ማውጫ
1 መቅድም 9
2 አንደኛ ትምህርት ሱረት አልፋትሓና አጫጭር ሱራዎች 10
3 ሁለተኛ ትምህርት የእስላም መእዘናት 10
4 ሶስተኛ ትምህርት የኢማን ማእዘናት 11
5 አራተኛ ትምህርት የተውሒድ ክፍሎችና የሽርክ ክፍሎች 11
6 አምስተኛ ትምህርት እሕሳን (ዕባዳን ማሳመር) 16
7 ስደስተኛ ትምህርት የሰላት መስፈርቶች (ሸርጦች) 16
8 ሰባተኛ ትምህርት የሰላት ማእዘናት (አርካን) 17
9 ስምንተኛ ትምህርት የሰላት ዋጅባቶች (ግዴታዎች) 18
10 ዘጠነኛ ትምህርት አት-ተሕያቱን (ተሸሁድን)ማብራራት 18
11 አስረኛ ትምህርት የሰላት ሱናዎች 20
12 አስራ አንደኛ ትምህርት ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች 22
13 አስራ ሁለተኛ ትምህርት የዉዱእ መስፈርቶች 22
14 አስራ ሶስተኛ ትምህርት የዉዱእ ግዴታዎች 23
15 አስራ አራተኛ ትምህርት ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች 24
16
አስራ አምስተኛ ትምህርት ሁሉም ሙስሊም ሊላበሳቸው
የሚገባ ስነምግባራት
25
17 አስራ ስድስተኛ ትምህርት እስላማዊ ስርኣቶች 25
18
አስራ ሰባተኛ ትምህርት ከሽርክና ሌሎች ወንጀሎች
ማስጠንቀቅ
25
19
አስራ ስምንተኛ ትምህርት ጀናዛ ላይ መስገድ፣ መሸኘትና
መቅበር
26
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
7
መቅድም
ምስጋና ለአላህ ለዓለማት ጌታ ይገባው፡፡ መጨረሻቸው ያማሬ
አላህን ለሚፈሩት ሰዎች ነው፡፡ የአላህ እዝነትና ሰላም በባርያውና
መልእክተኛው ሙሐመድ ላይ ይስፈን፡፡ እንደዛዉም በሁሉም
ቤተሰቦቻቸውና ባልደረቦቻቸው ላይም ይስፈን፡፡
በመቀጠል፡- ይህች ትምህርት በሁሉም ሙስሊም ላይ ማወቅ ግዴታ
የሚሆን ነገርን የሚታብራራ ናት፡፡ እሷም “አስፈላጊ ትምህርቶች
ለብዙሃኑ ህዝብ” ብዬ ሰየምኳት፡፡
አላህ በሷ ሙስሊሞችን እንድጠቅም ከኔም እንድቀበላት
እለምነዋለዉኝ፤ እሱ ቸር ነዉና፡፡
አብዱልዐዚዝ ቢን አብደላህ ቢን ባዝ
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
8 9
ቸልተኝነት የሌለበት መታዘዝ፣
ተቃውሞ የሌለበት መቀበል አና
ከአላህ ሌላ በሚመለከው ሁሉ መካድ ናቸው፡፡
በተጨማሪም “ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው የሚለውን
ምስክርን”ም ማብራራት ያስፈልጋል፡፡ የሷ ድንጋጌዎችም የሚከተሉት
ናቸው፡-
እሳቸው የተናገሩትን እውነት ብሎ መቀበል
ያዘዙትን መታዘዝ
የከለከሉትን መከልከል አና
አላህ ራሱ በደነገገውና መልእከተኛው በደነገጉት ብቻ አላህን
መገዛት ናቸው፡፡
በመቀጠልም ለተማሪዎች የቀሩትን የእስላም መእዘናት፤ ሶላት፣ ዘካ፣
የረመዳን ጾም እና ሐጅን ይገልፃል፡፡
ሶስተኛ ትምህርት የኢማን ማእዘናት
የኢማን ማእዘናት ስድስት ናቸው፡፡ እነሱም፡- በአላህ ማመን፣
በመላእክቶቹ፣ በመጽሐፍቶቹ፣ በመልእክተኞቹ፣ በአኺራ (መጨረሻው
ቀን) እና ደግም ሆነ ክፉም ቢሆን በአላህ ቀደር (ዉሳኔ) ማመን ነው፡፡
አራተኛ ትምህርት የተውሒድ ክፍሎችና የሽርክ
ክፍሎች
ተውሂድ በሶስት ይካፈላል፡፡ እነሱም፡- ተውሒድ አር-ሩቡብያ (የጌታ
አንደኛ ትምህርት ሱረት አልፋትሓና አጫጭር
ሱራዎች
ሱረት አልፋቲሓና የተቻሉትን አጫጭር ሱራዎችን ከሱረት አዝ-
ዘልዘላ እሰከ ሱረት አን-ናስ ድረስ ያሉቲን ንባብ ማስተካከል፣
ማሳፈዝ (በቃል ማስያዝ) እና መረዳቱ ግዴታ የሚሆነውን ትርጉም
ማብራራት፡፡
ሁለተኛ ትምህርት የእስላም ማእዘናት
አምስቱን የእስላም ማእዘናትን ማስተማር፡፡ የመጀመርያውና
አንጋፋው ‹ከአላህ ሌላ በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደ ሌለ እና
ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው፡፡
ይኸዉም ትርጉሟን ከማስረዳትና የ “ላ እላሀ እለሏህ”ን መስፈርት
ከማብራራት ጋር ነው፡፡
ትርጉሟም፡- “ላ እላሀ” የሚለው ቃል ከአላህ ሌላ የሚመለከውን
ሁሉ ማስወገድ ነው፤ “ኢለሏህ” የሚለው ደግሞ አምልኮትን ለአላህ
ብቻ ማረጋገጥ ነው፡፡
የ “ላ እላሀ ኢለሏህ” መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
መሃይምነትን የሚጻረር እውቀት፣
ጥርጣሬን የሚያስወግድ እርግጠኝነት፣
ማጋራትን የሚጻረር እክላስ፣
ማስተባበልን የሚያስወግድ ማፅደቅ፣
ጥላቻን የሚትፃረር ዉዴታ፣
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
10 11
‹‹እርሱን የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው
ተመልካቹ ነው፡፡›› አሽ-ሹራ፡ 11
የሽርክ (የማጋራት) ክፍሎችም ሶስት ናቸው፡ እነሱም ትልቁ ሽርክ፣
ትንሹ ሽርክና ድብቅ ሽርክ ይባላሉ፡፡
ትልቁ ሽርክ ሁሉንም መልካም ስራ ያጠፋል፤ በሱም ላይ የሞተው
ጀሀነም ይገባል፡፡
] ﴿ۓ ۓ ڭ ڭ ڭ ڭ ۇ﴾ ]الأنعام: 88
ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡
﴿ڌ ڎ ڎ ڈ ڈ ژ ژ ڑ ڑ ک کک
] ک گ گ گ گ ڳ ڳ﴾ ]التوبة: 17
ለአጋሪዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲኾኑ የአላህን
መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡
እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
በሱ ላይ የሞቴ ሰው አይማርም፡፡ ጀነት በርሱ ላይ እርም ነው፡፡ አላህ
(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡
] ﴿ڻ ڻ ۀ ۀ ہ ہ ہ ہ ھ ھ ھ ھ ے﴾ ]النساء: 48
አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም
(ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡
﴿چ چ چ چ ڇ ڇ ڇ ڇ ڍ ڍ ڌڌ ڎ ڎ
] ڈ ڈ﴾ ]المائدة: 72
እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም
አንድነት)፣ ተውሒድ አል-ኡሉሕያ (የአምላክነት አንድነት) እና ተውሒድ
አል-አስማእ ወስ-ሲፋት (የስሞችና የባህርያት አንድነት) ናቸው፡፡
“ተውሒድ አር-ሩቡብያ” ማለት አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና የነሱ
ተቆጣጣሪ መሆኑና በዚህ ዉስጥ አጋር እንደ ሌለው ማመን ነው፡፡
“ተውሒድ አል-ኡሉሕያ” ደግሞ በሐቅ የሚመለክ ብቸኛ አምላክ
አላህ መሆኑን ማመን ነው፡፡ እሱም የ “ላ እላሀ እለላህ” ትርጉም
ነው፡፡
ትርጉሟም፡ ከአላህ ሌላ በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም ማለት
ነው፡፡ ሁሉንም አምልኮት ጾምም ሆነ ሰላትን ለአላህ ብቻ ማድረግ
ግዴታ ይሆናል፡፡ አምልኮትን አሳልፎ ለሌላ መስጠት አይፈቀድም፡፡
“ተውሒድ አል-አስማእ ወስ-ሲፋት” (የስሞችና የባህርያት አንድነት)
ደግሞ በቁርኣንና ሐዲስ ዉስጥ የመጡትን ሁሉንም የአላህን ስሞችና
ባህርያቶችን ማመን ነው፡፡ ለአላህ በሚገባ መልኩ ትርጉሙን
ሳያጣሙ፣ ትርጉም ሳያሳጡ፣ ሁኔታ ሳያስቀምጡለትና በፍጡር
ሳያመሳስሉት ለሱ ማረጋገጥ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡፡
﴿ٱ ٻ ٻ ٻٻ پ پپ پ ڀ ڀ ڀڀ ٺ ٺ
]4- ٺ ٺ ٿ﴾ ]الإخلاص: 1
በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡
አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ አንድም ነገር ለርሱ ብጤ አል ሆነም››
አል-ኢኽላስ፡ 1-4
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡
] ﴿ٺ ٿ ٿٿ ٿ ٹ ٹ﴾ ]الشورى: 11
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
12 13
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሁንም በሌላ ሐዲሳቸው እንዲህ አሉ፡
» لا تقولوا: ما شاء الله وشاء فلان، ولكن قولوا: ما شاء الله ثم شاء فلان «
أخرجه أبو داود بإسناد صحيح، عن حذيفة بن اليمان رضي الله عنه.
‹‹አላህና እገሌ ያሹት አትበሉ፤ ነገር ግን አላህ ያሻው ከዚያም እገሌ
ያሻው በሉ፡፡›› አቡ ዳዉድ በትክክለኛ ሰነድ ከሑዘይፋ ዘግበውታል፡፡
ይህ የሽርክ ክፍል ከእስላም መውጣትም ሆነ በእሳት ዉስጥ
መዘውተርን አያስከትልም፡፡ ግን ግዴታ የሆነውን ተውሒድ
ምሉእነትን ይቃረናል፡፡
ሶስተኛ ክፍል ደግሞ “ድብቁ ሽርክ” ነው፡፡ ማስረጃዉም የነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡-
ألا أخبركم بما هو أخوف عليكم عندي من المسيح الدجال؟ قالوا: بلى «
يا رسول الله، قال: الشرك الخفي، يقوم الرجل فيصلي فيزين صلاته
رواه الإمام أحمد في مسنده، عن أبي سعيد الخدري » لما يرى من نظر الرجل إليه
رضي الله عنه.
‹‹አዋጅ! እኔ ዘንድ ከደጃል ይበልጥ የሚፈራላችሁን ነገር ልንገራችሁን?››
አሉ፡፡ ይንገሩን የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሉ፡፡ አሳቸውም አሉ፡-
‹‹ድብቅ ማጋራት ነው፤ እሱም ሰውየው ልሰግድ ይቁምና ሰው ወደሱ
መመልከቱን አይቶ ሰላቱን ያሳምራል፡፡›› እማሙ አሕመድ ሙስነዱ
ዉስጥ ከአቢ ሰዒድ ዘገበውታል፡፡
ሽርክን በሁለት ብቻ መክፈል ይቻላል፡፡ እሱም ትልቁና ትንሹ ሽርክ
ነው፡፡ ድብቅ ሽርክ ግን ሁለቱንም ያጠቃልላል፡፡
እሱም በትልቁ ሽርክ ዉስጥም ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የመናፍቃኖች
አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች
የሏቸውም፡፡
አይነቶቹም ሙታንንና ጣኦትን መለመን፤ እነሱን እርዳታ መጠየቅ፣
ለነሱ መሳል፣ ማረድ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ትንሹ ሽርክ ደግሞ ከቁርኣንና ሐዲስ ማስረጃ ሽርክ መሆናቸው
የተረጋገጠና ከትልቁ ሽርክ ያል ሆኑት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ለይዩልኝ
ብሎ ዒባዳን መስራት፣ ከአላህ ሌላ ባለው ነገር መማል፣ አላህና እገሌ
ያሹት ማለትንና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-
رواه » الرياء « : فسئل عنه، فقال » أخوف ما أخاف عليكم الشرك الأصغر «
الإمام أحمد، والطبراني، والبيهقي
ለናንተ ከሚፈራላችሁ ሁሉ የሚፈራው ነገር ቢኖር ትንሹ ሽርክ ነው
አሉ፡፡ ‹እሱ ምንድነው?› ተብሎ ተጠየቀው “ለይዩልኝ ብሎ መስራት
ነው” አሉ፡፡ አሕመድ፣ ጠብራኒና አልበይሀቂ ዘግበውታል፡፡
አሁንም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሌላ ሐዲሳቸው እንዲህ አሉ፡
رواه الإمام أحمد بإسناد صحيح » من حلف بشيء دون الله ففد أشرك «
‹‹ከአላህ ሌላ ባለው ነገር የማለ ሰው በርግጥ አጋርቷል፡፡›› እማሙ
አሕመድ በትክክለኛ ሰነድ (ሰንሰለት) ዘግበውታል፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሁንም በሌላ ሐዲሳቸው እንዲህ አሉ፡
» من حلف بغير الله فقد كفر أو أشرك «
‹‹ከአላህ ሌላ ባለው የማለ ሰው በርግጥ ክዷል ወይም አጋርቷል፡፡››
አቡ ዳዉድና ትርምዚ ከኢብን ዑመር ዘግበውታል፡፡
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
14 15
ኒያ ናቸው፡፡
ሰባተኛ ትምህርት የሰላት ማእዘናት1 (አርካን)
የሰላት ማእዘናት አስራ አራት ናቸው፡-
የቻለ ሰው መቆም
ወደ ሰላት መግቢያ ተክቢራ (አላሁ አክበር)
ሱረት አልፋቲሓን ማምበብ
ሩኩዕ (ማጎንበስ)
ከሩኩዕ ቀጥ ብሎ መቆም
በሰባት አካላት ላይ ሱጁድ ማድረግ
ከሱጁዱ መነሳት
በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ
በሁሉም የሰላት ስራዎች ዉስጥ መረጋጋት
በየማእዘናቱ መካከል ያለውን ቅደም ተከተል መጠበቅ
የመጨረሻውን አት-ተሕያቱን መቅራት
ለሱ መቀመጥ
በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ እና
በሁለቱም ጎን ማሰላመት ናቸው፡፡
1 የሰላት ማእዘን የሚባለው ወደ ሰላት ከተገባ በኋላ የሚተገበሩ የሰላት አካላት ናቸው፡፡
እነሱን ያጎደለ ሰው ሰላቱ ይበላሽበታል፡፡
ሽርክ፡፡ እነርሱ ሰውን ለማሳየትና ለነፍሶቻቸው ፈርቶ ዉድቅ
የሆነውን እምነታቸውን ይደብቁና እስልምናን ለሰው ያሳያሉ፡፡
ድብቅ ሽርክ በትንሹ ሽርክ ዉስጥም ይገኛል፤ ለምሳሌ ርያእ፡፡ ይህ
ባሳለፍነው ሐዲስ ዉስጥ ተጠቅሷል፡፡
አምስተኛ ትምህርት እሕሳን (ዕባዳን ማሳመር)
“እሕሳን” ማለት አላህን እንደ ሚትመለከት ሆነህ መገዛት ነው፤ እንደ
ሚትመለከተው ሆነህ መገዛት ካልቻልክ እርሱ እንደ ሚመለከትህ
አውቀህ መገዛትህ ነው፡፡
ስደስተኛ ትምህርት የሰላት መስፈርቶች1 (ሸርጦች)
የሰላት መስፈርቶች ዘጠኝ ናቸው፡-
ሙስሊም መሆን
አእምሮው ጤና መሆን
መጥፎንና ጥሩን ነገር የሚለይ እድሜ ላይ መድረስ
ሐደስ2ን ማስወገድ
ነጃሳን ማስወገድ
ህፍረተ ገላን መሸፈን
የሰላቱ ወቅት መግባት
ወደ ቅብላ (ከዕባ) መዞር እና
1 መስፈርት የሚባለው ወደ ሰላት ከመግባት በፊት መሟላት ያለበት ግዴታ ነው፡፡
2 ሐደስ ማለት ዉዱእን ማጥፋት ወይም ጀናባ መሆን ማለት ነው፡፡ እነሱን ማስወገድ
ማለት ዉዱእ ማድረግና መታጠብ ነው፡፡
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
16 17
ነቢይ ሆይ! ሰላም ባንቱ ላይ ይሁን፤ የአላህ እዝነትና በረከቱም፡፡
ሰላም በኛና በደጋግ የአላህ ባሮች ላይ ይሁን፡፡ ከአላህ ሌላ በሐቅ
የሚመለክ አምላክ እንደ ሌለ እመሰክራለዉኝ፤ ሙሐመድም የአላህ
ባርያና መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለዉኝ፡፡
ከዚህ በመቀጠል በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋትና በረከትን ያወርዳል፡፡
እሱም የሚከተለው ነው፡-
اللهم صل على محمد، وعلى آل محمد، كما صليت على إبراهيم وعلى آل
إبراهيم، إنك حميد مجيد، وبارك على محمد، وعلى آل محمد، كما باركت
على إبراهيم، وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
ያአላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትን እንዳወረድክ
ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትህን አዉርድ፡፡ አንተ
ምሰጉንና የላቅክ ነህና፡፡ በኢብራሂምና በቤተሰቦቹ ላይ በረከት
እንዳወረድከው ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቹ ላይ በረከት አዉርድ፤
አንተ ምሰጉንና የላቅክ ነህና፡፡
ከዚያም በመጨረሻም ቁጭታ ከገሐነምና ከቀብር ቅጣት በሕይወትም
ሳለ ሆነ ከሕይወት ሕልፈት በኋላ ከመቸገርና ከደጃል ችግር (ፈተና)
በአላህ ይጠበቅ፡፡ ከዚያም የፈለገውን ዱዓ ይምረጥ፤ በተለይ ከነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) የመጡ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከእነሱም፡-
اللهم أَعِني على ذكرك وشكرك وحسن عبادتك، اللهم إني ظلمت نفسي
ظلما كثيرا، ولا يغفر الذنوب إلا أنت، فاغفر لي مغفرة من عندك،
وارحمني إنك أنت الغفور الرحيم.
አላህ ሆይ! በዉዳሴህ፣ በምስጋናህና ዒባዳህን አሳምሬ እንዳመልክህ
አግዘኝ፡፡ አላህ ሆይ! እኔ ብዙ በደል ራሴን በድያለውኝ፤ ካንተ ሌላ
ስምንተኛ ትምህርት የሰላት ዋጅባቶች (ግዴታዎች)
የሰላት ዋጅባቶች ስምንት ናቸው፡-
ከመጀመርያ ተክቢራ ዉጭ ያሉ ሌሎች ተክቢራዎች፣
ለእማምና ብቻዉን ለሚሰግድ ሰው ‹ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደህ›
(አላህ እሱን ላመሰገኔ ሰው ሰሚ ነው) ማለት፣
ሁሉም ሰጋጅ ‹ረበና ወለከል ሐምድ› (ጌታችን ምስጋና ያንተ
ነው) ማለት፣
ሩኩዕ ዉስጥ ‹ሱብሓነ ረብየል ዐዚም› (ታላቁ ጌታዬ ላንተ
ከማይገባህ ሁሉ ጥራት ይገባህ) ማለት፣
ሱጁድ ዉስጥ ‹ሱብሓነ ረብየል አዕላ› (የላቄ ጌታዬ ላንተ
ከማይገባህ ሁሉ ጥራት ይገባህ) ማለት፣
በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ‹ረብግፍርሊ› (ጌታዬ ማረኝ) ማለት፣
የመጀመርያውን አት-ተሕያቱን መቅራት እና
ለሱ መቀመጥ ናቸው፡፡
ዘጠነኛ ትምህርት አት-ተሕያቱን (ተሸሁድን)
ማብራራት
አት-ተሕያቱ (ተሸሁድ) የሚከተለውን መቅራት ነው፡-
التحيات لله، والصلوات، والطيبات، السلام عليك أيها النبي ورحمة الله
وبركاته، السلام علينا وعلى عباد الله الصالحين، أشهد ألا إله إلا الله،
وأشهد أن محمدا عبده ورسوله.
ክብሮች ሁሉ የአላህ ናቸው፤ ፀሎቶችና መልካም ነገሮችም፡፡ አንቱ
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
18 19
ሱጁድ በሚወርድ ጊዜ የእጆቹን ጡንቻ ከጎኖቹ፣ ሆዱን
ከጭኖቹ እና ጭኖቹን ከባቶቹ ማራቅ
ሱጁድ ሲወርድ ክንዶችን ከመሬት ላይ ማንሣት
በመጀመረያዉ ተሸሁድና በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ባለዉ ጊዜ
የቀኝ እግሩን ጣት ተክሎ በግራ እግሩ ላይ መቀመጥ
በመጨረሻ ተሸሁድ የቀኝ እግሩን ጣት በመትከል መቀመጫውን
መሬት ማስነካት
በመጀመርያና ሁለተኛ ተሸሁድ ዉስጥ ከመጀመርያ
እስከመጨረሻ ድረስ በአመልካች ጣት ማመላከትና ዱዓእ
በሚያደርግ ጊዜ ማንቀሳቀስ
በመጀመረያዉ ተሸሁድ ሰላትንና ረድኤትን ለነቢዩ ሙሐመድና
ለቤተሰቦቻቸዉ፣ ለነቢዩ ኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸዉ መለመን
በመጨረሻዉ ተሸሁድ ፀሎት ማድረግ
በሱብሂ ሰላት፣ በጁሙዓ፣ በሁለቱ ዒዶች፣ በእስቲስቃእ
ሰላትና በመጀመርያዎቹ ሁለት ረከዓ የመግርብ እና የዒሻእ
ሰላት ዉስጥ ድምፅን ከፍ አድርጎ ቁርኣንን መቅራት
በዙህርና ዐስር ሰላት፣ እንዲውም የመግሪብ ሶስተኛ ረከዓና
የዒሻ ሁለቱ የመጨረሻ ረከዓዎች ዉስጥ ድምጽን ዝቅ አድርጎ
ቁርኣን መቅራት
ከፋቲሓ ዉጭ ሌላ ሱራን መቅራት፤ ይኸውም ሌሎች
ያልተናገርናቸውን የሰላት ሱናዎችን ከመጠበቅ ጋር ይሆናል፡፡
ለምሳሌ ከሩኩዕ በኋላ ‹ረበና ወለከል ሐምድ› ላይ ሌላ ዝክርን
ወንጀሊን የሚምር የለምና ካንተ ዘንድ የሆነ ምህረትን ለግሰኝ፡፡
አንተ መህሪ አዛኝም ስለ ሆንክ ማረኝ፡፡
በመጀመርያ ተሸሁድ ላይ በዙህር፣ ዐስር፣ መግርብና ዒሻእ ላይ
ከሁለቱ ምስካሬ (ሸሃደተይን) በኋላ ወደ ሶስተኛ ረከዓ ይነሳል፡፡
በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ቢያወርዲም የተመረጠ ነው፤ ሰለዋትን
አስመልክቶ የመጣ ሐዲስ ሁሉንም ያጠቃልላል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ
ሶስተኛ ረከዓ ይነሳል፡፡
አስረኛ ትምህርት የሰላት ሱናዎች
የሰላት ሱናዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡ እነሱም፡-
የሰላት መክፈቻ ዱዓእ ማድረግ
ከሩኩዕ በፊትና ከኋላ የቀኝ እጁን መዳፍ በግራ እጁ ላይ
አስቀምጦ በደረቱ ላይ ማድረግ
ሁለቱን እጆቹን ጣታቸውን አጠጋግተው ዘርግተው እስከ
ትከሻው ወይም ጆሮው ድረስ በመጀመርያ ተክቢራ፣ ሩኩዕ
በሚወርድ ጊዜ፣ ከዚያ ሲነሳና ከመጀመርያ ተሸሁድ ለሶስተኛ
ረከዓ ስነሳ ማንሳት
በሩኩዕና በሱጁድ ጊዜ ከአንድ በላይ ተስቢህ ማድረግ (አላህን
ማጥራት)
ከሩኩዕ በኋላ ከአንድ በላይ ‹ረበና ወለከል ሐምዱ› ማለት፤
በሁለቱ ሱጁድ መካከል ከአንድ ጊዜ በላይ ምህረትን መጠየቅ
ሩኩዕ ላይ እራስን ከወገብ ልክ ማድረግ
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
20 21
ዉዱእ እስከሚያጠናቅቁ ድረስ ላለማቋረጥ መወሰን
ዉዱእን የሚያፈርስ ነገርን ማስወገድ
ከሱ በፊት በዉሃ ወይም በድንጋይ እስትንጃ ማድረግ
ዉሃው ንፁህና መጠቀሙ የተፈቀደ መሆን
ዉሃው ወደ ሰዉነት እንዳይደርስ የሚከለክል ነገርን ማስወገድ
እና
ዉዱእ የሚያጠፋ ነገር ከሰዉነቱ ለማይቋረጥ ሰው የሚሰግደው
ሰላት ወቅት መግባት ናቸው፡፡
አስራ ሶስተኛ ትምህርት የዉዱእ ግዴታዎች
የዉዱእ ግዴታዎች ስድስት ናቸው፡፡ እነሱም፡-
ፊትን መታጠብ ሲሆን ኣፍን መጉመጥመጥና ዉሃን በአፍንጫ
ማስገባት ከዚው ይመደባል
ሁለቱን እጆች ከክርኖች ጋር ማጠብ
ሙሉ ራስን ከጆሮ ጭምር ማበስ
ሁለቱን እግሮች ከቁርጭምጭሚቶች ጋር ማጠብ
የተጠቀሱትን የዉዱን ድርግቶች ቅደም ተከተል መጠበቅ እና
ድርጊቶቹን ማከታተል ናቸው፡፡
የተጠቀሱትን የዉዱእ አካላትን ሶስት ጊዜ ማጠብ ይወደዳል፡፡
ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ብቻ ማጠብ ነው፡፡ጭንቅላትን ግን ከአንድ
ጊዜ በላይ ማበስ አይወደድም፡፡
መጨመርና ሩኩዕ ሲወርዱ የእጅ ጣቶችን ለያይቶ በጉልበት
ላይ ማድረግም ሱና ናቸው፡፡
አስራ አንደኛ ትምህርት ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች
ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች 8 (ስምንት) ናቸው፡፡ እነሱም፡
እያወቁና እያስታወሱ ሰላት ዉስጥ መናገር፡፡ ነገር ግን
በመርሳትና ባለማወቅ በመናገሩ ሰላቱ አይበላሽበትም፡፡
መሳቅ
መብላት
መጠጣት
ህፍረተ ገላ መገለጥ
ከቅብላ ብዙ መዞር
ሰላት ዉስጥ ብዙና ተከታታይ የሆነ እንቅስቃሴን ማድረግ እና
ጠሃራን ማፍረስ
አስራ ሁለተኛ ትምህርት የዉዱእ መስፈርቶች
የዉዱእ መስፈርቶች አስር ናቸው፡፡ እነሱም፡-
ሙስሊም መሆን
አእምሮው ጤና መሆን
መጥፎንና ጥሩን ነገርን የሚለይ እድሜ ላይ መድረስ
መነየት
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
22 23
አስራ አምስተኛ ትምህርት ሁሉም ሙስሊሞች
ሊላበሷቸው የሚገቡ ስነምግባራቶች
ሁሉም ሙስሊሞች ሊላበሷቸው ከሚገቡ ስነምግባራቶች መካከል
እውነተኛነት፣ ታማኝነት፣ ጥብቅነት፣ እፍረት (ሐያእ)፣ ጀግንነት፣
ቸርነት፣ ቃል ክዳን መሙላት፣ አላህ እርም ያደረጋቸውን ነገሮች
መራቅ፣ ጉርብትናን ማሳመር፣ በችሎታ ልክ ችግርተኛን መርዳትና
ሌሎችም ቁርኣንና ሐዲስ የደነገጋቸው ስነምግባራት ናቸው፡፡
አስራ ስድስተኛ ትምህርት እስላማዊ ስርኣቶች
እስላማዊ ስርኣቶች ሰላምተኛነት፣ ፈገግታ፣ በቀኝ መብላትና
መጠጣት፣ መጀመርያ ላይ ቢስምላህ ማለት፣ በመጨረሻም
አልሐምዱሊላህ ማለት፣ ካስነጠሰ በኋላ አልሐምዱሊላህ ማለት፣
ያስነጠሰ ሰው አልሐምዱሊላህ ካለ ‹ረሕመከላህ› ማለት፣ በሽተኛን
መጠየቅ፣ ጀናዛን ተከትለው በሱ ላይ መስገድና መቅበር፣ መስጂድና
ቤት ሲገቡ ወይም ሲወጡ፣ መንገድ ሲሄዱ፣ከወላጆች፣ ዘመዶች፣
ጎረቤት፣ ትላልቆችና ትናንሾች ጋር፣ የወለዱትና የተጋቡትን ሲመርቁ፣
የሞት አደጋ ያጋጠመውን በማጽናናትና ከዚህ ሌላ ባሉ ዉስጥም
ልብስ ሲለብሱ፣ ሲያወልቁና ጫማ ሲያደርጉ እስላማዊ ስርዓቶችን
መጠበቅ አለበት፡፡
አስራ ሰባተኛ ትምህርት ከሽርክና ሌሎች ወንጀሎች
ማስጠንቀቅ
ሽርክና ሌሎች ወንጀሎች በተባሉት ዉስጥ ሰባቱ ሰዉን አጥፊ
ወንጀሎች ይገኙበታል፡፡ እነሱም በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ
አስራ አራተኛ ትምህርት ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች
ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች 6 (ስድስት) ናቸው፡፡ እነሱም፡-
ከሁለቱ የቆሻሻ ማውጫ መንገዶች የወጣ ሁሉ
ከሰዉነታችን ዉስጥ የሚወጣ ነጃሳ ነገር
በእንቅልፍና በመሳሰሉት ነገራት አእምሮን መሳት
ሁለቱን ህፍረተ ገላዎች ያለ ሽፋን መንካት
የግመል ስጋን መብላት እና
ከእስሊምና መውጣት ናቸው፡፡ አላህ ከሱ ይጠብቀን
አስፈላጊ ማስታወሻ፡ ጀናዛን ማጠብ በትክክለኛው ራዕይ ዉዱን
አያጠፋም፡፡ ይህ ራዕይ የብዙሃን ዓሊሞች ራእይ ነው፤ ያጠፋል
ለማለትም ማስረጃ የለውም፡፡ ነገር ግን የአጣቢው እጅ የሟችን
ብልት ያለ ሽፋን ከነካ ዉዱእ ማድረግ ግዴታ ይሆንበታል፡፡ ሆኖም
አጣቢው የሬሳን ብልት ያለ ሽፋን መንካት የለበትም፡፡ እንደዚው
ከዓሊሞች ራዕይ ዉስጥ ተቃራኒ ፆታ ንክኪ በስሜትም ሆነ ያለ
ስሜት ብሆንም ዉዱን አያበላሽም የሚለው የተሻለ ነው፡፡ ከብልቱ
ፈሳሽ ከወጣ ግን ዉዱ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) ምስታቸውን ስመው ዉዱእ ሳያድሱ ሰግደዋሉ፡፡ በሱረት
አን-ኒሳእና አልማእዳ ዉስጥ ያለው
] ﴿ې ې ې﴾ ]النساء: 43
‹ወይም ሴቶችን ከነካችሁ› የሚለው የተፈለገው የገብረ ስጋ ግንኙነት
ነውና፡፡ ይህ የኢብን ዐባስና የብዙ ሰለፎች ራዕይ ነው፡፡
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
24 25
ይጨመቃል፡፡ በመቀጠልም አጣቢው እጁን በጨርቅ ነገር
ይጠቅልልና እስትንጃ ያደርግለታል፡፡ ከዚያም የሰላት ዉዱእን
ያደርግለታል፡፡ ቀጥለውም ጭንቅላቱንና ጽሙን በዉሃና ቁርቁራ
ወይም በመሳሰሉ ነገር ያጥባል፡፡ ከዚያም ቀኝ ጎኑን ያጥባል፤
ቀጥለው ግራውን፡፡ ቀጥለውም ለሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ
እንዲው ያጥበዋል፡፡ ሲያጥበውም ሆዱን በእጁ ይጫነዋል፡፡
የሆነ ነገር ከወጣ መውጫውን ያጥብና በጥጥ ወይም በሌላ
ነገር ይዝጋው፡፡ በዚህ ካልቆመ በጭቃ ወይም ዘመናዊ ህክምና
ባመጣ ነገር ይዝጋው፡፡ ዉዱእን ይደግምለታል፡፡ በሶስት ካልጸዳ
ወደ አምስት ወይም ሰባት ይጨምርና በልብስ ይጥረገው፡፡
በመተታጠፍያዎቹና ሱጁድ ቦታ ላይ ሽቶን ይቀባለት፡፡ ሰዉነቱን
ሁሉ ብያዳርስ የተሻለ ይሆናል፡፡ በከፈኑ ላይ እጣን ያጭስለት፡፡
ቀድሞ-ቀማስ ጥምና ጥፍሮች ረዥም ከሆኑ ይቆረጣሉ፡፡ ጸጉሩ
አይበጠርም፡፡ ብልት አከባቢ ያለው ጸጉሪም አይላጭም፤
አይገረዝምም፤ ይህ ሁሉ ማስረጃ ሲለሌለው ነው፡፡ ሴት ግን
ፀጉሯ ሶስት ጉንጉን ተጎንጉኖ ወደኋላዋ ይለቀቃል፡፡
እሬሳን መገነዝ ወንድ ከሆነ በሶስት ነጫጭ ጨርቆች፤
ቀሚስና ጥምጣም በሌላቸዉ መገነዙ ይበልጣል፡፡ ተራ በተራ
ይጠቀለልበታል፡፡ በቀሚስ በሽርጥና በአንድ ብትን መጠቅለያ
ቢገነዝ ምንም አይደል፡፡ ሴት ግን በአምስት ጨርቆች ማለትም
በቀሚስ በጉፍታ በአንድ ሽርጥና በሁለት መጠቅለያ ጨርቆች
ነዉ የምትገነዘዉ፡፡ ህጻን ልጅ ከአንድ እስከ ሦስት በሚሆን
ጨርቆች ይገነዛል፡፡ ሴት ህፃን በቀሚስና በሁለት ጨርቆች
ትገነዛለች፡፡
ክልክል ያደራጋትን ነፍስ ያለ አግባብ ማጥፋት፣ ወለድ መብላት፣
የየቲሞችን (ወላጅ አልባ ህፃናትን) ገንዘብ መብላት፣ የዘመቻ ቀን
መሸሽ እና ጥብቆች ከወንጀል ዘንጊ ምእመናትን በዝሙት መስደብ
ናቸው፡፡
ሌላው ወንጀል ደግሞ የወላጆችን ሐቅ ማጉደል፣ዝምድናን መቁረጥ፣
ሐሰት ምስክር፣ ሐሰት መሀላ፣ ጎረቤትን ማስቸገር፣ ሰዎችን በደም፣
በንብረትና በክብር ዉስጥ መበደል፣ አስካሪ መጠጥን መጠጣት፣
ቁማር መጫወት፣ ሐሜት፣ ወሬን ማቃበልና ሌሎችም አላህ ወይም
መልእክተኛው የከለከሉት ነገሮችን ሁሉ ያካትታል፡፡
አስራ ስምንተኛ ትምህርት ጀናዛ ላይ መስገድ፣
መሸኘትና መቅበር
በመጀመርያ ሟቹ ‹ላ እላሀ እለላህ› እንዲል ማስታወስ
ያስፈልጋል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- ‹ሟቾቻችሁን
ላ እላሀ እለላህ አስያዙት›› ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ ሟች
የተባለው ለሞት የቀረበና የሞት ምልክት የታየበት ሰው ነው፡፡
መሞቱ ሲረጋገጥ አይኖቹንና አፉን መገጣጠም፡፡
የሙስሊም እሬሳን ማጠብ ግዴታ ነው፡፡ በዘመቻ ዉስጥ
የሞቴ ከሆነ ግን አይታጠብም፤ አይሰገድበትም፡፡ በልብሱ
ራሱ ይቀበራል፡፡ ምክንያቱም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኡሑድ ላይ
በተገደሉት ሰዎች ላይ አልሰገዱም፤ አላጠቧቸውምም፡፡
እሬሳው ሲታጠብ እፍረተ ገላው ይሸፈናል፡፡ ከዚያም
ትንሽ ከፍ ይደረግና ከሆዱ ዉስጥ ንፋስ እንድወጣ በትንሹ
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
26 27
በሕይወት ያቆየኼውን በእስላም ላይ አቆየው፡፡ ከኛ ዉስጥ
ያሳረፍከዉን ደግማ በእምነት ላይ ዉሰደው፡፡ አላህ ሆይ!
ማረው፤ እዘንለትም፡፡ ጠብቀውም፤ ይቅርታም አድርግለት፡፡
ማረፍያዉንም አሳምርለት፤ መግቢያዉን አስፋለት፡፡ ወንጀሉንም
በዉሃ፣ ጤዛና በረዶ እጠብለት፡፡ ነጫጭ ልብሶች ከእድፍ
እንደሚፀዱ ሁሉ እሱንም ከወንጀሉ አፅዳው፡፡ ከቤቱ የተሻለ
ቤትና ከቤተሰቡ የተሻለ ቤተሰብ ቀይርለት፡፡ ጀነትም አስገባው፤
ከቀብር ቅጣትና ከእሳት ቅጣትም ጠብቀው፡፡ በቀብሩ ዉስጥም
ኣስፋለት፤ ዉሰጡንም አብራለት፡፡ አላህ ሆይ! ምንዳዉን
አትንፈገን ከሱ በኋላም አታጥምመን፡፡
በመቀጠልም አራተኛ ተክቢራ ያደርጋል፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ ወደ
ቀኝ ያሰላምታል፡፡ ከያንዳንዱ ተክቢራ ጋር እጆቹን ማንሳት
ይወደዳል፡፡
ሟቹ ህፃን ከሆነ ደግሞ ለሱ ምህረት ከመጠየቅ ይልቅ ቀጣዩን
ዱዓ ያደርጋል፡-
)اللهم اجعله فرطا وذُخْرَا لوالديه، وشفيعاَ مُجَابا، اللهم ثقل به
موازينهما، وأعظم به أجورهما، وألحقه بصالح سلف المؤمنين،
واجعله في كفالة إبراهيم عليه الصلاة والسلام، وَقِهِ برحمتك
عذاب الجحيم(.
አላህ ሆይ! ከወላጆቹ ቀድሞ በአኽራ የሚጠብቃቸው፣ የነሱ
የችግር ቀን አለኝታና ምልጃው ተቀባይነት ያለው አድርገው፡፡ አላህ
ሆይ! በርሱ የኸይር ሚዛናቸዉን አክብድላቸው፡፡ ምንዳቸዉንም
በርሱ ትልቅ አድርግላቸው፡፡ ከቀደምት ደጋግ ምእመናን ጋሪም
እሬሳን ማጠብ፣ በእሱ ላይ መስገድና የማስቀበር መብት ሟቹ
ለተናዘዘለት ሰዉ ነዉ፡፡ ከዚያን የሟቹ አባት፤ አያት፤ ወራሽ
ዘመዶች እንደየቅርበታቸዉ፡፡ ሴትን ለማጠብ ባለመብት
የተናዘዘችላት ስትሆን ከዚያም እናት፤ አያት፤ ከዚያም ሴት
ዘመዶች እንደየቅርበታቸዉ ደረጃ፡፡ ባልና ሚስት አንዱ
ሌላዉን ልያጥብ ይችላል፡፡ አቡበክር ሲድቅን ያጠቧቸዉ
ባለቤታቸዉ ነበሩ፡፡ ዐሊይ ባለቤታቸዉ ፋጥማን አጥበዋል፡፡
በሟች ላይ አሰጋገድ ስርዓት እንደሚከተለው ነው፡- አራት ጊዜ
ተክቢራ ይደረጋል፤ ቀጥሎም ሱረት አልፋቲሓን ይቀራል፡፡ ከሷ
ጋር አጫጭር ሱራ ወይም የተወሰነ አንቀፅ ቢቀራ ይመረጣል፡፡
ቀጥሎ ሁለተኛ ተክቢራ ይልና በነቢዩ (ሰዐወ) ላይ ሠለዋት
ያወርዳል፡፡ በመቀጠል ሶስተኛ ተክቢራ ብሎ የሚከተለዉን
ዱዓ ያደርጋል፡-
)اللهم اغفر لِحينا وميتِنا، وشاهدنا وغائبنا، وصغيرنا وكبيرنا،
وذَكَرِنا وأنثانَا، اللهم من أحيَيتَهُ منا فأحيه على الإسلام، ومن توفيته
منا فَتَوَفهُ على الإيمان، اللهَم اغفر له، وارحمه، وعافه، واعف عنه،
وأكرِم نُزُلَه، وَوَسع مُدخَلَه، واغسله بالماء والثلج وِالبرد، ونقه من
الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدَنس، وأبدلهُ دارا خيرا من
داره، وأهلا خيرا من أهله، وأدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر،
وعذاب النار، وافسح له في قبره، ونور له فيه، اللهم لا تَحرمنَا أجره
ولا تُضِلنا بعده(.
አላህ ሆይ! በሕይወት ላለን ለሟቾቻችንም፣ ቅርብ
ላለንና ሩቅ ላለንም፣ ለትናንሾቻችንና ለትላልቆቻችንም፣
ለወንዶቻችንና ለሴቶቻችንም ማረን፡፡ አላህ ሆይ! ከኛ ዉስጥ
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
28 29
መቃብሩ ስንዝር ያክል ከፍ ይደረጋል፤ ከተቻለ በመቃብሩ ላይ
አሸዋ ይደርግና ዉሃ ይፈሰስበታል፡፡
ሸኚዎች መቃብር ዘንድ ቆመው ለሟቹ ዱዓ ማድረግ
ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ነቢዩ (ሰዐወ) ሟችን ቀብረው ሲያበቁ
እዚያው ቆመው ቀጣዩን ይሉ ነበር፡-
استغفروا لأخيكم، واسألوا له التثبيت، فإنه الآن يسأَل
ለወንድማችሁ ምህረትን ጠይቁ፤ ፅናትንም ለምኑለት፡፡ እሱ
አሁን ይጠየቃልና፡፡
ያልተሰገደበት ሰው ከተቀበረም በኋላ በሱ ላይ መስገድ
ይፈቀድለታል፤
ምክምያቱም ነቢዩ (ሰዐወ) ተግብረውታልና፡፡ ነገር ግን በአንድ
ወር ግዜ ዉስጥ መሆን አለበት፡፡ ጊዜው ከወር በላይ ከሆነ
መቃብር ላይ መስገድ አይፈቀድም፡፡ ምክንያቱም ነቢዩ (ሰዐወ)
ሟች ተቀብሮ ከወር በኋላ አልሰገዱበትምና፡፡
የሟቹ ቤተሰቦች ለሰዎች ምግብ ማዘጋጀት አይፈቀድም፤
ምክንያቱም ጀሪር ቢን አብዱላህ አልበጀሊ እንዲህ ይላል፡-
كنا نعد الاجتماع إلى أهل الميت وصنعة الطعام بعد الدفن من «
رواه الإمام أحمد بسند حسن .» النياحة
“ከቀብር በኋላ በሟች ቤተሰብ ጋር መሰብሰብና ምግብ
ማዘጋጀትን ከጩሀት እንቆጥር ነበር፡፡” ኢማሙ አሕመድ
ሐሰን በሆነ ሰነድ ዘግበውታል፡፡
አስጠጋው፡፡ በነቢዩ ኢብራሂም ከለላ ዉስጥም ኣድርገው፡፡
በእዝነትህ ከገሀነም ቅጣትም ጠብቀው፡፡
የሚያሰግደው እማም ሟቹ ወንድ ከሆነ በጭንቅላቱ ልክ
መቆም፣ ሴት ከሆነች ደግሞ በመሐከለኛ ሰዉነቷ ልክ መቆም
ሱና ነው፡፡ ሟቾቹ ሴትና ወንድ አንድ ላይ ከሆኑ ወንዱ
በእማሙ በኩል ሲሆን ሴቷ በቅብላ በኩል ትሆናለች፡፡
ወንድ ህፃን ካለ ከሴት ይቀድማል፤ ሴት ህፃን ደግሞ ከሴት
በኋላ ትደረጋለች፡፡ የህፃኑ ራስ በወንዱ ራስ ልክ ሲሆን የሴት
መሐል ሰዉነት በወንዱ ራስ ልክ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የህፃኗ
ራስ በሴቷ ራስ ልክ፣ መሐከለኛ ሰዉነቷ በወንድ ራስ ልክ
ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰጋጆች ከኢማሙ በኋላ ይሆናሉ፤ ብቸኛ
ሆኖ ከኢማሙ በኋላ ቦታ ካላገኘ ግን በቀኙ በኩል ይቆማል፡፡
የአስክሬን አቀባበር በሸሪዓ የተደነገገው እስከ ሰዉየው
ግማሽ ድረስ መቃብሩን በጥልቀት መቆፈር፣ በቅብላ
በኩል መቃብር ዉስጥ ‹ለሕድ› ማዘጋጀት፣ ሟቹን በለሕዱ
ዉስጥ በቀኝ ጎኑ ማጋደምና ከፈኑን መፍታት ነው፡፡ ከፈኑን
ማውለቅ ግን አይፈቀድም፡፡ ጀናዛው ወንድም ሆነ ሴት ፊቱ
አይገለጥም፡፡ ከዚያም ሸክላ ለሕዱ ላይ ይደረደርና በጭቃ
ተመርጎ አፈር እንዳይደረመስበት ይደረጋል፡፡ ሸክላ ማግኘት
ካልተቻለ ከሱ ሌላ ባለው ነገር እንደ ጠውላ፣ ድንጋይ ወይም
እንጨት በመሳሰሉት ከአፈር ይጠበቃል፡፡ በመቀጠል አፈር
ይመለስበታል፡፡ በዚህ ጊዜ ቀጣዩን ዚክር ማለት ይወደዳል፡-
)بسم الله، وعلى ملة رسول الله(.
በአላህ ስም፣ በአላህ መልእክተኛ መንገድ ላይ
አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ
30 31
بكم لاحقون، نسأل الله لنا ولكم العافية، يرحم الله المتقدمين منا
.» والمستأخرين
የዚህ መቃብር ምእመናንና ሙስሊሞች ሰላም በናንተ ላይ
ይሁን፤ እኛም አላህ ካሻ ከናንተ ጋር እንገናኛለን፡፡ ለኛም
ለናንተም ሰላምን እንለምናለን፡፡ ከኛ የቀደሙትና የዘገዩትን
አላህ ይዘንላቸው፡፡
ለሴቶች ደግሞ መቃብር መዘየር አይፈቀድም፤
ምክንያቱም ነቢዩ (ሰዐወ) መቃብር የሚዘይሩ ሴቶችን
ረግመዋልና፡፡ እንደዚያዉም ሴቶች መቃብርን ከዘየሩ ፈተናና
ትእግስት ማጣት ይፈራላቸዋል፡፡ እንደዚያዉም ጀናዛን
መከተል አይፈቀድላቸዉም፤ ነቢዩ (ሰዐወ)ከልክለዋልና፡፡
መስጂድ ዉስጥ ወይም ሜዳ ላይ በአስክሬን ላይ መስገድ
ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ይፈቀዳል፡፡
የአላህ እዝነትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸዉና
በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን፡፡
ተፈፀመ!!!
ነገር ግን ሌላ ሰው ለነሱና ለእንግዶቻቸው ምግብ መስራት
ችግር የለዉም፡፡ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ለነሱ ምግብ መስራት
ይፈቀዳል፡፡ ምክንያቱም ነቢዩ (ሰዐወ) የጀዕፈር ቢን አቢ
ጣሊብ የሞት ዜና ሲደርሳቸው ሰዎች ለጀዕፈር ቤተሰብ ምግብ
እንድሰሩላቸው አዘዋልና፤ እንዲህም አሉ፡ “እነሆ! እነሱ ስራን
የሚያስፈታቸው ነገር አጋጥሟቸዋልና፡፡”
የሟች ቤተሰቦች ከተሰጣቸው ምግብ ጎረቤታቸውን ወይም
ሌላ ሰውን ጠርቶ ማብላት ችግር የለዉም፡፡ ይህ ደግሞ ከሸሪዓ
እስከሚናውቀው ድረስ የተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የለዉም፡፡
ለሴቶች ባሎቻቸው ከሆነ እንጅ ለሌላ ሰው ከሶስት ቀን በላይ
ለቅሶ መቀመጥ አይፈቀድላቸውም፡፡ ለባሎቻቸው ደግሞ
አራት ወር ከአስር ቀን ያዝናሉ፡፡ እርጉዝ ከሆነች ደግሞ እስክት
ወልድ ድረስ ትቀመጣለች፡፡ በዚህ መልኩ ትክክለኛ ሐዲስ
ከነቢዩ (ሰዐወ) ተዘግቧልና፡፡ ወንዶች ደግሞ ለማንም ለቅሶ
መቀመጥ አይፈቀድላቸዉም፡፡
ወንዶች በፈለጉ ጊዜ መቃብርን ዘይረው ዱዓ ሊያደርጉለት፤
እዝነትን ሊለምኑለትና ሞትን ማስታወስ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም
ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡- “መቃብሮችን ጎብኙ፤
እነሱ አኽራን ታስታዉሳችኋለችና፡፡” ኢማም ሙስሊም
ዘግበውታል፡፡
ሰሓቦች መቃብርን በዘየሩ ጊዜ ቀጣዩን ዱዓ እንዲያደርጉ
ያስተምሩ ነበር፡-