ፡፡


ይህንን ቢድዓ የሆነ ተወሱል በመቃወም እኛ የመጀመሪያ


አይደለንም፡፡ እንዲሁም በእስላም ይህ መሰረታዊ ሲሆን


የሚከለከሉት መጤ ቢድዓዎች ናቸው፡፡ እንዲሁም ይህ የሰሓቦች፣


የታቢዖች፣ የአራቱ ኢማሞችና የነሱ ተከታዮች መዝሀብ ነው፡፡


“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውን


(ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው


ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡” አን-ኒሳእ፡48


በወልዮች መንፈስ ላይ ማረድና ለአምልኮት መቃብራቸው


ዘንድ መቀመጥ


አንድ አንድ መኃይም የሆኑ ሙስሊሞች የሚሰሩት፣ በወሊዮች


መቃብር ላይ፣ በመሰብሰቢያቸውና በቁባቸው አከባቢ በተለያየ ጊዜ


የለመዱት እርድ፣ በሽተኛን ወደዚያ መውሰደ፣ ለአምልኮት እዚያ


መቆየት፣ ማደር፣ መቃብሩ ዉስጥ ባሉ ሰዎች ምልጃ መፈለግ፣ ከአላህ


ጋር እነሱን መለመን፣ ከነሱ ዱዓን መፈለግ እና ከነርሱ እርዳታን


መፈለግ እነዚህ ሁሉ ጥሜት የሆኑ ቢድዓዎች ናቸው፡፡ አላህም


አልፈቀደም፡፡ የቀደምት መኃይማን ስራና በዒባዳ ዉስጥ በአላህ


ማጋራትም ነው፡፡ አላህ (ሱወ) ከዚህ ሽርክ ስከለክል እንዲህ ይላል፡-





አላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ አን-ኒሳእ፡36





“እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን


አታድርጉ፡፡” አልበቀራ፡22


በዚህ ዉዳቂ ራዕይ ላይ የሚቆይና አይቶ ዚም የሚል ሰው


ሑክሙ (ብይኑ) አንድ ነው፡፡ እርሱም በአላህ ማጋራት ነው፡፡


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


23


ተወሱልን አስመልክቶ ሙስሊሞች


ከሐቅ ያፈነገጡባቸው ምክንያቶች


የመጀመሪያው ምክንያት፡ ተወሱልን አስመልክተው ለብዙ ሰዎች


ጥሜት ምክንያት የሆነው ጭፍን መከተል (ተቅሊድ) ነው፡፡ ተቅሊድ


ማለት አንድ ተናጋሪ ያለ ማስረጃ የተናገረውን ቃል መያዝ ነው፡፡


ይህ በሸሪዓም የተከለከለ ነው፡፡ ሙቀልድ የሚባለው አንድን ዓሊም


ብቻ የሚከተል ሰው ሲሆን በተቃራኒው ማስረጃ ቢረጋገጥም ከሱ


ቃል አይወጣም፡፡ ከእንዲህ አይነቱ ስራ አላህ (ሱወ) በብዙ የቁርኣን


አንቀፆች ዉስጥ ከልክሏል፡፡ አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡-





“ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ» በተባሉ ጊዜ «አይደለም


አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን» ይላሉ፡፡


አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ


(ይከተሉዋቸዋልን?)” አልበቀራ፡170


ቀደምት ዓሊሞችና የዚህ ኡማ ሙጅተህዶች ከንዲህ አይነቱ ተቅሊድ


ከልክለዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ ተቅሊድ ሙስሊሞች ለመጨቃጨቅና


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


24 25


አድርጎ ማቅረብ አላህን ንግግር ማጣመም ነው፡፡ ምክንያቱም አላህ


ያዘዘው ተወሱል መልካም ስራና እሱ የሚወደውን ነገር መስራት


ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተፍሲር ልቃዉንት ዘንድ ኽላፍ የለውም፡፡


ከሐዲስ ደግሞ ትክክለኛ ትርጉሙ የተምታታባቸው ቢኖር ዑመር


በዐባስ ተወሱል ማድረጉን ተናግረን ያሳለፍነው ነው፡፡ እሱ ለነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) ቅርብ ሲለሆነ በአካሉ ተወሱል አደረገ አሉ፡፡ እኛ


የሚንለው “የዚድ ቢን አስወድ አልጀርሺ ሙዓውያና ሙስሊሞች


ዝናብን ፈልገው በሱ ተወሱል ሲያደርጉ ጀርሺ ዱዓእ አደረገና


ዘነበላቸው፡፡” የርሱስ ምንድነው? የአይነ ስውሩ ሰዉዬ ሐዲስም


እንዲሁ ነበር፡፡ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ጤናዬን እንዲመልስልኝ አላህን


ለምንሉኝ” ኣላቸው፡፡ ነቢዩም (ሱ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ከፈለክ


እለምንልሃለው፤ ከፈለግክም ትታገሳለህ፡፡ እሱም የተሻለ ነው፡፡”


ሰዉየውም ለምንልኝ አላቸው፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ዉዱእ አሳምሮ


እንዲያደርግና ቀጣዩን ዱዓእ እንዲለምን አዘዙት፡-


አላህ ሆይ! እኔ ባንተ ነቢይ በሙሐመድ የእዝነት ነቢይ በሆነው


ወዳንተ ዞራለው፡፡ ሙሐመድ ሆይ! እኔ ጉዳዬ እንዲፈጸምልኝ ባንተ


ወደ ጌታዬ ዞራለው፡፡ አላህ ሆይ! ምልጃውን ተቀበልልኝ፡፡


አይኑም የሚያይ ሆኖ ተመለሰ፡፡ የሐዲሱ ትርጉም ግልፅ ነው፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዱዓእ እንዲያደርጉለት ጠየቃቸው፡፡ አላህ ከነቢዩም


(ሰ.ዐ.ወ) ዱዓቸውን እንዲቀበላቸው “አላህ ሆይ! ምልጃውን


ተቀበልልኝ” በማለት ለመነ፡፡


ሶስተኛ ምክንያት፡- ደዒፍና መውዱዕ በሆኑ መሰረት በሌላቸው


አንድነታቸው እንዲዳከም ምክንያት ይሆናል፡፡ አንድነት ነቢዩን


(ሰ.ዐ.ወ) በመከተል፣ በኽላፍ ጊዜ ወደ ቁርኣንና ሐዲስ በመመለስ


ይገኛል፡፡ ለዚህም አንዲም ሰሓባ አንድን ሰው ተቅሊድ ሲያደርግ አን-


ናይም፡፡ እንደዚያውም አራቱ ኢማሞች ለራዕያቸው ወገንተኝነትን


አልያዙም፡፡ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ብለው ራዕያቸውን ይተዋሉ፡፡


ሌሎችም የነሱን ማስረጃ ሳያዩ እነሱን እንዳይከተሉ ይከለክሉ ነበር፡፡


ቀጣዩን የአላህን ቃል ትርጉም ይረዱ ነበር፡-


] ﴿ٺ ٿ ٿ ٿ ٿ ٹ ٹ ٹ ٹ ڤ ڤڤ ڤ ڦ ڦ﴾ ]الأعراف: 3


“ከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ


ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡” አል-አዕራፍ፡3


ሁለተኛው ምክንያት፡ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾችና ሐዲስን ይዞ


ሌላውን መተው ነው፡፡ ይህም ሆኖ እነሱ ለፈለጉት ነገር ማስረጃ


አትሆንም፤ ራዕያቸውን አትደግፍም፡፡ ዳሩ ግን እነሱ ትርጉሟን


አልተረዱም ወይም ወድቅ የሆነን ትርጉም ሰጧት፡፡ ከነዚህ አንቀጸች


ዉስጥ አንዱ ቀጣዩው የአላህ (ሱወ) ቃል ነው፡-





“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ወደርሱም መቃረቢያን


(መልካም ሥራን) ፈልጉ፡፡” አልማኢዳ፡ 35


እዚህ ላይ መቃረቢያ የተባለው አላህን መታዘዝና እሱ የሚወደውን


ነገር መስራት ነው፡፡ ይህ በተፍሲር ልቃዉንት ዘንድ ኽላፍ የለውም፡፡


ይህን አንቀፅ ከአላህ ሌላ ያለውን ነገር እርዳታ ለመጠየቅ ማስረጃ


የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ተወሱል


26 27


የቁርኣንና የሐዲስ ዱዓእ ላይ ማተኮር አለበት፡፡ ምክንያቱም እሱ


ተቀባይነት ለማግኘት ይበልጥ ይቀርባልና፤ እንደዚሁም በቁርኣንና


በሐዲስ የመጡ ዱዓዎችን ማድረግ ምንዳን ያስገኛል፡፡


ተስፋ… አላህ ሆይ! እኛ በጥሩ ስሞችህና በተከበረ ባህርያቶችህ፣ ባንተ


ባመን እምነታችን፣ ለነቢይህ ባለን ዉዴታና እሱን በምንከተለው


ድርጊት፣ እንዲሁም ያንተን ፊት ፈልገን በሰራነው ስራ ሁሉ


“የተውሒድ ባለቤት ባሮችህ እንዲታደርገን፣ ባንተ መንገድ የሚሰሩ፣


ባንተ ጥሪ የሚጣሩና በነቢይህ (ሰ.ዐ.ወ) መመሪያ ላይ የሚንሆን


እንዲታደርገን፣ ሐቅ ላይ እንዲታጸናንና በጠላቶቻችን ላይ ድል


እንዲታጎናፅፈን እንለምንሃለን፡፡ አንተ ሰሚ፣ ዱዓእ ተቀባይ ነህና፡፡


የአላህ እዝነት በነቢያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣


በባልደረቦቻቸውና እስከ ቂያማ ድረስ እነሱን በተከተከለ ሁሉ ላይ


ይስፈን፡፡


ተፈፀመ!!!


ሐዲሶች መስራት ነው፡፡ እንደውም አንድ አንዴ የእስላምን መሰረት


የሚቃረን ልሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያህል የተወሰነውን እንጥቀስ፡፡


“በክብሬ ወደ አላህ ተቃረቡ፤ ክብሬ አላህ ዘንድ ትልቅ ነውና፡፡”


“አደም ወንጀል በሰራ ጊዜ ‹ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን እንዲትምረኝ


በሙሐመድ ሐቅ እለምንሃለው› አለ፡፡ አላህም ‹አደም ሆይ!


ሙሐመድን ሳልፈጥረው እንዴት አወቅከው?› አለው፡፡ አደምም


አለ፡- ‹ጌታዬ ሆይ! በእጅህ ፈጥረሄኝ አንተ ዘንድ ካለው ነፍስ


በነፋህብኝ ጊዜ ራሴን ቀና አደረግኩኝና የዐርሽ መቆሚያዎች ላይ ‹ላ


እላሀ እለላህ ሙሐመዱን ረሱሉላህ› የሚል አየሁኝ፡፡ እኔም ከሁሉም


በላይ ወዳንተ የሚወደድ ሰው ስም ወደ ራስህ እንዳስጠጋህ ገባኝ›


አለ፡፡ አላህም ‹ምረሃለው፤ ሙሐመድ ባይ ኖር ኖሮ አልፈጥርህም


ነበር› አለው፡፡” ኢማም አዝ-ዘሀቢ አልሚዛን ዉስጥ ይህ ሐዲስ


ዉድቅና መውዱዕ (የተፈበረከ ነው) ብለዋል፡፡


“ከቤቱ ወደ ሰላት ወጥቶ ‹አላህ ሆይ! እኔ ለማኞች ካንተ ባላቸው ሐቅ


እለምንሃለው፤ በዚህ እርምጃዬ ሐቅም እለምንሃለው› ያለ ሰው…”


ሐዲሱ ደዒፍ ነው፡፡ ሸይኹል ኢስላምና ዘሀቢ ደዒፍ አድርገውታል፡፡


በመጨረሻ፡- የተውሒድ ባለቤት የሆነ ሰው ይህን የተከለከለውን


ተወሱል የመራቅ ግዴታ አለበት፡፡ ምክንያቱም በሱ መስራት ትልቁ ሽርክ


ወይም ትንሹ ሽርክ ወይም ቢድዓ ዉስጥ ያስገበዋልና፡፡ እንዲሁም እሱ


በዱዓእ ውስጥ ድንበር ማለፍ ነው፡፡ ተቀባይነት እንዳያገኝ እሱ ብቻ


በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም አላህ (ሱወ) ከሱ ድንጋጌ ጋር የተስማማውን


ስራ ብቻ ይቀበላልና፡፡ አሁንም የተውሒድ ባለቤት የሆነ ሰው



 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ