
አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ
ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ
አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ
ዝግጅት፦ የተከበሩ ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን
ባዝ (አላህ ይዘንላቸው)
መግቢያ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ
በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው።
የመጨረሻውም ሀገር አላህን ለሚፈሩ ለጥንቁቆቹ ነው። የአላህ
ውዳሴና ሰላም የአላህ ባሪያውና መልዕክተኛው በሆኑት ነቢዩ
ሙሀመድ፣ በተከታዮቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ሁሉ
ይስፈን።
በመቀጠልም፦
ይህ መልዕክት አጠር ባለ መልኩ የተዘጋጀና ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ስለ ኢስላም ሊያውቃቸው የሚገቡ አንዳንድ ቁም
ነገሮችን የሚያብራራ ሲሆን ርዕሱንም፦ "አሳሳቢ ትምህርቶች
ለብዙሀኑ ህዝብ" በሚል ሰይሜዋለሁ።
በዚህ መልዕክት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሊጠቅምበት
ዘንድ፤ ይህንን ሥራዬን ሊቀበለኝም ዘንድ አሏህን
እማጸነዋለሁ። እርሱ በጣም ቸር እና ለጋሽ ነውና።
ዐብዱል ዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ
2
አሳሳቢ ትምህርቶች ለብዙሀኑ ህዝብ1 .
የመጀመሪያው ትምህርት ሱረቱል ፋቲሓ (የመክፈቻ
ምዕራፍ) እና አጫጭር ሱራዎች
ሱረቱል ፋቲሓ እና ከሱረቱ አዝ-ዘልዘላህ እስከ ሱረቱ አን-ናስ
ድረስ ያሉትን አጫጭር ምዕራፎች የተቻለውን ያህል ቃል
በቃል እንዲያጠኑ ማድረግ፤ የአነባበብ ስህተትንም
ማስተካከል፤ የሚያነቧቸውንም ምዕራፎች በቃላቸው
ማስሸምደድና ከምዕራፎቹ መረዳት የሚገባቸዉን መልዕክቶች
ማብራራት።
ሁለተኛ ትምህርት: የእስልምና ማዕዘናት
የእስልምና አምስቱ ማዕዘናት ማብራሪያ፡ የመጀመሪያውና
ትልቁ: "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና
ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር" ነው።
ይህም ትርጉሙን ከመተንተንና የ"ላኢላሃ ኢለሏህ"ን
መስፈርቶች ከማብራራት ጋር ነው። ትርጉሙም: - (ላኢላሃ)
የሚለው ቃል ከአላህ ውጪ የሚመለኩ ነገሮችን ባጠቃላይ
ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን (ኢለሏህ) የሚለው ቃል ደግሞ
አምልኮን አጋር ለሌለው ለአላህ ብቻ የሚያፀድቅ ነው።
የ(ላኢላሃ ኢለሏህ) መስፈርቶች ደግሞ: መሃይምነትን የሚፃረር
እውቀት፤ ጥርጣሬን የሚፃረር እርግጠኝነት፤ ሺርክን የሚፃረር
ለአላህ ብቻ ማጥራት (ኢኽላስ)፤ ማስተባበልን የሚፃረር
1(መጅሙዑ ፈታዋ ወመቃላት ሙተነዊዓህ) በሚለው በተከበሩት ሸይኽ መፅሀፍ
ውስጥ በቅፅ ሶስት ከገፅ (288 - 298) ተሰራጭታ ትገኛለች።
3
እውነት፤ ጥላቻን የሚፃረር ውዴታ፤ መተውን የሚፃረር
ታዛዥነት፤ እምቢተኝነትን የሚፃረር መቀበልና ከአላህ ውጪ
በሚመለኩ ነገሮች መካድ ናቸው። እነዚህ ስምንት
መስፈርቶችም ከዚህ ቀጥሎ ባሉ ስንኞች ተሰብስበው ይገኛሉ።
ማወቅ በእርግጠኝነት
ማጥራት በእውነተኝነት፤
መውደድ በታዛዥነት
መቀበል የርሱን ብቸኝነት
መካድ የቱንም ባላንጣነት
ጨምረው በስምንተኝነት።
በተጨማሪም "ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ ናቸው ብሎ
መመስከርን።" ማብራራትም ያስፈልጋል። እርሷም
የሚከተሉትን ታስፈርዳለች። እርሳቸው የተናገሩትን እውነት
ብሎ መቀበል፤ እርሳቸው ያዘዙትንም መታዘዝ፤ እርሳቸው
የከለከሉትንና ያስጠነቀቁትን መራቅ፤ አላህ ዐዘ ወጀልና
መልክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም
በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በደነገጉት መልኩ ካልሆነ በቀርም
አላህን አለማምለክ ነው። በመቀጠል የተቀሩትን የእስልምና
አምስት ማዕዘናትን ለተማሪው ያብራራል። እነርሱም:- ሶላት፣
ዘካህ፣ ረመዳንን መጾምና ወደርሱ መንገድን ለቻለ ሰው
የተከበረውን የአላህን ቤት ሐጅ ማድረግ ናቸው።
4
ሶስተኛ ትምህርት: የኢማን ማዕዘናት
የኢማን መሰረቶች ስድስት ናቸው። እነርሱም፡- በአላህ፣
በመላእክቶቹ፣ በመጻህፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻው
ቀን ማመን፣ እንዲሁም ጥሩም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔና
ፍቃድ (በቀደር) መሆኑን ማመን ናቸው።
አራተኛው ትምህርት: የተውሒድ ክፍሎች እና
የሺርክ ክፍሎች
የተውሒድ (አላህን የመነጠል) ክፍሎችን ማብራራት፤
ዓይነቶቹም ሦስት ሲሆኑ እነርሱም፦ በጌትነቱ መነጠል
(ተውሒድ አርሩቡቢያ) ፣ በተመላኪነቱ መነጠል (ተውሒድ
አልኡሉሂያ) እና በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል (ተውሒድ
አልአስማእ ወስሲፋት) ናቸው።
ተውሒድ አር-ሩቡቢያህ (በጌትነቱ መነጠል)፡- ማለት
አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና የሁሉም ነገር አስተናባሪም መሆኑን
በዚህም ላይ ምንም አጋር እንደሌለው ማመን ነው።
ተውሒድ አል-ኡሉሂያህ (በተመላኪነቱ መነጠል)
ማለት፡-
በእውነት የሚመለከው አሏህ ብቻ እንደሆነና በአምልኮ
ምንም አጋር እንደሌለው ማመን ነው። የ “ላኢላሀ ኢለላህ”
ትርጓሜውም ይህ ነው። ትርጉሙም ከአላህ ውጪ በእውነት
የሚመለክ አምላክ የለም ማለት ነውና። ሶላትና ፆም እንዲሁም
ሌሎችም የዒባዳ (አምልኮ) አይነቶችን በአጠቃላይ ለአላህ ብቻ
5
ጥርት አድርጎ መፈጸም የግድ ይላል። ከአላህ ውጪ ላለ
ለማንኛውም አካል እነዚህን አምልኮዎች መስጠት
አይፈቀድም።
ተውሒድ አል አስማእ ወስሲፋት (በስሞቹና
በባህሪያቱ መነጠል) ማለት፡-
በቁርኣንና በትክክለኛ ሐዲሦች ስለ አላህ ስሞችና ባህርያት
የተጠቀሱትን በሙሉ ማመን፤ እነዚህን ስምና ባህሪያቱን
ለእርሱ በሚገባው መልኩ ለብቻው ማፅደቅ፤ ይህንንም
ስናደርግ ያለ ተሕሪፍ (ትክክለኛ ትርጓሜያቸዉን ሳንቀይር) ፣
ያለ ተዕጢል (ትርጉም አልባ ሳናደርግ) ፣ ያለ ተክዪፍ (ዝርዝር
ሁኔታቸውን ሳንገልጽ) እና ያለ ተምሢል (ከፍጡራን ጋር
ሳናመሳስል) ማፅደቅ ነው። ይህንንም የምናደርገው
የሚከተለውን የአላህ ቃል መሰረት በማድረግ ነው፦
{በል «እርሱ አላህ አንድ ነው። (1) «አላህ (የሁሉ)
መጠጊያ ነው። (2) «አልወለደም፤ አልተወለደምም።(3)
«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»} [ሱረቱ አስሶመድ:
ሙሉ ሱራው].
አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህም ብሏል፦
{የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱም ሰሚው
ተመልካቹ ነው} [አሽ ሹራ፡ 11].
ከፊል ዑለሞች ደግሞ የተውሒድን ክፍሎች ሁለት አይነት
እንደሆኑ ጠቅሰዋል። የስምና ባህሪያት አሀዳዊነቱን በጌትነት
አሀዳዊነቱ ስር አጠቃለውት ማለት ነው። ይህንን
ማድረጋቸውም የሚያወዛግብ አይደለም። ምክንያቱም
በሁለቱም የአከፋፈል ዘዴዎች የተፈለገው ምን እንደሆነ ግልፅ
ነውና። የሺርክ ክፍሎች ሶስት አይነት ናቸው። ትልቁ ሺርክ፣
ትንሹ ሺርክና ድብቁ ሺርክ ናቸው።
ትልቁ ሺርክ: የስራን መበላሸትና በርሱ ላይ ለሞተ ሰውም
እሳት ውስጥ የመዘውተርን መዘዝ ያስከትላል። አላህ እንዲህ
ብሏል:-
﴿ ... ولو اوكشْأ طبلَ مهنع ام اونكَ نولمعي ﴾ ماعنلأا[ : 88 ] .
{ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር።}
[አል አንዓም፡ 88].
በሌላም አንቀጽ አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿ ام نكَ يكشْملل نأ اورمعي دجاسم للَّا نيدهاش عَ مهسفنأ رفكلاب
كئلوأ تطبح مهلامعأ فو رالنا مه نولَاخ ﴾ ةبولتا[ : 17 ] .
{ለከሓዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ
ሲኾኑ የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፡፡ እነዚያ
ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ እነሱም በእሳት ውስጥ
ዘውታሪዎች ናቸው፡፡} [አት ተውባህ፡ 17].
ሸርክን እየፈፀመ የሞተ ምህረትን አያገኝም ጀነትም በእርሱ
ላይ እርም ናት። አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ብሏል፦
﴿ ... نإ للَّا ل رفغي نأ كشْي هب رفغيو ام نود كلذ نمل ءاشي ... ﴾
ءاسنلا[ : 48 ] .
{አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። ከዚህ
ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል።}
[አንኒሳእ: 48].
በሌላም አንቀፅ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ
ብሏል:
{እነሆ በኣላሀ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ገነትን
በእርግጥ እርም አደረገ። መኖርያውም እሳት ናት።
ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የላቸውም::} [አል ማኢዳህ:72].
ከትልቁ ሽርክ አይነቶች መካከልም ሙታንንና ጣኦታትን
መለመን፣ እርዳታ ከነርሱ መፈለግ፣ ለእነርሱም ስለት መግባት፣
እርድ ማቅረብና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው።
ትንሹ ሽርክ (ሽርኩል-አስገር)፡- ይህ ደግሞ በቁርአንና
በሐዲሥ መረጃዎች ሽርክ የሚል ስያሜ ቢሰጠውም ነገር ግን
ከትልቁ ሽርክ የማይመደብ ነው። ለምሳሌ፡ አንዳንድ ስራዎችን
ለይዩልኝ መስራት፣ ከአላህ ውጪ ባለ አካል መማል፣ "አላህ እና
እገሌ የፈለጉት ሆነ" ብሎ ማለትና የመሳሰሉት ናቸው።
ይህንንም ያልንበት ምክንያት የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ
ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ ነው፦
{"በናንተ ላይ ከምፈራቸው ነገሮች መካከል እጅግ
አስፈሪው ነገር ትንሹ ሺርክ ነው። አሉ። ስለርሱም
ተጠየቁ። እርሳቸውም "ይዩልኝ ነው።" አሉ።}1.
ይህንንም ሐዲሥ ኢማሙ አሕመድ እና በይሀቂይ
ከመሕሙድ ቢን ለቢድ አልአንሷሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ
መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጠንካራ በሆነ ሰነድ
ዘግበውታል። ጠበራኒይም እንዲሁ ከመሕሙድ ቢን ለቢድ፣
መሕሙድ ደግሞ ከራፊዕ ኢብን ኸዲጅ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)
ጠንካራ በሆነ ሰነድ ዘግበውታል።
ተከታዩም የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
(የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር፦
{ከአላህ ውጭ ባለ አንዳች ነገር የማለ በእርግጥም
አጋርቷል።}2.
1አሕመድ (5/428)
2ቡኻሪይ በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ (6271)፤ ሙስሊም በአይማን ምዕራፍ
(1646)፤ ቲርሚዚይ በኑዙርና አይማን ምዕራፍ (1533)፤ ነሳኢይ በአይማንና ኑዙር
ምዕራፍ (3764)፤ አቡዳውድ በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ (3249)፤ ኢብኑማጀህ
በከፋራት ምዕራፍ (2094)፤ አሕመድ በ(1/47)፤ ማሊክ በኑዙርና አይማን ምዕራፍ
(1037)፤ ዳሪሚይ በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ (2341) ዘግበውታል።
9
ኢማሙ አሕመድ ከዑመር ቢን አልኸጧብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሶሒሕ በሆነ
ሰነድ ዘግበውታል። እንዲሁም አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚይም
ሶሒሕ በሆነ ሰነድ ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ
መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በተላለፈ ሐዲሥ ነቢዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ
ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል፦
{ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ በእርግጥም ክዷል
ወይም አጋርቷል።}1.
ተከታዩም የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
(የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር፦
{"አላህ እና እከሌ ከፈለጉ..." አትበሉ። ይልቁንም "አላህ
ከፈለገ ከዚያም እከሌ ከፈለገ..." በሉ።}2 .
አቡዳውድም ከሑዘይፋ ኢብኑል የማን ረዺየሏሁ ዐንሁ -
አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሶሒሕ ሰነድ
ዘግበውታል።
ይህ የሽርክ አይነት (ትንሹ ሽርክ) ከዲን እስከመውጣት
አያደርስም፤ እንዲሁም በእሳት ዘላለም ለመዘውተርም
1ቡኻሪይ በአደብ ምዕራፍ (5757)፤ ሙስሊም በአይማን ምዕራፍ (1646)፤ ቲርሚዚይ
በኑዙርና አይማን ምዕራፍ (1535)፤ ነሳኢይ በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ (3766)፤ አቡዳውድ
በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ (3251)፤ ኢብኑማጀህ በአልከፋራት ምዕራፍ (2094)፤ አሕመድ
በ(2/69)፤ ማሊክ በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ (1037)፤ ዳሪሚይ በአይማንና ኑዙር ምዕራፍ
(2341) ውስጥ ዘግበውታል።
2አቡዳውድ አልአደብ (4980)፤ አሕመድ በ(5/399) ዘግበውታል።
10
አይዳርግም፤ ነገር ግን ማመን ግዴታ የሆነውን የተውሒድን
ምሉዕነት (ከማል) ያጓድላል።
ሶስተኛው የሽርክ አይነት ደግሞ ድብቁ ሽርክ
(ሽርኩል ኸፍይ ይባላል)፡- ማስረጃውም የሚከተለው
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ ሶላትና ሰላም
በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር ነው፡-
{እኔ ዘንድ ከመሲሑ ደጃል ይበልጥ የምፈራላችሁን
ነገር አልነግራችሁምን?” አሉ። ሶሓቦችም፡ “አዎን
ይንገሩን የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!” አሉ፤ እሳቸውም
“ድብቁ ሽርክ ነው። (የዚህም ምሳሌው) አንድ ሰው
ለሰላት ይቆምና ሰዎች እርሱን የሚመለከቱት መሆኑን
ሲያውቅ ሰላቱን ይበልጥ ያሳምረዋል።}1.
ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው ከአቡሰዒድ አልኹድሪይ
ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና-
ዘግበውታል።
ሽርክን በሁለት ብቻ መክፈልም ይቻላል
እነርሱም፦
ትልቁና ትንሹ ናቸው። ድብቁ ሽርክ የተባለው ግን ሁለቱንም
የሽርክ አይነቶች የሚያጠቃልል ይሆናል።
1ኢብኑማጀህ አዝዙህድ (4204) ላይ፤ አሕመድ በ(3/30) ዘግበውታል።
11
(ድብቁ ሺርክ) ትልቁ ሽርክ ሆኖ ሊከሰትም ይችላል፤ የዚህም
ምሳሌው የሙናፊቆች ሽርክ ነው። ምክንያቱም ለነፍሳቸው
ፈርተው ለታይታ ከላይ ብቻ ኢስላምን እያንፀባረቁ ባጢል
የሆነውን እምነታቸውን ስለሚደብቁ ነው።
ትንሹ ሽርክ ሆኖ ሊከሰትም ይችላል፤ የዚህም ምሳሌው
ለታይታ መስራትን የመሰለው ነው። ቀደም ብሎ በተጠቀሰው
ከመሕሙድ ኢብኑ ለቢድ አልአንሳሪይና ከአቡሰዒድ
አልኹድሪይ በተላለፈው ሐዲሥ ላይ ተገልጿል። መልካምን
የሚገጥመው አላህ ብቻ ነው።
አምስተኛው ትምህርት: ኢሕሳን (በጎ ማድረግ)
የአል-ኢሕሳን (የበጎ ማድረግ) ማዕዘን፡- አላህን ልክ
እንደምታየው ሆነህ ልታመልከው ነው፤ አንተ ባታየው እንኳ
እርሱ ያይሃልና።
ስድስተኛው ትምህርት: የሶላት መስፈርቶች
የሰላት ቅድመ ሁኔታዎች (መስፈርቶች) ዘጠኝ ናቸው።
እነርሱም፦
ሙስሊም መሆን፣ የጤናማ አእምሮ ባለቤት መሆን፣
ነገሮችን መለየት የሚያስችል እድሜ ላይ መድረስ፣ ሐደሥን
ማስወገድ፣ ነጃሳን ማስወገድ፣ ሀፍረተ ገላን መሸፈን፣ የሰላት
ወቅት መግባት፣ ወደ ቂብላ (ካዕባ) አቅጣጫ መዞር እና ኒያ
ናቸው።
12
ሰባተኛው ትምህርት: የሶላት ማዕዘን
የሰላት ማዕዘናት (ሩክኖች) አስራ አራት ናቸው እነርሱም፡-
የመቆም አቅሙ ካለው ቆሞ መስገድ፤ ተክቢረተል ኢሕራም
(የመክፈቻ ተክቢራ)፤ የፋቲሓን ምዕራፍ ማንበብ፤ ሩኩዕ
ማድረግ (ማጐንበስ)፤ ከአጎነበሱበት ቀና ብሎ መቆም፤ በሰባቱ
የሰውነት አካላት ሱጁድ ማድረግ (በግንባር መሬት ላይ
መደፋት)፤ ከሱጁድ መነሳት፤ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል
መቀመጥ፤ በሁሉም የስግደት ተግባራት ላይ እርጋታን
መላበስ፤ በማእዘናቱ መካከል ያለውን ቅደም ተከተል
መጠበቅ፤ የመጨረሻው ተሸሁድ (አተሒያቱ) ማለት፤
ለተሸሁዱ መቀመጥ፤ በነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (የአላህ
ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላትን ማውረድ
እና ሁለቱ ተስሊሞች (በቀኝና በግራ እየዞሩ አሰላሙ ዐለይኩም)
ማለት ናቸው።
ስምንተኛው ትምህርት: የሶላት ዋጂቦች
(ግዴታዎች)
ስምንት ናቸው፤ እነርሱም፦
ከተክቢረተል ኢሕራም ውጪ ያሉት ተክቢራዎች በሙሉ፤
ኢማም ሆኖ ወይም ብቻውን ሆኖ ለሚሰግድ ሰው (ሰሚዓላሁ
ሊመን ሐሚዳህ) ማለቱ (ትርጉሙም፡ አላህ አመስጋኙን ሰሚ
ነው)፤ ለሁሉም ሰጋጅ (ረበና ወለከል ሐምድ) ማለቱ
(ትርጉሙም፡ ጌታችን ሆይ ምስጋና ለአንተ የተገባ ነው።)፤ ሩኩዕ
ላይ (ሱብሓነ ረቢየል ዓዚም) ማለት (ትርጉሙም፡ ታላቁ ጌታዬ
13
ከጉድለቶች ጥራት የተገባው ነው)፤ ሱጁድ ላይ (ሱብሓነ ረቢየል
አዕላ) ማለት (ትርጉሙም፡ የበላይ የሆነው ጌታ ጥራት
ይገባው)፤ በሁለቱ ሱጁዶች መካከልም (ረቢግፊርሊ) ማለት
(ትርጉሙም፡ ጌታዬ ማረኝ)፤ የመጀመሪያው ተሸሁድ ላይ
(አትተሒያቱ) ማለት፤ ለመጀመሪያው ተሸሁድ መቀመጥ
ናቸው።
ዘጠነኛው ትምህርት: የተሸሁድን ማብራሪያ
ይሀውም እንዲህ ማለት ነው፦
{አትተሒያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦዪባቱ አስሰላሙ
ዓለይከ አይዩሀ-ንነቢዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ አስሰላሙ
ዓለይና ወዓላ ዒባዲላሂ-ስሷሊሒን አሽሀዱ አን-ላኢላሀ ኢለላህ
ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ}.
(ትርጉሙም፦ ክብር ለአላህ የተገባ ነው። እዝነቶችና
መልካም ነገሮች ሁሉ የአላህ ናቸው። አንተ ነብይ ሆይ!
የአላህ ሰላም፣ እዝነትና በረከቱ ይስፈንብህ። በእኛና
በአላህ ቅን ባሪያዎች ላይም ሰላም ይስፈን። ከአላህ ሌላ
በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።
ሙሐመድም ባሪያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን
እመሰክራለሁ።).
14
በመቀጠል በነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋትና
በረካ ለማውረድ እንዲህ ይላል፦
{አልላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሐመድ ወዓላ አሊ ሙሐመድ ከማ
ሶለይተ ዓላ ኢብራሂም ወዓላ አሊ ኢብራሂም ኢንነከ ሓሚዱን
መጂድ ወባሪክ ዓላ ሙሐመድ ወዓላ አሊ ሙሐመድ ከማ
ባረክተ ዓላ ኢብራሂም ወዓላ አሊ ኢብራሂም ኢንነከ ሐሚዱን
መጂድ{.
(ትርጉሙም፡ አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው
ላይ ውዳሴህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሀመድና
በቤተሰቦቻቸው ላይም ውዳሴህን አውርድ፤ አንተ ምስጉንና
የላቅክ አምላክ ነህና። አላህ ሆይ! በኢብራሂምና
በቤተሰቦቻቸው ላይ በረከትህን እንዳሰፈንክ ሁሉ
በሙሓመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም በረከትህን
አዉርድ። አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህና።}.
የመጨረሻው ተሸሁድ ላይም ከጀሀነምና ከቀብር ቅጣት፣
በህይወት ሳለም ሆነ ከሞት በኋላ ከመፈተን፣ እንዲሁም
ከመሲህ ደጃል ፈተና የአሏህን ጥበቃ ይማፀናል። ከዚያም
የሚፈልገውን ዱዓእ መርጦ ያደርጋል። በተለይም ከነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተዘገቡትን ይበል፤ ከነዚህም
መካከል፦
{አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ ወሹክሪከ ወሑስኒ ዒባደቲክ፤)
{አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ ወሹክሪከ ወሑስኒ ዒባደቲክ፤
አልላሁመ ኢንኒ ዞለምቱ ነፍሲ ዙልመን ከሢራ ወላ የግፊሩ
ዙኑበ ኢላ አንተ ፈግፊርሊ መግፊረተን ሚን ዒንዲክ ወርሐምኒ
ኢንነከ አንተል ገፉሩ ረሒም}.
{ትርጉሙም፡- አላህ ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣
ለማመስገንና አምልኮህን ለማሳመር እርዳኝ። አላህ ሆይ!
እኔ ነፍሴን በበርካታ በደል በድያለሁ ኅጢአትንም ከአንተ
ውጭ የሚምር የለምና ከአንተ የሆነን ምህረት ለግሰኝ።
እዘንልኝም አንተ መሀሪና አዛኝ ነህና።}.
የመጀመሪያውን ተሸሁድ በተመለከተ በዙሁር፣ በዐስር፣
በመግሪብ እና በዒሻእ ሶላቶች ልክ ከሁለቱ የምስክርነት ቃላት
በኋላ ለሦስተኛው ረከዓ ይቆማል፤ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም ላይ ሰለዋት ካወረደ በኋላ መቆሙ ደሞ በላጭ ነው።
ይህም የሐዲሦቹ አጠቃላይ መልዕክት ይህን የሚያሲዝ
በመሆኑ ነው። ከዚያም ለሦስተኛው ረከዓ ይቆማል።
16
አስረኛ ትምህርት: የሶላት ሱናዎች
ከእነርሱም መካከል፦
1 - የመክፈቻ ዱዓእ (ዱዓኡል ኢስቲፍታሕ)
2 - ከሩኩዕ በፊትና በኋላ በሚቆም ጊዜ ቀኝን መዳፍ በግራ
መዳፍ ላይ አድርጎ ደረት ላይ ማሳረፍ፤
3 - የእጆችን ጣቶች ገጣጥሞ በመዘርጋት ከትከሻ ወይም
ከጆሮ ትይዩ አድርጎ ማንሳት፤ ይህም የሚደረገው
በሚከተሉት ቦታዎች ይሆናል። የመጀመሪያው የመክፈቻ
ተክቢራ ላይ፤ ሩኩዕ በሚደርግበት ጊዜ፤ ከሩኩዕ ቀና
በሚባልበት ጊዜ፤ ከመጀመሪያው ተሸሁድ በኋላ
ለሶስተኛው ረከዓ በሚነሱበት ጊዜ ናቸው።
4 - በሩኩዕና በሱጁድ ወቅት ከአንድ ጊዜ በላይ ተስቢሕ
(ሱብሓነ ረቢየል ዐዚም ወይም ሱብሓነ ረቢየል አዕላ)
ማለት፤
5 - ከሩኩዕ ቀና ካሉ በኋላ "ረበና ወለከል ሓምድ" ከሚለው
ሌላ ዱዓዎችን መጨመር፤ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል
በሚያደርገው ዱዓእ "ረብቢግፊርሊ" በሚለው መሀርታን
ሲጠይቁ ከአንድ ጊዜ በላይ መጨመር።
6 - ሩኩዕ በሚያደርጉበት ጊዜ ጭንቅላትን ከወገብ ትይዩ
ማድረግ።
7 - ሱጁድ በሚያደርጉበት ጊዜ የእጅን ጡንቻዎች ከጐኖቹ
ማላቀቅ እንዲሁም ሆድን ከታፋ፣ ታፋን ከባት ማራራቅ፤
8 - ሱጁድ በሚያደርጉበት ጊዜ ክንዶችን ከመሬት ከፍ
ማድረግ፤
17
9 - በሁለቱ ሱጁዶች መካከል እና በመጀመሪያው ተሸሁድ
ላይ ግራ እግርን አንጥፎ እላዩ ላይ በመቀመጥ የቀኝ እግርን
ጣቶች መትከል፤
10 - አራት እና ሦስት ረከዓዎች ባላቸው ሶላቶች የመጨረሻ
ተሸሁድ ላይ “ተወሩክ” በማድረግ መቀመጥ፤ “ተወሩክ”
ማለት ግራ እግርን ከቀኝ እግር ስር አሳልፎ የቀኝ እግር
ጣቶችን በመትከል መቀመጫን መሬት ላይ አሳርፎ
መቀመጥ ነው።
11 - በመጀመሪያው እና በመጨረሻው ተሸሁድ ላይ
ከተቀመጡበት ሰዓት አንስቶ እስከ ተሸሁድ መጨረሻው
ድረስ በአመልካች ጣት ማመላከትና ዱዓእ ላይ ጣትን
ማንቀሳቀስ።
12 - በመጀመሪያው ተሸሁድ ላይ በነብዩ ሙሐመድ እና
በቤተሰቦቻቸው
እንዲሁም
በኢብራሂምና
በቤተሰቦቻቸውም ላይ የአላህ ውዳሴና በረከት እንዲሰፍን
አሏህን መለመን፤
13 - በመጨረሻው ተሸሁድ ላይ ዱዓእ ማድረግ፤
14 - በፈጅር ሰላት፣ በጁምዓ ሰላት፣ በሁለቱ ኢዶች ሰላት
እና በኢስቲስቃእ (በዝናብ እጦት ጊዜ የሚሰገድ ሰላት) ላይ
እንዲሁም በመግሪብ እና በኢሻዕ የመጀመሪያ ሁለቱ
ረከዐዎች ላይ ድምፅን ከፍ አድርጐ መቅራት፤
15 - በዙህር እና ዐስር ሰላቶች እንዲሁም የዒሻእ
የመጨረሻዎቹ ሁለት ረከዓዎች እና የመግሪብ ሶስተኛው
ረከዓ ላይ ድምፅን ሳያሰሙ መቅራት፤
18
16 - ከፋቲሐ በተጨማሪ ሌላ የቁርአን ምዕራፍ ማንበብ
እንዲሁም ከላይ ከጠቅስናቸው በተጨማሪ ሌሎች የሰላት
ሱናዎችንም መተግበር፤ ከነዚህም ውስጥ፡- ለብቻው
የሚሰግድም ሆነ ኢማሙ ወይም ኢማሙን ተከትሎ
የሚሰግድ ሰው ከሩኩዕ በሚነሳበት ወቅት (ረበና ወለከል
ሐምድ) ከሚለው ውጪ ያሉ ተጨማሪ ውዳሴዎችን
ማድረግ ይህም ሱና ነው፤ ሩኩዕ በሚያደርግበት ጊዜ
የእጆቹን ጣቶች በመከፋፈት (በመሀከላቸው ክፍተት
በማድረግ) ሁለቱን እጆች ጉልበቶቹ ላይ ማሳረፍም ተጠቃሽ
ሱናዎች ናቸው።
አስራ አንደኛ ትምህርት: ሶላትን የሚያበላሹ
ነገሮች
ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች ስምንት ናቸው፤
እነርሱም፦
1 - በማወቅና እያስታወሱ በሶላት መሀል መናገር ሰላትን
ያበላሻል። የረሳ ወይም ያላወቀ ሆኖ ቢናገር ግን ሶላቱ
አይበላሽበትም።
2 -መሳቅ .
3 -መብላት .
4 -መጠጣት .
5 - የሐፍረተ ገላ መገለጥ .
6 - የቂብላ አቅጣጫን እጅግ በሳተ መልኩ መዞር .
7 - በሶላት ውሰጥ ከሶላቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን
ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ .
19