መጣጥፎች

“እነዚያ የካዱት በፍጹም የማይቀሰሱ መኾናቸውን አሰቡ፡


«አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ ከዚያም


በሠራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው»


በላቸው፡፡” አት-ተጋቡን፡7


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


28 29


የሰላት መስፈርቶች፣


ማእዘናቱና ግዴታዎቹ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡


የሰላት መስፈርቶች ዘጠኝ ናቸው፡፡


እነሱም፡-


ሙስሊም መሆን፣ አእምሮው ጤናማ መሆን፣ መጥፎንና ጥሩን ነገር


የሚለይ እድሜ ላይ መድረስ፣ ሐደስ1ን ማስወገድ፣ ነጃሳን ማስወገድ፣


ህፍረተ ገላን መሸፈን፣ የሰላት ወቅት መግባት፣ ወደ ቂብላ (ካዕባ)


መዞር እና ኒያ ናቸው፡፡


መስፈርት አንድ፡-


ሙስሊም መሆን፡፡ የዚህ ተቃራኒ ካፊር መሆን ሲሆን ካፊር ደግሞ


የፈለገ ስራ ቢሰራም በርሱ ላይ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ለዚህም ማስረጃው


የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


1 ሐደስ ማለት ዉዱእን ማጥፋት ወይም ጀናባ መሆን ማለት ነው፡፡ እርሱን ማስወገድ


ማለት ዉዱእ ማድረግና መታጠብ ማለት ነው፡፡


ጣኦት የሚባለው ሰዎች እርሱን በማምለክ፣ እርሱን በመከተል ወይም


በመታዘዝ ድንበር ያለፉት ነው፡፡ ጣዖታት ብዙ ናቸው፡፡ ቀንደኞቹ


ግን አምስት ናቸው፡፡ እነሱም፡-


ኢብሊስ (አላህ ይርገመው)፣


ወዶ የሚመለክ ሰው፣


ሰዎች እንዲያመልኩት ወደራሱ አምልኮት የሚጣራ ሰው፣


የሩቅ እውቀትን አውቃለው ያለ ሰዉና


አላህ ካወረደው ሌላ በሰው ሰራሽ ህግ የፈረደ ሰው ናቸው፡፡


ማስረጃውም ቀጣዩ የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“በሃይማኖት ዉስጥ ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው


በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው


ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም


ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡” አልበቀራ፡256


ይህ የ“ላ እላሀ እለላህ” ትርጉም ነው፡፡ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ዉስጥ


ቀጣዩ ይገኛል “የነገሮች ሁሉ ቁንጮ እስላም ነው፤ ምሶሶው ሰላት


ሲሆን የላኛ ሻኛው በአላህ መንገድ ላይ መታገል ነው፡፡”


አላህ ሁሉንም አዋቂ ነው፡፡ የአላህ እዘነትና ሰላም በሙሐመድ፣


በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን፡፡


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


30 31


መስፈርት አራት፡


ሐደስን ማስወገድ፡፡ ይህም ማለት የሚታወቀው ዉዱእ ራሱ ነው፡፡


ይህ ሐደስ ዉዱን ያስገድዳል፡፡ የዉዱእ መስፈርቶች አስር ናቸው፡፡


እነሱም፡-


ሙስሊም መሆን፣


አእምሮው ጤናማ መሆን፣


መጥፎንና ጥሩ ነገርን የሚለይ እድሜ ላይ መድረስ፣


መነየት፣


ዉዱእ እስኪያጠናቅቁ ድረስ ላለማቋረጥ መወሰን፣


ዉዱእን የሚያፈርስን ነገር ማስወገድ፣


ከሱ በፊት በዉሃ ወይም በድንጋይ እስትንጃ ማድረግ፣


ዉሃው ንፁህና መጠቀሙ የተፈቀደ መሆን፣


ዉሃ ወደ ሰዉነት እንዳይደርስ የሚከለክልን ነገር ማስወገድ እና


ዉዱን የሚያጠፋ ነገር ከሰዉነቱ ለማይቋረጥ ሰው


የሚሰግደው የሰላት ወቅት መግባት ናቸው፡፡


የዉዱእ ግዴታዎች ስድስት ናቸው፡፡ እነሱም፡-


ፊትን መታጠብ ሲሆን ኣፍን መጉመጥመጥና ዉሃን


በአፍንጫ መሳብ ከዚው ይመደባል፡፡ ፊት የሚባለው ከላይ


ወደታች ከጭንቅላት ፀጉር መብቀያ እስከ አገጭ ሲሆን በጎን


ደግሞ ከጆሮ እስከ ጆሮ ይሆናል፡፡





“ለከሓዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲኾኑ የአላህን


መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡


እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡” አት-ተውባ፡17





“ከሥራም ወደ ሠሩት እናስባለን፡፡ የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን፡፡”


አልፉርቃን፡23


መስፈርት ሁለት፡


ጤናማ አእምሮ ያለው መሆን ነው፡፡ ተቃራኒው እብደት


ነው፡፡ እብድ ደግሞ እስኪድን ድረስ ብእር ተነስቶለታል (ስራው


አይፃፍበትም)፡፡ ማስረጃውም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡- “ብእር


ከሶስት ሰዎች ተነስቶላቸዋል፡ ያንቀላፋ ሰው እስክነቃ ድረስ፣ እብድ


እስክድን ድረስ እና ህጻን ለአቅመ አዳም እስክደርስ ድረስ፡፡”


መስፈርት ሶስት፡


ተምዪዝ (መጥፎንና ጥሩን ነገር የሚለይ እድሜ ላይ መድረስ) ነው፡፡


ተቃራኒውም ህጻንነት ሲሆን እሱም እስከ ሰባት አመት ይዘልቃል፡፡


ከዚያ በኋላ በሰላት ይታዘዛል፡፡ ማስረጃውም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል


ነው፡- “ልጆቻችሁን ሰባት ዓመት ስሞላቸው ሰላትን እዘዙሃቸው፡፡


(ባይሰግዱ) አስር ዓመት ስሞላቸው በሷ ላይ ምቷቸው፡፡ በመኝታም


ለያዩዋቸው፡፡”


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


32 33


በእንቅልፍና በመሳሰሉት ነገሮች አእምሮን መሳት፣


በግብረ ስጋ ስሜት ሴቶችን (ተቃራኒ ጾታን) መንካት፣


ሁለቱን ሀፍረተ ገላዎች ያለ ሽፋን መንካት፣


የግመል ስጋን መብላት፣


ጀናዛናን ማጠብ እና


ከእስሊምና መውጣት ናቸው፡፡ አላህ ከሱ ይጠብቀን


መስፈርት አምስት፡


ነጃሳን ማስወገድ፡- ነጃሳን የሚናስወግደው ከሶስት ነገር ነው፡፡


እነሱም ከሰውነት፣ ከልብስና ከሰላት ቦታ ናቸው፡፡ ማስረጃውም


የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


] ﴿ڭ ۇ﴾ ]المدثر: 4


“ልብስህንም አጥራ፡፡” አልሙደስር፡4


መስፈርት ስድስት፡


ሀፍረተገላን መሸፈን ነው፡፡ መልበስ እየቻለ ራቆቱን የሰገደ ሰው


ሰላቱ ዉድቅ መሆኑን ዓሊሞች ተስማምተዋል፡፡ የወንድ ሀፍረተገላ


ከእንብርት እስከ ጉልበት ሲሆን ሴት ባሮችም እንዲሁ ናቸው፡፡


ሌሎች ሴቶች ደግሞ ፊታቸው ሲቀር ሌላውን መሸፈን ግዴታ ነው፡፡


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


] ﴿ٻ ٻ ٻ ٻ پ پ پ﴾ ]الأعراف: 31


ሁለቱን እጆች ከክርኖች ጋር ማጠብ


ሙሉ ራስን ከጆሮ ጭምር ማበስ


ሁለቱን እግሮች ከቁርጭምጭሚቶች ጋር ማጠብ


የተጠቀሱትን የዉዱን ድርጊቶች ቅደም ተከተል መጠበቅ እና


ድርጊቶቹን ማከታተል ናቸው፡፡


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሰላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ)


ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም


(በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡”


አልማኢዳ፡6


የቅደም ተከተል ማስረጃም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡- “አላህ


በጀመረው ነገር ጀምሩ፡፡” ዉዱን የማከታተል ማስረጃ ደግሞ በእግሩ


ተረከዝ ላይ ሳንቲምን የሚያክል ዉሃ ሳይነካው የቀረውን ሰዉዬ


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዉዱእ እንዲደግም ማዘዛቸው ነው፡፡ ዋጅቡ ደግሞ


ካስተወሱ “ብስምላህ” ማለት ነው፡፡ ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች 8


(ስምንት) ናቸው፡፡ እነሱም፡-


ከሁለቱ የቆሻሻ ማውጫ መንገዶች የወጣ ሁሉ፣


ከሰዉነታችን ዉስጥ የሚወጣ ነጃሳ ነገር፣


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


34 35


ቂብላ እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ


ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ)


ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡” አልበቀራ፡144


መስፈርት ዘጠኝ፡


መነየት ነው፡፡ ቦታው ልብ ሲሆን በአንደበት መናገር ቢድዓ ነው፡፡


ማስረጃውም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡- “ስራዎች ትክክል ሆነው


የሚገኙት ኒያ ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ሰው የነየተውን ያገኛል፡፡”


“የአዳም ልጆች ሆይ! (ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን


በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡” አል-አዕራፍ፡31


መስፈርት ሰባት፡


የሰላቱ ወቅት መግባት ነው፡፡ ማስረጃውም የጅብሪል ሐዲስ ነው፡-


ጅብሪል በመጀመሪያ ወቅትና በመጨረሻው ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) አሰገደና


ቀጥሎም እንዲህ አለ፡- “ሙሐመድ ሆይ! ሰላት በነዚህ ሁለቱ ወቅቶች


መካከል ነው፡፡” ሌላ ማስረጃ የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


] ﴿ڻ ۀ ۀ ہ ہ ہ ہ﴾ ]النساء: 103


“ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡” አን-ኒሳእ፡103


ሌላ የወ


“ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፡፡


የጎህንም ሶላት ስገድ፡፡ የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና፡፡”


አል-ኢስራእ፡78


መስፈርት ስምንት፡


ወደ ቅብላ (ከዕባ) መዞር ነው፡፡ ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


37


የሰላት ማእዘናት አስራ አራት ናቸው


የቻለ ሰው መቆም፣ወደ ሰላት መግቢያ ተክቢራ (አላሁ አክበር)፣ሱረት


አልፋቲሓን ማንበብ፣ ሩኩዕ (ማጎንበስ)፣ ከሩኩዕ ቀጥ ብሎ መቆም፣


በሰባት አካላት ሱጁድ ማድረግ፣ ከሱጁዱ መነሳት፣ በሁለቱ


ሱጁዶች መካከል መቀመጥ፣ በሁሉም የሰላት ስራዎች ዉስጥ


መረጋጋት፣ በየማእዘናቱ መካከል ያለውን ቅደም ተከተል መጠበቅ፣


የመጨረሻውን አት-ተሕያቱን መቅራት፣ ለሱም መቀመጥ፣ በነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ እና በሁለቱም ጎን ማሰላመት ናቸው፡፡


አንደኛው ማእዘን፡


የቻለ ሰው መቆም ነው፡፡ ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


] ﴿ٱ ٻ ٻ ٻ ٻ پ پ پ﴾ ]البقرة: 238


“በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱ ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች


ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡” አልበቀራ፡238


ሁለተኛው ማእዘን፡


ወደ ሰላት መግቢያ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ማለት ነው፡፡ ማስረጃውም


የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡-“(ሰላት ውስጥ የማይፈቀዱ ነገሮችን)


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


38 39


ሶስተኛው ማእዘን፡


ሱረት አልፋቲሓን ማንበብ ነው፡፡ እሱም በሁሉም ረከዓ ውስጥ


ማእዘን ነው፡፡ ማስረጃውም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡- “ፋቲሐት


አልኪታቢን ያልቀራ ሰው ሰላት የለውም፡፡” እሷ የቁርኣን እናት ናት፡፡





በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ ይህ ደግሞ


በረከትና እርዳታን ፍለጋ ነው፡፡ “አልሐምዱ” ውዳሴ ነው፡፡ በዐረብኛ


ህግ ‹አሊፍ› እና ‹ላም› ወይም “አል” ስለምታጠቃልል ምስጋናን ሁሉ


ታጠቃልላለች፡፡ ሰው እራሱ ባልሰራው ነገር እንደ ውበት ባለው ነገር


መወደሱ ሙገሳ እንጅ ምስጋና አይባልም፡፡ “ረብ አል-ዓለሚን” ‹ረብ›


ማለት የሚመለክ ፈጣሪ፣ ስሳይ ሰጪ፣ ንጉስ፣ ተቆጣጣሪና ሁሉንም


ፍጡር በፀጋው ተንከባካቢ እንደማለት ነው፡፡ ‹አል-ዓለሚን› ከአላህ


ውጭ ያለው ሁሉ ዓለም ይባላል፡፡ አላህ የሁሉም ጌታ ነው፡፡ “አር-


ረሕማን” ለሁሉም ፍጡራን የሚደርስ እዝነት ሲሆን “አር-ረሒም”


ደግሞ ለምእምናን ብቻ የሆነች እዝነት ናት፡፡ ማስረጃውም የአላህ


(ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው፡፡” አል-አሕዛብ፡43





የፍርዱ ቀን ባለቤት፤ ቀኑ የምርመራና የምንዳ ቀን ነው፡፡ ሁሉም


እርም የሚታደርግ ተክቢራ ሲትሆን የተፈቀደ የሚታደርግ ደግሞ


ማሰላመት ናት፡፡” ከሷ ቀጥሎ የመክፈቻ ዱዓእ ያደርጋል፡፡


እሱም፡-


» سبحانك اللهم وبحمدك وتبارك اسمك وتعالى جدك ولا إله غيرك «


“ሱብሓነከ-ልላሁመ፥ ወቢሐምዲከ፥ ወተባረከ ኢስሙከ፥ ወተዓላ


ጀድዱከ፥ ወላ ኢላሀ ገይሩከ”


ትርጉም፡- “አላህ ሆይ! አንተን ከማመስገን ጋር አጠረሃለው፡፡


ስምህም ተባረከ፡፡ ክብርህም ከፍ አለ፡፡ ካንተ ሌላ በሐቅ የሚመለክ


አምላክ የለም፡፡”


ሱብሓነከ ማለት ላንተ የሚገባውን ጥራት አጠረሃለው፣ ወቢሐምዲከ


ማለት ዉዳሰ ያንተ ነው፣ ወተባረከ ኢስሙከ ማለት በረካ አንተን


በማውሳት ይገኛል፣ ወተዓላ ጀድዱከ ማለት ክብርህ ከፍ አለ ሲሆን


“ወላ ኢላሀ ገይሩከ” ማለት ደግሞ በሰማይም ሆነ በምድር ካንተ


ውጭ በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም ማለት ነው፡፡ ቀጥሎም፡-


أعوذ بالله من الشيطان الرجيم


ከአላህ እዝነት ከተባረረው ሸይጣን በአላህ (ሱወ) እጠበቃለው፡፡


“አዑዙ” ማለት አላህ ሆይ! ወዳንተ እጠጋለው፤ ባንተ እጠበቃለውም


ማለት ነው፡፡ “አሸይጣን አር-ረጂም” ከአላህ እዝነት የተባረረና የራቀ


ሸይጣን በዱንያና በኀይማኖቴ ጉዳይ ውስጥ እንዳይጎዳኝ ባንተ


እጠበቃለው ማለት ነው፡፡


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች





“አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ


ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ


ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡” አን-ኒሳእ፡69


“ያልተቆጣህባቸውን ሰዎች መንገድ” አላህ የተቆጣባቸው ሰዎች


አይሁዶች ናቸው፡፡ እውቀት አላቸው፤ በእውቀታቸው አልሰሩም፡፡


አላህ ከመንገዳቸው እንዲያርቅህ እንለምነዋለን፡፡ “ያልተሳሳቱትንም


ሰዎች መንገድ” የተሳሳቱ ሰዎች ነሳራዎች ናቸው፡፡ በመኃይምነት ላይ


አላህን ይገዛሉ፡፡ አላህ ከመንገዳቸውም እንዲያርቅህ እንለምነዋለን፡፡


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?› በላቸው፡፡ እነዚያ


እነሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት


ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው፡፡” አልከህፍ፡103-104


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- “ቀስት ቀስትን የሚከተለውን ያክል


ከእናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦችን ትከተላላችሁ፡፡ የአርጃኖ (ወከሎ)


ጉድጋድ ቢገቡ እንኳ ትገባላችሁ፡፡” ‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ!


አይሁዶችና ነሳራዎች ናቸውን?› አሉ፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) “ታዲያ ማንን


ነው!!” አሉ፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ በሌላ ሐዲስ ነቢዩ


ሰው በሰራው ስራ ይመነዳል፡፡ ጥሩ ከሰራ በጥሩ ይመነዳል መጥፎም


ከሆነ በመጥፎ ይመነዳል፡፡ ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን


እንደኾነ ምን አሳወቀህ? (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ


ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን


ለአላህ ብቻ ነው፡፡” አል-ኢንፍጣር፡17-19


ሌላ ማስረጃም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው፡- “ብልህ ማለት የነፍሱን


ስሜት ተቆጣጥሮ ከሞት በኋላ ላለው ጊዜ የሰራ ሰው ነው፡፡ ደካማ


ደግሞ ነፍሱን ስሜቷን ያስከተሌና በአላህ ላይ ከንቱ ምኞትን የተመኘ


ሰው ነው፡፡” ‹አንተን ብቻ እንገዛለን› ማለት ካንተ ውጭ አንገዛም


ማለት ነው፡፡ ይህ በባርያና በጌታው መካከል ያለው ቃልክዳን ነው፡፡


እሱም ባርያው አላህን ብቻ ለመገዛት የገባው ቃል ነው፡፡ ‹አንተን


ብቻ እርዳታን እንጠይቃለን› ማለት ከአላህ ሌላ እርዳታ ላለ መጠየቅ


ባርያው ለአላህ ቃል እየገባ ነው፡፡ ‹ቀጥተኛን መንገድ ምራን› ምራን


ማለት አመላክተነንና በዚያ ላይ አፅናን ማለት ነው፡፡ መንገዱ ደግሞ


እስላም ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ናቸው ወይም ቁርኣን ነውም


ተብሏል፡፡ ሁሉም ሀቅ ነው፡፡ ቀጥተኛ ማለት ጥሜት የሌለበት ማለት


ነው፡፡ “የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን መንገድ” የሚለው


አላህ ውለታውን የዋለላቸው ሰዎች መንገድ ነው፡፡ ማስረጃውም


የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


42 43


በሐዲስ ውስጥ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “በሰባት አካላት ሱጁድ


መውረድ ታዘዝኩኝ፡፡”


ዘጠነኛው ማእዘን፡


በሁሉም የሰላት ስራዎች ዉስጥ መረጋጋት፣


አስረኛው ማእዘን፡


በየማእዘናቱ መካከል ያለውን ቅደም ተከተል መጠበቅ ነው፡፡


ማስረጃውም ሰላቱን ያበላሸ ሰውዬ ሐዲስ ነው፡፡ አቡ ሁረይራ


(ረዐ) እንዲህ ይላል፡- “አንዴ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ተቀምጠን


እያለን አንድ ሰው ገባና ሰግዶ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሰላምታ አላቸው፡፡


ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) “ተመልሰህ ስገድ አልሰገድክምና” አሉት፡፡ ሶስት


ጊዜ እንዲህ አደረገ፡፡ ሰውየውም ቀጥሎ እንዲህ አለ ‹በሐቅ በላከህ


ጌታ ይሁንብኝ! ከዚህ በላይ ማሳመር አልችልም፤ ስለዚህም


አስተምሩኝ፡፡› ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉት፡- “ለሰላት በተነሳህ


ጊዜ ተክቢራ አድርግ፡፡ ከዚያም ከቁርኣንም የቻልከውን ያህል ቅራ፡፡


ከዚያም በሩኩዕህ ላይ እስክትረጋጋ ድረስ ሩኩዕ አድርግ፡፡ ከዚያም


ከሩኩዕ ተነስተህ እስከምትረጋጋ ድረስ ቀጥ ብለህ ቁም፡፡ ከዚያም


በሱጁድ ላይ እስከምትረጋጋ ድረስ በመቀጠል ሱጁድ አድርግ፡፡


ከዚያም እስክትረጋጋ ድረስ ከሱጁድ ቀና በልና ተቀመጥ፡፡ ከዚያም


በሱጁድ ላይ እስከምትረጋጋ ድረስ ሱጁድ አድርግ፡፡ ከዚያም


በየሰላትህ ሁሉ እንዲሁ አድርግ፡፡”


(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “አይሁዶች በ 71 ጭፍራዎች ተከፋፈሉ፡፡


ነሳራዎች ደግሞ በ 72 ጭፍሮች ተከፋፈሉ፡፡ ይህች ኡማም ገና በ 73


ትከፋፈላለች፡፡”አንዷ ብቻ ሲትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው፡፡” ‹የአላህ


መልእክተኛ ሆይ! እሷ ማን ናት?› አልን፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) “እኔና


ሰሓቦቼ ባለንበት መንገድ አምሳያ ላይ የተገኘ ሰው ነው” አሉ፡፡


አራተኛው ማእዘን፡


ሩኩዕ ማድረግ (ማጎንበስ)፣


አምስተኛው ማእዘን፡


ከሩኩዕ ቀጥ ብሎ መቆም፣


ስድስተኛው ማእዘን፡


በሰባት አካላት ላይ ሱጁድ ማድረግ፣


ሰባተኛው ማእዘን፡


ከሱጁዱ መነሳት፣


ሰምንተኛው ማእዘን፡


በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ ነው፡፡ ማስረጃውም የአላህ


(ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


] ﴿گ ڳ ڳ ڳ ڳ﴾ ]الحج: 77


“እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም


ተደፉ፡፡” አልሐጅ፡77


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


44 45


ማድረግ፣ ዘላቂነት እና ዘውታርነት የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፡፡


ከነዚህ ውስጥ አንዱን ለሌላ የሰጠ ሰው ሙሽሪክ ከህዲ ይሆናል፡፡


“አስ-ሰለዋት” ደግሞ ፀሎቶችን ሁሉ ያካትታል፡፡ አምስቱ ሰላትም ነው


ተብሏል፡፡ “ወጥ-ጠይዪባቱ ሊላህ” አላህም ጥሩ ነው፡፡ ከንግግርና


ድርጊት መልካምን እንጂ አይቀበልም፡፡ “አንቱ ነቢይ ሆይ! ሰላም


ባንቱ ላይ ይሁን፤ የአላህ እዝነትና በረከቱም ” በሚለው ለነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) ሰላም፣ እዝነትና በረከትን ትለምናለህ፡፡ የሚለመንላቸው


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከአላህ ጋር አይለመኑም፡፡ “ሰላም በኛና በደጋግ የአላህ


ባሮች ላይ ይሁን” በሚለው ደግሞ ለራስህ፣ በሰማይና በምድር ውስጥ


ላሉት ለአላህ ባሮች ሁሉ ሰላምን ትለምናለህ፡፡ “አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ


ኢልለ-ልላህ ” በምድርና በሰማይ ውስጥ ከአላህ ሌላ በሐቅ የሚመለክ


አምላክ እንደሌለ እውነተኛ ምስክር ትመሰክራለህ፡፡ ሙሐመድ


የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር ደግሞ ባርያ ናቸው


አይመለኩም፤ መልእክተኛ ናቸው አናስተባብላቸውም የሚለውን


ያስይዛል፡፡ ይልቁንስ እንታዘዛቸዋለን፤ እንከተላቸዋለንም፡፡ አላህ


በባርያነት አከበራቸው፡፡ ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው


(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡” አልፉርቃን፡ 1


አስራ ሁለተኛው ማእዘን፡


ለተሸሁድ (አት-ተሕያቱ) መቀመጥ፣


አስራ አንደኛ ማእዘን፡


የመጨረሻውን አት-ተሕያቱን መቅራት ነው፡፡ እሱም በሐዲስ


እንደተጠቀሰው ግዴታ የሆነ ማእዘን ነው፡፡ ኢብን መስዑድ (ረዐ)


እንዲህ ይላል፡- አት-ተሕያቱን መቅራት በኛ ላይ ግዴታ ከመደረጉ


በፊት “ከባሮቹ የሆነ ሰላም በአላህ ላይ ይስፈን፤ ሰላም በጅብሪልና


ሚካኢል ላይ ይስፈን” እንል ነበር፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-


“ከባሮቹ የሆነ ሰላም በአላህ ላይ ይስፈን› አትበሉ፡፡ አላህ እራሱ


ሰላም ነው፡፡ ነገር ግን (የሚቀጥለውን) በሉ፡-





“አት-ተሒያቱ ሊልላሂ፥ ወስ-ሶለዋቱ ወጥ-ጠይዪባቱ፡፡ አስ-ሰላሙ


ዐለይከ አይዩሃን- ነቢዩ ወረሕመቱልላሂ ወበረካቱሁ፡፡ አስ-ሰላሙ


ዐለይና ወዐላ ዒባዲልላሂ አስ-ሷሊሒነ፡፡ አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለ-


ልላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡፡”


ትርጉም፡- ክብሮች ሁሉ የአላህ ናቸው፤ ፀሎቶችና መልካም


ነገሮችም፡፡ አንቱ ነቢይ ሆይ! ሰላም ባንቱ ላይ ይሁን፤ የአላህ እዝነትና


በረከቱም፡፡ ሰላም በኛና በደጋግ የአላህ ባሮች ላይ ይሁን፡፡ ከአላህ


ሌላ በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደ ሌለ እመሰክራለዉ፤ ሙሐመድም


የአላህ ባርያና መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለዉ፡፡


“አት-ተሕያቱ” ማለት የሁሉም ክብር ባለቤትና ልከበር የሚገባውም


አላህ ነው፡፡ ለምሳሌ ራስህን ዝቅ ማድረግ፣ ማጎንበስ፣ ሱጁድ


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


46 47


የሰላት ዋጅባቶች ስምንት ናቸው፡፡ እነሱም፡-


ከመጀመሪያ ተክቢራ ዉጭ ያሉ ሌሎች ተክቢራዎች፣


ሩኩዕ ዉስጥ ‹ሱብሓነ ረብየል ዐዚም› (ታላቁ ጌታዬ ላንተ


ከማይገባህ ሁሉ ጥራት ይገባህ) ማለት፣


ለእማምና ብቻዉን ለሚሰግድ ሰው ‹ሰሚዐላሁ ሊመን


ሐሚደህ› (አላህ እሱን ያመሰገኔን ሰው ሰምቷል) ማለት፣


ሁሉም ሰጋጅ ‹ረበና ወለከል ሐምዱ› (ጌታችን ሆይ! ምስጋና


ያንተ ነው) ማለት፣


ሱጁድ ዉስጥ ‹ሱብሓነ ረብየል አዕላ› (የላቄ ጌታዬ ላንተ


ከማይገባህ ሁሉ ጥራት ይገባህ) ማለት፣


በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ‹ረብግፍርሊ› (ጌታዬ ሆይ! ማረኝ)


ማለት፣


የመጀመሪያውን አት-ተሕያቱን መቅራት እና


ለሱም መቀመጥ ናቸው፡፡


ከማእዘናት መካከል በመርሳትም ሆነ ሆን ተብሎ የተተወ እሱን


በመተው ሰላቱ ይበላሻል፡፡ ከዋጅባቶች ደግሞ ሆን ተብሎ የተተወ


ከሆነ እሱን በመተው ሰላቱ ይበላሻል፡፡ በመርሳት ከሆነ ደግሞ “ሱጁድ


አስ-ሰህው” ይጠግነዋል፡፡ አላህ ሁሉንም አዋቂ ነው፡፡ ተፈፀመ!!!


አስራ ሶስተኛ ማእዘን፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰላዋት ማውረድ ነው፡፡ እሱም፡-





አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትን እንዳወረድክ ሁሉ


በሙሐመድና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትህን አዉርድ፡፡ አንተ ምሰጉንና


የላቅክ ነህና፡፡ በኢብራሂምና በቤተሰቦቹ ላይ በረከት እንዳወረድከው


ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቹ ላይ በረከት አዉርድ፤ አንተ ምሰጉንና


የላቅክ ነህና፡፡


አላህ ሰለዋት አደረገ የሚባለው ባርያውን በተከበሩት የላይኞቹ


ጭፍሮች (መላእክት) ውስጥ ማወደስ ነው፡፡ ይህንን ቡኻሪ ሰሒሕ


በሆነ ኪታባቸው ውስጥ ከአቢል ዓሊያ ዘግበውት እንዲህ አለ፡-


“የአላህ ሰለዋት የሚባለው ባርያውን በተከበሩት የላይኞቹ ጭፍሮች


(መላእክት) ውስጥ ማወደስ ነው፡፡” እዝነትም ነው Z ትክክለኛው


ራዕይ የመጀመሪያው ነው፡፡ የመላእኮች ሰለዋት ምህረትን መጠየቅ


ሲሆን የሰው ልጆች ደግሞ ዱዓእ ማድረግ ነው፡፡


አስራ አራተኛው ማእዘን፡


በሁለቱም ጎን ማሰላመት ነው፡፡ “ወበረካቱሁ” እና ከሱ በኋላ ያለው


ንግግርና ድርጊት ሁሉ ሱና ነው፡፡


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


49


አልቀዋዒድ አልአርበዐህ


አራቱ መሰረታዊ መርሆዎች


የትልቁ ዙፋን ባለቤት የሆነውን ቸሩን አላህ በአዱንያና በአኽራ


እንዲወድህ፣ ባለህበት ቦታ ሁሉ የተባረከ ሰው እንዲያደርግህ፣


የተሰጠ ግዜ አመስጋኝ፣ የተፈተነ ጊዜ ታጋሽና ባጠፋ ጊዜ ምህረት


የሚጠይቅ እንዲያደርግህም እለምነዋለው፡፡ እነዚህ ሶስቱ


የመጨረሻዎቹ የስኬት አይነቶች ናቸው፡፡ አላህ እሱን ለመታዘዝ


ያቅናህና ትክክለኛው የኢብራሂም መንገድ የሚባለው ለአላህ


ኀይማኖትን ጥርት አድርገህ እሱን ብቻ መገዛትህ መሆኑን እወቀው፡፡


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-


] ﴿ڄ ڄ ڄ ڃ ڃ ڃ﴾ ]الذاريات: 56


“ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡”


አዝ-ዛርያት፡56


አላህ (ሱወ) ለዒባዳው (እሱን ለመገዛት) እንደፈጠረን ካወቅክ፣


ሰላት ያለ ዉዱእ ሰላት እንደማይባል ሁሉ አምልኮትም ያለተውሒድ


ዒባዳ እንደማይባል እወቅ፡፡ ሽንት ዉዱን እንደሚያጠፋ ሁሉ ሽርክ


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


50 51


ማን ነው?» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ


(ለምን ታጋራላችሁ?) አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡” ዩኑስ፡31


ሁለተኛው መርህ፡


እነሱም (ካፊሮቹም) እንዲህ ይሉ ነበር “እኛ እነሱን የለመንና ወደነሱ


የዞርንበት ምክንያት ወደአላህ መቃረብና ምልጃን ፍለጋ ብቻ ነው፡፡


” መቃረብን ፍለጋ ለሚለው ማስረጃው የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ


ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም» (ይላሉ)፡፡ አላህ


በዚያ እነርሱ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡


አላህ እርሱ ውሸታም ከሓዲ የኾነን ሰው አያቀናም፡፡” አዝ-ዙመር፡3


የምልጃ ማስረጃም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡


«እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና


በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው፡፡


ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡” ዩኑስ፡18


ዒባዳ ውስጥ ከገባ ዒባዳውን ያበላሻል፡፡ ሽርክ ዒባዳ ጋር ከተቀላቀለ


ዒባዳውን እንደሚያበላሽና ስራውን አጥፍተውበት ባለቤቱ እሳት


ውስጥ ዘውታሪ መሆኑን ካወቅክ፣ ባንተ ላይ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ


የሚሆነው እሱን ማወቅ እንደሆነ ታውቀለህ፡፡ አላህ ከዚህ እውቀት


ከዚህ መረብ ሊያጠራህ ይከጀላልና፡፡ እሷም በአላህ (ሱወ) ማጋራት


ናት፡፡ አላህ ሽርክን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡-





“አላህ በርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ


ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡” አን-ኒሳእ፡116


ይኸም አላህ በቁርኣን ውስጥ የተናገራቸውን አራት መሰረታዊ


መርሆዎችን በማወቅ ይሆናል፡፡ እነሱም፡-


የመጀመሪያ መርህ፡


እነዚያ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተጋደሏቸው ካፊሮች አላህ (ሱወ) ፈጣሪ፣


ስሳይ ሰጪና ተቆጣጣሪ መሆኑን እንደሚያረጋግጡና ይህን


ማረጋገጣቸው ኢስላም ውስጥ እንዳላስገባቸው ማወቅህ ነው፡፡


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና


ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው? ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ


ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


52 53


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እነሱን ሳይለያዩዋቸው ተጋደሏቸው፡፡ ማስረጃውም


የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን


ድረስ ተጋደሏቸው፡፡” አል-አንፋል፡39


ፀሓይንና ጨረቃን የሚገዙ ሰዎች እንደነበሩ ማስረጃው የአላህ


(ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና


ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን


ብቻ የምትግገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡” ፉስለት፡37


የመላእክትም ማስረጃ የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ


ሊያዛችሁ (አይገባውም)፡፡” ኣሊ ዒምራን፡80


የነቢያቶችም ማስረጃ የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





ምልጃ (ሸፋዓ) በሁለት ይከፈላል፡፡ እነሱም የተከለከለ ሸፋዓና


የተፈቀደ ሸፋዓ ናቸው፡፡ የተከለከለ ሸፋዓ የሚባለው አላህ ብቻ


የሚችለውን ነገር ከአላህ ሌላ ካለው አካል የሚፈለግ ሲሆን


ማስረጃውም የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ውስጥ ሽያጭ (መበዠት)፣


ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ


ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡” አልበቀራ፡254


የተፈቀደ ሸፋዓ የሚባለው ከአላህ (ሱወ) የሚፈለገው ሲሆን


አማላጂው በምልጃው ይከበራል፡፡ ምልጃ የሚደረግለት ደግሞ


አላህ ንግግሩንና ስራውን የወደደለት ሰው ብቻ ነው፡፡ እሱም ከአላህ


ፈቃድ በኋላ ነው፡፡ አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡-





“ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?”


አልበቀራ፡255


ሶስተኛ መርህ፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላያዬ ነገር በሚገዙ ሰዎች ላይ መጡ፡፡ ከነሱ


ውስጥ መለይካዎችን የሚገዙ አሉ፡፡ ከነሱ መካከል ነቢያቶችንና


ደጋግ ሰዎችን የሚገዙትም ነበሩ፡፡ እንዲሁም ዛፎችንና ድንጋዎችን


የሚያመልኩም ነበሩ፡፡ ፀሓይንና ጨረቃን የሚገዙም እንዲሁ ነበሩ፡፡


አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ ሶስቱ መሰረታዊ መርሆዎች


54 55


የማንጠልጠሊያ ባለቤት ትባላለች፡፡ እኛም “አንቱ የአላህ መልእክተኛ


ሆይ! እነሱ ማንጠልጠሊያ እንዳላቸው ሁሉ ለኛም ማንጠልጠሊያ


አድርጉልን” አልን፡፡…”


አራተኛ መርህ፡


የዘመናችን ሙሽርኮች ሽርካቸው ከቀደምቶች ይበልጣል፡፡


ምክንያቱም ቀደምቶች በተድላ ጊዜ ያጋራሉ፤ በችግር ጊዜ ደግሞ


አምልኮትን ለአላህ ጥርት ያደርጋሉ፡፡ የዘመናችን ሙሽርኮች ደግሞ


ሽርካቸው በተድላም ሆነ በችግር ጊዜ ቋሚ ነው፡፡ ማስረጃውም


የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ


ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም


ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡” አል-ዐንከቡት፡65


ተፈፀመ!!!


የአላህ እዝነትና ሰላም በሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና


በባልደረቦቻቸው ላይ ስፈን፡፡


“አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን


ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን?» በሚለው


ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ለእኔ ተገቢዬ ያልኾነን ነገር


ማለት ለኔ አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደ ኾነም በእርግጥ ዐውቀኸዋል፡፡


በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን በነፍስህ ውስጥ ያለውን


አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና»


ይላል፡፡” አልማኢዳ፡116


የደጋግ ሰዎች ማስረጃ የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“እነዚያ እነርሱ የሚግገዟቸው ማንኛቸውም (ወደ አላህ) በጣም


ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን (ሥራ) ይፈልጋሉ፡፡


እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡ ቅጣቱንም ይፈራሉ፡፡” አል-ኢስራእ፡57


የዛፎችና የድንጋይዎች ማስረጃ የአላህ (ሱ.ወ) ቃል ነው፡-





“አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን


(አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?)” አን-ነጅም፡19-20


በሐዲስ ውስጥ ከአቢ ዋቅድ አል-ለይሲ (ረዐ) ተዘግበው እንዲህ ይላል፡-


“እኛ ጊዜያችን ወደ ኩፍር ቅርብ ሆኖ ሳለ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ ሑነይን


ወጣን፡፡ ሙሽርኮች ለአምልኮት እሷ ዘንድ የሚቀመጡና (በረከትን


ፍለጋ) መሳሪያቸውን የሚያንጠለጥሉባት ቁርቁራ ነበረቻቸው፡፡ እሷም



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ