መጣጥፎች




ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


إن الحمد لله نحمده، ونستعينه، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا،


من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده


لا شريك له، وأشهد أن محمدًا عبده ورسوله صلى الله عليه وعلى آله وصحبه


وسلم تسليمًا كثيرًا، أما بعد.


ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው፡፡ እናመሰግነዋለን፤ እርዳታም ከሱ


እንጠይቃለን፡፡ ከነፍሳችን ክፋትና ከስራዎቻችን ጥፋት በአላህ


እንጠበቃለን፡፡ አላህ የመራውን ሰው የሚያጠመው ነገር የለም፤


አላህ ያጠመመውን ደግሞ የሚመራው የለም፡፡ ከአላህ ሌላ በሐቅ


የሚመለክ አምላክ እንደ ሌለ፤ እሱ ብቸኛ ነው አምሳያ የለውም፡፡


ሙሐመድም (ሰዐወ) የአላህ ባርያና መልእክተኛው መሆናቸውን


እመሰክራለሁ፡፡


በመቀጠል፣ በሰዎች ዉስጥ ከተስፋፉና ከተሰራጩ ወንጀሎች መሐከል


አንጋፋው፣አላህ ብቻ ማድረግ የሚችለዉን ነገር ሆኖ ሳለ ሌላን አካል


መለመን ነዉ፡፡ ለምሳሌ ሀጃዎቻችንን ወይም ጉዳዮቻችንን ማስፈጸም


የሚችል፣ ካለንበት ችግር የሚያወጣን፣ የታመመን የሚፈዉስ፣ ልጅ


አጥቶ ለተቸገረ ልጅን የሚሰጥ፣ እና የመሳሰሉትን ማድረግ የሚችለዉ


አሸናፊዉና ሀያሉ ጌታ አላህ ብቻ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን በአሁን ግዜ


እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ከአላህ ሌላ


ያለን አካል መለመን በሰዎች ዉስጥ እየተስፋፋ እና አየተሰራጨ


ያለ ድርጊት ሆኖዋል፡፡ ይህ ድርጊት የጃህሊያ ወይም የአላዋቂዎች


6


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


መንገድ ሲሆን በኢስልምና ሀይማኖት ዉስጥ ፍጹም የተከለከለ እና


በአላህ ማጋራት እንደሆነም በግልጽ ሊታወቅ ይግገባል፡፡


ይህ ስራ ዉድቅ መሆኑን በአስር መንገድ መስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡


7


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ (ሱወ)


አላህ (ሱወ) መልእክተኛውን ከሱ ሌላን መለመን ከለከለ፡፡ ለተከበረ


መልእክተኛው እንዲህ ይላል፡-





«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም


አንተ ያን ጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ፡፡››(ዩኑስ፡ 106)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ለርሱ የማይመልስለትን አካል ከአላህ


ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው


ዘንጊዎች ናቸው፡፡ ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ (ጣዖቶቹ) ለነርሱ


ጠላቶች ይኾናሉ፤ (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡


(አል-አሕቃፍ፡ 5-6)


አላህ እንዲህ ይላል፡- ‹እነሆ መስጅዶች የአላህ ብቻ ናቸው፤ ከአላህ


ጋር አንድንም አትገዙ፡፡› (አልጅን፡ 18). ይህን መሰል መልእክት የያዙ


አንቀጾች ብዙ ናቸው፡፡





9


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ (ሱወ)


ከሱ ሌላ ያለውን ትተን እሱን ብቻ እንድንለምን አዘዘን አላህ እንዲህ


ይላል፡-





“ጌታችሁም አለ፡ ‹ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያ እኔን ከመግገዛት


የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡›› (ጋፊር፡ 60)


አላህ እንዲህ ይላል፡





“ባሮቼ ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፥ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፤


የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፤ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤


በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊምመሩ ይከጀላልና፡፡›› (አልበቀራ፡ 186)


አላህ እንዲህ ይላል፡





“ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣መከራንም የሚያስወግድ፣


10


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ፤ (ይበልጣልን? ወይስ


የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡››


ትርጉሙ፡ ከአላህ ሌላ ይህን ማድረግ የሚችል አለን? ማለት ነው፡፡


መልሱም፡ የለም፤ ይህን ማድረግ የሚችለው እሱ ብቻ ነው የሚል


ይሆናል፡፡


አላህ እንዲህ ይላል፡





“ጌታዬ በማስተካከል አዘዘ፡፡ በየመስጅድ ዘንድ (እርሱን ለመገዛት)


ፊቶቻችሁን አስተካክሉ፡፡ ኀይማኖትን ለርሱ ፍጹም አድርጋችሁ ተገዙት፡፡


እንደ ጀመረያችሁ ትመለሳላችሁ› በላቸው፡፡›› (አል-አእራፍ፡ 29).


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤


ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትኾኑ «ምስጋና ለዓለማት ጌታ


ለአላህ ይኹን” የምትሉ ኾናችሁ ተገዙት፡” (ጋፊር፡ 65).


አላህ እንዲህ ይላል፡-





11


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


“ጌታችሁን ተዋርዳችሁ፣ በድብቅ ለምኑት፤እርሱ ወሰን ሀላፊዎችን


አይወድምና፡፡ በምድር ውስጥ ከተበጀች በኃላ አታበላሹ፤ ፈርታችሁትና


ከጅላችሁ ተገዙት፤ የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና፡፡”


(አል-አዕራፍ፡ 55-56)


ኢማም አትርሚዚ በዘገቡት ሀዲስ አብዱላህ ቢን ዐባስ (ረዐ) እንዲህ


ይላል፡ በጉዞ ላይ ከነብዩ (ሰዐወ) በኋላ ነበርኩኝ፣ እንዲህ አሉኝ፡


يَا غُلامُ! إِنِّي مُعَلِّمُكَ كَلِمَاتٍ: احْفَظِ اللهَ يَحْفَظْكَ، احْفَظِ اللهَ تَجِدْهُ «


تُجَاهَكَ، وَإِذَا سَأَلْتَ فاَسْأَلِ اللهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللهِ، وَاعْلَمْ أَنَّ


الُْمَّةَ لَوِ اجْتَمَعُوا عَلَى أَنْ يَنْفَعُوكَ، لَمْ يَنْفَعُوكَ إِلا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللهُ لَكَ،


وَلَوِ اجْتَمَعُوا عَلَى أَنْ يَضُرُّوكَ، لَمْ يَضُرُّوكَ إِلا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللهُ عَلَيْكَ،


.» رُفِعَتِ الَْقْلامُ، وَجَفَّتِ الصُّحُفُ


‹አንተ ልጅ እኔ ቃላቶችን አስተምርሀለው፤ የአላህን ድምበር ጠብቅ፣


አላህ ይጠብቅሀልና፡፡ አላህን ጠብቅ አላህን ፊት ለፊትህ ታገኘዋለ፡፡


በምትለምንበት ጊዜ አላህን ለምን፡፡ እርዳታን ስት-ጠይቅ ከአላህ


ጠይቅ፡፡ ሰዎች ሁሉ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ አላህ በጻፈልህ


ነገር እንጂ አይጠቅሙሁም፡፡ አንተን ለመጉዳት ቢሰበሰቡም አላህ


ባንተ ላይ በጻፈ ነገር እንጂ አይጎዱሁም፡፡ መጻፊያዎምተነስታለች፤


ወረቀቷም ደርቃለች፡፡› ሰነዱ ጠንካራ ነው፤ ትርሚዚ ሀዲሱ ሀሰን


ሰሒሕ ነው አለ፡፡





13


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ በላቀ መጽሐፉ


ውስጥ ከአላህ ሌላ የለመነ ሰው ክህደትና ሽርክ ውስጥ እንደ ገባ


ይገልጻል፡አላህ እንዲህ ይላል፡





‹ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ፣ ለርሱ በርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ


ሰው፣ ምርመራው ጌታው ዘንድ ብቻ ነው፤ እነሆ ከሓዲዎች


አይድኑም፡፡› (አል-ሙእሚኑን፡ 117)


ይህን የሰራ ሰው አንቀጹ ውስጥ እንደተጠቀሰዉ ከሓዲ ነው፡፡


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ለርሱ የማይመልስለትን ነገር ከአላህ ሌላ


ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው


ዘንጊዎች ናቸው፡፡ ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ (ጣዖቶቹ) ለነርሱ ጠላቶች


ይኾናሉ፤ (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡› (አል-


አሕቃፍ፡ 5-6).


ይህን ድርጊት፣ ከአላህ ሌላ መለመንን፣ ከፈጸመ ሰው የበለጠ በደለኛ የለም፡፡


14


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ እንዲህ ይላል፡-





«እኔ የምግገዛው ጌታዬን ብቻ ነው፤ በርሱም አንድንም አላጋራም›


በል፡፡›› (አልጅን፡ 20).


ይህ ማለት ከሱ ውጭ ያሉ ፍጡራንን በመለመን አላጋራም ነው፡፡


15


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ (ሱ.ወ)


ሰዎች ደረጃቸው የፈለገ ያክል ቢከበርም አላህ ያስቻላቸው ነገር እንጂ


ሌላን እንደ ማይችሉ ነገረን፡፡ ሁላቸውም ከአላህ ከጃይ ናቸው፡፡


እነሱ እንደኛው ሰዎች ናቸው፤ ሰውን የሚያገጥም ሁሉ እነሱንም


ያጋጥማል፡፡ ይበላሉ፤ ይጠጣሉ፤ ይታመማሉ፤ ይሞታሉ፡፡


አላህ እንዲህ ይላል፡-





‹እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤


አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡› (ፋጢር፡ 15)


አላህ ከሙሳ ሲነግረን እንዲህ ይላል፡





“ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለሚወርደው ፈላጊ ነኝ› አለ፡፡››


(አል-ቀሰስ፡ 24).


አላህ ከኢብራም ሲነግረንም እንዲህ ይላል፡


] ﴿ئۇ ئۇ ئۆ ئۆ﴾ ]الشعراء: 80


“በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡›› (አሽ-ሹዐራእ፡ 80).


ዒሣና እናቱ ምግብ ይበሉ እንደ ነበረ ነገረን፡


16


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ





“የመርየም ልጅ አልመሲሕ፣ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ


መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡


ሁለቱም ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች)


እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት፤ ከዚያም (ከእውነት) እንዴት


እነደ ሚመለሱ ተመልከት፡፡” (አል-ማኢዳህ፡ 75)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





‹የመርየምን ልጅ አልመሲሕን፣ እናቱንም፣ በምድር ያለንም ሁሉ


ለማጥፋት ቢሻ፣ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው?” (አል-ማኢዳህ፡ 17)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ከአንተ በፊት ከመልእክተኞች፣ እነሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ፣


በገበያዎች የሚሄዱ ሆነው እንጅ አልላክንም፡፡› (አልፉርቃን፡ 20)


ስለነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) አላህ እንዲህ ይላል፡-


] ﴿ ئح ئم ئى ئي ﴾ ]الزمر: 30


‹አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው፡፡› (አዝ-ዙመር፡ 30)


17


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ለማንኛውም ነገር ‹እኔ ይህንን ነገ ሰሪ ነኝ› አት በል፤ “አላህ ያሻ እንደ


ሆነ (እሠራዋለሁ)’ ብትል እንጂ፡፡” (አልከህፍ፡ 23- 24)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት፣ ወደኔ የሚወረድልኝ


አምሣያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው


መልካም ስራን ይስራ፤ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ››


በላቸው፡፡” (አል-ከህፍ፡ 110)


እንዲያውም ከዚህ ጋር አያይዞ የተወሰኑ ነብያቶችን ህዝቦቻቸው


እንደ ገደሏቸው አላህ ነገረን፡





“ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር


(ከመከተል) ትኮራላችሁን? ከፊሉን አስተባበላችሁ፤ከፊሉንም


ትገድላላችሁ፡፡” (አልበቀራ፡ 87)


በመጨረሻ የሚንደርስበት ድምዳሜ፣ ዱዓን መለመን የሚቻለው


አላህ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ እሱ በሁሉም ነገር ቻይ የሆነ ጌታ፣


በመቻሉም ከፍጡራን የተለየበት ነገር ነውና፡፡


18


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚትገዟቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው፡፡


እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤


(መመለስ ግን አይችሉም)፡፡” (አል-አዕራፍ፡ 194)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም


አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት)


ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም


እንኳን (አይችሉም)፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ


አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡” (አል-ሐጅ፡ 73)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“(የአላህ ባሮች) እነዚያ ‘ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ


መልስልን ቅጣቷ የማይለቅ ነውና’ የሚሉት ናቸው፡፡” (አልፉርቃን፡ 65)


19


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ነብያቶች፣


የተከበሩ መልእክተኞች፣ ደጋግ የአላህ ባሮችና መላኢካዎች በሁሉም


ጉዳያቸውና ሁኔታቸው ውስጥ አላህን ብቻ እንደ ሚለምኑ አላህ


ነገረን፤ እነሱን መከተል ደግሞ በሁሉም ሰው ላይ ግዴታ ነው፡፡


ዩኑስ በዓሳ ሆድ ውሰጥ ሆኖ ያደረገውን ዱዓ አላህ ነገረን፡





‹የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም


ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡


በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት


ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡ ለርሱም


ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን


እናድናለን፡፡› (አል-አምብያእ፡ 87-88)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





20


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


“ዘከሪያንም ‘ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች


ሁሉ በላጭ ነህ’ ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ለእርሱም


ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ለእርሱም የሕያን ሰጠነው፡፡ ለእርሱም


ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና


ፈሪዎች ኾነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡”


(አል-አምብያእ፡ 89-90)


አላህ ከነቢ አዩብ ሲነግረን እንዲህ ይላል፡-





“አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች


ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ” ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ለእርሱም


ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ


አስወገድን፡፡ ቤተሰቦቹንም ከእነሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ


ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው፡፡›› (አል-አምብያእ፡ 83-84)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው


21


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ነገሩን


ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት


መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት


ጠብቃቸው፡፡’ እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ «ጌታችን


ሆይ! እነርሱንም፣ ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርዮቻቸውም፣


የበጀውን ሁሉ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው፡፡


አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ነህና፡፡” (ጋፊር፡ 7-8)


ሰሒሕ ውስጥ ከኢብን ዐባስ በተዘገበ ነብዩ (ሰዐወ) የበድር ዘመቻ


ቀንእለት እንዲህ አሉ፡


» اللَّهُمَّ إِنِّي أَنْشُدُكَ عَهْدَكَ وَوَعْدَكَ، اللَّهُمَّ إِنْ شِئْتَ لَمْ تُعْبَدْ «


“ያ አላህ ሆይ! በቃል ኪዳንህና በቀጠሮህ እለምንሃለው፤ ከፈለክ


ከዚህ ቡሃላ አትመለክም፡፡››


አቡ በክር እጃቸውን ያዘና ይበቃዎታል አላቸው፡፡ ከዚያም “ጭፍሮቹ


ይበተናሉ፤ ወደ ኋላም ይሸሻሉ›› እያሉ ወጡ፡፡


አልሓፊዝ በፈትሁል ባሪ ውስጥ እንዲህ ይላል፡ ኢማም አጥ-ጠብራኒ


ዘንድ ሐሰን በሆነ ሰነድ ከኢብን መስዑድ በተዘገበው እንዲህ አለ፡


“ነብዩ ሙሐመድ የበድር ዘመቻ ቀን ጌታቸውን ከጠየቁት የበለጠ


አንድም ጠያቂ የጠፋበትን ነገር ሲያጠያይቅ ሰምተን አናዉቅም፡ ‹ያ


አላህ ሆይ! እኔ በቃል ኪዳኒህ እጠይቀሃለው› አሉ፡፡››





23


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ፍጥረተ-ዓለሙና


በውስጡ ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ በሱ ቁጥጥር ስርም ነው፤


የሱ ይዞታም ነው፡፡ ስለዚህ ሊለመን የሚገባዉ እሱ ብቻ ነው፤


ምክንያቱም ስልጣኑ የሱ ነው፤ፍጥረቱም የሱ ፍጥረት ብቻ ነው፤


ትእዛዝም የሱ ትእዛዝ ብቻ ነውና፡፡


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“አልረሕማን በዐርሹ ላይ (ለሱ በሚገባው መልኩ) ተደላደለ፡፡


በሰማያት ያለው፣ በምድርም ያለው፣ በመካከላቸውም ያለው፣ ከአፈር


በታችም ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡›› (ጣሃ፡ 5-6).


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም


የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም


የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ


ተመልካች ነው፡፡›› (አልሐዲድ፡ 4).


24


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ


አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን


ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡›› (ፋጢር፡ 14)


አላህ እንዲህ ይላል፡-


] ﴿پ پ﴾ ]الإخلاص: 4


“አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡›› (አል-እክላስ፡ 4).


አሰመድ ማለት ፍጡራን ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ወደሱ የሚጠጉ


ማለት ነው፡፡


25


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ነብያቶችና የተከበሩ


መልእክተኞች በተወሰነ ግዜ ለጉዳያቸው አላህን ለምነው


እንዳልተቀበላቸውና ፍላጎታቸው እንዳልተሳካላቸው አላህ (ሱወ)


ነገረን፡፡ አላህ ከነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) እንዲህ ሲል ነገረን፡





“አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን


ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው፡፡›› (አል-ቀሠሥ፡ 56).


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-





“ለእነርሱ ምሕረትን ለምንላቸው፤ ወይም ለእነሱ ምሕረትን


አትለምንላቸው (እኩል ነው)፡፡ ለእነሱ ሰባ ጊዜ ምሕረትን


ብትለምንላቸው አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም፡፡ ይህ እነርሱ አላህና


መልክተኛውን በመካዳቸው ነው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን


አያቀናም፡፡›› (አት-ተውባ፡ 80)


አላህ እንዲህ ይላል፡-





ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


“ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢኾኑም


እንኳ እነሱ (ከሓዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መኾናቸው ከተገለጸላቸው


በኋላ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም፡፡›› (አት-ተውባ፡ 113)


ስለ ኢብራሂም ደግሞ አላህ እንዲህ ይላል፡





“የኢብራሂምም ለአባቱ ምሕረትን መለመን ለእርሱ ገብቶለት ለነበረችው


ቃል (ለመሙላት) እንጂ ለሌላ አልነበረም፡፡ እርሱም የአላህ ጠላት


መኾኑ ለእርሱ በተገለጸለት ጊዜ ከርሱ ራቀ፤ (ተወው)፡፡ ኢብራሂም


በእርግጥ በጣም ርኅሩኅ ታጋሽ ነውና፡፡›› (አት-ተውባ፡ 114)


አላህ (ሱወ) ይህን ዱዓውን አለ መቀበሉ ግልጽ ነው፡፡


ስለ ኑህ አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡





“ኑሕም ጌታውን ጠራ፡፡ አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው፡፡


ኪዳንህም እውነት ነው፡፡ አንተ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ፡፡


(አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም


ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤


እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ” አለ፡፡ «ጌታዬ ሆይ!


27


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ


እጠበቃለሁ፡፡ ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ”


አለ፡፡›› (ሁድ፡ 45-47) ታዲያ ከአላህ በታች እነሱን እንዴት ይለምናሉ?


አሁንም በድጋሜ እንመልከት፤ የኡሁድ ዘመቻ ቀን ሙስሊሞች


በአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) መሪነት ሙሽሪኮችን በተዋጉ ግዜ በነሱ


ላይ ድል ማግኘትን ይፈልጉ ነበር፡፡ ነገር ግን አስፈላጊዉን እንቅስቃሴ


ሁሉ ከማድረጋቸዉም ጋር አልተሳካላቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት


አላህ በአሊ-ዒምራን ምእራፍ ውስጥ ብዙ ግሳጼን የያዙ እና


ለሙስሊሞች አሰተማሪ የሆኑ አንቀጾችን አወረደ፡፡


የስፊን ዘመቻ ቀን በዐሊ ቢን አቡ ጣሊብ ላይ የተከሰተውንም


እንመልከት፤ በተቃራኒው ላይ ድል ለማግኘት ሞክሮ የቻለውን


ታግሎ ነበር፡፡ ግን ፍላጎቱ አልተሳካለትም፡፡


ሑሴንንም (ረዐ) እንመልከት፡ እሱና ከሱ ጋር የነበሩ ብዙ ቤተ ሰቦቹ


እስኪገደሉ ድረስ ታግለው ተዋግተው ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከራሱም ሆነ


ከቤተሰቦቹ ምንም ነገር መከላከል አልቻለም፡፡


ታድያ እነዚያ አላህን ትተው ዐሊንና ሑሴንን የሚለምኑ የት ነው


ያሉት? ከራሳቸውም መከላከል አልቻሉም፤ በነሱና በቤተሰቦቻቻው


የተላለፈውን የአላህን ቀደር መመለስም አልቻሉም፡፡ ይህ ጉዳይ(የአላህን


ቀደር መመለስ አለመቻል)ግልጽ እና በማንምጤናማ አእምሮም ባለዉ


ሰዉየ ሚታወቅ ነገር ነው፤ አንድም ሰው ከሱ ሊያመልጥ አይችልም፡፡


ተጨባጭ ጉዳይም ስለሆነ መካዱ አይመችም፡፡ ዐሊና ሑሴን በችግር


ጊዜ ወደአላህ ይመለሱና እሱን ይለምኑ ነበር፡፡ እነሱን ወዳለው የሚል


ሰው ሁሉ ላይ እነሱን መከተል ግዴታ ይሆናል፡፡


28


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


የተወሰኑ ሰዎች ድምበር አለፉና በአላህ ቤት ውስጥ ከዕባ ዘንድ እያሉ


ራሱ፣ መቆም ሲፈልጉ ‹ያ ዐሊ!› ይላሉ፡፡ የሆነ አዋቂ ሰምቶት እንዲህ


አለው፡- “በአንድ ሰው ቤት ውስጥ ብትሆንና ከቤቱ ውስጥ የሆነ


ነገር ብትፈልግ፣ ለጉዳዩ ወደ ቤቱ ጎሮቤት ነው ምትሄደው ወይስ ባለ


ቤቱን ራሱ ነው ምትጠይቀው?›› አለው፡፡ ሰውየውም ሌላ መልስ


አጣና ባለ ቤቱውን ነው ምጠይቀው አለ፡፡


ለዚህ ሲል አላህ እንዲህ ይላል፡-





“እነዚያ እነርሱ የሚግገዟቸው ማንኛቸውም (ወደ አላህ) በጣም


ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን (ሥራ) ይፈልጋሉ፡፡


እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡ ቅጣቱንም ይፈራሉ፡፡ የጌታህ ቅጣት የሚፈራ


ነውና፡፡›› (አል-ኢስራእ፡ 57)


ሁሉም ሰው የሚገነዘበውን ሌላ ምሳሌን አብራላለው፡ አንድን ሰው


በንብረት አላህ አብቃቃው፤ ብዙ ገንዘብን ሰጠው፡፡ ብዙ ልጆችም


ነበሩት፡፡ ሁሌም ለልጆቹ ገንዘብ፣ ምግብ ወይም ልብስ ስትፈልጉ


ንገሩኝ ይል ነበር፡፡ እነኚህ ልጆች እሱን አይጠይቁም፤ ወደ ጎረቤት


ሂደው እነሱን ይጠይቁ ነበር፡፡ ልጆቹ የሰሩት ስራ ከአእምሮ ጋር


የሚሄድ ነውን ወይስ አእምሮን የሚጋጭ ቂልነት ነው? ይሄ በፍጡራን


ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ የላቀ ባህርያት ያለው አላህ ጋር የተያያዘ


ጉዳይስ እንዴት ይሁን?


ሁሉም ባሮች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም እና ችግሮቻቸውን ለመፍታት፣


ፈጣርያቸውና አምላካቸው ወደ ሆነው ወደ አላህ መመለስ አለበት፡፡


29


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


የተወሰኑ ሰዎች ከአላህ ሌላ ነቢያቶችን ለመለመን የነሱን ተዓምር


ለመስረጃነት ያቀርባሉ፡- ለምሳሌ ሙሣ በብትራቸው ድንጋይን


ሲመቱ ውሃ ይፈልቅ ነበር፤ ዒሳ ደግሞ ሙታንን ይቀሰቅስ ነበር፤


እውራንና ለምጸኛን ያድን ነበር፡፡


ለዚህ ጥያቂ መልስ የሚከተለውን አቀርባለው፡-


1ኛ፡- እነዚህ ተዓምራቶች ከአላህ የተሰጣቸው ናቸው፡፡ አላህ


(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-





«እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ


ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም


እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም


ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም


አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ


እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ


በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡” (ኣሊ ዒምራን፡ 49)


በባርያ ላይ ያለው ግዴታ እነዚህን ተዓምራት የሰጣቸውን አላህን


ብቻ መለመን ነው፡፡


2ኛ፡- በብዙ አንቀጾች ውሰጥ እንዳሳለፍነው፣ እነዚህ ነቢያቶች


አላህን ይለምኑ ነበሩ፡፡ ሰው ሁሉ እነሱን መከተል አለበት፤ እነሱ


ጥሩ አርዓያ ናቸውና፡፡


30


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


3ኛ፡- ያለፉት መረጃዎች ከዚህ በመከልከል ግልጽ አስረጅዎች


ናቸው፡፡ እንደውም የሰው ልጅ በሚችለው ጉዳይ ላይ ራሱ


አስቀድሞ በአላህ መጀመር ይመረጣል፡፡


ከአቢ ጀዕፈረ ሙሐመድ አልባቂር እነደተዘገበ እንዲህ ይላል፡-


“ወደ ፍጡራን የሚወስደው ጉዳይ ያጋጠመው ሰው በአላህ (ሱወ)


ይጀምር፡፡››1


1- ኪታብ ‹አልሙሰተጊሲን ቢላህ› የኢብን በሽክዋል 68 ገጽ


31


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ (ሱወ) እሱን ብቻ


መለመን እንዳዘዘና ከሱ ሌላን መለመን እንደ ከለከለ፣ ባሮቹ በሁሉም


ጉዳያቸው አሱን መለመን፣ ከሱ እርዳታን መፈለግና ወደሱ መመለስን


ይወዳል፡፡ ዱዓ አለህ የሚወደው ዒባዳ ነው፤ ጌታውን የሚለምን


ሰው እሱ የሚወደውንና ወደሱ የሚያቃርብ ነገርን እየሰራ ነው፡፡


የዚህ መረጃ ሐዲስ አልቁድሲ ነው፤ እሱ ታላቅ ሐዲስ ሲሆን የአላህ


መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡-


يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ «


اللَّيْلِ الآخِرُ يَقُولُ: مَنْ يَدْعُونِي، فَأَسْتَجِيبَ لَهُ مَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ، مَنْ


» يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ


“ጌታችን በሁሉም ሌሊት ወደ ቅርቢቷ አለም ሰማይ ይወርዳል፤


‹ለምኖኝ የሚመልስለት ማነው? ጠይቆኝ የሚሰጠው ማነው?


ምህረት ጠይቆውኝ የሚምረው ማነው?› ይላል፡፡››


ይህ ሐዲስ ከብዙ ሠሓቦች ተዘግቧል፡፡ ይህ ሐዲስ በሠሒሐይን፣


ሱነንና ሙስነዶች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሙተዋትር (በብዙ አቅጣጫ


የተዘገበ) ሐዲስ ነው፤ ኢማም አድ-ዳረቁጥኒ እሱን ብቻ አስመልክቶ


አንድ መጽሐፍ አለው፡፡


የአላህን ችሮታ ተመልከት፤ በሁሉም ሌሊት ባሮቹ እሱን እንዲ ጠይቁና


እንዲ ለምኑት ይጠራቸዋል፡፡ እሱ ከነሱ የተብቃቃ ነው፡፡ባርያ ይህን


32


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ታላቅ የአላህን ቸርነት ተጠቅሞ ዱዓውን ማብዛት አለበት፡፡ የልቡን


መረጋጋት፣ የነፍሱን ማረፍና የኢማኑን መጨመር በቀላሉ ያገኛል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-


] ﴿ڭ ڭ ڭ ۇۇ ۆ ۆ ۈ ۈ ٷ ۋ﴾ ]النساء: 32


“አላህንም ከችሮታው ለምኑት፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡››


(አን-ኒሳእ፡ 32)


አቡ ዘር አል-ግፋሪ (ረዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሰዐወ) ከጌታቸው


በዘገቡልን አላህ እንዲህ አለ፡-


يَا عِبَادِي إِنِّي حَرَّمْتُ الظُّلْمَ عَلَى نَفْسِي، وَجَعَلْتُهُ بَيْنَكُمْ مُحَرَّمًا، فَلَ «


تَظَالَمُوا، يَا عِبَادِي كُلُّكُمْ ضَالٌّ إِلَّ مَنْ هَدَيْتُهُ، فَاسْتَهْدُونِي أَهْدِكُمْ، يَا عِبَادِي


كُلُّكُمْ جَائِعٌ، إِلَّ مَنْ أَطْعَمْتُهُ، فَاسْتَطْعِمُونِي أُطْعِمْكُمْ، يَا عِبَادِي كُلُّكُمْ عَارٍ، إِلَّ


.»... مَنْ كَسَوْتُهُ، فَاسْتَكْسُونِي أَكْسُكُمْ


“ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በራሴ ላይ እርም አድርግያለው፤


በናንተመካከልም እርም አደረኩኝ፤ ስለዚህ አትበዳደሉ፡፡ ‹ባሮቼ


ሆይ! ሁላችሁም ጠማሞች ናችሁ እኔ የመራሁት ሲቀር፤ መመራትን


ከኔ ለምኑ እመራችዋለው፡፡ ‹ባሮቼ ሆይ! ሁላችሁም ረሃብተኞች


ናችሁ እኔ ያበላሁት ሲቀር፤ ምግብን ከኔ ፈልጉ እመግባችዋለው፡፡


ባሮቼ ሆይ! ሁላችሁም ራቁት ናችሁ ያለበስኩት ሲቀር፤ ልብስን ከኔ


ጠይቁ ኣለብሳችዋለው፡፡›› (ሙስሊም ዘግቦታል)


አቡ ሁረይራ (ረዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ


ብለዋል፡- “አላህን ያል-ለመነ ሰው አላህ ይቆጣበታል፡፡›› ኢብን ማጃህ


ዘግበውታል፡፡ ይህን ሐዲስ የተወሰኑ ሊቃወንቶች አጠንክረዉታል፤


33


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ሐዲሱ ዶዒፍ (ደካማ) ነው፡፡ ግን የቁርኣንና ሐዲስ ማስረጃ ለትርጉሙ


ይመሰክራሉ፡፡ በጉዳዩ ሁሉ አላህን የማይለምን ሰው አላህ እንደ


ሚቆጣበት ግልጽ ነው፡፡ አላህን ጌታም ሆኔ አምላክ አላደረገምና፡፡


ከዱዓዎች ዉስጥ ግዴታ የሚሆኑት አሉ፤ ለምሳሌ መመራትን አላህን


መጠየቅ፣ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-


] ﴿ٹ ٹ ٹ﴾ ]الفاتحة: ٦


“ወደ ቀጥተኛ ጎዳና ምራን፡፡›› (አልፋትሓ፡ 6) በሁለቱ ሱጁድ


መካከል እንዳለው ምህረት አላህን መጠየቅ አይነት፡፡


በአረብኛ ግጥም ውስጥ ‹አላህ ልመናውን ከተውክ ይቆጣል፤ የኣደም


ልጅ ደግሞ ሲለመን ይቆጣል› ይላል፡፡





35


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ከቁርኣንና ሐዲስ


የሆኑ ሸሪዓዊ መስረጃዎች አላህ ብቻ በሚችለው ጉዳይ ላይ ከሱ


ሌላ መለመን ክልክል መሆኑን እንዳመላከቱ ሁሉ የሰው ተፈጥሮም


ይህንኑ ያመላክታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጅን በችግርና አደጋ


ግዜ ወደሱ በመመለስና እሱን በመለመን ላይ ነው የፈጠረው፡፡


ይሄ ከሃዲዎችንም ጨምሮ በሁሉም ሰው ውስጥ ይገኛል፡፡ አላህ


ከሙሽሪኮች ነግሮን እንዲህ ይላል፡-





“እርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም


ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ


ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡


ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ


መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት)


ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ


ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡›› (ዩኑስ፡ 22)


36


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-





“በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው (አማልክት)


ሁሉ ከእርሱ (ከአላህ) በቀር ይጠፋሉ፡፡ ወደ የብስም በማድረስ


ባዳናችሁ ጊዜ (እምነትን) ትተዋላችሁ፡፡ ሰውም በጣም ከሓዲ ነው፡፡››


(አል-ኢስራእ፡ 67)


እንዲያውም እንሰሳዎችም ወደ ፈጣሪያቸው በመመለስ ላይ ነው


የተፈጠሩት፤ አላህ (ሱ.ወ) ከሡለይማን እርግብ ሲነግረን እንዲህ ይላል፡-





“(ወፉ) ዕሩቅ ያልኾነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም «ያላወቅከውን


ነገር አወቅኩ፡፡ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ፡፡ «እኔ


የምትገዛቸው የኾነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ፡፡


ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡ «እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ


ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ ሥራዎቻቸውን


ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ


እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም፡፡” (አን-ነምል፡ 22-24)


ይህ ወፍ አላህን ትተው ወደ ፍጡራን የተመለሱ ሰዎችን ስራ እንዴት እንደ


ተቃወመ ተመልከት! ምክንያቱም ይህ ፍጥረት አላህ ፍጡራንን ባጠቃላይ


ሰውን፣ ጅንን፣ ተናጋሪዎችንና የማይናገሩትንም የፈጠረበት ባህሪ ነውና፡፡


37


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ሸሪዓና ፍጥረት


ሸሪዓና ፍጥረት በዚህ ላይ እንዳመላከቱ ሁሉ ትክክለኛ አእምሮም


ይህንኑ ይደግፋል፡፡ አእምሮ ያለው ሰው እነዚህ የሚመለኩ ነገራቶች


በፍጥረታቸውና ሰውነታቸው የሱ አምሳያ መሆናቸውን ያውቃል፡፡


ታዲያ እንዴት ከአላህ ሌላ እነሱን እርዳታ ይጠይቃል? አምሳያዎቹ


ሆኖስ እያሉ እንዴት ወደነሱ ተጠግቶ ማዳንና ሲሳይን ይለምናቸዋል?


አላህ (ሱ.ወ) ከነቢዩ ሲነግረን እንዲህ ይላል፡-


﴿ئي بج بح بخ بم بى بي تج تح تخ تمتى تي ثج ثم ثى ثي جح جم


] حج حم خج خح خم سج﴾ ]الكهف: 110


«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ


ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤


መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ”


በላቸው፡፡›› (አልከህፍ፡ 110)


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-





“መልክተኞቻቸው ለእነርሱ አሉ «እኛ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ


38


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አይደለንም ግን አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ይለግሳል፡፡ ለእኛም


በአላህ ፈቃድ እንጂ ማስረጃን ልናመጣላችሁ አይገባንም፡፡ በአላህም


ላይ ምእምናኖች ይጠጉ፡፡ (አል-ኢብራሂም፡ 11)


ባሳለፍነው አንቀጽ ውስጥ እንዲህ ይላል፡-





“እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው፡፡››


(አል-አዕራፍ፡ 194)


እንዲያውም ባሮች መተግበር የሚችሉት ጉዳይ ቢሆኒም አላህን


መለመንና ወደ ባሮች መዞር ማቆም ያስፈልጋል፡፡ የሚያሳዝነው ነገር


ግን ሰዎች ሲታመሙ ወዲያው ሩቃ (ሸሪዓዊ ህክምና) ወደ ሚቀራ ሰው


ይሄዳሉ፤ ከሱ የሚጠበቀው መጀመርያ በራሱ ላይ መቅራት ነበረበት፡፡


ከሙስሊሞች ውስጥ በራሱ ላይ ሱረት አል-ፋትሓ፣ ኣየት አልኩርሲይ፣


ሙዐወዘተይንና የመሳሰሉትን መቅራት የማይችል የለም፡፡


አንድ ሰው እራሱን በራሱ ሩቃ የሚያደርግ ከሆነ የበለጠ ትግል


ማድረጉ ግልጽ ነው፡፡ የሚቀራውም ነገር ከልብ የመነጨና ከአላህ


ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለው ይሆናል፡፡ ይህ ነው የበለጠ ተቀባይነት


ማግኘቱ የሚከጀለው፡፡ እራሱን በራሱ ሩቃ አድርጎ አላህ ያዳነው


ሰው ብዙ ነው፡፡


ሌላ ከዚው ጋር የተያያዘ ነጥብ ደግሞ የተወሰኑ ሰዎች ስራ ሲፈልጉ


ወዲያው የሚያገናኛቸውን ሰው መፈለግ ይጀምራሉ፡፡ አላህ እንዲያገራለት


ወደሱ ሳይመለስ እገሌንና እገሌን ማናገር ይጀምራል፡፡ አንድ ከቁርኣን


39


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ማሰራጫ ጣብያ የሰማውትን ታሪክ አስታውሳለው፡- አንድ ሰው ስራን


ፈለገና ጉዳዩ ወደ ሚመለከተው ሰው ሄደ፤ ዞረዉም አላዩትም፡፡ በጣም


አዝኖ ወደ አንድ አሊም ሄዶ ምልጃን ጠየቀው፡፡ አሊሙም ወደ አላህ


እንዲመለስ መከረው፤ የሱን ምክር ተቀብሎከሱብሒ ሰላት በፊት ተነስቶ


ሰግዶ ዱዓ አደረገ፡፡ ከዚያ በኋላ መጀመርያ ወደ ሄደባቸው ሰዎች ሄደ፡፡


ስራውን ማግኘትም ቀለለለት፡፡ እንደውም ከዚያ በፊት ሄዶበት የነበረው


ሰዉ ‹የት ነበርክ?› ብሎ ጠየቀው፡፡


አንድ አንድ ሰዎች ለራሳቸው ዱዓ ማድረግ ሲፈልጉ ሌሎች ሰዎች


እንድያደርጉላቸው ይጠይቃሉ፤ ጌታችን እንዲህ ይላል፡-


] ﴿ڀ ٺ ٺ ٺ ٺ﴾ ]غافر: 6


“ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት


የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡›› (ጋፊር፡ 60)


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-





“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡


የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤


በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡›› (አልበቀራ፡ 186)


አንድ አሥበግ ቢን ዘይድ አልወራቅ የሚባል ሰለፍ እንዲህ ይላል፡


- “እኔና ከኔ ጋር የቆዩ ሰዎች ለሶስት ቀን ምንም ሳንበላ ቆየን፡፡ ወደ


ታናሽ ሴት ልጄ ወጣሁኝ፤ ‹አባቴ ርቦኛል› አለች፡፡ እሷን ትቼ የዉዱ


ቦታ ሄድኩኝ፤ ዉዱ አድርጌ ሁለት ረከዓ ሰገድኩ፡፡ ዱዓ ለማድረግ


40


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


እጆቼን ስዘረጋ ከዚህ በፊት የማውቀው ዱዓ ሁሉ ጠፋብኝ፡፡”ያ አላህ


ሆይ! ሲሳይን ብትከለክለኝም ዱዓን ግን አትከልክለኝ›› አልኩኝ፡፡


ቀጥሎ ያለው ዱዓ መጣልኝ፡-


اللهم خشعت الأصوات لك، وضلت الأحلام فيك، وضاقت الأشياء «


دونك، وهرب كل شيء منك إليك، وتوكل كل مؤمن عليك، فأنت الرفيع في


جلالك، وأنت البهي في جمالك، وأنت العلي في قدرك، يا من هو في علوه


دان، وفي دونه عال، وفي سلطانه قوي صل على محمد وعلى آل محمد


وافتح عليّ منك رزق، لا تجعل عليّ فيه منّة، ولا لك علي فيه في الآخرة


.» تبعة، برحمتك يا أرحم الراحمين


“ያ አላህ ሆይ! ድምጾች ሁሉ ላንተ ዝቅ አሉ፤ትእግስቶች ሁሉ አንተ


ዘንድ አለቁ፡፡ ሁሉም ነገር ወዳንተ ከጀለ፤ ሁሉም ነገር ከንተ ወዳንተ


ሸሸ፡፡ ሁሉም ሙእሚን ባንተ ላይ ተመካ፡፡ አንተ በታላቅነትህ


ከፍ ብለሃል፡፡ በዉበትህም ድምበር የለህም፡፡ አንተ በደረጃህ


የላቅክ ነህ፡፡ ከሁሉም በላይ ከመሆንህ ጋር ቅርብ የሆንክና ቅርብ


ከመሆንም ጋር ከዐርሽ በላይ የሆንክ ሆይ! በስልጣንህም ጠንካራ


የሆንክ! በሙሐመድና በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ እዝነትህን


አውርድ፡፡ የኣዛኞች ሁሉ ኣዛኝ የሆንከዉ ጌታ ሆይ! በእዝነትህ


ካንተ የሆነ ሲሳይን ለግሰኝ፡፡ መመጻደቅንና በመጨረሻይቱ አለም


መቀጣትን በሱ ውስጥ አታድርግብኝ፡፡›› ከዚያ በኋላ ወደ ቤት


ተመለስኩ፡፡ ወዲያው ታላቅ ሴት ልጄ ወደኔ መጣችና “አባቴ ሆይ!


አጎቴ ይህን ቀረጢጥ ሙሉ ብር ይዞ፤ በሱ ላይ ዱቄትን ተሸክሞ፣


በግመል ላይ ደግሞ በገበያ ያለውን ሁሉ ጭኖበት መጣ፡፡ ‹ለወንድሜ


ሰላምታዬን ንገሪልኝ፤ የሆነ ነገር ስያስፈልግህ እሄን ዱዓ አድርግ፤


ወዲያው ጉዳይህ ይፈጸማል፡፡› አለ፡፡


41


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


አሥበግ ቢን ዘይድም አለ፡- “ወላሂ እኔ አንድም ወንድም አልነበረኝም፤


ይህ ተናጋሪ ማን እንደ ሆነ አላዉቅም፡፡ ነገር ግን አላህ ሁሉም ነገር


ላይ ቻይ ነው፤ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ለዓለማቱ ጌታ ይገባው፡፡››


ከዚህ ታሪክ የምንማረው ትምህርት፣ ይህ ሰዉዬ ወደ አላህ ተመልሰው


ሁለት ረከዓ ሰገደ፤ እጆቹንም ወደ አላህ ዘረጋ፡፡ መፍትሄዉም


ወዲያው ከአላህ ዘንድ መጣለት።


አንድ ታሪክ እብን ሐዝም ከአባቱ ዘግቦልን እንዲህ አለ፡- “አንድ ግዜ


አቡ መንሱር ቢን ዓሚር ከሰዎች ጋር ተቀምጦ እያለ የሆነ ወረቀት


ወደሱ መጣ፤ ወረቀቱ አንድ ልጇ ከታሰረባት እናት ሲሆን ልጁ


ባለ ስልጣኑን በማናደደ ወንጀል ነው የታሰረዉ፡፡ ወረቀቱ እዝነትን


ይጠይቅለት ነበር፡፡ አልመንሱር ሲያነበዉ የበለጠተናደደ፡፡ ወዲያው


አስታውሳችሁኝ ብሎ እንዲገደል ለመፈረም ወረቀት ወሰደ፡፡


ይገደል የሚለውን ለመጻፍ አስቦ ይለቀቅ የሚልን ጻፈ፡፡ ወረቀቱን


ወደ ሚኒስቴሩ ሲወረውር ቀለሙን ወስዶ መጻፍ ጀመረ፡፡


አልመንሱርም “ምን እየጻፍክ ነው?›› አለ፡፡ እንዲለቀቅ ነው አለው፡፡


ወረቀቱን በመቀበል የጻፈውን ሰርዞ ‹ይሰቀል› የሚለውን ለመጻፍ


ፈልጎ አሁንም ይለቀቅ የሚልን ጻፈ፡፡ ሚኒስቴሩም ወረቀቱን


ወስደው እንዲለቀቅ መጻፉን ቀጠለ፡፡አልመንሱርም አየውና “ምን


እየጻፍክ ነው?›› አለ፡፡ ልጁ እንዲለቀቅ ነው አለው፡፡ ከመጀመርያው


የበለጠ ቁጣ ተቆጥቶ “ማነው በዚህ ያዘዘህ?›› በማለት ወረቀቱን


ወስዶ ለሶስተኛ ግዜ በመሰረዝ አሁንም ‹ይሰቀል› የሚልን ለመጻፍ


ፈልጎ ‹ይለቀቅ› የሚል ጻፈ፡፡ ሚኒስቴሩም ወረቀቱን ወስዶ ይለቀቅ


የሚለውን መጻፉን ቀጠለበት፡፡ “ምን እየጻፍክ ነው?›› አለው፡፡ ልጁ


እንዲለቀቅ ነው አለው፡፡ ይህ ንግግር ሶስተኛ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ


42


ቡርሃን አላህን መለመን ግዴታ መሆኑ


ሲመለከት ተገረመ፡፡ “እኔ ባልፈልግም ይለቀቃል፤ አላህ እንዲለቀቅ


የፈለገዉ ሰው እኔ ምንም ማድረግ አልችልም›› አለ፡፡1


ይህን ንጉስ ተመልከት፤ “ይሰቀል›› የሚለውን መጻፍ ፈልጎነበር፡፡ እሱ


ቢፈልገዉምአላህ ግን አላሳካለትም፡፡ ይህን ነገር ሶስት ግዜ ሞከረ፤


በመሰረቱ ይህን መጻፍ ይችል ነበር፡፡ አላህ እሱ የሚጽፈውን


ፊደል ቀይሮበት ይሰቀል የሚል ቦታ ይለቀቅ የሚለውን ጻፈ


እንጂ፡፡ በመጨረሻው ላይ እንዲለቀቅ አዘዘ፡፡ “አላህ እንዲለቀቅ


የፈለገዉን ሰው እኔ ልገል አልችልም›› አለ፡፡ አላህ እውነቱን ተናገረ፡


- “አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም


የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ፡፡›› (አል-አንፋል፡ 24) ይች ሴት


ልጇ እንዲለቀቅላት አላህን ለመነች፤ አላህም ተቀበላት፡፡


አቡል ዐባስ አህመድ ቢን አብዱል ሐሊም እንዲህ አለ፡- “ሰዎች


ላይ መተግበሯ ግዴታ የማይሆን የአዱንያ ጉዳይን እነሱን መለመን


ገዴታም ተወዳጅም አይደለም፡፡ ይልቁንስ የታዘዝነው አላህን


መለመን፣ ከሱ መከጀልና በሱ ላይ መመካት ነው፡፡ ሰውን መለመን


በመሰረቱ ሐራም ነው፤ ለችግር ነው የተፈቀደ፡፡ በአላህ ላይ ተመክቶ


እሱን መተው ይመረጣል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-


]8 ، ﴿ۅ ۉ ۉ ې ې ې ې﴾ ]الشرح: 7


“በጨረስክም ጊዜ ልፋ (ቀጥል)፡፡ ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል፡፡›› (አሽ-


ሸርሕ፡ 7-8).


1- ኢማም ኢብን ሐዝም 80.


አላህን እንጂ ሌላን አትከጅል ማለቱ ነው፡፡ ገጠመኝ ሁሉ ከአላህ


ነው፡፡


ተናጋሪው: አብዱላህ ቢን አብዱረሕማን አስ-ሰዕድ


ጻፊው: ሰዕድ ቢን ሙሐመድ አልቀሕጣኒ


24 ዙልቀዕዳ 1427 አመተ ህጅራ



 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ