መጣጥፎች

መቅድሞች


የመቅድሞች ማውጫ


የዚህ ዓለም ታላቅ ፀጋ


በህይወት የመኖራችን ዓላማ


ኢሥላም ዓለም አቀፍ ሃይማኖት


በጌታና በባሪያው መሀል አማላጅ የለም


ኢስላመ የህይወት ሃይማኖት


የእስልምናን ሕግጋት ተማር


የሸሪዓ ሕግጋት


ሃይማኖታዊ ሕግጋትን እንዴት አውቃለሁ?


ኢስላም ፍትሀዊ ሃይማኖት ነው


ሃይማኖት ሁሉንም የህይወት ዘርፍ ያካትታል


ሥለ እስልምና በትክክል ማወቅ የምንችለው ሃይማኖቱን በመመር


መር እንጂ ሙስሊሞችን በማየት አይደለም


አምስቱ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች


መቅድሞች


22


> ኢስላም የዚህ ዓለም ታላቅ ፀጋ


ኃያሉ አላህ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፀጋዎችን ለሰው ዘር


አጎናፅፏል፡፡ ሁላችንም እነዚህን የአላህ ፀጋና ትሩፋቶች


ከማጣጣም ለአፍታም ተቆጥበን አናውቅም፡፡


ከጎደሎ ባህሪያት የጠራው ጌታ ብዙዎች ያጡትን


የማየትና የመስማት ታላቅ ፀጋን ችሮናል፡፡ አዕምሮን፣


ጤናን፣ ገንዘብን፣ ቤተሰብን ያለክፍያ ሰጥቶናል፡፡


ከዚህም አልፎ ተርፎ ፍጥረተ-ዓለሙ ሁሉ እኛን ያገለግል


ዘንድ ገርቶናል፡፡ ፀሐዩ፣ ሰማዩ፣ መሬቱ፣ ፍጥረታቱ ሁሉ


የእኛ አገልጋይ ተደርገዋል፡፡ «የአላህንም ፀጋ ብትቆጥሩ


አትዘልቋትም፤ አላህ በእርግጥ መሐሪ አዛኝ ነውና፡፡» /


አል-ነሕ፡18/


ይህም ሆኖ አጭሩ የዕድሜ ገደባችን ሲጠናቀቅ እነዚህ


ፀጋዎችም አብረው ያከትማሉ፡፡


በዚህ ዓለም /ዱንያ/ ላይ ደስታና ዕርካታን አጎናፅፎ


እስከቀጣዩ ዓለም /አኼራ/ ድረስ የሚሸጋገር አንድና


ብቸኛ ፀጋ ግን አለ፡፡ እርሱም ወደ ኢስላም ጎዳና


የመመራት ፀጋ ነው፡፡ ይህ አላህ ለባሮቹ ያጎናፀፈው


ታላቅ ፀጋ ነው፡፡


ይህ በመሆኑም ነው፥ አላህ ከሌሎች ፀጋዎች አስበልጦ


ይህንን ፀጋ ወደ ራሱ ያስጠጋው፡፡ እንዲህ ይለናል «…


ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ፀጋዬንም


በናንተ ላይ ፈፀምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት


በኩል ወደድኩ፤»/አል-ማኢዳህ፡3/


አንድን ሰው ከጨለማዎች ወደ ብርሃን በማውጣትና


እርሱ ወደ ወደደው ሃይማኖት ከመምራት የበለጠ ታላቅ


ፀጋ አላህ ለሰው ልጅ አጎናፅፎዋልን?! አላህ ለሰው ይህን


ፀጋ የቸረው፥ በህይወት የተገኘበት ዋንኛ ዓላማ የሆነውን


አላህን የመገዛት ተልዕኮ በአግባቡ ያሳካ ዘንድ ነው፡፡


ሰው ይህን በማድረጉ በዚህ ዓለም ላይ ደስታን ሲያገኝ


በቀጣዩ ዓለም ደግሞ የማይቋረጥ ምንዳ ይጠብቀዋል፡፡


አላህ ከሰዎች ሁሉ የበለጥን ምርጥ ህዝቦች እንድንሆን


አድርጎ በመምረጥ፥ ሰላም በነርሱ ላይ ይሁንና የነቢያትና


የመልእክተኞች ሁሉ ጥሪ የሆነውን «ከአላህ በስተቀር


በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም» የሚለውን ኃይለ-


ቃል እንድናነግብ ማድረጉ ለእኛ ታላቅ ፀጋ ነው፡፡ ከዚህ


የበለጠ ታላቅ ፀጋና በረከትስ ይኖራል?


አንዳንድ አላዋቂ ሰዎች ሙስሊም የሆኑት በፍፁም


ፈቃዳቸው ብቻ እንደሆነ አድርገው በመቁጠር በነቢዩ


ሙሐመድ /ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን/ ላይ አጉል


ለመመፃደቅ ሲዳዳቸው፥ አላህ ተችቷቸዋል፡፡ ወደዚህ


ሃይማኖት ጎዳና መመራት የሚቻለው በርሱ ፀጋ ብቻ


መሆኑን ገልፆላቸዋል፡፡ እንዲህ ይላል አላህ …«መስለማቸው


በአንተ ላይ ይመጣደቃሉ፤ በእስልምናችሁ በኔ ላይ


አትመጣደቁ፤ ይልቁንም አላህ ወደ እምነት ስለመራችሁ


ይመጣደቅባችኋል፤ እውነተኞች ብትኾኑ (መመጣደቅ


ለአላህ ነው) በላቸው፡፡» (አል-ሐሹራት፡17)


በእርግጥ የኃያሉ አላህ ፀጋዎች ብዙ ናቸው፡፡ እንደዚህም


ሆኖ በስም ጠቅሶ ያወሳውና ለእኛ እንዳጎናፀፈን የነገረን


አንድና ብቸኛ ፀጋ ወደ ኢስላም ጎዳና መመራት፣ እርሱን


መገዛትና አንድነቱን በተግባር ማረጋገጥ ነው፡፡


> የዚህ ዓለም ታላቅ ፀጋ


መቅድሞች


23


ይህ ፀጋ ከእኛው ጋር ቋሚና ዘውታሪ ሆኖ እንዲቆይ፥ ምስጋና ያስፈልገዋል፡፡ አላህም እንዲህ ብሏል… «ጌታችሁም


ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ፥ በትክዱም /እቀጣችኋለሁ/፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና በማለት ባስታወቀ


ጊዜ /አስታውሱ/፡፡»(ኢብራሂም፡7)


ይህን ፀጋ ማመስገን የሚቻለው እንዴት ነው?


ማመስገን የሚቻለው በሁለት መንገድ ነው፡-


> በህይወት የመኖራችን ዓላማ፡-


ለምን በህይወት ተገኘን? የመኖር ግቡ ምንድነው?


የሚሉትን እጅግ ወሳኝ የሆኑ የዘላለም ጥያቄዎችን


በመመለሱ ረገድ ብዙ አሳቢያንና ተመራማሪዎች


ተመሳሳይ በሆነ አኳኋን ሲደናገሩ ኖረዋል፡፡


ለምን ተፈጠርን?


ብሕይወት የመኖራችን አላማስ ምንድን ነው?


የተከበረው ቁርዓን የሰውን በህይወት የመኖር ዓላማና


ግብ በግልፅና ቁልጭ ባለ አኳኋን አስፍሮታል፡፡ ቁርዓን


እንዲህ ይላል …«ጋኔንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጂ ለሌላ


አልፈጠርኳቸውም፡፡» (አል-ዛሪያት 56)


በዚህ ምድር ላይ በህይወት የመኖራችን ግንባር ቀደሙ


ዓላማ አላህን መግገዛት ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ያሉት ነገር


ይህንን የሚከተሉና የሚያሟሉ ነገሮች ናቸው፡፡


ነገር ግን አላህን መግገዛት /ዒባዳ/ ማለት በኢስላም


ግንዛቤ መሠረት ባህታዊ መሆንና ከዓለማዊ ህይወት


ራስን መነጠል ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ከሶላት፣


ከፆምና ከዘካ ጎን ለጎን የሚካሄዱ ሥራ፣ ንግግር፣


ፈጠራ፣ የርስ በርስ ግንኙነትና የመሳሰሉት ሌሎች


ዓለማዊ ተግባራት ሁሉ ዓላማን /ኒያን/ አስካስተካከሉ


ድረስ ዒባዳ /አምልኮ/ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡


እንዲያውም ከዚህም አልፎ ለዓለማዊ ነገሮች


መጫወትና መደሰት ጥሩ በሆነ ዓላማና ለመልካም «ኒያ»


እስከሆነ ድረስ ከዒባዳ ተግባራት ተርታ ይመደባል፡፡


ለዚህ ነው ነቢዩ ሙሐመድ /ሰ.ዐ.ወ./ «በህጋዊ መንገድ


የሚካሄድ ተራክቦ ምፅዋት ነው፡፡» ያሉት ነብዩ /ሰ.ዐ.ወ./


ለማለት የፈለጉት ከባለቤታችሁ ጋር የምታደርጉት


የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሳይቀር ምንዳ የሚያስገኝ ዒባዳ


ነው፡፡


ዒባዳ /አምልኮ/ በህይወት የመኖር ግብ ከመሆኑ ጋር፥


ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ከተከናወነ ሙሉ ህይወት


ይሆናል፡፡ ሙስሊም በየህይወት እርከኑ የሚያከናውናቸው


ተግባራት በሙሉ ዒባዳ ይሆናሉ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል


…«ስግደቴ መገዛቴም፥ ሕይወቴም፥ ሞቴም ለዓለማት ጌታ


ለአላህ ነው በል፡፡» /አል-አንዓም፡162/


ጥበብና ትዕግስት በተሞላው አኳኋን


እስልምናን በማስተዋወቅና ወደርሱ


በመጣራት ነው፡፡ (ገጽ፣ 230


ተመልከት)


በሃይማኖት ላይ በመፅናትና በርሱ


ምክንያት ችግር ሲገጥም በመታገስ


(ገጽ፣ 229 ተመልከት)


1 2


መቅድሞች


24


> ኢስላም ዓለም አቀፍ ሃይማኖት፡-


የእስልምና ሃይማኖት የተደነገገው፥ በተለያየ


ባህል፣ ዘር፣ ልምድና ሃገር ውስጥ ለሚኖሩ ሁሉም


ዓይነት ሕዝቦች ዕዝነትና የህይወት ጎዳና ይሆን


ዘንድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል…«(ሙሐመድ


ሆይ!) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ


አላክንህም» (አል-አንቢያ፡107)


ለዚህ ነው የእስልምና ሃይማኖት የማንኛውንም


ሕዝብ ባህልና ልምድ የሚያከብረው፡፡ የእስልምናን


መሠረታዊ ህግጋት የማይጥስ እስከሆነ ድረስ አዲስ


ሰለምቴዎች የነበሩበትን ባህልና ልምድ እንዲተው


አይገደዱም፡፡


እስልምናን በግልፅ የሚቃረን ልምድና ባህል


ከሆነ ግን፥ ከሀይማኖቱ ጋር ተስማሚ በሆነ ባህል


መቀጠሩ ግድ ይላል፡፡ ከጉድለታት የጠራው


ኃያሉ አላህ አንድን ነገር የሚከለክለውም ሆነ


የሚያዘው ጥልቅና ውስጥ ዐዋቂነቱን መነሻ አድርጎ


ነው፡፡ ለአላህ ህግጋት ተገዥ መሆናችን፥ በርሱ


የማመናችን መገለጫ ነው፡፡


እዚህ ጋር አንድ ማሳሰብ የሚኖርብን ነገር


ይኖራል፡፡ ይኽውም አንድ አዲስ ሰለምቴ የሆነ


ሰው፥ ከእስልምና እና ከሕግጋቶቹ ጋር አንዳችም


ግንኙነት የሌላቸው ባሕላዊ ልምዶችን አንዳንድ


ሙስሊሞች ሲያከናውኑ አይቶ ይህንኑ ለመተግበር


መፈለጉ ተገቢ አይደለም፡፡ ይህ መሰሉ ተግባር


ሃይማኖት ሳይሆን በልምድ የተያዘና የተፈቀደ


የየዕለት ባህል መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡


መሬት ሁሉ አላህን የማምለኪያ ቦታ ነው፡-


በኢስላም አተያይ የትኛውም የመሬት ክፍል


ለመኖርም ሆነ አላህን ለማምለክ የተፈቀደና ምቹ


ነው፡፡ ሙስሊሞች ተሰደው ይኖሩበት ዘንድ


ግዴታ የተጣለባቸው ውሱን የሆነ ሃገርም ሆነ


ቦታ የለም፡፡ ዒባዳ ለማድረግ እስከቻሉ ድረስ


በየትኛውም ሃገር መኖር ይችላሉ፡፡


አንድ ሙስሊም ዒባዳ እንዳያደርግ የሚከለክለው


ኃይል እስካልገጠመው ድረስ ከአንድ ቦታ ወደ


ሌላ ቦታ ይሰደድ ዘንድ አይገደድም፡፡ አላህን


ከማምለክ የሚያግደው ከአቅም በላይ የሆነ ሐይል


ካጋጠመው ግን ዒባዳ ማድረግ ወደ ሚችልበት


ሌላ ቦታ መሰደድ ይኖርበታል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል…«እናንተ


ያመናችሁ ባሮች ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ


ተሰደዱ) እኔንም ብቻ ተገዙኝ፡፡» (አል-ዐንከቡት፡56)


መቅድሞች


25


> በእስልምና ሃይማኖት በጌታና በባሪያው መሃል አማላጅ የለም፡-


> በእስልምና ሃይማኖት በጌታና በባሪያው መሃል አማላጅ የለም፡-


ብዙ ሃይማኖቶች ለአንዳንድ ግለሰቦች ከሌላው


ሰው በተለየ መልኩ ሃይማኖታዊ መለያዎችን


ችረዋል፡፡ የሰዎች የአምልኮ ጥንካሬም ሆነ የእምነት


ደረጃ የሚለካው በእነዚህ ግለሰቦች ፈላጭ ቆራጭነት


እንዲሆን አድርገዋል፡፡


እነዚህ ግለሰቦች በእነዚህ ሃይማኖቶች መሠረት


በሰውና በአምላክ መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር


የሚያደርጉ አገናኝ ድልድዮች መሆናቸው ነው፡፡ ምህረት


የሚለግሱትም እነርሱ ናቸው፡፡ የሩቅ ምስጢር (ገይብ)


አዋቂ እንደሆኑ ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡ ይህ እነርሱን


ግልፅ ኪሳራ ላይ የጣላቸው የሃቅ ተቃራኒ የሆነና የሐሰት


ጥሪያቸው ነው፡፡


ነገርግን ኢስላም ብርሃኑን ፈነጠቀና ለሰው ልጅ ክብርን


አጎናፀፈው፣ ከፍ ያለ ደረጃም ሰጠው፡፡ የሰው ደስታ፣


ንሰሐም ሆነ አምልኮ መወሰን ያለበት የፈለገውን ያህል


ክብርና ደረጃ ይኑራቸው በጥቂት ግለሰቦች ፈቃደኝነት


ላይ ነው የሚለውን ከንቱ አስተሳሰብ ውድቅ አደረገው፡፡


የአንድ ሙስሊም የአምልኮ ተግባር የሚወሰነው


በርሱና በአላህ መካከል ብቻ ነው፡፡ ሌላ በመሃከል


ሆና የሚያገናኝ አማላጅ ግለሰብ አያስፈልግም፡፡ አላህ


ለባሪያው ቅርብ የሆነ ጌታ ነው፡፡ የባሪያውን ጥሪ


ሰምቶ ምላሽ መስጠት ይችላል፡፡ አምልኮውን፣ ሶላቱን


በመመልከትም ምንዳ ይሰጠዋል፡፡


መቅድሞች


26


ማንኛውም የሰው ዘር ምህረት የመቸርም ሆነ ንሰሀ


የመቀበል መብትም ሆነ ሥልጣን የለውም፡፡ አንድ


የአላህ ባሪያ የሆነ ግለሰብ ለአላህ ፍፁም ቅን ሆኖ ንሰሃ


እስከገባ ድረስ፥ አላህ ንሰሀውን ይቀበለዋል ምህረትም


ይለግሰዋል፡፡ ማንም ግለሰብ በዚህ ፍጥረተ-ዓለም


ውስጥ ተፅዕኖ የማሳደር መለኮታዊ ኃይል የለውም፡፡


ነገራት ሁሉ የሚከናወኑት በአላህ እጅ ነው፡፡


የእስልምና ሃይማኖት የሙስሊም አዕምሮ ነፃ እንዲሆን


አድርጓል፡፡ በጥልቅ እንዲያዝና እንዲመራመር ጥሪ


አቅርቦለታል፡፡ በአንድ ጉዳይ ሲወዘገብም በቁርዓንና


በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የተረጋገጠ ንግግርና ተግባር እንዲዳኝ


አዞታል፡፡


ከአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) በስተቀር ለማንኛውም


ሰው በሚናገረው ንግግር ሁሉ ሰዎች ለርሱ ፍፁም


ታዛዦች እንዲሆኑለት የማድረግ ስልጣን የለውም፡፡


ረሱል (ሰ.ዐ.ወ.) ግን ከአላህ በሆነ ወህይ (በራዕይ)


እገዛ ካልሆነ ከራሳቸው አፍልቀው የሚናገሩት አንዳችም


ነገር ስለሌለ እርሳቸውን ያለምንም ማወላዳት መታዘዙ


ተገቢ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል …«ከልብ ወለድም


አይናገርም፡፡ እርሱ (ንግግሩ) የሚወረድ ራእይ እንጅ


ሌላ አይደለም፡፡» (አል-ነጅም፡3-4)


አላህ በዚህ ሃይማኖት አማካኝነት ምን ያህል ታላቅ ፀጋ


እንዳጎናፀፈን እናስተውል! ሃይማኖቱ ከአፈጣጠራችን


ጋር ተስማሚ ነው፡፡ የሰውን ክቡርነት ይጠብቃል፡፡


ሰው ራሱን በራሱ ብቻ የሚገዛና ከአላህ ውጪ የማንም


ተገዢና ባሪያ እንዳይሆን ነፃ ያወጣል፡፡


መቅድሞች


27


> ኢስላም የህይወት ሃይማኖት


የእስልምና ሃይማኖት የዚህን ዓለም (ዱንያ) ህይወትና የቀጣዩን ዓለም (አኼራ) ህይወት አመዛዝኖ ጎን ለጎን የሚያስኬድ


ሃይማኖት ነው፡፡ ዱንያ ዘር የመዝሪያ ዓለም ነው፡፡ አንድ ሙስሊም በዚህም ሆነ በቀጣዩ ዓለም የዘራውን ለማጨድ፥


በሁሉም የህይወት ዘርፍ መልካም የተባሉ ነገሮችን ሁሉ የሚተክለው በዚህ የዱንያ ዓለም ውስጥ ነው፡፡


ይህንን ተክልና ዘር አግባብነት ባለው መልኩ ለመዝራትና ለመትከል፥ ህይወትን በቆራጥ ውሳኔና በፅናት ማስተናገድን


ይጠይቃል፡፡ ይህ ሁኔታ እንደሚከተለው ሊገለፅ ይችላል፡፡


ምድርን ማልማት


አላህ እንዲህ ይላል «… እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፤ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፡፡» (ሁድ፡61)


አላህ የዚህ ምድር ነዋሪዎች እንሆን ዘንድ ፈጥሮናል፡፡ እንድናለማት፣ አንድናሳድጋትና እንድናበለፅጋትም አዞናል፡፡ ገር


የሆነውን ኢስላማዊ ሸሪዓ በማይቃረን መልኩ ለሰው ልጅ ግልጋሎት ትውል ዘንድ መገንባት እንዳለብንም አዞናል፡፡


ሌላው ቀርቶ ከባድ ሁኔታ ባጋጠመህ ወቅት እንኳ ምድርን ማልማትና ማሳደግ የአምልኮ ተግባር (ዒባዳ) እንደፈፀምክ


ይቆጠርልሃል፡፡


ለዚህ ነው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.)፥ አንድ ሰው ችግኝ ለመትከል በእጁ ይዞ ሳለ ቂያማ ብትቆም እንኳ፥ እስከ ቻለ ድረስ ሰደቃ


ይሆንለት ዘንድ የያዛትን ችግኝ ይትከላት በማለት ያስገነዘቡት፡፡ (አል-ሙሰነድ፡ 2712)


ከሰዎች ጋር መኗኗር


የእስልምና ሃይማኖት ምድርን በመገንባቱና በማበልፀጉ ረገድ ከሰዎች ጋር እንድንተጋገዝ የበረታታናል፡፡ የየሰው ባህልና


ሃይማኖት የተለያየ ቢሆንም መልካም ሥነ-ምግባርና ሰናይ የሆነ ግብረ-ገብነትን በመላበስ ተቀላቅለን እንድንኗኗርና


እንድንተባበር ሃይማኖቱ ያዘናል፡፡


ከህብረተሰቡ ተነጥሎ መኖርና መገለል፥ የከሀዲዎችና የለውጥ አራማጆች መንገድ አለመሆኑንም ያስገነዝበናል፡፡


ይህ በመሆኑ ነበር የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ከሰዎች ጋር አብረው ይኖሩ የነበረውና የሚያደርሱባቸውን ሁከትና


ማዋከብም በፀጋ እንዲሁም በትዕግስት ያስተናግዱ የነበረው እንዲህ አይነቱ ሰው ከሚነጠለውና ከሚገለለው ሰው


የተሻለ ነውም ይሉ ነበር፡፡ (ኢብን ማጃህ፡ 4032)


> ኢስላም እንደ ሌሎች ሃይማኖቶች በሃይማኖትና በእውቀት መካከል የሚደረግን ጦርነት አያውቅም


መቅድሞች


28


> ኢስላማዊ ሕግጋትን ተማር


አንድ ሙስሊም በሁሉም የህይወት ዘርፍ ዙሪያ ያሉ ኢስላማዊ ሕግጋትን ለማወቅ መጓጓት ይኖርበታል፡፡ የአምልኮ፣


የየዕለት ውሎና ግንኙነት ሥርዓቶችን ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ካደረገ የዒባዳ ተግባሩን በዕውቀት ላይ ተመስርቶ


የሚያከናውን ይሆናል፡፡


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል «አላህ መልካም ነገር ላሰበለት ሰው የሃይማኖት ግንዛቤን ይሰጠዋል፡፡»


(አል- ቡኻሪ፡71 ሙስሊም፡1037)


በተለይ ግዴታ የሆኑ እንደ ሰላትና ንፅህና አጠባበቅ (ጠሃራ) የመሳሰሉ ህግጋትን መማር አለበት፡፡ የተከለከሉ የምግብ


ዓይነቶችን ማወቅም ይኖርበታል፡፡ ግዴታ ያልሆኑ ሆነው ሃይማኖቱ የሚያበረታታቸው አንዳንድ ነጥቦችን ማወቁም


ተገቢ ነው፡፡


የዕውቀት ሃይማኖት


በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ላይ የወረደው የመጀመሪያው የአላህ ቃል «አንብብ!» የሚለው መሆኑ እንዲሁ እንደዘበት


የተከሰተ ክስተት አይደለም፡፡ ለሰው ልጅ ጠቃሚ የሆኑ የዕውቀት ዘርፎች ሁሉ በእስልምና ሃይማኖት የተበረታቱ


ናቸው፡፡


ሌላው ቀርቶ አንድ ሙስሊም ዕውቀት ለመቅሰም ሲንቀሳቀስ ወደ ጀነት በሚያደርሰው ጎዳና ላይ እየተጓዘ መሆኑን ነብዩ


(ሰ.ዐ.ወ.) ተናግረዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል…«እውቀት በሚያስገበይ ተግባር ላይ የተሰማራ ሰው በዚህ ጥረቱ አላህ ወደ ጀነት


የሚያደርሰውን ጎዳና ገር ያደርግለታል፡፡» (ኢብን ሒባን ፡ 84)


ሌሎች ሃይማኖቶች እንደሚያስቡት የእስላም ሃይማኖት በዕውቀትና በሃይማኖት መካከል ግጭት አለ ብሎ


አያምንም፡፡ ይልቁንም ከዚህ በተቃራኒው ሃይማኖት ዕውቀትን ማፈላለጊያ ብርሃን ነው ብሎ ያምናል፡፡ ለሰው ልጅ


እስከጠቀመ ድረስ ማወቅና ማሳወቅ ተገቢ ተግባር መሆኑን እስልምና ያስገነዝባል፡፡


እንዲሁም የእስልምና ሃይማኖት፥ ለሰዎች መልካም ነገርን የሚያስተምር አዋቂና አስተማሪ ደረጃው እጅግ ከፍ ያለና


የተከበረ መሆኑን ይናገራል፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ፍጥረታት በጠቅላላ ለሰዎች መልካምን ነገር ለሚያስተምር


ግለሰብ እንደሚፀልዩ (ዱዓእ) እንደሚየደርጉ ተናግረዋል፡፡ (ቲርሚዚ ፡ 2685)


> አላህ መልካም ነገር የሻለት ሰው በዲን ላይ ያሳውቀዋል።


መቅድሞች


29


> የሸሪዓ ሕግጋት፡-


በሸሪዓ ሕግጋት መሠረት የአንድ ሰው ንግግርም ሆነ ተግባር ከአምሰት ማዕቀፎች ሊወጣ አይችልም፡፡


የግዴታ ተግባር ማለት አላህ ያዘዘው፣ ተግባሪው ምንዳ የሚያገኝበትና ከመተግበር የታቀበው ደግሞ


የሚቀጣበት ተግባር ማለት ነው፡፡ አምስቱ ሶላቶችና የረመዷን ፆምን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡


አልዋጂብ


(ግዴታ)


ክልክል ተግባር ማለት አላህ የከለከለው፣ ከመተግበር የታቀበው ምንዳ የሚያገኝበትና የተገበረው ደግሞ


ሐራም (ክልክል) የሚቀጣበት ተግባር ማለት ነው፡፡ ዝሙትና አስካሪ መጠጥን በምሳሌነት ማውሳት ይቻላል፡፡


ይህ ደግሞ ይተገበር ዘንድ ኢስላም ያበረታታው፣ ተግባሪው ምንዳ የሚያገኝበትና ከመተግበር የታቀበው


ደግሞ የማይቀጣበት ተግባር ማለት ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ የሆነን ፈገግታ ማሳየት፣ ቀድሞ ሰላምታ ማቅረብና


ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ሊጠቀስ ይችላል፡፡


አስሱና ወአል


ሙስተሐብ


(ተወዳጅ ተግባር)


የእስልምና ሃይማኖት አንዳይደረግ ያበረታታው ተግባር ማለት ሲሆን ይህን ተግባር ከማድረግ በመቆጠብ


ምንዳ የሚገኝ ሲሆን መተግበሩ ግን ለቅጣት አይዳርግም፡፡ በሶላት ውስጥ ጣትን እያነቃነቁ መጫወት ከዚህ


የተጠላ «መክሩህ» ተግባር ውሰጥ ሊመደብ ይችላል፡፡


የሚጠላ (ከርሃ)


ነገር ማለት


መተግበሩም ሆነ መቆጠቡ፥ ከልካይና አዛዥ ከሆነ የህግ (ሸሪዓ) መርህ ጋር ግንኙነት የሌለው ክንውን ማለት


ነው፡፡ ለምሳሌ መሠረታዊ በሆነ መልኩ መብላት፣ መጠጣት፣ መናገር ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡


የተፈቀደ


(ሙባሕ) ማለት


ደግሞ


መቅድሞች


30


ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም መሐመድ


የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር


ዘካን መስጠት ረመዷንን መፆም


ሶላትን መስገድ


ሐጅ ማድረግ


1


3 4


የእስልምና መሠረቶች


ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ


አምላክ የለም መሐመድ የአላህ


መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር


2 ሶላትን መስገድ


3 ዘካን መስጠት


4 ረመዷንን መፆም


5 ሐጅ ማድረግ





> አምስቱ የእስልምና መሠረቶች፡-


ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ይላሉ «እስልምና


በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል፡፡ ከአላህ በስተቀር


በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፣ ሙሐመድ የአላህ


መልዕክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሰላትን መስገድ፣


ዘካ መስጠት፣ሐጅ ማድረግና ረመዷንን መፆም


ናቸው፡፡» (አል-ቡኻሪ፡ 8 ሙስሊም፡16)


እነዚህ አምስቱ መሠረቶች ሃይማኖቱ የተገነባባቸው


ዋና ዋና ምሰሶዎች ናቸው፡፡ በሚቀጥሉት ክፍሎች


ዝርዝር ሕግና ስርዓታቸውን እናብራራለን፡፡


ከዚህ ለጥቆ ደግሞ ሰላት ይከተላል፡፡ ሰላት


ከአምልኮዎች (ኢባዳት) ሁሉ የተከበረውና ታላቁ ነው፡


፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡፡ «ሶላት


(የሃይማኖቱ) ምሰሶ ነው፡፡» (ቲርሚዚ፥2749)


መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ.) ለማለት የፈለጉት ፥ የእስልምና


ሃይማኖት ቀጥ ብሎ ሊቆምና ሊገነባ የሚችለው በሶላት


ነው፡፡ ያለ ሶላት ሃይማኖቱን መገንባት አይቻልም ነው፡፡


ሶላት ጤናማና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን መሟላት


ካለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ውሰጥ አንዱ ንፅህና


(ጠሃራ) ነው፡፡ ስለዚህ «ከእምነትህ» ቀጥሎ «ንፅህናን»


ከዚያም «ሶላትህ» ይከተላል፡፡


መቅድሞች


31


> የሃይማኖቱን ሕግጋት እንዴት አውቃለሁ?


አንድ ሰው ህመም ካጋጠመውና ይህን ህመሙን


የሚያሽር መፍትሄ ከፈለገ፥ በዘርፉ ብቃት ያላቸው


የህክምና ባለሞያዎች ማፈላለጉ የማይቀር ነው፡፡ ህይወቱ


እጅግ ውድ ዋጋ ያላት በመሆኗ ሐኪሙ ያዘዘለትን


መድሃኒት በታዘዘው መሠረት በአገባቡ ከመውሰድ


እንደማይዘናጋ እሙን ነው፡፡


ሃይማኖት ደግሞ ለሰው ከምንም በላይ ውድ ነገር


ነው፡፡ ሃይማኖቱን ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ


አለበት፡፡ የማያውቀውን ነገር ለመረዳትም ታማኝ የሆኑ


የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቆ መረዳት ይኖርበታል፡፡


ይህን መፅሐፍ ማንበብህ ስለ ሃይማኖትህ በትክክል


በማወቁ ረገድ እርምጃዎችን እንድትጀምር ያደርግሃል፡፡ አላህ


እንዲህ ብሏል«…የማታውቁ ብትሆኑ የዕውቀት ባለቤቶችን


ጠይቁ፡፡» (አል-ነሕል፡43)


ይህን መጽሐፍ ከማንበብ ባሻገርም ሌሎች


እርምጃዎችን መውሰድም ይኖርብሃል፡፡ አንዳንድ


ከበድ ያሉ ሁኔታዎች ሲገጥሙህ በአካባቢህ ያሉ


መሳጂዶችና ኢስላማዊ ማዕከሎች ጎራ በማለት ጠይቀህ


መረዳት ይኖርብሃል፡፡ ተከታዩን ድረ-ገፅ በመጎብኘትም


መረጃዎችን ማግኘት ትችላለህ፡፡


www.islamicfinder.org


የእስልምና ሃይማኖት ዕውታዎችን በማብራራቱ


ረገድ ታማኝ የሆነውን ተጨማሪ ድረ-ገፅ መጎብኘትም


ይኖርብሃል፡፡


www.newmuslimguide.com


www.guide-muslim.com


> አዲስ ሰለምቴ የሆነ ሙሰሊም ግለሰብ በአቅራቢያው


ከሚገኙ ኢስላማዊ ማዕከላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር


የተለያዩ ታማኝ መፅሐፍትን ማገላበጥና ድረ-ገፆችን


መጎብኘት ይጠበቅበታል፡፡


መቅድሞች


32


> እስልምና ሚዛናዊ ሃይማኖት ነው፡-


እስልምና ከመጠን በላይ አለማክረርና አለማካበድን እንዲሁም ከደረጃ በታች አለመውረድና አለመለስለስን


መለያው አድርጎ የተደነገገ ሃይማኖት ነው፡፡ ይህ መለያው በሁሉም ሃይማኖታዊና አምልኮአዊ መርሆቹ ውስጥ ጎልቶ


ይንፀባረቃል፡፡


አላህ (ሱ.ወ.) ለመልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ.) ለሰሀቦችም ሆነ ለምእመናን ሚዛናዊ ይሆኑ ዘንድ በማስገንዘብ አስረግጦ


ነግሯቸዋል፡፡ ይህም በሁለት መንገዶች ሊገለፅ ይችላል፡-


ከአክራሪነት፣ ከድንበር


አላፊነትና ከጠርዘኝነት


በመከልከል ናቸው፡፡


በሃይማኖት ጎዳና ላይ


በመፅናትና በልብ ውስጥ ለአላህ ሕግ


ጋቶች ከፍተኛ ቦታ በመስጠትና፡፡


1 2


ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡፡ «እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፤ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፤ ወሰንንም አትለፉ፤


እርሱ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡»(ሁድ፡112)


ጌታችን በዚህ አንቀፅ ለማለት የፈለገው በእውነት ላይ በመፅናት ብዙም ሳታካብዱና አላስፈላጊ ነገሮችን በመጨማመር


ድንበር አላፊ ሳትሆን ለዚሁ እየታገልክ ኑር ነው፡፡


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) በአንድ ወቅት የእምነት


ባልደረባቸውን (ሰሀባቸውን) ስለ ሐጅ ተግባራት ሲያስተምሩት፥


ያለፉት ህዝቦች ለጥፋት ሊዳረጉ የቻሉት ድንበር በማለፍ


መሆኑን በማውሳት፥ ሰሀቢው ከማካበድ ተግባር እንዲቆጠብ


አስገንዝበውታል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት…«አደራችሁን!


በሃይማኖት ውስጥ ማካበድን ተጠንቀቁ፥ ከእናንተ በፊት


የነበሩትን ህዝቦች ለጥፋት የዳረጋቸው ማካበድ ነው፡፡» (ኢብን


ማጃህ፡3029)


ለዚህ ነው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) «አደራችሁን


አቅማችሁ በሚፈቅደው ተግባር ላይ ብቻ ተሰማሩ» ያሉት (አል-


ቡኻሪ፡1100)


የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) የተልዕኮዋቸውን ትክክለኛ


ገፅታ ቁልጭ ባለ ቃል ገልፀዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የተላኩት


ለሰዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር ለማሸከም ሳይሆን፥


ገራገርና በጥበብ የተሞላ ዕውቀት ለማስጨበጥ


ነው፡፡ መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል አላህ


«አጨናናቂ ወይም አጣባቢ አድርጎ አልላከኝም


ነገር ግን አግራሪና አስተማሪ አድርጎ


ልኮኛል፡፡» (ሙስሊም፡1478)


መቅድሞች


33


> የእስልምና ሃይማኖት ሁሉንም የህይወት ዘርፍ ያካትታል፡-


እስልምና በመስጂድ ውስጥ ተወስኖ በዱዓ እና


በሶላት ብቻ የሚገለፅ ሙሰሊሞች የሚያከናውኑት


በመንፈሳዊነት የተገደበ ሃይማኖት አይደለም፡፡


ወይም ደግሞ ተከታዮቹ ግለሰቦች አምነው


የሚቀበሉት በልብ ውስጥ ብቻ የሚያድር እምነት


አይደለም፡፡


በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ የሚያተኩር


ሥርዓትም አይደለም፡፡


አሊያም ደግሞ አንድን ማህበረሰብ ለመገንባት ያለመ


ንድፈ-ሐሳብ ብቻም አይደለም፡፡


ወይም ደግሞ ከሌሎች ወገኖች ጋር በመኗኗሩ ረገድ


ሊኖር ስለሚገባው መልካም ሥነ-ምግባርና ግብረ-ገብ


የሚያስተምር የእነፃ ትምህርት ብቻም አይደለም፡፡


ይልቁንም ሁሉንም የህይወት ዘርፍ ያካተተ የተሟላ


አስተምህሮ ነው፡፡ እያንዳንዱን የኑሮ እርከን ያጠቃለለ


ነው፡፡


አላህ ይህን የመሰለ ፀጋ ሙስሊሞች እንዲጎናፀፉ


አድርጓል፡፡ ይህን ሙሉ ሃይማኖት እንከተለው


ዘንድም ወዶልናል፡፡ እንዲህ ይላል …«ዛሬ


ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ፀጋዬንም


በናንተ ላይ ፈፀምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን


ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡» (አል-ማኢዳህ፡3)


አንዱ የመካ ሙሽሪክ ለማሾፍ በመፈለግ ሰልማን


አል-ፋርሲ ለተባሉት ሰሀቢ እንዲህ አላቸው «ጓደኛችሁ


(ረሱልን ለማለት ነው) የመፀዳጃ ቤት ስርዓትን ጨምሮ


ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል፡፡» ታላቁ ሰሀቢም «አዎን


ያስተምሩናል!» ብለው መለሱና በዚሁ ዙሪያ ያለውን


ኢስላማዊ ሕግና ሥርዓት አብራሩለት፡፡


> እስልምና ሁሉንም የህይወት ዘርፍ የሚመለከት የተሟላ መመሪያ ነው


መቅድሞች


34


> አምስቱ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች፡-


እነዚህ አምስት ነገሮች ሰው


ተገቢ በሆነ መልኩ ይኖር ዘንድ


የሚያስፈልጉ ወሳኝ የሆኑ ጥቅሞች


ናቸው፡፡ ለሁሉም መለኮታዊ


ህግጋት የተደነገጉት እነዚህን ነገሮች


ለመጠበቅና እነዚህን ተቃርነው


የተገኙ ነገሮችን ለመከላከል ነው፡፡


እስልምና የተደነገገው፥ አንድ


ሙስሊም ለዱንያዊ ሆነ አኼራዊ


ህይወት በዚህ ዓለም ላይ ተረጋግቶ


ይሰራ ዘንድ፥ እነዚህን አምስት ነገሮች


ለመጠበቅና ለመንከባከብ ነው፡፡


ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚኖረው፥


እርስ በርሱ ተደጋግፎ እንደቆመ


ግንብ በመተሳሰር ነው፡፡ አንዱ አካል


ሲጎዳ ሌላውም ጉዳቱ በትኩሳትና


በእንቅልፍ ማጣት እንደሚሰማው


እንደ አንድ የሰውነት አካል ሆነው


ይኖራሉ፡፡


በመገንባትና


በመንከባከብ


ይህንኑ መጠበቅ


የሚቻለው በሁለት


መንገድ ነው፡-


1 2


> ተግባራችን ተገቢ ወዳልሆነ ተግባር ቢያሰማራንም የሰው ልጅን ነፍስ መጠበቅ እንደ


ሚኖርብን አላህ አዞናል፡፡


1 ሃይማኖት፡-


ሃይማኖት ማለት አላህ ሰዎችን ለዚሁ ዓላማ ሲል


የፈጠረበትና ታላቅ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ መልእክተኞች


የላከውም ይህንኑ እንዲጠብቁ ነው፡፡ አላህ እንዲህ


ብሏል… “በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም


ራቁ በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል…” (አል-


ነሕል፡36)


የሃይማኖትን ብፁዕነት የሚያቆሽሹና እንደ ሺርክ፣


ከንቱ እምነት፣ ወንጀልና ኃጢአት የመሳሰሉ ነገሮች


ሃይማኖትን ለመጠበቅ ሲባል ኢስላም ተከላክሏቸዋል፡፡


> እስልምና የሚለካው፥ በአንዳንድ ሙስሊሞች ተግባር ሳይሆን በሃይማኖቱ ምንነትና ምንጭ ነው፡፡


ጤናን የሚጎዳ ተግባር የሚፈፅም የጤና ባለሙያ


ወይም መልካም ሥነ- ምግባር የሌላው መምህር


ቢያጋጥምህ፥ የእነዚህ ሰዎች ተግባር ከተሰማሩበት


ሙያ ጋር የማይገጥምና የማይጣጣም በመሆኑ ትገረምና


ትደነቅ እንደሆን እንጂ የትምህርትም ሆነ የሕክምና ሙያ


ለህብረተሰቡም ሆነ ለብልፅግና የማይጠቅሙ አላስፈላጊ


ተግባራት ናቸው ወደሚል ድምዳሜ አትደርስም፡፡


ባይሆን ልትል የምትችለው ይህ ሐኪምም ሆነ


መምህር ከተሰማራበት ሙያ ጋር የማይጣጣም ተግባር


እየከናወነ ነው፡፡


አንዳንድ ሙስሊም ግለሰቦች ተገቢ ያልሆነ ተግባር


ሲፈፅሙ ካየን፥ ተግባራቸው እስልምናን እያንፀባረቀ


እንደሆነ አድርገን መቁጠር አይኖርብንም፡፡ ይልቁንም


ልክ ሐኪሙና መምህሩ ከሙያቸው ጋር የሚቃረን


ተግባር በልምድ እንዳከናወኑት ሁሉ፥ ከእስልምና ጋር


በጭራሽ ግንኙነት የሌለው በልምድና በባህል እንዲሁም


በሰብዓዊው ፍጡር ድክመት የሚሰሩ መጥፎ ተግባራት


መሆናቸውን ማወቅ አለብን፡፡


መቅድሞች


35


> የሰውን ክብርና ዘር መጠበቅ ከኢስላማዊ መርህ


ታላላቅ ዓላማዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡


2 አካል፡-


ተግባራችን ተገቢ ወዳልሆነ ነገር ቢያሰማራንም የሰው


ልጅን ነፍስ መጠበቅ እንዳለብን አላህ አዞናል፡፡ በአስገዳጅ


ሁኔታ ውስጥ እስከ ሆንን ድረስ አላህ ለእኛ ምህረትን


ይለግሰናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል… “… ሺፍታና ወሰን አላፊ


ሳይሆን (ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ ላይ ኃጢአት


የለበትም አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡” (አል-በቀራህ፡173)


የራስን ነፍስ መግደልና መጉዳትንም ከልክሏል፡፡


እንዲህ ይላል… “በአላህም መንገድ ለግሱ በእጆቻችሁም


(ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ…” (አል-በቀራህ፡195)


የእስልምና ሃይማኖት አንድ ሰው የትኛውም ሃይማኖት


ይከተል በሱ ላይ ድንበር እንዳይታለፍበትና ወንጀል


እንዳንፈፅምበት በሚል ወሰኖችን አበጅቷል መቀጣጫ


ህግጋትንም አኑሯል፡፡ እንዲህ ይለናል…«እናንተ ያመናችሁ


ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ማመሳሰል በናንተ ላይ ተፃፈ…»


(አል-በቀራህ፡178)


3 አዕምሮ፡-


አዕምሮ አላህ ከለገሳቸው ታላላቅ ፀጋዎች ውስጥ አንዱ


በመሆኑ፥ እርሱን የሚጎዱና አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፉበትን


ነገሮች እስልምና ከልክሎዋል፡፡ የሰው ክብርና ማንነት


የሚገለፀው በርሱ ነው፡፡ በዚህ ዓለም (ዱንያ) ሆነ በቀጣዩ


ዓለም አኼራ ሂሳቡን የሚያወራርደውና ጥያቄ የሚቀርብለት


በርሱ ነው፡፡


ለዚህ ነው አላህ ማንኛውንም ዓይነት አስካሪ መጠጥና


አደንዛዥ ዕፅን የከለከለው (ሃሐራም) ያደረገው ከፀያፍና


ከሸይጣን ተግባራት ተርታ መድቦታል፡፡ አላህ እንዲህ


ይላል “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣


ቁማርና ጣዖታትም የመጠንቆያ እንጨቶች (አዝላምም)


ከሰይጣን ስራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፤ እርኩስን


ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡” (አል-ማኢዳህ፡90)


4 ዘር፡-


የእስልምና ሃይማኖት ዘርን ለማስቀጠልና ለቤተሰብ


ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠውና ጥበቃ ያደረገለት ነገር


መሆኑ በተለያዩ መርሆቹና ህግጋቶቹ ውስጥ ጎልቶ ሲታይ


ይስታዋላል፡፡ ከዚህ ውስጥ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡-


• የእስልምና ሃይማኖት ለትዳር በጣም ያበረታታል፡፡ ቀለል


ባለ አኳኋን እንዲመሰረተም ይገፋፋል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎቹ


እንዳናካብዳቸውም ያዘናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል


“ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡” (አል-ኑር፡32)


• እስልምና ሕገ-ወጥ የሆኑ ማንኛውም ዓይነት የፆታ


ግንኙነቶችን ከልክሎዋል፡፡ ወደ እርሱ የሚያደርሱ


ጎዳናዎች ሁሉ ዝግ እንዲሆኙ አድርጓል፡፡ እንዲህ



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎ ...

በጠዋት እና ምሽት የሚባሉ ውዳሴዎች።

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የ ...

ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ...

እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት