መጣጥፎች

ወደ ተለያዩ ህዝቦች የተላኩ ነቢያት በሙሉ ይዘው በተነሱት


ተልእኮ ውስጥ “አላህ ያለማንም ተጋሪ በብቸኝነት መመለክ


የኖርበታል፡፡ ከርሱ ውጪ ሌላን በማምለክ ሊካድ አይገባውም”


የሚል ሙሉ ስምምነት አለ፡፡


ይህ ዕውነታ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ


የለም፡፡ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” የሚለውን ቃል


ያንፀባርቃል፡፡ አንድ ሰው ወደ አላህ ሃይማኖት ሊገባ የሚችለው


በዚህ ቃል አማካኝነት ነው፡፡


የክፍል አንድ ማውጫ


ሁለቱ ምስክርነቶች፤ ትርጉማቸውና ዓላማቸው


“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም!”


ለምን እንላለን?


“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል ትርጉም


“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል መሠረቶች


ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ስለመመስከር


የአላህ በረከትና ሠላም በርሳቸው ላይ ይሁንና ነቢዩን ማወቅ


“ነብዩ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” የሚለው ቃል ትርጉም


የስድስቱ እምነት መሠረቶች


አምልኮ ማለት ምን ማለት ነው?


ሽርክ (ለአላህ ተጋሪ ማበጀት)


በአላህ ሥሞችና ባህሪያት ማመን


በመላእክት መኖር ማመን


በመለኮታዊ መፅሐፍት ማመን


በመልእክተኞት መላክ ማመን


በመጨረሻው ቀን ማመን


በአላህ ውሣኔ ማመን


> ሁለቱ ምስክርነቶች፤ ትርጉማቸውና ዓላማቸው


ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩንና መሐመድ የአላህ መልእክተኛ


መሆናቸውን እመሰክራለሁ


“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ


የለም” የምንለው ለምንድ ነው?


• በሙስሊም ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ይህን ቃል


ማረጋገጥ ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ እስልምና መግባት


ከፈለገ በቃሉ ውስጥ ባለው ፅንሰ-ሃሳብ ማመንና ቃሉን


መግለፅ ይኖርበታል፡፡


• ቃሉ ባካተተው ዕውነታ ከልቡ አምኖና የአላህን


ውዴታ ፈልጎ ቃሉን በንግግር በመግለፅ የመሰከረ ሰው


ከእሳት ቅጣት ነፃ ለመውጣት ሰበብ ይሆነዋል፡፡ ነብዩ


(ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል… “(የአላህን ውዴታ በመፈለግ


ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ


የመሰከረ ሰው አላህ በርሱ ላይ እሳትን እርም አድርጓታል፡


፡” (አል-ቡከሪ፡415)


• ይህ ቃል በውስጡ ባካተተው ፅንሰ-ሃሳብ አምኖ


የሞተ ሰው የጀነት ነዋሪ ይሆናል፡፡ ነቡዩ (ሰ.ዐ.ወ.)


እነዲህ ብለዋል … “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ


አምላክ አለመኖሩን አውቆ የሞተ ሰው ጀነት ገብቷል፡፡”


(አህመድ፡464)


• ይህ በመሆኑም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ


አምላክ አለመኖሩን ማወቀ የግዴታዎች ሁሉ ተላቁ


ግዴታ ነው፡፡


“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ


የለም” የሚለው ቃል ትርጉም


ይህ ማለት ብቸኛ ከሆነው አላህ በስተቀር በዕውነት


የሚመለከ አምላክ የለም ማለት ነው፡፡ ከተቀደሰውና


ከፍ ካለው አላህ በስተቀር ከማንም ላይ መለኮታዊነትን


መሻር ማለት ሲሆን መለኮታዊ ስልጣንን አንድና አጋር


ለሌለው አላህ ብቻ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡


«አል-ኢላህ» (አምላክ)! ማለት የሚመለክ ማለት


ነው፡፡ አንድን ነገር ያመለከ ሰው ያንን ነገር ከአላህ ሌላ


አምላክ አድርጎ ይዞታል፡፡ ከተቀደሰው፣ ከፍ ካለውና


ፈጣሪ ከሆነው አንዱ ጌታ በስተቀር የሚመለኩ ነገሮች


በሙሉ ባጢል (ሐሰት) ናቸው፡፡


አምልኮ የሚገባው ከጉድለት የጠራውና ከፍ ያለው


አላህ ብቻ ነው፡፡ ቀልቦች በውዴታ፣ በማላቅ፣ በማክበር፣


በመተናነስ፣ በመፍራት፣ በርሱ ላይ በመመካት


ያመልኩታል፡፡ ለልመናም እርሱን ይጠሩታል፡፡ ከአላህ


ውጪ ለልመና የሚጠራ የለም፡፡ እርዳታ የሚጠየቀው


እርሱ ብቻ ነው፡፡ በርሱ ካልሆነ በማንም መመካት


አይቻልም፡፡ ለርሱ ካልሆነ ለማንም አይሰገድም፡፡


የአምልኮ እርድ ለርሱ ካልሆነ ለማንም አይታረድም፡፡


አምልኮ የተባለን በሙሉ ለርሱ ብቻ ማጥራት ግዴታ


ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡፡ “አላህን ሃይማኖትን ለርሱ


ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች ሆነው ሊገዙት፣ ሶላተንም


አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልተዘዙ


ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡” (አል-በይናህ፡4)


ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም


የሚለው ቃል በማረጋገጥ፥ አላህን ጥርት አድርጎ ያመለከ


ሰው፥ ታላቅ የሆነ ደስታን ይጎናፀፋል፡፡ እርጋታና ስክነት


ያለው መልካም ህይወት ይኖራል፡፡ አላህን በብቸኝነት


ከማምለክ ሌላ፥ ለቀልብ ትክክለኛ የሆነ መረጋጋትን፣


እርካታንና ረፍት የሚሰጥ ሌላ ነገር የለም፡፡ አላህ


እንዲህ ብሎዋል፡፡ “ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ


ሆኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን…”


(አል-ነሕል፡97)


“ከአላህ በስተቀር በእውነተ የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል መሠረቶች


የዚህ ታላቅ የሆነ ቃል ትርጉምና ዓላማ ግልፅ እንዲሆንልን ከተፈለገ ሁለት መሠረቶችን ማወቁ ግድ ይለናል፡፡


የመጀመሪያው መሠረት፡- «ላ ኢላሃ» (አምላከ


የለም) የሚለው ነው፡፡ ይህ ከአላህ ውጪ ባሉ


ነገሮች ላይ አምልኮን መሻራችንን ማረጋገጫ


ቃል ነው፡፡ ማጋራትን ውድቅ ማድረጊያ ቃል


ነው፡፡ ከአላህ ሌላ በሚመለኩ ነገሮች ሁሉ


መካድ ግዴታ ነው፡፡ ከአላህ ሌላ ሰውም ሆነ


እንሰሳትም ሆነ መቃብርም ሆነ ከዋክብትም ሆነ


ሌላ ማምለክ አይቻልም፡፡


ሁለተኛው መሠረት፡- ኢልለ ላህ (ከአላህ


በስተቀር) የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ


አምልኮን ለአላህ ብቻ የምናረጋግጥበት ቃል


ነው፡፡ ሶላትን፣ ዱዓእና መመካትን የመሳሰሉ


የአምልኮ ዓይነቶችን ሁሉ ለአላህ ብቻ


የምናውልበት ማረጋገጫ ነው፡፡


1 2


የአምልኮ ዓይነቶችን በሙሉ ልንሰጥ የሚገባው አንድና


አጋር ለሌለው አላህ ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን


እንኳ ከአላሀ ውጪ ላለ ነገር አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ


ይሆናል፡፡


አላህ እንዲሀ ይላል …“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለርሱ


በርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚግገዛ ሰው ምርመራው


ጌታው ዘንድ ብቻ ነው፤ እነሆ ከሀዲዎች አይድኑም፡፡”


(አል-ሙእሚን፡117)


ከአላሀ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም


የሚለው ቃል ትርጓሜና መሠረቶች እንዲህ በሚለው


የአላህ ቃል ውስጥ ተገልጿል… “በጣዖትም የሚክድና


በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ


ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡”


(አል-በቀራህ፡256)


በዚህ የአላህ ቃል ውስጥ “በጣዖትም የሚክድ”


የሚለው ቃል የመጀመሪያ መሠረት የሆነውን “አምላክ


የለም” የሚለውን ቃል ሲሆን ያረጋገጠው “በአላህ


የሚያምን” የሚለው የጌታችን ቃል ደግሞ ሁለተኛ


መሠረት የሆነውን ከአላህ በስተቀር የሚለውን ቃል


የረጋግጥልናል፡፡


> የቀልብ እርጋታና የነፍስ እርካታ የሚገኘው የአላህን


አንድነት በማረጋገጥ ነው፡፡


ለነቢይነት ማዕረግ


ከመብቃታቸው በፊት


ለአርባ አመታት ያህል


እ.ኤ.አ. (ከ570 -610)


ከቁረይሽ ጎሳዎች ጋር


ኖሩ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ


የታላቅ ሥነ-ምግባርና የፅናት ተምሳሌት እንዲሁም


መለያ ሆነው ቆይተዋል፡፡ «ታማኙ» «እውነተኛው»


በሚሉ የቅፅል ሥሞች በገሃድ ይታወቁ ነበር፡፡ እረኛ


ነበሩ፡፡ ከዚያም በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ነብይ ከመሆናቸው


በፊትም በኢብራሒም መንገድ በመጓዝ አላህን


በብቸኝነት ያመልኩ ነበር፡፡ የጣዖትና የባዕድ


አምልኮዎችን ይርቁና ይጠየፉ ነበር፡፡


ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) ማወቅ፡-


1 ልደታቸው፡- ህይወታቸውና እድገታቸው፡-


የተወለዱት


እ.ኤ.አ. በ570


መካ ውስጥ ነው፡፡


ሲወለዱ አባታቸው በህይወት


አልነበሩም፡፡ እናታቸውንም


ያጡት ገና ልጅ ሆነው


ሳለ ነው፡፡ ተንከባክበው


ያሳደጓቸው መጀመሪያ


አያታቸው ዓብዱል ሙጠሊብ


ሲሆኑ በመቀጠል ትንሽ አደግ


እንዳሉ ደግሞ አጎታቸው አቢ-


ጣሊብ ናቸው


የነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ሙሉ ስም፡-


ሙሐመድ ቢን አብደላህ ቢን ዓብዱል ሙጠሊብ ቢን ሃሺም አል-ቁረይሺ


የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ጎሳ በዓረቦች ዘንድ እጅግ የተከበረ ጎሳ ነው፡፡


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰው ዘር ሁሉ የተላኩ መልእክተኛ ናቸው፡፡


አላህ ነቢያችን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሁሉም የሰው ዘር በጠቅላላ ልኳቸዋል፡፡ እርሳቸውን መታዘዝ


በሁሉም ሰው ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው እናንተ ሰዎች


ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልእክተኛ ነኝ፡፡” (አል-ዕራፍ፡158)


>ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)


አርባ ዓመታትን በዚህ


ሁኔታ ካሳለፉ በኋላ፥ በመካ


አቅራቢያ ከሚገኙ ተራራዎች


አንዱ በሆነው «ኑር» ተራራ


ውስጥ በሚገኘው «ሒራእ» ዋሻ


ውስጥ በመሆን በጥልቅ ተመስጦ


አላህን ያመልኩ ነበር፡፡


ከዚያም ከአላህ ዘንድ የሆነ ወህይ (ራዕይ)


ይገለፅላቸው ጀመር፡፡ የአላህ ቃል የሆነው


ቁርኣን በእርሳቸው ላይ መውረድ ጀመረ፡፡


በመጀመሪያ በርሳቸው ላይ የወረደው የቁርኣን


ቃል…”አንብብ ፥ በዚያ ሁሉን በፈጠረው


ጌታህ ስም” የሚለው ነበር


ይህ የእርሳቸው ተልዕኮ ዕውቀትን፣ ንባብን፣


ብርሃንና የቀጥተኛ ጎዳናን የማብሰሪያ


አዲስ ዘመን ጅማሮ መሆኑን ለመግለፅ ይህ


አንቀፅ ወረደ፡፡


ከዚያ በሃያ ሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ


ሌሎች የቁርኣን አናቅፅ እየተከታተሉ


ወረዱ፡፡


ተልዕኳቸው፡-


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ለሦስት


ዓመታት ያህል ሰበካቸውን በድብቅ


አካሄዱ፡፡ ከዚያም ለተከታዮቹ


አስር ዓመታት ሰበካቸውን በግልፅና


በገሃዱ አደረጉ፡፡ ነቢዩና (ሰ.ዐ.ወ.)


የእምነት ባልደረቦቻቸው (ሶሃቦች)


ይህን በማድረጋቸው፥ ጎሳዎቻቸው


ከሆኑት ቁረይሾች ከፍተኛ የሆነ


ተቃውሞ፣ ሁከትና፣ ማዋከብ


ገጠማቸው፡፡


ወደ ሐጅ ለሚመላለሱ ጎሳዎች


የእስልምና ግብዣ ቀረበላቸው፡


፡ የመዲና ነዋሪዎች ዘንድ ጥሪው


ተቀባይነትን አገኘ፡፡ ከዚያ ቀስበቀስ


ወደ መዲና ከተማ የስደት ጉዞ


ተደረገ፡፡


የዳዕዋ (የሰበካ) መጀመር፡-


በርሳቸው ላይ ቁርኣንን አወረደ፡-


አላህ፥ ከፊቱም ሆነ ከኋላው ሃሰት የሌለውን ታላቅ መፅሐፍ ቁርኣን በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ላይ


አወረደ፡፡


የነቢያትና የመልእክተኞች መደምደሚያ፡-


አላህ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ.) የላከው የመጨረሻና መደምደሚያ ነቢይ አድርጎ ነው፡፡ ከርሳቸው በኋላ የሚነሳ


አንድም ነቢይ የለም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “…ግን የአላህ መልእክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡”


(አል-አሕዛብ፡4ዐ)


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) እ.ኤ.አ. በ622 ያኔ «የስሪብ»


ትባል ወደ ነበረችው መዲና ከተማ ስደት


አደረጉ፡፡ በወቅቱ የሃምሳ ሦስት ዓመት ጎልማሳ


ነበሩ፡፡ ዳዕዋቸውን ያወገዙ የቁረይሽ ጎሳ


ባላባቶች ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) ላይ ግድያ ለመፈፀመ


አሲረው ነበር፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ኢስላም እየተጣሩ ለአስር


አመታት ያህል በመዲና ከተማ ኖሩ፡፡ ሰላት፣


ዘካና ሌሎች የሸሪዓው ህግጋቶች እንዲተገበሩ


ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡


የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ ከ622-632 ባለው ጊዜ ውሰጥ የኢሰላማዊ


ስልጣኔ መሠረት ተክለዋል፡፡ አዲስ ሙስሊም ማህበረሰብ ፈጥረዋል፡፡ ዘረኝነትና


ጎሰኝነትን አስቀርተዋል፡፡ ዕውቀትን አሰራጭተዋል፡፡ የፍትህ፣ የፅናት፣ የወንድማማችነት፣


የመረዳዳት መርህን ገንብተዋል፡፡


አንዳንድ ጎሳዎች እስልምናን በአጭሩ በማስቀረት ተነሳስተው ነበር፡፡ በዚህም


ምክንያት ብዙ ጦርነቶች ተካሂደዋል፡፡ አላህ ሃይማኖቱንና መልእክተኛውን ረድቷል፡፡


ከዚህ በኋላ በመካ ነዋሪ የሆኑ ብዙ ጎሳዎች ወደ እስልምና ገብተዋል፡፡ በዓረብ


ፔንሱላ ከተማዎች የሚኖሩ በርካታ ጎሳዎችም በራሳቸው ምርጫ ፍላጎትና ውዴታ


ወደ ዚህ ታላቅ ሃይማኖት እየተግተለተሉ ገብተዋል፡፡


ስደት፡-


እስልምናን ማሰራጨት፡-


የአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ.) በሂጅራ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ሠፈር 11፣ መልእክታቸውን


አድርሰው ጨረሱ፣ አደራቸውንም ተወጡ፡፡ አላህም ሃይማኖቱን ሙሉ በማድረግ ለሰዎች


ፀጋውን አጎናፀፈ፡፡


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የወባ ህመም አጋጠማቸው፡፡ ያደረባቸው ህመም እየፀና ሄደ በወርሃ


ረቢዑል አወል በዕለተ ሰኞ በ11ኛው ዓመተ ሒጅራ ይህን ዓለም ተሰናብተው ወደ ቀጣዩ


ዓለም ተሸጋገሩ፡፡ ይህ ማለት እ.ኤ.አ. ሜይ 8¸ 632 መሆኑ ነው፡፡


ከዚህ ዓለም ሲለዩ የስድሳ ሦስት ዓመት አዛውንት ነበሩ፡፡ ግብአተ-መሬታቸው የተፈፀመው


ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ አጠገብ እሜቴ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ነው፡፡


7 ህልፈታችው፡-


> በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና (ሐዲስ) ውስጥ የተረጋገጡ እውነታዎችን አንድ ሙስሊም አምኖ የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡


«ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው» የሚለው ቃል ትርጉም


እንዲህ ብሎ መመስከር፥ የተናገሩትን አምኖ መቀበል፣ ትዕዛዛቸውን መፈፀምና ክልከላቸውን መታቀብ ማለት ነው፡፡


አላህንም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በደነገጉትና ባስተማሩን መሠረት ብቻ ማምለክና መግገዛት ማለት ነው፡፡


ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመኔ የሚያጠቃልለው ምንና ምንድ ነው?


ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) ሁሉንም ነገር አስመልክቶ የተናገሩትን እውነት ብሎ መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም፡-


• ከህዋስ ስለራቁ ምስጢራዊ ነገሮች፣ ስለመጨረሻው ቀን፣ ስለጀነት ፀጋዎችና ስለ እሳት ቅጣት፣


• በእለተ ቂያማ ሰለሚከሰቱ ነገሮችና ምልክቶቻቸው እንዲሁም በመጨረሻው ዘመን ስለሚሆኑ ነገሮች፡-


• ስላለፉና ስለቀደሙ ህዝቦች፣ በነቢያትና ጥሪ ባደረጉላቸው ህዝቦች መካከል ስለተፈጠሩት ነገሮች


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ያዘዟቸውን ነገሮች መተግበርና ከከለከሉት ተግባራት መታቀብም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም፡-


• ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የሚያዝዙን ትዕዛዛት ከራሳቸው አፍልቀው ሳይሆን ከአላህ በሚገለፅላቸው ራዕይ አማካኝነት


መሆኑን በእርግጥኝነት ማመን ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው፥ በእርግጥ


አላህን ታዘዘ፡፡” (አል-ኒሳእ፡80)


• እርሳቸው ከከለከሏቸው ሐራም ነገሮች፣ መጥፎና ጎጂ የሆኑ ሥነ-ምግባራትና ግብረ ገቦች መታቀብም ይኖርብናል፡


፡ እነዚህን ነገሮች እንዳናደርግ የከለከሉንም እውነታው ከእኛ ቢሰወርና ባናውቀውም ለአንዳች ጥበብ አላህ ፈልጎ


ያደረገው መሆኑንና ለራሳችን ጥቅም መሆኑን ማመን ይኖርብናል፡፡


• ያዘዙንን መተግበራችን፣ ከከለከሉን መታቀባችን ዞሮ ዞሮ ለእኛ መልካም እንደሆነና በዚህም ሆነ በቀጣዩ ዓለም


ደስታን እንደሚያጎናፅፈን በእርግጠኝነት ማመን ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል …”ይታዘንላችሁም ዘንድ


አላህንና መልእክተኛውን ታዘዙ፡፡” (አሊ-ዒምራን፡132)


• ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ትዕዛዝ ሆን ብሎ መጣስ ለቅጣት የሚዳርግ ተግባር መሆኑ ተገቢ ነገር መሆኑንም ማመን


ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “…እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሉ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ


ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡” (አል-ኑር፡63)


አላህን ማምለክ የሚኖርብን ነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ.) በደነገጉት መልኩ


ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ


ዕውነታ ብዙ ነገሮችን የሚያካትት


በመሆኑ ይህን ማረጋገጥ ተገቢ


ነው፡፡ ይኽውም፡-


• አርዓያነታቸውን መከተል፡-


የአላህ መልእክተኛን (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና


(የየእለት ተግባር) ፣ መመሪያና


ህይወት በአጠቃላይ ንግግራቸውን፣


ተግባራቸውንና አፅድቆታቸውን


ጨምሮ በሁሉም የህይወት እርከናችን


በአርዓያነት ልንከተለው ይገባል፡፡


አንድ የአላህ ባሪያ የአላህ መልእክተኛን


ሱንና ይበልጥ በአርዓያነት በተከተለ


ቁጥር፥ ይበልጥ ወደ አላህ የተጠጋና


ደረጃውም ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ አላህ


እንዲህ ይላል… “በላቸው አላህን


የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ አላህ


ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለናንተ


ይምራልና፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነው፡፡”


(አሊ-ዒምራን፡31)


• የተሟላ ህግ፡- የአላህ መልእክተኛ


(ሰ.ዐ.ወ.) ይዘው የመጡት ሃይማኖትና


ህግጋት በሁሉም ረገድ ምሉዕና


ጉድለት የሌለው ነው፡፡ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.)


ያልደነገጉትን የአመልኮ ተግባር በአዲስ


መልክ መፍጠር ለማንም ሰው ቢሆን


የተፈቀደ አይደለም፡፡


• አላህ የደነገገው ህግ በሁሉም ጊዜና ቦታ


ተስማሚ ነው፡- በአላህ መፅሐፍና በነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና ውስጥ የተደነገገው ህግና


ሥርዓት በሙሉ በየትኛውም ጊዜና ቦታ


ሁሉ ተስማሚ ነው፡፡ ሰዎችን ከምንም


ካስገኛቸውና ከፈጠራቸው ጌታ በላይ


ሰዎችን የሚጠቅም ነገር የሚያውቅም


ማንም የለም፡፡ > በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና (ሐዲስ) ውስጥ የተረጋገጡ እውነታዎችን


አንድ ሙስሊም አምኖ የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡


• ከሱንና ጋር ስምሙ መሆን፡- አንድ የአምልኮ


ተግባር አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው


ከተፈለገ የአላህን ውዴታ ብቻ አስቦ (ነይቶ)


መስራትና ከአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና


ጋር የተጣጣመ መሆኑ ግድ ይላል፡፡ አላህ እንዲህ


ይላል… “የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤


መልካም ስራን ይስራ በጌታውም መግገዛት


አንድንም አያጋራ በላቸው፡፡” (አል-ከህፍ፡110)


በዚህ አንቀፅ ውስጥ «መልካም ሥራ» በሚል


የተወሳው ከአላህ መልእክተኛ ሱንና ጋር ተጣጥሞ


የተገኘ ስራ ማለት ነው፡፡


ኢስላማዊው ህግ በአምልኮ ተግባር


ውስጥ አዲስ ፈጠራ መጨመርን አጥብቆ


የከለከለው፥ ሃይማኖትን የመበላሸትና


የመለዋወጥ አደጋ እንዳይደርስበት


ለመጠበቅ ነው፡፡ የሃይማኖት የሰዎች


ዝንባሌና ሥሜት መከማቻ ከመሆን


የተጠበቀ እንዲሆን በሚል ነው፡፡


ሆኖም ግን ለአሁኑም ሆነ ለወደፊት ሰውን


ሊያገለግሉና ሊጠቅሙ የሚችሉ ነገሮችን


እንዲፈጥርና እንዲፈላሰፍ የሰውን


አዕምሮ ያነሳሳል፡፡ የዚህን ፍጥረተ-ዓለም


ምስጢራት እንዲፈታ ያበረታታል፡፡


• ሃይማኖታዊ ተግባር መፍጠር ሃራም ነው፡- አላህን


ለማምለክ በሚል፥ የአላህ መልእከተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)


ያልደነገጉትንና ሸሪዓዊ ባልሆነ መንገድ አዲስ


የአምልኮ ተግባር የፈጠረ ሰው፥ የነቢዩን መንገድ


ተፃሮ የተገኘ በመሆኑ ወንጀለኛ ይሆናል፡፡ ስራውም


ተመላሽና ተቀባይነት የሌለው ይደረጋል፡፡ አላህ


እንዲህ ብሏል… “… እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ


መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት


እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡” (አል-ኑር፡63) ነቢዩም


(ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል “በዚህ ጉዳያችን ውስጥ


ከርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ፤ ሥራው ተመላሽ


ነው፡፡” (አል-ቡኻሪ፡2550 ሙስሊም 1718)


> ስድስቱ የእምነት መሠረቶች


በኃያሉ አላህ የማመን ትርጉም፡-


የኃያሉ አላህ መኖርን እውነት ብሎ አምኖ መቀበል ነው፡፡ ጌትነቱን፣ አምላክነቱን፣ ማረጋገጥ ነው፡፡ በስሞቹንና


በባህሪያቱ ማመን ነው።


ስለ እነዚህ አራት ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ዘርዘር ባለ መልኩ እንነጋገራለን፡-


በአላህ መኖር ማመን፡-


የአላህ ፍጥረት፡-


በአላህ መኖር ማመን ሰው በተፈጥሮው የሚያረጋግጠውና ሌላ ተጨማሪ መረጃ የማያስፈልገው ነገር ነው፡፡ ይህ


በመሆኑም ምንም የተለያየ ሃይማኖትና መንገድ ቢከተሉም በጣም በርካታ ሰዎች አላህ ለመኖሩ ዕውቅና ይሰጣሉ፡፡


የእርሱን መኖር የሚያረጋግጥ ጥልቅ የሆነ ስሜት


በቀልባችን ይሰማናል፡፡ በተፈጥሮው አማኝ በሆነው


ስሜታችን ገፋፊነት መጥፎና አስቸጋሪ ነገር ሲገጥመን


ወደርሱ እንሸሻለን፡፡ አንዳንዶች ለመሸፋፈንና


ለመዘናጋት ሙከራ ቢያደርጉም፥ አላህ በእያንዳንዱ ሰው


ነፍስ ውስጥ ወደ ሃይማኖተኛነት የመዘንበል ስሜትን


ፈጥሯል፡፡


እኛም አላህ ለተጣሪዎች ምላሸን ሲሰጥ፣ ለጠያቂዎች


የጠየቁትን ሲቸር፣ ለተለማማኞች ፍላጎታቸውን


ሲያሟላ ስለምናይና ስለምንሰማ፥ ይህ ሁኔታ አላህ


ለመኖሩ እርግጠኛ መረጃ ይሆነናል፡፡


አላህ መኖሩ እጅግ ግልፅ የሆነ ነገር ነው፡ መረጃዎችን


መዘርዘርም አያስፈልግም፡፡ ግልፅ ከሚያደርጉት ነገሮች


ውስጥም፡-


• በሁሉም ሰው ዘንድ እንደሚታወቀው ማንኛውም


ድርጊት አድራጊ ሊኖረው ግድ ነው፡፡ በየጊዜው


የምንመለከተው ይህ እጅግ በርካታ ፍጥረት አስገኚና


ፈጣሪ ሊኖረው ግድ ይላል፡፡ እርሱም ኃያሉና ታላቁ


አላህ ነው፡፡ አንድ ፍጡር ያለምንም ፈጣሪ ተገኘ


ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ራሱን በራሱ ፈጥሯል


ማለትም እንዲሁ አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ


ነገር ራሱን በራሱ ሊፈጥር አይችልም፡፡ አላህ እንዲህ


ይላል “ወይስ ያለ አንዳች ፈጣሪ ተፈጠሩን ወይስ


እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?” (አልጡር፡35)


በዚህ አንቀፅ መተላለፍ የተፈለገው መልእክት “እነርሱ


ያለፈጣሪ አልተፈጠሩም፡፡ እነርሱም ራሳቸውን


አልፈጠሩም፡፡ ስለዚህ ፈጣሪያቸው ሊሆን


የሚችለው የተቀደሰውና ከፍ ያለው አላህ ነው”


የሚል ነው፡፡


አትክሮት ላለውና ላስተነተነ ሰው አላህ ለመኖሩ ማስረጃ ከሚሆኑት


ታላላቅ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሰው እራሱ ነው፡፡ አላህ የአዕምሮን፣


የስሜት ህዋሳትንና፣ ሙሉ የሆነና ስርዓት ያለው አፈጣጠርን በፀጋነት


አጎናፅፎታል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል… “በነፍሶቻችሁም ውስጥ


(ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?” (አል-ዛሪያት፡21)


• ሰማዩ፣ ምድሩ፣ ከዋክብቱ፣ ዛፎቹና ይህ ፍጥረተ-


ዓለም በአጠቃላይ የተመሠረተበት ሥርዓት ግልፅ


በሆነ ሁኔታ የሚያሳየን ነገር ቢኖር፥ የዚህ ፍጥረተ-


ዓለም ፈጣሪ አንድ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ እርሱም


ከፍ ያለውና ከጉድለት የጠራው አላህ ነው፡፡ “…


የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውና የአላህን ጥበብ


(ተመልከት)፡፡” (አል-ነምል፡88)


ክዋክብቶችን በምሳሌነት እንውሰድ፥ ፅኑ በሆነ


አኳኋንና ስርዓት ነው የሚጓዙት፡፡ ሁሉም ኮከብ


ያለምንም መሰናክልና መወላገድ በራሱ በሆነ ምህዋር


ብቻ ይጓዛል፡፡


አላህ እንዲህ ይላል “ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት


አይገባትም፤ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ


አይኾንም፤ ሁሉም በመዞሪያቸው ውሰጥ ይዋኛሉ፡፡”


(ያሲን፡40)


በኃያሉ አላህ ጌትነት ማመን


በኃያሉ አላህ ጌትነት የማመን ትርጉም፡-


ኃያሉ አላህ የሁሉም ነገር ባለቤት፣ ፈጣሪና ሲሳይን


ሰጪ ነው ብሎ አምኖ መቀበልና እውነት ነው ብሎ


በቁርጠኝነት ማረጋገጥ ነው፡፡ በጌትነቱ ማመን ማለት


ህይወት የሚሰጠውና የሚነሳው፣ የሚጠቅመውና


የሚጎዳው እርሱ ብቻ ነው ብሎ ማመን ነው፡፡


የሁሉም ትዕዛዝ ባለቤት እርሱ ነው ማለት ነው፡፡


መልካም ነገር ሁሉ በእጁ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር


ላይ ቻይ ነው፡፡ በእነዚህ ሁሉ ነገሮችም ተጋሪ የለውም


ብሎ ማመን ነው፡፡


በፍጥረተ-ዓለሙ ውስጥ ያሉትን ነገሮች የፈጠረው


አላህ ብቻውን ነው ከርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም፡፡ አላህ


እንዲህ ብሏል… “አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡


እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡” (አል-


ዙመር፡62)


የሰው ተግባር ግን አንድን ነገር ወደ ሌላ ቅርፅ መቀየር


ወይም እርስ በእርሱ ማቆራኘትና የመሳሰሉት እንጂ


ከባድና ከምንም ተነስቶ የሚፈጥረው ነገር የለም፡


፡ ሙት የሆነውን ነገር ወደ ህይወት ማምጣትም


አይችልም፡፡


ለፍጥረታት ሁሉ ሲሳይን የሚሰጠው አላህ ነው፡


፡ ከርሱ ውጪ ሲሳይን ሰጪ የለም፡፡ አላህ እንዲህ


ይላል “በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም


ምግቧ በአላህ ላይ ቢሆን እንጂ…” (ሁድ፡6)


አላህ የሁሉም ነገር ባለቤት ነው፡፡ ከርሱ ሌላ


የነገሮች እውነተኛ ባለቤት የለም፡፡ አላህ እንዲህ


ይላል “የሰማያትና የምድር በውስጣቸውም ያለው


ሁሉ ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፤ እርሱም በነገሩ


ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡» (አል-ማኢዳህ፡12ዐ)


“በምድር ላይ ምንም


ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ


በአላህ ላይ ያለ ቢሆን


እንጂ፤” (ሁድ፡6)


ይህ እንግዲህ አላህ በተግባሩ ብቸኛ ነው ብሎ ማረጋገጥ


ነው፡፡ ስለዚህ እንደሚከተለው ማመን ያስፈልጋል፡-


የሁሉም ነገር አስተናባሪ እርሱ ነው፡፡ ከርሱ ሌላ


ነገሮችን የሚየሰተናብር የለም፡፡ እንዲህ ይላል…


«ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡»


(አል-ሰጅዳህ፡5)


ሰሰው ህይወቱንና ጉዳዮቹን የሚያስተናብረው


በተገደበና በተወሰነ መልኩ ነው፡፡ ባለውና


በሚችለው ነገር ብቻ ነው የሚያስተናብረው፡


፡ ይህ ማስተናበር ደግሞ ውጤታማ ሊሆንም


ላይሆን ይችላል፡፡ ከጉድለት የጠራውና የኃያሉ


ፈጣሪ ማሰተናበር ግን አጠቃላይ ነው፡፡ ከርሱ


ቁጥጥር የሚወጣ አንዳችም ነገር የለም፡፡


ያለማንምና ያለምንም ተቃውሞ ያሻውን ፈፃሚ


ነው፡፡ እንዲህ ይላል “ንቁ፤ መፍጠርና ማዘዝ


የርሱ ብቻ ነው፤ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ)


)ላቀ፡፡» (አል-አዕራፍ፡54


በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘመን የነበሩ አረብ


አጋሪዎች በአላህ ጌትነት ያምኑ ነበር፡-


በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘመን የነበሩ


ከሃዲያን አላህ፥ ፈጣሪ፣ ንጉሥና አስተናባሪ መሆኑን


ያምኑ ነበር፡፡ ይህ እምነታቸው ግን ወደ እስልምና


እንዲገቡ አላደረጋቸውም… “ሰማያትንና ምድርንም


የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ


ነው ይላሉ፡፡” (ሉቅማን፡25)


አላህ የአለማት ጌታ መሆኑን፣ ፈጣሪ፣ ባለቤትና


አስተናባሪ መሆኑን ያረጋገጠ ሰው፣ አላህን በብቸኝነት


ሊያመልክ ይገባዋል፡፡ የአምልኮ ተግባራትን ያለማንም


ተጋሪ ለርሱ ብቻ ማዋል ይኖርበታል፡፡


አንድ ሰው የፍጥረተ-ዓለሙ ፈጣሪ፣ አስተናባሪ፣


ህይወት ሰጪና ነሺ አላህ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ


የአምልኮ ዓይነቶችን ከርሱ ውጪ ላሉ ነገሮች ማዋል


በጣም የማያስገርም ነገር ነው፡፡ ይህ አስጠያፊ በደልና


ታላቅ ወንጀል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሉቅማን


ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ያሉት “… ልጄ ሆይ! በአላህ


(ጣዖትን) አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና ያለውን


(አስታውስ)፡፡” (ሉቅማን፡13)


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) አላህ ዘንድ ታላቅ


ወንጀል ምን እንደሆነ ሲጠየቁ “አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ


ተጋሪን ማድረግህ ነው፡፡” በማለት መልሰዋል፡፡ (አል-


ቡኻሪ፡4207 ሙስሊም፡86)


በአላህ ጌትነት ማመን ቀልብን ያረጋጋል፡-


አንድ የአላህ ባሪያ በእርግጠኝነት የሚያውቅ ከሆነ፥


ከኃያሉ አላህ ውሳኔ ውጭ ሊሆን የሚችል ፍጡር


እንደሌለ ይገነዘባል፡፡ ምክንያቱም የፍጥረታት ሁሉ


ባለቤት አላህ ሲሆን ከጥበቡ ጋር በሚስማማ መልኩ


እንዳሻው የሚያደርጋቸው እርሱ ነው፡፡


የሁሉም ፈጣሪ እርሱ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ያለው


ፍጥረት ሁሉ የተፈጠረና ፈጣሪው ወደ ሆነው አላህ


ፈላጊ ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ በአላሀ እጅ ናቸው፡፡ ከርሱ


ውጭ ፈጣሪ የለም፡፡ ከርሱ ውጭ ሲሳይን ሰጭ


የለም፡፡ ከርሱ ሌላ ፍጥረተ-ዓለሙን የሚያስተናብር


የለም፡፡ ያለርሱ ፈቃድ የምትንቀሳቀስ ቅንጣት ነገር


የለችም፡፡ ያለርሱ ትዕዛዝ የምትቆምም የለችም፡፡


ይህ እምነት ያለው ሰው ቀልቡ በአላህ ላይ ብቻ


ይንጠለጠላል፡፡ እርሱን ብቻ ይጠይቃል፣ ከርሱ ብቻ


ይፈልጋል፡፡ በሁሉም የህይወት ጉዳዩ የሚመካው በርሱ


ላይ ብቻ ይሆናል፡፡ ሁሉንም የህይወት ገጠመኝ በፅናት፣


በቁርጠኝነትና በተረጋጋ መንፈስ ይጋፈጣል፡፡ ምክንያቱም


ለህይወቱ የሚያስፈልገውን ለማግኘት ሁሉንም ሰበብ


ከመምከሩ ጎን ለጎን የአላህን እርዳታም ይጠይቃል፡፡


ኃላፊነቱንም ይወጣል፡፡


ይሄኔ ነፍሱ ትረጋጋለች፡፡ ሰው ዘንድ ያለውን


አይከጅልም፡፡ ሁሉም ነገር ያለው በአላህ እጅ ነው፡፡


የሚፈልገውን ይፈጥራል፡፡ ይመርጣልም፡፡


> በአላህ ጌትነት ማመን ቀልብን ያረጋጋል


በነፍስ ውስጥ የሚላወሱ መሰረት የለሽ ነገሮችን መዋጋት


ከኢስላም በፊት ዐረቦች፣ እንዲሁም የዓለም ሕዝብ በአጠቃላይ የተረት ተረትና መሰረት የለሽ አመለካከቶችና ቅዠቶች


ሰለባ ነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ ምድርን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያጥለቀለቃት፣ አንድ ሕዝብ ከሌላኛው ያልተሻለበት ሁኔታ ነበር፡፡


በመሆኑም፣ ዐረቦች በመጀመሪያ ሰሞን ቁርኣንን ተረት ተረት ወይም ድግምት ነው ብለው ገምተው ነበር፡፡


ኢስላም ብርሃኑን ¨Å ምÉር ይዞ በመጣ ጊዜ አዕምሮን ከመሰረት የለሽ አመለካከት፣ ከተረት ተረትና ቅዠት ቀንበር ነፃ


አወጣው፡፡ ይህም የሆነው በሕግጋቱና ጥቅል መመሪያዎቹ ሲሆን፣ እነርሱም የአዕምሮንና የነፍስን ጤናማነት የሚጠብቁ


እንዲሁም ከርሱ ሌላ ያለን በመተው ወደ አላህ ብቻ ወደ መንጠልጠል የሚያመላክቱ በመሆናቸው ነው፡፡


ድግምትና አስማተኝነትን መዋጋት


ኢስላም ድግምትን ሟርትንና ጥንቆላን በሙሉ እርም አድርጓል፡፡ የማጋራትና የØመት ዓይነት አድርጎ


መድቦታል፡፡ ድግምተኛ በቅርቢቱም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ለስኬት እንደማይበቃ ተናግሯል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)


እንዲህ ብሏል፡- «ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም፡፡»


በአንድ ሙስሊም ላይ ወደ ድግምተኞች መሄድን፣ እነርሱን መጠየቅን፣ ከነርሱ በሽታ መፈወስን መከጀል፣ ወይም


ሕክምና ወይም መፍትሄ መፈለግን እርም አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገ ሰው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ በተወረደው የካደ


መሆኑንም ገልጿል፡፡ ምክንያቱም መጥቀምም መጉዳትም በአላህ እጅ ነው፡፡ የሩቅን ምስጢር ከርሱ ሌላ የሚያውቅ


የለም፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «አንድን ጠንቋይ የመጣና የጠየቀው ከዚያም እውነት ብሎ የተቀበለው ሰው


በርግጥ እሱ በሙሐመድ ላይ በተወረደው ክዷል፡፡»


> አላህን በአምልኮ አንድ ማድረግ «ከአላህ በስተቀር በእውነተ የሚመለክ አምላክ የለም» የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም ነው፡፡


መጥቀምና መጉዳት በአላህ እጅ ነው፡፡


ኢስላም ፍጡራን በጠቅላላ፣ ሰውም፣ ዛፎችም፣


ድንጋዮችም፣ ከዋክብትም፣ ምንም ያህል ቢገዝፉም፣


የአላህን ኃያልነት የሚያስረዱ ምልክቶች እንጂ ሌላ


አለመሆናቸውን ገልጿል፡፡ ከሰው ልጅ አንድም


በፍጥረተ-ዓለም ላይ ጫና ሊያሳድር የሚችል፣ አስደናቂ


ኃይል ያለው የለም፡፡ መፍጠር፣ ማዘዝና ማዘጋጀት


በርሱ ትዕዛዝ ስር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-


«ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ


አላህ ላቀ፡፡» (አል-አዕራፍ፡ 54)


የእነዚህን ፍጥረታት ግዝፈትና [ቂቅ አፈጣጠራቸውን


ያስተዋለ ሰው፣ ፈጣሪያቸው ቻይና አስተናባሪ ጌታ


መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ስለሆነም እርሱ የአምልኮ ዓይነቶች


በሙሉ ሊፈፀሙለት የሚገባ እንደሆነም ያውቃል፡፡


እርሱ ፈጣሪ ነው፡፡ ከርሱ ሌላ ያለ ሁሉ ፍጡር ነው፡፡


አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ሌሊትና ቀንም ፀሐይና


ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ


አትስገዱ፡፡ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፤ እርሱን


ብቻ የምትገዙ እንደኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡»


ስውርንና የወደፊትን ከአላህ ሌላ ማንም


አያውቅም፡፡


ኢስላም ከአላህ ሌላ ስውርንና የወደፊትን የሚያውቅ


እንደሌለ ተናግሯል፡፡ ከጠንቋይም ሆነ ከሟርተኞች


መካከል ይህን አውቃለሁ ብሎ የሚል ውሸታም


ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «የሩቅ ነገርም


መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከርሱ በስተቀር


ማንም አያውቃቸውም፡፡»


ከፍጡራን ሁሉ የተከበሩትና የላቁት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)


እንኳን ለራሳቸው ጉዳትንም ሆነ ጥቅምን አያስገኙም፡፡


ስውርና የወደፊትንም የሚያውቁ አልነበሩም፡፡ በክብርም


ሆነ ደረጃ ከርሳቸው በታች የሆነማ እንዴት (ሊያውቅና


ሊኖረው) ይችላል?!! አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «አላህ


የሻውን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት


አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ


ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ


ለሚያምኑ ህዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም


በላቸው፡፡» (አል-አዕራፍ፡ 188)


ኢስላም በአዕዋፍ ገድ ማለትንና ማሟረትን እርም


አድርጓል፡፡


ኢስላም በአዕዋፍ፣ በመልክ፣ በንግግርና በተለያዩ


ነገሮች ገድ ማለትን፣ ማሟረትንና መሰል ነገሮችን


እርም አድርጓል፡፡ መልካም ምኞትንና ለመጪው ብሩህ


ተስፋና አመለካከት ማሳደርን አዟል፡፡


በአዕዋፍ ገድ የማለት ምሳሌ፡- አንድ የወፍ ዓይነትን


ሲመለከት፣ ከመንገዱ ወይም ከጉዞው በማሟረት


የሚስተጓጎል ወይም የሚቀር፣ ወይም የወፉን ድምፅ


በጉዞ ላይ ሆኖ ሲሰማ ጉዞውን ሳያጠናቅቅ አቋርጦ


መመለስ ገድን በወፍ የመተንበይ ምሳሌ ነው፡፡ ነቢዩ


(ሰ.ዐ.ወ) እነኚህ ነገሮች ማጋራት(ሺርክ) እንደሆኑ


ገልጸዋል፡፡ «በአዕዋፍ ገድ ማለት ማጋራት ነው፡፡»


(አቡዳውድ 3912፣ ኢብኑ ማጃህ 3538)


ምክንያቱም ይህ ነገር አንድ ሙስሊም ውስጥ ከሰረፀ፣


አላህ የፍጥረተ-ዓለም አስተናባሪ ነው፤ የሩቅን የሚያውቅ


እርሱ ብቻ ነው፤ ከርሱ ሌላ ማንም አያውቅም ከሚለው


እምነቱ ጋር ይቃረናል፡፡ በዚህ ተቃራኒ ደግሞ ኢስላም


መልካም ግምትንና ጥሩን መጠበቅን፣ በአላህ ላይ መልካም


ግምት ማሳደርን አዟል፡፡ ይህን የሚጠቁሙ ቃላቶችን


ምርጫ ማድረግ እንዳለብንም ነግሯል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


መልካም ምኞትን ወይም ግምትን ይወዱ ነበር፡፡ እሱም


መልካም ቃል ነው፡፡ (አህመድ 8393)


በአላህ አምላክነት ማመን


በኃያሉ አላህ የማመን ትርጉም፡-


ግልፅም ሆነ ድብቅ የአምልኮ ዓይነቶች ሁሉ የሚገቡት


ለኃያሉ አላህ ብቻ ነው ብሎ በቁርጠኝነት አምኖ መቀበል


ማለት ነው፡ ሁሉንም የአምልኮ ዓይነቶች ለአላህ ብቻ


እናውላለን፡፡ ዱዓእን፣ ፍራቻን፣ መመካትን፣ እርዳታ


መፈለግን፣ ሶላትን፣ ዘካንና ፆምን በምሳሌነት መጥቀስ


ይቻላል፡፡ ከአላደህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፡፡


አላህ እንዲህ ብሏል፡፡ 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ