መጣጥፎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?


የተከበረው ቁርኣን፥ ለሰው ልጆች የተፈጠሩበትን ዓላማ ሊያብራራ፣ በዱንያም ሆነ በመጨረሻውም ዓለም ደስታን


ወደሚጎናፀፉበት መንገድ ሊመራ፣ ከሞት በኋላ ካለው ዘልዓለማዊ መከራም ነፃ እንዲያደርጉበት የዓለማቱ ጌታ እና ፈጣሪያቸው


የነቢያትና መልእክተኞች መደምደሚያ በሆኑት ሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ላይ ያወረደው የአላህ ቃሉ ነው።


ቅዱስ ቁርኣን ዘላለማዊ ምልክትና ተዓምር ነው፤ የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ነብይ


ለመሆናቸው ማስረጃ ነው። አላህም የሰው ልጆችንና ጂኖችን የቁራኣንን አምሳያ ቢጤውን፤ እንዲያውም ይባስ ብሎ አንድ


ምዕራፍ እንኳ እንዲያመጡ ተወራረዳቸው። ነገር ግን አልቻሉም።


ከ1400 ዓመታት በፊት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ የማዛባት እና የመለወጥ እጅ አላረፈበትም፤ እናም በወረደበት የዐረብኛ ቋንቋ


ተጠብቆ ይቆያል። ጥራት የተገባው አምላክ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እንደሚጠብቀው ዋስትና ሰጥቷልና።


ቅዱስ ቁርኣን የእስልምና ዋና ምንጭ ነው፤ በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ የሰውን ህይወት የሚያደራጅ እና የሚመራ ህግም ነው።


ጥሪውም ብቸኛ የሆነውን ፈጣሪ ወደ ማምለክ ነው። የሰው ልጅ ጌታውን እና ሃይማኖቱን ለማወቅ የሚያስፈልገውን ያብራራል፤


የአጽናፈ ሰማይ ፍጥረት መጀመሪያ እና የሰው ልጅ የፍጥረት ደረጃዎችን ይገልጻል፤ ስላለፉም ይሁን ለወደፊት ስለሚታዩ የሩቅ


ሚስጥሮች እንዲሁም ስለቀደሙት ነቢያት ታሪክ የአላህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈንና አላህ እንዴት እንደረዳቸው እና


ጠላቶቻቸውንም እንዳጠፋ ይተርካል። በውስጡ የአምልኮና የግብይት መሠረቶች፣ ወደ መልካም ሥነ-ምግባርም መጣራት፣


ከወራዳ ሥነ-ምግባርም ማስጠንቀቂያን ይዟል። በመጨረሻይቱም ዓለም ስላለው ዕጣ ፈንታ፦ ወይ የምእመናን መኖርያ


ወደሆነችው ጀነት ወይ የበዳዮችና የከሓዲዎች መኖርያ ወደሆነችው ጀሀነም መሆኑን ይገልፃል።


አላህ በዐረብኛ ቋንቋ ባወረደው እና ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲደርስ (እንዲተላለፍ) ካዘዘበት የዚህ ታላቅ መጽሐፍ አስፈላጊነት


አንፃር እኛም - ውድ አንባቢ ሆይ! - የቁርኣኑን መልዕክት በቀላሉ እንዲረዱ ለማስቻልና ለማድረስም ሲባል የመልዕክቱን ትርጉም


በቋንቋዎ ስናቀርብልዎ እጅግ ደስታ ይሰማናል፤ የስራ ቡድኑ ትርጉሙን ለመረዳት እና ለመተርጎም የተቻለውን ሁሉ ጥረት


አድርጓል። ትርጉሙ የቱንም ያህል ትክክለኛና በጥንቃቄ የተሠራ ቢሆንም ከሰው ሥራ እጅጉን የላቀ የሆነው የቅዱስ ቁርኣን


ተአምራዊ ዋና ጽሑፍ (ነስ) የሚያመለክተውን መልዕክት ትርጉም ሙሉ በሙሉ መግለጽ እንደማይቻል በእርግጠኝነት ማወቅ


ይገባል። በመሆኑም ቅዱስ ቁርኣን የያዘውን ተጨማሪ እውነታዎች ላይ ለመድረስ ከፈለጉ ቁርአኑ የወረደበትን ዐረብኛ ቋንቋ


እንዲማሩ እንመክሮታለን።


በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን፤ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው።


የተከበረው ቁርኣን ኢንሳይክሎፔዲያ


www.quranenc.com


* በቅዱስ ቁርኣን ኢንሳይክሎፔዲያ ድህረ ገጽ (www.quranenc.com) ላይ በእያንዳንዱ አንቀጽ ፊት ለፊት ባለው የማስታወሻ


መስኮት ለትርጉሙ እድገት ያሎትን ጥቆማዎችና አስተያየት ስንቀበል በደስታ ነው። እኛን ማግኘት ከፈለጉ በኢሜል ሊልኩልን


ይችላሉ፡- info@quranenc.com


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡


የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?



የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲ ...

መልእክት ከሙስሊም ሰባኪ ለክርስቲያን ሰው

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነ ...

የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም በጎነት SHAWAL

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው? ...

የተከበረው ቁርኣን ምንድን ነው?

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰ ...

የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ሱና ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ስለመሆኑና የተቃወመም ከሃዲ መሆኑን በተመለከተ