መጣጥፎች

2- ፍፁም የማይወደዱ ብሎም ጠላት ተደርገው የሚያዙ አሉ እነሱም የለየላቸው ከሃዲያን ናቸው።


3- በአንድ በኩል የሚወደዱና በሌላ በኩል ደግሞ የሚጠሉ አሉ እነሱም ከሽርክ በታች ያሉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ አማኞች ናቸው እነዚህ ሰዎች ባላቸው መሰረታዊ እምነትና በሚሰሩት መልካም ሥራቸው ይወደዳሉ በሚፈፅሙት ወንጀል መጠን ደግሞ ይጠላሉ።


አል --ኢስላም ወይም እስልምና፡--


ኢስላም ማለት ለአላህ ብቻ ታዛዥ መሆን፤ ለሱም እጅ መስጠት፤ ከማጋራት እና ከአጋሪዎች ነፃ መሆን ማለት ነው።


የኢስላም አጠቃላይና ልዩ ትርጉም፡-


አላህ መልእክተኞችን ከላከበት ጊዜና ወቅት ጀምሮ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ እርሱ ባወጣው ህግና ስርዓት መሰረት እሱን ብቻ መገዛት የኢስላም አጠቃላይና ሰፊ ትርጉም ሲሆን ነቢዩ ሙሀመድ /ሶ.ዐ.ወ/ በተላኩበት ህግና ስርዓት ብቻ በመወሰን አላህን መገዛት ደግሞ የኢስላም ልዩ ትርጉም ይሆናል።


የእስልምና መሰረቶች፡--








“ በሚሰሩት መካም ሥራ የቅርቢቱን ሕይወትና ውበቷን የሚሹ ሰዎች ሙሉ የስራ ውጤታቸውን በዱንያ ላይ እያሉ እንከፍላቸዋለን። እነሱም በእርሷ ላይ እያሉ አይጓደልባቸውም። እነዚያ እነርሱ በመጭዋ ዓለም እሳት እንጂ የላቸውም” (ሁድ: 16)።


የአላህ መልእክተኛ // አህመድና አቡዳውድ በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ ለአላህ ፊት ብሎ መማር ያለበትን የሃይማኖት እውቀት ለዱንያ ጥቅም ብሎ የተማረ ሰው የጀነትን ሽታ አያገኝም ” ብለዋል ።


መሐላ፡--


አላህ፣ አረህማን፣ አልዐዚም፣ አሰሚዕ በሚሉት በአላህ ስሞች እና እንደዚሁም በእዝነቱ፤ ባሸናፊነቱ፤ በእውቀቱና በመሳሰሉት ባህሪያቱ መማል የተፈቀደ ሲሆን ከአላህ ሌላ በሆነ አካል መማል የተከለከለ ነው ።


የአላህ መልእክተኛ // አሊማሙ አህመድ፤ አቡ ዳውድና ቲርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ፡





“ ከአላህ ሌላ በሆነ አካል የማለ ሰው በእርግጥ ካደ ወይም አጋራ” ብለዋል።


76


ከአላህ ውጭ በሆነ አካል መማል በሁለት መልኩ ይታያል፡-


1- ከአላህ ውጭ የሚምልበትን አካል እንደ አላህ ወይም ከአላህ በላይ የሚያከብረው ከሆነ ከፍተኛው (ትልቁ) ሽርክ ሲሆን ፣


2- የሚምልበትን አካል እንደ አላህ የማያከብረው ከሆነ ደግሞ መለስተኛው( ትንሹ) ሽርክ ይሆናል።


ከአላህ ውጭ ያለ- አግባብ የሚማልባቸው ነገሮች ፦


ነቢያት፤ደጋግ ሰዎችና ወላጆች በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። በእነዚህና በመሳሰሉት ነገሮች መማል የተከከለ ነው።


ከዚህ ርእስ የምንማራቸው ጠቃሚ ነጥቦች፦


1- ከአላህ ሌላ በሆነ አካል መማል የማጋራት ወንጀል መሆኑን፤


2- በአላህ ስም በሀሰት መማል የተከለከለ መሆኑን፤


3-አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በአላህ ስም ብዙ ጊዜ መማል የማይፈቀድ መሆኑንና


4- አስፈላጊ ከሆነ በአላህ ስም መማል የተፈቀደ መሆኑን ነው።


ከአላህ ውጭ በሆነ አካል የማለ ሰው ለመሐላው ማሰረዣ ምን ማለት አለበ?፦


የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ በላትና በዑዛ የማለ ሰው ላኢላሀ ኢለላህ ( ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት አምላክ የለም) ይበል” ብለዋል። ላትና ዑዛ የተባሉት የጣዖት ስሞች ናቸው።


አላህንና ፍጡርን (እና) በሚለው አያያዥ ቃል ማጋራት ለምሳሌ፦


77


1- በአላህና ባንተ ፈቃድ ይህ ነገር ተሳካ፤


2- በአላህና በአንተ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ፣


3- ከአላህና ካንተ በስተቀር ለእኔ ማን ደራሽ አለኝ፣


4- ከአላህ ፍቃድ ጋር ይህ ነገር ይጠቅማል፤


አንድ ሰው እነዚህንና የመሳሰሉትን ቃላት ሲጠቀም ከአላህ ውጭ የሆነ አካል ከአላህ ጋር እኩል መሆኑን የሚያምን ከሆነ እምነቱ ከፍተኛው የማጋራት ወንጀል ሲሆን ይህ እምነት ከሌለው ደግሞ መለስተኛው የማጋራት ወንጀል ይሆናል።


ነገር ግን መባል ያለበት ነገሮችን ሁሉ ወደ አላህ በማስጠጋት፦ በአላህ ፍቃድ እንዲህ ሆነ፤ በአላህ ላይ ብቻ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አላህን ብቻ እገዛ እጠይቃለሁ ይህም አባባል የበለጠና የተሻለ ቢሆንም አላህን እገዛ እጠይቃለሁ ከዚያም አንተን ማለትም ይፈቀዳል።


ማሳሰቢያ፡-


(እና) በሚለው አያያዥ ቃል የተጠቀሱ ነገሮች መጀመሪያ ከተጠቀሰው ነገር ጋር በተፈለገው ጉዳይ ላይ እኩል መሆናቸውን ስንረዳ (ከዚያም) በሚለው አያያዥ ቃል የተጠቀሱ ነገሮች ግን መጀመሪያ ለተጠቀሰው ነገር ተከታይ መሆናቸውን እንረዳለን።


እንዲህ ቢሆን((ባይሆን) ) ኖሮ ይህ ባልሆነ ነበር ማለት፡--


እነዚህን ቃላት መጠቀም በሁለት ተከፍሎ ይታያል፡-


1- ለመልካም ስራ ያለውን ጉጉትና ምኞት ለመግለፅ ከሆነ ለምሳሌ፦ ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ አላህ በሚወደውና በሚፈልገው መንገድ ላይ ባዋልኩት ነበር


78


ብሎ መመኘት የተፈቀደና ብሎም የተመሰገነ ይሆናል። የአላህ መልእክተኛ // አህመድና ቲርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ አንድ ሰው፡-





“ ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ እንደ እገሌ መልካም በሰራሁ ነበር ሲል ሰሙት። ይህ ሰው በመልካም ምኞቱ መልካም ከሰራው ጋር እኩል ምንዳ አገኘ ” አሉ።


2- ቃሉን የተጠቀመው የአላህን ህግና ውሳኔ ለመቃወም ወይም ለወንጀል ያለውን ፍላጎት ለመግለፅ ከሆነ የተከለከለ ይሆናል። መናፍቃን የአላህን ውሳኔ ለመቃወም በጦርነት የተገደሉትን ሰዎች አስመልክተው “ቢታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር” “ ከእኛ ዘንድ ቢሆኑ ኖሮ ባልሞቱና ባልተገደሉ ነበር ” አሉ። የአላህ መልእክተኛ // አንድ ሰው ወንጀልን በመመኘት፡-





“ ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ እንደ እገሌ በሰራሁ ነበር ሲል ሰሙት ። ይህ ሰው ክፉ በማሰቡ ብቻ ወንጀል ከሰራው ጋር እኩል ናቸው ” አሉ።


ግዜን መሳደብ እና መተቸት፡--


ግዜን መሳደብ( መተቸት) በሶስት ተከፍሎ ይታያል፡-


1- ግዜውን ለመሳደብ ወይም ለመተቸት ሳይሆን በግዜው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመናገር ከሆነ ለምሳሌ፦ የዚህ ቀን ወይም ወር ሙቀት ወይም ብርድ አሰቃየን ማለት ነቢዩላህ ሉጥ “ይህ አደገኛ ቀን ነው ” እንዳሉት ሁሉ የተፈቀደ ይሆናል ።


2-ግዜውን አድራጊና ፈጣሪ አድርጎ በማሰብ መሳደብና መውቀስ እንደ ትልቁ ሽርክ የሚቆጠር ከባድ ወንጀል ነው ።


79


3- አድራጊና ፈጣሪው አላህ ብቻ መሆኑን እያመነ የሚጠላቸው ነገሮች በግዜው ውስጥ ስለሚፈራረቁ ብቻ ግዜን መሳደብና መተቸት ከታላላቅ ወንጀሎች የሚቆጠርና አላህን እንደመረበሽ የሚታይ እኮይ ተግባር ነው። የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ አላህ እንዲህ ይላል ብለዋል፡-





“ የአደም ልጅ ግዜን በመሳደብ ሊረብሸኝ ይሞክራል ሁሉም ነገር በእጄ ነው ሌሊትንና ቀንን አፈራርቃለሁ ። ”


ቃላት አጠቃቀምን በተመለከተ ሁለት ጠቃሚ ነጥቦች አሉ፡-


1- ውሸት መናገር፤ ወሬ ማናፈስ፤ ሐሜት፤ ከአላህ ውጭ በሆነ አካል መማልና የመሳሰሉት የተከለከሉ ስለሆኑ ከእነዚህ ነገሮች ምላሶቻችንን መቆጠብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም አንድ ሰው በተናገረው ነገር ሁሉ ተጠያቂ ስለሆነ ነው። ሌላው ደግሞ አንድ ሰው ግምት ሳይሰጠው በሚናገረው ቃል ሳቢያና መዘዝ ከኢስላም የሚወጣበት አጋጣሚ ሊፈጠር ስለሚችል ቃላትንና ፊደሎችን ስንጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።


2- ከማጋራት ወንጀል ላይ የሚጥሉ ቃላትንና ፊደሎችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል ።


ፈጠራ፡--


ቢድዓ (ፈጠራ) በሁለት ይከፈላል፡-


1- የቅርቢቱን ሕይወት በጥሩ ሁኔታ ለመኖር የሚያስችሉና የሚረዱ ነገሮችን መፍጠርና መስራት በኢስላም የተፈቀደና የተበረታታ ሲሆን፣


2- በሃይማኖት ጉዳይ የሚፈጠሩ ፈጠራዎች በሙሉ የተከለከሉና የተወገዙ ናቸው። ምክንያቱም ሃይማኖት ከአላህና ከመልእክተኛው የመጣውን ህግና ስርዓት መከተል እንጂ አዲስ ነገር መፍጠርና መጨመር ስለማይቻል ነው።


80


በሃይማኖት ዙሪያ የሚፈጠሩ ፈጠራዎች በሶስት ይከፈላሉ። እነሱም፦


1- እምነታዊ ፈጠራ ሲሆን እሱም አላህና መልእክተኛው በተናገሩት ተቃራኒ ማመን ነው። ለምሳሌ፦ የአላህን ስሞችና ባህሪያት ከፍጥረታት ስሞችና ባህሪያት ጋር ማመሳሰል፤ አዛብቶ መተርጎም ወይም ትርጉም አልባ ማድረግና አላህ ማንኛውንም ነገር ቀደም ሲል መወሰኑን አለመቀበል።


2- ተግባራዊ ፈጠራ ነው። እሱም አላህ ባላወረደው ህግና የነቢዩ ሙሀመድ // አስተምህሮት በሌለበት ሁኔታ አላህን መገዛት ሲሆን ይኽውም በበርካታ ነገሮች ይገለፃል።


1- በኢስላም የማይታወቅ አምልኮ መፍጠር ለምሳሌ ፦ በቀብር ዙሪያ መዞር፤ የተለያዩ ባእሎችን መፍጠርና ማክበር፤


2- መጨመርም ሆነ መቀነስ በማይፈቀድባቸው አምልኮዎች ላይ መጨመር ወይም መቀነስ፤


3- በተለየ ወቅት መፈፀም ያለበትን አምልኮ ሌላን ወቅት ፈጥሮ ማከናወን ወይም በአዲስ አሰራር መፈፀም፤


4- የተፈቀዱ ነገሮችን ለምሳሌ፦ ስጋ መብላት፤ ማግባት መተኛትና የመሳሰሉትን ራሱን ለመቅጣትና አምልኮ(ዒባዳ) ይሆናል በሚል ስሜት አለመጠቀምና የመሳሰሉት ናቸው።


ቢድዓ (ፈጠራ) ሁለት ዓይነቶች አሉት። እነሱም፡-


1- ከኢስላም የሚያስወጣ የቢድዓ ዓይነት ነው ። ለምሳሌ፦ ቁርኣን የአላህ ቃል መሆኑን በማመን ፈንታ የአላህ ቃል አይደለም ብሎ ማመን፣


2- ከኢስላም ባያስወጣም ነገር ግን አመፀኛና ወንጀለኛ የሚያሰኝ የቢድዓ ዓይነት ነው። ለምሳሌ፦ ተሰባስቦ በአንድ ድምፅ አላህን መዘከር ወይም


81


ማወደስ፤ ከሻዕባን ወር አስራ አምስተኛዋን ሌሊት ነቅቶ ማሳለፍ እና የመሳሰሉት ናቸው ።


ፈጠራን (ቢድዓን)የሚያወግዙና የሚያስጠንቅቁ የቁርኣን አንቀፆችና ሐዲሶች፡-


አላህ እንዲህ ይላል፡-





“ በዛሬው ዕለት ለእናንተ ሃይማኖታችሁን አሟላሁላችሁ ፀጋዬንም በእናንተ ላይ አትረፈረፍኩ ለእናንተም ከሃይማኖት ኢስላምን ወደድኩላችሁ” (አል-ማኢደህ: 3)


የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ በሃይማኖታችን ጉዳይ ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረና የጨመረ ሰው ፈጠራው ተመላሽ ነው ” ሙስሊም በሌላ ዘገባቸው “ ፍቃዳችን የሌለበትን ሥራ በአምልኮ ስም ያከናወነ ሰው ስራው ውድቅ (ተመላሽ) ነው ” ብለዋል ።


በሌላ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስም፡-


“ ከነገሮች ሁሉ አስቀያሚ ማለት በሃይማኖት ጉዳይ የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው”፣ “ ማንኛውም ፈጠራ ጥሜት ነው ” ብለዋል።


አል ኢማሙ ማሊክ የተባሉ ዓሊም “ በኢስላም አንድን ቢድዓ (ፈጠራ) መልካም ነው በሚል እሳቤ የፈጠረ ሰው ነቢዩ ሙሀመድ // ተልዕኳቸውን አላደረሱም እያለ መሆኑ አያጠራጥርም። በነቢዩ ዘመን ሃይማኖት ያልሆነ ነገር ዛሬ ሃይማኖት ሊሆን አይችልም ” ሲሉ ተናግረዋል ።


82


በኢስላም ጥሩ ፈጠራና መጥፎ ፈጠራ የሚባል አለን?


በሃይማኖት ጉዳይ የሚፈጠሩ ፈጠራዎችን ጥሩና መጥፎ ብሎ መከፋፈል (ማንኛውም ፈጥራ ጥመት ነው ) ከሚለው ነቢያዊ ሐዲስ ጋር የሚጋጭ የተሳሳተ አባባል ነው። ምክንያቱም ሐዲሱ ማንኛውም በሃይማኖት ጉዳይ የሚደረግ ፈጠራ ጥመት መሆኑን በግልፅ ያስረዳል።


ለቢድዓ/ ፈጠራ/ ምክንያት የሆኑ ነገሮች፡-


ሀ- ስለሃይማኖት አለማወቅ፣


ለ- ስሜትና ዝንባሌን መከተል፤


ሐ- ሀቅን በመቀበልና በመከተል ፈንታ ለተለያዩ ግለሰቦችና አስተያየቶች መወገን፣


ሠ- ከሃዲዎች ጋር መመሳሰል፣


ረ- መሰረተቢስና የተቀጠፉ ሐዲሶችን ማስረጃ ማድረግ፤


ሰ- ሃይማኖታዊ ማስረጃም ሆነ ንፁህ አእምሮ የማይደግፋቸውን ባህሎችና ልማዶችን ሙጥኝ ብሎ መያዝና የመሳሰሉት ናቸው።


አንድ ነገር ፈጠራ መሆኑን ለማወቅና ለቢድዓ ባለቤት በቂ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ወሳኝ ነጥቦች ፡-


1-የአምልኮ ዋና መነሻና መድረሻ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ማስረጃ የሌለውን ነገር በአምልኮ ስም ከመፈፀም መታቀብና መቆጠብ ከቢድዓ/ ከፈጠራ/ ለመዳን ዋና መሰረት ነው።


83


2- አንድ አምልኮ እንዲፈፀም የሚያስችል በነቢዩ /ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም/ ዘመን በቂ ምክንያት እያለው እሳቸውም ሆኑ ባልደረቦቻቸው ይህን ነገር አለመፈፀማቸው ይህ አምልኮ ፈጠራ መሆኑን በትክክል መረዳት ይቻላል።2


በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ በዝተውና ተሰራጭተው የሚስተዋሉ ፈጠራዎች፡


1- የነቢዩንም ሆነ የሌሎችን ግለሰቦች ልደት ማክበር፤


2- የአላህ መልእክተኛ // ወደ ሰማይ የወጡበትን (የሚዕራጅን) ሌሊት ነቅቶ በዒባዳ ማሳለፍ፤


3- ከሽዕባን ወር አስራ አምስተኛዋን ሌሊት ማክበር፤


4- ከሙታንም ሆነ በሕይወት ካሉ ግለሰቦች፤ ከስፍራዎች፤ ከቅርሶችና ከመሳሰሉት ነገሮች በረከትን(ረደኤትን) መፈለግ ፣


5- በህብረት አላህን መዘከር/ ማወደስ/፣


6- በአስክሬንና በቀብር ላይ ወይም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከቁርኣን ውስጥ የተለያዩ ምእራፎችንና አንቀፆችን ማንበብ ወይም ሰዎችን እንዲያነቡ መጠየቅ፣


7- ሶላት ለመስገድ ሲያስብ የሶላቱን ዓይነት፤ የረከዓዎችን ብዛት፤ ብቻውን ወይም በጀማዓ እንደሚሰግድ በአንደበቱ መናገር፤


8- አላህ ሆይ! በገሌ ወልይ ወይም በገሌ ሸይኽ ይሁንብህ እያሉ አላህን መማፀንና የመሳሰሉት ናቸው ።


ማሳሰቢያ፡-


2 ለዚህም መውሊድን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል። ምክንያቱም መውሊድን ለማውጣት ዋናው ምክንያት የነቢዩ // መወለድ ነው። ይህ ምክንያት በዘመናቸው ነበር። ታዲያ ልድታቸውን አከበሩ ወይስ አላከበሩም? ካከበሩም በምን መልኩ?


84


አንድ አምልኮ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው፡-


1ኛ- ሙታበዓ (መከተል) ሲሆን እሱም አላህን ስንገዛ በመልእክተኛው አማካኝነት በተዘረጋው ህግ መሰረት ብቻ መወሰንና


2ኛ- አምልኮን ለይስሙላ ሳይሆን ፍፁም ለአላህ ብቻ አድረጎ ማከናወን ናቸው።


ማሳሰቢያ፡-


ሙታበዓ(መከተል) የተባለው መስፈርት ይረጋገጥ ዘንድ የሚፈፀመው አምልኮ በስድስት ነገሮች ከሃይማኖቱ ህግና ደንብ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት እነሱም፡-


1- በምክንያቱ፤


2- በዓይነቱ፤


3- በብዛቱ፤


4- በአፈፃፀሙ፤


5- በግዜው እና


6- በስፍራው ናቸው።


ወደ ተውሂድ ጥሪ ማድረግ፡--


ወደ ተውሂድ ጥሪ ማድረግ ትልቅ ደረጃ ያለው የነቢያትና የመልዕክተኞች እንደዚሁም የተከታዮቻቸው የሥራ መስክ ነው። ይህም ትልቅ ሥራ አመርቂ ውጤት ያመጣ ዘንድ አላህ ያስቀመጣቸውን የዳዕዋ ስልቶችና የመልእክተኛውን የዳዕዋ አስተምህሮት መከተል ይበጃል። አላህ እንዲህ ይላል፡-


85





“ ወደ ጌታህ መንገድ በጥበብና በጥሩ ተግሳፅ ጥሪ አድርግ በመልካሟም ተከራከራቸው ” (አነህል: 125)


አላህ በሌላ አንቀፅ ላይ እንዲህ ይላል፡-





“ ይህች መንገዴ ናት ወደ አላህ እጠራለሁ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን አላህም በእርሱ ከሚያጋሩት ነገር የፀዳ ነው እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም በል” (ዩሱፍ : 108)


የአላህ መልእክተኛ // ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡-





“ በአላህ እምላለሁ አንድን ሰው አላህ በአንተ አማካኝነት ቀናውን መንገድ ቢመራው ለአንተ ብዙ ቀያይ ግመሎችን ከማግኘት ይበልጣል” አሉት።


በሌላ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስም፡-





“ ወደ ቀና መንገድ ጥሪ ያደረገ ሰው የተከታዮቹ ምንዳ ሳይቀነስ እነሱ የሚያገኙትን አጅርና ምንዳ ያህል ያገኛል ወደ ጥመት ጥሪ ያደረገም የተከታዮቹ


86


ወንጀል ሳይቀነስ በተከታዮቹ ላይ የተፃፈው ወንጀል በእርሱ ላይ ይፃፍበታል” ብለዋል ።


ተውሂድ ከማንኛውም ነገር ቅድሚያ መታወቅ ያለበትና ወደ እርሱ ጥሪ ሊደረግለት የሚገባው የመጀመሪያ ግዴታ ነው።


የአላህ መልእክተኛ // ሙዓዝ የተባለውን ታላቅ ሱሀቢ(ባልደረባ) ወደ የመን አገር ላስተማሪነት ሲልኩት፦





“ አንት መጽሐፍ የተሰጣቸውን ሰዎች ታገኛለሕ በቅድሚያ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና እኔ የአላህ መልእክተኛ መሆኔን አስተምራቸው ” አሉት።


ወደ ተውሂድ ጥሪ ለማድረግ ከሚያግዙ ነገሮች፡-


1- ከባለ- ሐብቶች ጋር በመተባበር የተውሂድ መፃሕፍትና ካሴቶችን አባዝቶ ለሰዎች እንዲደርሱ ማድረግ፣


2- ሰዎች በተውሂድ ዙሪያ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማስተማር፣


3- ልጆችን በተውሂድ ኮትኩቶ ማሳደግ፣


4-ኮርሶችንና ሙሃደራዎችን በማካሄድ የተውሂድን ወሳኝነት ለሰዎች ማስረዳት እና የመሳሰሉት ናቸው።


87


በመጨረሻም በእዝነቱና በችሮታው ይህን የተውሂድን መጽሐፍ በመተርጎም ለትልቅ ስራ ተሳታፊ ላደረገኝና ላበቃኝ ለአላህ ሰማያትንና ምድርን የሞላ ምስጋና ይገባው እያልኩ ይህን መጽሐፍ በማሳተምና በማባዛት ትብብሩን ላበረከተና በትርጉሙ ዙሪያ ገንቢና ጠቃሚ አስተያየቶን ለለገሰን ሁሉ አላህ ጥሩ ምንዳና ምህረት እንዲከፍለው ዱዓችን ነው።


በአላህ ፍቃድ እንደ- ሂጅራ አቆጣጠር በ17\06\1435 ላይ ተፈጸመ


وصلى الله عَل نبينا مُمد وعَل آلَ وصحبه وسلم تسليما



 



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ

ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ...

ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ማስገባት እና የፈጠራዉ አደጋ

10 ለአዲስ ሰለምቴ መመሪያ ሁሉን ...

10 ለአዲስ ሰለምቴ መመሪያ ሁሉንም የህይወት ዘርፎች የሚያካትቱ አስፈላጊ የሆኑ ሸሪዓዊ ማብራሪያዎችና ቀለል ያሉ ህግጋት ለአዲስ ሰለምቴዎች