ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ማስገባት እና የፈጠራዉ
አደጋ
ሼክ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ኡሴይሚን አላህ ይዘንላቸውና
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነዉ
ለአላህ ምስጋና ይገባዉ እናመሰግነዋለን በሱም እንታገዛለን ይቅርታ እንጠይቃለን ወደ እርሱም እንመለሳለን፡ ከነፍሶቻችን
ተንኮሎች እና ከመጥፎ ስራዎቻችን በአላህ እንጠበቃለን፡ አላህ የመራዉ የሚያሳሰተዉ የለም፡ እሱ ያሳሳተዉ ደግሞ የሚመራዉ
የለም።
አጋር ከሌለዉ አንድ አላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ፡ ሙሐመድም የአላህ ባሪያ እና መልዕክተኛዉ መሆኑን
እመሰክራለሁ፡አላህ በቀጥተኛዉ መንገድ እና በእዉነት ሀይማኖት ልኮታል መልዕክትን አድርሷል አደራንም ተወጥተዋል ኡማውን
መክረዋል ሞት እስኪመጣቸው ድረስ በአላህም መንገድ የሚገባውን ትግል ታግለዋል ።
ኡማውንም ንፁህና /ነጭ/ ግልፅ በሆነቺዋ መንገድ ትተዋል ለሊቷ ልክ እንደ ቀን ግልፅ በሆነችዋ መንገድ ከሷም አያፈነግጥም
ጠማማ ካልሆነ እንጂ፡ለኡማዉ በሁሉም ሁኔታዎች የሚያስፈልገዉን ነገር ግልጽ አድርጓል አቡ ዘር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል።
ነቢዩ የአላህ እዝነትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁንና ስለ አንድ በክንፉ በሠማይ ላይ የሚበረዉን ወፍ ሰለሱ እዉቀት ሳይነግረን አልተወም
ለሰልማን አል ፋሪሲ አላህ ስራውን ይዉደድለትና ከሙሽሪኮች የሆነዉ አንድ ሰውዬ እንዲህ አለዉ፡ ነቢያችሁ ስለ መጸዳጃ ቤት
እንኳ አስተማራችሁ፡ የመፀዳጃ ቤት ሥርዓቶች፡ እንዲህ አለ; አዎን፡ ስንፀዳዳ ወይም ስንሸና ወደ ቂብላ እንዳንዞር ከልክሎናል
ወይም ከሶስት ድንጋይ በታች ኢንቲንጃ እንዳናደርግ ከልክሎናል፡ ወይም በቀኝ እንዲሁም በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃ
እንዳናደርግ ከልክሎናል ይህ ታላቅ ቁርዓን አላህ የእምነት መሰረቶችን እና የዲን ትንታኔዎችን ያብራራበት መሆኑን ትመለከታለህ:
እንዲሁም የአላህን አንድነት ተዉሂድን ሁሉንም ዓይነቶች ግልጽ አድርገዋል፡ የአቀማመጥ ስርዓት እና የፍቃድ ስርዓትም ጭምር
ግልፅ አድርጎዋል፡ አላህም እንዲህ ይላል:
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ (ስፍራን) አስፉ፡፡ አላህ ያሰፋላችኋልና፡፡
(አል ሙጃዲላ 11) አላህም አለ፡-
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች
አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡ በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ ለእናንተ
እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ አትግቧት፡፡ ለእናንተ ተመለሱ ብትባሉም ተመለሱ፡፡ እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን
ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
(አን ኑር 27-28) የአለባበስ ሰርዓት እንኳን ሀያሉ አላህ እንዲህ ይላል ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ተቀማጮች
(ባልቴቶች)፤ በጌጥ የተገለፁ ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡ (አን ኑር 60)
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ
ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
(አል አህዛብ 59) ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ (አን ኑር 31) መልካም ሥራም ቤቶችን
ከጀርባዎቻቸው በመምጣታችሁ አይደለም፡፡ ግን የመልካም ሥራ ባለቤት የተጠነቀቀ ሰው ነው፡፡ ቤቶችንም ከደጃፎቻቸው በኩል
ግቡ፤ አላህንም ፍሩ ልትድኑ ይከጀላልና (በላቸው)፡፡ (አል በቀራህ 189) ይህ ሀይማኖት ሙሉ እና የተብቃቃ የሆነ እና ጭማሪ
የማየስፈልገዉ መሆኑን እንዲሁም ጉድለትም የማይታሰብበት መሆኑን እና የመሳሰሉትን የሚያብራሩ በቁርዓን ዉስጥ በርካታ
አንቀጾች ይገኛሉ፡ ለዚህም ሀያሉ አላህ ስለ ቁርዓን ሁኔት እንዲህ ይላል፡ መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ ኾኖ ባንተ ላይ
አወረድነው፡፡ (አን ነህል 89) በማንኛዉም ሁኔታ በዚህች በቅርቢቱ ሀገርም በዲንያ ትሁን በመጪዉም ዓለም ለሰዉ ልጆች
የሚያስፈልጋቸዉን ነገር አላህ በቁርዓን ዉስጥ በጽሁፍ መልኩም ይሁን በማመለከት ወይም በመጦቀም ወይም እንደሚረዳ ተደርጎ
ሳያብራራ አልተወም፡ ዉድ ወንድሞች፡ አንዳንድ ሰዎች የሀያሉን አላህ ቃል የሚተነትኑት፡ ከተንቀሳቃሽም በምድር (የሚኼድ)፤
በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም (አል
አንዓም 38) ይህ የአላህ ቃል የሚያብራራዉ በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም መጽሐፉም ቁርዓን ነዉ፡ ትክክለኛዉ
እዚህ ጋር ኪታብ ለማለት የተፈለገበት ለዉሀል መህፉዝ ነዉ፡ ቁርዓንን ደግሞ አላህ ሱ.ወ በጣም ከጉድለት የጠራ በመሆኑ ገልጾታል፡
መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡ ይህም ከዚህ ከአላህ ቃል በጣም ግልፅ ነዉ: በመጽሐፉ ውስጥ
ምንንም ነገር አልተውንም ከዚያም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ፡፡
ምናልባትም አንዱ እንዲህ ሊል ይችላል በቁርአን ውስጥ የአምስት ወቅት ሰለዋቶች ቁጥሮች ከዬት እናገኛለን?
የእያንዳንዱ ሰላት ቁጥር ብዛትስ?
እንዴትስ አግባብ ይሆናል በቁርዓን ዉስጥ ስለ ሰላት ዉስጥ ያሉትን የረከዓ ብዛት ማብራሪያ አናገኝም አላህ እንዲህ እያለ:
መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡ ለዚህ መልስ የሚሆነዉ፡ ሀያሉ አላህ በቁርዓን ዉስጥ እኛ ላይ ግዴታ
ያደረገዉ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ያሉትን እና ያመላከቱንን ነገሮች እንድንቀበል ነዉ ። መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡
ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)፡፡ በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ (አን ኒሳዕ 80)፣ መልክተኛውም የሰጣችሁን
(ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ (አል ሀሽር 7)፣
በሀዲሶች የተገለፁትን ደግሞ ቁርዓንም ወደሱ አመላክተዋል፡ ምክንያቱም አላህ በመልዕክተኛዉ ላይ ያወረደዉ እና ያስተማረዉ
አንዱ የወህይ ክፍል ስለሆነ ሀያሉ አላህ በቁርዓን እንዳለዉ: አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም
ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ (አን ኒሳዕ 113) በዚህ ዙሪያ በሀዲስ ዉስጥ የመጡት በእዉነትም
በሀያሉ የአላህ ቁርዓን ዉስጥ ተጠቅሰዋል፡
ዉድ ወንድሞቼ፡ ይሄ እናንተ ጋር የተረጋገጠ ከሆነ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ወደ አላህ ከሚያቃርቡት ነገሮች ከሀይማኖት የሆነን ነገር ሳይገልጹት
የቀረ ነገር አለን?
በጭራሽ፡ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ሀይማኖቱን በሙሉ በግልጽ አብራርተዋል በንግግሩ፡ አሊያም በተግባሩ፡ ወይንም በማረጋገጥ ወይንም
ከጅምሩ በማሳየት ወይም ለጥያቄ መልስ በመስጠት፡ አንዳንዴም አላህ አንድ በገጠር የሚኖርን ሰዉ ራቅ ካለ ከገጠር ክልል ይለከዉና
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ጋር ሄዶ ከነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ጋር የሚያዘወትሩት ሰሃባዎች እንኳ የማይጠይቁትን ጥያቄ ይጠይቃል፡ ለዚህም ነዉ አንድ
የገጠር ሰዉ መጥቶ ነቢዩን ሰ.ዐ.ወ ከአንዳንድ ጉዳዬች እንዲጠይቅ ይደሰቱ ነበር። ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ የሰዉ ልጆች በአምልኮ እንዲሁም
በግንኙነት እና በኑሮዋቸዉ ዉስጥ የሚያስፈልጋቸዉን ነገር አንድም ነገር ሳያብራሩ አልተዉትም የሚለዉን ያመላክተሃል፡ በዚህም
ዙሪያ ይህ የአላህ ቃል ያመለክተሃል፡ ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም
ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ (አል ማዒዳ 3) ሙስሊም ሆይ ይሄ አንተ ጋር የተረጋገጠ ከሆነ በአላህ ዲን ዉስጥ አዲስ
ፈጠራ ያመጣ ሰዉ በጥሩ ንያ እንኴን ቢያስበዉም ይሄ ፈጠራዉ ጥሜት በመሆኑም ጋር በአላህ ሱ.ወ ዲን ዉስጥ እንደማላገጥ
ይቆጠራል የአላህንም ቃል ማስዋሸት ይሆናል: ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡
ይህ ሙብተዲዕ በአላህ ሱ.ወ ሸሪዓ/ህግጋት ዉስጥ አዲስ ፈጠራን ያመጣዉ በርግጥ በአላህ ዲን ዉስጥ ይህ ባይኖርም የእርሱ ሁኔታ
የሚያመላክተዉ ዲኑ ሙሉዕ አይደለም ይቀረዋል የሚለዉ ሲሆን ይሄ እሱ ያመጣቸዉን አዲስ ፈጠራ ወደ አላህ ሱ.ወ ያቃርበኛል
ብሎ ማሰቡ ነዉ።
የሚገርመዉ ደግሞ አንድ ሰዉ በአላህ ሱ.ወ ዛት እንዲሁም በስሞቹ እና በበህሪያቱ ዉስጥ ፈጠራ ማስገባቱ ነዉ:ከዚያም በዚህ ላይ
አላህን ማክበር እና ማጥራቴ ፡ ለሀያሉ አላህ ቃል ማታዛዜ ነዉ ይላል : እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ
ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡ (አል በቀራ 22) አንድ ሙብተዲዕ በአላህ ዲን ዉስጥ በአላህ ዛት ላይ ፈጠራን ሲያመጣ ትገረማለህ፡
ይህም ነገር ከቀደምት የኡማዉ ደጋግ ሰዎችም ይሁን እንዲሁም መሪዎችዋ የሌሉበት ሆኖ ሳለ ፡ እኔ አላህን ከሌላ ነገር እያጠራዉ
ነዉ እያከበርኩት ነዉ ለአላህም ቃል ታዣዥ ነኝ ይላል፡ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ ይህንን የተቃወመ ሰዉ ደግሞ አስመሳይ
እንዲሁም ሌሎች አስጠሊ ስያሜዎችን በመጠቀም ይጠሩታል፡
የአላህ ዲን ዉስጥ የሌለዉን ነገር ከሚፈጥሩ ሰዎች አሁንም በጣም የሚገርምህ ነገር በተለይ ከረሱል ሰዐወ ጋር ተያይዘዉ ያሉት
ጉዳዮች ላይ እኛ የረሱል ሰዐወ ወዳጆች ነን እንወዳቸዋለን እንዲሁም እናከብረዋለን እያሉ መጣራታቸዉ ነዉ፡ በዚህ ፈጠራቸዉ
ደግሞ ከነሱ ጋር ያልተስማማዉን ረሱልን ሰዐወ ይጠላል አይወዳቸዉም እያሉ በሌሎችም መሰል መጥፎ ስያሜ ሲጠሩ ይስተዋላሉ፡
ከሚገርሙት ነገሮች እነኚህ ሰዎች እኛ አላህን እና ነቢዩን ሰዐወ በጣም እናከብራለን ይላሉ፡ ረሱል ሰዐወ ይዘዉት የመጡልን በአላህ
ሸሪዓ ዉስጥ የሌለዉን ፈጠራ ካመጡ ያለ ምንም ጥርጥር እነርሱ በአላህና በመልክተኛው ፊት እየቀድሙ ነዉ ፡ ሀያሉ አላህ እንዲህ
ብለዋል ፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ
ነውና፡፡ (አል ሁጁራት1)
ዉድ ወንድሞች፡ አጥብቄ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ ታዲያ ምላሻችሁ ስሜታዊ ሳይሆን ህሊናዊ መሆን አለበት፡፡ከሀይማኖታችሁ
እሴት እንጂ ከተለምዶ እና ከወጋችሁም መሆን የለበትም፡፡ በአላህ ዲን ውስጥ ከርሱ ያልሆነን ከአላህ ዛት ባህሪያትና ስያሜዎች ጋር
ወይም ከረሱል ሰዐወ ስብእና ጋር ተያያዝነት ያለው ነገር ስለሚፈጥሩ (ስለሚጨምሩ) ሰዎች ምን ትላላችሁ ከዚያም እኛ አላህንና
መልክተኛውን አላቂዎች ነን ይላሉ፡፡ (ታዲያ ) እነኚህ አላህንና መልክተኛውን በማላቅ የተገቡ ናቸውን?
ወይስ እነኚያ ከአላህ ህግጋትና መመሪያ የስንዝር ያክል የማያፈነግጡት በሸሪዓ የተደነገገን በሙሉ አምነናል በርሱ የተነገረንም
ተቀብለናል በታዘዝነው ወይም በተከለከልነው ሁሉ ሰሚዎች ታዛዦች ሆነናል የሚሉ የሸሪዓ መመሪያ ባልተላለፈበት ጉዳይ ላይ
እንታቀባለን አላህና መልክተኛውን ልንጥስ ወይም ልናልፍ በፍፁም አይገባንም ከርሱ ያልሆነን ነገር በአላህ ዲን ላይ አንናገርም
የሚሉ፡፡የትኞቹ ናቸው ታዲያ አላህን እና መልክተኛውን በመውደድና በማላቅ ተገቢዎች?
እነኚያ በርሱ በነገረን አምነናል አፅድቀናል በርሱ ባዘዘን ነገር ላይም ሰሚዎች ታዛዦች ሆነናል ያሉት በእርሱ ያልታዘዝንበትን
ታቅበናል ተከልክለናል ያሉት፡ እኛ በነፍሶቻችን ውስጥ በአላህ ድንጋጌና ህግ ውስጥ ከርሱ ያልሆነን ከማዶል ወይም በአላህ ዲን
ውስጥ ከርሱ ያልሆነን ከመፍጠር ያነሰ ዝቅተኛ ደረጃ ወይም ቦታ ያለው የለም ብለው ያሉ (የተገቡ ለመሆናቸው) ጥርጥር የለውም
እነኚህ እነርሱ በርግጥ የነፍሶቻቸውን ደረጃ እንዲሁም የፈጣሪያቸውንም ደረጃና ክብር ያወቁ ለመሆናቸውም ጥርጥር የለውም
እነኚህ ናቸው አላህና መልክተኛውን በትክክል ያላቁ እነርሱ ናቸው ለአላህና ለመልክተኛው ሰ.ዐ.ወ ያላቸውን ውዴታ በይፋ ያሳዩ፡፡
እኚህ በአቂዳ ፡ በንግግር እና በተግባር ዉስጣ በአላህ ዲን ዉስጥ የሌላን ፈጠራ የሚስገቡ ሳይሆኑ አንተ የረሱልን ሰዐወ ንግግርን
ከሚያዉቁ ሰዎች ትደነቃለህ አዲስ መጤ ጉዳዮችን ተጠንቀቁ አዲሰ መጤ በሙሉ ፈጠራ ነው ፈጠራ በሙሉ ጥመት ነው ጥመት
በሙሉ በእሳት ውስጥ (ወዳቂ ተቀጪ) ነው፡፡ ያቃሉ ደግሞ ይህ የሱ ንግግር ሁሉም ፈጠራ ጥቅላዊ ሁሉንም የሚያካትት እንዲሁም
ጥቅላዊነትና አካታችነትን በሚገልጽ ጠንካራ ገለጻ የተነገረ ነው፡፡ ሁሉም በዚህች ሁሉም በምትለዉ ቃል የተናገረዉ የአላህ እዝነት
እና ሰላም በሱ ላይ ይሁንና የዚህች ቃል አመላካችን ያዉቃል፡ ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው ምን እየተናገረ እንዳለና የንግግሩን
መልክትና ትርጓሜ ያውቃል፡ ይህ ንግግር ፍፁም ለህዝቡ መልካም ከማሰብ የመነጨ ነው፡፡ በአንድ ንግግር ውስጥ እነኚህ ሶስት
ነገራት ማለትም ፍፁም ታማኝነትና ተነሳሽነት ሙሉዕ የሆነ ገለፃና አንደበተ ርቱእነት የተሟላ እውቀትና ተሞክሮ ከተሟሉ
በንግግሩ የሚፈለገው ያ እርሱ ሊያስተላልፍ የሚችለውን መልክት እንደሆነ ያስረዳል፡፡ታዲያ ከዚህ ሁሉ ጥቅላዊ ማብራሪያ ቡሃላም
ቢድዓን በሶስት ወይም በአምስት ክፍሎች መክፈል ተገቢ ነውን?
አንዳንድ ቢድዓ ሀሰና የሚባል አለ የሚሉ ኡላሞች:በጭራሽ ይህ ትክክል አይደለም፡ ከሁለት ሁኔታዎች አይወጣም፡
ቢድዓ አለመሆንዋ ነዉ ነገር ግን ብድዓ ናት ብሎ ያስባል
ቢድዓ ሆና መጥፎም ናት ነጋር ግን መጥፎ መሆንዋን አያዉቅም
እያንዳንዱ መልካም ፈጠራ ወይም ቢድዓ መሆኑ የተነገረለት (ያለመሆኑ) ምላሽ የሚሰጠው በዚህ ነው በመዳፋችን ውስጥ ከረሱል
ሰ.ዐ.ወ የተሰጠ ይህ ቆራጭ ጎራዴ እያለ የቢድዓ አራማጆች ፈጠራዎቻቸውን መልካም ፈጠራ ብለው ለማለት በዚህ ላይ
የሚያሳልፋቸው መግቢያ አይኖራቸውም ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው ይህ ቆራጭ ጎራዴ የተመረተው በነብይነትና በመለክተኛነት
ኢንዱስትሪ ውስጥ ነው፡ በተዘበራረቀና በተናወጠ ኢንዳስትሪ ውስጥ አይደለም የተመረተው ነገር ግን በነብይነት ኢንዱስትሪ ውስጥ
ነው በቀጥታ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ናቸው በእንደዚህ መልኩ ዲካ የደረሰ መሳልን የሳሉት በእጁ ይህ ቆራጭ ጎራዴ ያለው ሰው ማንም በጎ
ቢደዓ በሚል ሊገጥመው አይችልም ረሱል ሰ.ዐ.ወ ደግሞ እንዲህ ይላሉ: ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው በውስጣችሁ የሆነ
የሚቆረቁራችሁ ነገር እንዳለ ይሰማኛል (እርሱም) ለትክክለኛነት የተገጠመ ስለሆነው የሙዕሚኖች መሪ ኡመር ቢን ከጣብ ምን
ትላለህ ለኡበይ ቢን ካእብና ለተሚም አድዳሪ በረመዳን ሰዎችን እንዲያሰግዱ ባዘዘ ጊዜ ሰዎችም ኢማማቸውን (ተከትለው
ለመስገድ) ተሰባሰበው ወጥቶ ሲመለከት እንዲህ አለ፡፡ ይህች ሰናይ ፈጠራ ናት (ይሁን እንጂ) ከርሷ የተኙት ከሚሰዷት በላጭ
ናቸው፡፡ በነዚህ ላይ መልሱን በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል: የመጀመሪያው እነሆ ከሰዎች ለአንዳቸውም በፈለገው አይነት ንግግር
የመልክተኛውን ንግግር ሊቃረን አይፈቀድለትም፡፡ አቡበከር በዚህ ህዝብ ውስጥ ከነብዩ ቀጥሎ በላጩ ሰው ቢሆንም እንኳን በርሱ
ንግግርም ይሁን ከነበዩ ቀጥሎ በዚህ ህዝብ ውስጥ ሁለተኛው በላጩ ሰው በሆነወ በኡመር ንግግር ወይም በዚህ ህዝብ ውስጥ ከነብዩ
ቀጥሎ ሶሰተኛው በላጩ ሰው በሆነው በኡስማን ንግግር ከነብዩ ቀጥሎ በዚህ ህዝብ ውስጥ አራተኛው በላጩ ሰው በሆነው በአሊይ
ንግግር እንዲሁም ከነርሱ ሌላም በማንም ንግግር (መቃረን አይፈቀድለትም) ምክንያቱም አላህ ሱ.ወ እንዲህ ብሏል፡ እነዚያም
ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡ (አን ኑር 63) አል ኢማም
አህመድ አላህ ይዘንለት እንዲህ ይላል: ፍትና ምን እንደሆነ ታዉቃለህ? መከራ (ፈተና) ሺርክ ነው የነብዩ ሰ.ዐ.ወ ን አንዳንድ
ንግግሮች ሲያስተባብል ወይም አልቀበልም ብሎ ሲመልስ በልቦናው ውስጥ ወደ ሺርክ መዘንበል ይገጥመውና ይቀሰፋል ተቋጨ
ኢብን ዐባስ አላህ ስራቸዉን ይውደድላቸው እንዲህ ይላሉ: ከሰማይ ላይ ድንጋይ እንዳይወርድባችሁ ይጠረጠራል እኔ ረሱል ሰ.ዐ.ወ
እንዲህ አለ እላችኋለዉ እናንተ ደግሞ አቡበክር እና ኡመር እንዲህ አለ ትላላችሁ ሁለተኛው እኛ የምዕመናን መሪ ኡመር ቢን
ከጣብ ረአ የአላህና የመልክተኛውን ንግግር በማላቁ ረገድ እጅግ ጠንካራው ሰው እንደሆነ በርግጠኛነት እናዉቃለን የአላህ ድንበርን
ሳይተላለፍ በመቆም ይታወቃል የአላህ ንግግር ዘንድ የሚቆም በሚል እስከመታቅ ደርሰዋል የማህርን ልክ መገደብን በተመለከተ
የሞገተችው ሴት ታሪክ የማይታወቅ ታሪክ አይደለም የትርከቱ ዘገባ ትክክል ከሆነ! እንዲህ በሚለው ( የአላህ ቃል ማስረጃነት) ነበር
የተቃወመችው፡ ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ በእርግጥ የደረሰ ሲኾንና ከእናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ኪዳንን የያዙባችሁ ሲኾኑ እንዴት
ትወስዱታላችሁ! (አን ኒሳዕ 21) ኡመር ካሰበዉ መህርን ከመወሰን ተቆጠበ ነገር ግን ይህ ታሪክ ትክክለኛነቱ አነጋጋሪ ነው፡ ይሁን
እንጂ ለማለት የተፈለገው ኡመር የአላህ ድንበር ዘንድ የሚቆም በፍፁም የማይጥሰው መሆኑን መግለፅ ነው በመሆኑም ኡመር
ከእርሱ እርሱነት አኳያ የሰው ዘር አይና የሆኑትን የሙሀመድን ሰ.ዐ.ወ ንግግር ሊቃረንና ስለ ቢድዓ (ሰናይ ቢድዓ) ብል ሊል
አያምርበትም (ከማንነቱ ጋርም አይጣጣምም) ሰናይ ፈጠራ (ያውም) ይህች ፈጠራ ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ በማለት በንግግራቸው
(ሊያወግዟት) የፈለጓት ሆና ሳለ፡ ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው እንደውም ኡመር ሰናይ ፈጠራ ብሎ ያላት ፈጠራ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ
በንግግራቸው ሊያወግዟት የፈለጓት ፈጠራ ውስጥ የምትገባ ወይም የምትካተት አትሆንም ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው ኡመር ሰናይ
ፈጠራ በሚለው ንግግሩ የፈለገው ሰዎች ተበታትነው (ይሰግዱ) ከነበረበት ሁኔታ በአንድ ኢማም መሰባሰባቸውን ለመጠቆም ነው
የረመዳን የሌሊት ስግደት መሰረቱ ከረሱል ሰ.ዐ.ወ የተሰገደ ነው በቡካሪና ሙስሊም ዘገባ እመት ዓኢሻ ባስተላለፈችው ሀዲስ ነብዩ
ሰ.ዐ.ወ ለሶስት ሌሊቶች ሰዎች ካሰገዱ ቡሃላ በአራተኛው ሌሊት ቀሩባቸው እንዲህም አሉ፡ እኔ እናንተ ላይ ግዴታ ሆኖ እናንተ
እንዳትዳከሙ ፈራለሁ
ስለዚህ በረመዳን ውስጥ የለሊት ስግደት ከረሱል ሰ.ዐ.ወ ሱና (የሚመደብ) ነው፡ ኡመር ፈጠራ ብሎ የጠራው ረሱል ሰ.ዐ.ወ
(በአራተኛው ሌሊት ላይ) ማሰገድ ሲተዉ ሰዎች ከመበታተናቸው አንፃር ነው አንድ ሰው ለብቻው ሌላኛው አንድ ሰው አስከትሎ
ሶስተኛው ደግሞ ሁለት ሰዎች ተከትለውት ብዙ ሁነውም በመስጂድ ውስጥ ይሰግዱ ነበር (በዚህን ጊዜ) የሙእሚኖች መሪ ኡመር
ረ.አ በዚያ ለትክክለኛ አቋም የታደለ በሆነው እይታው ሰዎችን በአንድ ኢማም ሊያሰባስብ አሰበ ይህ ተግባር ቀደም ሲል ሰዎች
ተበታትነው (ለብቻ ለብቻ) ይሰግዱ ከነበረበት አንፃር ፈጠራ ነው ፈጠራነቱ ግን አንፃራዊ ተቀጥላ እንጂ ኡመር በአዲስ መልኩ
ያነፀው ጥንስሳዊ ገደብ አልባ ፈጠራ አይደለም ምክንያቱም ይህ ተግባር በረሱል ሰ.ዐ.ወ የህይወት ዘመንም የነበረ ሲሆን ሱናም ነው
ነገር ግን ከረሱል ሰ.ዐ.ወ የህይወት ዘመን ጀምሮ ኡመር ረ.ዐ ወደ ተግባር እስከመለሰበት ጊዜ ድረስ ተትቶ ነበር ስለሆም በዚህ
አቀማመጡ ወይም ይዘቱ በፍፁም የፈጠራ አራማጆች ከዚህ ከኡመር ንግግር ሰናይ አድርገው ለሚያስቡት ፈጠራቸው መውጫ
ክፍተት አያገኙም፡
ምልባትም አንድ ሰው እንዲህ ይል ይሆናል በነብዩ ሰዐወ የህይወት ዘመን የሚታወቁ ያልነበሩ(ግን) ሙስሊሞች የተቀበሏቸውና
በተግባር ያዋሏቸው ፈጠራ የሆኑ ነገራት አሉ ትምህርት ቤት መፅሀፍ ማዘጋጀትና የማሰሰሉት ነገሮች እነኚህን ፈጠራዎች
ሙሰሊሞች በሰናይነት ተቀብለዋቸው ተግብረዋቸዋል ምርጥ የስራ አይነቶች ናቸው ብለውም ያስባሉ ታዲያ በዚህ ሙስሊሞች
በአንድ ድምፅ ሊቀበሉት የቀረበውን ጉዳይ እና የሙስሊሞች መሪ ነብይ የሆኑት የአለማት ጌታ መልክተኛ ንግግርን እንዴት
ማጣጣም ይቻላል ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው ለዚህ መልሱ በመሰረቱ ይህ ወደ ህጋዊ ተግባር መዳረሻ መንገድ አንጂ ፈጠራ
አይደለም የሚል ነው መዳረሻ ደግሞ እንደ ቦታና ወቅት ይለያያል (ይቀያየራል) መዳረሻዎች የግቦች ብይን አንዳላቸው (በሸሪዓዊ)
ህገ ደንብ ላይ ፀድቋል ህጋዊ መዳረሻዎች ህጋዊ ናቸው ህገ ወጥ መዳረሻዎችም ህገ ወጥ ናቸው እንደውም ሀራም መዳረሻዎች
ሀራም ናቸው መልካም ነገርም ለመጥፎ መዳረሻ ከዋለ ክልክል ነው አላህ ሱ.ወ የሚለውን በአስተውሎት ተመልከት እነዚያንም
ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን (ጣዖታትን) አትስደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡ (አል አንዓም 108)
የሙሽሪኮችን አማልከት መሳደብ ድንበር ማለፍ አይደለም እንደውም በተገቢው ቦታ የሆነ እውነት ነው ነገርግን የአለማት ጌታን
መሳደብ ድንበር ማለፍ ነው ያለ ተገቢው ቦታ የዋለም ነው ድንበር ማለፍ በደል ነው ለዚህም ነው የሚያስመሰግን የሆነው
የሙሽሪኮችን አማልክት መሳደብ ክልክልና እርም ወደሆነው አላህን ወደ መሳደብ የሚገፋና የሚያነሳሳ መንስኤ ስለሆነ (ክልክል
ሊሆን ችሏል) ይህን ያጣቀስኩት መዳረሻዎች የአላማዎች ብይን ወይም ሁክም ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃነት ነው ትምህርት
ቤቶች እውቀትን በፅሁፍ መተየብ መፅሀፍትን ማዘጋጀት በነብዩ ሰ.ዐ.ወ የህይወት ዘመን ያልነበሩ ፈጠራዎች ቢሆኑም በራሳቸው
ግቦች አይደሉም መዳራሻዎች ናቸው መዳረሻዎች ደግሞ የግቦች ብይን ይኖራቸዋል
ስለዚህ አንድ ሰዉ ሀራም የሆነን ነገር ሊያስተምርበት ትምህርት ቤት ቢገነባ ግንባታዉ ሀራም ነው፡ ነገር ግን ሸሪዓዊ እዉቀት
ሊያስተምርበት ትምህርት ቤት ቢገነባ ግን ግንባታዉ የተፈቀደ ነዉ ያሚሆነዉ
አንዱ እንዲህ ቢል፡ ይህን የነቢዩ ሰዐወ ንግግር እንዴት ብለህ ትመልሳለህ: በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ(ሱና) ፈር የቀደደ እስከ
ቂያማ ቀን ለእርሱ የዚህ ስራ ምንዳ እና ይህንን ፈለጉን ተከትሎ የሚሰራ ሰውን ሁሉ ምንዳ አለው፡ ሱና አደረገ ስንል መንገድ/ሸሪዓ
አደረገ ማለታችን ነዉ መልሱ: እንዲህ ላለ ሰዉ በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ (ሱና) ፈር የቀደደ እርሱ እንዲህ ያለ ነዉ፡ ሁሉም
ፈጠራ ጥመት ነው ከእውነተኛውና እውነተኛነታቸው ከተመሰከረላቸው (ነብዩ ሰ.ዐ.ወ) ሌላው ንግግራቸው የሚያስተባብለው የሆነ
ንግግር ከአፋቸው አይወጣም የረሱል ሰ.ዐ.ወ ንግግር በፍፁም እርስ በርሱ የሚጋጭ ሊሆን አይችልም አንድ ወጥ በሆነ ጉዳይ
በጭራሽ የሚጣረስ መልዕክት ሊተላለፍ አይችልም የአላህ ወይም የመልክተኛዉ ሰ.ዐ.ወ ንግግር ይጋጫል የሚል ጥርጣሬ ያለበት
ሰው ቆም ብሎ ያስተንትን ይህ ግምቱ ወይም ጥርጣሬው ከርሱ የግንዛቤ ጉድለት ወይም ድክመት የመነጨ ነው በአላህ ንግግር
ውስጥ ወይም በመልክተኛው ሰ.ዐ.ወ ንግግር ውስጥ በምንም መልኩ በፍፁም ግጭትና መጣረስ ሊኖር አይችልም፡ (እውነታው)
እንዲያ ከሆነ በመሰረቱ ሀዲስ ግጭት እንደሌለው ግልፅ ነው ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው ለዚህ ሀዲስ በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ
(ሱና) ፈር የቀደደ ነቢዩ የአላህ እዝነትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን እንዲህ ይላል: በኢስላም ውስጥ ፈር የቀደደ ቢድዓ ደግሞ
ከኢስላም አይደለም፡ እዚህ ጋ ጥሩ ይላል ቢድዓ ደግሞ ጥሩ አይደለም፡ በሱና እና በቢድዓ መሃከል አለያይቶዋል፡
(ለዚህ)ጥሩ ምላሽ አለ(እርሱም) ፈር የቀደደ ማለት የነበረችን ፈለግ ህያው ያደረገ ጠፍታ የነበረውን እንድታንሰራራ ያደረገ ማለት
ነው በዚህ መሰረት ልክአንድ ሱና ከተተወና ከተረሳ ቡሃላ ህያው ላደረገ አንፃራዊ ተቀጥላ እንደሚባለው ለፈጠራ በተመሳሳይ መልኩ
ፈለግነቱም አንፃራዊ ተቀጥላ ነው
ሶስተኛ መልስም አለ ለሀዲሱ መነገር ምክንያት የሆነው ጉዳይ (ለዚህ ምላሽ) እንደ ማስረጃ (ይቀርባል) እሱም ወደ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ
ዘንድ የመጡ ልኡኮች ታሪክ ነው በጣም ከባድ አጣብቂኝ (ችግር) ውስጥ ነበሩ ስለሆነም ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ለነርሱ እርዳታ እንዲለግሱ
(ለሰሃቦቻቸው) ጥሪ አደረጉ (ከዚያም) አንድ የመዲና ነዋሪ የሆነ ሰውዬ እጁ መሸከም ሊሳነው የቀረበ የሆነ ብር የተሞላ ቀረጪት
በእጁ ይዞ መጣና ረሱል ሰ.ዐ.ወ ፊት ለፊት አስቀመጠው (በዚህን ጊዜ) ከደስታ የተነሳ የነብዩ ሰ.ዐ.ወ ፊት አብረቀረቀ እንዲህም
አሉ፡ በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ(ሱና) ፈር የቀደደ እስከ ቂያማ ቀን ለእርሱ የዚህ ስራ ምንዳ እና ይህንን ፈለጉን ተከትሎ
የሚሰራ ሰውን ሁሉ ምንዳ አለው፡ እዚህ ጋ ፈር ቀደደ ስንል አንድን ስራ ሸሪዓ ወይም ህግ አደረገ ሳይሆን ሊተገበር መንገድ አደረገ
ይሆናል፡ ትርጉሙም እንዲህ ይሆናል በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ (ሱና) ፈር የቀደደ ለሸሪዓ ሳይሆን ለመፈጸም ብቻ ከሰራ፡ ሸሪዓ
ማድረግ ክልክል ሰለሆነ ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው
ዉድ ወንድሞች ነብዩን ሰ,ዓ,ወ መከተል ስራዉ ከሸሪዓ ጋር በነዚህ ስድስት ነገሮች እስኪገጣጠም ድረስ እዉን አይሆንም፡
የመጀመሪያዉ፡ (የአምልኮው) ምክንያቱ ነው የሰው ልጅ ሸሪኣዊ (ህጋዊ) ካልሆነ ምክንያት ጋር የተቆራኘ በሆነ አምልኮ አላህን
ካመለከ (ያ አምልኮ) ፈጠራ ወይም ቢድዓ ነው በሰውዬው ላይ ተመላሸ ይሆናል ለዚህ ምሳሌው አንዳንድ ሰዎች የረጀብን ወር ሃያ
ሰባተኛ ሌሊት ነጥለው (የተለያዩ አምልኮዎችን በመስራት) ያሳልፋሉ እንደ ምክንያት ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡት ረሱል
ሰ.ዐ.ወ ወደ ሰማይ እንዲያርጉ የተደረገበት ሌሊት መሆኑን ነው ሌሊት መስገድ ኢባዳ ነው ነገር ግን ከዚህ ምክንያት ጋር ሲቆራኝ
ቢድኣ ፈጠራ ሆነ ምክንያቱም ይህን አምልኮ የጠነሰሰው በሸሪኣ ያልፀደቀ በሆነ መንስኤ ወይም ሰበብ ላይ ነው ይህ (የአምልኮ)
ይዘት የኢባዳ ሰበብ ከሸሪኣ ጋር መጣጣምን የሚወክል ሲሆነ ጉዳዩ አንገብጋቢና ብዙ ጊዜ ሱና ተደርገው የሚታዩ ነገር ግን ከሱና
ያልሆኑ ፈጠራዎች የሚጋለጡበት ነው፡፡
ሁለተኛው፡ (የአምልኮው) አይነቱ ነው አምልኮ የግድ በአይነቱም ከሸሪኣ ጋር የሚገጥም መሆን ይኖርበታል አንድ ሰው የኢባዳው
አይነቱ በሸሪኣ ያልተደነገገ በሆነ ኢባዳ አምልኮ ቢፈፅም ተቀባይነት አይኖረውም ለዚህ ምሳሌው አንድ ሰው ፈረስ እርድ ቢያርድ
ትክክለኛ የቁርባን እርድ አይሆንም ምክንያቱም በእርዱ አይነት ሸሪኣን ተቃርኗል (የቁርባን) እርድ ከከብት አይነት ማለትም ግመል
ላም ወይም በሬ በግና ፍየል እንጂ ሌላ አይቻልም
ሶስተኛው፡ (የአምልኮው) ልክና መጠኑ ነው አንድ ሰው የግዴታ ሰላቶችን መጠን መጨመር ቢፈልግ ይህ ቢድኣ ነው ተቀባይነትም
የለውም እንላለን ምክንያቱም መጠንና ልክ ላይ ሸሪኣን የሚቃረን ነው አንድ ሰው ዙህርን አምስት ረከኣ ቢሰግድ ሰላቱ ትክክል
እንዳልሆነ ሁሉም የተስማማበት ጉዳይ ነው፡፡
አራተኛው፡ (የአምልኮው) እንዴታነት ነው አንድ ሰው ውዱዕ ሲያደርግ ከእግሩ ቢጀምር ከዚያም ጭንቅላቱን ቢያብስ ከዚያም
ሁለት እጆቹን ቢያጥብ በመጨረሻም ፊቱን ቢታጠብ ውዱኡ ውድቅ ነው እንላለን ምክንያቱም በእንዴታነቱ ውስጥ ሸሪዓን
ተቃርኗል፡
አምስተኛው፡ (የአምልኮው) ወቅት ነው አንድ ሰው በዙልሂጃ የመጀመሪያ ቀናት የቁርባን እርድ ቢያርድ (አርዱ መፈፀም ያለበት)
ወቅት ከሸሪኣ የሚቃረን በመሆኑ እርዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡ አንዳንደ ሰዎች በረመዳን ወር ወደ አላህ ለመቃረቢያነት ፍየል
እንደሚያርዱ ሰምቻለሁ ይህ ተግባር በዚህ መልኩ መፈፀሙ ቢድኣ (ፈጠራ) ነው፡ ምክንያቱም ከኡድሂያ ከሀድይና ከአቂቃ በስተቀር
ወደ አላህ የሚቃረቡበት የሆነ እርድ የለም በረመዳን ውስጥ ልክ እንደ ኡድሂያ በኣል እርድ እመነዳበታለሁ በሚል እሳቤ ማረድ ረጠራ
ነው፡ ለስጋ አምሮት ማረድ ግን ይቻላል፡
ስድስተኛው፡ (የአምልኮው) ቦታ ነው አንድ ሰው ከመስጂድ ውጭ ኢዕቲካፍ ቢቀመጥ ኢእቲካፉ ትክክል አይደለም ይሀውም
ኢዕቲካፍ በመስጂድ ውስጥ በስተቀር አይሆንም፡፡ አንዲት ሴት በቤቴ መስገጃ ስፍራ ኢእቲካፍ ማድረግ እፈልጋለሁ ብትል ከቦታ
አኳያ የሸሪዓ ድንጋጌን የሚቃረን በመሆኑ ኢእቲካፏ ትክክል አይሆንም፡ ሌላው ምሳሌ አንድ ሰው ጠዋፍ ማድረግ ቢፈልግና ጠዋፍ
ማድረጊያው በሰው ተሞልቶ ቢመለከት በዙሪያው ያለው ቦታም (በጠዋፍ አድራጊዎች) ተጨናንቆ ቢያገኝ ከዚያም ከመስጂዱ
ውጭ ከጀርባ ጠዋፍ ቢያደርግ ጠዋፉ ትክክል አይደለም ምክንያቱም ጠዋፍ ማድረጊያ ቦታ በይት (ካእባና ዙሪያው ብቻ) ነው፡ አላህ
ሱ.ወ ለወዳጁ ኢብራሂም እንዲህ ብሏል ቤቴንም ለሚዞሩት ንጹሕ አድርግላቸው (አል ሐጅ 26)
ኢባዳ ወይም አምልኮ ሁለት መስፈርቶችን ሳታሟላ መልካም ስራ አትሆንም፡
የመጀመሪያዉ፡ አምልኮው ለአላህ ብቻ መደረግ አለበት (ኢኽላስ) ወይም ፍፁማዊነት ሁላተኛዉ፡ ነብዩን ሰ,ዓ,ወ መከተል
(ሙታበዓ)፡ ሙታበዓ ደግሞ ስድስት ከዚህ በፊት የጠቀስናቸዉ ነገሮች እንጂ እዉን አትሆንም
ለእነኚህ ምናልባትም እሳቢያቸው ወይም አላማቸው ጥሩ የሆኑ ፅድቅን የሚፈልጉ ግን በፈጠራ ለተለከፉና ለተፈተኑ እኔ የምለው
ቢኖር ፅድቅን የምትፈልጉ ከሆነ በአላህ ስም እምልላችኋለሁ ከቀደምት ሰለፎች የተሻለ መንገድ አናውቅም፡
የተከበራችሁ ወንድሞች የረሱልን ሰአወ ፈለግ በቀንጣጤዎቻችሁ ነክሳችሁ ያዙ በቀደምት ፃድቃን አበዎች መንገድ ተጓዙ እነርሱ
በነበሩበት ላይ ሁኑ ያ እናንተን የሚያስወቅስ ነው አይደለም ማለትን ተመልከቱ
እኔ ይህን ስል በርስ እውቀቱ በሌለኝ ነገር እንዳልናገር በአላህ የምጠበቅ ሆኜ ነው (እናም የሚከተለውን) እላለሁ ከእነኚህ በፈጠራ
(ቢድኣ) ላይ ቧላይ ከሆኑት አብዛኛዎቹ በሸሪኣ የፀኑትና በሱና የፀደቁ ጉዳዮችን በመፈፀሙ ረገድ ዝንጉዎችና ሰነፎች ሆነው
ታገኛቸዋለህ ፈጠራዎችን ሲጨርሱ የፀደቁ ሱናዎችን መተግብር ይሳናቸዋል ይህ ሁሉ ቢድኣ በቀልቦች ላይ የሚያስከትለው ውጤት
ወይም ተፅእኖ ነው ፈጠራ በቀልቦች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከባድ ነው በዲን ላይ የሚጋርጠው አደጋም ግዙፍ ነው፡፡ የሆኑ
ህዝቦች በአላህ ዲን ውስጥ አንድ ፈጠራን አይፈጥሩም በዚያው ልክ ወይም የበለጠ ሱናን ቢያጠፉ እንጂ! ይህን(እውነታ) አንዳንድ
ቀደምት የእውቀት ባለቤት ሰለፎች/አበዎች አውስተውታል፡፡
ነገር ግን የሰው ልጅ እነሆ እርሱ ተከታይ እንጂ ደንጋጊ ወይም ህግ አውጪ እንዳልሆነ ከተሰማው በዚህ (ስሜቱ) ለአለማት ጌታ
ሙሉእ የሆነ ፍራቻን መተናነስን መዋረድንና መገዛትን ያገኛል እንዲሁም የፊሪሃውያን መሪ የመልክተኞች አለቃ የአለማት ጌታ
መልክተኛ ለሆኑት ለሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ የተሟላ ተከታይነትን ይላበሳል፡፡
እኔ ለነዚያ ከአላህ አካል ጋር በተያየዘ ወይም በአላህ ስያሜዎች ወይም በአላህ ባህሪያት ወይም ከረሱል ሰ.ዐ.ወ እና እርሳቸውን
ከማላቅ ጋር በተያያዘ ፈጠራን እንደ በጎ ወይም ሰናይ አድርገው ለሚመለከቱ ለሙስሊም ወንድሞቼ በጠቅላላ የማስተላልፈው
መልክት አላህን እንዲፈሩና ከዚያ እራሳቸውን እንዲያገሉ ነገራቸውን በፈጠራ ላይ ሳይሆን በመከተል ላይ በሺርክ ላይ ሳይሆን
በኢክላስ ላይ በቢድኣ ላይ ሳይሆን በሱና ላይ ሰይጣን በሚወደው ላይ ሳይሆን አርራህማን በሚወደው ላይ እንዲገነቡ ነው (ከዚያም)
ቀልቦቻቸው የሚያገኙትን ሰላም ህያውነት መረጋጋት እፎይታና ታላቅ ብርሃን ይመልከቱ (ያስተውሉ)፡፡
ለአላዩን አላህ የቀናኢያን መሪዎች የተሀድሶ አራማጆች ፋና ወጊዎች እንዲያደርገን ቀልቦቻችንን በኢማንና በእውቀት
እንዲያበራልን ያወቅነውን በኛ ላይ ሸክም እንዳያደርግብን በምእመናን ባሪያዎቹ ጎዳና ላይ እንዲያስጉዘን ከፈሪሃውያን ወዳጆቹ
ከዳኑ አንጃዎቹ እንዲያደርገን እማፀነዋለሁ፡ የአላህ አድናቆትና ሰላም በነብያችን ሙሐመድ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው
በጠቅላላ ላይ ይስፈን፡፡
ሙሉ በሆነዉ ሸሪዓ ዉስጥ ፈጠራን ማስገባት እና የፈጠራዉ አደጋ